3
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው መግቢያ ክቡር አንቢ ሆይ! በማዕከላችን ከዚህች ከቁጥር 4 ፓምፕሌታችን በፊት ቁጥር 1.ለምን ተፈጠርን? ቁጥር 2. የትኛውን መመሪያ ልከተል? የክርስትና ወይስ እስልምናን?ቁጥር 3 እስላም ምንድን ነው? እስላም የተሟላ የህይወት መመሪያ ነው! በሚሉ ርዕሶች ላይ ስለ ክርስትና ሀይማኖትና እስልምና ሀይማኖት ጥቅት የማነጻጸሪያ ነጥቦችና የተፈጥሮ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ሊረደን የሚችል አጠር ያሉ መነባነቦችን አዘጋጅተናልከዚህ በፊት ያሉትን ካለነበቡ ወይንም እነዚህን ፓምፕሌቶች በኦሮሚኛ ቋንቋ ለማግኛት ከፈለጉ በዚህ ፓምፕሌት ላይ በሚያገኙት አድራሻ ሊያገኙንና ልወስዱ እንደሚችሉ በደስታ ልናስታሶ እንወዳለንአንድ ሰው እስላም ለመሆን ምን ይጠበቅበታል? አንድ ሰው እስላም ለመሆን ስለ አላህ ብቸኛ አምላክ መሆኑከሱ ጋር አምልኮት የሚገባው በሰማይም ሆነ በምድር አለመኖሩን አውቆ ማመን። ሙሐመድም(..) ከአላህ ዘንድ የተላካ ነቢይና የአላህ ባሪያ መሆናቸውን ማመን። ይህን ስናምን እርሳቸው ከአላህ ዘንድ ለመጨረሻ የነቢይ/መልክ/ መቋጫ በሆነው በሙሉ መመሪያ ቁርዓን የተላኩ ሲሆኑ የሀይማኖቱ ተግባራትን ስንፈጽምና አላህን በብቸኝነት ልናመልክ በእርሳቸው መንገድ (ፈለግ) መሆን እንዳለበት ማወቅ አለብንአንድ ሰው ይህን አውቆ ልቡ መነበትያመነበትን የአላህን ብቸኝነትና የሙሐመድ መልዕክተኛነትን በልቡና በአንደቱም ሁለቱን የምስክር ቃል "ሸሃዳተይን" መናገር /ማወጅ/ አለበት። እንደሚከተለው በማለት:- "አሽሀዱ አነ-ኢላሀ ኢለ-አላህ አሽሀዱ አነ-ሙሐመደን ረሱሉላህ" ትርጉሙም ቃል በቃል ሲናየው:- ቃሉ ትርጉሙ ቃሉ ትርጉሙ "አሽሀዱ" እመሰክራለሁ እንዲሁም "አነ-" በእርግጥ አለ መኖሩን "አሽሀዱ" እመሰክራለሁ ኢላሀ አምላክ - ሐመደን በእርግጥ ሙሐመድ ኢለ-አላህ (ኢለሏህ) ከአላህ በስተቀር ረሱሉሏየአላህ መልዕክተኛ መሆኑን ወጥ ትርጉሙ= ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ አለመኖሩንና ሙሐመድም ከአላህ ዘንድ የተላከ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ። ማለት ነው። አሁን ከላይ የጠቀስናቸው ሸሃዳዎች የየራሳቸው የሆነ ልተኮሪበት የሚገባ መመሪያ አላቸው። እንግድህ ይህን ከነመመሪያቸው አውቆ አምኖ በልቡና በአንደበቱ የምስክርነትን ቃል የሰጠ ሙስልም ይባላል። ይህን ለመጎጸፍም ሰውነትን ታጥቦ ሁለቱን የምስክር ለአላህ መስጠት ነው። እስከ አሁን ባገኘሀው እውቀት ወደዚህ ሀቅ ልትደርስ ከመራህና ሀቁን ተቀብለህ ከላይ የተገለጸውን ከልብ እንኳን ደስ አለህ()! እጅግ በጠም ታድለሃል(ሻል) እላለምክንያቱም አላህ ከማይገባው እንከን ሁሉ ጥራት ገባውና እስራእ በተባለው የቁርዓን ምዕራፍ ውስጥ በአንቀጽ 157:- «ለነዚያ ተውራትና በእንጅል (ኦሪትና ወንጌል)... እነዚህ ያመኑት፥ ያከበሩት፥ አጋር የሆኑትና ከራሱ ጋር ብርሃን የተከተሉት እነርሱ በእርግጥም ስኬታማዎቹ ናቸው።» በማለት በስረናልና። /የዚህን አንቀጽ ይዘት ከዚህ በፊት ጠቅሰናል/ የእስልምና ሀይማኖት እምነትና ተግባራቶቹ ምንድን ቸው? በእስልምና ሀይማኖት የእምነትና የተግባር ደረጃዎች ናቸው። እነርሱም እስላም ኢማን ኢህሳን ይባላሉ። በዚህ ጽሑፋችን የመጀመሪያውን እስላምን በአጭሩ ስለ ኢማንና ኢህሳን በአላህ ፊቃድ በሌላ ጽሑፍ እንሞክራለን። የመጀመሪያ ደረጃ ከሦስቱ የእምነትና የተግባር ደረጃዎች እስላም ሲሆን አምስት መሠረቶች አሉት። 1) ሁለቱ የምስክር /ሸሃዳ/ 2) ሰላት 3) ዘካ 4) ጾምና 5)ሐጅ 1) ሁለቱ የምስክር ቃ(ሸሃደተይን) «አሽሀዱ አን-ኢላሀ ኢለሏህ አሽሀዱ አንነ-ረሱሉሏህ» = ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ ሌላ አለመኖሩን እናሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ እመሰክራለሁዋናው የእስላም ማዕዘንና መሠረቱ ነው። ቃሉንና በአጭሩ በሠንጠረዥ ውስጥ ጠቅሰነዋል። ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ ሌላ አምላክ የለም። ይህን ስንል አላህ የሚለው የአረብኛ ቃል ከሱ ምንም ሊራበለት ማለትም ወደ ወንድና ሴት ጾታም ሆነ ወደ መግለጫ ቃል መለወጥ የማይችል አንድ አምላክን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት አምሳያ የሌለውና ከማንም የተብቃቃ አይነት ረዳትምስትልጅና ጓደኛ የማያስፈልገው ማለትም ሀያል ፈጣሪን አሀዳዊነት /ብቸኛ አምላክነት/ ቃል ነው። ይህን ቃል መመስከራችን ፍጹም በአለም ላይ በስተቀር በሚመለኩ ጌቶች ሁሉ መካድንና አላህን ብቻ ተግባራት ማገልገልን ይፈልግብናል። አላህ2 1 ر اተቀ. 4

What is Islam1 - Weeblyethioislamicar.weebly.com/.../what_is_islam1.pdf · ˘ ˇ ˆ ˙! ˛ ˚˜ ˇ ˜! ˜"#˘ 4 %& '( ˇ ) * "#˘ 1.-ˇ ./0˘ˇ ? "#˘ 2. 2*3 ˇ 4 5˜.5 ? 2 ˘* 6˙

  • Upload
    others

  • View
    3

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው

መግቢያ ክቡር አንባቢ ሆይ! በማዕከላችን ከዚህች ከቁጥር 4 ፓምፕሌታችን በፊት ቁጥር 1.ለምን ተፈጠርን? ቁጥር 2. የትኛውን መመሪያ

ልከተል? የክርስትና ወይስ እስልምናን?፤ ቁጥር 3 እስላም ምንድን ነው? እስላም የተሟላ የህይወት መመሪያ ነው! በሚሉ ርዕሶች ላይ

ስለ ክርስትና ሀይማኖትና እስልምና ሀይማኖት ጥቅት የማነጻጸሪያ

ነጥቦችና የተፈጥሮ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ሊረደን

የሚችል አጠር ያሉ መነባነቦችን አዘጋጅተናል። ከዚህ በፊት ያሉትን

ካለነበቡ ወይንም እነዚህን ፓምፕሌቶች በኦሮሚኛ ቋንቋ ለማግኛት

ከፈለጉ በዚህ ፓምፕሌት ላይ በሚያገኙት አድራሻ ሊያገኙንና

ልወስዱ እንደሚችሉ በደስታ ልናስታውሶ እንወዳለን።

አንድ ሰው እስላም ለመሆን ምን ይጠበቅበታል?

አንድ ሰው እስላም ለመሆን ስለ አላህ ብቸኛ አምላክ መሆኑንና

ከሱ ጋር አምልኮት የሚገባው በሰማይም ሆነ በምድር አለመኖሩን

አውቆ ማመን። ሙሐመድም(ሰ.ዐ.ወ) ከአላህ ዘንድ የተላካ

ነቢይና የአላህ ባሪያ መሆናቸውን ማመን። ይህን ስናምን

እርሳቸው ከአላህ ዘንድ ለመጨረሻ የነቢይ/መልክት/ መቋጫ

በሆነው በሙሉ መመሪያ ቁርዓን የተላኩ ሲሆኑ የሀይማኖቱ

ተግባራትን ስንፈጽምና አላህን በብቸኝነት ልናመልክ በእርሳቸው

መንገድ (ፈለግ) መሆን እንዳለበት ማወቅ አለብን። አንድ ሰው

ይህን አውቆ በልቡ ካመነበት፣ ያመነበትን የአላህን ብቸኝነትና

የሙሐመድ መልዕክተኛነትን በልቡና በአንደበቱም ሁለቱን

የምስክር ቃል "ሸሃዳተይን" መናገር /ማወጅ/ አለበት።

እንደሚከተለው በማለት:- "አሽሀዱ አነ-ላ ኢላሀ ኢለ-አላህ ወ

አሽሀዱ አነ-ሙሐመደን ረሱሉላህ"

ትርጉሙም ቃል በቃል ሲናየው:-

ቃሉ ትርጉሙ ቃሉ ትርጉሙ

"አሽሀዱ" እመሰክራለሁ ወ እንዲሁም

"አነ-ላ" በእርግጥ አለ

መኖሩን

"አሽሀዱ" እመሰክራለሁ

ኢላሀ አምላክ አንነ-

ሙሐመደን

በእርግጥ

ሙሐመድ

ኢለ-አላህ

(ኢለሏህ)

ከአላህ

በስተቀር

ረሱሉሏህ የአላህ

መልዕክተኛ

መሆኑን

ወጥ ትርጉሙ= ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ

አለመኖሩንና ሙሐመድም ከአላህ ዘንድ የተላከ መልዕክተኛ

መሆናቸውን እመሰክራለሁ። ማለት ነው።

አሁን ከላይ የጠቀስናቸው ሸሃዳዎች የየራሳቸው የሆነ ልተኮሪበት

የሚገባ መመሪያ አላቸው። እንግድህ ይህን ከነመመሪያቸው

አውቆ አምኖ በልቡና በአንደበቱ የምስክርነትን ቃል የሰጠ ሁሉ

ሙስልም ይባላል።

ይህን ለመጎናጸፍም ሰውነትን ታጥቦ ሁለቱን የምስክር ቃል

ለአላህ መስጠት ነው።

እስከ አሁን ባገኘሀው እውቀት ወደዚህ ሀቅ ልትደርስ ፈጣሪህ

ከመራህና ሀቁን ተቀብለህ ከላይ የተገለጸውን ከልብ ከፈጸምክ፤

እንኳን ደስ አለህ(ሽ)! እጅግ በጠም ታድለሃል(ሻል) እላለሁ።

ምክንያቱም አላህ ከማይገባው እንከን ሁሉ ጥራት ይገባውና አል

እስራእ በተባለው የቁርዓን ምዕራፍ ውስጥ በአንቀጽ ቁጥር 157:-

«ለነዚያ በተውራትና በእንጅል (ኦሪትና ወንጌል)... እነዚህ በርሱ

ያመኑት፥ ያከበሩት፥ አጋር የሆኑትና ከራሱ ጋር የወረደውን

ብርሃን የተከተሉት እነርሱ በእርግጥም ስኬታማዎቹ እነርሱ

ናቸው።» በማለት ያበስረናልና። /የዚህን አንቀጽ ሙሉውን

ይዘት ከዚህ በፊት ጠቅሰናል/

የእስልምና ሀይማኖት እምነትና ተግባራቶቹ ምንድን ናቸው?

በእስልምና ሀይማኖት የእምነትና የተግባር ደረጃዎች ሦስት

ናቸው። እነርሱም እስላም፥ ኢማንና ኢህሳን ይባላሉ። አሁን

በዚህ ጽሑፋችን የመጀመሪያውን እስላምን በአጭሩ እንቃኛለን።

ስለ ኢማንና ኢህሳን በአላህ ፊቃድ በሌላ ጽሑፍ ለመዳሰስ

እንሞክራለን።

የመጀመሪያ ደረጃ

ከሦስቱ የእምነትና የተግባር ደረጃዎች እስላም የመጀመሪያው

ሲሆን አምስት መሠረቶች አሉት። 1) ሁለቱ የምስክር ቃል

/ሸሃዳ/ 2) ሰላት 3) ዘካ 4) ጾምና 5)ሐጅ ናቸው።

1) ሁለቱ የምስክር ቃል (ሸሃደተይን)

«አሽሀዱ አን-ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወ አሽሀዱ አንነ-ሙሐመደን

ረሱሉሏህ» = ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ ሌላ አምላክ

አለመኖሩን እና። ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን

እመሰክራለሁ።

ዋናው የእስላም ማዕዘንና መሠረቱ ነው። ቃሉንና ትርጉሙንም

በአጭሩ በሠንጠረዥ ውስጥ ጠቅሰነዋል።

ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ ሌላ አምላክ የለም።

ይህን ስንል አላህ የሚለው የአረብኛ ቃል ከሱ ምንም ቃል

ሊራበለት ማለትም ወደ ወንድና ሴት ጾታም ሆነ ወደ ብዙ

መግለጫ ቃል መለወጥ የማይችል አንድ አምላክን ብቻ የሚገልጽ

ሲሆን ምንም አይነት አምሳያ የሌለውና ከማንም የተብቃቃ ምንም

አይነት ረዳት፥ ምስት፥ ልጅና ጓደኛ የማያስፈልገው የተውሂድ

ማለትም ሀያል ፈጣሪን አሀዳዊነት /ብቸኛ አምላክነት/ የሚያሳይ

ቃል ነው። ይህን ቃል መመስከራችን ፍጹም በአለም ላይ ከአላህ

በስተቀር በሚመለኩ ጌቶች ሁሉ መካድንና አላህን ብቻ በአምልኮ

ተግባራት ማገልገልን ይፈልግብናል። የአላህን አሀዳዊና

2

1

ا����ر��ተቀ. 4

አምላክነትን አውቆ፥ አምኖ፥ እውነት ነው ብሎና ወዶ መቀበል፤

ከሱ ውጭ ያሉ በሀቅ አምልኮት የሚገባቸው አማልክት

አለመኖራቸውንና አሉ የሚባሉት ሁሉ ያማይገባቸውን እዳ

መሸከማቸውን አውቆ ማስተባበልና በተግባሪም ከአንድ ሀያል

ፈጣሪ ከአላህ ውጭ የሉትን አካላት መካድ ያስፈልጋል።

እንድሁም :-

ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው። ስንል የነቢዩ

ሙሐመድን(ሰ.ዐ.ወ) ነቢይ /መልዕክተኛነት/ መመስከር ማለት

ነው። እርሳቸው ከአላህ ዘንድ መልዕክቱን ለህዝብ ለማድረስ

የተላኩ የመጨረሻ ነቢይ መሆናቸውን፥ ከአላህ ዘንድ

የተገለጸላቸውን እውነት እንጅ በስሜት የማያዙ መሆናቸውን፥

ያዘዙትን መልዕክት እውነት ነው ብሎ መቀበልና መፈጸም፥

የከለከሉትን መታቀብ። አላህን እርሳቸው ባዘዙት መንገድ ብቻ

ማምለክ። በእርሳቸው ጊዜ ካሉት ሰዎች ጀምሮ እስካ አለም

የመጨረሻ ቀን ድረስ ላሉት ለሰው ልጆች በአጠቃላይ

መላካቸውን ማወቅ ማመን። የአላህ አገልጋይ (የአላህ ባሪያ)

እንደሆኑ፥ እንደማይመለኩ፥ የታዘዛቸው ጀነት፥ ያልታዘዛቸውና

ያመጻባቸው ጀሀነም (የእሳት ቅጣት) እንደሚጠቢቃቸው ማወቅና

ማመን ነው። እንዲሁም በእምነትና አመለካከት፥ በአምልኮ

ስርዓት፥ በሕግና አስተዳደር፥ በስነ-ምግባር፥ በቤተሰባዊ

ጉዳዮች፥ ሐላልና (የሚፈቀዱ) ሐራም (የማይፈቀዱ) ጉዳዮች፥

… ወዘተ የአላህን ህግ ከእርሳቸው እንደምንቀበል ማወቅና ማመን

የግድ ይሆናል። ምክንያቱም የፈጠሪን መልዕክት ለሰው ልጆች

አድራሽ ናቸውና።

2.) ሰላት

ሰላት /ስግደት / በእስላም ውስጥ ትልቅ ቦታ አላት። ጠቀሜታዋም

እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው። ምንም አጠጥሜ አሳምሬ ብጽፈውና

ባወራው እውነተኛ ጣዕሙንና ጥቅሙን ሊገልጽልህ አልችልም።

በእርግጥም ሲትቀምሰው በህይዎትህ ላይ ስትተገብረው ብቻ

የሚታገኘው ይሆናል። ሰላት:- ✓ የእስላም ምሰሶ ነው። ✓ ከጅሃድም ምርጥ ጅሃድ ነው። ✓ የጀነት ቁልፍ ነው። ✓ የሙዕምን/አማኝ/ ብርሃን ነው። ✓ ከወንጀሎች ትከለክላለች። ✓ሓሳብና ጭንቀትን

ታስወግዳለች።

እያንዳንዱ ሙስልም /ሙዕምን/ ማወቅ ያለበት ጉዳይ እስላም

ከተመሠረተበት ዋና የምስክር ቃል(ሸሃደተይን) ቀጥሎ ትለቁ

የእስላም ምሰሶ ሰላት መሆኑን ነው። ሰላት እስላም /አማኝ/

በመሆንና ከሃዲ በመሆን /ኩፍር/ መሀከል ያለች ድንበር ናት።

ቁርዓንና የነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ትምህርት /ሀዲስ/ እሄንኑ

ያብራራሉ። በአንድ ቀንና ሌሊት(24ሰዓት) ውስጥ አምስት ጊዜ

ይፈጸማል። በሰላት ውስጥ ያለ ምንም አገናኝ ከአላህ ጋር

ትገናኛለህ። የተሟላ ንጽህና አድርገህ የምትለብሰውና

የሚትሰግድበትም ቦታ ንጹህ መሆን አለበት። በዚህ አይነት

ሁኔታ የአለማት ጌታ አላህ ፊት ለመቆም በንጹህ ልብ

ትዘጋጃለህ። በሰላትህ ውስጥም እሱ ፈጣሪህ አንቴ ፍጡር ነህና

በመተናነስ ምህረቱንና እዝነቱን ትጠይቃለህ። ሰላት አማኙ

በሁለንተናዊ አካላቱና በቀልቡ /በልቡ/ አላህን የሚያመልክበት፤

የምስክር ቃሉን በተግባር የሚያድስበት የአምልኮ ተግባር ነው።

በጊዜያት የተደነገገችና የተሟላ ስነ-ስርዓት ያለት ስትሆን

ሙስሊሞች ከወንድሞቻቸው ጋር ተሰባስቦ በጋራ ወደ አንድ

አቅጣጫ /ካዕባ/፤ አንድ ፈጣሪያቸውን፤ በአንድ መሪ፤ አንድ

አይነት ተግባር፤ አንድ አይነት ስርዓት በመፈጸም ፈጣሪን

የሚያመልኩ በጣም አስደሳች የሆነ የኢባዳ ስርዓት ነው።

ይህንንም ሆነ ሌሎች የአምልኮት ተግባራት በሙሉ ደስ ስለሚሉ፤

በሌሎች እንድንታወቅና እንድንወደድ፤ ሰው ስለሚያደርግ

የሚናደርግ ከሆና ግን ጥፍጥናውንና ሌሎች በሰላት ምክንያት

ቃል የተገቡትን ዱንያዊ /ምድራዊ/ ጥቅምም ሆነ በአላህ ፍት

የመጨረሻ /የፍርድ/ ቀን የሚናገኘው ትሩፋት አይኖረንም።

ለፈጣሪያችን አላህ ብቻ ባለ መፈጸሙ ወደ ሌላ አስከፊ ጉዳይ

ይከተናል። በሌላ ቋንቋ በኢክላስ /ለፈጣሪ ብቻ/ መፈጸም የግድ

ይሆናል ማለት ነው።

አምስቱ ሰላቶች

በቀንና በሌሊት ውስጥ ሁሉም አዋቂ ሙስሊም እንዲሰግድ

የሚጠበቂበት አምስት ሰላት ነው። እነሱም በሙዕምኖች ላይ

በጊዜያት የተደነገጉ ለአላህ ብቻ የሚፈጸሙ ሁሉንም የኢባዳ

/የአምልኮት/ አይነቶች (የልብ እምነት ንግግር እንቅስቃሴ

/ተግባር/ አምልኮት አይነት ነች።

ሰጋጁ ሰላቱን ለመስገድ ሲቆም የሰላት ቅድመ ሁኔታን

ማሟላት ያስፈልጋል። እነሱም ጠሃራ/ንጽህና/ ከሁለቱ

ሀፍረተ ገላችን ከሚወጡት ከማናቸውም ነገር (ቆሻሻ)

ለመንጻት የሚደረጉ ንጽህና ጠሃራ ይባላል። የተለያየ

ደረጃዎችና የአደራረግ ስነ-ስርዓቶች አሉት። ከሽንትና ከሰገራ

በንጹህና ደረቅ ያልተከለከሉ እንደ ድንጋይ ደረቅ አፈር

ወረቀት ሶፈፍት ጨርቅ… ወዘተ ባሉ ነገሮች ቆሻሻ

ማውጫውን ቦታ ብቻ መጸዳዳት (እስትጅማር) ወይንም በውሃ

መታጠብ (እስትንጃእ) ከቆሻሻው መጽዳት አለብን። በስሜትና

ከተቃራኒ ጾታ ፊላጎት በመነሳት የሚወጣውን አሟላጭ የሆና

ፈሳሽ ሲወጣ /መዝይ/ ከብልታችን ሲወጣ በዊሃ

ከሰውነታችንና ከልብስ ላይም ማጠብ አለብን።

ሌሎች እንደ የወር አበባ፤ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በማድረግ

ወይም በመጫወት፣ በህልምና በመመኘት የዘር ፊሬ ፈሳሽ

ሲወጣን፤ ከወልድ ደም ከመሳሰሉት መጸዳዳት የምንችለው

ሰውነትን በመታጠብ፣ ውሃ ካጣን እስከምናገኘው ጊዜ ብቻ

በንጹህ አፈር ማበስ (ተየሙም) በማድረግ ጠሃራ ማድረግ

ይጠበቅብናል።

ከነዚህ በኋላ ዉድዕ ማድረግ (ለሰላት ሌሎችን:- ፊት÷ እጅ÷

ጸጉርና ጆሮን ማበስ እንደሁም እግርን መታጠብ)

ይኖርብናል። በእየንዳንዱን እንቅስቃሴና የአምልኮት ተግባራት

ውስጥ መረሳት እንደሌለበት ሁሉ ኒያ ማድረግም አስፈላጊ

ነው። ይህንን የተሟላ ንጽህና የሚናደርገው አላህ ፊት በሰላት

ለማቆም መሆኑን በልባችን ማሰቡ(ኒያ) ከሰላት በፊት

የሚደረጉ ቅድሚያ ዝግጅት ውስጥ ችላ ልባሉ አይገባም።

ሰላትን በአላሁ አክበር ጀምረን በበሠላምታ እስከምን

ጨሪሰው ያለውን ሂደት በዚህ ጹሑፍ ለመዳሰስ ስለማንችል

አላህ ካለ ስለ ዝዝር ህጉና ስነ-ስርዓቱ በሌላ ጽሑፍ ለመዳሰስ

እንሞክራለን።

የአምስቱን ሰላት ዝርዝር ስማቸውን፣ ረካዓቸውንና

የሚፈጸሙበት ጊዜያቶችን በሚከተለው ሠንጠረዥ ውስጥ

ላማስታወስ እሞክራለሁ።

የሰላቱ ስም የረከዓ

ብዛት የሚጀምርበት

ጊዜው

የመጨረሻው ጊዜ

ሱብህ

/ፈጅር

2 ንጋት(የሁለተኛ

ጎህ) ሲቀድ

ጸሓይ ከመውጣቷ

በፊት አንዷን ረከዓ

ከደረሰ

ዙህሪ(የቀትር) 4 ጸሓይ ከእኩለ ቀን

ወደ ምዕራብ ጋደል

ካለች

የያንዳንዱ ነገር ጥለ

ከቁመቱ ጋር እኩል

እስክሆን

አስር 4 የአንድ ነገር ጥለ

ከቁመቱ ጋር እኩል

ሲሆን

ጸሓይ ልትጠልቅ

ስትል

መግሪብ 3 ልክ ጸሓይ እንደ

ጠለቀች

ቀዩ ውጋገን ሲጠፋ

ያበቃል

ኢሻእ

/የሚሽት

4 ቀዩ ውጋገን

እንደጠፋ

ይጀምራል

እስከ እኩለ ሌሊት

ድረስ

3.) ዘካት

ከእስልምና መዕዘናት (ምሰሶ) ሦስተኛው ዘካ ነው። ዘካ ማለት

ምጽዋ /ካለህ ገንዘብ (ሀብት) ላይ ለድሃ የምትሰጠው መጠን/

ማለት ነው። ይህም በአመት ውስጥ አንድ ጊዜ ባለሀብት

ሙስልም ካለውና ዘካ መስጠት የግድ ከሚሆንባቸው የሀብት

አይነቶች ላይ ያወጣል።

ዘካ እጅግ በጣም ትንሽ የሆነ ገንዘብ በአመት ውስጥ ለድሆችና

ሌሎች ዘካ መቀበል ለሚገባቸው አካል የሚሰጥ ሲሆን ለዘካ

አውጭውና ለተቀባዩም የየራሱ የሆነ ጠቀሜታ አላው።

ሀብታሙን ከደሃ ያገነኛል። ባለ ሀብቱን በቀሪ ሀብቱ ላይ በረከት፣

የአላህን እዝነትና ትሩፋት ያስገኝለታል። የቸርነትን፥

3 4 5

የለጋሽነትን፥ ለሌሎች ማሰብን፥ ማህበራዊና የልብ ንጽህና

የመሳሰሉ ጸጋዎችን ያጎናጽፈዋል። ዘካ ሲሰጥ ወዶና በደስታ

መስጠት አለበት። ዘካውን ሲሰጥ ከሰጣቸው ሰዎች ምንም አይነት

ውለታ መጠበቅ የለበትም። በነሱ ላይም አለመመጻደቅ። እነሱን

በዚህ ሰበብ አለማወክ የግድ ይሆንበታል። ይህን ያህል ካለን ቀሪ

ዕውቀቶቹን(ከምን ዓይነት ሀብት? ምን ያህል ይወጣል? ድሃ

ሲባልና ሌሎች ዘካ የሚሰጣቸው እነማን ናቸው? መቼ ጊዜና

እንዴት?) ለሚሉት ዝርዝር የዘካ ዕውቀት ሰፋ ባለ ጽሑፍ ውስጥ

የሚዳሰስ ስሆን አንባቢው ከአዋቂዎች ጠጋ ብሎ ስለ ማንኛውም

የእምነቱ እውቀት የማግኛት ግዴታ አለበት።

4.) ጾም

በአመት ውስጥ አንድ የረመዳን ወርን መጾም ከእምነቱ የአራተኛ

ማዕዘን/ምሰሶ/ ነው። እጅግ በጣም ምስጥራዊ የሆነ ለአላህ ብቻ

የሚፈጸም ተግባር ነው። ጾም ማለት በእስልምና ከሚበላና

ከሚጠጣ ነገሮች ብቻ መታቀብ አይደለም። በተጨማሪ

ካልተፈቀዱ ጉዳዮች በሙሉ መታቀብ ነው። ከረመዳን ወር

የመጀመሪያ ቀን ጎህ ከመቅደዱ በፊት ጀምሮ እስከ ጸሓይ

መጥለቂያ ያለውን ጊዜ በወሩ ቀናቶቹ ሁሉ ውስጥ ከመብላት፥

ከመጠጣት፥ ከግብረ ስጋ ግንኙነት፥ ከማማት፥ ከመዋሻት፥

ከመበደል፥ በአይን ያልተፈቀዱ ሀራም ነገሮችን ከማየትና በጆሮ

ያልተፈቀዱ ሀራም ነገሮችን ከመስማት ሁሉ ይታቀባል። ሆኖም

ግን አላህ ለሽማግሌ፥ ለመንገደኛ፥ ለበሽተኛ፥ በወር አበባ ላይ

ላሌች ሴት፥ ለነፍሰጡር፥ ለአራስእና ለሚታጠባ እናት

አፈጻጸሙን አቅሎላቸዋል። እያንዳንዱን የሚመለከቱ የማቃለያ

ድንጋጌዎችን ደንግጓል። ምስጋና ለቸሩ የአለማት ጌታ እጅግ

በጣም አዛኝና ሩህሩህ ለሆነው ይሁን።

ጾም ቀልብን/ልብን/ በማጽዳት ወደ ፈጣሪ እንድትጓጓ ያደርጋል።

አላቂና አላፊ የዚህች አለም ብልጭልጭታዎችን ፊላጎት

ያከስምና በአላህ ዘንድ ያለውን ዘላለማዊ ጸጋዎችና በረከቱን

እንድትከጅል ያደርጋል። ሀብታሙ የደሃ ወንድሙን ችግር

የሚያስታውስበትና ልቡ የሚያዝንበት አላህ በሰጠው ሀብት

የሚያመሰግንበት ጊዜ ይሆናል።

5.) ሐጅ

ሐጅ ማለት በተቀደሰችው መካ ከተማ ውስጥ የለውን የአላህን

ቤት/ካዕባ/ መጎብኘት ማለት ነው። ሐጅ በእድሜህ ውስጥ አንድ

ጊዜ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ ብቻ የሚፈጽም የእስልምና

አምስተኛው ምሰሶ ነው። ቅድመ ሁኔታዎቹም፦ እድሜህ

ለአቅመ አዳም/ሄዋን/ መድረስና ሙስሊም መሆን፤ ደርሰህ

የሚትመጣበትን መጓጓዣ፤ ለመንገድ የሚያስፈልግህ ገነዘብ፥

ቀለብ፥ ደርሰህ እስክትመጣ ቤተሰቦችህ የሚጠቀሙበት ቀለብ፥

ወደዚያ የመሄዱ መንገድ ሠላም መሆንና ሄዴህ እስክትመጣ

ድረስ መሄድህ ቤተሰቦችህ ላይ አደጋ የማይጥል ከሆነ ሐጅ

ማድረጉ ግዴታ ይሆንብሃል። ይህን ማድረግ ያሰበ ሰው

መጀመሪያ ወደ አላህ ተውባ /ንሰሃ/ በማድረግ ከሳለፈቸው

ወንጀሎች ተጸጽቶ ወደ እርሱ ምህረት መከጀል አለበት። እዛም

ሲደርስ አላህን በማተለቅና በመወደስ በሐጅ ስነ-ስርዓት

የሚፈጸመውን የአምልኮ ተግባር ለአላህ ይፈጽማል። ካዕባና

ሌሎችም በመካ ያሉ የተቀደሱ የአምልኮ ቦታዎች ሁሉ

እንደማይመለኩ በደንብ ለይቶ ማወቅ አለበት። መጥቀምም ሆነ

መጉዳት እንደማይችሉ ማወቅ አለበት። ወደዚህች የተከበረች

ቦታ ሄዶ ሐጅ ማድረጉን አላህ ባያዝ ኖሮ የሐጅ ስርዓት መፈጸሙ

ባልተፈቀደ ነበር። እናም በዚህ የሐጅ ስነ-ስርዓት ላይ ከዓለማችን

የምድር ክፍል ሁሉ የተሰበሰቡ ሙስሊሞች ሁሉም ነጭ ያልተሰፈ

ልብስ ለብሶ፤ ጥቁሩ ከነጭ፥ ሀብታሙ ከደሃ፥ መሪው ከተመሪ

ሳይለይ ሁሉም ለአላህ ታዛዥነታቸውን ጥሪ በአንድ ቋንቋ

እያስተጋቡ አንድ ፈጣሪያቸውን ያመልካሉ። ይህም ስርዓት

በመጨረሻ የፍርዱ ቀን ከሞት ተቀስቅሶ ሁሉም በአንድ አይነት

ወደ ሀያሉ አላህ ፊት ለፍርዱ የሚቆሙበትን ስርዓት

ያስታወሳቸዋል። ልቦቻቸው ያዝናል። ወደርሱ ይከጅላሉ።

ይማጸኑታል ጉዳያቸውን ሁሉ ወደርሱ ይጸልያሉ። እንግድህ

እጅግ ጣም በጥቅቱ ለመዳሰስ የሞከርኩት የእስልምና ምንነትና

ማዕዘናቱን ነው። በዚህች በራሪ ወረቀት በዚሁ አርእስት ላይ ብዙ

ያልተዳሰሱ ነጥቦች አሉ። በአጭሩ ከተነኩት ይልቅ ያልተነኩ

ነጥቦች በብዙ እጥፍ ይበልጣሉ። ይህን ነው ለአንባቢው በዚህች

ጽሑፍ ማለት የሚችለው። አንተ ሀቅን ለማወቅ ከታገልክ ፈጣሪ

አላህ ያገራልሃል።

ምስጋና ለአላህ ይሁን እስላምን እንደሀይማኖት የመረጠልኝና ለአለም

ሁሉ እስልምናን መርጦ የወደደለቸው። የአላህ እዝነትና ሠላም

ከተላለፈለት መለኮታዊ ትዕዛዝ በስተቀር በስሜቱ የማያወራ የአላህ

መልዕክተኛ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ይሁን። እምነቱንም ለሙሉ የህይዎታችን እስትንፋስና ለእለት ተዕለት ተግባሬችን እንዲያገራል ን

በቸሪነቱና በእዝነቱ እማጸነዋለሁ እርሱ ነውና ወደ ቀጥተኛ ብርሃን

የሚመራ።

-----/ ሁላችንም ወደ ቀጥተኛ ብርሃን ይምራን። አሚን /----

[email protected]

6

7