36

Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

  • Upload
    others

  • View
    38

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና
Page 2: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

Contents December 2014 ታህሳስ 2007

Language Matters

Volume 3 3ኛ እትም

is an annual publication of

SIL Ethiopia.

If you have comments or questions,

please contact us.

SIL Ethiopia

Multilingual Education (MLE)

Department

PO Box 2576

Addis Ababa

011 321 38 25/27

[email protected]

Mesfin Derash, Editor-in-Chief

Letter from the Editor 1

Mesfin Derash

Multilingual Education Coordinator

SIL Ethiopia

Our Children Have Become Very Clever 4

Douglas Blacksten

Country Director

SIL Ethiopia

Language Development and Planning

in Ethiopia 6

Alemayehu Getachew

Senior Language Expert

Ministry of Culture and Tourism

Mother Tongue as a Subject

Why Learn a Language You Already Know? 10

Aija Katriina Ahlberg

Literacy Advisor

SIL Ethiopia

International Mother Tongue Language Day 15

Michael Bryant

Language Program Director

SIL Ethiopia

The Strengths and Challenges of Sustainable

Language Development in Ethiopia 18

Michael Bryant and Mesfin Derash

This is Our Descendent 20

Travis Williamson

Translation Advisor

SIL Ethiopia

Growing a Multilingual Education Program 23

Dr. Patricia Davis

Senior Literacy and Education Consultant

SIL International

Page 3: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters

Mesfin Derash

W elcome to our third volume of Language

Matters. The purpose and ultimate goal

of this journal is to enhance all language

development and multilingual education efforts.

The importance of education for all is undisputable.

However, when it comes to dealing with formal

education, there are various significant factors in

contributing toward its effectiveness and success,

factors without which, formal education would be a

failure or even impossible. At the forefront of these

factors are two key issues: relevant curriculum for

mother tongue education for children at primary school,

and appropriately trained mother tongue teachers.

The mother tongue or first language of children at

primary school is decisive for their educational

achievement and success. This does not mean

avoiding Amharic lessons; as it is the federal working

language, our constitution and the education and

training policy have explicitly stated that Amharic

should be a taught at school. Neither does mother

tongue education mean that we avoid English lessons,

since English is a language of wider communication

and a medium of instruction at secondary and tertiary

levels. The major principle of mother tongue

education is that children should not be hampered in

their early learning; comprehension is enhanced

because their teacher is using a language they know.

Students can more easily grasp the concepts of any

lesson that is taught in their mother tongue. Without

understanding, there is no learning. Indeed, the central

role of language in processes of cognition and learning

is a well-established fact. Many research findings from

around the world have proven that success in

education is strongly tied with knowing the language.

One very relevant publication is UNESCO’s Mother

Tongue Based Literacy Program Case Studies of Best

Practices in Asia.

These concepts have already been embraced by our

educational policy makers; what we must now strive

for in Ethiopia is quality. Quality should be the

concern of all relevant stakeholders, and a coherent

strategy is needed. This is the very purpose for which

the Ethiopian Multilingual (MLE) Network was

established a few years ago. SIL Ethiopia hosted a

one-day conference on December 16, 2014. There

were delegates from several universities, NGOs and

INGOs, as well as representatives and guests of honor

from the Ministry of Education and the Ministry of

መስፍን ደራሽ

ንኳን ወደ ሶስተኛው ቅጽ የቋንቋ ጉዳይ እትማችን መጣችሁ። የመጽሄታችን ዓላማ እና የመጨረሻ ግብ በቋንቋ ልማትና በልሳነ ብዙ ትምህርት ዙሪያ የሚደረጉ ጥረቶችን ሁሉ መደገፍና ማበረታታት ነው። የትምህርት ለሁሉም አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም። ይሁንና ወደ መደበኛው ትምህርት ስንመጣ ለስኬታማነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በርካታ ታሳቢ ጉዳዮች አሉ። ያለ እነዚህ ታሳቢ ጉዳዮች የመደበኛ ትምህርትን ስኬት ማለም ከንቱ ነው። ምናልባትም ውድቀት ይሆን እንጂ።

ከእነዚሁኔታዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚነሱ ሁለት ታሳቢ ጉዳዮች አሉ። የመጀመሪያው ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት የሚውል ተገቢ ስርአተ ትምህርት የማዘጋጀት ጉዳይ ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ በወጉ የሰለጠኑ የአፍ መፍቻ ቋንቋ መምህራን መኖር ነው። በአንደኛ ደረጃ ውስጥ የሚሰጠው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ለህጻናቱ የወደፊት የትምህርት ስኬታማነት ወሳኝ ነገር ነው።

ይህን ስንል ግን የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ፈጽመን እናስወግድ ማለታችን አይደለም። አማርኛ የፌደራል የስራ ቋንቋ መሆኑ በህገመንስታችንና በትምህርት ፖሊሲው እንደመገለጹ ልጆች በትምህርት ቤታቸው ሊማሩት ይገባል። ባንጻሩም የአፍ መፍቻ ቋንቋን እናስተምር ስንል በአለም ላይ በስፋት ለመግባቢያነት የሚጠቅመውን፣ የሁለተኛ እና የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ የሆነውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን እንተው ማለታችንም እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል።

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ዓላማ ህጻናት በማያውቁት ቋንቋ እየተማሩ ለጋ የመማር አጋጣሚያቸው በጭንቀት የተሞላ እንዳይሆን ማድረግ ነው። መምህራቸው በሚያውቁት ቋንቋ ሲነግራቸው የመረዳት አቅማቸውም ይጨምራል።

Letter from the Editor

የዋና አዘጋጁ መልዕክት

Participants at the one day conference for the

Ethiopian MLE Network

Page 4: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

2 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

በየትኛውም የትምህርት ዓይነት የሚገለጽ ጽንሰ ሃሳብ በአፍመፍቻ ቋንቋቸው የሚተላለፍ ከሆነ በቀላሉ ይረዱታል።

ልብ ሊባል የሚገባው ነገር በቋንቋ መረዳት ካልተቻለ ትምህርት የሚባል ነገር አለመኖሩ ነው። በርግጥ የቋንቋ ጉዳይ አንድን ነገር ለማውጠንጠንና ለመረዳት የሚያገለግል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። በአለም ላይ የተደረጉ በርካታ ጥናቶች የትምህርት ስኬታማነት ከቋንቋ ጋር እንደሚያያዝ አስረግጠው ያስረዳሉ። ለዚህ አስረጂ ከሆኑትና ለህትመት ከበቁት ምርምሮች ውስጥ Mother

Tongue Based Literacy Program Case Studies of Best Practices in Asia. በሚል በዩኔስኮ የተደረገው ጥናት ነው።

በዚህ ጥናት ውስጥ የተገለጸው ሃሳብ አሁን ለትምህርት ጥራት ከምናደርገው ርብርብ ጋር የሚመሳል በመሆኑ ሃሳቡ አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና ተያያዥ ስትራቴጄዎች የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጉዳይ ነው። ከጥቂት አመታት በፊት የ Ethiopian Multilingual (MLE) Network የኢትዮጵያ ልሳነ ብዙ ትምህርት ቅንጅት መመስረትም ይህንን አላማ ለማሳካት የታቀደ ነው። በዚህ ዙሪያ በኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት ሲሰራ የቆየው ኤስ አይ ኤል ኢትዮጵያ (SILEthiopia) ታህሳስ 7/2007 ዓ.ም ሰፊ ኮንፈረንስ አዘጋጅቶ ነበር። በእለቱ የMLE Networkን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉትን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ዲኤታ ክቡር አቶ ሙሉጌታ ሰይድን ጨምሮ መንግስታዊና መንግሳታዊ ካልሆኑ ተቋማትና ከበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተው ነበር።

የልሳነ ብዙ ትምህርት (MLE) ዓላማና የተሳታፊ አባላት ተግባር እንደየ ሃገሩ አውድ የሚለያይ ሲሆን በኢትዮጵያ የተዘረጋው ቅንጅት ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው።

የአፍመፍቻ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የልሳነብዙ ትምህርትን በተቀናጀ መልኩ በመደገፍ ለትምህርት ጥራት እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮችን መለየትና ማስወገድ፣

Culture and Tourism who addressed the audience and

wholeheartedly supported the efforts of the Ethiopian

MLE Network.

The objectives and tasks of various working groups

devoted to MLE issues differ from country to

country, based on the context. The objectives of the

Ethiopian MLE Network will be the following:

To help identify and remove barriers of access to

quality education through coordinated support for

Mother Tongue Based-MLE (MTB-MLE).

To promote linguistically and culturally

appropriate education as an integral part of quality

mother tongue education.

To create an environment that fosters collaborative

effort among academics, practitioners, and other

stakeholders regarding their endeavors in the area

of MTB-MLE.

SIL Ethiopia envisions these objectives being refined

and agreed upon by all the participating organizations

in the Network. These objectives will help to define

our mission and goals. Some of the proposed tasks of

the Network will be as follows:

Identify technical problems regarding MTB-MLE

implementation in Ethiopia.

Create a forum for scholars and academics to

collaborate on innovative solutions for

implementing MTB-MLE

Disseminate research-based evidence and resources

about MTB-MLE

Generate ways to inform and influence local

community stakeholders, and advocate for

community participation in language decisions

The Ethiopian MLE Network met on December 16, 2014.

Pictured above are His Excellency Ato Mulugeta Seid the State Minister of Culture and Tourism, Dr. Alemayehu Hailu, SIL Director for

Eastern and Southern Africa, and Awlachew Shumneka, Director for Languages and Cultural Values Directorate, MOCT.

photo

by

SIL

Eth

iop

ia

Page 5: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 3

Contribute to the capacity development of

curriculum implementers, trainers, and teachers

Communicate with the international education

community about the Ethiopian context

I am sure many other relevant stakeholders will join

this Network for the betterment of Mother Tongue

Based Multilingual Education in the county.

May God Bless Ethiopia. Enjoy reading!

Mesfin Derash

Multilingual Education (MLE)

Coordinator, SIL Ethiopia

ጥራት ካለው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ጎን ለጎን ስነልሳናዊና ባህላዊ ተገቢነት ያለውን ትምህርት ማበረታታት፣

የአፍ መፍቻ ቋንቋን መሰረት ባደረገ የልሳነብዙ ትምህርት ዙሪያ የሚሰሩ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ተባባሪዎች እና ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት በትብብር የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት ናቸው።

ኤስ አይ ኤል ኢትዮጵያ በህብረቱ (ቅንጅቱ) አባል የሆኑ በዓላማው ላይ ባለድርሻ አካላትና ተሳታፊዎች ከተስማሙና ካዳበሯቸው በኋላ እነዚህን አላማዎች በተጠቀሰው መልኩ አዘጋጅቶ አቅርቧል። እነዚህ ዓላማዎች ተልእኳችንና ግባችንን እንድንለይ ረድተውናል። የቅንጅቱ ተግባር እንዲሆኑ ከቀረቡ ሃሳቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

በኢትዮጵያ የአፍመፍቻ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የልሳነብዙ ትምህርት ትግበራ የሚያጋጥመው የቴክንኒክ ችግር መለየት፣

የአፍ መፍቻ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የልሳነብዙ ትምህርት ዙሪያ ለሚጽፉ ተመራማሪዎችና የትምህርት ባለሞያዎች የተመቻቸ መድረክ መፍጠር፣

የአፍመፍቻ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የልሳነብዙ ትምህርትን በተመለከተ በጥናት ላይ የተመሰረቱ አዳዲስ ግኝቶችን ማሰራጨት፣

በቋንቋ ጉዳይ በየአካባቢው ያሉ የማህበረሰቡ አባላት ና የባለድርሻ አካላት በቋንቋ ውሳኔ ሰጪነት ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን፣ ግንዛቤ የሚጨብጡበትን መንገዶች መፍጠር፣

የስርአተ ትምህርት ትግበራ ላይ ተሳታፊዎችን፣ አሰልጣኞችን እና መምህራን አቅም መገንባት፣

የኢትዮጵያን የትምህርት ዐውድ ለዓለም አቀፉ የትምህርት ማህበረሰብ ማስተዋወቅ የሚሉት ናቸው።

በመጨረሻም በሀገራችን የአፍ መፍቻ ቋንቋን መሰረት ያደረገውን የልሳነብዙ ትምህርት ፕሮግራም የተሻለ ለማድረግ የሚመለከታቸው በርካታ ባለድርሻ አካላት ይህን ቅንጅት እንደሚቀላቀሉት እርግጠኛ ነኝ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ። መልካም ንባብ!

መስፍን ደራሽ

የልሳነ ብዙ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ኤስ አይ ኤል ኢትዮጵያ

Pictured above are some of the participants at the one day conference for the Ethiopian MLE Network.

all

ph

oto

s b

y S

IL E

thio

pia

Page 6: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

4 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Douglas Blacksten

P arental support and involvement in education

are increasingly viewed as significant factors

in a child’s achievements at school in several

areas. Research indicates a correlation between

parental involvement and higher academic success,

along with a better attendance record and an overall

positive attitude toward learning.

If parental engagement contributes to success in

general education, then it is especially important for

mother tongue education. Parents must be well

informed about the benefits of mother tongue instruc-

tion; they need reassurance that it is not going to put

their children at a disadvantage. In fact, when child-

ren begin school by learning in their mother tongue,

the knowledge they bring to the classroom is valued

and affirmed. They gain confidence in their skills in

their first language first. Then, when they bridge to a

second language, they have already had a positive

learning experience; success breeds success.

Representatives of a monitoring and evaluation team

recently visited a major mother-tongue-based

Our Children Have

ልጆቻችን በጣም ጎበዞች ሆነዋል!

ል ጆች በትምህርት ቤት ለሚያስመዘግቡት ውጤት

የወላጆች ድጋፍና ክትትል ወሳኝ ነው የሚለው

አስተሳሰብ በብዙዎች ዘንድ እየተስፋፋና

ተቀባይነት እያገኘ ነው። ወላጆች በትምህርተ ቤት

የሚያደርጉት ተሳትፎ፣ ለልጆች (ተማሪዎች) በትምህርት

ገበታ ላይ ሳይቀሩ መገኘት እንዲሁም ለመማር ያለ ቀና

አስተሳሰብ ለከፍተኛ የትምህርት ውጤታማነት ትልቅ

ግብአቶች እንደሆኑ ጥናቶች ያመለክታሉ።

እንግዲህ የወላጆች ተሳትፎ ለአጠቃላዩ ትምህርት

ስኬታማነት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ከሆነ ለአፍ መፍቻ

ቋንቋ ትምህርት ደግሞ ይበልጥ ጠቃሚ እንደሆነ መገመት

አያዳግትም። ስለሆነም ወላጆች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት

የሚሰጠውን ጥቅም አስመልክቶ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ

ይገባል። ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ስለተማሩ ተጎጂ

ይሆናሉ ብለው እንዳያስቡና ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እርግጠኞች

እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል። በርግጥም ልጆች ትምህርታቸውን

በአፍ መፍቻ ቋንቋ ሲጀምሩ ከቤታቸው ይዘውት

የሚመጡት እውቀት ዋጋ ያለው ይሆናል፤ በመጀመሪያ

ቋንቋቸው ቀድመው ባዳበሩት ክህሎት ዙሪያ ያላቸው የራስ

መተማመን ይጎለብታል። ወደ ሁለተኛ ቋንቋ በሚሸጋገሩበት

Become Very Clever!

When language is no longer a barrier to parents’ participation in their children’s schooling, they can confidently contribute their

knowledge and skills to the educational experience.

ph

oto

s b

y A

nd

rea

s N

eud

orf

Page 7: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 5

Become Very Clever!

multilingual education program in the Benishangul

Gumuz region. At one particular meeting, the regional

Culture and Education Bureau officials were joined by

many local parents who came to have their say.

Among the encouraging remarks about the program,

some of the most appreciative comments came from

these parents:

Before, when our children went to school and

everything was taught in Amharic, we saw how

they were suffering and how disappointed they

were. It was a very negative experience.

Children dropping out of school – it was a

normal occurrence. As parents, we were

reluctant to bother sending them to school. But

now they are learning in our own language, the

mother tongue as medium of instruction, and

they are excelling – not just in the mother

tongue class, but in ALL their other classes too.

They have become very clever!

We are amazed to hear our kids reading to us.

Now we understand that our language is just as

good as every other language. Before we

thought it was inferior because our children

were not learning it at school. This gives us

equal status with all other language groups.

Since our children now get a better education,

our own interest in school is high. We now

participate in all kinds of school-related

activities: we help to take care of the school,

and we meet to discuss the well-being of our

children. This kind of thing never happened

before.

The use of a child’s familiar language for instruction

will endorse local culture and knowledge, creating a

bridge between home and school, as well as with the

community. When language is no longer a barrier to

parents’ participation in their children’s schooling,

they can confidently contribute their knowledge and

skills to the educational experience. This will in turn,

further encourage and strenghten parental

involvement.

Douglas Blacksten

Country Director SIL Ethiopia

ጊዜ ደግሞ አስቀድመው ለትምህርት አዎንታዊ አስተሳሰብ አጎልብተዋልና ከስኬት ወደ ስኬት ይሸጋገራሉ።

በቅርቡ የድርጅታችን የክትትልና ግምገማ ቡድን ተወካዮች በቤንሻንጉል ክልል የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ፕሮግራም ዙሪያ ጉብኝት አድርገው ነበር። እዚያም የክልሉ ባህልና ትምህርት ቢሮ የስራ ሃላፊዎችና በርካታ ወላጆች ጋር አንድ ለየት ያለ ስብሰባ አድርገዋል። እነዚህ ተሳታፊ ወላጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋ ፕሮግራም ላይ አስገራሚ አስተያየቶች ሰንዝረው ነበር። ካቀረቡት አስተያየቶች መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

ቀደም ሲል ልጆቻችንን ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ሁሉንም ነገር የሚማሩት በአማርኛ ቋንቋ ነበር፤ እንዴት እንደሚቸገሩና ተስፋ እንደሚቆርጡም አይተናል። በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ነው። ልጆች ትምህርታቸውን ሲያቋርጡ ማየት የለት ተለት ክስተት ነበር። እኛም እንደ ወላጅ ልጆችን ወደትምህርት ቤት የመላክ ጉዳይ ብዙም አያሳስበንም ነበር። አሁን በቋንቋቸው ይማራሉ፤ የትምህርት መስጫ ቋንቋው የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ነው። ስለዚህ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ትምህርቶች ላቅ ያለ እውቀት እየገበዩ ነው። በጣም ጎበዞች ሆነዋል። ህጻናት ልጆቻችን ወረቀት ሲያነቡልን በጣም እንገረማለን።

አሁን የኛም ቋንቋ እንደሌሎቹ ቋንቋዎች ጥሩ ቋንቋ መሆኑን ተገንዝበናል። ቀደም ሲል ልጆቻችን የኛን ቋንቋ በትምህርት ቤት ስለማይማሩት ቋንቋችን ከሌሎች ቋንቋዎች ያንሳል ብለን እናስብ ነበር። ይሁንና ዛሬ ቋንቋችን ከሌሎች ቋንቋዎች ተርታ የመሰለፍ እድል አግኝቷል።

ዛሬ ልጆቻችን የተሻለ ትምህርት እያገኙ ስለሆነ እኛም በትምህርት ቤት ጉዳይ ላይ ያለን ፍላጎት ከፍተኛ ሆኗል።

ህጻናት የሚያውቁትን ቋንቋ ለትምህርት ማስተማሪያነት ሲውል፤ የአካባቢው ባህልና እውቀትም እውቅናን የሚያገኝበት እድል ይፈጠራል። በትምህርት ቤት፣ በቤት እንዲሁም በማህበረሰቡ መካከልም ጥሩ የመሸጋገሪያ ድልድይ ይሆናል። ወላጆች በልጆቻቸው ትምህርት ዙሪያ ተሳትፎ ለማድረግ የቋንቋ እንቅፋት የማያጋጥማቸው ከሆነ በትምህርት ቤት ውስጥ እውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለማካፈል የሚኖራቸው የራስ መተማመን ሙሉ ይሆናል። ይህም ወላጆች በትምህርት ቤት ዙሪያ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩና እንዲደፋፈሩ ያደርጋቸዋል።

photo

by

SIL

Eth

iop

ia

For the development of our mother tongue and our reading

culture/tradition, the role of parents is all-important!

Page 8: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

6 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

በዓለማየሁ ጌታቸው

የ ቋንቋ ልማት ማለት የቋንቋውን ተፈጥሮአዊ ኡደት ሳይጠበቅ ይሁነኝ ተብሎ ቋንቋው ለአንዳች እንዲያገለግል ግብ ጣልቃ በመግባት የሚሰራ ስራ ነው። ለቋንቋ ልማት መከወን የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ከነዚህ

መካከል አበይት የሚባሉት ብዝኃ ሥነ-ልሳናዊነት አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ የስልጣኔና ልማት ፍላጎት ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የአንድን አካባቢ ቋንቋ (vernacular language) በአንድ በተወሰነ ክልል እና አካባቢ ብዝኃ ሥነ-ልሳናዊነት ሲኖር የትኛውን ቋንቋ ለየትኛው አገልግሎት የሚል ጥያቄም ሲነሳ ወይም ግንዛቤው ሲፈጠርም የቋንቋውን የልማት ጥያቄ ያመጣል። በዚህም ምክንያት ለተለያዩ አገለግሎቶች አንድ ወይም ከአንድ በላይ ቋንቋዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ሲወሰን ለዚያ ቋንቋ የልማት ሥራ እንዲከናወንበት እቅድ ሊዘጋጅ ይገባል። ማንኛውም ማህበረሰብ ለመልማት እንዲሁም እድገት እና ስልጣኔ ለማስመዝገብ ለተግባቦት ሂደት የጽሁፍ ቋንቋ መጠቀም አለበት። ስለዚህም በቋንቋዎቹ ላይ የልማት ስራ መሰራት ያስፈልገዋል። ቋንቋን ለማልማት ቀዳሚው ሥራ የስርዓት ጽህፈት ቀረጻ ሲሆን ሌሎችም ተጨማሪ ስራዎች እንደዚሁ ማከናወን አስፈላጊ ነው፤ ለምሳሌ፡- መዝገበ ቃላት ዝግጅት፣ የሰዋሰው ጥናት እና ቋንቋውን በመጠቀም የተለያዩ መጻህፍትን ማዘጋጀት የዚሁ ልማት አካል ነው። የቋንቋ ልማት ሥራው አመኔታ ካገኘ እና ውሳኔ ከተሰጠበት ቀጥሎ የሚመጣውን ጉዳይ የቋንቋ ልማት እቅድ ነው። እቅዱ ሲዘጋጅ ምን፣ መቼ፣ እንዴት እና የት የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ አለበት።

የቋንቋ እቅድ ሶስት አይነቶች ናቸው። እነዚህም እስታተስ ፕላኒንግ፣ ኮርፐስ ፕላኒንግና አክዊዚሽን ፕላኒንግ ይባላሉ። እስታተስ ፕላኒንግ የሚባለው የቋንቋውን ወይም የዘዬውን አጠቃቀም ማህበራዊ ደረጃ ማስተካከል/ከፍ ማድረግ ሲሆን/በሌላ አገላለጽ ቋንቋው የትምህርት፣ የስራ፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ ወዘተ… እንዲሆን የመወሰንና የመሥራት ነው። ኮርፐስ ፕላኒንግ ደግም ቋንቋውን ለተጨማሪ አገልግሎት ለማብቃት የሚደረግ የሥነ-ልሳን ጥናትችን ነው። አክዊዚሽን ፕላኒንግ ቋንቋውን በተወሰነለት የአገልግሎት መስክ ተግባራዊ እንዲሆን የሚደረግ ስራን ያመላክታል። በኮርፐስ ፕላኒንግ እቀዳ ወቅት የሚደረጉ ሥነ-ልሳናዊ የጥናት ውጤቶች ለሥርዓተ-ጽሕፈት ቀረጻ፣ለሰዋሰው ዝግጅት እና ለመዝገበ ቃላት ሥራ እንደ ግብዓትነትም ሆነ እንደ መነሻ ሊያገለግሉ ይችላሉ። ሥርዓተ-ጽሕፈት በሌለበት ስለአንድ ቋንቋ ልማት ማሰብ አስቸጋሪ ነው። ስለዚህም በቋንቋ ልማት የመጀመሪያው ሥራ የሥርዓተ-ጽሕፈት ቀረጻ ነው። አንድን ቋንቋ ከንግግር ወደ ጽህፈት ለማሸጋገር ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ ሊታቀድ ይገባል። ሥርዓት ጽህፈት በሚቀረጽበት ወቅት ተከታዮቹ ነጥቦች በጥንቃቄ መታሰብ አለባችው። ስለዚህም በኮርፐስ ፕላኒንግ ተከታዮቹ ነጥቦች አትኩሮት ሊሰጣቸው ይገባል፡- የቋንቋውን ዘዬዎች መለየት፤ በዚህን ጊዜ ከአገልግሎት አንጻር የሚያስፍልገው ሥርዓት ጽህፈት ዘዬ - ዘለል

Language Development

Planning in Ethiopia

Alemayehu Getachew

English translation/summary by

Hussein Mohammed

W hat are the essential

components of a

successful language

development program? The first

step, of course, is to have a well-

defined plan. Next is to establish a

writing system, based on the

results of phonological analysis. In

addition, other resources should be

prepared: a dictionary, a grammar

and other reading materials. In this

article we will look at each of

these components in detail, and

consider some of the challenges to

language development in Ethiopia.

Language planning is a

prerequisite. There must be an explicit and

systematic effort to resolve

problems and achieve related

goals through institutionally

organized intervention in the use

of languages. There are three

kinds of language planning: status

planning, corpus planning, and

acquisition planning. In this

article we will consider only the

first two. Acquisition planning

deals with influencing the teach-

ing and learning of a language,

and will not be discussed here.

Status planning is concerned with

the role given to a language – it

may be used as an official or

educational language, and also for

other cultural purposes such as

የቋንቋ ልማት፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጅምር የልማት ሥራና እቀዳ

&

Page 9: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 7

ሥርዓተ ጽህፈት (ሥርዓተ ጽሕፈቱ ለሁሉም የቋንቋው ተናጋሪዎች አገልግሎት እንዲሰጥ የሚዘጋጅ ነው)፤ ውስን ሥርዓተ ጽህፈት (ሥርዓተ ጽሕፈቱ ለአንድ ዘዬ ብቻ መሰረት ያደረገ የሚዘጋጅ ነው) ወይስ አጠቃላይ ሥርዓተ ጽህፈት (ሥርዓተ ጽሕፈቱ መሰረት ያደረገው አንድ ዘዬን ቢሆንም ለሌሎች ዘዬዎችም በብቃት አገልግሎት ሊሰጥ ይሚችል ነው?) የሚሉት ጥያቄዎች በወጉ መመለስ አለባችችው። ከቅለት እና ክብደት አንጻር ለመረዳት የቀለለ ሥርዓተ ጽህፈት (ይህ ኤይነቱ ሥርዓተ ጽህፈት አንባቢው በንባብ ወቅት የተለዩ ህጎችን/ግራሞ-ሞርፎሚክ/እንዲያስታውስ አይገደድም) ወይስ ለመረዳት አሽቸጋሪ ሥርዓተ ጽህፈት (ይህ ኤይነቱ ሥርዓተ ጽህፈት አንባቢው በንባቡ ወቅት ተገቢ የሆኑ ህጎችን እንዲያስታውስ የሚያስገድድ። ለምሳሌ በእንግሊዘኛ ፡ <-ed> ሶስት አይነት ንበት አለው። /has 3 different pronunciations in <stopped>,

<robbed>, and <skidded>/ ድ፡ እድ እና ት ናቸው።) ሥርዓተ ጽህፈቱም ምን ያህል ለመማር ማስተማር ቀላል ነው? አንድ ሰው ሥርዓተ ጽህፈቱን ለመልመድ ምን ያህል ጊዜ የወስድበታል። እያንዳንዱ በቋንቋው ውስጥ ያሉ ድምጾች በአንድ ምልክት የመወከላቸው ጉዳይ፤ አንድ ድምጽ በተለያዩ ምልክቶች ሲወከል፣ ምሳሌ፡(/s/: <ሰ> እና <ሠ>)(በአማርኛ) ወይም አንድ ምልክት ከአንድ በላይ ድምጾችን ሲወክል፣ ምሳሌ፡ (<c>: [s], [k], [tʃ])

(በእንግሊዘኛ) አንድ ሥርዓተ ጽህፈት የቋንቋውን ድምጾች በትክክል መወከሉ (ድምጸልሳናዊ የአናባቢ ቆጠራ፡ ድምጸልሳናዊ የተነባቢ ቆጠራ፡ ሱፕራ ሴግመንታል ድምጸልሳናዊ ቆጠራ ወዘተ...) በጥልቀት ግምት ውስጥ መግባት አለበት። ስርዓተ ጽህፈት የልተዘጋጀለት ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰብ መገለጫ ከሆኑት ነጥቦች መካከል አንዱ ስለ ቋንቋው ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛነት ነው ይህንንም በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በመክፈት ሊታረቅ ይቻላል። ሁለተኛ የቋንቋውን የአገልግሎት ደረጃ ለማስፋት የቋንቋ ትምህርት ስያሜ ቃላቶችን ማካተት። የቋንቋ ትምህርት ስያሜ ቃላት የሚባሉት በአጠቃላይ በቋንቋ ጥናት ትምህርትና ምርምር ሂደት እንደ ሞያዊ ቃላት የምንጠቀምባቸው የቋንቋ ሞያዊ ቃላት ናቸው። እነዚህም የቃላት (የንግግር) ክፍሎች ለምሳሌ፡- ስም፡ ቅጽል፡ ግስ፡ ተውሳከ ግስ እና መስተዋድድ፤ ስለ ጽሑፍ ቋንቋ ስንናገር መሰረታዊ ከሚባሉ ሞያዊ ስያሜዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው። የሥርዓተ ጽሕፈት ስያሜዎች፡ ሆሄ፣ ተነባቢዎች፣ አናባቢዎች፣ ቀለም፣ወዘተ…፤ lሥነምዕላዳዊ ስያሜዎች፡ መዕላድ (ነጻና ጥገኛ)፣የቃላት እርባታ፣ የቃላት ምስረታ፣ ድግግሞሽ (ደጋሚ ድምጽ)፣ ወዘተ፤ ለሰዋስዋዊ አገልግሎት የሚውሉ ስያሜዎች፡ ባለቤት፣ ተሳቢ (ቀጥተኛ ፣ኢቀጥተኛ)፣ ማሰርያ አንቀጽ፣ ወዘተ…፡ የሥነ-ጽሑፍ ስያሜዎች፡ ጽሑፍ፣አንቀጽ፣ መስመር፣ አርዕስት፣ ርዕስ፣ ንዑስ ርዕስ፣ ወዘተ...፤ የስርዓተ ነጥብ ስያሜዎች፡ ነጠላ ሰረዝ፣ ነቁጥ፣ ድርብ ሰረዝ፣ ጥያቄ ምልክት፣ ትምዕርተ አንክሮ፣ ወዘተ…፤ እኒህ ስያሜዎች ሥርዓተ

media and religion. Status

planning deals with the allocation

of functional domains for a

language in a given speech

community.

Corpus planning deals with

language development and

promotion. It involves the

analysis of the linguistic structure

and standardization. Corpus

planning is geared toward

establishing and developing

spelling norms, and sets

standards for grammar use and

for expanding the lexicon.

As mentioned, the first step after

planning is to establish a writing

system, that is, the creation of a

standard orthography. The

orthography should reflect the

phonological reality of the dialect

on which the standard is based.

Furthermore, it is necessary to

choose a standard dialect serving

as a written form and for setting

orthography rules, such as

capitalization and punctuation.

The orthography must be settled

before written materials are

published.

Modernization is concerned with

the expansion of the lexicon –

adding new vocabulary to the

language, either by coinage or

borrowing from other languages.

As knowledge and technology

progress, there is a constant need

for extending the vocabulary by

creating and expanding the

appropriate terminology for

commercial, professional, and

scientific domains. The

vocabulary should undergo

continuous expansion in a

controllable way, particularly in

the domain of education.

So, the essential components for

successful language development

are: a well-organized plan, a

standard orthography, a reliable

reference grammar, a

comprehensive monolingual

dictionary, a controlled and

continuous expansion of the

lexicon, sufficient reading

The first step in a successful language development program

is to have a well-defined plan.

photo

by

SIL

Eth

iop

ia

Page 10: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

8 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

materials, and adequate teacher

training manuals.

Some challenges In Ethiopia, at least 81 speech

varieties are estimated to exist.

Among these, some languages

such as Qimant and Zay, are

considered to be endangered

languages. According to Article

Five of the FDRE Constitution, all

Ethiopian languages enjoy equal

state recognition. In the

democratic education system,

every language has the right to be

taught in school. Mother tongue

education has received wide

acceptance in the different parts of

the country. According to current

information, the number of

languages used as media of

instruction is estimated to be about

45 (24 of them are from the

SNNPR). Encouraging as this is,

there are still some issues to be

addressed:

ጽህፈት በተቀረጸለት አዲስ ቋንቋ መዘጋጀት አለባቸው። ቀጣዩ ሥራ መሰረተ ትምህርት መሰጠት ካስፈለገ ይዘቱ እንደማንኛውም መሰረተ ትምህርት አጠቃላይ መሆን ይገባዋል። ስለዚህም፣ ሙያዊ የቃላት ስያሜ በየተውኛውም የኑሮ መስክ በወጉ ተይዞ ሊዘጋጅ ይገባል። ለምሳሌ፡- የሂሳብ ዕወቀት ስያሜዎች፣ የቴክኖሎጂ ዕወቀት ስያሜዎች፣ ለሁሉም የሳይንስ ዘርፍ ዕወቀት የሚውሉ ስያሜዎች፡ ለህክምና ሳይንስ፣ ለኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ለመሳሰሉ የሞያ መስኮች በቋንቋው ሙያዊ መድብለ ቃላት ሊዘጋጅላቸው ይገባል።

ከክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች በደረስን መረጃ መሰረት እና የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን በማመሳከር ለማረጋገጥ እንደተሞከረው በሃገራችን በእሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የልማት ጅምር ግዕዝና የምልክት ቋንቋን ጨምሮ፣ የውጭ ቋንቋዎችን ሳይጨምር 81 ያህል ቋንቋዎች እንድሚነገሩ ተረጋግጧል ከነዚህ ውስጥ ክማንትነይ (በአማራ ክልል)፤ ዛይ፣ ሆዜ፣ ሴዞ እና እንፌሎ (በኦሮሚያ ክልል)፤ ሙርሌና ኦንጎታ (በድቡብ ክልል) በመጥፉት አደጋ ላይ ያሉ ቋንቋዎች መሆናችውን የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ያሳያሉ። በጠቅላላ በሀገሪቱ የሚገኙ ቋንቋዎች በየክልሎቹ ነባር ብሔርሰቦች በሚከተለው መልኩ ተሰራጭተዋል። በትግራይ ክልል 3 ቋንቋዎች፤ ትግሪኛ፣ ኩናማና ሳሆ፤በአማራ ክልል 5 ቋንቋዎች፤ አማርኛ፣ ኽምጣንጛ፣ አውንጚ፣ አርጎባና ኦሮሚኛ፤ በእፋር ክልል 2 ቋንቋዎች፤ አፋር እና አርጎባ፤ በኦሮሚያ ክልል 5 ቋንቋዎች፤ ኦሮሚኛ እና ዛይ፤ ሱማሌ ክልል 1 ቋንቋ፤ ሱማልኛ፤ጋምቤላ ክልል 5 ቋንቋዎች፤ አኙዋክ፣ ኑዌር፣ መጀንግ፣ ኦፖና ኮሞ፤ ቤኒሻንጉል ክልል 5 ቋንቋዎች፤ ሺናሻ፣ በርታ፣ ኮሞ፣ ጉሙዝና ጓዋም ሲሆኑ በደቡብ ክልል 55 ቋንቋዎች ይነገራሉ እነርሱም፤ ሃላባኛ፣ ሀመርኛ፣ ሃዲይኛ፣መኤኒትኛ፣ መዠንገርኛ፣ ሙሩልኛ፣ ሙርስኛ፣ ማልኛ፣ ማረቆኛ (ሊብዶ)፣ ማሾሌኛ፣

Mother tongue education has received wide acceptance in many areas of Ethiopia.

ph

oto

by

SIL

Eth

iop

ia

Page 11: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 9

A number of languages are

benefiting from language

development activities some-

how, but these activities are not

well coordinated;

Churches, for evangelistic

purposes, are involved in lang-

uage development activities, but

they are not working together

with government institutions in

their respective areas.

Research and educational

institutions, as well as NGOs, do

not discharge their responsibili-

ties according to the needs of the

regions they work in.

Some NGOs are involved in

language development activities

without permission.

Language development activities

are carried out by different

parties in the same linguistic

area; often there is no coordi-

nation, even within the same

region.

To solve these problems, all

stakeholders need to take

necessary measures. Generally, a

lack of systematic coordination is

the major challenge as far as

language development in Ethiopia

is concerned. Hence, all stake-

holders have to combine their

available resources and efforts,

share their experience, and work

together for their common goals.

It must be clear who is doing each

assigned task. Working together as

a team will help to overcome these

challenges.

Alemayehu Getachew

Senior Language Expert

Ministry of Culture and Tourism

ሞስይኛ፣ ሱርምኛ፣ ሲዳምኛ፣ ስልጥኛ፣ ሸክችኛ፣ ሸክኛ፣ ቀቤንኛ፣ በንኛ፣

አለኛ፣ አሪኛ፣ አርቦርኛ፣ ኦንጎታኛ፣ ኦይዳኛ፣ ከምባትኛ፣ ኩሱሚኛ፣ ኩዌጉኛ፣ ካሮኛ፣ ካፊኖኖ፣ ኮረትኛ፣ ኮንሶኛ፣ ኮንትኛ፣ ዎላይትኛ፣ ዛይስኛ፣ ዝልማምኛ፣ የምኛ(የምሳ)፣ ዲምኛ፣ ዲራሽኛ፣ ዲዚኛ፣ ዳሰነችኛ፣ ዳውሮኛ፣ ጉራግኛ፣ ጋሞኛ፣ ጌድኦኛ፣ ግድችኛ፣ ጎፋኛ፣ ጠንባሮኛ፣ ጫራኛ እና ፀመይኛ ናቸው።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 5 እና 39 “ማንኛውም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በእኩልነት የመንግስት እውቅና ይኖራቸዋል።” እና “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔርሰብ፣ ሕዝብ በቋንቋው የመናገር፣ የመጻፍ፣ ቋንቋውን የማሳደግ እና ባሕሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው።” ይላል በዚህ መሰረት ሁሉም ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ይህንኑ መሰረታዊ የሕገ መንግስት ፅንሰ ሀሳብ በማካተት በየክልሎቻቸው ለሚገኙ ቋንቋዎች የልማት ስራ ሰርተዋል። ከነዚህ መካከል

ትግራይ ክልል በክልሉ የሚገኙትን 3 (ሶስት) ቋንቋዎች

አማራ ክልል በክልሉ ከሚገኙት 3 (ሶስት) ቋንቋዎች

ኦሮሚያ ክልል በክልሉ ከሚገኙት 1 (አንድ) ቋንቋ

ሱማሌ ክልል በክልሉ የሚገኘውን 1 (አንድ) ቋንቋ

ሐረሪ ክልል በክልሉ የሚገኘውን 1 (አንድ) ቋንቋ

ቤኒሻንጉል ክልል በክልሉ ከሚገኙት 5 (አምስት) ቋንቋዎች

ጋምቤላ ክልል በክልሉ በሚገኙት 5 (አምስት) ቋንቋዎች

ደቡብ ክልል በክልሉ ከሚገኙት 24 (ሃያ አራት) ያህል ቋንቋዎች

አፋር ክልል በክልሉ በሚገኙት 2 (ሁለት) ቋንቋዎች

በጠቅላላው በሀግሪቱ ግዕዝና የምልክት ቋንቋን ጨምሮ በአርባ አምስት በሚያክሉ (45) ቋንቋዎች ሥርዓተ -ጽህፈት ተቀርጸላቸው ወደ ትምህርት ሥርዓቱ ገብተዋል። ይህም በመቶኛ ሲሰላ በሀገሪቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ 53% ቋንቋዎች ወደ ትምህርት ሥርአቱ ገብተዋል።

ባልፉት ዓምታት በርካታ ቋንቋዎች የልማት ትሩፋት ተቋዳሽ ቢሆኑም ልማቱ በተቀነጀ መልክ አለመምራቱ እንደ ችግር ተዳሷል፤

አብያት ክርስቲያናት ለወንጌል ስርጭት ሲሉ በልማት ስራ ውስጥ ቢገቡም ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በቅንጅት ሥራውን አለማከናወናቸው እንደ ችግር ተቃኝቷል፤

የሚመለከታቸው የምርምር እና የትምህርት ተቋማት እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ግብረሰናይ ድርጅቶች የምርምር ስራዎቻቸው የክልሎችን ወቅታዊ ፍላጎት ባማከለ ምልኩ የመስራት ልማድ አልዳበረም፤

በቋንቋ ልማት ፈቃድ ያላገኙ ግብረ ስናይ ድርጅቶች በዚህ መስክ መሳተፋቸው ተገምግሟል።

የቋንቋው ልማት እንደ ክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታዎች በተለያየ አካላት መምራቱ፤ በሌላ በኩል በክልል ደረጃ እንኳን ቅንጅታዊ አስራር በውጉ አለመዘርጋቱ በሀገራችን የቋንቋ ልማት ሂደት የታዩ ክፍተቶች ናቸው።

ከላይ የተጠቀሱትን የቅንጅታዊ አሰራር ክፍተቶች ለማረቅ እና መስኩን በተሸለና ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ለማልማት እና ሕብረተሰቡም በቋንቋዎቹ መልማት የሚጎናጸፋቸውን ትሩፋቶች ለማበራከተ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሁልም ባለድርሻ አካላት ሊወስዱ ግድ ይላል። (ታህሳስ ፳፻፭ ቸርችል ሆቴል)

Page 12: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

10 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Aija Katriina Ahlberg

W hat good is it for our children to learn in

our own language? How will they be

different from us, since we didn’t go to

school? These used to be common questions amongst

parents who hadn’t gone to school themselves. In

people’s minds, being educated meant being able to

use languages other than the local vernacular.

This attitude is gradually changing. More and more

people understand that education is not only about

learning languages. It also requires a variety of other

skills and knowledge, and these are more easily

acquired in a language one already knows.

So far so good. But what about the reasons for

learning the mother tongue as a subject? It seems

obvious that using the mother tongue as the language

Mother Tongue as a Subject Why Learn a Language You Already Know?

ል ጆቻችንን በራሳቸው ቋንቋ እንዲማሩ የማድረግ ጥቅሙ ምንድን ነው? በምናውቀው ቋንቋ ተማሩ የሚባሉት ልጆቻችንስ ከኛ ትምህርት

ቤት ካልገባነው ሰዎች በምን ሊለዩ ይችላሉ? እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ በተለይ የትምህርት ቤት ደጃፍን የመርገጥ እድል ያላገኙ የብዙ ወላጆች ጥያቄ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ “የተማረ ሰው” የሚባለው በአካባቢያቸው ከሚነገረው ቋንቋ ይልቅ የውጪ ያለ ቋንቋ የሚናገር ነው የሚል እምነት ስር ሰዶ መቆየቱ ነው። ይሁንና አሁን ትምህርት ማለት ቋንቋን ማወቅ ብቻ እንዳልሆነና ማንኛውንም ትምህርት ተምሮ የሚፈለገውን እውቀት ለማግኘት ልዩ ልዩ ግብአቶችና እውቀቶች እንደሚያስፈልጉ ብዙዎች እየተገነዘቡ መተዋል። በመሆኑም እንዲህ ዓይነቱ አመለካከት ከቀን ወደ ቀን እየተቀየረ ሄዷል። ከዚህ ባሻገር እነዚህ ግብአቶች ደግሞ

የአፍ መፍቻ ቋንቋ - እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ለመሆኑ አፍ የፈታንበትን ቋንቋ ትምህርት ቤት ገብተን ለምን እንማረዋለን?

Eager Sheko students in the mother tongue pilot class at Gayzika Primary School in the Bench-Maji Zone

ph

oto

by

Aij

a K

atr

iin

a A

hlb

erg

10 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Page 13: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 11

ተማሪው አስቀድሞ በሚያውቀው የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚቀርቡ ከሆነ ከተማሪው ጋር በቀላሉ ሊዋሃዱ እንደሚችሉ ግንዛቤ እየዳበረ መጥቷል።

ለመንደርደሪያ ይህን ያህል ካልን “የአፍ መፍቻ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት መማር ለምን ያስፈልጋል?” የሚለውን ጥያቄ እናንሳ። በርግጥ የትምህርት መስጫ ቋንቋው የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሆነ እንደሆነ ያ ቋንቋ በክፍል ውስጥ ከሚሰጡት የትምህርት ዓይነቶች እንደ አንዱ ሆኖ ሊሰጥ እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ስለዚህም የተማሪው የየቀን መርሃ ግብር ይሆናል። የመጽሀፍትና የስርዓተ ትምህርት አዘጋጆች ግን ከዚህ በላይ በጥልቀት የሚያስቡበት ጉዳይ ነው።

በመጀመሪያዎቹ የክፍል ደረጃዎች ውስጥ የአፍ መፍቻ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት የማስተማር ዓላማና ጥቅሙ የሚያከራክር አይደለም። ምክንያቱም አንድ ተማሪ በቋንቋው የሚጻፈውን ሃሳብ በቀላሉ አንብቦ ለመረዳት እንዲችል በዚያ ቋንቋ እንዴት ማንበብና መጻፍ እንዳለበት መማር ስለሚገባው ነው።

በቤንች ማጂ ዞን* በአራት ቋንቋዎች የአፍ መፍቻ የሙከራ ትምህርት ስንጀምር ሁላችንም ህፃናቱ 1ኛ ክፍል ሲጨርሱ በቋንቋቸው ማንበብና መጻፍ የመቻላቸው ጉዳይ አስግቶን ነበር። እንደተፈራውም አንደኛ ክፍልን ካጠናቀቁት ልጆች ጥቂቶቹ ብቻ ነበሩ ማንበብና መጻፍ የቻሉት። እውነቱ ይሄ ቢሆንም “ለምን እንዲህ ሆነ?” ብሎ መጠየቅ ደግሞ አግባብ ነው። ለዚህ ምክንያቶቹ ብዙ ነበሩ። የመጀመሪያው ምክንያት በልጆቹ ችሎታ ላይ

እምነት የነበራቸው ጥቂቶች ብቻ መሆናቸው ነበር። ሁለተኛው ትልቁ መሰናክል ደግሞ ቀደም ሲል የንባብ ልምምድ ሲደረግበት የቆየው በአማርኛ በተጻፉ ጽሁፎች መሆኑ ነበር። እንደሚታወቀው የአማርኛ ፊደላት ቀለማዊ (syllabic) በመሆናቸው አነባበቡም ቀለማቱን ተከከትሎ የሚከናወን ነው። ባንጻሩ ደግሞ የላቲኑ አጻጻፍ ከቀለማዊ አጻጻፍ የተለየ አቀራረብን ይጠይቅ ነበር። ስለዚህ ከተለመደው ቀለማዊ የአነባበብ ስርአት ወጥቶ ልጆችን በላቲን ፊደላት ማለማመድ ለመምህራን ትልቅ ፈተና

ነበር። በተለይ ደግሞ ተነባቢዎችን ልዩ ልዩ አናባቢዎች ሲከተሏቸው የሚያመጡትን የንበት ልዩነት ለማስለየት መምህራኑ የሚገጥማቸው ተግዳሮት ቀላል አልነበረም። ይሁንና መምህራኑ በማስተማር ልምድ እያገኙ በሄዱ ቁጥር በቤንች ማጂ የነበሩት አንዳንድ እንቅፋቶች ደረጃ በደረጃ እተቀረፉ ሄደዋል። በመሆኑም አሁን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አቀላጥፈው የሚያነቡ ልጆች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ሆኖም አሁንም ቢሆን በገጠሩ አካባቢ ያሉ

of instruction should also include teaching the mother

tongue as such; thus it should be part of the students’

daily schedule. Yet textbook writers and curriculum

developers need to go deeper than that.

The learning goals for mother tongue

as a subject in the early grades are

undisputable: in order to study in a

particular language, one needs to know

how to read and write that language.

When the mother tongue medium pilot

classes in four languages commenced

in the Bench-Maji Zone,* we were

surprised to discover that hardly

anyone took seriously the idea of

teaching children to read by the end of

grade one. Alas, very few first grade graduates did

learn to read. Why? There was a myriad of reasons,

one of them being that very few believed in the

students’ ability. Another big stumbling block was that

reading had always been taught using the Amharic

script, which is close to a syllabic writing system.

Therefore, the teaching of reading in languages using a

Latin script requires a very different approach. The

teachers found it especially difficult to teach how the

consonants’ sounds vary when followed by different

vowels. Some of that stumbling block is gradually

being removed in Bench-Maji as teachers gain

experience, and there now is a growing number of

fluent mother tongue readers. Still, a lot remains to be

done countrywide in supporting the present generation

of teachers to learn well the methodology of teaching

reading and writing in languages that

use a Latin script.

When moving on to grade two, many

children are still practicing the

recognition of the sound-symbol

relationship. This is the cornerstone

for reading words and sentences and

starting to make sense of the meanings

in a text. Yet the quickest learners are

already getting into meaningful

reading, and need more advanced

fluency practice. The textbooks must

be designed to accommodate all learners. For grade

two in Bench-Maji, we decided to invest in stories.

The textbook writers had training in story writing from

professional authors of children’s literature. Then,

using the themes from the national syllabus, they

created stories that the children would enjoy reading.

When children enjoy the readings in their mother

tongue textbooks, they are more likely to practice

reading, and at the same time, develop an interest in

Textbooks must be

designed to

accommodate

all learners.

* A pilot program to use mother tongue as the medium of

instruction for primary cycle one in Bench Maji Zone started in

2004 Ethiopian Calendar (Sept 2011) in selected schools amongst

grade one students in Bench, Diizin, Me’en, and Sheko languages.

የመማሪያ መጻህፍት

ዝግጅት ሁሉንም

ዓይነት ተማሪዎች

ከግምት ውስጥ ያስገባ

ሊሆን ይገባል።

*ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትምህርት እንዲጀምሩ በቤንች ማጂ

በአንደኛ ደረጃ የመጀመሪያው እርከን ሙከራ ትምህርት በተመረጡ

ጥቂት የትምህርት ቤቶች ውስጥ በቤንች፣ በዲዚ፣ በመኤን እና በሸኮ

ቋንቋ በ2004 ዓ.ም ተጀመረ።

Page 14: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

12 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

reading. Alongside the stories, the grade two textbook

includes a lot of reading practice on word level, and a

variety of oral and writing exercises.

If not earlier, in grades three and four, children should

be able to move from learning to read into reading to

learn – that is, to read fluently enough to be able to

learn new information as they read. To offer practice

in this, the mother tongue subject textbook should

include a variety of genres and text types, and the

comprehension exercises should guide the student to

identify the text type and analyse the text. One

example of this is a problem/solution text where the

student is asked to identify the problem presented in

the text and then identify the solutions offered. In the

mother tongue textbooks in Bench-Maji, the third

grade book includes many types of texts: reports,

instructions, argumentative texts, letters, dialogues,

stories, and forms, etc. The fourth grade book divides

the texts into types according to their structure:

problem and solutions, cause and effect, sequence, and

description, etc.

Texts and comprehension exercises offer practice in

fluent reading. The other exercises help the children to

learn new vocabulary, to spell accurately, to express

one’s thoughts in speaking and in writing, and to

understand the grammar of the language i.e. its

structures and regularities.

Grammar is a fascinating feature of language. Every

mother tongue speaker knows how his/her language

expresses different concepts and recognizes when they

are not expressed correctly. Yet it will require learning

አዳዲስ መምህራን በላቲን የአጻጻፍ ስርአትና የማንበብ ስነ ዘዴ ዙሪያ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል።

ወደ ሁለተኛ ክፍል ስንሻገር ደግሞ በርካታ ልጆች አሁንም በድምጽና በወካዩ መካከል ያለውን ዝምድና ለመገንዘብ የሚያደርጉትን ብርቱ ልምምድና ጥረት እናገኛለን። ይህ ደግሞ ቃላትንና ዓረፍተ ነገሮችን ለማንበብ እንዲሁም በአውድ ውስጥ ሲገቡ ልዩ ልዩ ፍቺዎችን እንደሚሰጡ ለመገንዘብ የሚችሉበት ዋነኛ የማእዘን ድንጋይ ነው። ይህ የክፍል ደረጃ ውስጥ ፈጣን ተማሪዎች ከሌሎች ጓደኞቻቸው ቀደም ብለው ትርጉም ያለው ንባብ ሊያነቡ የሚችሉበት የክፍል ደረጃ ነው። በመሆኑም እንደነዚህ ዓይነት ፈጣን ልጆች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገንዘብ ልጆቹ የንባብ ቅልጥፍናቸውን የሚያጎለብቱበት በሰል ያሉ መለማመጃዎችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው። ስለዚህ የመማሪያ መጻህፍት ዝግጅት ሁሉንም ዓይነት ተማሪዎች ከግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ይገባል። እኛም ከዚህ ሃሳብ በመነሳት በቤንች ማጂ ዞን ላሉ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ ልዩ ታሪኮችን የያዙ የህጻናት መጻህፍት ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ተገንዝበናል። እናም እነዚህን የፈጠራ ጽሁፎች የሚያዘጋጁ መጻህፍት አዘጋጆች መረጥን፤ ከዚያም የህጻናት የንባብ መጻህፍት በሚጽፉ ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች አማካኝነት ስልጠና እንዲወስዱ አደረግን። በመጨረሻም በአገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀውን መርሃ ትምህርት መሰረት አድርገው ልጆች እያነበቡ የሚዝናኑባቸውን ታሪኮች የሚጽፉበት ሁኔታ ተመቻችቷል። ከታሪኮቹ ጋር በተያያዘም በሁለተኛ ክፍል መማሪያ መጻህፍት በቃላት ደረጃ፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ያቃልና የጽህፈት መለማመጃዎች ተካተዋል። ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የተጻፉ አስደሳች ታሪኮችን በሚያነቡበት ጊዜ የንባብ ልምምዳቸውን ያዳብራሉ፤ እግረመንገዳቸውንም የማንበብ ፍላጎታቸውን ያጎለብታሉ።

የሶስተኛ እና የአራተኛ ክፍል ደረጃዎችን ስንመለከት ደግሞ በእነዚህ የክፍል ደረጃዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በጣም ቸኮሉ ካልተባለ በስተቀር ንባብን ከመልመድ አልፈው በንባብ አማካኝነት ሌሎች መረጃዎችን ተቀብለው ለመማሪያ የሚገለገሉበት የክፍል ደረጃ የደረሱ ናቸው። ማለትም ልጆቹ በቅልጥፍና ማንበብ ከመቻላቸውም ባሻገር እያነበቡ ሌሎች አዳዲስ መረጃዎችን ሊያገኙ ይችላሉ ማለት ነው። በዚህ ረገድ እንዲህ ዓይነቱን ልምምድ ለማዳበር በተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት ውስጥ ልዩ ልዩ ዓይነት ዘውግ ያላቸው ጽሁፎች ማካተት ይገባል። ከሚቀርቡ ምንባቦች የሚወጡ ጥያቄዎችን በማዘጋጀትም ተማሪዎች የጽሁፉን አይነት አንዲረዱና እንዲያገናዝቡ ማድረግ ይገባል። ለምሳሌ ችግሮችና መፍትሄዎችን የያዙ ጽሁፎችን በማዘጋጀት ተማሪዎች አስቀድመው ችግሩን እንዲለዩ ማድረግ፤ ቀጥለው ደግሞ መፍትሄውን ከጽሁፉ ውስጥ እንዲፈልጉ ማድረግ ይቻላል። በቤንች ማጂ የ3ኛ ክፍል የተማሪው መማሪያ መጽሃፍ ውስጥ አከራካሪ ጽሁፎች፣ ደብዳቤዎች፣ ምልልስ፣ የፈጠራ ጽሁፎች (ታሪኮች) ና የመሳሰሉ በርካታ የጽሁፍ ዓይነቶች እንደቀረቡ ልብ ይሏል።

የአራተኛ ክፍል መማሪያ መጽሃፍ ደግሞ ጽሁፎችን በአወቃቀራቸው መሰረት ከፋፍሎ ይዟል፤ ለምሳሌ ችግሮችና መፍትሔዎች፣ ምክንያትና ውጤት፣ ቅደም Mother tongue students at the primary school

in the village of Boyta

ph

oto

by

Aij

a K

atr

iin

a A

hlb

erg

Page 15: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 13

to bring this knowledge into a conscious level, and to

learn the rules that must be followed when writing.

The role of teaching grammar in mother tongue

lessons is somewhat controversial. How important is it

to bring the grammar rules into a conscious level?

What is that knowledge useful for? In spoken

language we don’t always use grammar rules

correctly, and yet the listener normally understands

the message. But if we ignore grammar rules when

writing, it can be difficult for a reader to grasp our

meaning. Learning the standard way of writing a

language, including the grammar rules, will ensure

that readers understand our intended message.

In many regions of Ethiopia, the mother tongue is

used as the language of education only up to grade

four or six. Also, apart from the Amhara region,

students have a need to learn Amharic as a second

language. It is beneficial to learn grammar rules such

as word classes (nouns, verbs, adjectives, etc.),

inflection of verbs, and plural marking in one’s own

language first. This is of great help

when students learn how to express

grammar concepts in another

language. Therefore, the earlier they

need to begin studying other subjects

in a new language, the earlier they also

need to understand and apply grammar

rules–first in the mother tongue and

then in the new language.

Yet, knowing grammar rules in one’s

own language does not automatically

help learning another language.

Teachers must help their students

make the link between the two. For

example, children whose mother

tongue is Amharic will understand the

difference between I eat injera and I

am eating injera, if the teacher helps

them to think through and discover first the difference

between እንጀራ እበላለሁ and እንጀራ እየበላሁ ነው. And,

although strictly speaking, the range of English

present simple and present continuous are not exactly

the same as the Amharic expressions, they are close

enough for students to greatly benefit from comparing

the English expressions with their mother tongue.

Therefore it would be helpful if the curriculum and

teaching materials for mother tongue and for second

language(s) considered this linking concept. There

must be a horizontal relationship between language

subjects, in order to make use of the support that

mother tongue as a subject, when taught at its best,

can give to learning other languages.

So, why learn a language you already know? Learning

the mother tongue as a subject at school enables

students to understand their own language more

deeply, and to express themselves better, both orally

ተከተልን ማስተካከል፣ ገላጭ ጽሁፎችን …ወዘተ የመሳሰሉ ጽሁፎችን አካቷል። በመማሪያ መጻህፉ ውስጥ የቀረቡት ምንባቦችና ከምንባቡ የወጡ ጥያቄዎችም ልጆች አቀላጥፈው የማንበብ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩ ያግዟቸዋል። ሌሎቹ መለማመጃዎች ደግሞ ልጆች አዳዲስ ቃላት እንዲያውቁና ባግባቡ እንዲያነቧቸው እድል ይፈጥሩላቸዋል። ሃሳባቸውንም በንግግርና በጽሁፍ የሚገልጹበትን እድል ያመቻቻሉ። የቋንቋውንም ሰዋሰው (አወቃቀርና ስርዓት) የሚማሩበት አጋጣሚ ይኖራቸዋል።

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ማንኛውም ሰው አንድ ሃሳብ በቋንቋው እንዴት እንደሚገለጽ ያውቃል። ያም ብቻ አይደለም ሃሳቦች በተገቢው መንገድ ሳይገለጹ ከቀሩም ወዲያውኑ መለየት ይችላል። ትምህርት ደግሞ እንደነዚህ ያሉ በልማድ የተገኙ እውቀቶች እንዲዳብሩ በማድረግ እያንዳንዷን የቋንቋ አጠቃቀም በተመለከተ በጥንቃቄ ማስተዋል ወደሚቻልበት ደረጃ ያሳድጋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም አንድን ሁኔታ ባግባቡ የመግለጽና የመጻፍ ችሎታ ደረጃውን(ጊዜውን) ጠብቆ እንዲመጣ ያደርጋል።

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ የቋንቋውን ስርአት(ሰዋሰው) ን የማስተማር ሚናን በተመለከተ

አወዛጋቢ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ። ከአስተያየቶቹ መካከል “የሰዋሰው ህጎችን በማስተማር ተማሪዎች የቋንቋውን ህግ እንዲያስተውሉ ማድረግ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? ዕውቀቱስ ለምን ይጠቅማል?” የሚል ነው። በርግጥ በንግግር ወቅት አድማጫችን የሚፈልገው የሚተላለፈውን መልክእክት ወይም ሃሳብ ብቻ በመሆኑ ንግግራችን የቋንቋውን ሰዋሰው መጠበቁ የግድ ላይሆን ይችላል። ይሁንና በምንጽፍበት ጊዜ ሰዋሰውን ችላ የምንል ከሆነ ግን አንባቢያችን ምን ዓይነት ሃሳብ ለማስተላለፍ እንደፈለግን ባግባቡ ላይረዳ ይችላል። የቋንቋውን ህግና ስርአት ጠብቀን የምንጽፍ ከሆነ ግን አንባቢያችን ልናስተላልፍ የፈለግነውን ሃሳብ በቀላሉ ይረዳልናል።

በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ እስከ 4ኛ ወይም እስከ 6ኛ ክፍል ባሉት የትምህርት ደረጃዎች ውስጥ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማሪያ ቋንቋ ሆኖ ያገለግላል። በሌላ በኩል ደግሞ ከአማራ ክልልና ከአዲስ አበባና ከአንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር በሌሎቹ ክልሎች ያሉ ተማሪዎች አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይማሩታል። በዚህ ረገድ ሰዋሰው (ስም፣ግስ፣ገላጭን… ወዘተ)፣ የቃላት አረባብ፣ የአብዢ ቅጥያዎችን) ወዘተ አስቀድሞ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መለማመድ የሁለተኛ ቋንቋውን ሰዋሰው ለመረዳት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። በመሆኑም ተማሪዎች ገና በልጅነታቸው በአዲስ ቋንቋ ትምህርታቸውን እንዲማሩ የሚፈለግ ከሆነ በቋንቋው በሚገባ መገልገል እንዲችሉ አስቀድመው የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን የቋንቋ ስርዓት(ሰዋሰው) በመቀጠል ደግሞ የአዲሱን ቋንቋ ሰዋሰው ቀደም ብለው መማራቸው የግድ ይሆናል።

ይሁንና አንድ ሰው የአፍ መፍቻ ቋንቋውን ሰዋሰው አወቀ ማለት ወዲያው ሌላ ቋንቋ ይለምዳል ማለት አይደለም። በዚህ ረገድ መምህራን የአፍ መፍቻ ቋንቋን ሰዋሰው

Learning the mother

tongue as a subject

enables students to

understand their

own language more

deeply, and to

express themselves

better, both orally

and in writing.

Page 16: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

14 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

and in writing. It is also a useful tool in learning

other languages, as students learn skills for

comparing these other languages with their own.

And finally, it must be acknowledged that, in the

case of languages that are still in their early stages of

writing, mother tongue teaching in schools serves the

development of the language. If children learn to

write according to the standard writing system that is

established, the mere practice of reading and writing

will strengthen the spelling conventions. It will also

gradually give the language community an avenue of

further developing the written expression. However,

the school should not be left alone in this historical

task. There should be additional language develop-

ment activities outside the schools: collecting oral

literature and putting it into writing; creating new

literature in the language; and storing the unique

treasures of indigenous knowledge. Mother tongue

teaching in schools, when at its best, can strengthen

that knowledge by passing it on to the students. But

it is not solely the task of the school community to

keep a language alive. It will take the efforts of an

entire society.

Aija Katriina Ahlberg

Literacy Advisor

SIL Ethiopia

በማወቅ የሁለተኛ ቋንቋን ለመልመድ እንዴት ሊያግዝ እንደሚችል ልዩ ልዩ አብነቶችን በማንሳት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። ለምሳሌ አንድ የአፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ የሆነ ልጅ “እንጀራ እበላለሁ” እና “እንጀራ እየበላሁ ነው” በሚሉት ሁለት ሃሳቦች መካከል ያለውን ልዩነት ይረዳል። መምህሩም የእነዚህን ሁለት ሃሳቦች ልዩነት ልጆቹ መረዳታቸውን ካረጋገጠ በኋላ ከእንግሊዝኛው የአሁን ጊዜ (Present simple) እና የህዋላ ሃላፊ ጊዜ (present continuous) ጋር ያላቸውን የሃሳብ መመሳሰል እያወዳደሩ እንዲረዱ ሊረዷቸው ይገባል። በሁለቱ ቋንቋዎች የተገለጹት ሃሳቦች ቁርጥ አንድ ባይሆንም በጣም ተቀራራቢ በመሆናቸው ተማሪዎች ሁለቱን ቋንቋዎች በማወዳደር የሚያደርጉት ተግባር ቋንቋን በመልመድ ተጠቃሚዎች ያደርጋቸዋል። በመሆኑም የቋንቋ ስርዓተ ትምህርቶችም ሆነ የሚዘጋጁ መጻህፍት በአፍ መፍቻ ቋንቋ እና በሁለተኛ ቋንቋ መካከል ያለውን ግንኙነት ያገናዘቡ ቢሆኑ በጣም ጠቃሚ ነው።

የአፍ መፍቻ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት አይነት በሚገባ (በጥሩ ሁኔታ) ስናስተምር ሌሎች ቋንቋዎችንም በቀላሉ ለመልመድ እድል ስለሚፈጥር(ስለሚያመቻች) በቋንቋ ትምህርቶች መካከል ጎናዊ ዝምድና ሊኖር ይገባል።

አሁን “የምናውቀውን ቋንቋ ለምን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንማረዋለን?” ለሚለው ጥያቄ ተገቢ መልስ ማግኘት እንችላለን። የመጀመሪያው ቁም ነገር ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን በትምህርት ቤት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ሲማሩት ቋንቋቸውን በጥልቀት የሚያረዱበት አጋጣሚ መፈጠሩ ነው። በሌላ በኩል ተማሪዎች ራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ በቃልና በጽሁፍ መግለጽ እንዲችሉ ያደርጋል። ከዚህ ባሻገር ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ስርዓት ከሌሎች ቋንቋዎች ህጎች ጋር የሚያነጻጽሩበት ክሂል ሌሎች ቋንቋዎችን ለመልመድ የሚያግዝ ጠቃሚ መሳሪያ ሆኖ ማገልገሉ ነው። በመጨረሻም ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መጻፍ ከሚጀምሩበት ጊዜ ጀምሮ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርትን በትምህርት ቤት የማስተማር ተግባር ለቋንቋ ልማት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው እውቅና ሊሰጠው ይገባል። ልጆች መደበኛውን ስርዓተ ጽህፈት አንድ ጊዜ ከተማሩ በኋላ በቀጣይ የሚያከናውኑት የንባብና የጽህፈት ልምምድ ስርአተ ሆሄን (ስፔሊንግ)ን አጣርቶ ለማወቅ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያጠናክር ይሆናል። ይህ ደግሞ የቋንቋው ማህበረሰብ ሃሳቡን በጽሁፍ የሚገልጽበትን መንገድ እያጠናከረው ይመጣል። ይሁንና እንዲህ ዓይነቱ ታሪካዊ ሃላፊነት ለትምህርት ቤቶች ብቻ የሚተው አይደለም። ከትምህርት ቤት ውጭም የቋንቋ ልማቱን የሚያጠናክሩ ልዩ ልዩ ተግባራት ሊከናወኑ ይገባል። ለምሳሌ ስነቃሎችን መሰብሰብና በጽሁፍ መልክ ማኖር፣የፈጠራ ጽሁፎችን በቋንቋው ማዘጋጀት፤ ለየት ያሉ አገር በቀል እውቀቶችን መዝግቦ ማቆየትና የመሳሰሉትን ተግባራት ማከናወን ይገባል። ተማሪዎች በተገቢው ጊዜ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን በትምህርት ቤት የሚማሩ ከሆነ በቋንቋው አማካኝነት የሚተላለፉትን ዕውቀቶች በሚገባ እንዲረዷቸው ያደርጋል። ይሁንና ቋንቋውን ህያው እድርጎ የማቆየት ሃላፊነት የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ብቻ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፤ ይልቁንም የመላው ማህበረሰብ ተሳትፎን የሚጠይቅ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

photo

by

SIL

Eth

iop

ia

What did you learn today?

Page 17: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 15

Michael Bryant

T he annual International Mother Tongue Language Day (IMLD)

celebrates language diversity, variety and multilingualism world-

wide every February 21. It was created by UNESCO fifteen years

ago, to promote the dissemination of mother tongues and a fuller

awareness of linguistic and cultural traditions throughout the world.

UN Secretary-General, Ban Ki-Moon said:

IMLD celebrates linguistic and cultural diversity alongside

multilingualism as a force for peace and sustainable development...

This diversity can encourage dialogue, mutual understanding, inno-

vation and creativity. As the late President Nelson Mandela once

said, “If you talk to a man in a language he understands, that goes

to his head. If you talk to him in his language, that goes to his heart.”

The Ministry of Culture and Tourism hosted the event in 2014, celebrated

at the Sidama Cultural Center in Hawassa, under the theme Mother Lang-

uages, Our Historical Identity. We arrived just in time to enjoy the

parade of several choirs of school children with a marching band and

ዓ ለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን (IMLD) የቋንቋ ብዝሃነትንና፣ ልዩነትን እንዲሁም ልሳነ-ብዙነትን

የሚያከብር ሲሆን መከበር የጀመረው ከዛሬ አስራ አምስት አመት በፊት እኤአ የካቲት 21 ቀን በዩኔስኮ (UNESCO) ውሳኔ መሰረት ነው። ዓላማውም በአለም ዙሪያ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች እንዲጎለብቱ ቅስቀሳ ማድረግ፣ የሥነልሳንን ባህላዊ ልማዶች ግንዛቤ እንዲጨምር ማድረግና ቋንቋዎች ሁሉ እኩል እንደሆኑና ሊጎለብቱ እንደሚገባ ማብሰርና ስልት መቀየስ ነው።

በአንድ ወቅት የተባበሩት መንግስታት ሴክሬተሪ ጀነራል ባን ኪ-ሙን የሚከተለውን ተናግረው ነበር፤

Mother Tongue International

Language Day

ዓለም አቀፍ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን

photo

by

SIL

Eth

iop

ia

Page 18: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

16 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

many people carrying banners that

announced the celebration. It

seemed that everyone in Hawassa

was excited about the event.

The first day’s program highlighted

the country’s cultural diversity

through an array of artistic perfor-

mances: readings of poetry and

other original compositions in the

mother tongue; songs and cultural

dances from a variety of people

groups; and several dramas pre-

sented by actors from the National

Theatre in Addis Ababa, focusing

on the advantages of using the

mother tongue in education.

Several organizations, including SIL

Ethiopia and the National Archives,

were given spaces for displaying a

variety of printed materials in the mother tongue. These displays were

visited by the dignitaries, including His Excellency Ato Mulugeta Seid

the State Minister of Culture and Tourism, Her Excellency Wizero Hiwot

Hailu, South Nation Nationalities and Peoples’ State Council Speaker,

and His Excellency Amin Abdulkadir, the Minister of Culture and

Tourism, pictured below.

His Excellency Amin Abdulkadir said promoting and preserving mother

tongue languages would be a comprehensive solution to preserving the

country’s social, cultural and historical assets. He further stated that over

30 mother tongue languages in Ethiopia are already being used as a

medium of instruction in primary schools across the country, adding that

the Ministry has a mandate to preserve the multicultural and historical

assets of the people by studying and promoting their languages.

Weyzero Hiwot Hailu added, “Learning in vernacular languages is instru-

mental to delivering quality education. Since the right to education in mother

“በዓለም አቀፉ የአፍ መፍቻ ቀን የሥነልሳንና፣ የባህል ብዝሃነት ከልሳነ ብዙነት ጋር ሲከበር ሰላምና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ አንድ ሃይል ነው። ይህ ብዝሃነት መግባባትን፣ የጋራ ስምምነትን እና አዳዲስ ግኝቶችን ያበረታታል።” በሞት የተለዩን ኒልሰን ማንዴላም ይህንን ብለው ነበር “አንድን ሰው በማንኛውም ቋንቋ ብትነግረው የነገርከው ነገር ጭንቅላቱ ላይ ይቀራል፤ በራሱ ቋንቋ ብትነግረው ግን ንግግርህ ወደ ልቡ ይዘልቃል”።

እንደሌላ ጊዜ ሁሉ በለፈው ዓመት አለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀንን ያስተናገደው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነው። ወደ በዓሉ የታደምነው ቀደም ብለን ነበር። የበአሉን አከባበር የሚዘክር መዝሙር የሚዘምሩ ህጻናቶችና ልዩ ልዩ ባነሮች በአሉን አድምቀውት ነበር። የበአሉ ታዳሚዎች በሙሉ ሃዋሳ በነበረው አከባበር ደስተኞች ሆነው ታይተዋል።

የመጀመሪያው ቀን ፕሮግራም ትኩረት የሀገሪቱን የባህል ብዝሃነት በልዩ ልዩ ኪነጥበባዊ እንቅስቃሴዎች በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ሲሆን ግጥሞች እንዲሁም በአፍመፍቻ ቋንቋ የተደረሱ ወጥ ድረሰቶች ቀርበዋል። ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመጡ የባህል ቡድኖችም ልዩ ልዩ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና ዘፈኖች እድምተኛውን ከመዝናናታችውም ሌላ፤ ከአዲስ አበባ ብሄራዊ ቲያትር በመጡ ተዋንያኖች አማካኝነት ትምህርትን በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር በሚሰጠው ጥቅም ላይ ያተኮሩ በርካታ ድራማዎች ቀርበዋል።

photo

by

SIL

Eth

iop

ia

ph

oto

by

SIL

Eth

iop

ia

Page 19: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 17

tongue languages is granted in the

Ethiopian constitution, all stake-

holders should be working closely

for the promotion and development

of mother tongue languages, thereby

preserving their history and culture.”

The program on the second day

included a forum for discussion on

various academic topics. Along

with my colleague Ato Mesfin

Derash, the Multilingual Education

Coordinator of SIL Ethiopia, we

gave a presentation on The Strengths

& Challenges of Sustainable

Language Development in

Ethiopia, which is briefly

summarized on the next page.

There were also presentations by

Professor Baye Yiman and Dr.

Moges Yigezu from Addis Ababa

University. Another notable

presentation was by Dr. Fiqde

Minuta from Hawassa University,

who shared statistics on the status

of development of all the

languages in the SNNPR.

Summary: Recommendations for

Achieving Sustainable Language

Development in Ethiopia

Language communities should be

encouraged to produce more liter-

ature in the mother tongue. This

should be literature that is wanted

by the community and ideally

include both print and non-print

media. Secondly, improve the

quality of teaching. This can be

achieved through training oppor-

tunities, mentoring, and increasing

the status of the teaching profes-

sion in general. Thirdly, parents

must become more involved in their

children’s education. And lastly,

we must plan well. Let us work

together for sustainable language

development in Ethiopia.

Michael Bryant

Language Programs Director

SIL Ethiopia

ኤስ አይ ኤል (SIL)ን ጨምሮ በርካታ ከለሎችና ድርጅቶች በአፍ መፍቻ ቋንቋ ያዘጋጇቸውን ልዩ ልዩ መጻህፍት የሚያሳዩበት አውደ ርእይም ተመቻችቶ ነበር። አውደ ርእዩ በተከበሩ አቶ አሚን አብዱልቃድር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ በተከበሩ አቶ ሙልጌታ ሰይድ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዴኤታ፣ በተከበሩ ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል አፈ-ጉባኤ እና በሌሎች የመንግስት ሃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተጎብኝቷል።

የተከበሩ አቶ አሚን አብዱል ቃድር በወቅቱ እንደተናገሩት የአፍመፍቻ ቋንቋን መጠበቅ፣ መደገፍና ማጎልበት የአንድን ሀገር ማህበራዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ እሴትን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው። አክለውም በኢትዮጵያ ሰላሳ የሚሆኑ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች በሀገሪቱ ልዩ ልዩ ክልሎች በሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የማስተማሪያ ቋንቋ በመሆን ወደ ትግበራ ገብተዋል። አያይዘውም የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የህዝቦች ቋንቋን በማጥናትና በማስፋፋት የብዝሃ ባህልንና የታሪካዊ ቅርሶችን የመጠበቅ ሃላፊነት (ማንዴት) እንዳለው ጠቁመዋል።

የተከበሩ ወይዘሮ ህይወት ኃይሉም “በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፤ በኢትየጵያ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የማስተማር መብት በህገ መንግስቱ ስለተረጋገጠ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የአፍ መፍቻ ቋንቋን ለማስፋፋትና ለማልማት ተቀራርበው መስራት ይኖርባቸዋል፤ በዚህም ታሪክንና ባህልን ጠብቀው ማቆየት ይችላሉ” ብለዋል።

የሁለተኛው ቀን ፕሮግራም በልዩ ልዩ ትምህርታዊ ርእሰ-ጉዳዮች ላይ ውዉይት የተደረገበት መድረክ ነበር። እኔም በSIL የልሳነ-ብዙ ትምህርት አስተባባሪ ከሆኑትና ከስራ ባልደረባዬ ከአቶ መስፍን ደራሽ ጋር በመሆን “በኢትዮጵያ ዘላቂ የቋንቋ ልማት ለማምጣት መልካም አጋጣሚዎችና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበን ነበር። የጥናቱ ጭምቅ ሃሳብም ከዚህ ቀጥሎ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፕሮፌሰር ባዬ ይማም እና በዶ/ር ሞገስ ይገዙ የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎችም ነበሩ። ሌላው ተጠቃሽ ጥናታዊ ጽሁፍ ከሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በዶ/ር ፈቀደ ምኖታ የቀረበው ሲሆን፣ የጥናታዊ ጽሁፉ ትኩረትም በደ/ብ/ብ/ህ/ክ ያለውን የቋንቋ ልማት ደረጃን በሚያመላክት ስታትስቲካዊ መረጃ ላይ ነበር።

ማጠቃለያ በኢትዮጵያ ዘላቂ የቋንቋ ልማት ለማምጣት የምንጠቁማቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚከተሉት ናቸው።

አስቀድሞ የቋንቋ ማህበረሰቡ በአፍ መፍቻ ቋንቋው በርካታ የሥነጽሁፍ ስራዎችን እንዲያዘጋጅ መበረታታት አለበት። እነዚህን በህብረተሰቡ የሚወደዱ የስነጽሁፍ ውጤቶች በህትመት ሊረጋገጥ የሚችለው ወይም በሌላ መንገድ እንዲገኙ ማድረግ ይቻላል። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የትምህርት አሰጣጡን የማሻሻል ጉዳይ ነው። ይህም የስልጠና ሁኔታዎችን በማመቻቸት፣ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ባጠቃላይ የመምህርነትን የሙያ ደረጃ ከፍ በማድረግ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ሊታይ የሚገባው የወላጆች በትምህርት ዙሪያ ተሳታፊ የመሆን ጉዳይ ነው። በመጨረሻም ሁሉም ነገር ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ ደህና አድርጎ ማቀድ ይገባል እንላለን።

ለኢትዮጵያ ዘላቂ የቋንቋ ልማት የህበረተሰብ አቅም ግንባታ ስራ በጋራ ተያይዘን እንስራ።

Page 20: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

18 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

I t is a formidable task to understand and analyze the complexities of language vitality and endangerment.

The process has recently been simplified by Gary Simons, Paul Lewis, et al, who combined several of the

previous analysis models into one: the Sustainable Use Model (SUM) for language development. The

SUM does not address every possible issue related to language endangerment/vitality. However, it is a viable

framework that assists language development practitioners to understand the current situation, to identify a

way forward in their activities, and to provide a means for ongoing monitoring and evaluation.

Minority language communities today are facing unprecedented pressure to abandon their local language and

identity. Therefore it is helpful to estimate the current vitality of a language, in order to determine its prospects

for maintenance and potential for development. This vitality can be measured by a language vitality scale

(known as the Expanded Graded Intergenerational Disruption Scale or EGIDS) which has defined 13 different

levels of language vitality. For example, English is defined as an “International” language, which is a level

zero in the EGIDS. On the other end of the scale, we would find a language that is extinct, where there is no

community that even identifies itself with the language any longer; this would be a level ten. Once the current

level of vitality is identified, a community can determine which of the sustainable levels of use it desires to

work towards, and a language development program can be designed.

The basic premise of the SUM is that there are only four inherently sustainable levels of language use.

History: No one in the community identifies with or speaks the language any longer, even though

they know it is a part of their history.

Identity: The community does not use the language for daily communication, but they identify

themselves with the language.

Orality: Community identity is strong and the language is used orally by all generations.

Literacy: The language is used in written form in all areas of the society and literacy in the

language is transmitted from one generation to the next.

Each level of sustainability builds on the preceding one. Certain conditions must be met for a sustainable level

of language development to be reached or maintained. Those interested in language revitalization can have a

more informed strategy by exploring the following five criteria, given the acronym The FAMED Conditions:

Functions: The language must be used or fulfill the functions (history, identity, orality, literacy) that the

language community desires in order to maintain a given level of sustainability.

Acquisition: A means of acquiring the needed proficiency to use the language for those functions must be

operational.

Motivation: Community members must be motivated to use the language for those functions.

Environment: The external environment (e.g., policy, attitudes) must be conducive to the use of the language

for those functions.

Differentiation: The language community agrees on when to use the local language versus another/a more

dominant one.

All these conditions must be satisfied in order for a sustainable level of language development to be reached.

In summary The key focus of minority language development must be on achieving a sustainable level of language use.

The sustainable levels of language use are: history, identity, orality, and literacy.

Careful analysis using The FAMED Conditions will help identify which components of sustainable use may be

lacking in each context.

To read the complete article on the Sustainable Use Model online go to: http://www-01.sil.org/~simonsg/presentation/

Applying the SUM.pdf

To read more about the EGIDS online go to: http://www.ethnologue.com/about/language-status

The Strengths & Challenges Sustainable Language Development in Ethiopia of

18 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Page 21: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 19

በ ቋንቋ ህያውነትና አደጋ ላይ መሆን ዙሪያ ያለውን ውስብስብ ጉዳይ መመርመርና መረዳት አስቸጋሪ ጉዳይ ነው። ይሁንና ይህ አስቸጋሪ ጉዳይ በቅርቡ Gary Simons እና Paul Lewis በተባሉ ሰዎች አማካኝነት ሂደቱ ቀለል እንዲል ተደርጓል። ይኸውም ልዩ ልዩ የትንተና ሞዴሎችን በማዋሃድ “Sustainable Use Model (SUM) for Language

Development” የሚል ሞዴል በመስራታቸው ነው። ሞዴሉ በቋንቋ ህያውነት ወይም አደጋ ላይ መሆን ዙሪያ ያሉትን ጉዳዮች በሙሉ የሚያነሳ አይደለም። ይሁንና በቋንቋ ልማት ዙሪያ ለተሰማሩ ባለሞያዎች የሚያተኩሩበት ቋንቋ በጊዜው ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፣ ስራቸውን የሚያከናውኑበትን የሚለዩበትን መንገድ ለማሳየት፣ በሂደት ክትትልና ግምገማ የሚያካሄዱበትን ዘዴ ለመጠቆም የሚረዳና በተግባር ሊተረጎም የሚችል ማዕቀፍ ነው።

አሁን አነስተኛ ተናጋሪ ያላቸው የቋንቋ ማህበረሰብ ክፍሎች ቋንቋቸውና መለያቸውን ሊያጠፉ በሚችሉ ሁኔታዎችና ጫናዎች ውስጥ ይገኛሉ። ስለዚህ ቢያንስ የቋንቋዎቹ ህያውነት በምን ዓይነት ደረጃ ላይ ይገኛል ብሎ ግምት መውሰዱ ቋንቋዎቹ እንደገና የሚንሰራሩበትና የሚለሙበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ይጠቅማል። “Expanded Graded Intergenerational Disruption

Scale (EGIDS)” በሚል ስያሜ የሚታወቀው መለኪያ አስራ ሶስት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን የቋንቋ ህያውነትን መለካት ያስችላል። ለምሳሌ እንግሊዝኛ እንደ ዓለምአቀፍ ቋንቋ በ EGIDS ሲለካ በዜሮ ደረጃ ላይ ይገኛል። ከአንግሊዝኛ በተቃራኒ ሌላ ጫፍ ላይ የሚገኝ ቋንቋ ደግሞ የጠፋ ቋንቋ ወይም ምንም ተናጋሪ የሌለው ወይም ደግሞ እኔ የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ነኝ የሚል የህብረተሰብ ክፍል የሌለው ማለት ነው። በመለኪያው መሰረት ሲገለጽ ደግሞ በአስረኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ነው።

የአንድ ቋንቋ ህያውነት ደረጃ አንድ ጊዜ ከተለየ፤ የቋንቋው ማህበረሰብ ቋንቋውን በዘላቂነት የሚጠቀምበትን ደረጃ ለማውጣትና የቋንቋ ልማት ፕሮግራም ለመቅረጽ ይረዳዋል።

የSUM ሞዴል መሰረታዊ መነሻ ዘላቂነት ያለው የቋንቋ አጠቃቀም ደረጃዎች አራት ብቻ ናቸው የሚል ነው። እነሱም፡-

በታሪክነት ደረጃ - ማህበረሰቡ ስለ ቋንቋው ታሪክ ብቻ ያውቃሉ፤ ይሁንና ይ ቋንቋውን እናገራለሁ። ወይም የእኔ ቋንቋ ነው የሚል ማህበረሰብ ሳይኖርው ሲቀር፥

በመማንነት ደረጃ - ቋንቋው ባንድ ወቅት የእኛ ነበር የሚል የማህበረስብ ሲኖርና ዛሬ ላይ ግን ከቶውንም የሚናገርው ስው ሳይኖርው ሲቀር

በቃል ደረጃ (ቃላዊነት) - ቋንቋው የማህበረሰቡ ጠንካራ መለያ ነው። ትውልዱ ቋንቋውን በቃል(በንግግር) ደረጃ ብቻ ሲጠቀምበትና ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ ሲችል

በማንበብና በመጻፍ ደረጃ - ማህበረሰቡ ባለበት አካባቢ ሁሉ ቋንቋው ለጽሁፍ የዋለ ሲሆን፣ የማንበብና የመጻፍ ትምህርቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ በቋንቋው የሚተላለፉ ሲሆን

አንድ የተወሰነ ዘላቂ የቋንቋ ልማት ክመጨረሻው አራተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ የተወሰኑ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው። ቋንቋዎች እንዲንሰራሩ ፍላጎት ያለው ሰው ከዚህ በታች FAMED በሚል ምህጻረ ቃል ስር የተዘረዘሩትን አምስት መመዘኛዎች በመመርመር ሰፋ ያሉ ስትራቴጂዎችን መቀየስ ይችላል። እነሱም፤-

አገልግሎት (Functions) - ቋንቋው ለ(ታሪክ፣ ለማንነት መለያ፣ ለንግግር፤ ለለማንበብና መጻፍ) አገልግሎት መዋል/ማሟላት አለበት ። የቋንቋ ማህበረሰብም ያለውን የዘላቂነት ደረጃ ጠብቆ ለማቆየት ፍላጎት ሊኖረው ይገባል።

ለመዳ (Acquisition) - ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች በተግባር መጠቀም የሚያስችል የቋንቋ ብቃት የሚለመድበት(የሚታወቅበት) መንገድን ይመለከታል።

ተነሳሽነት (Motivation) - የቋንቋ ማህበረሰቡ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለመጠቀም ተነሳሽ የመሆን ጉዳይን ይመለከታል።

የአካባቢ ሁኔታ (Environment) - የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለመጠቀም የአካባቢው (ለምሳሌ ፖሊሲ፣ አመለካከት) አመቺ መሆንን ይመለከታል።

የአጠቃቀም ሁኔታ ልዩነት (Differentiation) - የቋንቋ ማህበረሰብ የአካባቢውን ቋንቋ በምን ሁኔታና መቼ መጠቀም እንዳለበትና ሌላውን ወይም በስፋት የሚነገረውን ቋንቋ ደግሞ በምን ሁኔታና ጊዜ መጠቀም እንዳለበት ስምምነት ላይ መድረስን ይመለከታል።

ዘላቂ የቋንቋ ልማት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ሁሉ ሊሟሉ ይገባል።

በርካታ ተናጋሪ የሌላቸው ቋንቋዎች ልማት ቁልፍ ትኩረት ዘላቂ የቋንቋ አጠቃቀም ላይ መሆን ይገባዋል።

ዘላቂ የቋንቋ አጠቃቀም ደረጃዎች ታሪክዊንት፣ ማንነት፣ በንግግር ብቻ የሚገለጽ መሆን እና ማንበብና መጻፍ ናቸው።

FAMED በሚል ምህጻረ ቃል ተገልጸው የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ተጠቅሞ በርካታ ምርመራ በማካሄድ ቋንቋውን በዘላቂነት ጥቅም ላይ ለማዋል የማያስችሉ ጉዳዮችን ከእያንዳንዱ ሁኔታዎች ውስጥ ለይቶ ለማውጣት ይጠቅማል።

በ Sustainable Use Model ዙሪያ የተጻፈውን ሙሉ መጣጥፍ ለማንበብ የሚከተለውን ድረገጽ መጎብኘት ይቻላል።

http://www.ol.sil.org/-simonsg/presentation/Applying the SUM.pdf

በ EGIDS ዙሪያ ተጨማሪ ንባብ ማድረግ ለሚፈልግ http://www.ethnologue.com/about/language-status መጎብኘት ይችላል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ የቋንቋ ልማት ለማምጣት መልካም አጋጣሚዎችና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 19

Page 22: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

20 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Travis Williamson

T he late dry season sun scorches the lowlands

in Western Ethiopia. Yet despite its menacing

strength, it can’t stop Gumuz men and

women from working, talking and singing out in their

fields. “Better together,” as one English saying goes,

the Gumuz people learned long ago that cooperative

working in each others’ fields can produce much

more, not only in their grain

houses, but more importantly in

their social harmony. Yet, the

very foundation of this

community-driven culture is

being tested as more and more

young Gumuz men and women

are leaving the traditional

fieldwork behind in preference

for higher levels of education and

employment. Such is the case for

Thomas, Janey and Work’u, three

Gumuz men who spend their days

hard at work, not under the

merciless afternoon sun, but

rather behind computer screens as

they write and translate materials

into their mother tongue. It is my

great privilege to work with these

men.

While checking a translated story

prior to publication, the Gumuz

team and I encountered the

rhetorical question, “Who can speak of his

descendants?” stated with regard to a young man who

had died. The implications of this lament were: “He

never reached the point in his life where he bore

children; he would not leave behind a legacy; his life

was snuffed out much too early!”

I sat back in my chair and looked at my co-workers;

all of them are in their mid-twenties. Work’u married

just two years ago, Janey married this past rainy

season, and Thomas was eagerly counting the final

days until his own wedding. Knowing that none of

them had any children yet, and wanting to make sure

this story’s statement of lament was communicating

clearly, I asked, “What does this question mean when

a Gumuz person reads it?” Their response was strong

and clear, “Not having children means he had nothing

to leave behind; he only lived and died; his life had

no meaning…” That, it seems, is a point worthy of

የ ሀሩሩ ንዳድ የቆላውን ምዕራብ ኢትዮጵያ ያንገበግበዋል። የዚህ ሀሩር ጉልበት ለማያውቁት ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ ቢሆንም የጉምዝን ሴትና

ወንድ ልጆች ግን ከስራ አላገዳቸውም።እነሱ በማሳቸው ላይ እየዘመሩ፣ እየተጫወቱ ይሰራሉ። “አብሮነት ይሻላል” እንደሚለው የእንግሊዝኛ አባባል የጉምዝ ህዝቦች በእያንዳንዱ ሰው ማሳ ላይ ተባብሮ የመስራት ጥቅም

ገብቷቸዋል። ጥቅሙ ጎተራቸውን የሚሞላ ምርት ለማስገኝት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ትስስራቸውን እንደሚያጠናክርላቸው ከተገነዘቡ ከርመዋል። ይሁንና የጉምዝ ወጣት ሴትና ወንድ ልጆች የገጠሩን ባህላዊ የመስክ ስራ እየተዉ የከፍተኛ ትምህርትና ተቀጥሮ መስራትን ምርጫቸው እያደረጉ ሲመጡ የዚህ የማህበረሰብ-መር ባህል መሰረት ፈተና ውስጥ እየወደቀ ነው። ይሄ ደግሞ ቶማስ፣ ጃኒ እና ወርቁ የተባሉ የሶስት ወንድ ወጣቶች ታሪክ ነው። እነዚህ ወጣቶች ቀኑን በከባድ ስራ ላይ ተጠምደው ያሳልፋሉ። ሆኖም ስራቸውን የሚሰሩት ምህረት የለሽ በሆነው ጠራራ ፀሀይ ላይ ሆነው አይደለም፤ ይልቁንም በኮምፒዩተር ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ልዩ ልዩ ጽሁፎችን ወደ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲተረጉሙ ይውላሉ። ለእኔ ከእነዚህ ሰዎች ጋር አብሮ የመስራት አጋጣሚ ማግኘቴ ትልቅ እድል ነው።

የተተረጎሙት ታሪኮች ወደ ህትመት ከመሄዳቸው በፊት የማጣራት ስራ እንሰራለን፤ በዚህ ጊዜ አንድ የበሞት የተለየ ወጣትን በተመለከተ “ስለ አብራኩ ክፋዮች የሚናገርለት ማን ይሆን?” በሚል የተጻፈውን አነበብን።እናም እኔና የጉምዝ ቋንቋ ቡድን ምላሽ ከማናገኝላቸው ጥያቄዎች ጋር ተፋጠጥን። በዚህ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ሊገለጽ የተፈለገው የሰቆቃ ድምጽ “ወጣቱ ሟች በህይወት ዘመኑ የአብራኩን ክፋይ ሳያይ ተቀጨ” የሚል ነበር። እንድምታውም ዘር ሳይተካ ባጭሩ ተቀጭቷል የሚል ነው።

ወንበሬ ላይ ደገፍ ብዬ በስራ የሚረዱኝን ወጣቶች አየኋቸው፤ የሁሉም እድሜ በሃያዎቹ መካከል ውስጥ የሚገኝነው። ወርቁ ከሁለት ዓመት በፊት ትዳር ይዟል፤ ጃኒ ባለፈው ክረምት ውስጥ አግብቷል፤ ቶማስ ደግሞ የሚያገባበትን ቀን እየቆጠረ ነው። ከእነዚህ ወጣቶች መካከል እስካሁን ድረስ ማንኛቸውም ልጅ እንደሌላቸው አውቃለሁ፤ ከላይ በተገለጸው አሳዛኝ ታሪክ ውስጥ

This is Our Descendant ይኸው የኛ የአብራካችን ክፋይ

Gumuz farmers know that working

cooperatively brings greater benefits, not only

in their grain houses, but more importantly in

their social harmony.

photo

by

Tra

vis

Wil

lia

mso

n

Page 23: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 21

lament in any culture. “So,” I continued, “if one of

you dies before your wife gives birth, could this same

statement be said about you?” They nodded their

heads in silence. After a moment, Thomas sat straight

up in his chair and, with astonishing insight, pointed

at the computer screen in front of us. “No!” he said,

“This is our descendant!”

The wisdom of Thomas’ statement struck me at a

profound level. These Gumuz writers and translators

are undeniably leaving a legacy by helping to produce

some of the first literature in their mother tongue.

These books will be read by Gumuz people not only

now, but for generations to come. And so, Thomas’

assessment was exactly correct, he and his fellow

translators are leaving a significant legacy in the

development of their language.

Yet, there are those who discourage such work,

saying, “The Gumuz people have lived for genera-

tions without needing written materials and literacy.

Why impose these outside values upon an otherwise

content society?” Granted, the introduction of lang-

uage development does initiate cultural change. But

the reverse is also equally true,

perhaps even more so. The languages

and cultures of Ethiopia, as

everywhere else in the world, are

already facing unavoidable change.

The Ethiopian Road Authority is

quickly improving transportation to

previously isolated areas of the country.

Ethiopian Telecom is expanding its phone and

Internet connectivity, even into remote corners of this

land. Education bureaus are working hard in

producing new materials, opening and promoting new

schools among previously uneducated people. Health

bureaus, agricultural bureaus, and many others are

expanding their efforts in impressive ways. And so, as

transportation, communication, education, health and

livelihoods are being improved, the cultures of

Ethiopia are already finding themselves in an

unprecedented period of change.

ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ግልጽ መሆኑን ለማወቅ ስለፈለግሁ “ይህ ታሪክ በጉምዝ ሰው ሲነበብ የሚያስተላልፈው መልእክት ምንድን ነው?” ስል ወጣቶቹን ጠየቅሁ። መልሳቸውም ግልጽና ጠንከር ያለ ነበር። “አንድ ሰው ልጆች አልወለደም ማለት በዚህ ምድር ላይ ምንም ነገር ጥሎ አላለፈም ማለት ነው። የህይወቱ ትርጉሙም ኖረ ሞተ ከመባል ያለፈ አይደለም።” “እና እናንተም ልጅ ከመውለዳችሁ በፊት ብትሞቱ የናንተም ታሪክ ይኸው ይሆናል ማለት ነው?” ስል ጥያቄዬን አስከተልኩኝ። ሁሉም በዝምታ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁ። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ቶማስ ከተደገፈበት ወንበሩ ላይ ቀና ብሎ በመደነቅ ወደ ኮምፒዩተሩ እየተመለከተና በእጁ እየጠቆመ “በጭራሽ አልስማማም ይኼው የኛ የአብራካችን ክፋይ” አለ።

የቶማስ ጥበብ የተሞላበት ምላሽ በጣም አስደነቀኝ። እነዚህ የጉምዝ ቋንቋ ጸሃፊዎች እና ተርጓሚዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመጀመሪያው ሥነጽሁፍ ተግባራዊ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረጋቸው በርግጥም አሻራቸውን ወይም ሌጋሲያቸውን ትተዋል። እውነትም በእነዚህ ወጣቶች የተዘጋጁት መጻህፍት በጉምዝ ህዝብ የሚነበቡት ዛሬ ብቻ አይደለም፤ በመጪውም ትውልድ ይነበባሉ። የቶማስም እይታ ትክክል ነበር። ቶማስና ሌሎቹ ተርጓሚ ጓደኞቹ ቋንቋቸውን በማልማት ታሪክ ውስጥ የማይናቅ አሻራቸውን እያስቀመጡ ነው።

ባንጻሩ ደግሞ “የጉምዝ ህዝብ እኮ በቋንቋው የተጻፉ መጻህፍት ሳያስፈልጉትና ሳይማር ለብዙ ዘመናት የኖረ ህዝብ ነው፤ ታዲያ ለምንድነው ከማህበረሰቡ ባህልና ልማድ ውጪ የሆነውን ነገር በህብረተሰቡ ላይ የሚጭኑት በማለት ይህን ስራ የሚያጣጥሉም አልጠፉም። እርግጥ ነው፤ የቋንቋ ልማትን መጀመር የባህል ለውጥ እንዲከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ተቃራኒውም የዚያኑ ያህል ምናልባትም በበለጠ እውነት ነው። እንደማናቸውም የአለም ቋንቋዎችና ባህሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎችም በማይቀረው የለውጥ ጎዳና ውስጥ ገብተዋል። ቀድሞ በመንገድ አለመኖር ምክንያት ተገልለው በነበሩ

አካባቢዎች አሁን እድሜ ለኢትዮጵያ አውራ ጎዳና ባለስልጣን በፍጥነት የትራንስፖርት አገልግሎቶች እየተሻሻሉ ናቸው።የኢትዮጵያ ቴሌኮም በጣም ገጠር በሆኑ ኣካባቢዎች እንኳ ሳይቀር የቴሌፎንና የኢንተርኔትን አገልግሎት እያስፋፋ ነው። ትምህርት ቢሮዎች ኣዳዲስ የትምህርት ማቴርያሎችን ለማስፋፋት ጠንክረው እየሰሩ ነው። ያልተማሩ ሰዎች በሚገኙበት

አአካባቢዎች አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን እየገነቡ ነው። የጤና ቢሮዎች፣ የግብርና ቢሮዎች ስራቸውን ለማስፋፋት በአሰገራሚ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ነው። እናም የትራንስፖርት ሁኔታ፣ የሰዎች የእርስ በርስ ግንኙነት፣ የትምህርት፣ የጤና ሁኔታና የሰዎች አኗኗር እየተሸሻለ ሲመጣ የኢትዮጵያ ባህል አይቶት በማያውቀው የለውጥ ዘመን ውስጥ እየገባ መሄዱ ግድ ነው። መልካም የሚባሉ ለውጦች በዙሪያችን እየተከናወኑ ቢሆንም በአካባቢ (ኢንቫይሮመንት) ላይ የሚከሰተው ለውጥ ግን አስጨናቂ ጉዳይ ነው። የመሰረተ ልማትና የትምህርት መስፋፋት፣ የቴክኖሎጂ ትውውቅ ባህላዊ ውህደት እንዲከሰት

Any new innovation

brings with it

cultural change.

Thomas, Work’u, and Janey attending a linguistics workshop in

Addis Ababa

photo

by

Tra

vis

Wil

lia

mso

n

Page 24: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

22 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Good change is happening all around us, and yet, in

that environment of change we find a point of tension.

Development in the form of infrastructure, education,

and the introduction of technology has the natural

result of encouraging cultural assimilation. Yet, uniform-

ity of culture is not the desired end. Ethiopians value

their cultural diversity! They value their diverse peo-

ples, heritages and traditions. And so, in the context

of a rapidly changing world, SIL and its many part-

ners are supporting yet another change: language

development. Yet, whereas any new innovation

brings with it cultural change, language development

has the complimentary effect of preserving one’s

culture, that is, by sustaining one of its most precious

resources, its language.

Our mother tongue is the language by which we first

understood our world. It contains the categories by

which we make associations in learning and encodes

each particular culture’s worldview in a way that no

other medium can. By preserving and strengthening the

languages of Ethiopia, the wonderful tapestry of cul-

tural diversity will thus be preserved in the midst of

the many other exciting changes already taking place.

And so I spent a moment in thought, having explored

only the surface of Thomas’ insightful comment. Are

today’s Gumuz writers, curriculum and dictionary

developers and translators making an important

contribution to their people and

culture? Most certainly! And who

will speak of their descendants?

Without a doubt, we all will!

Travis Williamson

Translation Advisor

SIL Ethiopia

ምክንያት መሆኑ አይቀርም። ለውጡ ሄዶ ሄዶ ተመሳሳይ ባህል እንዲፈጠር ያደርጋል ማለት ግን አይደለም። በተለይ ኢትዮያውያን ለባህል ብዝሃነታቸውን ትልቅ ስፍራ ይሰጣሉ። የህዝቦች ብዝሃነታቸውን፣ ቅርሶቻቸውና ባህላቸውን ያከብራሉ። ዓለም በገባበት በዚህ በፈጣን የለውጥ አውድ ውስጥ ኤስ አይ ኤል (SIL) እና በርካታ አጋር ድርጅቶችም በቋንቋ ልማት ዙሪያ የሚደረገውን ለውጥ በመደገፍ ላይ ናቸው። ከማንኛውም አዲስ ግኝት ጋር የተያያዘ ለውጥ የባህል ለውጥ ያስከትላል፤ በቋንቋ ልማት የአቅም ግንባታ ሥራ አማካኝነት የሚመጣ ለውጥ ግን ባህልን ጠብቆ የማቆየት ተደጋጋፊ ውጤት አለው። ያም ውጤት የባህል ውድ መገለጫ ወይም ሃብት የሆነውን ቋንቋ ጠብቆ የማቆየት ተግባር ነው። የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ አካባቢያችንን የምንገነዘብበት ቋንቋ ነው። የአፍ መፍቻ ቋንቋ አንድን ነገር በቀላሉ መረዳት (መማር) እንድንችል የሚያግዙ የማገናዘቢያ ቋቶች አሉት፤ እንዲሁም እያንዳንዱን ባህል ልንረዳበት የሚያስችለን ቋት አለው። የትኛውም የሃሳብ ማስተላለፊያ መንገድ (ሚዲያ) እንዲህ አይነቱ ብቃት የለውም። ዘመኑ በርካታ አስገራሚ ለውጦች እየታዩበት ያባሉበት ወቅት ነው። ይሁንና በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቋንቋዎችን በማጠናከርና በመጠበቅ፣ በቀለማት ተውቦ እንደተሰራ መጎናጸፊ የሚያምረውን የባህል ብዝሃነት ጠብቆ ማቆየት ይቻላል።

የቶማስን የጠለቀ አስተያየት ላይ ላዩንም ቢሆን ለመገንዘብ ጥቀት ጊዜ ሳውጠነጥን ቆየሁ። የአሁኖቹ የጉምዝ ቋንቋ ጸሃፊዎች፣ የስርዓተ ትምህርትና የመዝገበ ቃላት አዘጋጆች እንዲሁም ተርጓሚዎች ለህዝባቸውና ለቋንቀቸው ጠቃሚ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይሆን? ስለአብራኮቻቸው ክፋይስ በርግጠኝነት የሚናገርላቸው ማን ይሆን? ያለጥርጥር እኛ ነን፤ እኛ ሁላችን እንናገርላቸዋለን።

Students and children in the village of Kushaamba gather around a new text in order to practice their reading skills.

photo

by

Tra

vis

Wil

lia

mso

n

Page 25: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 23

Dr. Patricia Davis

A s an education consultant, I have made two visits to Ethiopia. The first was more than 20 years ago. In 1992, I was busily submitting

my Ph.D. dissertation proposal at the University of Texas, not keenly aware of events unfolding in East Africa, when – to my great surprise – a fax message arrived from the Transitional Government of Ethiopia’s Ministry of Education, informing me that I was expected in Addis Ababa in two weeks to lead a work-shop! In 2013, I was invited again to give consultant help for the Reading for Ethiopia's Achievement Developed (READ) Technical Assistance (TA) project, focusing on curriculum revision and textbook development. The contrasts between my two visits were both surprising and very encouraging.

Background As you know, Amharic was the only language allowed in education and business in Ethiopia during the reign of Haile Selassie. The subsequent regime, in spite of all their faults, ostensibly stood for the oppressed peoples, and their new education policy committed to adult education in 15 languages. In 1974, the Head of Adult Education was charged with making adult literacy primers. By 1988, basic

በ ኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት አማካሪ ሆኜ እንድሰራ ሁለት እድሎች አግኝቻለሁ። የመጀመሪያው ከሀያ ዓመት በፊት እ.ኤ.አ በ1992 ነበር። ያኔ በቴክሳስ

ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለዶክቶሬት ድግሪ ማሟያ የሚሆን የጥናት ጸሁፍ ፕሮፖዛል ለማቅረብ ላይ ታች የምልበት ጊዜ ነበር። ወደ ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ምን እየተከናወነ እንዳለ ፈጽሞ በማላውቅበት በዚህ ጊዜ ድንገት አስደሳች የፋክስ መልዕክት ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ደረሰኝ። መልዕክቱም በሁለት ሳምንት ውስጥ አዲስ አበባ ገብቼ በወቅቱ የሚካሄደውን ዓውደ ጥናት እንድመራ የሚያበስር ነበር። ከብዙ አመታት በኋላ እንደገና እ ኤ አ 2013

(Reading for Ethiopia’s Achievement Developed - Technical Assistance “READ-TA”) ለተሰኘ ሌላ ፕሮጀክት የቴክኒክ ድጋፍ እንዳደርግ ተጋበዝሁ። የፕሮጀክቱም ትኩረት የስርዓተ-ትምህርት ክለሳና የመማሪያ መጽህፍት ዝግጅት ነበር። የሁለቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ጉብኝቶቼ አጋጣሚዎች አስገራሚም አበረታችም ነበሩ።

የጽሁፌ ዳራ የሶሻሊስቱ አገዛዝ ከወደቀ በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀዳሚው ጉዳይ አዲስ ሕገ መንግስት ማርቀቅ ነበር። በዚህ ወቅት ቋንቋቸው የትምህርት መስጫ ቋንቋ ያልሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትምህርት እንዲሰጥላቸው ፍላጎታቸውን አሳይተው ነበር።

Growing a Multilingual

የልሳነ-ብዙ ትምህርት ፕሮግራምን ማሳደግ

Representatives from thirteen language communities enthusiastically participated in the 1992 workshop.

Education Program

photo

by

Patr

icia

Da

vis

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 23

Page 26: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

24 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

teaching materials for adult literacy had been provided in the 15 selected languages.

Also during this era, secondary school graduates were expected to participate in the Zemecha campaign to increase literacy in the rural areas of Ethiopia. The nationwide literacy rate at that time was estimated to be around 55%.

When the Socialist regime was overthrown, one of the first matters of concern was to draft a new consti-tution. By this time, the minority language communi-ties of the country were demanding education in their mother tongues. The provisional government consented, and it was established as part of the new constitution. Mother tongue education for children was a radical new concept that was acclaimed, but very few people had any idea how to go about it.

By 1992, the Ministry of Education (MOE) had been given the task of implementing the new mother-tongue education policy and was seeking assistance. They ran an article in the local newspaper asking for help with developing primary education materials. Dr. Ernst-August Gutt, who was the director of SIL Ethiopia at that time, responded with a proposal offering help with this endeavor. Together with Dr. Steve Walters, the SIL International Literacy Coordinator, they submitted a one-year proposal that included, among other things, a workshop for MOE personnel led by Patricia Davis! This is when the surprise fax arrived.

I had not known about the events that led up to the invitation and did not see how I could possibly go to Ethiopia, but Dr. Walters insisted that it was impor-tant. He also informed me that what was needed was a blueprint for a bilingual education program, not a course in linguistics.

My qualifications for the job, in addition to an MA in Foreign Language Education and Ph.D. studies in curriculum and instruction, included experience in every aspect of the Peru Bilingual Education program–

በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር መብት በአዲሱ ሕገ መንግስት ውስጥ በመካተቱ የእነዚህ ህብረተሰብ ክፍሎች ፍላጎት ዕውን ሊሆን ችሏል። ይሁንና በወቅቱ ህፃናትን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የማስተማር ሂደቱ አዲስ ጽንሰ ሃሳብ በመሆኑ ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ የተገነዘቡ ሰዎች በጣም ጥቂቶች ነበሩ።

ከዚህ አኳያ እ.ኤ.አ በ1992 ለትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚለውን መመሪያ እንዲያስፈጽም ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶት ስለነበር ወቅቱ የባለሙያዎችን ድጋፍ የሚሻበት ጊዜ ሆነ። ትምህርት ሚኒስቴርም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የማስተማሪያ ማቴሪያል ዝግጅትን በተመለከተ የባለሙያ ድጋፍ እንደሚሻ የሚጠቁም ጽሁፍ በአንድ አገራዊ ጋዜጣ ላይ አወጥቶ በነበረበት ሁኔታ በወቅቱ በኢትዮጵያ የኤስ አይ ኤል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር እርንስት ኦገስት ጉት ይህንን ጥረት ለማገዝ ፈቃደኛነታቸውን የሚገልጽ ሃሳብ በማቅረብ ምላሽ ሰጡ። እሳቸውም ዶ/ር ስቲቭ ዋልተርስ ከተባሉ የኤስ አይ ኤል አለም አቀፍ የመሰረተ ትምህርት አስተባባሪ ጋር በመሆን የአንድ አመት የሥራ ፕሮፖዛል አቀረቡ። ፕሮፖዛሉ ከያዛቸው በርካታ ነገሮች መካከል ለትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች የሚዘጋጅ ዓውደ ጥናት ይገኝበታል። አወደ ጥናቱም የሚመራው በእኔ ፓትሪሺያ ዳቪስ እንዲሆን ተወስኖ ስለነበር ይህሄው አስደሳች መልዕክትና ግብዣ ባለሁበት በአሜሪካ ደረሰኝ።

ያኔ ይህ ግብዣ ሲደረግልኝ ስለ ርእሰ ጉዳዩ ብዙም የማውቀው ነገር አልነበረም። ወደ ኢትዮጵያም እንዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ይሁንና ዶ/ር ዋልተር የጉዳዩን አስፈላጊነት አስረድቶኝ ወደ ኢትዮጵያ እንድመጣ ግድ አለኝ። እንዲሁም የሚፈለገው ነገር በልሳነ-ክልኤ ትምህርት (Multilingual Education) ዙሪያ ማዕቀፍ ወይም ዕቅድ ማዘጋጀት እንጂ የስነ-ልሳን ኮርስ የመስጠት ጉዳይ እንዳልሆነ አስረድቶ አበረታታኝ።

በውጭ ቋንቋ ትምህርት የማስተርስ ድግሪ፣ በስርዓተ ትምህርትና ስልጠና የዶክትሬት ድግሪ ያለኝና እንዲሁም በፔሩ የልሳነ ክልኤ ፕሮግራም ውስጥ ልዩ ልዩ የስራ ድርሻዎችን ወስጄ ተሳትፎ አድርጌ ሰለነበር ለስራው አዲስ እንደማልሆነ ተገነዘብኩ። በዚህም በፔሩ ውስጥ ሀያ የቋንቋ ማህበረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ንቅናቄ በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ብዙ ድርሻ አበርክቻልሁ። በዚያን ወቅት እኔ በመማሪያ መጽሐፍት ዝግጅትና አርትዖት ስራ፣ በመምህራን ስልጠና፣ የአካባቢ ትምህርት ኃላፊዎችን በማማከርና በማግባባት፣ በየመንደሩ ያሉ ትምህርት ቤቶች ላይ የሱፐርቪዥን ስራ በመስራት፣ የስልጠና ማቴሪያሎችን በማዘጋጀት ስራ ላይ እሳተፍ ነበር። በመሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ ታቅዶ የነበረው ዓውደ ጥናት ከእኔ የትምህርትና የስራ ልምድ ጋር ተቀራራቢ በመሆኑ ለአዲስ አበባው ጉዞ ራሴን ማዘጋጀት ጀመርሁ።

ዓውደ ጥናቱ ትምህርት ሚኒስቴር የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርትን በተመለከተ ስልጠና ለመስጠት ፍላጎትና አቅም ያላቸውን የትምህርት ባለሙያዎች እና አሰልጣኞችን እንደሚፈልግ በራዲዮና በጋዜጦች አስታወቀ። አመልካቾቹም ከአካባቢያቸው የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው እንዲመጡ ተነገረ። ምንም እንኳን ማስታወቂያው አጭር ቢሆንም በትምህርት

It was a complete surprise to receive a fax from

the Ministry of Education in Ethiopia!

Page 27: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 25

a mother tongue education initiative that had been implemented with solid success in twenty-eight language communities. I had been involved in textbook development and editing, teacher training, liaison with local education officials, supervision of village schools, and preparation of training materials. So the proposed workshop in Ethiopia was certainly within my range of experience; I began to make preparations for the trip to Addis Ababa.

The workshop The MOE announced by radio and newspaper that they were seeking educators and potential trainers interested in mother tongue education for children, and whose application was supported by letters from their community leaders. Although notice was very short, the office of the Curiculum and Research Depart-ment (CRD) of the Ministry of Education was quickly innundated with applicants. People were literally fighting in the hall to get into the class. A few managed to get in by their absolute, indomitable insistence; such was their enthusiasm. In the end, 38 men were accepted from 13 language communities. In class they were grouped by language to form commit-tees: Ageu, Oromo, Wolaytta, Hadiyya, Keffa-Sheka, Gede'o, Somali, Sidama, Kambaata, Gurage, Gamo, Kistane and Silt'e.

Course content The workshop was received with great openness and elation. I have never seen teachers more eager to achieve education in their mother tongues. Since the training was only three weeks in duration, the goal was limited to giving an overview of a multilingual education program. I divided the teaching into three parts:

1. Writing our language; thinking like a linguist We began with basic linguistic principles; some of the participants were not sure of their orthography or had difficulties with marking tone. SIL linguist Simon Gardener kindly worked through the most pressing of the difficulties with the not-yet-well-defined writing systems.

This was the first time many of the men had ever written in their mother tongue. The joy expressed in the classroom on the first day of story writing was both dramatic and heart wrenching. Participants eagerly shared their “wonderful stories written in the

ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ጥናትና ምርምር መምሪያ ለምዝገባ በመጡ ሰዎች ተጥለቀለቀ። ለምዝገባው የመጡ ሰዎች ወደ ምዝገባ አዳራሽ ለመግባት ሲታገሉ ጥቂቶች እንደምንም ታግለው ወደ ውስጥ ሲገቡ ይታይ ነበር። በእርግጥም ያ ትዕይንት የጉጉታቸውን ጥልቀት አመላካች ነው።በመጨረሻም ከ13 የቋንቋ ማህበረሰብ ውስጥ 38 ሰዎች ተቀባይነትን አግኝተው ተመዘገቡ። በክፍል ውስጥም በየቋንቋቸው እየተጎዳኙ ኮሚቴ እንዲመሰርቱ ተደረገ። በዚህ መሰረት የአገው፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ፣ ሀድያ፣ ከፍቾ፥ ሸካ፣ ጌዴዖ፣ ሱማሌ፣ ሲዳማ፣ ከምባታ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ ክስታኔ፣ እና የስልጤ ቋንቋዎች ኮሚቴዎች ተዋቀሩ።

የስልጠናው ይዘት ዓውደ ጥናቱ ፍፁም ግልጽነትና ደስታ የተሞላበት ነበር። መምህራን ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲሰጥላቸው ያሳዩ የነበሩትን የዚህ አይነት ጉጉት የትም አይቼ አላውቅም። ስልጠናው የሚቆየው ለሦስት ሳምንታት ሲሆን፣ ግቡም የልሳነ-ብዙ ትምህርት ፕሮግራምን ማስተዋወቅ ነበር። እኔም ስልጠናውን እንደሚከተለው በሶስት ክፍል አዘጋጀሁት፡-

1. በቋንቋ ለመፃፍ-እንደ ስነልሳን ባለሙያ ማሰብ ይህን ርዕስ ጉዳይ በመሰረታዊ የስነ-ልሳን መርህ ላይ ትኩረት በማድረግ ጀመርን፤ ከተሳታፊዎቹ መካከል አንዳንዶች በቋንቋው ስነ-ጽህፈት አስመልክቶ የድምፀት (tonal) ችግር ሊያጋጥማቸው እንደሚችል እርግጠኛ አልነበሩም።በወቅቱ በኤስ አይ ኤል ውስጥ የስነ-ልሳን ባለሙያ የሆነው ሲሞን ጋርድነር በዚህ እና የጽህፈት ስርዓታቸው ገና በውል ባልታወቀላቸው ቋንቋዎች ዙሪያ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በጽኑ ደክሟል።

ለብዙዎቹ ተሳታፊዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲጽፉ የመጀመሪያቸው ነበር። በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ታሪክ እንዲጽፉ የተደረገበት የመጀመሪያው ቀን ላይ ይታይ የነበረው ደስታ በርግጥም ትዕይንታዊና ልብ የሚነካ ነበር። ተሳታፊዎች በሚያምረውና ትሁት በሆነው የአባቶች ለዛ የተፃፈውን ታሪክ ለተሳታፊ ጓደኞቻቸው ያነቡላቸው ነበር። ሁለተኛ ቋንቋ ላይ የሚገጥማቸው ችግር ተወግዶ ያለምንም እንቅፋት ሃሳባቸውን እንደልብ በመግለጻቸው ከፍተኛ ደስታ ነበራቸው።ያየሁት ነገር አስደናቂ የመሆኑን ያህል እንዲህ አይነቱ ደስታ በብዙዎች ዘንድ ለዘመናት ተነፍጎ መቆየቱ ደግሞ በሃዘን ያስደምማል።

በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት የመማር ምክንያታቸውን እናዳምጥ ነበር። በዚህ ጊዜ ከሚነሱት ሃሳቦች መካከል ህፃናት በማያውቁት ቋንቋ እንዲማሩ መገደዳቸው ምን ያህል ፍትህ አልባ መሆኑ፤

Cheha-Gurage participants Classroom discussion

photo

s by

Patr

icia

Davi

s

Page 28: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

26 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

beautiful, polite language of our elders.” They were thrilled to be able to express their thoughts without the inhibitions of a second language. Wonderful as it was, I remember thinking how unspeakably sad that this delight had been denied to so many for so long!

Early in the first week, while listing the reasons for mother tongue educa-tion, we discussed the difficulty of children having to learn in a language they do not know, and how it hampers educational development. Suddenly, anger clouded the classroom. These educators strongly identified with the experience and still felt the indig-nation. There were several first hand accounts about how, as children, they had been punished for using their mother tongue in school. They had been severely discriminated against, their assignments often rejected or declared invalid, when they were unable to write well in Amharic. I quickly pointed out that bilingual education is a double-edged sword: it can be used to divide, or to unite. I encour-aged them to use it for good in their language communi-ties. Thankfully the atmosphere in the room relaxed.

2. Writing materials; thinking like an educator Having been assured that the committees could write their languages, we turned next to educational considera-tions. Each language group did a letter frequency count; and once they understood the progression of a good reading program, they tried their hand at writing actual primer lessons. They approached every new challenge with resolve, and by the end of the second week were beginning to be more comfortable with the process of primer construction.

3. Administrating the program; thinking like

a supervisor With no infractructure yet in place to support a bilingual school program, the men faced enormous challenges. In the final week we talked about the publication, storage, and distribution of books, offices from which to operate, selection of supervisors, training of teachers, and organizing multilingual education classes. Then each team developed a five-year plan for the implementation of their program.

Language vs Dialect One day as I was planning lessons, a Ministry official approached me with a question: “Do you know the difference between a dialect and a language?”

“I think I do,” I responded.

“Well,” he said, “we have recently had some teams translating the textbooks of the curriculum into several languages. They worked day and night to have the books ready for the coming school year, and when they finished, they took the books to their home areas to present them. Most of the parents and commu-nity leaders readily accepted the new materials, but in one location, a mob marched into the school brandishing sticks and threatening the translators.

በትምህርታቸውም ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖም ከባድ እንደሆነ በውይይት ወቅት ይገለጽ ነበር። በውይይታችን መሃል ድንገት የቁጭት ደመና ክፍሉን ይሞላዋል፤ የትምህርትን መሰረታዊ እውነት ባለሙያዎቹ ይበልጥ እያወቁ

በመጡ ቁጥር ቁጭት ውስጥ ይገቡ ነበር። በልጅነት እድሜያቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን በትምህርት ቤት በመጠቀማቸው ምክንያት ቁጣና ግርፋት እንዴት ይገጥማቸው እንደነበር የሚያሳዩ በርካታ ተሞክሮዎች ነበራቸው። በማያውቅት ቋንቋ መፃፍ ሲያቅታቸው የተሰጣቸውን የቤት ስራ እንዳልሰሩ፤ ዋጋ እንደሌላቸው ተቆጥረው ከፍተኛ መገለል ይደርስባቸው እንደነበር አስታወሱ። እኔም

ፈጥኜ ልሳነ-ክልኤ ትምህርት ለልዩነትም ሆነ ለግኑኝነት የሚያመች ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍ መሆኑን ጠቆምኳቸው። በመሆኑም ሁለት ቋንቋ ማወቃቸውን እንደጥሩ አጋጣሚ እንዲወስዱት አሳሰብኳቸው። ደግነቱ ከዚህ ሃሳብ በኋላ በክፍሉ የተረጋጋ ድባብ ሰፈነ።

2. ለመጽሐፍት ዝግጅት - እንደ ትምህርት ባለሙያ ማሰብ የኮሚቴዎቹ አባላት በራሳቸው ቋንቋ መፃፋቸውን እርግጠኛ ከሆንን በኋላ ከስነ-ትምህርት አኳያ ትኩረት ሊደረግባቸው ወደሚገቡ ጉዳዮች ፊታችንን መለስን፤ እያንዳንዱ የቋንቋ ቡድን በቋንቋው ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ፊደላትን ለይተው አወጡ። ከዚያም ደረጃ በደረጃ አያደገ ስለሚሄድ የጥሩ ንባብ ፕሮግራም ግንዛቤ ካገኙ በኋላ የመማሪያ መጻህፍት ለማዘጋጀት አንዳንድ ክፍለ ትምህርቶችን ይዘው ለመስራት ሙከራ ማድረግ ጀመሩ። የሚገጥማቸውንም አዳዲስ ችግሮች እየፈቱ በሁለተኛው ሳምንት መጨረሻ ላይ በመማሪያ መጽሐፍት አዘገጃጀት ዙሪያ ይበልጥ ልምድ እያዳበሩ መጡ።

3. ፕሮግራምን ለማስተዳደር - እንደ ሱፐርቫይዘር ማሰብ የልሳነ-ክልኤ ፕሮግራምን ለማገዝ ምንም አይነት መዋቅር ባልተዘረጋበት ሁኔታ ሰዎች በርካታ ተግዳሮቶች እንደሚገጥማቸው ይታወቃል። በመጨረሻዎቹ ሳምንታት የተነጋገርንባቸው ጉዳዮች የመጽሐፍት ሕትመትን፣ የማቆያ ግምጃ ቤትና ስርጭት እንዲሁም እነዚህ ስራዎችን ለመስራት ስለሚያስፈልጉ ቢሮዎች፣ ሱፐርቫይዘር ምርጫ፣ የመምህራን ስልጠና እና ልሳነ-ብዙ ትምህርት መስጫ ክፍሎችን ማደራጀትን በተመለከተ ነበር። ከዚህ በኋላ እያንዳንዱ ቡድን ፕሮግራማቸውን መዘርጋት የሚያስችላቸውን የአምስት አመት እቅድ አዘጋጁ።

ቋንቋ እና ዘዬ በአንድ ክፍለ-ትምህርት ዙሪያ የማስተምረውን ነገር እያቀድኩ በነበርኩበት ግዜ የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊ ወደ እኔ መጥተው “በአንድ ቋንቋ እና በዘዬ መካከል ያለውን ልዩነት ታውቂያለሽ?” ሲሉ ጥያቄ አቀረቡልኝ፤

እኔም “የማውቅ ይመስለኛል” ብዬ መለስኩላቸው፤

“ደህና! እኛ አሁን በቅርቡ የመማሪያ መጽሐፍቶቻችንን ወደ ልዩ ልዩ በርካታ ቋንቋዎች የሚተረጉሙ ቡድኖችን አደራጅተናል። እነሱም ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት መጽሐፍቱን ዝግጁ ለማድረግ ላይ ታች እያሉ ነበር።

Do you know the

difference between

a dialect and

a language?

Page 29: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 27

‘You cannot impose these books on us!’ they shouted. ‘This is not our language!’ ”

The gentleman continued his story, “We know that these two language variants are very closely related and should be able to use the same materials. The translators even made special efforts to include alter-nate terms in parenthesis, trying to accommodate both dialects. However, one group is very angry, and the translators are devastated. We have asked the oppos-ing group to come to Addis Ababa to talk about this, and we need to shed more light than heat. Would you be willing to talk to them about the difference between a language and a dialect?”

“I'll do my best,” I promised.

Feeling the need for some support, I contacted Mr. Brady Anderson who had been directing language surveys in several African countries and was currently based in Ethiopia. He gave me the African word list used by the surveyors, and reminded me of basic prin-ciples relating to the language/dialect debate. Fortified, I returned to my office to prepare. But how should I approach the subject? Any mention of specific Ethiopian languages might cause contention. I decided to use the example of the Matsigenka language in Peru, where I had previously worked. There, a different dialect is found on every river. Using the principles from the lang-uage survey manual, I could clarify the process for dis-tinguishing between languages and dialects. With a map and lesson outline prepared, I waited. This was obvious-ly going to be a sensitive and emotive discussion!

No one arrived from the language community that had rejected the new textbooks - not even one represen-tative. Then one day in class, I learned that one of the language teams was dealing with seven dialects and needed somehow to reconcile the materials so as to serve the largest population possible.

“Are others of you also dealing with dialects?” I asked.

It became apparent that almost everyone was. So, taking a deep breath, I inquired, “Would you like to talk about the difference between a language and a dialect?”

There was a resounding, “Yes!”

“All right, we’ll talk about it tomorrow.”

ስራቸውን ከጨረሱ በኋላ መጽሐፍቱን ለማስተዋወቅ ወደየመጡበት ቀዬ ሄደው ነበር። አብዛኛዎቹ የማህበረሰብ መሪዎች መጽሐፍቱን ለመቀበል ዝግጁ ነበሩ። ይሁንና በአንዳንድ አካባቢዎች ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር። “እነዚህን መጽሐፍት ተቀበሉ ብላችሁ ልታስገድዱን አትችሉም። ይህ የእኛ ቋንቋ አይደለም” ሲሉ የተቃወሙ የማህበረሰብ ክፍሎች ነበሩ። ኃላፊውም ቀጠል አድርገው “መጻህቱ በተዘጋጁበት ቋንቋ እና ሰዎቹ የኛ በሚሉት ቋንቋዎች መካከል ያለው ልዩነት በጣም ተቀራራቢ እንደሆነና በአንድ መጽሐፍ ሊገለገሉ እንደሚችሉ እናውቃለን፤ መጽሃፉ በሚዘጋጅበት ጊዜ ተርጓሚዎች ተጨማሪ ቃላትን በቅንፍ ውስጥ በማስቀመጥ በዘዬ ምክንያት የሚመጣውን ልዩነት ለማጥበብ ሞክረዋል። ይሁንና አንዱ ቡድን ላይ ከፍተኛ ቁጣ ገጥሞት ተርጓሚዎችም እስከመባረር ደርሰው ነበር። ለዚህ ሁኔታ ከተዳረጉት ሁለት ቡድኖች ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ጠይቀን ነበር። ችግሩንም ከማራገብ ይልቅ እውነታውን ማሳወቅ እንደሚያስፈልግ ተረድተናል። ስለዚህም ከነሱ ጋር በቋንቋ እና በዘዬ መካከል ስላለው ልዩነት ልትወያዪ ትችያለሽ?” ሲሉ የትምህርት ኃላፊው ጠየቁኝ። እኔም “አዎን የቻልኩትን ያህል አደርጋለሁ” ስል ቃል ገባሁላቸው።

በዚህ ጉዳይ ላይ ድጋፍ ሊያደርግልኝ ይችላል ብዬ ካሰብሁት ከሚስተር ብራዲ አንደርሰን ጋር ተገናኘሁ። ብራዲ አንደርሰን በዚያን ጊዜ መቀመጫው ኢትዮጵያ ይሁን እንጂ በበርካታ የአፍሪካ አገራት የቋንቋ ቅኝትን/ሰርቬይ ሲመራ የነበረ ሰው ነው። እሱም ቅኝት አድራጊዎች የሚጠቀሙባቸውን የቃላት ዝርዝር ሰጠኝ። ዝርዝሮቹ የቋንቋ እና የዘዬ ክርክሮችን በተመለከተ መሰረታዊ የሆኑ መርሆችንም አስታወሱኝ። እኔም በዚህ ተበረታታሁ። ለማንኛውም ዝግጅቴን ለማድረግ ወደ ቢሮዬ ተመለስሁ። ይህን ጉዳይ በምን መልኩ ነው ማቅረብ ያለብኝ ብዬ ትንሽ አሰብሁ። ቀደም ሲል እሰራበት ከነበረው አገር ከፔሩ “ማጽኛካ” ከተሰኘ ቋንቋ ምሳሌዎችን ማቅረብ ፈለግሁ። እዚያም በየወንዙ አዋሳኞች ሁሉ ልዩ ልዩ ዘዬዎች ይገኛሉ። ከቋንቋ ቅኝት ማንዋሉ ባገኘሁት መርሆዎች መሰረት በቋንቋ እና በዘዬ መካከል ያለውን ልዩነት የሚያመለክት የመለያ ሂደትን ግልጽ ለማድረግ ቻልኩ። ከዚያም የካርታውን እና የትምህርቱን ቢጋር አዘጋጅቼ ጠበቅሁ። ይህም ለውይይት ቀስቃሽና/አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ መገመት አያዳግትም። በአዲስ መልክ የተዘጋጁትን መጽሐፍት ከተቃወሙት የሕብረተሰብ

All the language groups worked diligently to produce their exhibits for the closing ceremony.

Here the Hadiyissa team were working on their progress chart and letter frequency chart.

photo

by

Patr

icia

Davi

s

photo

by

Bra

dy

Ander

son

Page 30: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

28 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

The next day, I could hardly believe my eyes; the class-room was packed. The Director of the Curriculum and Research Department and almost every staff member were there. The class participants were all sitting on the edge of their seats. I didn't dare falter in this lecture!

Slowly and carefully, we examined the diversity of the Matsigenka situation. Using the word list, and com-paring roots, an adjacent variant turned out to be more than 60% different (the difference between English and German). We classified it as a separate language. All the other variants on approximately eight rivers were mutually intelligible; so the question became, “Which was the central dialect?”

We applied the criteria of perceived purity, central location, direction of trade, who visits whom, etc., as outlined in the survey manual. In the end, the class decided, as the Matsigenka linguists had, that there were two central dialects. In the process, they had learned the steps for diagnosing a linguistic situation. They had also learned that dialects having greater than 85% similarity can use the same materials, if the parties are willing. With a lesser percentage, however, it would be very difficult for combined materials to function well. Grammar differences, moreover, are more difficult to reconcile than differences in terms. We did a bit of practice with the African word list, and then the class filed out, without a single comment. I wondered if the lesson had failed.

Three days later, one of the translators whose work had been so violently rejected, came to see me, obvious-ly excited about something. “We sat with our brothers from the other group,” he explained, “and in all the language we can find only fifty words that are different. And now our brothers say, amazed, ‘We are one!’ ”

The closing ceremony At the closing ceremony, the walls were covered with posters, each language team displaying the results of their hard work. The participants and the Minister gave me lovely gifts of jewelry and a traditional dress and held a banquet in my honor. One couldn't have felt more sincerely appreciated.

መካከል አንድ ተወካይ እንኳን አልቀረበም። አንድ ቀን በክፍል ውስጥ በነበረን ውይይት አንድ ነገር ተረዳሁ። ከቡድኖቹ መካከል አንዱ ሰባት ዘዬ ያሉት ቋንቋዎች ላይ እየሰራ እንደሆነ ተረዳሁ። በመሆኑም መጽሐፉ በርከት ያሉ ተናጋሪዎች ያሉትን ማህበረሰብ ክፍል እንዲያገለግል እንደገና መቃኘት እንዳለበት አሰብኩ። ቡድኖቹንም “ሌሎቻችሁም እንዲሁ ዘዬ ያላቸው ቋንቋዎች አሏችሁ?” ስል ጠየቅሁ። አብዛኛዎቹ ቡድኖች በቋንቋዎቻቸው ውስጥ የተለያዩ ዘዬ ያላቸው ነበሩ። አኔም በረጅሙ ተነፈስኩና ጥያቄዬን ቀጠልሁ። “በቋንቋ እና በዘዬ መካከል ስላለው ልዩነት እንድንነጋገር ትፈልጋላችሁ?” ስል ጠየቅሁ። ሁሉም በአንድ ድምጽ “አዎን!” ብለው መለሱ። “ደህና እንግዲህ በዚህ ጉዳይ ነገ እንነጋገራለን”

በማግስቱ አይኔን ማመን እስኪያቅተኝ ክፍሉ በሙሉ በሰዎች ተሞልቶ ጠበቀኝ። የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ጥናትና ምርምር ዳይሬክተርና በዚያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ሳይቀሩ ተገኝተው ተሳታፊዎች በተገኘው ቦታ ሁሉ ተጠጋግተው ይቀመጡ ነበር። በዚህ ሁሉ ሰው ፊት ለመቆም ብርክ ያሲዛል። በርጋታና በጥንቃቄ በማጽኛካ ቋንቋ የተከሰተውን የዘዬ ልዩነት መመርመር ጀመርን። ከስርወ-ቃሉ ጋር ሲነጻጸሩ በሁለቱ ተቀራራቢ ቃላት መካከል ያለው ልዩነት ከስልሳ በመቶ በላይ እንደሆነ መገንዘብ ተቻለ። እንዲህ አይነት ልዩነት ያላቸውን እንደ አንድ የተለየ ቋንቋ ተደርገው እንዲፈረጁ ተስማማን። በሌሎች 8 ወንዞች ዙሪያ የሚገኙ ዘዬዎች አንዱ የሌላውን ቋንቋ መረዳት በሚያስችል ደረጃ የነበሩ ዘዬዎች ነበሩ። ስለዚህ ጥያቄው “ማዕከላዊው ዘዬ የትኛው ነው?” የሚለው ነበር። እኛም በቅኝት ማንዋሉ ላይ እንደቀረበው ቢጋር “ጥርት ብሉ የሚለየው የቱ ነው”፣ “ማዕከላዊ አካባቢ”፣ “የመገበያያ አቅጣጫ”፣ “ማን ማንን ዘወትር ይጎበኛል” የሚሉትን መስፈርቶች ተግባራዊ አደረግን። በመጨረሻም ክፍሉ በሙሉ ልክ የማጽኛካ የስነ-ልሳን ባለሙያዎች እንዳደረጉት ሁለት ማዕከላዊ ዘዬዎች እንዳሉ አረጋገጥን። እግረ መንገድም ተሳታፊዎች ስነ-ልሳናዊ ጉዳዮች እንዴት ደረጃ በደረጃ እንደሚተነተኑ ትምህርት አግኝተዋል። በሌላ በኩልም የሁለት ዘዬ ባለቤቶች እስከተስማሙ ድረስ ከ85 በመቶ በላይ ተመሳሳይነት ያላቸው ዘዬዎች በአንድ አይነት መጽሐፍ ሊገለገሉ እንደሚችሉ ግንዛቤ ላይ ተደርሷል።

The Oromo display included the alphabet, morphology, some dictionary making, sample reading lesson, a morpheme analysis and a story.

photo

by

Bra

dy

Ander

son

28 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Page 31: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 29

In my closing remarks, I said to the participants and assembled guests:

This course has been a pioneer endeavor. Its

purpose has been to facilitate bilingual education

for the many nationality languages of this beautiful

nation. The participants are also pioneeers – 38

courageous educators, all highly skilled, willing to

undertake the challenge of making mother tongue

education available to their own people...

In the exhibits you will find reflected the topics of

our discussions... What the exhibits... cannot

possibly convey, however, is the excitement and joy

which has repeatedly been evidenced as workshop

participants found the tools [they will need for

their future work]. Friendships have developed as

participants from very different areas of the

country have come to know and appreciate each

other. Bilingual education has knit us together in

unity.

Experience in other countries has taught us,

however, that bilingual education is a long and

arduous process as well as a joyful one... Neverthe-

less, the core of specialists now exiting from this

course—if given the proper facilities—can form the

nucleus of a national bilingual education system.

The experience they now possess, and will continue

to gain, will provide a solid basis for gradual

expansion, and workshops can provide additional

knowledge in areas where more depth is desired.

I would like to express my appreciation to the

authorities who have extended this unique and

precious opportunity... Words of special tribute

also are due the course participants. You have

given of yourselves with a high level of dedication.

You have demonstrated superior skills... Together

we have shared something of the freedom and

delight we all experience when we are released to

communicate in our mother tongue, the language

of our hearts.

ይሁንና ከዚህ ፐርሰንት በታች ተመሳሳይነት ላላቸው ዘዬዎች ተመሳሳይ መጽሐፍት/ጥምር መጽሐፍት መጠቀም አስቸጋሪ ነው። በተጨማሪም የሰዋሰው ልዩነት ያላቸውን ዘዬዎች ማጣመርና በአንድ መጽሐፍ ለመጠቀም መሞከር በቃል አጠራር ደረጃ ልዩነት ካላቸው ዘዬዎች ይልቅ ይበልጥ አስቸጋሪ ነው። በመጨረሻም የአፍሪካውያንን የቃላት ዝርዝር ይዘን ትንሽ ሙከራ አደረግን። በክፍሉ ውስጥ የነበሩ ተሳታፊዎችም ያለአንዳች እርማት ሁሉንም መስራት ችለዋል። በዚህ ሁኔታ ሰርተን ስልጠናው የተሳካ ባይሆን ኖሮ በጣም እደነቅ ነበር።

ከሶስት ቀን በኋላ ስራው ክፉኛ ውድቅ የተደረገበት የትርጉም ባለሙያ ወደ እኔ መጣ። በአንድ ነገር ደስተኛ እንደነበር ያስታውቃል። “ከሌሎች ቡድን ወንድሞቻችን ጋር ቁጭ አልን” ሲል ሃሳቡን መግለጽ ጀመረ። “በሁሉም ቋንቋዎች ውስጥ ያሉት ለየት ያሉት ቃላት ከሃምሳ እንደማይበልጡ አረጋግጥን” እናም እነዚህ ወንድሞቼ “እኛ አንድ ነን” ሲሉ ተናገሩ፤ ይገርማል።

የስልጠና ማጠቃለያና ሽልማት በስልጠና መዝጊያ ስነስርዓቱ ወቅት ግርግዳዎች በሙሉ በፖስተሮች ተሸፍነው ነበር። እያንዳንዱ ቡድን የደከመበትን ስራ ለማሳየት ተዘጋጅቷል። ተሳታፊዎችና ትምህርት ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ገነት ዘውዴ የአክብሮት የእራት ግብዣ አድርገው ባህላዊ ልብስና የጌጣጌጥ ስጦታ አበረከቱልኝ። እንዲህ ያለ በቅንነት የተሞላ አድናቆት ማንም ሊሰጥ አይችልም። ተሳታፊዎቹ አውደ ጥናቱን ያጠናቀቁት በታላቅ ደስታ ነበር። ይሁንና እኔ አንድ ነገር ተገነዘብሁ። ይኸውም እነዚህ ለአሰልጣኝነት የተመለመሉ ሰዎች በሥልጣናቸው አንዲት ነገር የመለወጥ አቅም የሌላቸውና ቀደም ሲል አስተማሪዎች የነበሩ ሰዎች ናቸው። አብዛኞቹ የራሳቸው የቋንቋ ማህበረሰብ አባል በሌለበት ትምህርት ቤት ተመድበው ሲያስተምሩ የቆዩ ናቸው። አንዳንዶቹም አምስትና ስድስት ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ሲያስተምሩ የቆዩ ናቸው። በርካታ ተግዳሮቶች ከፊታቸው እንደተደቀነ መገመት አያዳግትም።

The Silte team explain their exhibit to the Minister of Education. Gede-Uffa team (Gedeo) with their exhibit prepared for the

closing ceremony.

photo

by

Bra

dy

Ander

son

photo

by

Patr

icia

Davi

s

Page 32: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

30 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

Participants left the workshop with great enthusiasm, but I recognised that these men, chosen to be trainers, were primarily classroom teachers with no authority to make changes. Several were assigned to teach in schools of a language community other than their own, and some of them managed classrooms with students from five or six different languages. Many challenges lay ahead for them.

Immediately after the workshop, Mr. Ken Boothe, an SIL linguist and trainer, gave computer and linguistic training to Ministry of Education personnel. A little later, Dr. Elizabeth Gfeller, an SIL educator from Switzerland, worked for a number of years in the southwestern regions of Ethiopia, helping with development of the mother tongues and bilingual education programs. Ms. Mary Clarkson, a computer specialist, came from Kenya and provided computer training for some of the textbook makers.

The READ-TA project I returned to Ethiopia in 2013 to give consultant help for the Reading for Ethiopia's Achievement Developed (READ) Technical Assistance (TA) project. READ-TA supports the Ministry of Education and the Regional State Education Bureaus in its efforts to develop a nationwide reading and writing program in seven mother tongue languages and English. The objective of the project is to improve the reading and writing skills of children in grades one through eight in both their mother tongue and English, as measured by improvements in learning outcomes. The project is expected to reach 15 million children in all schools and all regions of Ethiopia. The project started in October 2012, and will end in October 2017. RTI International is leading a consortium of five partners in the implementation of this initiative; one of those partners is SIL.

For a short period in July and August, I was asked to help during the planning of the Scope and Sequence phase of the project. Dr. Agatha van Ginkel, however, had this process well under way and the developers were accustomed to working with her. So, instead, I trained the storywriters. I helped to prepare them and the curriculum developers to orient the new, larger team that would arrive later in the year to develop the actual primer pages. I modelled Reading Readiness classes, taught grade-level story-writing techniques,

አውደ ጥናቱ በተጠናቀቀ ማግስት ሚስተር ኬን ቦዝ በኤስ አይ ኤል የስልጠና ባለሙያና አሰልጣኝ ለትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች የስነ-ልሳን ስልጠና የሰጠ ሲሆን በተጨማሪም የኮምፕዩተር ስጦታ አበርክቶላቸዋል። ከትንሽ ግዜ በኋላ ደግሞ በኤስ አይ ኤል የስነ-ትምህርት ባለሙያ የሆኑት ስዊዘርላንድአዊት ዶ/ር ኤልሳቤጥ ገፈለር በደቡባዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ልማትንና የልሳነ-ክልኤ ትምህርት ፕሮግራም ትግበራን በማገዝ ለተወሰኑ ኣመታት ሰርተዋል። የኮፖምፒዩተር ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሜሪ ክላርክሰን ደግሞ ከኬንያ መጥተው ለተወሰኑ የትምህርት መማሪያ መጽሐፍት አዘጋጆች የኮምፕዩተር ስልጠና ሰጥተዋል።

የ ሪድ ቲኤ (READ-TA) ዩኤስ አይ ዲ (USAID) ፕሮጄክት

ለREAD-TA ፕሮጄክት የምክር አገልግሎት ለመስጠት እ.ኤ.አ በ2013 ወደ ኢትዮጵያ ተመለስኩ። ይህ ፕሮጄክት በትምህርት ሚኒስቴር እና በክልሎች ውስጥ እንግሊዝኛን ጨምሮ በሰባት የአፍ መፍቻ ቋንቋ የማንበብና የመጻፍ ልምድን ለማዳበር በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል። ዓላማው ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ያሉ ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የንባብና የመጻፍ ክሂላቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ነው። ለውጡ የሚለካው ተማሪዎች በትምህርት አቀባበል ላይ ባሳዩት መሻሻል ነው።

ፕሮጄክቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ክልሎችና ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ 15 ሚሊዮን ተማሪዎችን ይደርሳል የሚል እሳቤ አለ። የተጀመረውም እ.ኤ.አ ጥቅምት 2012 ሲሆን የሚጠናቀቀው ደግሞ ጥቅምት 2017 እኤአ ይሆናል።

ዓለም አቀፉ አር ቲ አይ (RTI) ይህንን መርሃ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ ተነሳሽነት ከወሰዱ አምስት አጋር ድርጅቶች መካከል የመጀመሪያው ነው። ኤስ አይ ኤልም (SIL) ሌላው አጋር ነው።

በሃምሌ እና በነሃሴ ወር በነበረኝ አጭር ጊዜ ውስጥ የፕሮጄክቱን መጠነ-ርእይ እና ቅደም ተከተል አስመልክቶ እቅድ በሚዘጋጅበት ጊዜ ድጋፍ እንዳደርግ ተጠየቅሁ። ይሁንና ዶ/ር አጋታ ቫን ኺንከል ይህን ስራ ደህና አድርጋ እያስኬደችው ነበር፤ ባለሞያዎችም ከእሷ ጋር በቅርበት መስራቱን ተለማምደውታል። እኔም ልዩ ልዩ

What is RTI?

RTI International is one of the world's leading research institutes, dedicated to improving the human

condition by turning knowledge into practice. They provide services to governments and businesses in

more than 75 countries, with many areas of expertise, including education.

In the international education sector, from their longstanding work in post-apartheid South Africa to

innovative work in Early Grade Reading Assessment (EGRA), including recently in Ethiopia, RTI works

to improve education quality, relevance, access, and efficiency around the world.

www.rti.org/idg

Page 33: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

December 2014 ታህሳስ 2007 Language Matters 31

mentored the storywriters, and prepared sample formats for lessons and teacher guides.

The READ-TA project has the wonderful benefit of full government support. This stands in sharp contrast to countries where interest in multilingual education is in name only. This support may be one of the most important factors in the success of Ethiopia’s educational reforms.

From what I observed during my time in Hawassa, in the Southern Region, under Dr. van Ginkel's capable leadership, the READ-TA project appears to be well organized and is progressing on schedule. The Southern Region participants are among the most educated, experienced, skilled and capable group with whom I have ever had the pleasure to work, and their motivation is very high. I was proud of their willingness both to accept new ideas and to train teachers to use them.

I observed many changes since my first visit. Ethiopia in 1992 was in a state of disarray. By contrast, in 2013 I was delighted to see a new prosperity. “This is a time of construction,” my taxi driver asserted. He spoke truly. Everywhere one looks, new structures—some of them skyscrapers—are underway. Many buildings and roads are now repaired, parks and flowers flourish. The rich farmland I saw between Addis Ababa and Hawassa is yielding bountiful harvests.

Obviously, some of the most encouraging changes for me are in the area of education. The government is supporting mother tongue education on a much larger scale: teaching children in their mother tongue is now widely practiced throughout the country. Textbooks for primary school children are available in many languages, and bureaus of education are organized to manage multilingual education, whereas before there were very few mother tongue materials

ታሪኮችን የሚጽፉ ባለሞያዎችን ለማሰልጠን ሃሳቡ ነበረኝ። ከዚያ ይልቅ ግን የመደበኛውን መማሪያ መጽሃፍ ለማዘጋጀት ዘግየት ብለው ለመጡ በርካታና አዳዲስ ባለሞያዎች ገለጻ የሚደረግበትን መንገድ ለስርዓተ ትምህርት ባለሞያዎችና ለሌሎቹ ባለሞያዎች በማሳየት የድጋፍ ስራ መስራቱን መረጥኩ። የንባብ ዝግጁነት ክፍልን እንደ ናሙና በመጠቀም ለየክፍል ደረጃው የሚመጥኑ ታሪኮች የመጻፊያ ዘዴዎችን (ቴክኒኮችን) አስተማርኩ። ታሪክ ለሚጽፉ ባለሙያዎችም የቅርብ ክትትል በማድረግ ድጋፍ አደርግሁ። ከዚያም የአንድ ክፍለ ትምህርት ናሙና እና የመምህሩ መምሪያን አዘጋጀን።

የREAD-TA ፕሮጄክት የመንግስት ሙሉ ድጋፍ ከማግኘቱ አኳያ በጣም ተጠቃሚ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ ድጋፍ ልሳነ ብዙ ትምህርትን በስም ብቻ እንደግፋለን ከሚሉ ከብዙ አገሮች በጅጉ የተለየ ነበር። ይህ ዓይነቱ ድጋፍ በኢትዮጵ ላለው የትምህርት ሪፎርም ስኬታማነት አብይ ምክንያት ነው ሊባል ይችላል።

በደቡብ ክልል ሃዋሳ በነበርኩበት ጊዜ ካስተዋልኳቸው ነገሮች መካከል በዶ/ር ቫን ኺንከል አመራር ሰጪነት የሚካሄደው (READ-TA) ፕሮጄክት በደንብ የተቀናጀና በተያዘለት መርሃግብ መሰረት እየተካሄደ የነበረ ፐሮጄክት መሆኑ ነው። የደቡብ ክልል ተሳታፊዎች በጣም የተማሩና በቂ ልምድና ክህሎት ያላቸው ከመሆናቸውም ባሻገር በስልጠናው ወቅት ያሳዩት የነበረው ተሳትፎ ከእነሱ ጋር አብሮ ለመስራት አስደሳች ሁኔታን የሚፈጥር ነበር። አዳዲስ ሃሳቦችን ለመቀበልና ሌሎች መምህራንን ለማሰልጠን የነበራቸው ፈቃደኝነት በርግጥም የሚያኮራ ነው።

ከመጀመሪያው የጉብኝት ጊዜዬ ይልቅ አሁን በኢትዮጵያ በርካታ ለውጦችን አስተውያለሁ። በዚህ ጉብኝቴ አስደሳች የሆነ አዲስ የብልጽግና ክስተት ያየሁበት ወቅት ነው። በርካታ ህንጻዎችና መንገዶች ፈርሰው እየተሰሩ ነው። አበቦች በየመናፈሻው ፈክተው ይታያሉ። በአዲስ አበባና በሃዋሳ መካከል ያየኋቸው ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች ላይ ምርት እየተሰበሰበባቸው ነው።

Southern Region participants in the READ-TA project in Hawassa, 2013

photo

by

Agath

a v

an G

inke

l

Page 34: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና

32 Language Matters December 2014 ታህሳስ 2007

available and no infrastructure for this type of learning to take place. Educators now seem to have considerably more training and are more capable of leading educational reform; I met a number who had had the advantage of a multilingual school experience. I also met educators from Sidama, Hadiyya and Wolaytta who proudly showed me the textbooks for grades one to four in their own languages, now used in the schools for many years.

I was able to meet only one of the participants from the 1992 workshop. But I am happy to see that, on those early foundations established for mother tongue education in Ethiopia, a tall tower has been built; increasingly, students now have the freedom and delight of learning and communicating in their mother tongue, the language of their hearts.

Dr. Patricia Davis

Senior Literacy and Education

Consultant

SIL International

From 1964 to 1971 Patricia worked beside her

husband Harold in Peru, South America, under SIL

auspices, cooperating with the Peruvian Ministry of

Education in supervision, teacher training, and

textbook preparation for the Matsigenka bilingual

schools. After her husband's death, she continued

until 1984, serving as advisor, teacher trainer and

textbook editor for school programs of 28

ethnolinguistic groups. She has consulted, lectured

and taught in 17 countries and in U.S. universities.

She is also author, or co-author, of some 50 titles

including the books Bilingual Education: An

Experience in Peruvian Amazonia, Cognition and

Learning, and a series of textbooks that teach

Spanish as a second language.

በርግጥ ለእኔ ደግሞ እጅግ አበረታች ለውጥ ሆኖ ያገኘሁት በትምህርት ሴክተሩ ዙሪያ የተደረገው ለውጥ ነው። መንግስት የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርትን በስፋት እየደገፈ ነው። ህጻናትን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር በሀገሪቱ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። በበርካታ ቋንቋዎች የተጻፉ የህጻናት መጻህፍት እንደልብ ይገኛሉ። ቢሮዎች የልሳነ ብዙ ትምህርትን ለማሳለጥ በሚገባ ተደራጅተዋል።ቀድሞ እንዲህ ዓይነቱ ዝግጅትና የመጻህፍት አቅርቦት ፈጽሞ አልነበረም። የትምህርት ባለሙያዎቹ አሁን በዚህ ዙሪያ ልምድ ያካበቱና ይህን ለውጥ ለመምራት ብቁ የሆኑ ይመስላል። በልሳነ ብዙ ትምህርት ቤት ውስጥ ባገኙት ልምድ ተጠቃሚ የሆኑ ብዙ ሰዎችን አግኝቻለሁ። እንዲሁም ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል በራሳቸው ቋንቋ ማለትም በሲዳምኛ፣ በሃዲይኛ እና በወላይትኛ ያዘጋጁዋቸውንና አሁን ረዘም ላለ ጊዜ በትምህርት ላይ የሚገኙትን መጻህፍት በልበሙሉነት ይኸው ብለው ያሳዩኝ የትምህርት ባለሙያዎችን አግኝቻለሁ።

እኤአ በ1992 ከተዘጋጀው አውደጥናት ተሳታፊዎች ከነበሩት መካከል ያገኘሁት አንድ ሰው ብቻ ነበር። ይሁንና የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት መሰረት ከተጣለበት ጀምሮ አሁን እንዲህ ተመንድጎና አድጎ ማየቴ በጣም አስደስቶኛል። አሁን ተማሪዎች ከልብ በሚወዱት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እየተማሩና እየተግባቡ ነፃነታቸውን በደስታ እያጣጣሙ ናቸው።

በኤስ አይ ኤል SIL ድጋፍ አማካኝነት ዶ/ር ፓትሪሻ ዳቪስ እኤአ ከ1964 እስከ 1971 ከባለቤታቸው ሃሮልድ ጋር በመሆን በደቡብ አሜሪካ ፔሩ ውስጥ አገልግለዋል። ያገለገሉበትም መስክ ከፔሩ የትምህርት ሚንስተር ጋር በመተባበር በሱፐርቪዥን፣ በመምህራን ስልጠና፣ ለማፂኛካ ልሳነ-ክልኤ ትምህርት ቤት መማሪያ መጻህፍትን በማዘጋጀት ነበር። ባለቤታቸው በሞት ከተለያቸው በኋላ ደግሞ በአማካሪነት፣ በመምህራን አሰልጣኝነት፣ ለ28 የስነልሳን ቡድኖች የትምህርት ቤት ፕሮግራም የሚሆን የመማሪያ መጻህፍት ኤዲተር በመሆን አገልግሎታቸውን ቀጥለዋል። በአሜሪካ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በ17 አገሮች ተዘዋውረው የማማከር ስራ፣ ሌክቸር ወይም ገለጻ የማድረግ እና የማስተማር ስራ አከናውነዋል። እንዲሁም በልሳነ ክልኤ ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ በተጻፉ 50 በሚደርሱ ጽሁፎች ላይ እና Bilingual Education An

Experience in Pervian Amazonia, Cognition and Learning በሚል ርእስ በተዘጋጀው መጽሃፍ ውስጥ በደራሲነትና በተባባሪ ጸሃፊነት ሰርተዋል። ከዚህ ባሻገር ስፓኝ ቋንቋን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለማስተማሪያነት የሚጠቅም ተከታታይ የማማሪያ መጻህፍትም አዘጋጅ ናቸው።

Dr. Patricia Davis returned to Ethiopia in 2013 as a consultant

for the READ-TA project in Hawassa.

photo

by

Agath

a v

an G

inke

l

Page 35: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና
Page 36: Contents - sil.org · አስቀድሞ በእኛ የትምህርት ፖሊሲ አዘጋጆች የታወቀ ጉዳይ ነበር ማለት ይቻላል። የትምህርት ጥራትና