Upload
others
View
56
Download
0
Embed Size (px)
Citation preview
1
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት
ደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ
DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTHERN NATIONS,
NATIONALITIES AND PEOPLE’S REGIONAL STATE
የተሻሻው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግስት የመንግስት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ----/2011 በክልሉ መንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ
የሚካሄደውን የምልመላና መረጣ ሥርዓትን
በመሰረታዊነት በመለወጥና በአገር አቀፍ ደረጃ
የሚዘረጋውን የሙያና የሥራ ብቃት ማረጋገጫ
ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል
አሠራር ስርዓት ለመፍጠር ፣ እንዲሁም
የመንግስት ሠራተኛው በዚህ ሥርዓት ውስጥ
እንዲያልፍ በማድረግ ብዝሀነትን ያረጋገጠና
ሀገሪቱ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት
ለማስቀጠል የሚያስችል ፐብሊክ ሰርቪስ
ለመገንባትና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም
በሰው ሃብት ሥራ አመራር ረገድ ያመጣቸውን
ውጤቶች ለማጎልበትና ለማስቀጠል የሚያስችል
ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤
በመንግስት መሥሪያ ቤቶች ያሉ ሰራተኞችን
ወጥነት ባለው መልኩ ለመምራትና
The Revised Draft Proclamation No- /
2018 of Civil Servants of South Nations,
Nationalities and Peoples’ Region
WHEREAS it has become necessary to
promulgate a law that enable the making
of fundamental changes in the system of
recruitment and selection and the
introduction of national system for the
certification of professional and
occupational competence as well as the
subjecting of civil servants to undergo
through such process and thereby build a
civil service that could guarantee diversity
and the sustainability of the country’s
growth and the enhancement and
sustainability of the achievements of the
civil service reform program in human
resource management;
WHEREAS it has become necessary to
establish a system for adopting uniform
administration of civil servants and proper
------------ ›mT qÜ_R --------------
hêú -------------- qN 2011 ›.M
uÅu<w wN?a‹'
wN?[cx‹“ Q´x‹
¡ML© S”ÓYƒ U¡`
u?ƒ Övm’ƒ ¾¨× ›ªÏ
------------ year No --------------------
Hawassa-----------2018
2
እውቀታቸውንና ችሎታቸውን በተገቢው ሁኔታ
ለመጠቀም የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት
መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የመንግስት መስሪያ ቤቶች ያሏቸውን ሠራተኞች
በስራው ላይ በማቆየትና አዳዲስ ሰራተኞችን
በመሳብ ተወዳዳሪ ለመሆን እንዲችሉ የተሻሻሉ
የሥራ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ፤
የክልሉ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ 47/94 እና
ከመሠረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት ትግበራ
ወዲህ በአፈጻጸም ሂደት የተስተዋሉ ችግሮችን
መቅረፍ በማስፈለጉ፣
በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 51 ንዑስ አንቀጽ 3/ሀ/
መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
ክፍል አንድ ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል መንግሥት የመንግሥት
ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር --- /2011” ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው
use of their knowledge and skill;
WHEREAS it has become necessary to
improve conditions of work so that
government offices could become
competitive through retaining their
employees and attracting new entrants;
WHEREAS it has become necessary to
solve the problems after the implementation
of basic work process study during the
process of implementation of the Region
civil servant’s Proclamation 47/2002.
NOW, THEREFFORE, in accordance with
Sub-Article 1/a/ of Article 51 the
Constitution of the South Nations,
Nationalities and People’s Region , it is
hereby proclaimed as follows:
SECTION ONE
GENERAL 1. Short Title
This Proclamation may be cited as the
“South Nations, Nationalities and People’s
Region Civil Servants Proclamation No. ----
/2018.”
2. Definitions
In this Proclamation, unless the context
3
ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፣
1. “ ክልል ” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል ነው፡፡
2. “ቢሮ ወይም ቢሮ ኃላፊ” ማለት እንደየቅደም
ተከተሉ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት
ልማት ቢሮ ወይም ቢሮ ኃላፊ ነው፡፡
3. “የመንግሥት መሥሪያ ቤት” ማለት ራሱን
ችሎ በአዋጅ ወይም በደንብ የተቋቋመና
ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከመንግሥት
በሚመደብለት በጀት የሚተዳደር የክልሉ
የመንግሥት መሥሪያ ቤት ነው፤
4. “የመንግሥት ሠራተኛ” ማለት በክልሉ
መንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት
ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፤ ሆኖም
የሚከተሉትን አይጨምርም፤
G/ ¾S”ÓYƒ ተሿሚዎችን'
K/ ¾¡MM' ¾µ”' ¾M¿ ¨[Ç' ¾¨[Ç“
¾kuK? U¡` u?ƒ“ wN?[cx‹ U¡`
u?ƒ ›vM J’¨< uøwK=¡ c`y=e
}SÉu}¨< ¾TÁÑKÓK<ƒ”'
N/ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የፍርድ ቤት
ዳኞችን፣ዐቃቤ ሕጎችን፣
መ) yKLlù ±lþS xƧTN በፖሊስ ደንብ
y¸tÄd„ ¿‰t®Cን#
otherwise requires:
1. “Region” means the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Region.
2. “Bureau or Head of the Bureau”
means; of Public service and Human
Resouce development Bureau or Head
of the Bureau.
3. "Government Institution" means office
established as an autonomous entity by
a Proclamation or Regulation and fully
or partially financed by government
budget of the Region Government
Institution;
4. "Civil Servant" means a person
employed permanently by Region
government institution; provided,
however, that it shall not include the
following:
a) Appointees
b) Member of Region, Zonal, Special
Woreda, Woreda and Kebele
Council and Nations council and
works as a civil servant
c) Court judges and Prosecutors that
are fonud in each level of the
Region;
d) Members of the police and the
Region Police including other
employees governed by the
4
ሠ/ ›Óvw vK¨< K?L IÓ u²=I ›ªÏ
•እ”ÇÃgð’< ¾}Å[Ñ< c^}™‹”'
5. “ጊዚያዊ ሠራተኛ” ማለት በመንግሥት
መሥሪያ ቤት ውስጥ የዘላቂነት ባሕርይ
በሌለው ወይም ሁኔታዎች ሲያስገድዱ
በቋሚ የሥራ መደብ ላይ በጊዚያዊነት
ተቀጥሮ የሚሠራ ሰው ነው፤ ሆኖም
የሚከተሉትን አይጨምርም፤
ሀ) በቀን ሂሳብ እየተከፈላቸው የሚሠሩ
የቀን ሠራተኞችን፤
ለ) በመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ
ለሙያ መልመጃ ወይም ለተግባር
ሥልጠና የተመደቡ ሰዎችን፤
ሐ) ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋር
በሚገቡት ውል መሠረት ዋጋ
እየተከፈላቸው በራሳቸው የንግድ ሥራ
ወይም የሙያ ኃላፊነት የሚሠሩ
ሰዎችን፤
መ) ባላቸው ልዩ እውቀትና ችሎታ
ምክንያት ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋር
በሚገቡት ውል መሠረት ዋጋ
እየተከፈላቸው በትርፍ ጊዜያቸው የሚሠሩ
ባለሙያዎችን፤
6. “የበላይ ኃላፊ” ማለት የመንግሥት መሥሪያ
Regulations of the Police;
e) employees excluded from the
coverage of this Proclamation by
other appropriate laws;
5. “Temporary employee” means a person
employed in a government institution
for a job which is not permanent in
nature or where circumstances so
require temporarily assigned to a
permanent position; provided, however,
that it shall not include the following:
a) persons employed as daily laborers
and paid on daily basis;
b) persons assigned in a government
institution for apprenticeship or
internship;
c) persons who enter into contract with
a government institution to work for
consideration and on the basis of
their own business or professional
responsibility;
d) Persons who enter into a contract
with a government office due to their
special skills and ability on part-time
basis for consideration.
6. ‘’Head of a government Institution’’
5
ቤትን በበላይነት የሚመራ ወይም ምክትል
ነው፤
7. “የሥራ መደብ” ማለት በአንድ የመንግስት
ሠራተኛ ሙሉ የሥራ ጊዜ እንዲከናወን
ሥልጣን ባለው አካል የተሰጠ ተግባርና
ኃላፊነት ነው፤
8. “የደረጃ ዕድገት” ማለት የመንግሥት
ሠራተኛን ከያዘው የሥራ ደረጃ ከፍ ወዳለ
የሥራ ደረጃ ማሳደግ ነው፤
9. “የብቃት ማረጋገጫ ስርዓት” ማለት አንድ
የመንግስት ሠራተኛ ወይም አዲስ ተቀጣሪ
ሰው ስለተመደበበት ወይም ስለሚቀጠርበት
የስራ መደብ ብቁ ስለመሆኑ የሚረጋገጥበት
ስርዓት ነው፡፡
10. “ደመወዝ” ማለት በአንድ የሥራ ደረጃ
ለተመደቡ ሥራዎች የተወሰነ መነሻ ክፍያ
ወይም የእርከን ክፍያ ነው፤
11. “የሥራ ሁኔታ” ማለት በመንግሥት
መሥሪያ ቤት እና በመንግሥት ሠራተኞች
መካከል ያለ ጠቅላላ የሥራ ግንኙነት ሲሆን
ይህም የሥራ ሰዓትን፣ ደመወዝን፣ ልዩ ልዩ
ፈቃዶችን፣ የሥራ አካባቢ ጤንነትና
ደህንነትን፣ የሠራተኞች የሥራ ስንብት
ሁኔታና ክፍያን፣ የዲሲፕሊን አፈጻጸምና
የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓቶችን እና
means a government official who
directs the institution and includes his
deputies;
7. “position” means a set of duties and
responsibilities assigned by a competent
authority to be performed full time by
an individual civil servant;
8. “Promotion” means assigning a civil
servant to a higher grade;
9. "Competency assuring Procedure" is a
system that ensures that a government
employee or new employee is qualified
for the job assigned or employed.
10. “salary’’ means base or step pay
authorized for jobs classified in the
same grade;
11. “conditions of work” means the entire
field of relations between a government
institution and civil servants and
includes working hours, salary, various
leaves, occupational health and safety,
conditions of termination of service and
severance pay, disciplinary and
grievance procedures and similar
matters;
6
የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፤
12. “ድልድል” ማለት አንድን የመንግሥት
ሠራተኛ በተመሳሳይ ደረጃና ደመወዝ ወይም
ከፍ ባለ ደረጃና ደመወዝ ወይም በሠራተኛው
ስምምነት ዝቅ ባለ ደረጃ መድቦ ማሠራት
ነው፤
13. "የዲሲፕሊን እርምጃ" ማለት ማንኛውም
የመንግስት ሠራተኛ ይህንን አዋጅ ወይም
አዋጁን ለማስፈፀም የሚወጡ ደንቦችና
መመሪያዎችን ወይም የመንግስት ሠራተኞች
ሥነ-ምግባር ኮድ በመተላለፍ ለሚያደርሰው
ጥፋት የሚወሰንበት ቅጣት ነው፤
14. “ጾታዊ ትንኮሳ” ማለት በሥራ ቦታ
የሚፈጸም ሆኖ ከሌላው ወገን ፈቃድ ውጪ
የሚቀርብ የወሲብ ሀሳብ ወይም ጥያቄ
ወይም ሌላ ወሲባዊ ተፈጥሮ ያለው የቃል
ወይም የአካል ንኪኪ ተግባር ሲሆን
የሚከተሉትን ያካትታል፤
ሀ) ከሌላው ወገን ፈቃድ ውጪ የመሳም፣
የሰውነት አካልን የመዳሰስ፣ የመጎንተል
ወይም የመሳሰለውን የሰውነት ንክኪ
የመፈጸም ድርጊት፤
ለ) ወሲብ አዘል በሆነ ሁኔታ ተጠቂውን
መከታተል ወይም እንቅስቃሴውን መገደብ፤
ሐ) ለቅጥር፣ ለደረጃ እድገት፣ ለዝውውር፣
ለድልድል፣ ለሥልጠና፣ ለትምህርት፣
ለጥቅማ ጥቅሞች ወይም ማንኛውንም
12. “Redeployment” means assigning a
civil servant to a similar position of an
equal grade or to a higher position and
grade or to a lower grade where the
civil servant so agrees;
13. “disciplinary measure” means a penalty
imposed on a civil servant for an
offence committed in violation of this
Proclamation or regulations and
directives issued for the implementation
of this Proclamation or code of ethics;
14. “sexual harassment” means unwelcome
sexual advance or request or other
verbal or physical conduct of a sexual
nature in work place and includes:
a) unwelcome kissing, patting,
pinching or making other similar
bodily contact;
b) following the victim or blocking the
path of the victim in a manner of
sexual nature;
c) put sexual favor as prerequisite for
employment, promotion,transfer,
7
የሰው ሀብት ሥራ አመራር ተግባር
ለመፈጸም ወይም ለመፍቀድ ወሲብን
እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ፣
3. የጾታ አገላለጽ
ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸው ሴት ጾታንም ያካትታል፡፡
4. የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ አዋጅ “የመንግሥት መሥሪያ ቤት” እና “የመንግሥት ሠራተኛ” በሚል ትርጉም በሚሸፈኑ መሥሪያ ቤቶችና ሠራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት የመንግሥት መሥሪያ ቤት አደረጃጀት፣ የሥራ
ምዘና፣ የደመወዝ ስኬል እና አበል
5. የመንግሥት መሥሪያ ቤት አደረጃጀት
1. ማንኛውም የክልሉ መንግሥት
መሥሪያ ቤት የተቋቋመለትን ዓላማ
ስኬታማ ለማድረግ የሚያስፈልገውን
አደረጃጀትና የሰው ኃይል ፍላጎት
አጥንቶ ለቢሮው አቅርቦ ያስወስናል፡፡
2. ቢሮው የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ
መሥሪያ ቤቶችን አደረጃጀት
አግባብነትና ውጤታማነት እያጠና
ማሻሻያ ሲያስፈልግ ለክልሉ
መስተዳደር ምክር ቤት ለውሳኔ
ያቀርባል፡፡
redeployment, training, education,
benefits or for executing or
authorizing any human resource
management act.
3. Gender Expression
Any expression in the masculine gender
shall also include the feminine gender.
4. Scope of Application
This proclamation shall be applicable on
"government institutions" and; "civil
servants" covered by the definition given
under article of this proclamation.
SECTION TWO
Organizational Structure of government
institution, Job Evaluation, Salary Scale
and Allowance
5. Organizational Structure of
government institution
1. Any government institution of the
Region shall undertake studies and
decide its own organizational
structure and staffing plan to enable
it to achieve its goals.
2. The Bureau shall undertake studies
on the appropriateness and
effectiveness of the organization of
the Region executive organs
andsubmit reorganization proposals
to the Council of Region where
necessary.
8
6. የሥራ ምዘና
1. ቢሮው በአገር አቀፍ ደረጃ በሚወሰነው
ተስማሚ የሥራ ምዘና ዘዴን
በመንግሥት መሥሪያ ቤት ተግባራዊ
እንዲሆን ያደርጋል፡፡
2. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
ደረጃቸው ያልተወሰነላቸው አዳዲስ
የሥራ መደቦችን የሥራ ዝርዝር
አዘጋጅቶ ለቢሮው በማቅረብ
ደረጃቸውን ያስወስናል፡፡
3. የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን በሀገር
አቀፍ ደረጃ በሚወሰነው ስርዓት ላይ
ተመሥርቶ የክልል መስተዳድር ምክር
ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡
7. ደመወዝ ስኬል
1. የክልሉ መንግሥት ልማት ድርጅቶችና
በክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት በልዩ
ሁኔታ የሚቋቋም ተቋም ሠራተኞች
የደመወዝ ስኬል የመንግሥትን
የፋይናንስ አቅም፣ የህዝቡን አጠቃላይ
የኑሮ ሁኔታ፣ የሥራ ደረጃዎች እና
አግባብነት ያላቸውን ሌሎች
ሁኔታዎችን ባገናዘበ መንገድ በየጊዜው
እያጠና በክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት
የሚወሰን ይሆናል፡፡
6. Job Evaluation
1. The Bureau shall adopt appropriate
job evaluation methods and enforce
the implementation of same in
government institutions.
2. Any government institution shall
prepare job descriptions for new
positions and submit same to the
Bureau for grading.
3. Job evaluation and grading shall be
conducted in accordance with
sytems to be issued in the National
level and shall be decided by the
Regulation issued by the council of
the Region.
7. Salary Scale
1. The salary scale applicable to civil
servants shall be determined from
time to time by considering the
Government’s financial capability,
the general living conditions of the
society, price levels and other
relevant factors for the Region
Government Development
Institutions and the Institution
established by the Council of the
Region.
9
2. ቢሮው አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው ጊዜ
ከሚመለከታቸው የመንግሥት
መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር
የደመወዝ ስኬል በማጥናትና ሙያዊ
አስተያየት ለክልሉ መስተዳደር ምክር
ቤት ለውሳኔ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም
አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፡፡
3. የደመወዝ ስኬል ለእያንዳንዱ ደረጃ
መነሻና መድረሻ ደመወዝ፣ እንዲሁም
በየጊዜው የሚደረገውን የደመወዝ
ጭማሪ የሚያመለክቱ እርከኖች
ይኖሩታል፡፡
8. ለእኩል ሥራዎች እኩል ደመወዝ ስለመክፈል፣
እኩል ዋጋ ያላቸው ሥራዎች ሁሉ እኩል መነሻ ደመወዝ ይኖራቸዋል፡፡
9. የደመወዝ ክፍያ
1. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
በየወሩ መጨረሻ ለሠራተኞቹ ወይም
ለሕጋዊ ወኪሎቻቸው የደመወዝ ክፍያ
ይፈጽማል፡፡
2. የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
ደመወዝ ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ
የሚችለው፡-
ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሑፍ
ሲገልጽ፣
ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣
2. The bureau shall, in collaboration
with the concerned government
institutions, upon undertaking studies
prepare salary scale and submits to
the Council of Region, and supervise
its proper implementation upon
approval.
3. The salary scale shall contain the
base, maximum pay and step
increments of each grade.
8. Equal Pay for Equal Work
All positions of equal value shall have equal
base salary.
9. Payment of Salary
1. Any Government office, shall, at the
end of every month, make payments of
salary to civil servants or their legal
representatives.
2. The Salary of a civil servant shall not
be attached or deducted except in
accordance with:
a) a written consent of the civil
servant;
b) court order; or
10
ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት
ሲወሰን ብቻ ነው፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2(ለ) ወይም
(ሐ) መሠረት ከሠራተኛ ደመወዝ በየወሩ
የሚቆረጠው ከደመወዙ አንድ ሦስተኛ
አይበልጥም፡፡
10.አበል
1. ማንኛውም አበል የሚከፈለው
የመንግሥትን ሥራ ለማከናወን አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡
2. ቢሮው ከመንግሥት መስሪያ ቤቶች
የሚቀርቡ የአበል ዓይነቶችን እና
ክፍያዎችን እያጠና ለክልሉ መስተዳደር
ምክር ቤት ለውሳኔ ያቀርባል፣ ሲፈቀዱም
አፈጻጸማቸውን ይቆጣጠራል፡፡
ክፍል ሦስት
የሰው ሀብት ዕቅድ፣ ስምሪት እና የሥራ
አፈጻጸም ምዘና
ንኡስ ክፍል አንድ
ምልመላና መረጣ
11. የሰው ሀብት ዕቅድ
1. የሰው ሀብት ዕቅድ ዓላማ ማንኛውም
የመንግሥት መሥሪያ ቤት በስትራቴጂያዊ
ዕቅድ ላይ የተቀመጡትን ዓላማዎች
ለማሳካት የሰው ሀብት ፍላጎት
c) the provisions of the law.
3. Monthly deductions from the salary of
civil servant to be made pursuant to
Sub-Article (l) (b) or (c) of this Article
shall not exceed one third of his
salary.
10. Allowances
1. Any allowance shall be paid only
for the purpose of carrying out the
functions of the civil service.
2. The Bureau shall undertake studies
on the types and payment of various
allowances and submit the same to
the Council of Region and, upon
approval, supervise their
implementation.
SECTION THREE
Human Resource Planning,
Deplyment and Performance
Evaluation
Sub- Section One
Recruitment and Selection
11. Human Resource Planning
1. The purpose of Human Resource
Planning shall be to enable a
government institution to take measure
to meet the objective specified in the
strategic plan, to forecast its human
11
ለመተንበይ፣ የሚያስፈልገውን የሰው ሀብት
በዓይነትና በብዛት ለማሟላት፣ ለማልማት፣
በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዙ
እርምጃዎችን ለመውሰድና ውጤቱንም
በየጊዜው እየገመገመ ማሻሻያ ለማድረግ
ነው፡፡
2. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
ስትራቴጂያዊ ዕቅዱን መሠረት በማድረግ
የአጭር፣የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የሰው
ሀብት ዕቅዱን አጥንቶ ተግባራዊ ማድረግ
አለበት፡፡
3. ክፍት የሥራ መደቦችን በሠራተኛ
ማስያዝ የሚቻለው የሰው ሀብት ዕቅድን
መሠረት በማድረግ በደረጃ ዕድገት ወይም
በቅጥር ወይም በዝውውር ወይም
በድልድል ይሆናል፤ ዝርዝሩ በመመሪያ
ይወሰናል፡፡
12. ወደ መንግሥት መሥሪያ ቤት የመግቢያና የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት
1. ቢሮው በክፍት የሥራ መደቦች ላይ
አመልካቾች ተወዳድረው ስለሚቀጠሩበትና
ስለሚያድጉበት የመግቢያና የብቃት
ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችሉ
መመዘኛዎችና መለኪያዎች በአገር አቀፍ
ደረጃ የሚዘጋጀውን ተከትሎ በክልሉ
በሚገኙ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች
ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
resource demand, to acquire human
resource in the right number and type,
to develop and properly utilize it,
monitor and evaluate its result and
make corrective measures from time to
time.
2. Any government institution based on
itsstrategic plan shall prepare and
implement short, medium and long
term human resource plan.
3. Vacant positions shall be filled through
promotion or recruitment ortransfer or
redeployment in accordance with
human resource plans.
12. Eligibility to Join Government
Institution and Competence Certification
System
1. The Bureau shall prepare national
criteria and parameters to establish
eligibility and competency
certification system whereby
candidates for vacant positions shall
be recruited and promoted on the basis
of competition in government
institutions of the Region.
12
2. መመዘኛዎቹና መለኪያዎቹ ሥራ ላይ
ስለሚውሉበት ሁኔታ የክልሉ መስተዳደር
ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1)
የተመለከተውን የመግቢያና የብቃት
ማረጋገጫ ሥርዓትን የሚያስፈጽም ተቋም
ሊቋቋም ይችላል፡፡
13. ምልመላና መረጣ
1. የመንግሥት የሠራተኛ ቅጥር
የሚፈጸመው በክልል ደረጃ በሚወጣው
መመዘኛ በሚሰጠው የፈተና ውጤት
ወይም በሌላ ማናቸውም ዓይነት
ተጨባጭ የሙያና ሥራ ብቃት ማረጋገጫ
ላይ ብቻ ተመስርቶ ይሆናል፡፡
2. በብሔረሰብ፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣
በፖለቲካ አመለካከት፣ በአካል ጉዳት፣
በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ወይም በሌላም ሁኔታ
በሥራ ፈላጊዎችም ሆነ በመንግሥት
ሠራተኞች መካከል ልዩነት ማድረግ
የተከለከለ ነው፡፡
3. በአዋጁ ከአንቀጽ 47 እስከ 50 የተጠቀሱት
አዎንታዊ ድጋፍ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ
ሆነው በክፍት የሥራ መደብ ላይ ሠራተኛ
የሚመደበው ለሥራ መደቡ የሚጠየቀውን
ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟላና ከሌሎች
ተወዳዳሪዎች ጋር ተወዳድሮ ብልጫ
2. The criteria and parameters shall be
implemented in accordance with
regulations to be issued by the Council
of Region.
3. An institution may be established for
the implementation of the eligibility
and competency certification system
referred to in sub-article (1) of this
Article.
13. Recruitment and Selection
1. Any type of recruitment of a civil
servant shall be affected only on the
result of examination conducted on
the basis of nationally set criteria or
on the basis of any other type of
objective certification of professional
and occupational competence.
2. There shall be no discrimination
among job seekers or civil servants
infilling vacancies because of their
ethnic origin sex, religion, political
outlook, disability, HIVIAIDS or any
other ground.
3. Without prejudice to the provisions of
Article 47 to 50 of this Proclamation,
vacant position shall be filled only by
a person who meets the qualification
required for the position and scores
higher than other candidates.
13
ያለው ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡
14. የመንግሥት ሠራተኛ ሆኖ ለመቀጠር የማያስችሉ ሁኔታዎች፣
1. የሚከተሉት የመንግሥት ሠራተኛ
ሆነው ሊቀጠሩ አይችሉም፤
ሀ) ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ
ሰው፤
ለ) ቅጣቱ ከተፈጸመ፣ በይርጋ ከታገደ
ወይም በይቅርታ ከተሠረዘ በኋላ
አምስት ዓመት ያለፈው ካልሆነ
በስተቀር የሙስና፣ የእምነት
ማጉደል፣ የስርቆት፣ የማጭበርበር
ወይም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል
ፈጽሞ ፍርድ ቤት የተፈረደበት ሰው፤
ሐ) የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ የሌለው
ሰው፤
መ) በአዋጁ አንቀጽ 17 መሠረት ቃለ
መሀላ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው፣
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1)(ለ)
ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ከማንኛውም
የመንግሥት መሥሪያ ቤት በአዋጁ
አንቀጽ 85 መሠረት በዲስፕሊን
ጉድለት ምክንያት ከሥራ የተሰናበተ
ሰው ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ
አምስት ዓመት ከመሙላቱ በፊት
በመንግሥት ሠራተኛነት ሊቀጠር
አይችልም፡
15. Ineligibility
1. The following shall not be eligible
to be civil servants;
a) a person under the age of 18
years;
b) any person who has been
convicted by a court of
competent jurisdiction of
breach of trust, theft, or fraud;
c) a person having no certificate
of competence;
d) any person who is unwilling to
take oath fidelity according to
Article 18 of this Proclamation.
2. Without prejudice to sub-article (1)
(b) of this Article, a person whose
service is terminated from any
government institution on grounds of
disciplinary offence in accordance
with Article 85 of this Proclamation
shall not be recruited before the lapse
of five years from the date of
termination of him.
14
3. በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ (1)(ሐ)
ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም
አመልካች በመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ
ለማገልገል ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ
ከኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ምርመራ በስተቀር
የጤንነት ማረጋገጫ የሕክምና ምርመራ
እና በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1)(ለ)
ከተጠቀሱት ወንጀሎች ነጻ መሆኑን
የሚያረጋግጥ ከፖሊስ የተሰጠ ማስረጃ
የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
4. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1)(ሀ)
ቢኖርም ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ
የሆናቸውና አሥራ ስምንት ዓመት
ያልሞላቸው ወጣቶች ስለሚቀጠሩበትና
ስለሥራ ሁኔታቸው ቢሮው መመሪያ
ያወጣል፡፡
15.የውጭ አገር ዜጎች ቅጥር
ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎችን
በተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ
በወጣው አዋጅ ቁጥር 270/1994 አንቀጽ
5(2) እና የዚህ አዋጅ አንቀጽ 21(2)
እንደተጠበቁ ሆነው ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ
ያልሆነ ሰው በመንግሥት ሠራተኛነት
ሊቀጠር አይችልም፡፡
3. Without prejudice to sub-article
(1)(c)of this Article, any candidate
shall submit medical certificate,
except HIV1AIDS test, to prove his
fitness for service and written
testimony of police to prove that he
has no record of crimes referred to in
sub-article (1)(b)of this Article.
4. Notwithstanding sub-article (1)(a) of
this Article, the Bureau may issue
directives on circumstances in which
young persons above the age of 14
and under 18 may be recruited as
civil servants and on the conditions
of work applicable to them.
15. Employment of Foreigners
Without prejudice to Article5(2) of
the Proclamation providing Foreign
Nationals of Ethiopian Origin with
Certain Rights to be Exercised in
their
Country of Origin under
Proclamation No 270/2002 and
Article 21(2) of this
Proclamation, a person who is not an
Ethiopian national may not be
eligible to be a civil servant.
15
16. ማስታወቂያ ስለማውጣትና ስለቅጥር አፈጻጸም
1. ማንኛውም የክልሉ መንግሥት መሥሪያ
ቤት ክፍት ሥራ ቦታ ሲኖረው
ማስታወቂያ በማውጣት አመልካቾች
እንዲመዘገቡ መጋበዝ አለበት፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ
ቢኖርም ማንኛውም የመንግሥት
መሥሪያ ቤት በገበያ ላይ እጥረት
ባለባቸው ሙያዎች ከከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር
ምሩቃንን በመጋበዝ በማወዳደር ቅጥር
መፈጸም ይችላል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (2)
መሠረት የሚቀጠሩ ምሩቃን በአዋጁ
አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ (1)(ሐ)
የተመለከተውን የብቃት ማረጋገጫ
ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥር
አፈጻጸም ዝርዝር ሁኔታ ቢሮው
መመሪያ ያወጣል፡፡
17. ቃለ መሐላ
የተመረጠው አመልካች ሥራ ከመጀመሩ
በፊት የሚከተለውን ቃለ መሐላ
ይፈጽማል፤
“እኔ ---------------------- በመንግሥት
ሠራተኛነቴ ከሁሉም በላይ አድርጌ
16. Vacancy Announcement and
Recruitment Procedures
1. Any government institution of the
Region shall advertise every vacant
position to invite candidates to apply
for the position.
2. Notwithstanding Sub-Article /1/ of this
Article, whenever there is shortage of
professionals in the labour market,
government institution maysolicit
graduates of higher educational
institutions for recruitment in
cooperation with the institutions.
3. Graduates to be recruited pursuant to
sub-article (2) of this Article shall
berequired to present certificates of
competence referred to in sub-article
(1) (c) of Article 14 of this
Proclamation.
4. The Bureau shall issue directives on
detailed recruitment procedures.
17. Oath of Fidelity
The selected candidate shall, before
commencement of his work, take the
following oath of fidelity:
"I _______being a civil servant
solemnly swear to sincerely,
faithfully and ethically serve the
16
በእውነት፣ በታማኝነትና ሥነ-ምግባር
ሕዝብን ለማገልገልና የመንግሥትን
ፖሊሲዎች ለመፈጸም፣ በማንኛውም
ጊዜ ሕገ መንግሥቱንና የአገሪቱን
ሕጎች ለማክበር እና በሥራዬ
ምክንያት ያወቅሁትንና በሕግ ወይም
በሚመለከተው አካል ውሳኔ
በምስጢርነት የተመደቡትን ለሌላ
ለማንኛውም ወገን ላለመግለጽ ቃል
እገባለሁ፡፡”
18. የመቀጠሪያ ደመወዝ አወሳሰን
ማንኛውም አዲስ ተቀጣሪ የመንግሥት
ሠራተኛ በመንግሥት ሠራተኞች
የደመወዝ ስኬል መሠረት ለተቀጠረበት
የሥራ መደብ የተወሰነው ደረጃ መነሻ
ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡
19.የሙከራ ጊዜ
1. የሙከራ ጊዜ ዓላማ አዲስ የተቀጠረ
የመንግሥት ሠራተኛ ስለሥራ
አፈጻጸሙ ክትትል እየተደረገ
ብቃቱን ለማረጋገጥ ይሆናል፡፡
2. የተመረጠው አመልካች የሥራ
መደቡን መጠሪያ፣ የተመደበበትን
ደረጃ፣ ደመወዙንና ሥራውን
የሚጀምርበትን ቀን የሚገልጽ
በአሠሪው መሥሪያ ቤት የበላይ
ኃላፊ ወይም ሠራተኛን ለመቅጠር
people and execute government
policy, and to respect at all times the
Constitution and the laws of the
Country and not to disclose to any
party information that is revealed to
me by reason of myduties and is
classified as confidential by law or
decision of the appropriate body."
18. Determination of Starting Salary
Any newly appointed civil servant
shall be paid the base salary as fixed
by the civil service salary scale for
the position he has been appointed.
19. Probation
1. The purpose of probation shall be to
prove the competence of a newly
appointed civil servant through follow-
up of his performance.
2. The selected candidate shall be served
with a letter of probation recruitment
signed by the head or any other
authorized official of the government
institution, stating the title and grade of
his position, his salary, and date of
17
ውክልና በተሰጠው የሥራ ኃላፊ
የተፈረመ የሙከራ ቅጥር ደብዳቤ
በሥራ መደቡ ከሚያከናውነው
የሥራ ዝርዝር መግለጫ ጋር
ይሰጠዋል፡፡
3. የሠራተኛው የሙከራ ጊዜ
በተቀጠረበት የሥራ መደብ ላይ
ለስድስት ወር ሆኖ የሥራ አፈጻጸም
ምዘና ውጤቱ ከመካከለኛ በታች
ሆኖ ከተገኘ የሙከራ ጊዜው
ለተጨማሪ ሦስት ወር ሊራዘም
ይችላል፡፡
4. በተራዘመው የሙከራ ጊዜ ውስጥ
ሠራተኛው መካከለኛ ወይም ከዚያ
በላይ የተጠቃለለ የሥራ አፈጻጸም
ምዘና ውጤት ካላገኘ ከሥራ
ይሰናበታል፡፡
5. የአዋጁ አንቀጽ 59(3) እና (4)
ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው
በሙከራ ላይ ያለ የመንግሥት
ሠራተኛ በሥራ ምክንያት በሚመጣ
በሽታ ወይም በሥራ ላይ በሚደርስ
አደጋ ምክንያት ከሥራ የቀረ
እንደሆነ ያልጨረሰውን የሙከራ
ጊዜ ከሕመሙ ወይም ከጉዳቱ
ከዳነበት ጊዜ አንስቶ እንዲጨርስ
ይደረጋል፡፡
6. በሙከራ ላይ የሚገኝ የመንግሥት
commencement of his job together with
job descriptions of his position.
3. The period of probation of a civil
servant on the position of his
appointment shall be for six months;
provided however, if the performance
result is below satisfactory, it may be
extended for an additional period of
three months.
4. The' service of a probationary civil
servantshall be terminated where the
performanceevaluation result is below
satisfactory for the extended period of
probation.
5. Where the civil servant on probation is
absent from his work due to
employment injury and without
prejudice to the provisions of sub
Articles (3) and (4) of Article 59 of this
proclamation, he shall be allowed to
complete the remaining probation
period following the date of his
recovery.
6. Where the civil servant on probation
18
ሠራተኛ ከአቅም በላይ በሆነ
ምክንያት ከአንድ ወር በታች
በሥራው ላይ ካልተገኘ በሥራው
ላይ የተገኘበት ጊዜ ብቻ ታስቦ
የሥራ አፈጻጸም ይሞላለታል፡፡
7. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5)
ድንጋጌ ቢኖርም በወሊድ ምክንያት
ከአንድ ወር በላይ በሥራዋ ላይ
ያልተገኘች የሙከራ ሠራተኛ
የወሊድ ፈቃዷ እንደተጠናቀቀ
የሙከራ ጊዜ እንድትጨርስ
ይደረጋል፤ ሆኖም በሙከራ ሥራዋ
ላይ ያልተገኘችበት ጊዜ ከአንድ ወር
በታች ከሆነ የሥራ አፈጻጸም ምዘና
ውጤቷ በሥራ ላይ በቆየችበት ጊዜ
ታስቦ ይሞላላታል፡፡
8. በሌላ ሕግ ካልተደነገገ በስተቀር
በሙከራ ላይ ያለ የመንግሥት
ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ
የመንግሥት ሠራተኛ ያለው
መብትና ግዴታ ይኖረዋል፡፡
9. በሙከራ ላይ ያለን የመንግሥት
ሠራተኛ የሥራ አፈጻጸም ወቅቱን
ጠብቆ ያልሞላ የሥራ ኃላፊ
በዲሲፕሊን ተጠያቂ ይሆናል፡፡
period is absent due to force majeure
for a period less than one month, the
performance evaluation will cover only
the period in which he was present at
work.
7. Notwithstanding the provision of sub-
Article (5) of this Article, a civil servant
on probation is absent due to maternity
leave, for a period of more than one
month,' she shall be allowed to
complete the remaining probation
period following the end of her
maternity leave. However, that if her
absence is less than a month, her
evaluation will cover only the period in
which she was present at work.
8. Unless otherwise provided in this
Proclamation, a probationary civil
servant shall have the same rights and
obligations with that of a civil servant
who has completed his probation.
9. Any officer who fails to timely evaluate
the performance of a probationary civil
servant shall be liable to disciplinary
penalty.
19
20. ቋሚ የመንግሥት ሠራተኛ ስለመሆን
1. በሙከራ ጊዜው መካከለኛ ወይም ከዚያ
በላይ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት
ያስመዘገበ የመንግሥት ሠራተኛ በቋሚነት
መቀጠሩን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ
ይሰጠዋል፡፡
2. በሙከራ ላይ የሚገኝ የመንግሥት
ሠራተኛ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት
ጊዜውን ጠብቆ ያልተሞላለት እንደሆነ
በአዋጁ አንቀጽ 19(3) እና (4)
የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ
ሆነው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሥራ
አፈጻጸም ምዘና እንዲሞላ ተደርጎ
ለሙከራ ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ ቋሚ
የመንግሥት ሠራተኛ ይሆናል፡፡
21. ጊዚያዊ ሠራተኛ ስለመቅጠር
1. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የመንግሥት
መሥሪያ ቤት ጊዚያዊ ሠራተኛ ሊቀጥር
የሚችለው የዘላቂነት ባሕርይ በሌለው
ሥራ መደብ ላይ ነው፤ ሆኖም ሁኔታዎች
ሲያስገድዱ በቋሚ የሥራ መደብ ላይ
ጊዚያዊ ሠራተኛ መቅጠር ይችላል፡፡
2. አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ከፍተኛ
ባለሙያ ለሚጠይቅ ማናቸውም ክፍት
የሥራ መደብ በደረጃ ዕድገት፣ በዝውውር
20. Permanent Appointment
1. Where the civil servant on probation
has recorded satisfactory or above
satisfactory performance result, a
letter of permanent appointment
shall be issued to a civil servant.
2. If performance evaluation result of the
civilservant. on probation is not
evaluated before the expiry date of the
probation period and without prejudice
to the responsibility of the official
concerned, the performance ,evaluation
shall be carried out within one month
following the probation period.
21. Temporary employment
1. Without prejudice to Sub- Article 2 of
this Article, a government institution
may appoint a temporary civil servant
only for a job which is not of a
permanent nature, provided, however,
that a government office may, where
circumstances so require, appoint a
temporary civil servant to a permanent
position.
2. A government office may appoint a
foreign national on temporary bases,
where it is proved that it is impossible
to filI a vacantposition that requires
20
ወይም በቅጥር ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
ለማግኘት የማይቻል መሆኑን በማረጋገጥ
የውጭ አገር ዜጋ በጊዚያዊነት ሊቀጥር
ይችላል፡፡
3. ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ አገር ዜጋ
ጊዚያዊ ሠራተኞች አቀጣጠር፣
የሚኖራቸው መብቶችና ግዴታዎች
እንዲሁም ስለሚጠበቁላቸው የሥራ
ሁኔታዎች ዝርዝር ሁኔታ የመስተዳደር
ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡
22. ሥራዎችን በውል ለሦስተኛ ወገኖች አሸጋግሮ ስለማሠራት
1. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማንኛውም
የመንግሥት መሥሪያ ቤት ቢሮውን
በማስፈቀድ የሕዝብን ጥቅም በማይጎዱ
የተወሰኑ የሥራ መደቦችን ወይም
ሥራዎችን ለግል ድርጅቶች ወይም
ለሌሎች ተቋማት በውል በማሸጋገር
እንዲሠሩ ማድረግ ይችላል፡፡
2. ለግል ድርጅቶችና ለሌሎች ተቋማት
በውል ሊሸጋገሩ ስለሚችሉ ሥራዎች
ቢሮው ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ
ያወጣል፡፡
high level professional by an
Ethiopian through promotion, transfer
or recruitment.
3. The appointment of temporary
employee of an Ethiopian or a foreign
national, their rights and obligations as
well as the conditions of work
applicable to them shall be prescribed
by regulation to be issued by the
Council of Region.
22. Outsourcing
1. Where necessary and upon obtaining
the permission of the Ministry, any
government institution may outsource
certain positions or tasks, that would
not compromise public interest, to
private enterprises or to other
institutions.
2. The Bureau shall issue detailed
directives regarding positions and tasks
that may be outsourced to private
enterprises or other institutions.
21
ንኡስ ክፍል ሁለት
የደረጃ ዕድገት
23. የደረጃ ዕድገት ዓላማ
የደረጃ ዕድገት ዓላማ ሥራው ብቃት ባለው
ሠራተኛ እንዲከናወን ለማስቻል፣
የመሥሪያ ቤቱን የሥራ ውጤት ለማሻሻል
እና ሠራተኛውን ለማበረታታት ነው፡፡
24. የደረጃ ዕድገት አሰጣጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ለደረጃ እድገት ለመወዳደር በአዋጁ አንቀጽ 12(1) መሠረት የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
2. የሙከራ ጊዜውን ያላጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ ለደረጃ ዕድገት መወዳደር አይችልም፡፡
3. የደረጃ ዕድገት ስለሚሰጥበት ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች ቢሮው በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡
ንኡስ ክፍል ሦስት ዝውውርና ድልድል
25. የውስጥ ዝውውር
1. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
ለሥራው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው
ግልጽ የሆነ አሠራርን በመከተል
የመንግሥት ሠራተኛን በዚያው
በመሥሪያ ቤት ውስጥ እኩል በሆነ
Sub- Section Two
Promotion
23. Objectives Promotion shall be given for the
purpose of executing works by
competent employees, enhancing the
performance of government
institutions and for motivating
employees.
24. Selection for Promotion
1. Any civil servant shall present
certificate of competence issued
pursuant to Article 12(1) of this
Proclamation to compete for
promotion.
2. Any civil servant who has not
completed his probation period may
not compete for promotion.
3. The Bureau shall issue detailed
directives on other conditions
applicable to the promotion of civil
servants.
SUB- SECTION THREE
TRANSFER AND REDPLOYMENT
25. Internal Transfer
1. A government institution may,
whenever necessary, based on a
transparent procedure, transfer a civil
servant to another similar position of an
equal grade and salary or to another
22
የሥራ ደረጃና ደመወዝ ወደ ሌላ የሥራ
መደብ ወይም ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ
ሌላ ሥራ ቦታ በማዛወር ሊያሠራ
ይችላል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1)
የተደነገገው ቢኖርም በመሥሪያ ቤቱ
ላይ አደጋ እንዳይደርስ ለመከላከል
ወይም አደጋው ያደረሰውን ጉዳት
ለማስተካከል ሲባል ማናኛውም
የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዙ
ሳይቀነስ፣ ደረጃው ወይም የሥራው
ዓይነት ሳይጠበቅ አንድ ዓመት
ላልበለጠ ጊዜ በጊዜያዊነት አዛውሮ
ማሠራት ይችላል፡፡
3. የመንግሥት ሠራተኛ በጤና መታወክ
ምክንያት በያዘው የሥራ መደብ ወይም
ባለበት የሥራ ቦታ ላይ ሊሠራ
አለመቻሉ በሐኪም ማስረጃ ሲረጋገጥ፣
ሀ) በተመሳሳይ ደረጃ ሊመደብ
የሚችልበት ክፍት የሥራ መደብ
ካለ በያዘው ደረጃ፣ ወይም
ለ) በተመሳሳይ ደረጃ ሊመደብ
የሚችልበት ክፍት የሥራ መደብ
ከሌለና ሠራተኛው ዝቅ ባለ ደረጃ
place of work within the government
institution.
2. Notwithstanding the provisions of sub-
article (1) of this Article, a civil servant
may, without affecting his salary, be
temporarily transferred to another
position, for not more than a year,
irrespective of the grade or type of
functions where it is required to prevent
the occurrence of danger or torectify
the damages caused by such danger to
the government institution.
3. Where it is proved by a medical
certificate that a civil servant who has
completed his probation period is
unable to carry out the functions of his
position or to reside in his place of
work due to his health condition, he
shall be transferred to another suitable
position or place of work with:
a) the same grade where such vacant
position is available; or
b) a lower grade where a vacant
position of the same grade is not
available and he is willing to be
transferred to a position of lower
23
ላይ ለመሥራት ፈቃደኛ ከሆነ
ደረጃው ተቀንሶ ወደ ሚስማማው
የሥራ መደብ ወይም የሥራ ቦታ
ይዛወራል፡፡
4. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ
መደብ የተሰረዘ እንደሆነ በመሥሪያ ቤቱ
ውስጥ ተመሳሳይ ደረጃ ወዳለው የሥራ
መደብ ማዛወር ይቻላል፡፡
5. በዚህ ንዑስ አንቀጽ ሠራተኛውን
ለመመደብ በመስሪያ ቤቱ ተመሳሳይ ስራ
መደብና ደረጃ ያልተገኘ እንደሆነ ቢሮው
በሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤቶች
በሚገኙ ክፍት የስራ መደቦች ይመድባል፡፡
26.በተጠባባቂነት ማሠራት
1. ሁኔታዎች ሲያስገድዱ ማንኛውም
የመንግሥት ሠራተኛ ከአንድ ዓመት
ላልበለጠ ጊዜ ከፍ ያለ ደረጃ ባለው
የሥራ መደብ ላይ በተጠባባቂነት
እንዲሠራ ማድረግ ይቻላል፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ
ቢኖርም ከአንድ ዓመት በላይ ለሚፈጅ
ትምህርት ወይም ስልጠና የሄደን
የመንግሥት ሠራተኛ ለመተካት
ትምህርቱ ወይም ሥልጠናው
ለሚፈጀው ጊዜ ድረስ የሥራ መደቡን
ግልጽ በሆነ መስፈርት በውድድር
በተጠባባቂ ሠራተኛ ማሠራት ይቻላል፡፡
grade.
4. Where the position of a civil servant is
abolished, he shall be transferred to
another position of an equal grade
within the government institution.
5. Where the same postion and level are
not found to be assigned to this sub-
article, the Bureau shall allocate
vacancy positions in other government
offices.
26. Acting- Assignment
1. Where circumstances so require a
civil servant may be assigned to a
higher position in an acting capacity
for not more than a year.
2. Notwithstanding the provision of
sub-article (1) of this Article a civil
servant may, following transparent
and competitive procedure, be
assigned to higher position in acting
capacity to replace a civil servant
who is on education or training
program that lasts more than a year.
24
3. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
በተጠባባቂነት እንዲሠራ ሲደረግ
የተጠባባቂነት አበል ይከፈለዋል፡፡
ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል፡፡
27.ከሌላ መሥሪያ ቤት የሚደረግ ዝውውር
1. ማንኛውም የክልል መንግሥት
መሥሪያ ቤት ለሥራው አስፈላጊ ሆኖ
ሲያገኘው ግልጽ ማስታወቂያ
በማውጣትና በማወዳደር ላኪና ተቀባይ
መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ሠራተኛው
ሲስማሙ ማንኛውንም የመንግሥት
ሠራተኛ እኩል በሆነ ደረጃና ደመወዝ
ቢሮውን በማሳወቅ አዛውሮ ማሠራት
ይችላል፡፡
2. የሚመለከተው የመንግሥት ሠራተኛ
በክልሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤት እና
በየደረጃው የሚገኝ መንግሥት መሥሪያ
ቤት ሲስማሙ በክልሉ ዝውውርን
ለማጽደቅ ስልጣን የተሰጠው አካል
ሲያጸድቀው ማንኛውንም የመንግሥት
ሠራተኛ እኩል በሆነ ደረጃና ደመወዝ
አዛውሮ ማሠራት ይቻላል፡፡
3. በተመሳሳይ ደረጃ ለመቀጠር አመልክቶ
በውድድሩ የተመረጠ የመንግስት
ሠራተኛ በዝውውር ሥርዓት
3. Any civil servant assigned in an
acting capacity shall be entitled to
acting allowance. Details shall be
determined by the Directives.
27. Transfer from another
Government Institution
1. A government institution may,
whenever necessary and the recipient
and sender government institutions as
well as the civil servant so agree,
transfer a civil servant to a similar
position of equal grade and salary from
another government institution by
notifying the Bureau.
2. Where the concerned civil servant,
regional government institution and the
recipient federal government
institution so agree and when the
appropriate authority in the region
approves it, a civil servant may be
transferred from a regional government
institution to a federal government
institution to similar position of equal
grade and salary.
3. A civil servant who competed and
selected for appointment to a position
of a similar grade shall be assigned
25
እንዲመደብ ይደረጋል፡፡
4. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5)
እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አንቀጽ
መሠረት የሚዛወር ሠራተኛ የክልሉ
መንግሥት ሠራተኞች ሕግ በሚያዘው
መሠረት በያዘው የሥራ ደረጃና
በአገልግሎት ዘመኑ ምክንያት ያገኝ
የነበረው ደመወዝና መብቶቹ
አይቀነሱበትም፡፡
5. የትዳር አጋሮችን ለማገናኘት ሲባል
አንድን የመንግስት ሠራተኛ በተመሳሳይ
ደረጃና ደመወዝ፣ ተመሳሳይ ደረጃና
ደመወዝ ካልተገኘ በሠራተኛው
ስምምነት ዝቅ ባለ ደረጃ አዛውሮ
ማሰራት ይቻላል፡፡
28.የትውስት ዝውውር
1. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ላኪው የመንግሥት
መሥሪያ ቤትና ሠራተኛው ሲስማሙ
አንድን የመንግሥት ሠራተኛ በሌላ
የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም
ወይም በመንግሥት የልማት ድርጅት
ወይም መንግሥታዊ ወዳልሆኑ ድርጅቶች
ከአንድ ዓመት ለማይበልጥ ጊዜ
በትውስት ተዛውሮ እንዲሠራ ማድረግ
ይቻላል፡፡
2. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከመንግሥት
through transfer procedure.
4. Without prejudice to sub-article (5) of
this Article, a civil servant of a Region
transferred pursuant to this Article
shall not lose the salary and benefits
acquired by virtue of his grade and
service before the transfer in
compliance with the Region civil
service laws.
5. A civil servant may, for the purpose of
re-union of spouses, be transferred to a
position of equal grade and salary or,
where there is no such position and the
civil servant so agrees, to a position of
lower grade.
28. Secondment
1. A civil servant may, where it is
necessary and the government
institution and the civil servant so
agree, be seconded to another
government institution or regional
government institution or public
enterprise or non-governmental
organizations to perform a specific duty
for a period not exceeding one year.
2. Where it is necessary, any government
institution may second an employee
from public enterprise, regional
26
ልማት ድርጅት ወይም መንግሥታዊ
ካልሆነ ድርጅት ማንኛውንም ሠራተኛ
ከአንድ ዓመት ለማይበልጥ ጊዜ
በትውስት አዛውሮ ማሠራት ይችላል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1)
የተደነገገው ቢኖርም የክልል መንግሥት
በሕዝብ ላይ የሚደርስ ድንገተኛ አደጋን
ለመከላከል ወይም አደጋው ያደረሰውን
ጉዳት ለማስተካከል ሲባል ማንኛውንም
የመንግሥት ሠራተኛ በያዘው ደመወዝ
በክልሉ ከአንድ አስተዳደር እርከን ወደ
ሌላ አስተዳደር እርከን ወደሚገኝ
መንግሥት መሥሪያ ቤት ለአንድ ዓመት
ለማይበልጥ ጊዜ በትውስት አዛውሮ
ማሠራት ይችላል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት
በትውስት የተዛወረ ሠራተኛ፣
ሀ) ደመወዝና ማንኛውም ጥቅሙ
በዝውውሩ ምክንያት ሳይጓደል
በትውሰት አዛውሮ በሚያሰራው
መስሪያ ቤት ይፈጸምለታል፤
ለ) የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤቱ
በትውሰት አዛውሮ በሚያሰራው
መስሪያ ቤት ተሞልቶ ለቀጣሪው
መሥሪያ ቤት ይተላለፋል፤
ሐ)የዲሲፕሊን ጥፋት የፈጸመ እንደሆነ
government institution or non-
governmental organization for a period
not exceeding one year.
3. Notwithstanding sub-article (1) of this
Article, the Region Government may
transfer a civil servant on secondment,
without affecting his salary, to another
government institution or based on the
request of a regional state to a
government institution of such state, for
a period not exceeding one year to
prevent the occurrence of danger to the
country or the public or to rectify the
damages caused by such occurrence.
4. Where a civil servant seconded in
accordance with sub-article (1) of this
Article:
a) his salary and other benefits shall not
be affected because of his
secondment and shall be settled by
the institution to which he is
seconded;
b) his performance shall be evaluated by
the institution to which he is
seconded and be submitted to the
employer;
c) commits a disciplinary offence, the
institution to which he is seconded
27
በትውስት ተቀባዩ መስሪያ ቤት ለቀጣሪ
መሥሪያ ቤቱ ከዝርዝር ማስረጃ ጋር
ያሳውቃል፣ ቀጣሪ መሥሪያ ቤቱም
ጉዳዩን አጣርቶ እንደ አስፈላጊነቱ
ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
29. ድልድል
1. የመንግሥት መሥሪያ ቤት አዲስ
አደረጃጀት አጥንቶ ተግባራዊ ሲያደርግ
ሠራተኞቹን በማወዳደር ደልድሎ
ማሠራት አለበት፡፡
2. በማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
የሚገኝ ክፍት የሥራ መደብ ከሌላ
የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚደለደል
የመንግሥት ሠራተኛ እንዲያዝ
የሚደረገው መሥሪያ ቤቱ የተዘጋ
ወይም ትርፍ የሰው ኃይል ሲኖረው
ወይም የሥራ መደቡ የተሰረዘ ከሆነና
ድልድሉን ቢሮው ሲወስን ወይም ቢሮው
በክልሉ መንግስት ሲታዘዝ ነው፡፡
3. በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚደለደል
ሠራተኛ ቀደም ሲል ይዞት በነበረው
ደረጃና በአገልግሎት ዘመኑ ምክንያት
ያገኝ የነበረው ደመወዝና ጥቅሞቹ
አይቀነሱበትም፡፡
ንኡስ ክፍል አራት
የሥራ አፈጻጸም
30. የሥራ አፈጻጸም ምዘና
shall inform same to the employer
together with detailed evidence; and
the employer shall, upon
investigating the case, take
appropriate measure as necessary.
29. Redeployment
1. Any government institution shall
redeploy its employees on the basis of
competition when it implements a
new organizational structure.
2. The filing of a vacant position in any
government institution through
redeployment of a permanent civil
servant from another government
institution shall be made only where
the government institution is closed
or it has redundant manpower or the
position of the civil servant is
abolished and the Bureau so decides
or instructed by the Government.
3. A civil servant redeployed under this
Article shall be entitled to his
previous salary and benefits acquired
by virtue of his grade and service.
Sub- Section Four
Performance Evaluation
30. Performance Evaluation
28
1. የሥራ አፈጻጸም ምዘና ዓላማ በሥራ
እቅድ ላይ የተመሠረተ ሆኖ፣
ሀ) ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
ሥራውን በሚጠበቀው መጠን፣
ጥራት፣ ጊዜ እና ወጪ በተሟላ
ሁኔታ እንዲያከናውን ለማድረግ፣
ለ) ተከታታይ የሥራ አፈጻጸም ምዘና
በማካሄድ የመንግስት ሠራተኛውን
ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት ቀጣዩ
የሥራ አፈጻጸሙ እንዲሻሻል በማድረግ
ውጤታማ እንዲሆን ለማብቃት፣
ሐ) የመንግሥት ሠራተኛውን
የሥልጠናና የመሻሻል ፍላጎት በትክክል
ለይቶ ለማወቅ፣
መ) በውጤት ላይ የተመሠረተ ማትጊያ
ለመስጠት፣
ሠ) የመንግስት መሥሪያ ቤቱ በተጨባጭ
መረጃ ላይ ተመሥርቶ አስተዳደራዊ
ውሳኔዎችን እንዲሰጥ ለማስቻል ነው፡፡
2. በመንግስት መስሪያ ቤት የሚከናወን
የሥራ አፈጻጸም ምዘና ሥርዓት፣
ሀ)ግልጽና በተጨባጭ መረጃ ላይ
የተመሠረተ የውጤት ምዘና ለማከናወን
የሚያስችል፣
ለ) የተከናወነው ሥራ ከተመደበው
በጀት፣ ጊዜ፣ መጠንና ጥራት ጋር
1. The purpose of performance
evaluation shall, based on work plans,
be to:
a) enable a civil servant to effectively
discharge his duties in accordance
with the expected volume, quality,
time and cost;
b) to evaluate civil servants on
continuous basis and identify their
strengths and weaknesses with a
view to improve their future
performance;
c) to identify training needs of
employees;
d) to give reward based on result;
e) enable the government institution to
make its personnel administration
decisions based on facts.
2. The performance evaluation system to be
implemented by a government institution
shall:
a) enable transparent and evidence
based objective evaluation of
performance results;
b) enable the verification of actual
performance results in comparison
29
በማነጻጸር ትክክለኛውን ውጤት
ለመመዘን የሚያስችል፣
ሐ) የቡድን አሠራርንና የጋራ ተነሳሽነትን
የሚያጎልብት፣
መ) በመንግሥት ሠራተኞች ወይም
ቡድኖች መካከል ጤናማ የውድድር
መንፈስን በመፍጠር ተቋማዊ
ውጤትን ለማሻሻል የሚያግዝ፣
ሠ) በአፈጻጸም ተከታታይነትና
ተመጋጋቢነት ባላቸው ሥራዎች
መካከል አንዱ በሌላኛው ውጤት
ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ
ለመገምገም የሚያስችል፣መሆን
አለበት፡፡
3. የስራ አፈጻጸም ምዘና ቢሮው በሚያወጣው
መመሪያ መሠረት ይፈጸማል፡፡
31. የደመወዝ ጭማሪና ማበረታቻ አወሳሰን
1. የመንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ እርከን
ጭማሪ የሚያገኘው በሥራ አፈጻጸም ምዘና
ውጤት ላይ በመመስረት በየሁለት ዓመቱ
ይሆናል፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ የሥራ አፈጻጸም
ውጤትን መሰረት በማድረግ ለመንግስት
ሠራተኛ ማበረታቻ ይሰጣል፡፡
3. ቢሮው የሥራ አፈጻጸም ምዘና
ስለሚከናወንበት ሥርዓት፣ የእርከን ጭማሪ
with the planned budget, time,
volume and quality;
c) encourage team work and common
initiatives;
d) promote healthy competition among
civil servants and teams to improve
institutional performance results;
e) enable impact assessment of
performance results among
successive and interrelated tasks.
3. Performance evaluation shall be
implemented by the Directive issued
by the Bureau.
31. Salary Increment and Incentives
1. A civil servant shall be entitled to
salary step increment every two years
based on his performance evaluation
result.
2. Without prejudice to sub-article (1) of
this Article, a civil servant shall be
provided with incentive based on
performance result.
3. The Bureau shall issue detailed
directives on performan evaluation
30
እና ማበረታቻ ስለሚሰጥበት ሁኔታ ዝርዝር
የአፈጻጸም መመሪያ ያወጣል፡፡
ክፍል አራት የሥራ ሰዓትና ፍቃድ ንኡስ ክፍል አንድ
የሥራ ሰዓት
32. መደበኛ የሥራ ሰዓት
የመንግሥት ሠራተኞች መደበኛ የሥራ
ሰዓት እንደየሥራው ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ
በሳምንት ከ39 ሰዓት መብለጥ የለበትም፡፡
33. የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት
የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ መግቢያና
መውጫ ሰዓት የክልሉ መስተዳደር ምክር
ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡
34. የትርፍ ሰዓት ሥራ
1. የትርፍ ሰዓት ሥራ ለሠራ ማንኛውም
የመንግሥት ሠራተኛ በሠራተኛው ምርጫ
መሠረት የማካካሻ ዕረፍት ወይም የትርፍ
ሰዓት ክፍያ ይሰጠዋል፡፡
2. የትርፍ ሰዓት ሥራ ስለሚፈቀዱባቸው
ሁኔታዎች፣ ስለክፍያው መጠንና የማካካሻ
ዕረፍት ስለሚሰጥበት ሁኔታ ቢሮው
ዝርዝር መመሪያ ያወጣል፡፡
35.የሕዝብ በዓላት እና የሳምንት የዕረፍት ቀናት
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በሕዝብ
system, salary step increment and
provision of incentive.
SECTION FOUR
WORKING HOURS AND LEAVES
SECTION - PART ONE
WORKING HOURS
32. Regular Working Hours
Regular working hours of civil servants shall be
determined on the basis of the conditions of
work and shall not exceed 39 hours a week.
33. Office Hours
The time when the office hours of civil servants
begins and ends shall be determined by
Regulations of the Council of Region.
34. Overtime Work
1. Any civil servant who has worked
overtime is entitled to compensatory
leave or overtime pay based on his
preference.
2. The Bureau shall issue directive on
the conditions of overtime work,
amount of payment and
compensatory leave.
35. Public Holidays and Weekly Rest Day
1. Any civil servant shall incur no
31
በዓል፣ በሳምንት የዕረፍት ቀናት ወይም
በመንግሥት ውሳኔ መሥሪያ ቤቶች ዝግ
ሆነው በሚውሉበት ቀን ባለመሥራቱ
መደበኛ የደመወዝ ክፍያ አይቀነስበትም፡፡
2. የሥራው ሁኔታ አስገድዶ በሕዝብ በዓል
ወይም በመንግሥት ውሳኔ መሥሪያ
ቤቶች ዝግ ሆነው በሚውሉበት ቀን
እንዲሠራ የታዘዘ የመንግሥት ሠራተኛ
ምርጫውን መሠረት በማድረግ የትርፍ
ሰዓት ክፍያ ወይም የማካካሻ ዕረፍት
ይሰጠዋል፡፡
3. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም
የሥራው ሁኔታ አስገድዶ በሳምንት
የዕረፍት ቀናት እንዲሠራ የታዘዘ
የመንግሥት ሠራተኛ በተከታዩ ሳምንት
የሥራ ቀናት ውስጥ የማካካሻ ዕረፍት
እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
ንኡስ ክፍል ሁለት
ፈቃድ
36. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ዓላማ
1. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ የሚሰጠው
የመንግሥት ሠራተኛው ለተወሰነ ጊዜ
በማረፍ አገልግሎቱን በታደሰ መንፈስ
እንዲቀጥል ለማስቻል ነው፡፡
2. ማንኛውም አዲስ ተቀጣሪ የመንግሥት
ሠራተኛ የአስራ አንድ ወራት አገልግሎት
ከመስጠቱ በፊት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ
reduction in his regular pay on account
of having not worked on public
holiday or weekly rest day or on a day
offices are closed by the order of the
government.
2. Any civil servant ordered to work on a
public holiday or on a day government
institutions are closed by the order of
the government, due to compelling
circumstances, shall be entitled to
overtime payor compensatory leave
based on his preference.
3. Notwithstanding the provision of Sub
Article (1) of this Proclamation a civil
servant ordered to work on a weekly
rest day, due to compelling
circumstances, shall be granted a
compensatory leave during working
days of the next week.
SECTION - PART TWO
LEAVE
36. Annual Leave
1. The purpose of annual leave is to
enable a civil servant get rest and
resume work with renewed strength.
2. Any newly appointed civil servant
shall not be entitled to annual leave
before serving for eleven months.
32
የማግኘት መብት የለውም፡፡
3. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ በገንዘብ
አይለወጥም፤ ሆኖም የሠራተኛው
አገልግሎት በመቋረጡ ያልተወሰደ
የዓመት ዕረፍት ፈቃድ በገንዘብ
እንዲለወጥ ይደረጋል፡፡
37. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ቀናት
1. አንድ ዓመት ያገለገለ የመንግሥት
ሠራተኛ 20 የሥራ ቀናት የዓመት
ዕረፍት ፈቃድ ያገኛል፡፡
2. ከአንድ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ
ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት አንድ
የሥራ ቀን እየታከለበት የዓመት ዕረፍት
ፈቃድ ያገኛል፣ ሆኖም የሚሰጠው
የአንድ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ከ30
የሥራ ቀኖች መብለጥ የለበትም፡፡
3. በሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ቀደም
ሲል የተሰጠ አገልግሎት በዚህ አንቀጽ
ንዑስ አንቀጽ (2) አፈጻጸም የሚታሰብ
ይሆናል፡፡
38. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ አሰጣጥ፤
1. የዓመት ዕረፍትፈቃድ የመሥሪያ ቤቱን
ዕቅድ መሠረት በማድረግና በተቻለ
መጠን የሠራተኛውን ፍላጎት በማመዛዘን
በሚዘጋጀውና ሠራተኛውም
እንዲያውቀው በሚደረግ ፕሮግራም
መሠረት በበጀት ዓመቱ ውስጥ
3. There shall be no payment in lieu of
annual leave; provided, however, that
payment may be made for unused
annual leave due to termination of
appointment.
37. Duration of Annual Leave
1. A civil servant shall be entitled to
annual leave of 20 working days for
his first year of service.
2. A civil servant having a service of
more than a year shall be entitled to
additional leave of one working day
for every additional year of service;
provided, however, that the duration
of annual leave shall not exceed 30
working days.
3. Previous service rendered in any
government institutions shall be
considered for the application of
Sub Article (2) of this Article.
38. Granting of Annual Leave
1. Annual leave. shall be granted within
the budget year in accordance with a
leave made known to the civil
servants and leave made and prepared
on the basis of due consideration of
the interest of the government office
33
ይሰጣል፡፡
2. ሠራተኛው የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን
በሚወስድበት ጊዜ በዕረፍት ላይ
የሚቆይበትን የወር ደመወዙን በቅድሚያ
ሊወስድ ይችላል፡፡
3. የአዋጁ አንቀጽ 36(2) እንደተጠበቀ
ሆኖ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ አስራ
አንድ ወሩን ካጠናቀቀ በኋላ ባገለገለበት
በጀት ዓመት ለሰጠው አገልግሎት
የዓመት ዕረፍት ፈቃዱ በአገልግሎቱ
መጠን ተሰልቶ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
4. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የበጀት
ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት የዕረፍት
ፈቃድ ወስዶ አገልግሎቱን በራሱ ፈቃድ
ያቋረጠ የመንግስት ሰራተኛ አገልግሎት
ያልሰጠበት ጊዜ ታስቦ በፈቃድ ላይ እያለ
የተከፈለውን ደመወዝ እንዲመልስ
ይደረጋል፡፡
39. የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ማስተላለፍ
1. የአዋጁ አንቀጽ 38(1) ድንጋጌ ቢኖርም የሥራው ሁኔታ በማስገደዱ ምክንያት መሥሪያ ቤቱ ለሠራተኛው የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን በበጀት ዓመቱ ውስጥ ሊሰጠው ያልቻለ እንደሆነ የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ከሁለት የበጀት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሊያስተላልፈው ይችላል፣ ሆኖም ያልተጠቀመበት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ በሦስተኛው በጀት ዓመት ለሠራተኛው መሰጠት አለበት፡፡
and, as much as possible, the
preference of each civil servant.
2. A civil servant shall be entitled to
advance payment of his monthly
salary at the time of taking his annual
leave.
3. Without prejudice to the provisions of
Article 36(2) a civil servant after the
completion of 11 months shall be
granted annual leave based on the
service rendered.
4. A civil servant who resigns after
taking his annual leave in accordance
with Sub Article (1) of this Article
before the end of the budget year
shalI be liable to pay back part of
theadvance salary for which he has
not rendered servIce.
39. Postponement of Annual Leave
1. Notwithstanding the provisions of
Article 38(1) of the Proclamation, the
head of a government institution may
authorize the postponement of annual
leave for two budget years, where the
government office, due to compelIing
reasons, is unable to grant a civil servant
his annual leave within the same budget
year; provided however, that the
34
2. የአዋጁ አንቀጽ 36(3) ድንጋጌ ቢኖርም
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የዓመት ዕረፍት ፈቃዱ ለሚተላለፍበትና ፈቃዱ በገንዘብ ተለውጦ እንዲሰጠው ለሚጠይቅ ሠራተኛ በጀት በቅድሚያ በማስያዝ ከተላለፈው የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ውስጥ የመጀመሪያውን የአንድ ዓመት ዕረፍት ፈቃድ ብቻ በገንዘብ ተለውጦ እንዲሰጠው ማድረግ አለበት፡፡
3. የአንድ መንግሥት ሠራተኛ የዓመት
ዕረፍት ፈቃድ በገንዘብ ሲለወጥ የሠራተኛው የአንድ ቀን ደመወዝ የሚታሰበው ያልተጣራ የወር ደመወዙን በ30 ቀናት በማካፈል ነው፡፡
40. ያልተወሰደ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ
1. የመንግሥት ሠራተኛው አገልግሎት
በመቋረጡ ያልተወሰደ የዓመት ዕረፍት
ፈቃድ የሥራ ቀናቶች ብቻ ታስበው
በገንዘብ ተለውጦ ይሰጠዋል፡፡
2. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ በአዋጁ
አንቀጽ 25 መሠረት ለተዛወረ ወይም
በአንቀጽ 28(2) መሠረት ለተደለደለ
የመንግሥት ሠራተኛ ተፈፃሚ
አይሆንም፤ ሆኖም ሠራተኛው በነበረበት
የመንግሥት መሥሪያ ቤት የአዋጁ
አንቀጽ 39(1) መሠረት የተላለፈለት
accumulated leave shall be granted to the
civil servant in the third budget year.
2. Notwithstanding the provisions of
Article 36(3) of this Proclamation, a
civil servant whose annual leave is
postponed for two years in accordance
with sub-Article (1) of this Article may
claim payment, and the government
institution shall make the payment
forthe first year of the accumulated
annual leave from a budget alIocated for
such purpose.
3. Where payment is made to a civil
servant in lieu of his accumulated leave,
his daily salary shall be calculated by
dividing his monthly salary by 30 days.
40. Unused Annual Leave
1. Where the appointment of a civil
servant is terminated, payment shall be
made to the civil servant for the number
of working days of unused annual
leaves.
2. The provision of Sub Article (1) of this
Article shall not apply to the civil
servant transferred under Article 28(2)
of this Proclamation or redeployed
under Article 25 of this Proclamation.
However, unused leave that had been
postponed as specified under article 39
35
የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወደ ተዛወረበት
ወይም ወደ ተደለደለበት የመንግሥት
መሥሪያ ቤት ይተላለፍለታል፡፡
41.የወሊድ ፈቃድ
1. ነፍሰ ጡር የሆነች የመንግሥት
ሠራተኛ፣
ሀ) ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ
ምርመራ ለማድረግ ሐኪም
በሚያዘው መሠረት ደመወዝ
የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፤
ለ)ከመውለዷ በፊት ዕረፍት
እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ
የሚከፈልበት ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው
ፈቃድ እንደ ህመም ፈቃድ
አይቆጠርም፡፡
3. ነፍሰ ጡር የሆነች የመንግሥት
ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ
እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን
በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ
ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ
ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ
ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ
ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ
ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
(1) of this Proclamation will be
transferred to the government
institution to which he is transferred
or redeployed.
41. Maternity Leave
1. A pregnant civil servant shall be
entitled to:
a) paid leave for medical examination
in accordance with a doctor's
recommend dation;
b) paid leave before delivery if
recommended by a doctor.
2. The leave referred to in sub-article (1)
of this Article shall not be considered as
sick leave.
3. A pregnant civil servant shall be
entitled to a period of 30 consecutive
days of prenatal leave preceding the
presumed date of her confinement and a
period of 90 consecutive days after her
confinement, in total 120 days of
maternity leave with pay.
36
4. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት
ሠራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ
ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች
ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ
ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ
እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡
5. ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ
ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ
እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት
የሥራ ቀናት የምትቆይበት ዕረፍት
በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ዕረፍት
ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት
ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው
የበጀት ዓመት የዕረፍት ፈቃዷ
ይተካል፡፡
6. ሠራተኛዋ በዚህ ንዑስ አንቀጽ (3)
የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች
በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ
የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም
ከተረጋገጠ በአዋጁ አንቀጽ 42(1)
በተደነገገው መሠረት የሕመም ፈቃድ
መውሰድ ትችላለች፡፡
7. ማንኛውም ስድስት ወር የሞላት
ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሠራተኛ
የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ
በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ
ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ
ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ
4. If the pregnant civil servant delivers
before the completion of the prenatal
leave which is granted under sub-article
(3) of this Article, the unused prenatal
leave shall be granted after her
confinement.
5. If the pregnant civil servant does not
deliver on the presumed date, the days
subsequently taken before her
confinement shall be replaced by the
annual leave she is entitled to within the
budget year or that of the following
budget year if no annual leave is left.
6. The civil servant shall be entitled to
sick leave in accordance with Article
42(1) of this Proclamation, if she
becomes sick after completion of her
maternity leave under sub-Article (3) of
this Article.
7. Any civil servant who encounters a
miscarriage of not less than six month’s
pregnancy prior to her prenatal leave
shall be entitled to 60 days post
confinement maternity leave if the
miscarriage is confirmed by medical
37
ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
8. የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ
የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው
የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ
ንኡስ አንቀጽ (3) የተመለከተው የ90
ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
9. ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባለው
የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ
ያጋጠማት የመንግሥት ሠራተኛ
ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ
ቀን ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
10. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ
የሚከፈልበት 10 የሥራ ቀን ፈቃድ
ይሰጠዋል፡፡
42. የሕመም ፈቃድ,
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በሕመም ምክንያት ሥራ መሥራት ያልቻለ እንደሆነ ደመወዝ የሚከፈልበት የሕመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሙከራ ጊዜውን ላጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ የሚሰጥ የሕመም ፈቃድ በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ ቢወስድም ሕመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ባለው አስራ ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ከስምንት ወር ወይም በአራት ዓመት ውስጥ ከአሥራ
certificate.
8. If a civil servant on prenatal leave
encounters a miscarriage of pregnancy,
her prenatal leave shall terminate and
she shall be entitled to the 90 days post
confinement maternity leave referred to
in sub-article (3) of this Article.
9. Any civil servant who encounters a
miscarriage of three to six month’s
pregnancy shall be granted 30
consecutive days leave with pay if the
miscarriage is confirmed by medical
certificate.
10. Any civil servant shall be entitled a
paternity leave with pay for 10 working
days at the time of his wife's delivery.
42. Sick Leave
1. Any civil servant shall be entitled to
sick leave where he is unable to work
due to sickness.
2. The duration of sick leave to be
granted to a permanent civil servant
in accordance with Sub-Article (1) of
this Article shall not exceed eight
months in a year or twelve months in
four years, whether counted
consecutively or separately starting
38
ሁለት ወር አይበልጥም፡፡
3. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት የሚሰጥ የሕመም ፈቃድ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከሙሉ ደመወዝ ጋር እና ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ከግማሽ ደመወዝ ጋር ይሆናል፡፡
4. የሙከራ ጊዜውን ያላጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ ከታመመ የህክምና ማስረጃ የሚቀርብበት የአንድ ወር የሕመም ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
5. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
ሲታመም፣
ሀ) ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት
ካላጋጠመው በስተቀር በተቻለ
ፍጥነት መታመሙን ለመሥሪያ
ቤቱ ማሳወቅ አለበት፣
ለ) በተከታታይ ከሦስት ቀናት ወይም
በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ
ከስድስት ቀናት በላይ በሕመሙ
ምክንያት ከሥራ የቀረ እንደሆነ
ለመታመሙ የሕክምና ማስረጃ
ማቅረብ አለበት፡፡
6. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግስት
ሠራተኛ በዓመት ፈቃድ ላይ እያለ
መታመሙን የሚያረጋግጥ የህክምና
ማስረጃ ካቀረበ የዓመት ፈቃዱ ተቋርጦ
የሕመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
from the first day of his sickness.
3. Sick leave to be granted in
accordance with Sub-Article (2) of
this Article shall be with full pay for
the first three months, half pay for the
next three months.
4. A Civil Servant on probation shall be
entitled to one month sick leave with
pay.
5. Where any civil servant is absent
from work due to sickness:
a) he shall, as soon as possible, notify
the government institution unless
prevented by force majeure;
b) He shall produce a medical
certificate in case of absence for
three consecutive days or for more
than six days within a budget year.
6. Where a civil servant who has
completed his probation and who is
on annual leave gets sick and
presents a medical certificate, his
annual leave shall be interrupted and
replaced by sick leave.
39
7. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (6) መሠረት
የተቋረጠው የዓመት ፈቃድ የሕመም
ፈቃዱ እንደተጠናቀቀ እንዲቀጥል
ይደረጋል፡፡
43. የህክምና ማስረጃ
1. “የሕክምና ማስረጃ” ማለት በሀገር
ውስጥ አግባብ ባለው ባለሥልጣን
ፈቃድ ከተሰጠው የግልም ሆነ
የመንግሥት የሕክምና ተቋም የሚሰጥ
ወይም ከሀገር ውጭ የተገኘና
ስለትክክለኛነቱ አግባብ ባለው
ባለሥልጣን የተረጋገጠ የምስክር
ወረቀት ነው፤ቢሮው የአፈጻጸም
መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፡፡
2. የምስክር ወረቀቱ ስለመንግሥት
ሠራተኛ የጤና ሁኔታና ስለሚሰጠው
የሕመም ፈቃድ መግለጽ አለበት፡፡
44. ለግል ጉዳይ የሚሰጥ ፈቃድ
ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
ለሐዘን፣ለጋብቻ እና ለፈተና በአንድ የበጀት
ዓመት ውስጥ ሰባት የሥራ ቀናት ፈቃድ
ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
45.ከደመወዝ ጋር የሚሰጥ ልዩ ፈቃድ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ፣
ከፍርድ ቤት ወይም ከሌሎች ሥልጣን
ከተሰጣቸው አካላት መጥሪያ ሲደርሰው
7. The annual leave interrupted pursuant
to sub-article (6) of this Article shall
be resumed upon completion of the
sick leave.
43. Medical Certificate 1. “Medical certificate” means a
certificate issued by a local private or
public medical institution licensed by
the appropriate authority or where it
is acquired from abroad it is verified
by an authorized body; the Bureau
shall issue implementing Dicective.
2. The certificate shall describe the
health condition and the sick leave to
begranted to a civil servant.
44. Leave for Personal Matters
Any civil servant shall be entitled to
leave for personal matters such as
mourning, wedding, examination and
the like for seven days within a
budget year.
45. Special Leave with Pay
1. Any civil servant shall be entitled to
special leave with pay where he is
summoned by a court or any other
40
የተጠራበት ጉዳይ ለሚጠይቀው ጊዜ፣
2. ከሕዝባዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ጉዳይ
ሲሆን ምርጫው ለሚወስድበት ጊዜ፣
ከደመወዝ ጋር ልዩ ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
46. ያለደመወዝ የሚሰጥ ልዩ ፈቃድ
1. የመንግሥት ሠራተኛ በበቂ ምክንያት
ደመወዝ የማይከፈልበት ልዩ ፈቃድ
እንዲሰጠው ሲጠይቅና የመሥሪያ ቤቱን
ጥቅም የማይጎዳ ሲሆን የመሥሪያ ቤቱ
የበላይ ኃላፊ ከአንድ ዓመት ለማይበልጥ
ጊዜ ሊፈቅድለት ይችላል፡፡
2. የመንግሥት ሠራተኛ በሕዝብ ምርጫ
ለመወዳደር ተወዳዳሪ ሆኖ ሲቀርብ የምርጫ
ቅስቀሳ በሚካሄድበት ወቅት እና ምርጫው
በሚከናወንበት ጊዜ ያለ ደመወዝ ፈቃድ
እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
3. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም
የመንግሥት ሠራተኛው ያለደመወዝ ልዩ
ፈቃድ እንዲሰጠው የጠየቀው የመንግሥት
መሥሪያ ቤትን በሚመለከት የፕሮጀክት
ሥራ ላይ በመመደቡ ወይም በትዳር
ጓደኛው ለዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ሥራ
በውጭ ሀገር መመደብ ምክንያት ከሆነ ልዩ
ፈቃዱ የፕሮጀክት ወይም የዲፕሎማቲክ
ሚሲዮን ሥራው እስከሚጠናቀቅ ላለው ጊዜ
ሊሰጠው ይችላል፡፡
competent authority, for the time
utilized for the same purpose;
2. for cases involving popular election,
for the duration of the election.
46. Special Leave without Pay
1. Where a civil servant applies, on
justifiable ground, for a special leave
without pay, the head of the
government institution may authorize
the granting of such leave a period not
exceeding one year if it does not
adversely affect the interest of the
institution.
2. Where a civil servant runs for election,
he shall be entitled to leave without
pay during the election campaign and
for the duration of the voting.
3. Notwithstanding sub-article (1) of this
Article, where a civil servant applies
for special leave without pay due to
his assignment on a project run by a
government institution or due to the
assignment of his spouse to a
diplomatic mission abroad, he may be
granted with such leave for the
duration of the project or the
completion of the diplomatic mission.
41
ክፍል አምስት
ተጨማሪ የድጋፍ እርምጃ የሚስፈልጋቸው
የኅብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ሁኔታ
47.ለሴት ሠራተኞች የሚጠበቁ የሥራ ሁኔታዎች
1. ማንኛውም የመንግስት መሥሪያ ቤት
ሴት የመንግሥት ሠራተኞችን
ለማብቃትና በውሳኔ ሰጪ የሥራ ቦታዎች
ላይ እንዲመደቡ ለማድረግ የሚያስችሉ
የተጨማሪ ድጋፍ እርምጃዎችን መውሰድ
አለበት፡፡
2. ሴቶች በቅጥር፣ በደረጃ እድገት፣
በዝውውር፣ በድልድል፣ በትምህርትና
ሥልጠና አፈጻጸም የተጨማሪ ድጋፍ
እርምጃ ተጠቃሚ መሆን አለባቸው፡፡
3. ነፍሰ ጡር የሆነችን የመንግሥት
ሠራተኛ በቅጥር ወይም በደረጃ ዕድገት
ከተመደበችበት የሥራ መደብ ወደ ሌላ
የሥራ መደብ መደቦ ማሰራት የተከለከለ
ነው፤ ሆኖም ለራሷ ጤንነት ወይም
ለፅንሱ አደገኛ መሆኑ በሕክምና ማስረጃ
ሲረጋገጥ ተስማሚ ወደ ሆነ የሥራ
መደብ ወይም የሥራ ቦታ ተመድባ
እንድትሰራ መደረግ አለበት፡፡
4. ማንኛዋም የመንግስት መስሪያ ቤት ሴት
የመንግስት ሠራተኛ ነፍሰጡር በሆነችበት
SECTION FIVE
Conditions of Work Applicable to
Members of the Society Deserving
Affirmative Action
47. Conditions of Work Applicable to
Female Civil Servants
1. Any government institution shall take
affirmative actions that enable female
civil servants to improve their
competence and to assume decision
making positions.
2. Women shall be entitled to affirmative
actions in recruitment, promotion,
transfer, redeployment, education and
training.
3. It is prohibited to assign a pregnant
civil servant to a position other than the
position she assumed through
recruitment or promotion; provided,
however, that where so recommended
by a medical certificate due to the risk
to her health or to the fetus, she shall be
transferred to another position or place
of work.
4. Any government institution shall not
discharge a female civil servant by way
42
ጊዜና ከወለደችበት ቀን ጀምሮ በአራት ወር
ጊዜ ውስጥ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 86
መሠረት በሚያደርገው የሠራተኛ ቅነሳ
ከሥራ ሊያሰናብታት አይችልም፡፡
5. ማንኛዋም ሴት የመንግሥት ሠራተኛ
አንድ ዓመት ያልሞላውን ሕጻን ልጇን
ለማሳከም በህክምና ማስረጃ ለተረጋገጠ
ጊዜ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
ይሰጣታል፡፡
6. ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት ሴት የመንግስት ሠራተኞች ህጻናት ልጆቻቸውን የሚያጠቡበትና ህጻናቱን የሚንከባከቡበት የህጻናት ማቆያ ማቋቋም አለበት፤ዝርዝር አፈጻጸሙ የሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡
48.ለአካል ጉዳተኞች የሚጠበቁ የሥራ ሁኔታዎች
1. አካል ጉዳተኞች በቅጥር፣ በደረጃ
ዕድገት፣ በዝውውር፣ በድልድል፣
በትምህርትና ሥልጠና አፈጻጸም
የተጨማሪ ድጋፍ እርምጃ ተጠቃሚ
መሆን አለባቸው፡፡
2. ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት
የሥራ አካባቢው ለአካል ጉዳተኛ
ሠራተኞቹ ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ለሥራ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችንና
ቁሳቁሶችን ማሟላትና ስለአጠቃቀማቸው
አስፈላጊውን ሥልጠና እንዲያገኙ
of retrenchment pursuant to Article 87
of this Proclamation during her
pregnancy or within four months after
delivery.
5. Any female civil servant shall, when
confirmed by medical certificate, be
entitle to leave with pay for the time
spent in the follow up of medical
treatment of her child who has not
attained the age of one year.
6. Any government institution shall
establish a nursery where female civil
servants could breast-feed and take care
of their babies; the details of its
implementation shall be determined by
directives to be issued by the
appropriate government institution.
48. Conditions of Work Applicable to
Persons with Disabilities
1. Persons with disabilities shall be
entitled to affirmative actions in
recruitment, promotion, transfer,
redeployment, education and
training.
2. Any government institution shall
ensure that its working environment
is conducive to civil servants with
disabilities, provide them with the
necessary tools and materials and
train them how to use such tools and
43
ማድረግ አለበት፡፡
3. ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት
ረዳት ለሚያስፈልገው የአካል ጉዳተኛ
የሆነ የመንግስት ሠራተኛ ተገቢውን
ድጋፍ ሊሰጥ የሚችል ረዳት
እንዲመደብለት የማድረግ ኃላፊነት
አለበት፡፡
4. በሌሎች ሕጎች ለአካል ጉዳተኞች
የተሰጡ መብቶች ለአዋጁ አፈጻጻም
ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
49. አነስተኛ ብሔራዊ ተዋጽኦ ካላቸው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚጠበቁ የሥራ ሁኔታዎች
1. በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ
የሚፈጸም የሠራተኛ ስምሪት የብሔር፣
ብሔረሰብና ህዝቦች ሚዛናዊ ተዋጽኦ
ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡
2. በመንግስት መስሪያ ቤቱ ውስጥ አነስተኛ
ብሔራዊ ተዋፅኦ ያላቸው የብሔር፣
ብሔረሰብና ህዝቦች በቅጥር፣ በደረጃ
ዕድገት፣ በዝውውር፣ በድልድል፣
በትምህርትና ሥልጠና አፈጻጸም
የተጨማሪ ድጋፍ እርምጃ ተጠቃሚ
መሆን አለባቸው፡፡
materials.
3. Any government institution shall
have the responsibility to assign an
assistant for those civil servants with
disability that requires assistance.
4. Privileges prescribed by other laws to
persons with disabilities shall be
applicable for the implementation of
this Proclamation.
49. Expected work Conditions of Work
Applicable from minority national
contribution of Nations, Nationalities
and Peoples
1. The placement of personnel in a
government institution shall take into
account fair representation of nations
and nationalities.
2. Nations and nationalities having
lesser representations within a
government institution shall be given
the advantage of affirmative actions
in recruitment, promotion, transfer,
redeployment, education and
training.
44
50. መመሪያ ስለማውጣት
በዚህ ክፍል ለተመለከቱት የተጨማሪ
የድጋፍ እርምጃዎች አፈጻጸም ቢሮው
ዝርዝር መመሪያ ያወጣል፡
ክፍል ስድስት
የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት
51. ዓላማና ተፈጻሚነት
1. የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት
ዓላማ፣
ሀ) የመንግሥት ሠራተኞችን
ደህንነትና ጤንነት በመጠበቅ የሥራ
ብቃትን ማጐልበት፣
ለ) የሥራ ቦታን ለመንግሥት ሠራተኞች
ደህንነትና ጤንነት በሚስማማ መልኩ
ማዘጋጀት፣ ማሻሻልና መጠበቅ፣ እና
ሐ) የመንግሥት መሥሪያ ቤት በጐ
በሆነ ማህበራዊ ሕይወት ላይ
ተመሥርቶ አመርቂ የሥራ
ውጤት እንዲያስመዘግብ ማብቃት
ይሆናል፡፡
2. የዚህ ክፍል ድንጋጌዎች ለጊዜያዊ
ሠራተኞችም ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
52. በሥራ ላይ ስለሚደርስ ጉዳት
1. “በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት” ማለት
በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም
50. Issuance of Directives
The Bureau shall issue detailed directives for
the implementation of affirmative actions
provided for under this Section
SECTION SIX
OCCUPATIONAL SAFETY AND
HEALTH
51. Objectives and Applicability
1. The objectives of occupational safety
and health shall be:
a) to maintain the safety and health of
civil servants and enhance their
productivity;
b) to arrange, improve and keep
suitable work place for the safety and
health of civil servants; and
c) to guarantee high level performance
of a government institution based on
social wellbeing.
2. The provisions of this Section shall
also be applicable to temporary
workers.
52. Employment Injury
1. "Employment Injury" means
employment accident or occupational
45
በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡
2. “በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ” ማለት
የመንግስት ሠራተኛው መደበኛ
ሥራውን በማከናወን ላይ እንዳለ ወይም
ከሥራው ጋር በተያያዘ ምክንያት
በአካሉ ወይም በአካሉ የተፈጥሮ ተግባር
ላይ በድንገት የሚደርስ ጉዳት ሲሆን
የሚከተሉትን ይጨምራል፤
ሀ) የመንግሥት ሠራተኛው ከመደበኛ
ሥራው፣የሥራ ቦታው ወይም
የሥራ ሰዓቱ ውጭ ሥልጣኑ
በሚፈቅድለት ሰው የተሰጠውን
ትዕዛዝ በመፈጸም ላይ እያለ
የደረሰን ጉዳት፤
ለ) ሥልጣኑ በሚፈቅድለት ሰው
የተሰጠው ትዕዛዝ ባይኖርም
የመንግሥት ሠራተኛው በመሥሪያ
ቤቱ ውስጥ የደረሰን ድንገተኛ አደጋ
ወይም ጥፋት ለመከላከል በሥራ
ሰዓት ወይም ከሥራ ሰዓት ውጭ
በሚፈጽመው ተግባር ምክንያት
የደረሰን ጉዳት፤
ሐ) የመንግሥት ሠራተኛው ወደ ሥራ
ቦታው ወይም ከሥራ ቦታው
መሥሪያ ቤቱ ለሠራተኞች
አገልግሎት እንዲሰጥ በመደበው
የመጓጓዣ አገልግሎት ወይም
disease.
2. "Employment Accident" means any
organic injury or functional disorder
suddenly sustained by a civil servant
during or in connection with the
performance of his work, and shall
include the following:
a) injury sustained by a civil servant
outside of his regular work, or
outside of his regularworking place
or hours, while carrying out orders by
a competent authority;
b) injury sustained bya civil servant
during or outside of working hours
while attempting to save his work
place from destruction of imminent
danger, though without order by a
competent authority;
c) injury sustained by a civil servant
while he is proceeding to or from his
place of work in a transport service
vehicle provided by the government
institution which is available for the
common use of its employees or in a
46
መሥሪያ ቤቱ ለዚህ ተግባር
በተከራየውና በግልጽ በመደበው
የመጓጓዣ አገልግሎት በመጓዝ ላይ
በነበረበት ጊዜ የደረሰን ጉዳት፤
መ) የመንግሥት ሠራተኛው ከሥራው
ጋር በተያያዘ ተግባሩ ምክንያት
ከሥራው በፊት ወይም በኋላ ወይም
ሥራው ለጊዜው ተቋርጦ በነበረበት
ጊዜ በሥራው ቦታ ወይም በመሥሪያ
ቤቱ ግቢ ውስጥ በመገኘት የደረሰበትን
ማንኛውንም ጉዳት፤
ሠ) የመንግሥት ሠራተኛው ሥራውን
በማከናወን ላይ ባለበት ጊዜ
በመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ወይም
በሦስተኛ ወገን ድርጊት ምክንያት
የደረሰበትን ጉዳት፣
3. “በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ” ማለት
የመንግሥት ሠራተኛው ከሚሠራው
የሥራ ዓይነት ወይም ሥራውን
ከሚያከናውንበት አካባቢ የተነሳ በሽታን
ለሚያስከትሉ ሁኔታዎች ተጋልጦ
በመቆየቱ ምክንያት የደረሰ የጤና መታወክ
ሲሆን፣ ሥራውን በሚያከናውንበት ቦታ
የሚዛመቱና የሚይዙ ነዋሪ ወይም ተላላፊ
በሽታዎችን አይጨምርም፡፡
vehicle hired and expressly destined
by the office for the same purpose;
d) any injury sustained by a civil servant
before or after his work or during any
interruption of work, if he is present
in the work place or the premises of
the undertaking by reason of his
duties in connection with this work;
e) any injury sustained by a civil servant
as a result of an action of the
government institution or a third
party during the performance of his
work.
3. "Occupational disease" means any
pathological condition of a civil servant
which arises as a consequence of the
kind of work he performs or because of
his exposure to the agent that causes the
disease for a certain period prior to the
date in which the disease became
evident; provided, however, that it does
not include endemic or epidemic
diseases which are prevalent and
contracted in the area where the work is
done.
47
4. በዚህ ንኡስ አንቀጽ (3) የተመለከተው
ቢኖርም በመደበኛ ሥራው ምክንያት
ተላላፊ ወይም ነዋሪ በሽታዎችን በማጥፋት
ላይ የተሰማራ የመንግስት ሠራተኛ በዚሁ
በሽታ ከተያዘ በሥራ ምክንያት የመጣ
በሽታ እንደያዘው ይቆጠራል፡፡
5. በሥራ ላይ በሚደርስ ጉዳት ምክንያት
የሚከሰት የአካል ጉዳት መጠን አግባብ
ባለው የመንግሥት ሠራተኞች ጡረታ ሕግ
ድንጋጌዎች መሠረት ይወሰናል፡፡
6. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም
ሠራተኛው ሆነ ብሎ በተለይም በመሥሪያ
ቤቱ አስቀድሞ በግልጽ የተሰጡትን
የደህንነት መጠበቂያ መመሪያዎች በመጣስ
ወይም በመጠጥ ወይም በአደንዛዥ ዕፅ
ሰክሮ በሥራ ላይ በመገኘቱ የደረሰበት
ጉዳት በሥራ ምክንያት እንደደረሰ ጉዳት
አይቆጠርም፡፡
53.የአደጋ መከላከያ እርምጃዎች
1. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት፣
ሀ) የሥራ ቦታው በሠራተኞች ደህንነትና
ጤንነት ላይ አደጋ የማያስከትል
መሆኑን ማረጋገጥ፣
ለ)የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎችንና
ቁሳቁሶችን ለሠራተኞች የማቅረብና
ስለአጠቃቀማቸው መመሪያ
የመስጠት፣ኃላፊነት አለበት፡፡
4. Notwithstanding sub-article (3) of this
Article, if a civil servant engaged in
combating epidemic or endemic disease
contracted with such disease, it shall be
considered as occupational disease.
5. The extent of disability caused by an
employment injury shall be determined
pursuant to the relevant provisions of
the public servants pension law.
6. Notwithstanding the provisions of sub-
article (1) of this Article, any injury
sustained by the deliberate act of the
civil servant, particularly, by his
nonobservance of express safety rules
or by reporting to work in a state of
intoxication caused by drinks or drugs
shall not be deemed an employment
injury.
53. Safety Measures
1. Any government institution shall have
the responsibility to:
a) ensure that the work place does not
cause hazard to the health and safety
of civil servants;
b) provide civil servants with protective
devices and materials and give them
instructions on their usage.
2. Any civil servant shall have the
obligation to:
48
2. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ፣
ሀ) ደህንነትና ጤንነትን ለመጠበቅ የወጡ
መመሪያዎችን የማክበር፣
ለ) የተሰጡትን የአደጋ መከላከያ
መሣሪያዎችንና ቁሳቁሳችን በአግባቡ
የመጠቀም፣ እና
ሐ) አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ
ሁኔታዎች መኖራቸውን ሲገምት
ለሚመለከተው የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ
ወዲያውኑ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
3. ቢሮው የሥራ አካባቢ ደህንነትና
ጤንነት የመጠበቂያና የመከላከያ
ዘዴዎችን ያጠናል፤ የመንግሥት
መሥሪያ ቤቶች ሥራ ላይ
እንዲያውሉት ሥልጠና ስለሚሰጥበት
ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
4. ቢሮው በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች
ውስጥ የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት
ተግባራዊ መሆኑን ይቆጣጠራል፤
የአደጋ መከላከያ እርምጃዎችን
በተመለከተ በመመሪያ ይወሰናል፡፡
54. የአካል ጉዳት
1. “የአካል ጉዳት” ማለት የመሥራት ችሎታ
መቀነስን ወይም ማጣትን በሚያስከትል
ሁኔታ በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት
a) observe directives issued in relation
to safety and health;
b) properly use safety devices and
marterials; and
c) promptly inform the concerned
official of any situation which he
may have reason to believe could
present a hazard.
3. The Bureau shall undertake studies on
methods of maintaining occupational
safety and health; and facilitate the
provision of training for their
implementation in government
institutions.
4. The Bureau shall supervise the
implementation of occupational safety
and health measures in government
institutions and shall issue directives
regarding safety precaution measures.
54. Disability
1. "Disablement" means any employment
injury as consequence of which there
is a decrease or loss of capacity to
work.
49
ነው፡፡
2. በሥራ ላይ የደረሰ የአካል ጉዳት ጊዜያዊ
የአካል ጉዳት፣ ዘላቂ ከፊል የአካል
ጉዳት፣ ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት
ወይም ሞትን የሚያስከትል ውጤት
ይኖረዋል፡፡
55. ጊዚያዊ የአካል ጉዳት
“ጊዜያዊ የአካል ጉዳት” ማለት ለተወሰነ ጊዜ
በሙሉ ወይም በከፊል የመሥራት
ችሎታን ማጣት ነው፡፡
56. ዘላቂ ከፊል የአካል ጉዳት
“ዘላቂ ከፊል የአካል ጉዳት” ማለት
የመሥራት ችሎታ የሚቀንስ የማይድን
በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው፡፡
57.ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት
“ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት” ማለት ጉዳት
የደረሰበትን የመንግሥት ሠራተኛ
ማናቸውንም ደመወዝ የሚያስገኝ ሥራ
ለመሥራት የሚከለክለው የማይድን በሥራ
ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው፡፡
58. ከሥራ በመጣ ጉዳት ምክንያት የሚሰጥ ህክምና እና ፈቃድ
1. በሥራው ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት
የመንግሥት ሠራተኛ በሀገር ውስጥ
ለሚሰጡ ለሚከተሉት የሕክምና
አገልግሎቶች የሚያስፈልገው ወጪ
በመሥሪያ ቤቱ ይሸፈናል፤
2. The effects of disablement are
temporary disablement, permanent
partial disablement, permanent total
disablement and death.
55. Temporary Disability "Temporary disablement" means the
reduction for a limited period of time
of the worker's capacity for work
partially or totally.
56. Permanent Partial Disability
"Permanent partial disability" means
incurable employment injury reducing
the capacity to work.
57. Permanent Total Disability "Permanent total disability" means
incurable employment injury, which
prevents the injured civil servant
from engaging in any kind of
remunerated work.
58. Medical Benefits and Injury
Leave
1. The government institution shall
cover the expenses for the following
locally provided medical treatments to
a civil servant who has sustained
employment injury:
50
ሀ) የጠቅላላና የልዩ ሕክምና እንዲሁም
የቀዶ ሕክምና ወጪዎች፤
ለ) የሆስፒታልና የመድኃኒት ወጪዎች፤
ሐ) የማንኛውም አስፈላጊ ሰው ሰራሽ
ምትክ ወይም ተጨማሪ አካሎችና
የአጥንት ጥገና ወጪዎች፡
2. ጉዳት ለደረሰበት የመንግሥት ሠራተኛ
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1)
መሠረት የሚሰጠው የህክምና
አገልግሎት በግል የህክምና ተቋም
እንዲሰጠው የሚደረገው አገልግሎቱ
በመንግሥት የሕክምና ተቋማት
ሊሰጠው የማይችል ሲሆን ብቻ ነው፡፡
3. በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት
ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
የጉዳቱ መጠን ታይቶ በህክምና ማስረጃ
በሚገለጸው መሰረት ከጉዳቱ ድኖ ወደ
ሥራው እስከሚመለስ ወይም በጉዳቱ
ምክንያት ለዘለቄታ መሥራት የማይችል
መሆኑ በሕክምና ማስረጃ እስከሚረጋገጥ
ድረስ የሕመም ፈቃድ ከሙሉ ደመወዝ
ጋር ይሰጠዋል፡፡ የመንግሥት
ሠራተኛው ለዘለቄታው መሥራት
ያለመቻሉ በሕክምና ማስረጃ ከተረጋገጠ
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 59 የተደነገጉት
ጥቅሞች ይጠበቁለታል፡፡
4. ሠራተኛው ሕክምናውን በአግባቡ
a) general and special medical
treatment and surgical care;
b) hospital and pharmaceutical care;
c) any necessary prosthetic or
orthopedic appliance.
2. The medical treatment to which an
injured civil servant is entitled
pursuant to sub-article (1) of this
Article shall be provided by private
medical institutions where the
treatment in question could not be
provided by public medical
institutions.
3. Any civil servant who has sustained
an employment injury shall be entitled
to injury leave with pay until he
recovers and resumes work or until it
is medically certified that he is
permanently disabled. Where it is
medically certified that the civil
servant is permanently disabled, he
shall be entitled to the benefits
provided for under Article 59 of this
Proclamation.
4. Where the civil servant intentionally
51
ባለመከታተሉ ወይም በሐኪም
የተሰጠውን ትዕዛዝ ባለማክበሩ
ሕክምናውን ያጓተተ እንደሆነ በዚህ
አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2)
መሠረት የሚሰጠው ሕክምና እና ፈቃድ
ይቋረጥበታል፡፡
5. ቢሮው በንዑስ አንቀጽ (1)
ስለተመለከተው የህክምና ወጪ
አከፋፈል የአፈጻጸም መመሪያ ያወጣል፡፡
59. የጉዳት ጡረታ አበል እና የጉዳት ዳረጎት፣
1. ከሥራ በመጣ የአካል ጉዳት ምክንያት
ዘላቂ ሙሉ ወይም ከፊል የመሥራት
ችሎታውን ያጣ ማንኛውም የመንግሥት
ሠራተኛ በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ
ሕግ የተሰጡት መብቶችና ጥቅሞች
ይጠበቁለታል፡፡
2. ከባድ የአካል ወይም ከባድ የመልክ
መበላሸትን ያስከተለ ጉዳት የመሥራት
ችሎታ ማጣትን ባያስከትልም ለጉዳት
ካሣ አከፋፈልና ለሌሎች ጥቅማጥቅሞች
አሰጣጥ ሲባል እንደ ዘላቂ ከፊል የአካል
ጉዳት ይቆጠራል፡፡
3. በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ ሕግ
የተደነገገው የአካል ጉዳት መጠን
አወሳሰን ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2)
delays his recovery by not following
the medical treatment properly or by
his non-observance of doctor's
instructions, his entitlement of
medical benefits and leave under
subarticles (1) and (2) of this Article
shall cease.
5. The Ministry may issue
implementation directives regarding
the payment of medical expenses
referred to in sub-article (1) of this
Article.
59. Disability Pension and Gratuity
1. Any civil servant who has sustained
permanent total or partial disability
due to employment injury shall be
entitled to benefits provided for in the
public servant's pension law.
2. Injuries which, although not resulting
in incapacity to work, cause serious
mutilation or disfigurement of the
injured civil servant, shall be
considered permanent partial disability
for the purpose of payment of
compensation and other benefits.
3. The assessment of the extent of
employment injure as provided for by
the public servants pension law shall
also apply for the implementation of
52
አፈጻጸም ተግባራዊ ይሆናል፡፡
4. የመንግሥት ሠራተኛ በደረሰበት ጉዳት
ምክንያት የሞተ እንደሆነ፣ በመንግሥት
ሠራተኞች የጡረታ ሕግ መሠረት የጡረታ
አበል ለተተኪዎቹ ይከፈላል፡፡
60. ከግብር ነፃ ስለመሆን
በአዋጁ አንቀጽ 59 መሠረት የሚደረግ ክፍያ
ከግብር ነፃ ይሆናል፤ እንዲሁም በዕዳ
ምክንያት ሊያዝ ወይም ማቻቻያ ሊደረግ
ወይም ባለመብቱ ሊያስተላልፈው አይችልም፡፡
61.ከሦስተኛ ወገን ስለሚጠየቅ የካሣ ክፍያ
1. በሠራተኛው ላይ የደረሰው ጉዳት በሦስተኛ
ወገን ጥፋት ምክንያት የደረሰ እንደሆነ
የመንግሥት መሥሪያ ቤቱ በጉዳቱ
ምክንያት ለሠራተኛው ባወጣው ወጪ
መጠን ጉዳቱን ካደረሰው ወገን ካሣ
የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡
2. ሠራተኛው ጉዳቱን ካደረሰበት ወገን ካሣ
የተቀበለ እንደሆነ መሥሪያ ቤቱ በአዋጁ
አንቀጽ 59(1) እና (3) መሠረት ያወጣውን
ወጪ ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ ይቀንሳል፤
ሠራተኛው የተቀበለው የካሣ መጠን
መሥሪያ ቤቱ ካወጣው ወጪ ያነሰ ከሆነ
ልዩነቱን መሥሪያ ቤቱ ከሦስተኛው ወገን
መጠየቅ ይችላል፡፡
Sub-article (2) of this Article.
4. Where an employment injury has
resulted in the death of a civil servant,
his survivors shall receive gratuity
provided for by the public servants
pension law.
60. Tax Exemption Any payment to be made pursuant to
Article 60 of this Proclamation shall
be exempt from tax and may not be
attached or set off, or assigned by the
beneficiary.
61. Claims of Compensation from Third Party
1. Where the injury sustained by the
civil servant is caused by the fault of
a third party, the government institution shall be entitled to claim
compensation from the third party an amount equal to the expenses whichit has incurred due to the injury.
2. In the event that the civil servant receives compensation from the third
party who caused injury, the government institution may deduct from the salary of the civil servant
the expenses incurred pursuant to Article 59(1) and (3)of this
Proclamation. Where the amount of compensation received by the civil servant is less than the cost incurred
by the government institution, the institution can claim the difference
from the third party.
53
ክፍል ሰባት
የመንግሥት ሠራተኞች የመረጃ አያያዝ
62.የግል ማኅደር
1. ማንኛውም የክልሉ መንግሥት መሥሪያ
ቤት እና ቢሮው ስለእያንዳንዱ
የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ጊዜያዊ
ሠራተኛ አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች
በዘመናዊ ሁኔታ አደራጅተው ይይዛሉ፡፡
2. ቢሮው በንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት
የሚላኩለት የሰው ሀብት መረጃዎች ይህን
አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም የወጡ
መመሪያዎችን የተከተሉ መሆናቸውን
በማረጋጋጥ ይመዘግባል፡፡
3. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በግል
ማህደሩ ውስጥ የሚገኙትን ማስረጃዎች
የመመልከት ወይም ቅጂውን የመውሰድ
መብት አለው፡፡
4. ከሚመለከታቸው የአስተዳደር ሠራተኞች
በስተቀር፣ ያለሠራተኛው ስምምነት፣
የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም በሕግ
በተደነገገው መሠረት ካልሆነ በስተቀር
ማንኛውም ሰው የመንግሥት ሠራተኛውን
የግል ማህደር ማየት አይችልም፡፡
SECTION SEVEN
MANAGING INFORMATION PROFILES
OF CIVIL SERVANTS
62. Personnel Records
1. Any government institution and the
Bureau shall keep relevant personnel
data organized in a modern way
regarding each civil servant or
temporary employee.
2. The Bureau shall register the human
resource information sent to it
pursuant to sub-article (1) of this
Article upon ascertaining their
compliance with the provisions of
this Proclamation and directives
issued for the implementation of this
Proclamation.
3. Any civil servant shall have right to
access to all information contained in
his personnel records or to have a
copy thereof.
4. Any person other than the concerned
administrative staff shall not have
access to personnel records of a civil
servant without his consent unless
authorized by a court order or by the
provision of the law.
54
5. የመንግሥት ሠራተኛው እንዲያውቀው
ያልተደረገ ወይም ያልተገለጸለትን የጽሁፍ
ማስረጃ በግል ማህደሩ ውስጥ ማስቀመጥ
ክልክል ነው፡፡
63.የመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ የማደራጀት ኃላፊነት
1. ቢሮው፣
ሀ) በክልል ደረጃ የሰው ሀብት ሥራ
አመራር መረጃ ሥርዓት በወጥነት
እንዲተገበር የማድረግ፣
ለ) ክልላዊ የመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ
ቋት የማደራጀት፣
ሐ) የመንግሥት ሠራተኞችን የሚመለከቱ
ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣
የማጠናቀር እና የማሰራጨት ኃላፊነት
አለበት፡፡
2. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
በቢሮው ለሚደራጀው የሰው ሀብት መረጃ
ቋት መረጃዎችን ወቅቱን ጠብቆ የመላክ
ግዴታ አለበት፡፡
3. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
የእያንዳንዱን ሠራተኛ መረጃ ለቢሮው
መላክ አለበት፡፡
5. It is prohibited to deposit any
document in the personnel records of
a civil servant which is not made
known or informed to him.
63. The Responsibility of Organizing
Profile of Civil Servants
1. The Bureau shall have the duty to:
a) implement uniform human resource
management information system at a
national level;
b) organize civil servants data base at
national level;
c) collect, compile and disseminate
statistical data relating to civil
servants.
2. Any government institution shall have
duty to send information on timely
basis to the Ministry's human resource
database.
3. Any government institution shall send
to the Ministry personnel data of every
employee.
55
ክፍል ስምንት
መብቶችና ግዴታዎች
64.የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ኃላፊነት
በሌሎች ሕግ ድንጋጌዎች የተመለከቱት ኃላፊነቶች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖሩታል፤
1. የመንግስት ሠራተኞች በመንግስት
ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ሕጎች ላይ በቂ
ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማድረግ፤
2. የመሥሪያ ቤቱ የሥራ አካባቢ ከማንኛውም
ዓይነት ኃይማኖታዊ ተግባራት ነጻ መሆኑን
የማረጋገጥ፤
3. ለእያንዳንዱ የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ
ዝርዝር መግለጫ የመስጠትና በሥራ ዕቅድ
ላይ ተመሥርቶ የሠራተኛውን የሥራ
አፈጻጸም ውጤት የመለካት፤
4. ለመንግሥት ሠራተኞች ለሥራ
የሚያስፈልጓቸውን መሣያዎች የማቅረብና
አጠቃቀማቸውን የማሳወቅ፤
5. የሥራ አካባቢውን ለመንግሥት ሠራተኞች
ጤንነትና ደህንነት አመቺ የማድረግ
ኃላፍነት አለበት፡፡
65. የመንግሥት ሠራተኞች ግዴታዎች
ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ የሚከተሉት
ግዴታዎች ይኖሩበታል፤
SECTION EIGHT
RIGHTS AND OBLIGATIONS
64. Responsibilities of Government
Institutions
Without prejudice to other provisions of this
Proclamation, any government
institution shall have responsibilities to:
1. make civil servants fully aware of
government policies, strategies and
laws;
2. ensure that its working environment
is free from any form of religious
practices or activities;
3. provide job description to each civil
servant and evaluate his performance
based on work plans;
4. proved necessary work appliances to
civil servants and orient them about
their usages;
5. create conducive working
environment to the health and safety
of civil servants.
65. Obligations of Civil Servants
Any civil servant shall have the following
obligations:
56
1. ለሕዝብና ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ
መሆንና የሕግ የበላይነትን የማክበር፤
2. መንግሥት የሚያወጣቸውን ሕጎችና
ፖሊሲዎችን በብቃት የመፈጸም፤
3. በማናቸውም ሁኔታ ሕዝብንና ሀገርን
ያለአድልዎ የማገልገል፤
4. መላ ዕውቀቱንና ችሎታውን ለሕዝብ
አገልግሎት የማዋል፤
5. በሥራ ዝርዝሩ የተመለከቱትንና በቅርብ
ኃላፊው የሚሰጠውን ሕጋዊ ትዕዛዝ
የመፈጸም፤
6. በማናቸውም ሁኔታ በሥራ ቦታ ላይ የግል
እምንነቱን ወይም ኃይማኖቱን
የሚያንጸባርቅ ተግባር አለመፈጸም፤
7. ሚስጢር ተብለው የተለዩና በሥራው
አጋጣሚ ያወቃቸውን የመሥሪያ ቤቱን
ምስጢሮች የመጠበቅ፤
8. በተገልጋዮች መካከል በፆታ፣ በቋንቋ፣
በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣
በአካል ጉዳት ወይም በሌሎች ልዩነት
በሚፈጥሩ ሁኔታዎች መድሎ ያለመፈጸም፤
9. ለመስሪያ ቤቱ የሚሰጠውን አገልግሎት
የሚያጓድል ወይም በማናቸውም አኳኋን
ከተመደበበት ሥራ ጋር የሚቃረን ወይም
ከመንግስት ሠራተኝነቱ ጋር የማይጣጣም
ማናቸውንም ሌላ ሥራ ያለመስራት፤
1. be loyal to the public and the
Constitution and respect the law;
2. effectively execute the laws and
policies issued by the Government;
3. serve the public and the country
without having any form of bias;
4. devote his whole energy and ability to
the service of the public;
5. discharge the functions specified in his
job description and the lawful orders
of his immediate supervisor;
6. be reserved from exercising any
activity or practice reflecting his own
faith or religion at the place of work;
7. not disclose confidential matters of the
government institution classified as
such;
8. avoid discriminatory treatment of
clients on the basis of gender,
language, ethnicity, religion, political
stand, physical disability or other
forms of differentiations;
9. not engage in any other activity that
compromise his service to the
government institution or otherwise
conflict with his duties or is
incompatible with his status as a civil
servant;
57
10. ሥራውን ለፖለቲካ ጥቅሙ ያለማዋልና
በዚህም ምክንያት አድሎ ያለመፈጸም፤
11. በመንግስት ሠራተኝነቱ ለሰጠው ወይም
እንዲሰጥ ለሚጠበቀው አገልግሎት
ማንኛውንም ዓይነት ስጦታ ወይም ዋጋ
ያላቸው ነገሮች ያለመጠየቅ ወይም
ያለመቀበል፤
12. ለሥራ ማከናወኛ የተሰጡትን
መሣሪያዎችና መገልገያዎች በአግባቡ
የመጠቀምና የመጠበቅ፤
13. ከኤች አይ ቪ/ኤድስ በስተቀር ከሥራው
ጋራ በተያያዘ በበቂ ምክንያት የህክምና
ምርመራ እንዲያደርግ በመንግስት መሥሪያ
ቤቱ ሲጠየቅ ለምርመራ የመቅረብ፤
14. ስለሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ
የወጡ መመሪያዎችን የማክበር፡፡
66. በዕዳ የመጠየቅ ኃላፊነት
ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ለሥራው
ማከናወኛ በተሰጡት መሣሪያዎችና መገልገያዎች
ላይ በሚደርስ ጉዳት ወይም ጥፋት በዕዳ ተጠያቂ
የሚሆነው ጉዳቱ ወይም ጥፋቱ በሠራተኛው
ቸልተኝነት ወይም ሆነ ተብሎ በተፈፀመ ድርጊት
ምክንያት የደረሰ እንደሆነ ነው፡፡
10. not use his position to advance his
political interest and thereby exercise
discriminatory practice;
11. not solicit or accept any gift or a
present having a value in consideration
of the service he renders or expected
to render as a civil servant;
12. properly use and handle equipment
and implements supplied to him for
the purpose of doing his job;
13. submit for medical examination, other
than examination for HIV/AIDS, when
required by the government institution
on sufficient grounds related to his
service;
14. observe occupational safety and
health rules.
66. Extent of Liability
Any civil servant shall be liable for the
damage or loss of equipment and
implements supplied to him for the purpose
of doing his job, where such damage or loss
is caused by his negligence or intentional
act.
58
ክፍል ዘጠኝ የዲስፕሊን እርምጃዎች እና የቅሬታ አፈታት
ንኡስ ክፍል አንድ የዲስፕሊን እርምጃዎች
67. የዲስፕሊን ቅጣት ዓላማ
የዲስፕሊን ቅጣት ዓላማ የመንግሥት
ሠራተኛው በፈጸመው የዲስፕሊን ጉድለት
ተፀፅቶ በአመለካከቱና በሥነ-ምግባሩ
እንዲታረምና ብቁ ሠራተኛ እንዲሆን
ለማስቻል ወይም የማይታረም ሆኖ ሲገኝ
ለማሰናበት ነው፡፡
68. የዲስፕሊን ቅጣት ዓይነቶችና አመዳደብ
1. የዲስፕሊን ጉድለት የፈጸመ የመንግሥት
ሠራተኛ እንደጥፋቱ ክብደት ከሚከተሉት
ቅጣቶች አንዱ ሊወሰንበት ይችላል፤
ሀ) የቃል ማስጠንቀቂያ፤
ለ) የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፤
ሐ) እስከ አሥራ አምስት ቀን ደመወዝ
የሚደርስ መቀጮ፤
መ) እስከ ሦስት ወር ደመወዝ የሚደርስ
መቀጮ፤
ሠ) እስከ ሁለት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ
በሥራ ደረጃ እና ደመወዝ ዝቅ ማድረግ፤
ረ) ከሥራ ማሰናበት፣
‹
SECTION NINE
DISCIPLINARY MEASURES AND
GRIEVANCE HANDLING
SUB- SECTION ONE
DISCIPLINARY MEASURES
67. Objective of Disciplinary Penalty
The objectives of disciplinary penalty
shall be to rehabilitate a delinquent civil
servant when he can learn from his
mistakes and become a reliable civil
servant or to discharge him when he
becomes recalcitrant.
68. Types and Classification of
Disciplinary Penalties
1. Depending on the gravity of the offence,
one of the following penalties may be
imposed on a civil servant for breach of
discipline:
a) oral warning;
b) written warning;
c) fine up to fifteen da's salary;
d) fine up to three moth's salary;
e) down grading up to the period of two
years;
f) dismissal
59
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1)(ሀ) እስከ (ሐ)
የተዘረዘሩት ቅጣቶች ቀላል የዲሲፕሊን
ቅጣቶች ተብለው ይመደባሉ፡፡
3. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1)(መ) እስከ (ረ)
የተዘረዘሩት ቅጣቶች ከባድ የዲሲፕሊን
ቅጣቶች ተብለው ይመደባሉ፡፡
4. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1)(ሠ) መሠረት
ከሥራ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ በማድረግ
የተቀጣ የመንግሥት ሠራተኛ የቅጣት
ጊዜውን ሲያጠናቅቅ፣
ሀ) ከመቀጣቱ በፊት ይዞት ከነበረው
የሥራ መደብ ጋር ተመሳሳይ ክፍት
የሥራ መደብ ካለ ያለምንም
ተጨማሪ የደረጃ ዕድገት አፈጻጸም
መመሪያ እና፣
ለ) ከመቀጣቱ በፊት ይዞት ከነበረው የሥራ
መደብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ክፍት የሥራ
መደብ ካልተገኘ ከፍት የሥራ መደቡ
በተገኘ ጊዜ ያለምንም ተጨማሪ የደረጃ
ዕድገት አፈጻጸም መመሪያ፣በሥራ መደቡ
ላይ እንዲመደብ ይደረጋል፡፡
5. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
በዲስፕሊን ከተቀጣ በኋላ ቅጣቱ
በሪከርድነት ሊቆይና ሊጠቀስበት
የሚችለው፣
ሀ) ቀላል የዲስፕሊን ቅጣት ከሆነ ቅጣቱ
ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ለሁለት ዓመት፣
2. The penalties specified under Sub-
Article (1) (a)-(c) of this Article shall be
classified as simple disciplinary
penalties.
3. The penalties specified under Sub-
Article (1) (d) - (t) of this Article shall
be classified as rigorous penalties.
4. A civil servant who is demoted in
accordance Article (1) (e) of this Article
and upon the lapse of his period of
punishment, shall be reinstated:
a) when a similar vacant post is
available, without any promotion
procedures;
b) in the absence of a vacant post, he
shall be reinstated to a similar post
without any promotion procedures
when it becomes available at a later
time.
5. After a disciplinary measure has been
taken on a civil servant, such measure
shall be refer to and remain as a record:
a) for two years, where the penalty is
simple;
60
ለ) ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት ከሆነ ቅጣቱ
ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ዓመት
ይሆናል፡፡
69. ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች
የሚከተሉት ጥፋቶች ከባድ የዲስፕሊን
ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች ናቸው፤
1. ሕጋዊ ትእዛዝን ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣
በመለገም፣ ወይም ሆነ ብሎ የአሠራር ሥነ-
ሥርዓት ወይም የመንግስትን ፖሊሲ
ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፤
2. ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም
ባለጉዳዮችን ማጉላላት፤
3. ሥራ እንዳይሠራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፤
4. በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፤
5. በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነት መደባደብ፤
6. በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፤
7. ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤
8. በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም፤
9. የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤
b) for five years, where the penalty is
rigorous.
69. Offences Entailing Rigorous Penalties
Rigorous disciplinary penalties may be
imposed for the following offences:
1. to undermine one's duty by being
disobedient, negligent or tardy or by
none observance of working
procedures;
2. deliberate procrastination of cases or
mistreatment of clients;
3. to deliberately obstruct work or to
collaborate with others in committing
such offence;
4. unjustifiable repeated absenteeism or
nonobservance of office hours in spite
of being penalized by simple
disciplinary penalties;
5. to initiate physical violence at the place
of work;
6. neglect of duty by being alcoholic or
drugaddict;
7. to accept or demand bribes;
8. to commit an immoral act at the place
of work;
9. to commit an act of theft or breach of
trust;
61
10. የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤
11. በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
12. በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም፤
13. በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም፤
14. በዚህ አንቀጽ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈጸም፡፡
70. የዲስፕሊን እርምጃ አወሳሰድ
1. ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
መደበኛ የዲስፕሊን ምርመራ
የሚያካሂድና የውሳኔ ሀሳብ ለመሥሪያ
ቤቱ የበላይ ኃላፊ የሚያቀርብ
የዲስፕሊን ኮሚቴ ማቋቋም አለበት፡፡
2. የዲስፕሊን ቅጣት የማንኛውንም
ፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ ወይም
ሳይከተል ሊወሰን ይችላል፡፡
3. ቢሮው የዲስፕሊን አፈጻጸም ዝርዝር
መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፡፡
71.ሠራተኛን ከሥራ አግዶ ስለማቆየት
1. 1. ማንኛውንም የመንግሥት ሠራተኛ
ከሥራ አግዶ ማቆየት የሚቻለው፣
ሀ) ከተጠረጠረበት ጉዳይ ጋር አግባብነት
10. to commit an act of
misrepresentation 'or
fraudulent act;
11. to inflict damages to the property of
the government due to an intentional
act or negligence;
12. abuse of power;
13. to commit sexual harassment at the
place of work;
14. to commit any breach of discipline of
equal gravity with the offences
specified under this Article. .
70. Taking Disciplinary Measures
1. Any government institution shall
establish a disciplinary committee
which shall conduct formal
disciplinary investigation and thereby
submit recommendations to the head of
the government institution.
2. Disciplinary measures may be
takenirrespective of any court
proceedings or decision.
3. The Bureau shall issue the descpilnary
implementing directives.
71. Suspension from Duty
1. Any civil servant will be suspended
from duty if it is presumed that:
a) he may obstruct the investigation by
62
ያላቸውን ማስረጃዎች በማበላሸት፣
በመደበቅ ወይም በማጥፋት
ምርመራውን ያሰናክላል፣ወይም
ለ) በመንግሥት ንብረት ላይ ተጨማሪ
ጉዳት ያደርሳል፣
ሐ) ከተከሰሰበት ጥፋት ክብደት አንጻር
የሌሎችን ሠራተኞች ሞራል የሚነካ
ወይም የተገልጋዩ ሕዝብ በመሥሪያ ቤቱ
ላይ ሊኖረው የሚገባውን እምነት
ያዛባል፣ወይም
መ) ተፈጸመ የሚባለው ጥፋት ከሥራ
ያስወጣል፣ተብሎ ሲገመት ነው፡፡
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት አንድ
ሠራተኛ ከሥራና ከደመወዝ ታግዶ ሊቆይ
የሚችለው ከሁለት ወር ለማይበልጥ ጊዜ
ይሆናል፡፡
3. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት ከሥራና
ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይ የሚደረግ
የመንግሥት ሠራተኛ ከመደበኛ ሥራው
ታግዶ የሚቆይበት ጊዜና ከሥራ
የታገደበት ምክንያት በመሥሪያ ቤቱ
የበላይ ኃላፊ ወይም በተወካዩ በጽሑፍ
እንዲገለጽለትና ቢሮው በግልባጭ
እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
4. የመንግሥት ሠራተኛው በተከሰሰበት
የዲስፕሊን ጥፋት ምክንያት ከሥራ
concealing, damaging or destroying
evidence related to the alleged offence;
b) he may commit additional offence on
the property of the government
institution;
c) the alleged offence is so grave as to
demoralize other civil servants or
negatively affect the public trust
towards civil servants; or
d) the disciplinary offence may lead to
dismissal.
2. A civil servant may be suspended from
duty and payment of salary in
accordance with sub-article (1) of this
Article only for a maximum period of
two months.
3. The decision given in accordance with
sub-article (2) of this Article shall be
communicated to the civil servant in
writing, stating the grounds and
duration of his suspension and signed
by the head of the government
institution or his representative and
copied to the Bureau.
4. Unless a decision of dismissal is
rendered against a suspended civil
63
እንዲሰናበት ካልተወሰነበት በስተቀር
በእግዱ ወቅት ሳይከፈለው የቀረው
ደመወዝ ያለወለድ ይከፈለዋል፡፡
5. የመንግሥት ሠራተኛው ከሥራ በመታገዱ
ምክንያት ከዕግዱ ጋር ያልተያያዙ ሌሎች
መብቶቹንና ግዴታዎቹን ተፈጻሚነት
አያስቀርም፡፡
6. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (2) ድንጋጌ ቢኖርም
ከሥራና ደመወዝ ታግዶ የቆየ ሠራተኛ
ከሥራ እንዲሰናበት ወይም በዚህ አንቀጽ
በንዑስ አንቀጽ (4) መሠረት ደመወዙ
እንዲከፈለውና ወደ ሥራው እንዲመለስ
ሳይደረግ የዕግዱ ጊዜ ካበቃ፣
ሀ) የመዘግየቱ ምክንያት የዲስፕሊን
ክሱን የማጣራቱ ሂደት
ውስብስብነት ከሆነ የመንግሥት
ሠራተኛው ግማሽ ደመወዙ
እየተከፈለው፣ ወይም
ለ) ለመዘግየቱ ምክንያት የሆነው
የመንግሥት ሠራተኛው ራሱ ከሆነ
ያለደመወዝ ክፍያ፣እግዱ እስከ አንድ
ወር ድረስ እንዲራዘም የመሥሪያ
ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሊወስን ይችላል፡፡
7. ከሥራና ደመወዝ ታግዶ የቆየ
የመንግሥት ሠራተኛ ከሥራ እንዲሰናበት
ወይም በዚህ ንዑስ አንቀጽ (4) መሠረት
servant, the salary withheld during the
suspension shall be paid to him without
interest.
5. The suspension of a civil servant shall
not deprive him of other rights and
duties that are not affected by the
suspension.
6. Notwithstanding the provisions of sub-
article (2) of this Article, if the
suspension period of a civil servant
form duty and payment of salary
expires before his dismissal or
reinstatement with payment of salary in
accordance with sub-article (4) of this
Article, the head of the government
institution may extend the suspension
for a period of up to one month:
a) with payment of half salary if the
delay is caused by the complexity of
investigation of the disciplinary
charge; or
b) with out payment of salary if the
cause of delay is attributable to the
civil servant himself.
7. If the initial or extended period of
suspension of a civil servant form duty
and payment of salary expires either
before the dismissal of the civil servant
or his reinstatement with payment of
his salary in accordance with sub-article
(4) of this Article, the suspension from
64
ደመወዙ እንዲከፈለውና ወደ ሥራው
እንዲመለስ ሳይደረግ መደበኛውም ሆነ
የተራዘመው የዕግድ ጊዜ ከተጠናቀቀ
የሥራና የደመወዝ እግዱ ተነስቶ
የዲስፕሊን ክሱ መታየት ይቀጥላል፤
ሆኖም ለመዘግየቱ ምክንያት የሆኑ
የኮሚቴ አባላትና የሥራ ኃላፊዎች
በዲስፕሊን ጥፋት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
72. የይርጋ ጊዜ
1. ቀላል የዲስፕሊን ቅጣት የሚያስከትል
ጥፋት የፈፀመ የመንግሥት ሠራተኛ
የፈጸመው ጥፋት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ
እስከ ስድስት ወር እርምጃ ካልተወሰደበት
በዲስፕሊን ተጠያቂ አይሆንም፤ ሆኖም
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እርምጃ
ያልወሰደው የሥራ ኃላፊ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡
2. በወንጀል ጭምር የሚያስጠይቅ ከባድ
የዲስፕሊን ቅጣት የሚያስከትል ጥፋት
የፈጸመ የመንግሥት ሠራተኛ የወንጀሉን
ክስ ለማቅረብ በወንጀል ሕጉ በተቀመጠው
የይርጋ ጊዜ ውስጥ በዲስፕሊን ካልተከሰሰ
በጥፋቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
3. በወንጀል የማያስጠይቅ ከባድ የዲስፕሊን
duty and payment of salary shall be
lifted and the investigation of the
disciplinary charge shall continue;
provided, however, that committee
members and officers responsible for
the delay shall be liable for disciplinary
offence.
72. Period of Limitation
1. Disciplinary measure shall not be taken
against a civil servant who has
committed an offence entailing simple
disciplinary penalty unless such measure
is taken within six months, from the time
the commission of the offence is known;
provided , however, that the official who
has failed to take the disciplinary
measures within the time limit shall be
held responsible.
2. No disciplinary charge shall be brought
against a civil servant who has
committed an offense entailing rigorous
disciplinary penalty and such offense
also subjected to criminal liability,
Unless the disciplinary charges is
brought within the time limit provided in
the criminal code for such criminal
offense.
3. No disciplinary charge shall be brought
65
ቅጣት የሚያስከትል ጥፋት የፈጸመ
የመንግሥት ሠራተኛ የደንብ መተላለፍን
ክስን ለማቅረብ በወንጀል ሕጉ በተደነገገው
የይርጋ ጊዜ ውስጥ በዲስፕሊን ካልተከሰሰ
በጥፋቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
4. በዚህ ንኡስ አንቀጽ (2) እና (3) የተደነገጉት
የዲስፕሊን ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜያት
ቢኖሩም የዲስፕሊን ክስ ለማቅረብ ኃላፊነት
ያለበት የሚመለከተው የሥራ ኃላፊ ጥፋት
መፈጸሙን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ስድስት
ወር ውስጥ ክሱን ካላቀረበ በዲስፕሊን
ጥፋት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
5. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ከገንዘብ
ጋር የተያያዙ መብቶቹን ለሚመለከተው
አካል በስድስት ወር ውስጥ ካላቀረበ
በይርጋ ይታገዳል፡፡
ንኡስ ክፍል ሁለት
የቅሬታ አቀራረብና አፈታት
73. ቅሬታ
ለዚህ ንኡስ ክፍል አፈጻጸም “ቅሬታ” ማለት
የመንግስት ሠራተኛ ከቅርብ ኃላፊው ወይም
ከሚመለከተው የሥራ ኃላፊ ጋር በሚደረገው
ውይይት ሊፈታ ያልቻለና በመደበኛ የማጣራት
ሂደት ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው አቤቱታ ነው፡፡
ቢሮው ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ያወጣል፡፡
against a civil servant who has
committed an offense entailing rigorous
disciplinary penalty and such offense is
not subjected to criminal liability, Unless
the disciplinary charges is brought
within the time limit provided in the
criminal code for petty offenses.
4. Notwithstanding the provisions of Sub-
Articles (2) and (3)of this Article the
official, who has failed to take the
measures within a peiod of one year,
shall be held responsible.
5. Any c1aim by a civil servant for
payment ofmoney shall be barred by
limitation after six months from the date
it becomes due.
SUB- SECTION TWO GRIEVANCE HANDLING PROCEDURE
73. Grievance
For the purpose of application of this Sub-
Section, “grievance” means a complaint of a
civil servant that could not be resolved
through discussion conducted with the civil
servant’s immediate supervisor or with the
concerned officer and should be addressed
through a formal review procedure. The
Bureau shall issue the detail dicectives.
66
74. የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ዓላ
የመንግሥት ሠራተኞች ቅሬታ አቀራረብና አፈታት የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፤
1. ለቅሬታዎች አፋጣኝ መፍትሔ የመስጠት፤
2. ለቅሬታዎች መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉ ስህተቶችንና ድክመቶችን የማረም፤ እና
3. ሁሉንም የመንግሥት ሠራተኞች በእኩልነት ለማስተናገድ የሚያስችል እና ፍትሐዊ የሆነ አሠራር በማስፈን የሰመረ የሥራ ግንኙነት የማዳበር፡፡
75. የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ማቋቋም
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
የመንግሥት ሠራተኞች የሚያቀርቡትን
ቅሬታ እየተቀበለ በማጣራት የውሳኔ ሀሳብ
ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የሚያቀርብ
የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ማቋቋም አለበት፡፡
76. የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴው ተግባር
የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ከሚከተሉት ጋር
በተያያዘ የመንግሥት ሠራተኛው
የሚያቀርባቸውን ቅሬታዎች እያጣራ የውሣኔ
ሀሣብ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፤
1. ከሕጎችና መመሪያዎች አተረጓጎም ወይም
አፈጻጸም፤
2. ከመብቶችና ጥቅሞች አጠባበቅ፤
3. ከሥራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት
ሁኔታዎች፤
74. Objectives of Grievance Handling Procedure
Civil servants’ grievance handling procedure
of shall have the following
objectives:
1. to provide expeditious remedy for
grievances;
2. to rectify mistakes and weaknesses that
are causes for grievances;
3. to provide equitable and fair treatment
to all civil servants and thereby
promote smooth work relationship.
75. Establishment of Grievance
Handling Committee
Any government institution shall
establish a grievance handling committee
that conducts grievance inquiry, and
submits recommendation to the Head of
the government institution.
76. Duties of Grievance Handling
Committee
A grievance handling committee shall have
the duty to investigate complaints
lodged by civil servants and submit
recommendations relating to:
1. interpretation and implementation of
laws and directives;
2. protection of rights and benefits;
3. occupational safety and health;
67
4. ከሥራ ምደባና ደረጃ አሰጣጥ፤
5. ከሥራ አፈጻጸም ምዘና፤
6. በሥራ ኃላፊ ከሚፈጸሙ ተገቢ ያልሆኑ
ተፅዕኖዎች፤
7. በአዋጁ አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ (1)(ሀ)
እና (ለ) በተመለከቱት መሠረት
ከሚወሰዱ የዲስፕሊን እርምጃዎች፤
8. የሥራ ሁኔታዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች
ጉዳዮች፡
77. አስተዳደራዊ ውሳኔ
1. “አስተዳደራዊ ውሳኔ” ማለት
የመንግሥት መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ
በዚህ ክፍል የተደነገጉትን ጉዳዮች
በሚመለከት በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም
በዲስፕሊን ኮሚቴ ተጣርተው በቀረቡ
ጉዳዮች ወይም በቀጥታ በሕግ በተሰጡት
ሌሎች ጉዳዮች ላይ በጽሁፍ የሚሰጠው
ውሳኔ ነው፡፡
2. የዚህ ንኡስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም
የመንግስት መስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ
ሥነ-ሥርዓቱን ሳይጠብቅም ሆነ በቃል
የሚሰጠው ውሳኔ ለሰራተኛው ፍትህ
የማግኘት መብት ለማረጋገጥ ሲባል
ሰራተኛው በቃለ መሃላ ካረጋገጠ እንደ
አስተዳደር ውሳኔ ይቆጠራል፡፡
4. placement and promotion;
5. performance appraisal;
6. undue influence exerted by supervisors;
7. disciplinary measures provided under
Article 68(1)(a) and (b)
8. other issues related to conditions of
service.
77. Administrative Decision
1. “Administrative decision” means a
decision given in writing by the head of
a government institution in the case of
matters referred to in this Section on the
recommendation of disciplinary or
grievance committee or on other matters
directly falling under his authority in
accordance with the law.
2. Notwithstanding sub-article (1) of
this Article, a decision given by the
head of a government institution
either without following the formal
procedure or verbally shall be
construed as an administrative
decision.
68
ክፍል አስር
የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት
78. መቋቋም
1. የመንግሥት ሠራተኞች በዚህ አዋጅ
አንቀጽ 81 መሠረት የሚያቀርቡትን
የስራ ክርክር አይቶ የሚወስን
አስተዳደር ፍርድ ቤት በዚህ አዋጅ
ተቋቁሟል፡፡
2. የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ የሚቀርቡለትን
ይግባኞች መርምረው ውሳኔ የሚሰጡ
ችሎቶች ይኖሩታል፡፡
3. እያንዳንዱ ችሎት በቢሮው የሚሰየሙ
አንድ ሰብሳቢና ሁለት አባላት ያሉት
ዳኞች ይኖሩታል፡፡
4. የአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች
ሥራቸውን ስለሚሠሩበት ሁኔታ፣
መጠበቅ ስለሚገቧቸው ሥነ-ምግባር፣ እና
ሌሎች ሁኔታዎች በቢሮው በሚወጣ
መመሪያ ይወሰናል፡፡
79. የአስተዳደር ፍርድ ቤት ሥልጣንና ተግባር
1. የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ፣
ሀ) የሚቀርቡለትን ጉዳዮች በዳኝነት
የማየትና ትዕዛዝና ውሳኔ የመስጠት፣
ለ) የመንግሥት ሠራተኛ ውሳኔ
ተሰጥቷል ብሎ በቃለ መሃላ አስደግፎ
የሚያቀርበውን ይግባኝ ተቀብሎ
SECTION TEN
CIVIL SEREVANTS ADMINISTRATIVE
TRIBUNAL
78. Establishment
1. An Administrative Tribunal, which
hears, litigates and decides cases
brought to it on the basis of Article 81
of this Proclamation, is hereby
established.
2. The Administrative Tribunal shall have
chambers which examine and decide
on appeal cases.
3. Each chamber shall have a chairperson
and two members designated by the
Bureau.
4. The Bureau shall issue directives
relating to the manner of execution of
function of judges of the
Administrative Tribunal, the code of
ethics they should observe, and other
related matters.
79. The powers and duties of the
Administrative Tribunal
1. The Administrative Tribunal shall
have:
a) the Judicial power to give decision
and order for issues related to
judicial inquiry,
b) the power to hear and decide on
69
የማየት፣ የዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል፡፡
2. አስተዳደር ፍርድ ቤቱ የሚሰጣቸው
ትዕዛዞችና ውሳኔዎች እንደ ማናቸውም
የፍትሐብሔር ፍርድ ቤት ትዕዛዞችና
ውሳኔዎች ይቆጠራሉ፡፡
80.በአስተዳደር ፍርድ ቤት ስለሚታዩ ጉዳዮች
የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ የሚከተሉትን ጉዳዮች
አይቶ የመወሰን ሥልጣን ይኖረዋል፤
1. ከሚከተሉት ጋር በተያያዘ በመንግሥት
ሠራተኞች የሚቀርቡለትን ይግባኞች፤
ሀ) ከሕግ ውጪ ከሥራ መታገድ ወይም
አገልግሎት መቋረጥ፤
ለ) ከከባድ የዲስፕሊን ቅጣት ውሳኔ፤
ሐ) ከሕግ ውጪ የደመወዝ ወይም ሌሎች
ክፍያዎች መያዝ ወይም መቆረጥ፤
መ) በሥራ ምክንያት ከደረሰ ጉዳት
የመነጨ መብት መጓደል፤
ሠ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 77(7)
ከተመለከተው በስተቀር በቅሬታ አጣሪ
ኮሚቴ ታይተው ውሳኔ
ከተሰጠባቸው ጉዳዮች፤
ረ) የሥራ መልቀቂያና የአገልግሎት
ማስረጃ ለማግኘት ከቀረበ ጥያቄ፤
2. ጊዚያዊ ሠራተኞችና በማቋቋሚያ ሕጋቸው
የመንግስት ሠራተኞች ሕግ መሠረታዊ
appeals brought by a civil servant
on thebasis os oath.
2. The orders and decisions given by the
ተhe Administrative Tribunal shall be
deemed to be the order and decision of
any court of competent jurisdiction.
80. Jurisdiction of the
Administrative Tribunal
The Administrative Tribunal shall have the
power to hear and decide on:
1. appeals lodged by civil servants
relating to:
a) unlawful suspension or termination
of service;
b) rigorous disciplinary penalty;
c) unlawful attachment or deduction
of salary or other payments;
d) infringement of rights arising from
employment injury;
e) except provided under Article
77(7) of this Proclamation, cases
decided upon investigation by
grievance handling committee;
f) request for termination letters and
certificate of service;
2. appeals lodged by temporary
employees and employees of
government institutions authorized by
70
ዓላማዎችን በመከተል በራሳቸው የውስጥ
መመሪያ ሠራተኞቻቸውን እንዲያስተዳድሩ
የተፈቀደላቸው መሥሪያ ቤቶች ውስጥ
ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች
የሚያቀርቧቸውን ይግባኞች፣
3. የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ይግባኝ የተባለበትን
አስተዳደራዊ ውሳኔ ከመረመረ በኋላ
ውሳኔውን ለማጽናት፣ ለመሻር ወይም
ለማሻሻል ይችላል፡፡
4. የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሰጠ
በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ የውሳኔን
ግልባጭ ለይግባኝ ባዩ ወይም ለመስሪያ
ቤቱ ተወካይ እንዲደርሰው ማድረግ
አለበት፡፡
5. የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ በፍሬ ነገር
ክርክር የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ
ይሆናል፤ ሆኖም የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ
ውሳኔ የሕግ ስህተት አለበት ብሎ
የሚከራከር ወገን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ
በደረሰው በ60 ቀን ውስጥ ይግባኙን
ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ
ይችላል፡፡
81.የውሳኔ አፈጻጸም
1. ማንኛውም የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤት
የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ
በደረሰው በአስር የስራ ቀናት ውስጥ
መፈጸም አለበት፡፡
their establishment legislations to
administer their employees in
accordance with directives issued
following the basic principles of the
civil service laws.
3. The Administrative Tribunal may, after
hearing an appeal, confirm, reverse or
vary an administrative decision.
4. The Administrative Tribunal shall
make a copy of the decision be
received by the appealer or the
representative of the Bureau with in
five working days.
5. The decision of the Administrative
Tribunal on question of facts shall be
final; provided, however, that any
party who claims that the decision of
the Administrative Tribunal has error
of law, may appeal to the Federal
Supreme Court within 60 days from
the date of decision of the
Administrative Tribunal.
81. Execution of Decision
1. Any government institution of the
Region shall comply with the
decision of the Administrative
Tribunal within ten business days.
71
2. በአዋጁ አንቀጽ 80(3) እና (4) መሠረት
ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ እስከ 30 ቀን
ድረስ አልተፈጸመልኝም በማለት የውሳኔው
ተጠቃሚ ሲያመለክት የአስተዳደር ፍርድ
ቤቱ ውሳኔውን እንዲያስፈጽምለት በክልሉ
ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
ይመራለታል፡፡
3. የአስተዳደር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ
ያላስፈጸመው የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ
በመስሪያ ቤቱና በሠራተኛው ላይ
ለሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
ክፍል አስራ አንድ የሥራ ውል ማቋረጥና ማራዘም
82.በራስ ፈቃድ የሥራ ውል ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
በማንኛውም ጊዜ የአንድ ወር ቅድሚያ
ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሥራውን
በፈቃዱ ሊለቅ ይችላል፤ ሆኖም መስሪያ
ቤቱ ሠራተኛውን በቀላሉ ሊተካው
የሚችል ከሆነ የአንድ ወሩን ጊዜ
ሳይጠብቅ ስንብቱን ሊፈቅድለት
ይችላል፡፡
2. Where the beneficiary of a decision
pleaded that the decision of the
Administrative Tribunal given in
accordance with Article 80(3) and
(4) of this Proclamation is not
executed within 30 days, the
Administrative Tribunal shall refer
the case to the Region First Instance
Court to enforce the execution of the
decision.
3. The head of the government
institution who failed to execute the
decision of the Administrative
Tribunal shall be liable for the
damage sustained by the institution
and the civil servant.
SECTION ELEVN
TERMINATION AND EXTENSION OF
SERVICE
82. Resignation of a license willingly
1. Any civil servant may, by giving a
one month prior notice, resign at any
time; provided, however, that the
government institution may release
him prior to the end of the notice
period if it can easily replace him.
72
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተውን
የአንድ ወር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ
ሳይሰጥ አገልግሎቱን ያቋረጠ የመንግሥት
ሠራተኛ ግዴታውን ባለመወጣቱ
ለሚደርሰው ጉዳት እንደተገቢነቱ በፍትሐ
ብሔር እና በወንጀል ሕግ መሠረት
ተጠያቂ ይሆናል፡፡
3. የመንግሥት ሠራተኛው ለሥራው እጅግ
አስፈላጊና በቀላሉ ለመተካት የማይቻል
ሆኖ ሲገኝ ወደ ፊት ከሚቀጠርበት መስሪያ
ቤት ጋር በመስማማት የመልቀቂያውን
ጥያቄ ሠራተኛው ካመለከተበት ቀን ጀምሮ
ከሦስት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ሊራዘም
ይችላል፡፡
83. በሕመም ምክንያት አገልግሎት ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በዚህ
አዋጅ አንቀጽ 42(2) ወይም (4)
በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ
ለመመለስ ካልቻለ በሕመም ምክንያት
አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
2. የአዋጁ አንቀጽ 59(3) ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ በሥራው ምክንያት
ጉዳት የደረሰበት የመንግሥት ሠራተኛ
ለዘለቄታው መሥራት አለመቻሉ
በሕክምና ማስረጃ ሲረጋገጥ አገልግሎቱ
ይቋረጣል፡፡
2. Any civil servant, who has
terminated his service without giving
a one month prior notice referred to
in sub-article (1) of this Article, shall
have civil and criminal liability for
any damages caused by such failure.
3. Where the service of the civil servant
is indispensable and he could not be
replaced easily, his release may, in
agreement with his future employer,
be delayed for a period not exceeding
three months counted from the date
of application.
83. Termination Due to Illness
1. Where a civil servant is unable to
resume work within the time
specified under Article 42(2) or (4)
of this Proclamation, he shall be
deemed unfit for service and his
service shall be terminated.
2. Without prejudice to the provisions
of Article 59(3) of this Proclamation,
where a civil servant who has
sustained employment injury is
medically determined to be
permanently disabled, his service
shall forthwith be terminated.
73
3. የአዋጅ አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ (3)(ለ)
መሠረት በሚፈጸመው ዝውውር
ተስማምቶ ለመስራት ፈቃደኛ ያልሆነ
የመንግሥት ሠራተኛ አገልግሎቱ
ይቋረጣል፡፡
84.በችሎታ ማነስ ምክንያት ከሥራ ማሰናበት
1. የሙከራው ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግስት
ሠራተኛ በሥራ አፈጻጸም ውጤቱ
የችሎታ ማነስ ከታየበት ተገቢው የአቅም
ማጎልበት ሥልጠናዎች ተሰጥተውት
ካልተሻሻለ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
2. የመንግሥት ሠራተኛ ያለውን ዕውቀትና
ችሎታ እየተጠቀመ በተመደበበት ሥራ
ላይ የሥራ አፈጻጸም ውጤቱ በተከታታይ
ለሶስት ጊዜ ከሚጠበቀው ውጤት በታች
ከሆነ በችሎታ ማነስ አገልግሎቱ
ይቋረጣል፡፡
3. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (2) ድንጋጌ ቢኖርም
ለተከታታይ አምስት ዓመታት ከፍተኛ
የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ሲያገኝ
የነበረ የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ
አፈጻጸም ምዘና ውጤቱ በተከታታይ
ለአራት ጊዜ ከሚጠበቀው ውጤት በታች
ካልሆነ በስተቀር ከሥራ አይሰናበትም፡፡
3. If a civil servant does not agree on a
transfer that could be affected in
accordance with sub-article 3(b) of
Article 25 of this Proclamation, his
service shall be terminated.
84. Termination on Grounds of
Inefficiency
1. The service of a civil servant who has
completed his probation period may be
terminated due to inefficiency where his
performance evaluation result indicate
his inefficiency and has shown no
improvement after being given
appropriate capacity building training.
2. The service of a civil servant may be
terminated due to inefficiency where his
performance evaluation result is below
satisfactory for three successive
evaluation periods despite exerting all
his knowledge and ability to accomplish
his work.
3. Notwithstanding the provisions of sub-
article (2) of this Article, a civil servant
whose performance evaluation result is
above satisfactory for five successive
years may not be dismissed on grounds
of inefficiency unless his performance
evaluation result becomes below
satisfactory for the following four
successive evaluation periods.
74
4. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (2) እና (3) መሠረት
የመንግሥት ሠራተኛውን ከሥራ
ማሰናበት የሚቻለው እንደአስፈላጊነቱ
በአዋጁ አንቀጽ 30 ላይ የተቀመጠውን
የሥራ አፈጻጸም ምዘና ዓላማ በመከተል
ይሆናል፡፡
85. ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሥራ ማሰናበት
1. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግሥት
ሠራተኛ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት
በሥራ ገበታው ላይ ካልተገኘ ምክንያቱን
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለመሥሪያ ቤቱ
ማሳወቅ አለበት፡፡
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት
ሪፖርት የተደረገለት የመንግሥት
መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ ወይም
ተወካዩ ሠራተኛው ከሥራ ገበታው ላይ
የተለየበት ምክንያት ከአቅም በላይ
መሆኑን ካረጋገጠ የመንግሥት
ሠራተኛው ይዞት የነበረውን የሥራ
መደብ ለስድስት ወር ክፍት አድርጎ
መጠበቅ አለበት፡፡ ሆኖም የመንግሥት
ሠራተኛው በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ
ወደ ሥራው ካልተመለሰ ከሥራ
ማሰናበት ይቻላል፡፡
3. የዚህ ንኡስ አንቀጽ (2) ድንጋጌ ቢኖርም
የመንግስት ሰራተኛው ከስድስት ወር
በላይ በሥራ ላይ ያልተገኘው በእስር
4. The termination of service of a civil
servant under sub-article (2) and (3) of
this Article shall, as may be necessary,
be effected for the achievement of' the
purposes of performance evaluation
under Article 30 of this Proclamation.
85. Termination due to Force Majeure
Situations
1. A civil servant who has completed
probation and is absent from work due
to force majeure, shall inform the
situation within one month to the
respective government institution.
2. The government institution that has
received the reasons of absence of a
civil servant in accordance with sub-
Article (1) of this Article shall, after
verifying the validity of the reason,
keep the post of the civil servant vacant
for six months. Provided, however, that
the service of a civil servant may be
terminated if he is unable to resume
work within the six months.
3. Notwithstanding sub-article (2) of this
Article, if a civil servant who isabsent
from work due to detention for more
75
ምክንያት ከሆነና ከተጠረጠረበት
የወንጀል ድርጊት በነፃ ስለመለቀቁ
ማስረጃ ካቀረበ የመንግስት መስሪያ ቤቱ
ባለው ክፍት የሥራ መደብ ቀደም ሲል
ይከፈለው የነበረውን ደመወዝ እያገኘ
ወደ ሥራ እንዲመለስ ማድረግ አለበት፡፡
4. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ የሙከራ ጊዜውን
ያጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ
ባልታወቀ ምክንያት ለተከታታይ አሥር
ቀናት ከመደበኛ የሥራ ቦታው ላይ
ከተለየ በየአስር ቀናት ልዩነት
በተከታታይ ለሁለት ጊዜ በማስታወቂያ
ተጠርቶ ለመንግስት መሥሪያ ቤቱ
ሪፖርት ካላደረገ ከሥራ ይሰናበታል፡፡
5. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (4) መሠረት
በማስታወቂያ ጥሪ የተደረገለት
የመንግሥት ሠራተኛ ከሥራ ከተለየበት
ቀን ጀምሮ አንድ ወር ከመሙላቱ በፊት
ወደ ሥራው ለመመለስ ለመንግስት
መሥሪያ ቤቱ ሪፖርት ካደረገ የመሥሪያ
ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሠራተኛው ከሥራ
የቀረበትን ምክንያት በመመርመር
የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ
እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ሥራው
እንዲመለስ ይደረጋል፡፡
6. የዚህ ንዑስ አንቀጽ (4) ቢኖርም ከስራ
than six months produces an evidence
of his acquittal, the government
institution shall reinstate him on any
vacant position by maintaining his
previous salary.
4. Without prejudice to the provisions of
sub-article (1) of this Article, when a
civil servant who has completed his
probation is absent from his work for
ten consecutive workings days due to
unknown reasons, the government
institution may terminate his service
after calling him to report by two
consecutive notices of ten days each.
5. A civil servant who has reported to
work pursuant to the notices made in
accordance with sub-article (4) of this
Article if reports to work within a
month from the first day of his absence
shall, without prejudice to the
administrative measure that may be
taken by the head of the government
institution upon examining the reasons
of his absence, be reinstated to his
position.
6. Notwithstanding the provisions of sub-
article (4) of this Article, a government
76
የተሰናበተ ሰራተኛ ከሥራ ከቀረበት ቀን
ጀምሮ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከሥራ
የቀረበት ምክንያት ከአቅም በላይ
ለመሆኑ ለመሥሪያ ቤቱ ሪፖርት
ካደረገና በቂ ማስረጃ ካቀረበ በመሥሪያ
ቤቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ ክፍት
የሥራ መደብ ከተገኘ የመሥሪያ ቤቱ
የበላይ ኃላፊ ወይም ተወካዩ ሲፈቅድ
ወደ ሥራ ሊመለስ ይችላል፡፡
7. የሙከራ ጊዜውን ያላጠናቀቀ
የመንግሥት ሠራተኛ ባልታወቀ
ምክንያት ለአንድ ወር ጊዜ በሥራ
ገበታው ላይ ካልተገኘ ያለተጨማሪ ሥነ-
ሥርዓት አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
86. የሠራተኛ ቅነሳ
1. ማንኛውንም የመንግሥት ሠራተኛ፣
ሀ) የሥራ መደቡ ሲሰረዝ፣
ለ) መሥሪያ ቤቱ ሲዘጋ፣
ሐ) ትርፍ የሰው ኃይል ሲኖር፣
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 29(1) መሠረት
ለመደልደል ካልተቻለ ወይም የመንግሥት
ሠራተኛው ዝቅ ባለ የሥራ ደረጃ ላይ
ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆነ ከሥራ
ይሰናበታል፡፡
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1)(ሐ) መሠረት
ቅነሳ የሚደረገው የመንግሥት
ሠራተኛው በመሥሪያ ቤት ውስጥ
institution may, upon authorization by
the head of the institution or his
representative, reinstate a civil servant
to a similar vacant position if he reports
to work within six months from the date
of his absence by producing sufficient
evidence to prove that his absence was
caused by force majeure.
7. The service of a civil servant who has
not completed his probation shall be
terminated without any additional
formality where he is absent from work
due to unknown reasons.
86. Retrenchment
1. Any civil servant shall be retrenched
where: a) his position is abolished;
b) the government institution is closed; or
c) redundancy of man power is
created;
and where it is not possible to reassign him
in accordance with Article
29(1) of this Proclamation or where he is
reluctant to accept a position of a lower
grade.
2. Retrenchment of a civil servant in
accordance with sub-article (1) (c) of
this Article shall be made when it is
77
በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ ካሉ
ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ጋር
ሲወዳደር በሥራ ውጤቱና ባለው
ችሎታ ዝቅተኛ መሆኑ ሲረጋገጥ
ነው፡፡
87. በዲስፕሊን ምክንያት ከሥራ ማሰናበት
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ (1)(ረ) መሠረት በዲስፕሊን ቅጣት የተወሰነበትና በአስተዳደራዊ ይግባኝ ውሳኔው ያልተሰረዘለት የመንግሥት ሠራተኛ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
88. በዕድሜ ምክንያት አገልግሎት ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በዚህ
አዋጅ አንቀጽ 93 መሠረት አገልግሎቱ
ካልተራዘመ በስተቀር በሕግ ከተወሰነው
የመጦሪያ ዕድሜ ከደረሰበት የመጨረሻ
ወር የመጨረሻ ቀን ጀምሮ አገልግሎቱ
እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት በጡረታ
ለሚሰናበት የመንግሥት ሠራተኛ ጡረታ
ከመውጣቱ ከሶስት ወር በፊት በጽሑፍ
እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
89. በሞት ምክንያት አገልግሎት ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
ከሞተበት ቀን ጀምሮ አገልግሎቱ
proved that his performance and
qualification are lower when compared
with other civil servants holding the
same position.
87. Termination of Service on
Disciplinary Grounds
The service of a civil servant shall be
terminated where a disciplinary penalty
under sub-article (1) (f) of Article 68 of this
Proclamation is imposed on him and the
penalty is not reversed by the Administrative
Tribunal on appeal.
88. Retirement
1. The service of a civil servant whose
service is not extended beyond
retirement age pursuant to Article 93 of
this Proclamation shall be terminated on
the last day of the last month in which
he attained the retirement age
determined by law.
2. A civil servant who retires in
accordance with sub-article (1) of this
Article shall be notified of his
retirement in writing three months prior
to his retirement.
89. Termination on the Ground of
Death
1. The service of a civil servant shall be
terminated on the day of his death.
78
ይቋረጣል፡፡
2. አገልግሎቱ በሞት ምክንያት የተቋረጠ
የመንግሥት ሠራተኛ የሞተበት ወር
ሙሉ ደመወዙ እንዲሁም በዚህ አዋጅ
አንቀጽ 40(1) መሠረት ላልተወሰደ
የዓመት ዕረፍት ፈቃድ የሚፈጸም ክፍያ
ለትዳር ጓደኛው፣ የትዳር ጓደኛ ከሌለው
ለሕጋዊ ወራሾች ይከፈላል፡፡
3. አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የመንግሥት
ሠራተኛ በሞት ምክንያት አገልግሎቱ
ሲቋረጥ ለሚሠራበት መሥሪያ ቤት
በጽሑፍ ላሳወቃቸው የትዳር ጓደኛው
ወይም በስሩ ይተዳደሩ ለነበሩ ቤተሰቦች
የሦስት ወር ደመወዝ በአንድ ጊዜ
ይከፈላል፤ ሆኖም የትዳር ጓደኛውን
ወይም በሥሩ የሚተዳደሩ ቤተሰቦቹን
ሳያስመዘግብ የሞተ እንደሆነ ሥልጣን
ካለው አካል ወይም ፍርድ ቤት በሚሰጥ
ማስረጃ መሠረት ክፍያው ይፈጸማል፡፡
4. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት
የሚሰጠው ክፍያ ከግብርና ከጡረታ
መዋጮ ነጻ ይሆናል፤ እንዲሁም በዕዳ
ሊከበር ወይም በማቻቻያነት ሊያዝ
አይችልም፡፡
90 .የአገልግሎት ምስክር ወረቀት አሠጣጥ
1. ለማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
2. The full salary for the month in which a
civil servant has passed away as well as
the payment referred to in Article 41(1)
of this Proclamation for unused annual
leaves shall be paid to his spouse or in
the absence of spouse to his legal heirs.
3. Without prejudice to the provisions of
the relevant pension law, where a civil
servant dies, a lump sum of payment
equivalent to his three months’ salary
shall be paid to his spouse or members
of his family who were dependent on
him, and were communicated, in
writing, by him to the government
institution; provided, however, that in
the absence of such communication of
the spouse or family members, the
payment shall be effected upon the
production of evidence given by a
competent body or court.
4. The payment under sub-article (3) of
this Article shall be exempted fromtax
and pension contribution; and shall not
be subject to attachment or setoff.
90. Certificate of Service
1. A certificate of service to be issued
79
የሚሰጥ የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት
ሠራተኛው ሲያከናውን የነበረውን የሥራ
ዓይነት፣ የአገልግሎት ዘመኑና ሲከፈለው
የነበረውን ደመወዝ የሚገልጽ መሆን
አለበት፡፡
2. የሥልጠና ውል ግዴታ ወይም
በመንግሥት መሥሪያ ቤቱ የሚፈለግበት
ማናቸውም ዕዳ ያለበት የመንግስት
ሠራተኛ በማንኛውም ምክንያት
አገልግሎቱን ሲያቋርጥ የውል ግዴታውን
ስለመፈጸሙ ወይም ከዕዳ ነጻ መሆኑን
የሚገልጽ ማስረጃ ከማግኘቱ በፊት የሥራ
ልምድ የምስክር ወረቀት አይሰጠውም፡፡
3. የዚህ ንኡስ አንቀጽ (2) በሥራ ላይ እያለ
የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት
ለሚጠይቅ የመንግስት ሠራተኛ ተፈጻሚ
አይሆንም፡፡
91. አገልግሎት ሲቋረጥ የሚፈጸም ክፍያ
1. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግሥት
ሠራተኛ በአዋጁ አንቀጽ 86 መሠረት
በቅነሳ ምክንያት ከሥራ ከተሰናበተና
የሥራ ውሉ በተቋረጠበት ዕለት የጡረታ
አበል የማይከፈለው ከሆነ፣
ሀ) ለመጀመሪያ አንድ ዓመት የሦስት ወር
ደመወዝ፣
ለ) በተጨማሪ ለአገለገለበት ለእያንዳንዱ
ዓመት የወር ደመወዙ አንድ ሦስተኛ
to any civil servant shall indicate the
type and length of his service as well
as his salary.
2. If a civil servant who is bound by an
obligation of a training contract or is
indebted towards the government
institution terminates his service for
any reason, he shall not be entitle to
a certificate of service before
obtaining a clearance certificate for
discharging his obligations.
3. The provisions of sub-article (2) of
this Article shall not be applicable to
a civil servant whose service is not
terminated.
91. Severance Pay
1. Any civil servant who has been
retrenched under Article 86 of this
Proclamation and is not entitled to
pension allowance on the date of the
termination of his service shall be paid:
a) his three months’ salary for the first
year of his service; and
b) One-third of his monthly salary for
each additional year of his service;
80
እየታከለ፣ይከፈለዋል፤ሆኖም የሚሰጠው
ክፍያ ከሠራተኛው የአሥራ ሁለት ወር
ደመወዙ መብለጥ የለበትም፡፡
2. የሙከራ ጊዜውን ለጨረሰና ከአንድ ዓመት
በታች ላገለገለ የመንግስት ሠራተኛ
የሚፈጸመው ክፍያ ከአገልግሎቱ ጋር
ተመጣጣኝ ይሆናል፡፡
92.አገልግሎትን ማራዘም
1. የመንግሥት ሠራተኛ የመጦሪያ ዕድሜው
ከደረሰ በኋላ በአንድ ጊዜ እስከ አምስት
ዓመት በጠቅላላው ከአሥር ዓመት
ለማይበልጥ ጊዜ አገልግሎቱን ማራዘም
ይቻላል፡፡
2. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የአንድን
የመንግሥት ሠራተኛ አገልግሎት
ማራዘም የሚቻለው፣
ሀ) የሠራተኛው ትምህርት፣ ልዩ ዕውቀትና ችሎታ ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ ጠቃሚ ሆኖ ሲገኝ፣
ለ) በደረጃ ዕድገት፣ በዝውውር ወይም በቅጥር ተተኪ ሠራተኛ ለማግኘት አለመቻሉ ሲረጋገጥ፣
ሐ) ሠራተኛው ለሥራው ብቁ መሆኑ በሕክምና ማስረጃ ሲረጋገጥ፣
መ) ሠራተኛው አገልግሎቱን ለመቀጠል ሲስማማ፣ እና
ሠ) የአገልግሎቱ መራዘም ጥያቄው የመጦሪያ ዕድሜው ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ለቢሮው ቀርቦ ሲፈቀድ
provided, however, that such payment
shall not exceed his 12 months’salary.
2. A civil servant who has completed his
probation and served for less than one
year shall be entitled to severance pay in
proportion to his service.
92. Extension of Service
1. The service of a civil servant may be
extended beyond his retirement age for
a period up to five years at a time and
for a period not exceeding ten years in
total.
2. The service of a civil servant may be
extended under sub-article (1) of this
Article where:
a) his qualification, special skill and
ability is found to be essential to the
government institution;
b) it is not possible to replace him by
another civil servant through
promotion, transfer or recruitment;
c) he is proved fit for service by
medical certificate;
d) he has agreed to the extension of his
service; and
e) the extension is approved by the
Bureau upon a request submitted
three months prior to the date of his
retirement.
81
ነው፡፡
ክፍል አሥራ ሁለት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
93. የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ የደመወዝ
ጭማሪና ሌላ ጥቅም መሰረዝ
1. የሐሰት የትምህርት ወይም የሥራ ልምድ
ማስረጃ በማቅረብ ወይም ሥልጣን
በሌለው ሰው ወይም ይህን አዋጅ ወይም
አዋጁን ለማስፈጸም የወጣውን ደንብና
መመሪያ ወይም ሌላ ማናቸውንም ሕግ
በመተላለፍ የተፈፀመ ቅጥር፣ የደረጃ
ዕድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ ወይም ሌላ
ጥቅም በዲስፕሊንና በወንጀል
የሚያስከትለው ተጠያቂነት እንደተጠበቀ
ሆኖ በመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም
ቢሮው በማናቸውም ጊዜ ይሰርዛል፡፡
2. የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ የደመወዝ
ጭማሪ ወይም ሌላ ጥቅም የተሰረዘበት
የመንግሥት ሠራተኛ በዲስፕሊንና
በወንጀል መጠየቁ እንደተጠበቀ ሆኖ
የመሰረዙ እርምጃ እስከተወሰደበት ጊዜ
ድረስ የተከፈለውን ደመወዝና ሌሎች
ጥቅሞች እንዲመልስ አይጠይቅም፡፡
3. ከሕግ ውጭ ቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣
የደመወዝ ጭማሪ ወይም ሌላ ጥቅም
SECTION TWELVE
MISCELLANEOUS PROVISIONS
93. Nullification of Appointment,
Promotion, Salary Increment and
Other Benefits
1. If any appointment, promotion, salary
increment or other benefits is effected
upon presentation of false evidence of
education or experience or effected by
unauthorized person or contravenes this
Proclamation, regulations and directives
issued for the implementation of this
Proclamation or any other law, it shall,
without prejudice to disciplinary and
criminal liabilities, be nullified by the
head of the government institution or the
Bureau.
2. Without prejudice to his disciplinary and
criminal liability, a civil servant whose
appointment, promotion, salary
increment or other benefits has been
nullified may not be requested to pay
back the salary and other benefits he has
received up to the date of the
nullification.
3. An official or member of a committee
who intentionally or with gross
negligence authorizes unlawful
82
እንዲሰጥ ሆን ብሎ ወይም በከባድ
ቸልተኝነት የፈቀደ የሥራ ኃላፊ ወይም
የኮሚቴ አባል አግባብ ባለው የዲስፕሊን፣
የወንጀል ሕግ እና የፍትሐብሔር ሕግ
ድንጋጌዎች መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
4. በዚህ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት
የተጠቀሰው ጥፋት መፈጸሙን የመሥሪያ
ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም ቢሮው
ከደረሰበት ጥፋቱን ለማረም የሚያስችል
እርምጃ መውሰድ እና ኃላፊውን ወይም
የኮሚቴ አባሉን በወንጀልና በፍትሐብሔር
ሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ሥልጣን ላለው
የመንግሥት አካል የተፈጸመውን ድርጊት
በማስረጃ አስደግፎ ማቅረብ አለበት፡፡
94. የሥልጣን ውክልና ስለመስጠት
ቢሮው የፐብሊክ ሰርቪሱን የሰው ሀብት ሥራ
አመራር ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በዚህ አዋጅ
የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት ለመሥሪያ
ቤቶች በውክልና ማስተላለፍ ይችላል፡፡
95. የአዋጁን አፈጻጸም ስለመቆጣጠር
1. ቢሮው ይህን አዋጅና በአዋጁ መሠረት
የሚወጡትን ደንቦችና መመሪያዎች
በትክክል በሥራ ላይ መዋላቸውን
የመቆጣጠር ሥልጣንና ኃላፊነት
appointment, promotion, salary
increment or other benefits shall be
liable under the relevant disciplinary,
criminal and civil law provisions.
4. Where the head of the government
institution or the Bureau finds out that a
fault specified under sub-article (3) of
this Article has been committed, it shall
take corrective measure and submit the
case with pertinent evidence to the
relevant government body that has the
power to initiate criminal or civil
proceedings against the persons
responsible for the violation.
94. Delegation of Power
The Bureau may delegate its powers and
duties under this Proclamation to
government institutions where it deems it
necessary for the efficient and effective
human resource management of the public
service.
95. Supervision of Implementation of
the Proclamation
1. The Bureau shall have the powers and
duties to supervise the proper
implementation of this Proclamation
and regulations and directives issued
hereunder.
83
ይኖረዋል፡፡
2. ቢሮው በዚህ ንዑስ አንቀጽ (1)
የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት ተግባራዊ
ለማድረግ በማናቸውም ጊዜ፣
ሀ) በመንግስት መሥሪያ ቤቶች በመገኘት ወይም እንዲላኩለት በማዘዝ ማህደሮችንና ሌሎች መረጃዎችን መመርመር፣ እና
ለ) ጉዳዩ የሚመለከተውን የሥራ ኃላፊ ወይም ሌሎች የመንግስት ሠራተኞች በቃል ወይም በጽሁፍ እንዲያስረዱ መጠየቅ፣ይችላል፡፡
3. ቢሮው በዚህ ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት በሚያደርገው ምርመራ ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ ሕግ መጣሱን ወይም አድሎ መፈጸሙን ከደረሰበት፣
ሀ) ትክክል ያልሆነ አሠራር እንዲስተካከል የማዘዝ፣
ለ) ጉዳዩ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ አፈጻጸሙን የማገድ፣
ሐ) ለድርጊቱ ተጠያቂ በሆነው የሥራ ኃላፊ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ ላይ ተገቢው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የማድረግ፣ እና
መ) በአዋጁ አንቀጽ 93(4) መሠረት የመፈጸም፣ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
2. The Bureau, in exercising its powers
and duties under sub-article (1) of this
Article, may at any time:
a) examine files and other records by
sending inspectors to government
institution or by ordering them to
submit such files and records; and
b) require the concerned official or other
civil servants to give oral or written
explanation.
3. Where the Bureau, through its
investigation under sub-article (2) of
this Article or otherwise, discovers that
the law is infringed or a discriminatory
act is committed, it shall have the
power:
a) to order the rectification of the
irregularities;
b) to suspend the execution of the
matter until decision is made there
on;
c) to cause the taking of appropriate
administrative measures against the
official or the civil servant
responsible for the act; and
d) to act in accordance with Article 93
(4) of this Proclamation.
84
96.ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን
1. አዋጁን ለማስፈጸም የሚያስፈልግ ደንብ የክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት ሊያወጣ ይችላል፡፡
2. ቢሮው አዋጁንም ሆነ ደንቡን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
97. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች
1. ቢሮው ለክፍት የሥራ መደቦች
አመልካቾች በፈተና ተወዳድረው
የሚመረጡበትን የመግቢያና የብቃት
ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችሉ
መመዘኛዎችና መለኪያዎች በአገር አቀፍ
ደረጃ እስኪዘረጋ ድረስ የመንግሥት
ሠራተኞች ቅጥርን፣ የደረጃ እድገትን፣
ዝውውርና ድልድልን በተመለከተ በዚህ
አዋጅ በተደነገጉት ሌሎች መስፈርቶች
ብቻ አፈጻጸማቸው ይቀጥላል፡፡
2. የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ምደባና
የደመወዝ ደረጃ ደንብ ቁጥር 2 (የሕግ
ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 419/1964)፣
እና በሥራ ላይ ያሉ መመሪያዎች የአዋጁ
ድንጋጌዎች እስካልተቃረኑ እና በዚህ
አዋጅ አንቀጽ 96 መሠረት በሚወጡ
ደንቦች እና መመሪያዎች እስከሚተኩ
ድረስ ተፈጻሚነታቸው ይቀጥላል፡፡
96. Power to Issue Regulations and
Directives
1. The Council of the Region may issue
regulations necessary for the
implementation of this Proclamation.
2. The Bureau may issue directives
necessary for the implementation of the
Proclamation and Regulation.
97. Provisions
1. Until the Bureau adopts national criteria
and parameters that enable the
establishment of eligibility and
competence certification for examining
and selecting applicants for vacant
posts, the other selection criteria
provided for by this Proclamation alone
shall continue to apply to the
recruitment, promotion, transfer and
redeployment of civil servants.
2. The relevant provisions of the Public
Service Position Classification and
Scale Regulations No. 2 (Legal Notice
No. 419 of 1972), and existing
directives shall, in so far as they are
consistent with this Proclamation,
remain in force until replaced by
regulations and directives issued in
accordance with Article 96 of this
Proclamation.
85
98. የተሻሩ ሕጎች
1. የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ 47/94 በዚህ አዋጅ ተሽሯል፡፡
2. ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ፣ መመሪያ፣ የአሠራር ልምድ በዚህ አዋጅ ውስጥ የተደነገጉትን ጉዳዮች በሚመለከት ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
99. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ በክልሉ ምክር ቤት ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
ሀዋሳ --------------- ቀን 2011 ዓ.ም
ሚሊዮን ማቴዎስ
የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት ፕሬዝደንት
98. Repealed Laws
1. The South Nations, Nationalities and
Peoples Region Civil Servants
Proclamation No. 47/2002 is here by
repealed.
2. No law, directive or practice shall, in so
far as it is inconsistent with this
Proclamation, have force or effect in
respect of matters provided for by this
Proclamation.
99. Effective Date
This Proclamation shall enter into
force on the date of its approval by
the Region council.
Hawassa --------------- 2018
Milion Mathewos
South Nations, Nationalities and Peoples’
Region State President
1
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት
ደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ
DEBUB NEGARIT GAZETA
OF THE SOUTHERN NATIONS, NATIONALITEIS AND PEOPLES REGIONAL STATE
የተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን
ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር /2011
መግቢያ፣
የክልሉ መንግሥት በሃገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ዘላቂ እና ተቋማዊ
ለማድረግ እንዲሁም የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎቻችን ለመወጣት የሚያሰችልና
ከደረስንበት ዕድገት ደረጃ አንጻር የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ፈትሾ
ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
የክልላችንን የኢኮኖሚ ዕድገት በላቀ ደረጃ ለማፋጠን የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት የተልዕኳቸውን
ስፋትና ተቀራራቢነት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደገና መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣
በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕገ-መንግስት አንቀፅ 51 ንዑስ
አንቀፅ 3 (ሀ) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
bdb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ
?ZïC KLልE መንግሥት Mክር b@T ጠባቂነት የወጣ
ዋጅ
Year No
Hawassa /2018
›mT q$_R
hêú qN ጥቅምት //፪ሺ፲፩ ዓ.M
2
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ
አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር /2011” ተብሎተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡-
1) “ክልል” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ነው፡፡
2) “ክልል ምክር ቤት” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት ምክር ቤት ነው፡፡
3) “መስተዳድር ምክር ቤት” ማለት በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 65 መሠረት የተገለጸው ሆኖ በዚህ አዋጅ
አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው ከፍተኛ የአስፈፃሚ አካል ወይም ካቢኔ
ነው፡፡
4) “አስተዳደር ምክር ቤት” ማለት እንደአግባብነቱ የዞን፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣
የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ አስተዳደር አስፈፃሚ አካል ወይም ካቢኔ ነው፡፡
5) “አስተዳደር እርከን” ማለት እንደአግባብነቱ በክልሉ የሚገኙ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣
የወረዳ፣ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ እና የገጠርና ከተማ ቀበሌ አስተዳደርን
ያጠቃልላል፡፡
6) “የአስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤት” ማለት ቢሮ፣ ኮሚሽን፣ ኤጀንሲ፣ ኢንስቲቲዩት፣
ጽሕፈት ቤት፣ ባለስልጣን መሥሪያ ቤት እና ሌሎች የመንግሥት አስተዳደር
3
ተግባር ለማከናወን በዚህ አዋጅና በሌሎች ሕጐች መሰረት የተቋቋሙትንና
በሥራቸው ያሉትን መሥሪያ ቤቶችን ያጠቃልላል፡፡
7) “ቢሮ” ማለት ለመስተዳደር ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑ የክልሉ አስፈፃሚ መስሪያ
ቤቶች ናቸው፡፡
8) “ኃላፊ ወይም ምክትል ኃላፊ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የአስፈፃሚ አካላት
መሥሪያ ቤቶችን በበላይነት ለመምራት በኃላፊነት የተሾመ ወይም የተመደበ ኃላፊ
ወይም ምክትል ኃላፊ ነው፡፡
9) “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡
ክፍል ሁለት
ስለአስፈፃሚ አካላት መስሪያ ቤቶች
3. መቋቋም
1) የሚከተሉት የአስፈፃሚ አካላት መስሪያ ቤቶች የመስተዳደር ምክር ቤት አባል
ሆነው በዚህ አዋጅ ተቋቁመዋል፡፡
1) የሰላምና ፀጥታ ቢሮ
2) የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
3) ጠቅላይ አቃቤ ህግ
4) የግብርና ቢሮ
5) የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
6) የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
7) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
8) የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ
9) የትምህርት ቢሮ
10) የጤና ቢሮ
11) የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ
12) የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ
4
13) ¾›=”}`ý^õ‹“ ¾›=”Æeƒ] MTƒ u=a
14) የገቢዎች ባለሥልጣን
15) የባህል፤ ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ
16) ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ
17) የሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ
18) የእንስሳት እና አሳ ሃብት ልማት ቢሮ
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የተቋቋሙ የአስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤቶች
ተጠሪነት ለክልል መንግሥት መስተዳድር ምክር ቤትና ለርዕሰ መስተዳድሩ ይሆናል፡፡
ክፍል ሦስት
ስለርዕሰ መስተዳድሩ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና መስተዳድር ምክር ቤት
4. መስተዳድር ምክር ቤት
1) የሚከተሉት የመስተዳድር ምክር ቤት አባላት ናቸው፣
ሀ) ርዕሰ መስተዳድሩ፣
ለ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ እና
ሐ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 ከተራ ቁጥር 1 እስከ 17
የተመለከቱትን አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎች፡፡
2) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 (ሐ) የተመለከተው ማንኛውም ኃላፊ በመስተዳደር
ምክር ቤቱ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መገኘት
በማይችልበት ጊዜ ምክትሉ ወይም ካንድ በላይ ምክትሎች ባሉ ጊዜ፤ በግልፅ
ተለይቶ በፅሁፍ ውክልና የተሠጠው ምክትል ኃላፊ ወይም በግልፅ ተለይቶ በፅሁፍ
ውክልና የተሠጠው ከሌለ በሹመት ቅድሚያ ያለው ምክትል ኃላፊ በመስተዳደር
ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ይገኛል፡፡
3)
5
5. የርዕሰ መስተደድሩ ስልጣንና ተግባር
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሥልጣንና ተግባር በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 68 የተመለከተው ይሆናል፡፡
6. የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ሥልጣንና ተግባር
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሥልጣንና ተግባር በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 69 የተመለከተው ይሆናል፣
7. የክልል መስተዳድር ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 66 የተመለከተው ይሆናል፡፡
8. የመስተዳደር ምክር ቤት አሰራር
1) የመስተዳደር ምክር ቤት ፡-
ሀ/ የራሱ የውስጥ ደንብ ይኖረዋል፤
ለ/ በውስጥ ደንቡ በሚወሰነው መሠረት መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች
ያደርጋል፤
ሐ/ ምልአተ ጉባኤ የሚባለው ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ሲገኙ ይሆናል፤
መ/ የሚያስተላልፈው ውሳኔ በተባበረ ድምጽ ይሆናል፤ በተባበረ ድምጽ መወሰን
ካልተቻለ በድምጽ ብልጫ ይወሰናል፡፡
2) ርዕሰ መስተዳድሩ፡-
ሀ/ የመስተዳደር ምክር ቤት አባላት አጀንዳ የማስያዝ መብታቸው እንደ ተጠበቀ
ሆኖ፣ ለምክር ቤቱ በአጀንዳ የሚቀርቡ ጉዳዮችን ይወስናል፤
ለ/ የመስተዳድር ምክር ቤቱን ስብሰባ ይመራል፤
6
ሐ/ ለመስተዳድር ምክር ቤቱ በአጀንዳ የቀረበ ጉዳይ በርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት
ቤት መታየት የሚያስፈልገው ሆኖ ካገኘው አጀንዳውን ለሌላ ጊዜ
ሊያስተላልፍ ይችላል፤
9. የርዕሰ መስተዳድር ጽህðት ቤት
1) የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት በተሻሻለው የክልሉ መንግሥት ሕገ-መንግሥት
አንቀጽ 70 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት የክልሉ መስተዳድር እና የርዕሰ መስተዳድር
ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ይሆናል፡፡
2) የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሥልጣንና ተግባር በተሻሻለው የክልሉ
መንግሥት ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 70 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ የተመለከተው
ይሆናል፡፡
3) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 ላይ የተÖቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ርዕስ መስተዳደሩ
ስልጣንና ተግባሩን ለማከናወን የሚረዱ ልዩ ልዩ ጽህፈት ቤቶችን ሊያቋቁም
ይችላል፡፡ ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል፡፡
ክፍል አራት
የአስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤቶች ሥልጣንና ተግባር
10. የወል ስልጣንና ተግባር
1) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 መሠረት የመስተዳድር ምክር ቤት አባል የሆነ እያንዳንዱ
የአስፈፃሚ አካል መሥሪያ ቤት በሥራው መስክ፡-
ሀ) ሕግና ፖሊሲዎች ያመነጫል፣ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም በስራ
ላይ ያውላል፣
ለ) ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፣ የአቅም ግንባታ ኘሮግራሞችን ተግባራዊ
ያደርጋል፣ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያደራጃል፣ እንደአስፈላጊነቱ
ያሰራጫል፣
7
ሐ) የፌዴራልና የክልሉን ሕጐች በስራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤
መ) በሕግ መሰረት ውሎችና ስምምነቶች ያደርጋል፣ ሠራተኛ ይቀጥራል፣
ያስተዳድራል፣ ያሰናብታል፣
ረ) የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂዎችንና የአካል ጉዳተኞችን የእኩል ተጠቃሚ
እና ሙሉ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ያመቻቻል፣
ሰ) በሚያዘጋጃቸው ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
የሴቶችንና የወጣቶችን ጉዳይ፣ የሕጻናት ጥቅምና ደህንነትን ያስጠብቃል፣
የአካባቢ ጥበቃን፣ የአደጋ ስጋት ስራ አመራርን፣ የሰብዓዊ መብት የድርጊት
መርሃ ግብር መካተታቸውን ያረጋግጣል፣ ተግባራዊ ያደርጋል ፣
2) በየአስተዳደር እርከን የሚገኙትን የአስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤቶችን እና
በማቋቋሚያ ሕጐቻቸው ተጠሪ የሆኑ የአስፈፃሚ አካላት መስሪያ ቤቶችን አፈፃጸም
በበላይት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ አደረጃጀታቸው፣ የሥራ ፕሮግራሞቻቸውን
እና በጀታቸውን መርምሮ ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንዲያቀርቡ
ይወስናል፣
3) ተጠሪው የሆኑ የክልሉ መንግስት የልማት ድርጅቶችን አግባብ ባለው ሕግ መሠረት
ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ የልማቱ አጋዥ ሆነው መስራታቸውን ያረጋግጣል፤
4) በዚህ አዋጅና በሌሎች ህጎች የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ
ያውላል፤
5) ስለሥራው አፈፃፀም በየወቅቱ ለርዕሰ መስተዳድሩ እና ለመስተዳድር ምክር ቤት
ሪፓርት ያቀርባል፣
8
11. የሠላምና ፀጥታ ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
1) ሰላምን ለማስጠበቅ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤ የአገርና ሕዝብ
ሰላም፣ ደህንነትና ነጻነት እንዲከበሩ የሚያስችል ስልት ይነድፋል፤ የግንዛቤና የንቅናቄ
ሥራዎችን ያከናውናል፤
2) በተለያዩ ኃይማኖቶችና እምነቶች ተከታዮች፣ እንዲሁም በተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግ አግባብ ካላቸው የመንግሥት
አካላት፣ የባህልና የኃይማኖት ተቋማት፣ እንዲሁም ከሌሎች አግባብነት ካላቸው አካላት
ጋር በመተባበር ይሠራል፤
3) ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር አገራዊ አንድነትና መግባባትን የሚያጎለብት
የባህል ልውውጥ፣ የስነ-ዜጋ ትምህርት እና ኪነ-ጥበብ የሚስፋፋበትን ሁኔታ
ያመቻቻል፤
4) በክልሉ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከል የሰላም፣ የመከባበርና የመቻቻል ባህል
እንዲዳብር የግንዛቤና ንቅናቄ ስልቶችን ይቀይሳል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፤
5) የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ በሚመለከት ጥናትና ክትትል ያደርጋል፣ የፀጥታ መረጃዎችን
ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ያሰራጫል ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል የክልሉን ሰላም
ያረጋግጣል፣
6) የክልሉን ሕዝብ ደህንነት፣ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር
ተባብሮ ይሠራል፣
7) በክልሉ ውስጥ ዘመናዊ የሆነ የፀጥታ መረጃ ፍሰት አያያዝና አደረጃጀት እንዲኖር
ስልት ይቀይሳል፣ ይተገብራል፣
8) የፀጥታ መረጃ ለማሰባሰብና ለማስተዳደር የሚረዳ ልዩ የፋይናንስና የበጀት አስተዳደር
እንዲሁም የሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ በመስተዳደር ምክር ቤት ውሳኔ ተግባራዊ
ያደርጋል፣
9) ከአጐራባች ክልሎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ፀጥታን በሚመለከት ግንኙነት
ያደረጋል፣ በድንበር አከባቢ ያለውን ህብረተሰብ ግንኙነት እንዲሻሻልና እንዲጠናከር
የሚረዱ ሥራዎችን ይሠራል፣
9
10) ክልሉ በሚያዋስናቸው ጐረቤት አገሮች ድንበር አካባቢ የግጭት ሁኔታ በመከታተል
መረጃ ያሰባስባል፣ ግጭት እንዳይከሰት የመከላከል ሥራዎችን ይሠራል፡፡ ሲከሰትም
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሔ እንዲያገኙ ያደረጋል፣
11) ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በግጭት መነሻ ምክንያቶች ላይ ጥናትና
ምርምር ያካሂዳል፣ የመፍትሔ ሃሳቦችና የአፈፃፀም ስትራቴጂዎችን ያቀርባል፣
ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
12) በክልሉ በሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች መካከል ግጭቶች እንዳይነሱ የመከላከል
ሥራዎችን ይሠራል፣ ሲከሰቱም በቁጥጥር ሥር ያውላል፣ የግጭቱን መንስዔ
አጣርቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣
13) በክልሉ በሰው ሰራሽ ወይም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን
በቋሚነት መልሶ ለማቋቋም የሚረዱ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶች አጥንቶ
ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያÅርጋል፣
14) በዕለት ዕርዳታ ስራ ላይ ከሚንሳቀሳቀሱ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ
ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል፣ አሰራራቸውን በበላይነት ይመራል ይቆጣጠራል፣
15) የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት eራዎችን ያከናውናል፣ የምግብ ዋስትና ችግር
ባለባቸው አካባቢዎች የሚካሄደውን የማገገሚያ ስርዐት ይዘረጋል፣ ሁሉም የምግብ
ዋስትና ፕሮግራሞች ተቀናጅተው እንዲፈፀሙ ያÅርጋል፣ ይቆጣጠራል፣
16) በተለያዩ ሃይማኖቶችና እምነቶች ተከታዮች መካከል ሠላምና መከባበር እንዲሰፍን
ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብ ካላቸው የመንግሥት አካላት፣
የሃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ማናቸውም አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤
17) በክልሉ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ የሀይማኖትና የእምነት ተቋማትን ይከታተላል፡፡
ፈቃድ ያድሣል፣ ሕገ-ወጥ ሆኖ ሲገኝም ፈቃድ ያግዳል፣ ይዘርዛል፤
18) የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ይከታተላል፣ በዚህም የሚፈጠሩ ችግሮችን
ለመፍታት የሚያስችሉ አሠራሮችን አጥንቶ ተግባራዊ ያደረጋል፣
19) በክልሉ ውስጥ ባሉ አስተዳደር እርከኖች መካከል የሚነሱ የማካለል ጥያቄዎች
በሠላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያደርጋል፣
10
20) የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽን ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
ያስተባብራል፣
21) በክልሉ በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ከብሔረሰቦች ማንነት ጋር ተያይዘው
በሚነሱ የድንበር ማካለል ጉዳዮች በብሔረሰቦች ምክር ቤት የሚሰጡትን ውሣኔዎች
ተግባራዊ ያደርጋል ፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
22) የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በአስቸኳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲቻል
ሲታዘዝ የፀጥታ ኃይል ያሠማራል፣
23) የፀጥታ መደፍረስ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት በሚወሰደው የመከላከል እርምጃ
በሴቶችና በህፃናት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የጥንቃቄ እርምጃ ይወስዳል፣
24) የሚሊሽያ ኃይልን አቅም በመገንባት የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ እንዲጠበቅ
ያደርጋል፣
25) ሚሊሻውን ፀጥታን ለማስከበር በሚያስችል አኳኋን ያደራጃል፣ እንደአስፈላጊነቱ
ከህዝቡና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
26) ሚሊሺያው ለረጅም ጊዜ ከምርት ሥራው ሳይነጠል በፀጥታና ሌሎች መንግሥታዊ
ሥራዎች ላይ እንዲሰማራ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
27) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
12. የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚŸተሉት ሥልጣንና ተግባራት Ãኖሩል፣
1) የክልሉን የልማት ዕቅድ አዘገጃጀትና አፈፃፀም ሥርዓት ይዘረጋል፣
የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር የክልሉን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት
ዕቅድ ያዘጋጃል ሲፈቀድም ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
2) የክልል መንግስት በጀት ያዘጋጃል፣ በተፈቀደው በጀት መሰረት ክፍያ ይፈፅማል፣
የበጀቱን አፈፃፀም ያስተዳድራል፣ ይገመግማል፣ ይቆጣጠራል፣
3) የክልሉ መንግስትን የበጀት፣ የሂሳብ፣ የክፍያና፣ የውስጥ ኦዲት ሥርዓት ይዘረጋል፣
በስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
11
4) የክልሉን መንግስት የገንዘብ ሰነዶች፣ ገንዘቦችና ንብረቶች ይይዛል ያስተዳድራል፣
5) የክልሉን መንግስት የብድርና ዕርዳታ ስምምነቶች ይፈርማል፣ ያስተዳድራል፣
6) ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትና ዕድገት የሚረዱ ጥናቶችን ያደርጋል ያሰራጫል፣
7) በኢኮኖሚና ማሕበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶችን ስራ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፣
8) የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መረጃዎችን ይሰበስባል ያደራጃል፣
ይተነትናል፣ ያሰራጫል፣
9) የክልሉን የፊዚካልና ማህበራዊ መሰረተ-ልማት ስርጭትና የተፈጥሮ ሀብት
የሚያሳይ ካርታና አትላስ ያዘጋጃል፣ ያሰራጫል፣
10) ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር የሂሳብ አያያዝ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር ስርዓት
ይመሰርታል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፣
11) የክልሉን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ያከናውናል፣ እርምጃ
ይወስዳል እንዲወስድም ያደርጋል'
12) የክልሉን የሥነ-ሕዝብ ጉዳይ በበላይነት ይመራል ያስተባብራል፣
13) የክልሉን መንግስት የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ያሳትማል፣ ያሰራጫል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል'
14) የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ህጎች ላይ ማብራሪያ ያዘጋጃል ያሰራጫል፣
15) ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ፕሮግራሞች
እንዲጠኑ ያደርጋል፣ አፈፃፀማቸውን ይገመግማል፡፡
16) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
13. ጠቅላይ አቃቤ ህግ
ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሚከተሉት ስልጣንና ተÓባራት ይ•ሩል፡-
1) በሕግ ጉዳዮች የክልል መንግስት ዋና አማካሪ እና ተወካይ ሆኖ ይሰራል፤
12
2) በፌደራል መንግስት ተዘጋጅቶ የጸደቀውን የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ በክልሉ ውስጥ
ተግባራዊ እንዲሆን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
3) የወንጀል ፍትሕ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማደራጀት፣ መተንተንና ማሰራጨት
የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስፈፅማል፡፡
4) በፌዴራልና በክልሉ ሕገ-መንግስታት እና በሌሎች ሕጎች የተደነገጉ የግልና የቡድን
መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች መከበራቸውን ያረጋግጣል፣
5) የወንጀል ጉዳይን በተመለከተ፤
ሀ) በክልሉ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር በሚወድቁ በማናቸዉም የፀረ-ሙስና እና
የታክስ ህጎችን በመጣስ በሚፈፀሙ የወንጀል ጉዳዮች እንዲሁም ከባድና
ውስብስብ በሆኑ ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች የወንጀል ምርመራ ከፖሊስ
ጋር አብሮ ያጣራል፣ምርመራውን በበላይነት ይመራል፡፡
ለ) በሕዝብ ጥቅም መነሻ ወይም በወንጀል የማያስጠይቅ ሁኔታ መኖሩ በግልፅ
ሲታወቅ የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ ወይም የተቋረጠው የወንጀል
ምርመራ እንዲቀጥል ያደርጋል፤ ማናቸውም የወንጀል ምርመራዎች በሕግ
መሰረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ አስፈላጊውን ህጋዊ ትእዛዝ
ለሚመለከተዉ አካል ይሰጣል፣
ሐ) ምርመራቸው በፖሊስ በተጀመረባቸው መካከለኛ፣ ቀላል እና በግል አቤቱታ
በሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ በአግባቡ ስለመከናወኑ በቅርበት
ክትትል ያደርጋል፤ በተጀመረ የወንጀል ምርመራ አስመልክቶ ፖሊስ
ለዓቃቤ ህግ ማሳወቁን ያረጋግጣል፤
መ) በወንጀል መዝገብ ላይ የተሰጠ የዓቃቤ ሕግና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን
ለሚመለከተው ፖሊስ ያሳውቃል፣ የወንጀል ምርመራ መዝገቦችን
አስመልክቶ በየደረጃው ባሉ ዓቃቤያነ ሕግ በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ በፖሊስ
የሚቀርቡ አቤቱታ ተቀብሎ ውሳኔ ይሰጣል፤
13
ሠ) የተጠናቀቁ የምርመራ መዝገቦችን ከሕግና ከማስረጃ አንፃር መርምሮ በሥነ-
ሥርዓት ሕግ መሰረት የተቀመጡ መመዘኛዎች ሲሟሉ የ’አያስከስስም’
ወይም የ’ተዘግቷል’ ውሳኔ ይሰጣል፤
ረ) የጥፋተኝነት ድርድር ይወስናል፣ ድርድር ያደርጋል፣ አማራጭ የመፍትሄ
እርምጃ እንዲወሰድ ይወስናል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
ሰ) መንግስትን በመወከል የወንጀል ጉዳዩች ክስ ይመሰረታል፣ ይከራከራል፣
ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ክስ ያነሳል፣ የተነሳ ክስ እንዲቀጥል
ያደርጋል፡፡
ሸ) የወንጀል ድርጊት ጠቋሚዎችና ምስክሮች በህግ መሰረት ጥበቃና ከለላ
እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
ቀ) በማረፊያ ቤትና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር ሥር ያሉ ተጠሪጣሪዎችንና
ታራሚዎችን ይጎበኛል፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ መሰረት
መፈጸሙን ያረጋግጣል፣ ሕገ ወጥ ተግባር ተፈፅሞ እንደሆነ እንዲታረም
ያደርጋል፡፡ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ
ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
በ) በዕርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶች በእርቅ የሚጠናቀቁበትን ሁኔታ
ያመቻቻል፣
ተ) ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጡዋቸው ውሳኔዎችና ትእዛዞች
መፈፀማቸውንና መከበራቸውን ይከታተላል፣ ሳይፈፀሙ ከቀሩ ወይም
አፈፃፀማማቸው ሕግን ያልተከተለ ከሆነ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ
ቤት በማመልከት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
ቸ) በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የወንጀል ቅጣቶች በአግባቡ እንዲፈፀሙ ለማድረግ
የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ያደራጃል ወይም መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፤
14
ኀ) የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በኩል እንዲቀርብ ያደርጋል፤
አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
6) የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በተመለከተ፤
ሀ) በክልል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የሕዝብ እና የክልል መንግስት መብትና
ጥቅም ወኪል ሆኖ ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ እንዲከበሩ ያደርጋል፣
የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
ለ) ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶችን የውል ዝግጅት እና ድርድር ከሚመለከታቸው
አካላት ጋር በመሆን ያደርጋል፣ የሕዝብና የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች
ጥቅም ይጎዳል ብሎ ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች ውል እና የመግባቢያ ሰነዶች
ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል ወይም የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤
ሐ) የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶችን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ ይመሰርታል፤
በከሰሱበት ወይም በተከሰሱበት የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ክርክር ያደርጋል፤
በተጀመረ ክርክር ተቋማትን ተክቶ በተናጠል ወይም በጋራ ይከራከራል፣ ወይም
በክርክር አመራር ላይ ለመሥሪያ ቤቶች አቅጣጫ ይሰጣል፣ በሕግ መሠረት
ለተሰጡ ዉሳኔዎች ፍርድን ያስፈፅማል፤
መ) በክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና በግል ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች መካከል
የሚከሰቱ የፍትሐብሔር ክርክሮች በድርድር እንዲያልቁ ጥረት ያደርጋል፤
ድርድሩ ካልተሳካ ጉዳዩን ስልጣኑ ለሚፈቅድለት ፍርድ ቤት አቅርቦ
ይከራከራል፣
ሠ) የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸው ያልተግባቡባቸው
የፍትሐብሔር ጉዳዩች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ
የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሳኔ ሀሳብ ይሰጣል፤ በውሳኔው መሰረት
መፈፀሙን ያረጋግጣል፤
15
ረ) የተመዘበረ የመንግስት ገንዘብ ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ
ያስመልሳል፡፡ የሙስና ወንጀል ዉጤት የሆኑት እና በፍርድ ሂደት ላይ ያሉ
ንብረቶችን ያስተዳድራል፤ እንዲወረስ ዉሳኔ የተሰጠባቸዉን ንብረቶች
ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል ያስተላልፋል፡፡
ሰ) የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም
ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ ይከራከራል፤
ሸ) የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ተበዳዩች እንዲካሱ መልሰው
እንዲቋቋሙ እንዲሁም ከጉዳቱ የተያያዙ የፍትሐብሔር ጥቅማቸውን
ለማስጠበቅ እነሱን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ ያቀርባል ወይም ይደራደራል፤
7) የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅ እና ማስረፅ ሥራን በተመለከተ፤
ሀ) በክልል መንግሥት የሚወጡ ሕጎች የሕግ ረቂቅ ዝግጅት ስራ ይሰራል፤
የመንግስት አካላት የሚያዘጋጁት ረቂቅ ህግ ከፌዴራልና ከክልሉ ሕገ መንግስትና
ከሌሎች ሕጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ለሚመለከታቸው
ክፍሎችም አስተያየት ያቀርባል፤
ለ) በክልሉ በስራ ላይ ባሉ ህጎች ጥናት በማድረግ ሕጎች እንዲሻሻሉ የውሳኔ ሀሳብ
ያቀርባል፣ ሲደገፍም ለተባሉት ማሻሻያዎች ረቂቆችን በማዘጋጀት
ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣
ሐ) ሕጐችን የማሰባሰብ፣የማጠቃለልና የኮዲፊኬሽን ሥራ ይሰራል፤ የክልሉን ህጎች
በባለአደራነት ይይዛል፣ ያሰራጫል፤
መ) ዓቃቤያነ ሕግ ስለ ስራቸው ያላቸውን አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት
በተከታታይ እና በየደረጃው ለማሳደግ ትምህርት እና ሥልጠና ይሰጣል፤
እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤
ሠ) የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ለማዳበር ለክልሉ ህብረተሰብ በተለያዩ ዜደዎች የንቃተ
ህግ ትምህርት ይሰጣል፤
16
8) የጠበቆች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት እና የሰነድ ማረጋገጥን በተመለከተ፤
ሀ) በክልሉ ፍርድ ቤቶች ለሚከራከሩ ጠበቆች ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ስራቸውን
ይቆጣጠራል፣ የጠበቆችን ዲሲፕሊን ጉዳዮች አይቶ ይወስናል፤ በህግ መሰረት
ይሰርዛል፣
ለ) በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያውያን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ማህበራትን
ይመዘግባል፣ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ስራቸውን
ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፣ በሕግ መሰረት ይሰርዛል፣
ሐ) አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ሰነዶችን ይመዘግባል፣ ያረጋግጣል፣ ይሽራል፣
ይሰርዛል፣
መ) ነፃ የሕግ ድጋፍ አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን ይቀርፃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን ያስተባብራል፤
9) ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀግብር መነሻ በማድረግ ክልላዊ ሰብአዊ መብት
የድርጊት መርሀ ግብርን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ አፈፃፀሙን
ይከታተላል፤ በክልል ደረጃ የሚመለከታቸውን አካላት ያስተባብራል፣ ለሚመለከታቸው
አካላት ሪፖርት ያቀርባል፤
10) የዓቃቤ ሕግ የውሳኔ አሰጣጥ እና የፍቅደ ሥልጣን አጠቃቀም ወጥነትን ለማረጋገጥ
በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የፀደቀ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፤
11) በዓቃቤያነ ሕግ የሚሰጡ ውሳኔዎች በሕግ መሰረት መከናወናቸውን የሚያረጋግጥ
የኢንስፔክሽን ክፍል ያደራጃል፣ ጉድለቶችን በጥናት አስደግፎ ይለያል፤ በግኝቱ መሠረትም
እንዲታረሙ ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፣
መልካም ተሞክሮዎችን ይቀምራል፤ ያስፋፋል፤
12) የክልሉን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
ያስተባብራል፤የህግ ታራሚዎች ይቅርታ የሚያገኙበትን ስርዓት ይዘረጋል፡፡
13) የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና
ተግባር በሚወስነው አዋጅ የመስተዳድር ምክር ቤት አባል ለሆኑ አስፈፃሚ አካል መስሪያ
ቤቶች የተሠጡ የወል ሥልጣንና ተግባርን ሥራ ላይ ያውላል፤
17
14) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
14. የግብርና ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት Ãኖሩል፣
1) የግብርና ልማትን ለማስፋፋት የግብርና ግብዓቶችን ማባዣ፣ የዕፅዋት ጥራት
ቁጥጥር ማዕከላትን፣ ማሰልጠኛ ተቋማትንና ላቦራ„ሪዎችን ያቋቁማል፣
ያeፋፋል፣
2) በግብርና ልማት ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ባለሀብቶች እና
ባለድርሻ አካላት መረጃና የቴክኒክ ድጋፍ ያÅርጋል፣
3) የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለአርብቶ
አደሩ እና ለግል ባለሀብቱ የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የሥልጠና አገልግሎቶች
እንዲስፋፉ ያÅርጋል፣
4) የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናው ኮሌጆችን ያስተዳድራል፣
የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ከክልሉ የሰው ኃይል ፍላጎት ጋር
መጣጣሙን ያረጋግጣል፣ ስልጠናው ፍላጎትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን
ያÅርጋል፣
5) የግብርና ግብዓት አቅርቦት፣ ስርጭትና ግብይት አቅምን ይገነባል፣ የብድር
አቅርቦትና ስርጭት ያመቻቻል፣ ያረÒግጣል፣
6) የግብርና ምርት ግብዓት ወይም ግብዓት ብዜት ዘርፍ ለሚሰማሩ ድርጅቶች
ወይም ግለሰቦች የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣ በሕግ
መሰረት ይcርዛል፣
7) የግብርና ኤክስቴንሽን መርሃ-ግብር ያዘጋጃል፣ ስትራቴጃዎችና ስልቶችን
ይቀይሳል፣ ይተÑብራል፣ የኤክስቴሽን ስርዓቱን uማጥናት እንዲሻሻል ያÅርጋል፣
8) አርሶ አደሮች በህብረት ስራ ማሕበራትና በግል ባለሀብቶች አማካይነት የሚካሄዱ
የዘር ብዜት ስራዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ የቴክኒክ ድጋፍና የምክር
አገልግሎት Ãሰጣል፣
9) ሕገ-ወጥ የግብርና ግብዓቶች ግብይትና ዝውውር ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ በሕግ
መሰረት እርምጃ ይወስÇM፣
18
10) ¾ግብርና ልማት ባለሙያዎችን መልምሎ ያሰለጥናል፣ የአርሶ ›ደሮች የስልጠና
ማዕከላትን ያsቁማል፣ ያስተÇÉራል፣
11) ከአጎራባች ክልሎች ወደ ክልሉ የሚገቡ የእፅዋት፣ የአዝርዕት እና ተዋፅኦ ላይ
ተገቢውን ቁጥጥር ያÅርጋል፣
12) በክልሉ የሰብል ሃብት ላይ ወረርሽን እንዳይከሰትና የደን ቃጠሎ እንዳይነሳ
ይከላከላል፣ ከተከሰተም በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር እንዲውል ያÅርጋል፣
13) በግብርና ምርት ላይ ተፅዕኖ የሚያስከትሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ይከታተላል፣
የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ይዘረጋል፣ አፋጣኝ እርምጃ ይ¨ስዳል፣
14) የሰፈራ ፕሮግራም በበላይነት ይመራል፣ ሰፋሪው እስከ መቋቋም ድረስ አስፈላጊ
የሆኑ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ግብዓትና መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ያÅ`Òል፣
15) የግብርና ምርቶች ግብዐት መሰረተ-ልማቶች ይገነባል፣ እንዲገነቡና እንዲስፋፉ
ያደርጋል፣
16) u›ጠቃላይ የክልሉን የግብርና፣ ግብዐትና የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ
ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ይተነትናል፣ ለሚመለከታቸው አካላት ያcራጫል'
17) ግብርና ምርምር ባለድርሻ አካላት በp”σ“ በትብብር የሚሰሩበትን ስርዓት
òረጋል፣
18) የሰብል ሃብት ልማት እንዲስፋፋ ያደርጋል፣ ተስማሚ ፖኬጆችን ያዘጋጃል፣
ተግባራዊ ያደርጋል፣
19) ¾ግብርና ምርት ግብዓት ጥራት አጠባበቅ ለ›Uራቾችና ለለ?ሎች ተዋንያን ¾U¡`
አገልግሎትና ስልጠና ይሰጣል፣ የግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ያÅርጋል'
20) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
15. የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል
1) ቢሮው ለአርሶ አደሩ፣ ለአርብቶ አደሩና ለግል ባለሃብቱ የሚሰጡ የዘርፉ የኤክስቴንሽን
አገልግሎት ቀልጣፋና ጥራት ያለው፣ ተደራሽና ውጤታማ እንዲሆን ሥርዓት
ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
2) ዘርፉ የሚጠይቀውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በትምህርት ዝግጅትና በሙያ መስክ
በጥናት ይለያል፣ ከሚመለከታቸው የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር በቅንጅት
ይሠራል፣
19
3) በምርታማነታቸውና በሽታን በመቋቋም የታወቁ የሀገረሰብና የውጭ ዝሪያ ያለቸው
እንስሳትን ይለያል፣ የዝርያ ማሻሻያ ሥራ ይሠራል፣ ያስፋፋል፣
4) በየደረጃው አስፈላጊ የሆኑ አደረጃጀቶች፣ ማሰልጠኛና ሠርቶ ማሣያ ማዕከላት፣
የህክመና መስጫ ተቋማት፣ ላብራቶሪዎችና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ያቋቁማል፣
የአስተዳደር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስተዳድራል፣
5) የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት በገበያ እንዲመራ ያደርጋል፣ የእንስሳትና አንስሳት
ተዋጽኦ ምርቶች ምርታማነትና የጥራት ደረጃ እንዲሻሻል ይሠራል፣ ቅድመና ድህረ-
ምርት ቴክኖሎጂዎች ያስተዋውቃል፣ አቅርቦቱን ይደግፋል፣ ያስፋፋል፣
6) በክልሉ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት የምርምር አቅም ይገነባል፣ የምርምርና
ስርፀት ሥርዓት ይዘረጋል፣
7) የእንስሳትና ዓሣ ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያና ማሻሻያ ግብአቶች አቀርቦትን
ያመቻቻል፣ እንዲመረቱ ያደርጋል፣ በዘርፉ የሚሰማሩ አካላትን አቅም ይገነባል፣
የብቃት ማረጋገጫ ይሠጣል፣ ይሰርዛል፣
8) የእንስሳት ክትባትና መድሐኒት አቅርቦት፣ ግብይት፣ አያያዝ ዝውውር ስርዓት
ይዘረጋል፣ የብቃት ማረጋገጫ ይሠጣል፣ ይቆጣጠራል፣ በህግ መሠረት እርምጃ
ይወስዳል፣
9) የእንስሳት ገበያና የዝውውር መስመሮችን ይወስናል፣ ይቆጣጠራል፣ የኳራንቲይን
አገልግሎት ይሰጣል፣ ከአጎራባች ክልሎችና ከፌዴራል መንግሥት አካላት ጋር
በቅንጅትና ትብብር ይሠራል፣
10) የእንስሣት በሽታ ወረርሽኝና ተዛማች በሽታዎች እና የውሃ አካላት ብክለት
የመከላከያና የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስፈጽማል፣ ሲከሰትም አፋጣኝ
እርምጃ ይወሰዳል፣
11) የእንስሳት የጤና አገልግሎት ይሰጣል፣ የእንስሳት በሽታዎች ምረመራ፣ አሰሳና
ቁጥጥር ሥራዎችን ያካሄዳል፣
12) በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ባለሀብቶ የቴክኖሎጂ አቅርቦትና
የኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ይሰጣል፣ ከአርሶ አደሩ ወይም አርብቶ አደሩ ጋር
በምርትና በግብይት እንዲተሳሰሩ ይደግፋል፣
13) የእንስሳትና ዓሳ ሀብት በልማት ቀጠናዎች ይለያል፣ እንዲለማ ተገቢውን ድጋፍ
ያደረጋል፣
20
14) በክልሉ ለሚገኙ ቄራዎችና የእርድ ቦታዎች የቁም እንስሳትና የበድን ስጋ ምርመራና
ቁጥጥር ያደርጋል፣ መስፈርቶችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊነታቸውን ይቆጣጠራል፣
ባለሙያ ይመድባል፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁትን ይዘጋል፣ አስፈላጊ እርምጃ
በሚመለከተው አካል እንዲወሰድ ያደርጋል፣
15) ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
16. የንግድ ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት Ãኖሩል፣
1) ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፣
2) በክልሉ ውስጥ ንግድን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ቀልጣፋ የግብይት ሥርዓትና
ተገቢ የንግድ አሠራር እንዲሰፍን ያደርጋል፣
3) አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣል፣
ይቆጣጠራል፣ ይሰርዛል፣ የንግድ መዝገብ ያደራጃል፣
4) በህግ በልዮ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ህገ-ወጥ
የግብርና ምርቶች ዝውውር ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ በህግ አግባብ እርምጃ
ይወስዳል፣
5) በህግ በልዮ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ የግብይትን
ሥርዓትን በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣
6) ተገቢ ያልሆነ የንግድ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የተሟላ ሥርዓት
ይዘረጋል፣ የንግድ ሕጎች መከበራቸውን ያረጋግጣል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣
7) በሕግ መሰረት ለሸማቾች ጥበቃ ያደርጋል፣ የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን
ሥርጨት ይቆጣጠራል፣
8) አገባብ ባለው አካል የዋጋ ቁጥጥር የተደረገባቸውን መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎችና
አገልግሎቶች መተግበራቸውን ይቆጣጠራል፣
21
9) አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸው የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የደረጃውን
መስፈርት ማሟላታቸውን ይቆጣጠራል፤ ከተዘጋጀላቸው ደረጃ በታች ሆነው
በተገኙት ላይ እርምጃ ይወስዳል፤
10) የሀገሪቱን ሕጋዊ ሥነልክ ሥርዓት በአግባቡ መተግበሩን ይቆጣጠራል፣
11) የንግድ የዘርፍና የሙያ ማህበራት እንዲቋቋሙ ያበረታታል፣ የተቋቋሙትንም
እንዲጠናከሩ ያደርጋል፣
12) ንግድን በማስፋፋት ረገድ የከተማና የገጠር፣ የከተሞች የእርስ በርስ ትስስር
እንዲጠናከር ስትራቴጂ ይቀይሳል ተግባራዊ ያደርጋል፣
13) በከተማ ስራ አጥ ዜጐች በጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ሥራዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ
የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ ያደራጃል፣ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
14) የኤግዚብሽንና ፕሮሞሽን ስራዎችን በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣
15) የግብርና ምርት ውጤቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ተገቢውን ገበያ በአገር ውስጥና
በውጭ እንዲያገኙ
16) ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣
17. የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል
1) በክልሉ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣
2) የትራንስፖርት አገልግሎቶች አቅርቦት በተቀናጀ መንገድ እንዲፈፀምና የክልሉን
የልማት ስትራቴጂዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲያገለግል መደረጉን ያረጋግጣል፤
3) የትራንስፖርት አገልግሎቶች አስተማማኝና ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ
የሚያስችል የቁጥጥር ሥርዓት እንዲዘረጋና ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
4) በሀገሪቱን የትራንስፖርት ፖሊሲዎች መሰረት በክልሉ በሚገኙ ውሃ አካላት ላይ
የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስፋፋ ያበረታታል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ይሰርዛል
5) በክልሉ የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ እንዲሻሻልና እንዲጠገን
ያደርጋል፣
22
6) የክልሉን የመንገድ ልማት ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣ ድረጃ ይወስናል፣
ያስተዳድራል፣ የዲዛይንና የግንባታ ጥራት ቁጥጥር ስራዎችን ያካሂዳል፣
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
7) በከተማ ታክሲ አገልግሎት ለሚሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ፈቃድ ይሰጣል፣ በዘርፉ
የሚቋቋሙ ማህበራትን ይመዘግባል፣ ስምሪት ይሰጣል፣
8) በክልሉ ለሚቋቋሙ የተሸከርካሪ ጥገና ጋራዦች፣ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትና
ለተሸከርካሪ አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣
ይሰርዛል፣
9) በህዝብና በጭነት ማመላለሻ ሥራ ላይ ለሚሰማሩ አካላት የብቃትና የሙያ ፈቃድ
ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ይሰርዛል፤ ለሚሰጡት አገልግሎት የሚያስከፍሉትን ታሪፍ
ያወጣል፣ ይከታተላል፤ ለህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችም ደረጃ ያወጣል፣ ያድሳል
10) ለአሽከርካሪዎችና ለተሸከርካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣
ይሰርዛል፣
11) የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና እና የቴክኒሻኖች ማሰልጠኛ ማዕከላት ያቋቁማል፣
ስልጠና ይሰጣል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ያደርጋል፣
12) የሕዝብና የጭነት ማመላለሻ መናኸሪያዎች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣ ያስተዳድራል፣
13) የመንገድ ትራንስፖርት ሕጎች መከበራቸውን ይከታተላል፣እርምጃ ይወስዳል፣
14) ባለሞተር ተሸከርካሪዎች ላይ የሚለጠፉ ሰሌዳዎችንና የትራንስፖርት ህትመቶችን
ያሳትማል፣ ያሰራጫ፣
15) በክልሉ የመንገድ ደህንነት ፈንድና ካውንስል ያቋቁማል፣
16) የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ሲከሰት ወይም በሌሎች አስፈላጊ ምክንያቶች የንግድ
ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን በአስፈላጊው ቦታና መስመር ደልድሎ ያሰማራል፣
ይከታተላል፣
17) ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል በቅንጅት ይሠራል፣
18) ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣
23
18. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩል፣
1) የከተማ ልማትንና ኮንስትራክሽንን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን፣
የልማት ፓኬጆችን እና ፕሮግራሞችን ይቅርጻል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣
2) የከተማ ነዋሪው ሕዝብ ከአቅሙ ጋር የተመጣጠነ መኖሪያ ቤት እንዲሰራ አጠቃላይ
አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ለተግባራዊነታቸውም ለከተሞች
የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣል፣
3) የከተሞችን የደረጃ መመዘኛና ደረጃ ይወስናል፣ ዕውቅና እንዲያገኙ ያደርጋል፣
4) ከተሞች የአካባቢያቸው የልማት ማዕከል እንዲሆኑ የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፣
5) የከተሞች ልማት ከገጠር ልማት እና ከድህነት ቅነሳ ጋር በተቀናጀ መንገድ
የሚከናወንበትን ሁኔታ በሚመለከት ጥናት ያደርጋል፣ ተግባራዊ እንዲሆን
ያግዛል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣
6) በከተሞች ዘመናዊ መሰረተ-ልማት እንዲስፋፋ ጥረት ያደርጋል፣ ለተለያዩ
አገልግሎቶች የሚውል የለማ መሬት ያዘጋጃል፣
7) የክልሉን ከተሞች ፕላን ያዘጋጃል፣ አተገባበራቸውን ይከታተላል፣ድጋፍ ይሰጣል
8) በከተማ ፕላን ዝግጅት ለሚሰማሩ አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል
ደረጃቸውን ይወስናል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይሰርዛል፣
9) ከተሞች የሚያመነጯቸውን ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች የሚወገድበትንና ውበት
ያላቸው የመናፈሻ አገልግሎቶች የሚመሰረቱበትን የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣
ድጋፍ ያደርጋል፣
10) በከተሞች ለሕዝብ ልማት ሲባል ለመንግስታዊ ፕሮጀክቶችና ለሌሎች አገልግሎቶች
ለሚዛወሩ ይዞታዎችና ከይዞታቸው ለሚፈናቀሉ ሰዎች ካሳ የሚከፈልበት ሥርዓት
እንዲዘረጋ ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
11) ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የለማ መሬት ያዘጋጃል፣ ለተገልጋይ ያቀርባል፣
የአቅርቦቱን ፍትሐዊነት ያረጋግጣል፤ የተላለፈ መሬት ህጋዊነቱን ተከትሎ
24
ለልማት መዋሉን ይከታተላል፣ ህገወጥ ግንባታዎችን ይቆጣጠራል ህጋዊ
ሥርዓትን ያስይዛል፤
12) የመሬትና የንብረት ዋስትና ካሳ ሥርዓት ይዘረጋል፣
13) በቴክኖሎጂ የተደገፈና ወጥ የሆነ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና የአድራሻ መረጃ
ሥርዓት በክልሉ ይዘረጋል፣
14) በከተሞች የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ነዋሪው ህዝብ በተደራጀ
አግባብ እንዲሳተፍ ለማስቻል የአሠራር ስርዓት ይዘረጋል፣ የማስፈጸም አቅም
ይገነባል፤ ያስተባብራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
15) የቤቶች ልማት ፕሮግራሞችን ይመራል፣ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል
የከተማ ነዋሪ ሕዝብ ከአቅሙ ጋር የተመጣጠነ የመኖሪያ ቤት እንዲሰራ ስልት
ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
16) የኮንስትራክሽን ዘርፉን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ
ይነድፋል፣ ይተገብራል፤ ለዘርፉ ዕድገት አስፈላጊ የሆኑ ጥናቶችን ከሚመለከታቸው
አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ይተገብራል፤
17) በሃገር አቀፍ ደረጃ የተወዳዳሪነት ብቃት ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
ለመገንባት የሚያስችሉ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፤ በዲዛይን፣
በጨረታና፣ በኮንትራት ይዘት ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት
ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
18) በኮንስትራክሽ ሥራዎች ላይ ተገቢውን ቁጥጥር ያደርጋል፤ የኮንስትራክሽን
ሥራዎችን ደረጃ ያወጣል፣ መከበራቸውን ይከታተላል፤
19) በክልሉ መንግሥት በጀት ለሚሠሩ ሕንፃዎች ዲዛይኖችና የግንባታ ውሎች
እንዲዘጋጁ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣ የግንባታ ሥራዎችን ይቆጣጠራል
20) የሕንፃ ኮድና ስታንዳርዶች በከተሞች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ተገቢው አደረጃጀት፣
አሠራርና የሰው ሃይል አቅም እንዲፈጠር ድጋፍ ያደርጋል፤
21) በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰማሩ መሐንዲሶችና አርክቴክቶችን ይመዘግባል፣ የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ የሥራ ተቋራጮችንና የአማካሪዎችን
25
ደረጃ ይወስናል፤ ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ መሥራት ለሚችሉ የሥራ
ተቋራጮችና አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል።
22) በሥራ ላይ ባሉ ሌሎች ሕጎችና ድንጋጌዎች ለከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ እና
ለኮንስትራክሽን ቢሮ ተሰጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባራት በዚህ አዋጅ ለከተማ
ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ተሰጥተዋል።
23) በሥራ ላይ ባሉ የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች ለኮንስትራክሽንን ቢሮ ተሰጥተው
የነበሩ ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ተሰጥተዋል፡፡
24) ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
19. የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይ•ሩታል፣
1) የ¡ልሉን የውሃ ሀብት ያስተÇድራል፣
2) የክልሉን የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሃ ሀብት በመጠንና በጥራት ይለያል፣
ጥቅም ላይ የሚውልበትን ሁኔታ ያSቻቻል፣
3) የውሃ ልማትና አስተዳደር ማኑዋሎችንና ደረጃዎችን ያ²ጋጃል እንዲሁም ሌሎች
የውሃ ሴክተር ስራዎችን ይቆ×ጠራል፣
4) የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ዝርዝር ጥናት ያጠናል፣ ግንባታዎችን ያከናውናል፣
5) የከተማና ገጠር የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን እንዲያድግ ያደርጋል፣
ደረጃውን ይወስናል፣ የ‚¡ኒካዊ ሥራዎችን ›ፈፃፀም ይከታተላል፣
6) የገጠር መጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ኮሚቴዎችን ያደራጃል ሕጋዊ የሰውነት
ፈቃድ ይሰጣል፣ የከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅቶችን ያደራጃል፣
7) በክልሉ የውሃ ተፋሰሶች ፍትሐዊና ሚዛናዊ የውሃ ክፍፍልና ምደባ መኖሩን
ይቆ×ጠራል፣
26
8) የውሃ ዕጥረት ባለባቸው የክልሉ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ የውሃ አቅርቦት
ያመቻቻል፣ ችግሩንም በዘለቄታዊነት ለማስወገድ የሚያስችሉ ተግባራትን
ያከናውናል፣
9) የውሃ አካላት ብክለትን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ የውሃ ናሙና ይሰበስባል፣
የላብራቶሪ ምርመራ ያÅርጋል፣
10) በውሃና በመስኖ ልማት ስራ ለሚሰማሩ ተቋራጮች፣ አማ"ሪዎችና ባለሞያዎች
ደረጃቸውን ይወስናል፣ የሥራ ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይcርዛል፣
11) የክልሉን የመስኖ ልማት ሽፋን ለማሳደግ የመስኖ ልማትና የማጠንፈፍ ሥራዎች
ጥናትና ዲዛይን ያከናውናል፣ የግንባታ ጨረታ ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
12) የወንዞች ፍሰት አቅጣጫ መግራት እና የጐርፍ መከላከያ ሥራዎች ጥናት ዲዛይንና
ግንባታ ቁጥጥር ሥራዎችን ያከናውናል፣
13) በክልሉ የሚካሄዱ የመስኖ ኮንስትራክሽን ሥራዎች መስፈርት ያዘጋጃል፣
ተግባራዊነቱን ይመራል፣
14) የመስኖ አለኝታ ጥናት፣ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ይመራል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣ አቅም ይገነባል፣
15) የመስኖ ተቋማትን ይንከባከባል፣ ይጠግናል፣ የመስኖ ተቋሞችን በአካባቢው
ሙያተኞችን በማሰልጠን እንዲንከባከቡና እንዲያስተዳድሩ ያበቃል፣
16) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
20. የትምህርት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
1) የመማር ማስተማር ሥራን በበላይነት ይመራል፣
27
2) የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን፣ ኮሌጆችን፣ የመምህራን ማሠልጠኛ
ተቋማትን፣ የትምህርት በሬዲዮ ማሠራጫ ጣቢያዎችን፣ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን
ያቋቁማል፣ ያስተዳድራል፣
3) የክልሉ ትምህርትና ሥልጠና ደረጃውንና ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፣
ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፣ መጽሐፍትንና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን
ያሟላል፣ ያሠራጫል፣
4) የመምህራን ድልድልና ምደባ ያካሂዳል፣ በየደረጃው ለማስተማር ብቁ የሚያደርጉ
ሁኔታዎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ ለመምህራን ስልጠና ይሰጣል፣
5) የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ያዘጋጃል፣ አፈፃፀሙን
ያስተዳድራል፣ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣
6) በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁ ፈተናዎችን በክልሉ ያስፈጽማል፣
7) በክልሉ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትና ወጣቶች የመማር ዕድል
የሚያገኙበትን ስልት ይቀይሣል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
8) የአርብቶ አደር አካባቢ የትምህርት እንቅስቃሴ ያበረታታል፣ ልዩ ድጋፍ ይሰጣል፣
9) የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ መጽሐፍት ህትመትና ስርጭት
ያከናውናል፣ እንዲከናወን ያደርጋል፣
10) የመንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የግል ትምህርት ቤቶችን የብቃት
ደረጃ ያረጋግጣል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይሰርዛል፣
11) የትምህርት ተቋማትን የማስፈፀም አቅም ችግሮችን ይለያል፣ ዕቅድ በመንደፍ
ለችግሮቹ መፍትሔ ይሰጣል፣
12) የመምህራንና የትምህርት አመራር አካላት የመፈፀም አቅም ይገነባል፣
13) የቅድመ መደበኛ፣ የልዩ ፍላጐት፣ የጐልማሶችና የአማራጭ መሠረታዊ
ትምህርቶችን አደረጃጀት ይወስናል ፣ መርሃ ግብር ያወጣል ይከታተላል፣ ድጋፍ
ይሰጣል፣
14) የመማር ማስተማር ምዘና አሰጣጥ ችግሮችና ውጤታማነት ላይ ጥናት ያካሂዳል፣
የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ይቀይሳል፣ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፣
28
15) የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሥርዓተ-ትምህርትን ያዘጋጃል፣ በክልሉ ተግባራዊ
ያደርጋል፣
16) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
21. የጤና ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት Ãኖሩል፣
1) በክልሉ ጤናና ጤና ነክ ጉዳዮችን በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣
2) የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲያድግ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፣
3) በብድርና ዕርዳታ የሚከናወኑ የጤና ፕሮግራሞችን አፈፃፀም ይከታተላል፣
ያስተባብራል፣
4) የጤናውን ዘርፍ ልማት ክልላዊ ፕሮግራም ይነድፋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
ይገመግማል፣
5) ክልላዊ የጤና መረጃ ሥርዓቱን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
6) ወረርሽኝና ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ስልቶችን ይቀይሳል፣
ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣
7) ክልላዊ የአመጋገብ ሥርዓት ስትራቴጂን አፈጻፀም ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣
8) የሕብረተሰቡን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ ድንገተኛ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የመከላከል
እርምጃ ይወስዳል ያስተባብራል፣
9) በክልሉ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ መድሐኒቶችና የሕክምና መሳሪያዎች በበቂ መጠን
መኖራቸውንና በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፣
10) በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ጤና ተቋማትን ያደራጃል፣ ያስተዳድራል፣
11) የጤና ሥርዓቱን ካርታ ያዘጋጃል፣ የጤና መሰረተ ልማቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣
ድጋፍም ይሰጣል፣
29
12) በክልሉ ኤች አይቪ ኤድስን የመከላከል፣ የመቆጣጠርና የዘርፈ ብዙ ምላሽ ተግባርን
በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
13) የክልሉን የጤና ችግር ለመፍታትና የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚረዱ
ምርምሮች እንዲካሄዱ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፣
14) አግባብነት ያላቸው የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የጤና አጠባበቅ ትምህርት
እንዲስፋፋ ያደርጋል፣
15) በክልሉ የጤና ትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ያቋቁማል፣ ያደራጃል፣
ያስተዳድራል፣
16) በክልሉ የምግብ፣ የመድሐኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ሥራዎች
በአግባቡ መፈፀማቸውን ያረጋግጣል፣
17) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
22. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት Ãኖሩል፣
1) በክልሉ የሚከናወኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞ‹ አገር አቀፍ
ደረጃቸውን ጠብቀው መካሄዳቸውን ያረጋግጣል፣
2) ደረጃውን የጠበቀ መሰረታዊ መለስተኛና መካከለኛ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና
ሥልጠና ሥርዓተ-ትምህርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
3) በክልሉ የመሰረታዊ የመለስተኛና መካከለኛ ደረጃ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና
ሥልጠና ተቋማት ያቋቁማል፣ ያስፋፋል፣ ያስተዳድራል፣
4) የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ከክልሉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ጋር
መጣጣሙን ያረጋግጣል፣ ጥራትና አግባብነቱን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ
ይወስዳል፣
5) ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆችና በዘርፉ ለሚሰማሩ ሌሎች
ማሰልጠኛ ተቋማት የቅድመ-ዕውቅናና ዕውቅና ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል ከደረጃው
በታች ሆነው ሲገኙ ፈቃዳቸውን ይሰርዛል፣
30
6) የትምህርትና ሥልጠና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት ያዘጋጃል፣ ተፈፃሚነቱን
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
7) የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከላት የቴክኖሎጂ የዕውቀትና ክህሎት
ሽግግር ማዕከላት እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
8) ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ የግል ባለሀብቶችና መንግስታዊ
ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሳተፉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ ያበረታታል፣ አስፈላጊውን
ድጋፍ ይሰጣል፣
9) የክልሉን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ ያዘጋጃል ሲፈቀድም
ይፈፅማል፣ ያስፈጽማል፣
10) ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ቅድመ
ዕውቅናና ዕውቀና ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ይሰርዛል፣
11) ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
23. የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩል፣
1) የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች መብትና ጥቅሞችን በማስከበር ዙሪያ ግንዛቤና ንቅናቄ
እንዲፈጠር ያደርጋል፣
2) የሴቶችን፣ የሕፃናትና የወጣቶችን ሁኔታ የሚያመላክቱ ዝርዝር መረጃዎችን
ይሰበስባል ያደራጃል፣ በሚመለከታቸው ሁሉ እንዲታወቁ ያደርጋል፣
3) ሴቶችና ወጣቶች በክልሉ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት
ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ዕድሎች የተመቻቹላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፣
4) ሴቶችና ወጣቶች እንደየፍላጎቶቻቸውና እንደ ችግሮቻቸው ተደራጅተው ለመብቶቻቸው
እንዲታገሉና ችግሮቻቸውን ማስወገድ እንዲችሉ ያበረታታል፣ ሁኔታዎችን
ያመቻቻል፣
31
5) በክልሉ መንግስት አካላት የሚያዘጋጁ ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ የልማት ፕሮግራሞችና
ፕሮጀክቶች የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ እንዲያካትቱ ስልት ይነድፋል፣ ይገመግማል፣
ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፣
6) በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚቃጡ መድሎዎችን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ጥቃቶችን
በጥናት በመለየት የሚወገዱባቸውን ሁኔታዎች ያመቻቻል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣
ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ይሰራል፣
7) ሴቶች በተለያዩ የመንግስት አካላት በወሳኔ ሰጪ የስራ ቦታዎች ላይ ለመመደብ በቂ
ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን ያረጋግጣል፣
8) በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚረዱ
ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ተግባራዊ እንዲሆኑ
ያደርጋል፣ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
አፈጻፀሙን ይከታተላል፣
9) ሴቶችና ወጣቶች በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ
ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስልት ይቀይሳል ድጋፍ ይሰጣል፣
10) የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ጥናቶችን
ያካሂዳል፣ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ የስልጠና አገልግሎት የሚሰጥበትን አሰራር
ያመቻቻል፣ ያስተባብራል፣
11) የእናቶች የኑሮ ሁኔታ ስለሚሻሻልበትና የሕፃናት መብትና ደህንነት ስለሚጠበቅበት
ሁኔታ ያጠናል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ተግባራዊ ያደርጋል፣
12) በክልሉ ሴቶችንና ሕጻናትን የሚመለከቱ ሀገራችን የፈረመቻቸው አለም አቀፍ
ውሎችና ስምምነቶች አፈጻፀም ይከታተላል፣ ለሚመለከታቸው አካላትም ሪፖርት
ያቀርባል፡፡
24. የሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩል፣
1) የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲጠበቅ፤
ሀ/ ሠራተኞችና አሠሪዎች በማኅበር የመደራጀትና የሕብረት ድርድር የማድረግ መብቶቻቸውን እንዲጠቀሙ ያበረታታል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
32
ለ/ በአሠሪዎችና በሠራተኞች መካከል የሁለትዮሽ እንዲሁም የመንግሥት ወገንን ጨምሮ የሦስትዮሽ አሠራሮች እንዲለመዱ ያደርጋል፤
ሐ/ የሥራ ክርክሮች በተቀላጠፈ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኙ የሚያስችሉ
አሠራሮችን ይዘረጋል፤
2) የሙያ ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ የወጡ የሥራ ሁኔታ ደረጃዎችና የመከላከያ
ዘዴዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
3) በክልሉ ውስጥ መደበኛና መደበኛ ባልሆነ ሥራ የተሰማራውን የሰው ኃይልና የስራ
አጥነት ችግር ያጠናል፣ ሥራ ፈላጊዎችንና ክፍት የሥራ መደቦችን ያጠናል፣
ይመዘግባል፣ ሥራና ሠራተኛ ለማገናኘት የሚያስችሉ እርምጃዎችን ይወስዳል፣
4) በክልሉ ውስጥ የሚቋቋሙትን አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችንና ወኪል
ቀጣሪዎችን ይመዘግባል፣ የሥራ ፈቃድ ይሰጣል፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በመተባበር ይቆጣጠራል፣ በሕግ መሠረት ያግዳል፣ ፈቃዳቸውን ይሰርዛል፣
5) የሥራ ገበያ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ያጠናቅራል፣ ያሰራጫል፤
6) የሠራተኞችን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ የወጡ የሥራ ሁኔታ ደረጃዎችና የመከላከያ
ዘዴዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
7) በክልል አቀፍ ደረጃ የሚደራጁትን የሠራተኛና የአሰሪ ማኅበራት ይመዘግባል፤ በአሰሪና
ሠራተኛ ማህበራት መካከል የሚደረጉ የሕብረት ስምምነቶችን መርምሮ ይመዘግባል፣
8) የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ይከላከላል፣ ከሚመለከታቸዉ ጋር በመተባበር መብቶቻቸዉ
መከበሩን ይከታተላል፣
9) ህጋዊ የሥራ ፈቃድ አግኝተዉ በክልሉ በተለያዩ የሥራ መስኮች የሚሰሩ የዉጭ ዜጎችን
ይመዘግባል፣ ይከታተላል፣ የሥራ ፈቃዳቸዉ መታደሱን ያረጋግጣል፣
10) የዜጐች ማኅበራዊ ደህንነት የሚጠበቁባቸውንና የሚሻሻሉባቸውን ዘዴዎች በተለይም፡-
ሀ/ የአካል ጉዳተኞች እኩል ዕድል ተጠቃሚና ሙሉ ተሳታፊ ሊሆኑ
ስለሚችሉበት፣
ለ/ አረጋዊያን እንክብካቤ ስለሚያገኙበትና ተሳትፎአቸው ሊጎለብት ስለሚችልበት፣
ሐ/ የማኅበራዊ ችግሮችን ስለመከላከልና በችግሩ ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ
ክፍሎች የተሐድሶ አገልግሎት ስለሚያገኙበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው
ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፣ ማህበረሰብ አቀፍ ማህበራዊ ጥበቃ
33
አሰራርና አደረጃጀቶችን ያጠናክራል፣ሥራ ላይ የሚውልበትን ሁኔታ
ያመቻቻል፣
መ/ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ ያሉና ቀጥታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሰብ
ክፍሎች በጥናት በመለየት የቀጥታ ድጋፉን እንዲያገኙ ያደርጋል፣ ድጋፉ
ከሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ጋር ተጣምሮ መሰጠቱን ያረጋግጣል፣
11) የአካል ጉዳተኞችን ተሀድሶ ማዕከላት በክልሉ ያቋቁማል፣ ያጠናክራል፤ ያስተዳድራል፣
12) በክልሉ መንግሥት አካላት የሚዘጋጁ ፓሊሲዎች፣ የልማት ፕሮግራሞች፣ ፕሮጄክቶችና
ዕቅዶች የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያንን ጉዳዮች እንዲያካትቱ ስልት ይነድፋል፣ በጋራ
ይገመግማል፣ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፣
13) የቤተሰብ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ይነድፋል፣ ተግባራዊ
ያደርጋል፤
14) ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣
25. ¾›=”}`ý^õ‹“ ›=”Æeƒ] MTƒ u=a
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩል፣
1) ኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዞች እንዲስፋፋ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል
2) የኢንዱስትሪ የዘርፍና የሙያ ማህበራት እንዲቋቋሙ ያበረታታል፣ የተቋቋሙትንም
እንዲጠናከሩ ያደርጋል፣
3) ኢንዱስትሪን በማስፋፋት ረገድ የከተማና የገጠር፣ የከተሞች የእርስ በርስ ትስስር
እንዲጠናከር ስትራቴጂ ይቀይሳል ተግባራዊ ያደርጋል፣
4) በከተማ ስራ አጥ ዜጐች በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ሥራዎች ተሳታፊና
ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ ያደራጃል፣ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
5) በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባላሀብቶች ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፣ ድጋፍ
ይሰጣል፣ ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
6) ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የኢንዱስትሪ መንደሮች የሚለሙበትን ሁኔታ
ያመቻቻል፣ መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸው ያደርጋል፤
7) በክልሉ የካይዘን ፍልስፍና አስተሳሰብ ያሰርጻል፣ ውጤታማ እንዲሆንም ተቋማዊ ድጋፍ
ይሰጣል፤ ክትትል ያደርጋል፣
34
8) ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣
26. የገቢዎች ባለሥልጣን
ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
1) የክልሉን የታክስና የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በበላይነት ይመራል፣ ያስተዳድራል፤
2) በክልሉ በመካሄድ ላይ ያለውን የታክስ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም አፈጻጸም
በባለቤትነት ይመራል፣ ያስተባብራል፤
3) ቀልጣፋ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት
ይዘረጋል፡፡
4) ለታክስ ከፋዩ አማራጭ የታክስ መክፈያ ተቋማትን ያመቻቻል፤
5) ታክስ ከፋዮች በፍቃደኝነት ታክስ የመክፈል ባህልን እንዲያዳብሩ የግንዛቤ
ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ተግባራዊ ያደርጋል፤
6) በክልሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ተመሰርቶ ጥናቶችን በማካሄድ የክልሉን የገቢ
መሠረት ያሰፋል፣ በታክስ አስተዳደሩ የሚከሰቱ ችግሮች እንዲፈቱ ያደርጋል፣
የፖሊሲና የሕግ ሀሳቦችን ያመነጫል፤
7) የታክስ ሕጐችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ በማናቸውም ሰው እጅ የሚገቡ ሰነዶችን
ይመረምራል፣ ይይዛል፤
8) ለታክስ አወሳሰን የሚያስፈልጉት መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያጠናክራል፣ እነዚህኑ
በመጠቀም ታክስ ይወስናል፣ ይከሳል፤
9) ታክስ ያልሆኑ የከተማ ቦታ ይዞታ፣ የቤት ባለቤትነት፣ የንብረትና የአገልግሎት
ክፍያ አወሳሰንና አሰባሰብ የሚያገለግሉ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣
ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
10) ከተሞች የማዘጋጃ ቤቶች ገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ጥናት ያደርጋል፣ ገቢዎችን
በሕጉ መሠረት ይሰበስባል፣ ለመንግስት ግምጃ ቤት ገቢ ያደርጋል፣
11) የታክስ ወይም የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ የግብር ወይም የታክስ ከፋዬችን
ንብረት በህግ መሠረት ያሰከብራል፣ ያስይዛል፣ በሃራጅ እንዲሸጥ ያደርጋል፣
35
12) በታክስ እና በግብር ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይመረምራል ውሣኔ ይሰጣል
መቀጫዎችን በሕግ መሠረት ይጥላል፣ ያነሳል፣
13) ለግብር ይግባኝ ጉባዔ የሚቅረቡ የግብር ወይም የታክስ አወሳሰን ጉዳዮችን
ይከታተላል ያስወስናል፣
14) ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
27. የባህል፤ ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ
የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡-
1) በክልሉ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ ቅርሶችና እሴቶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁ
ለሣይንስና ቴክኖሎጂ አገልግሎት እንዲውሉ ያደርጋል፤
2) በክልሉ የሚገኙ ቋንቋዎች እንዲጠኑ፣ ሥነ-ጽሑፎቻቸው እንዲዳብሩና እንዲስፋፉ
ያደርጋል፤
3) የትርጉም አገልግሎትና የአስተርጓሚነት ሙያ ዕውቀት እንዲዳብርና እንዲስፋፋ
የሚያደርጉ ተግባሮችን ያከናውናል፤ ደረጃውን የጠበቀ የሥራ ቋንቋ አጠቃቀም
እና የትርጉም አገልግሎት እንዲኖር ይደግፋል፣ ክትትል ያደርጋል፤
4) በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተፅእኖ ሳቢያ ማኀበራዊ እድገትን የሚያጓትቱ
አመለካከቶችን፤ እምነቶችንና ልማዳዊ አሰራሮችን የመለወጥ ተግባሮች
ያከናውናል፤
5) ለክልሉ ልማት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ባህሎች እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
6) በባህል ዘርፍ የሕዝቡን ተሳትፎ ተቋማዊ መሠረት ለማስያዝ የባህል ተቋማት
እንዲስፋፉ ያደርጋል፤
7) የዕደ ጥበብ፣ የኪነ ጥበብና የሥነ-ጥበብ ሥራዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ ለልማቱ
የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የዘርፉን መረጃዎች በዘመናዊ መንገድ
እንዲደራጁ ያደርጋል፣ ተደራሽነቱንም ያረጋግጣል፣
8) በዘርፉ ውጤታማ የፈጠራ ሥራዎችን ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማትና
ማበረታቻ የሚሰጥበት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፣
9) በክልሉ የፊልም ተውኔት ጥበብ ሥራዎች የሚያድጉበትን አግባብ ያመቻቸል፣
36
10) የክልሉን የቱሪዝም መስሕቦችና መልካም ገፅታ ያስተዋውቃል፤ ቱሪዝም በክልሉ
እንዲስፋፉ ያበረታታል፤
11) የክልሉን ቱሪስት መስሕቦች ተለይተው እንዲታውቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው
እንዲለሙና እንዲደራጁ፣ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እንዲስፋፉ፣
የየአካባቢው ማኀበረሰብም ከቱሪዝም ጥቅሞች ተካፋይ እንዲሆን የሚደረግበትን
አግባብ ያመቻቻል፤
12) የክልሊ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው
እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ በሃገር
አቀፍ ደረጃ በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት የክልሉ
ቅርሶች በአለም አቀፍ ቅርስነት የሚመዘገቡበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር ያመቻቻል፣
13) የባህልና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን
ይቆጣጠራል፣
14) በቱሪዝም የሠመረ አገልግሎት እንዲኖር የቱሪስቶችም ደህንንት እንዲረጋገጥ
የሚያስፈልገው የብዙ ወገኖች የሥራ ቅንጅት እውን እንዲሆን ለሚፈጠሩ የጋራ
መድረኮች በማዕከልነት ያገለግላል፣
15) በሰው ኃይል ሥልጠናና በሙያ ምክር አገልግሎት አማካይነት የባህል፣ የስፖርትና
የቱሪዝም ሴክተርን የማስፈጸም አቅም ይገነባል፣
16) የባህል፣ ስፖርትና ቱሪዝም መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ያሰራጫል፡፡
17) ህዝቡን በስፖርት ለሁሉምና ባህላዊ ስፖርት ተሳታፊና ተጠቃሚ ያደርጋል፣
18) የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራትና ብቃትን ለማሳደግ የስፖርት ትምህርት፣ ሥልጠናና
ምርምር ተቋሞች የሚቋቋሙበትን ሥልት በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
19) የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችንና የስፖርት ማበልጸጊያ ማዕከላትን ያስፋፋል፤
20) ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የስፖርት ህክምና አገልግሎት ያደራጃል፤
በስፖርት አበረታች መድሃኒቶችና ዕፆች መጠቀምን ለመላከል የሚያስችል ሥርዓት
ይዘረጋል፣
21) ውድድሮችንና ፌስቲቫሎችን በማዘጋጀት የስፖርቱ ዘርፍ የገቢ መሠረቶችን ያሰፋል፣
የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያሳድጋል፣
37
22) የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ መመሪያ ያወጣል፤ በፌደራል ደረጃ
የሚቋቋሙ የስፖርት ማህበራትን ይመዘግባል፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፡፡
23) በሥራ ላይ ባሉ የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች ስፖርትን በሚመለከት ለወጣቶችና
ስፖርት ቢሮ ተሰጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለባህል፣ ቱሪዝምና
ስፖርት ቢሮ ተሰጥተዋል፡፡
28. ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩል፣
1) የክልሉ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስ ብቃት ያለውና ውጤታማ መሆኑን
ያረጋግጣል፣
2) የክልል መንግስት ሰራተኞች ምልመላና መረጣ በብቃት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን
ያደርጋል፣
3) የፐብሊክ ሰርቪሱ የሰው ኃይል በቀጣይነት በሚለማበት ጥቅም ላይ የሚውልበትን
ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣
4) ለፐብሊክ ሰርቫንቱ በብቃትና በአፈጻፀም ውጤታማነት ላይ የተመሰረተ የክፍያና
የማበረታቻ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ውጤታማነቱን ይገመግማል
አስፈላገጊውን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፣
5) የክልል መንግስት ሰራተኞች ሥነ-ምግባር መከታተያ ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣
አፈጻፀሙን ይከታተላል፣
6) የክልል መንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ሕጎች በትክክል ስራ ላይ መዋላቸውን
ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
7) የመንግስት ዘርፍ አቅም ግንባታ ስራዎችን ያስተባብራል፣ የመንግስት ዘርፍ
አገልግሎት በቀጣይነት የሚሻሻልበትና ውጤታማ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል
ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
8) የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀት አግባብነትን ይመረምራል፣
በአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናቶች ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፣
38
9) በክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ የቅሬታ
አቀራረብና አፈታት ሥርዓት መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፣
10) የፐብሊክ ሰርቪሱ የሰው ሃብት አመራርና የተቋማዊ መረጃዎች ሥርዓት በወጥነት
እንዲዳብርና እንዲተገብር ያደርጋል ማዕከላዊ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፣
11) የክልሉን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን የሰው ሀብት አስተዳደር በበላይነት ይመራል፣
የስራ አመራር መመሪያዎችና የአፈፃፀም መስፈርቶችን ያዘጋጃል ያስፈፅማል፣
12) የመንግስት ሰራተኞችን የደመወዝ፣ የልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማ ጥቅሞች ማሻሻያ
ያጠናል ሲፈቀድም ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
13) በሕግ መሰረት የክልል መንግስት ሰራተኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በላይ
በአገልግሎት ላይ ስለማቆየት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣
14) ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
ክፍል አምስት
ስለሌሎች አስፈፃሚ አካለት እና ተጠሪነት
29. ሌሎች የአስፈጻሚ አካላት መስሪያ ቤቶች
1) በዚህ አዋጅ ውሰጥ ያልተመለከቱ ሌሎች የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ አካላት
በማቋቋሚያ ሕጎቻቸው መሰረት ስራቸውን ይቀጥላሉ፡፡
2) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት አዲስ
አስፈፃሚ አካላት፤
1) የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን፣
2) የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት፣
3) የአካባቢ ጥበቃ፣ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን፣
4) የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኮሚሽን፣
5) የእንስሳት ሀብት ልማት ኮሚሽን፣
6) የልዩ ድጋፍ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት፣
7) የአርብቶ አደር ኮሚሽን፣
39
8) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣
9) የኢንተርፕራይዞች ልማት አጄንሲ፣
10) የፓሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት፣
11) የኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣
12) የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣
13) ፕሬስ ሴክሬተሪያት
14) የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ እና
15) የስፖርት ኮሚሽን፤ በዚህ አዋጅ ተቋቁመዋል፡፡
3) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተቋቋሙት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት፣
ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ በመስተዳደር ምክር ቤት በሚወጣው ደንብ መሠረት
ይወሰናል፡፡ ‹
30. ስለተጠሪ አስፈፃሚ አካላት
1) በሚከተሉት ንዑሳን አንቀጾች የተደረጉት የተጠሪነት ማሻሻያዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣
ሌሎች አስፈፃሚ አካላት በተቋቋሙባቸው ሕጎች በተደነገገው መሠረት ሥራቸውን
ይቀጥላሉ፡፡
2) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የስያሜና የተጠሪነት
ማሻሻያ የተደረገባቸው አስፈፃሚ አካላት በመስተዳደር ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ መሰረት
አደረጃጀትና ስልጣንና ተግባራት የሚወሰን ይሆናል፡፡
3) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት ተጠሪነት ለርዕሰ መስተዳደሩ ይሆናል፡፡
ሀ) ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣
ለ) የአካባቢ ጥበቃ፣ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን
ሐ) የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኮሚሽን፣
ረ) የፓሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት
ሰ) ፕሬስ ሴክሬተሪያት
4) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት ለሠላምና ፀጥታ ቢሮ ተጠሪ ይሆናል
ሀ) ፓሊስ ኮሚሽን
ለ) ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት
ሐ) ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
40
መ) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣
5) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የግብር ቢሮ ተጠሪ ይሆናል
ሀ)) ህብረት ስራ ልማት ኤጄንሲ፣
ለ) ደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት
ሐ) ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን
መ) ግብርና ግብዓት ቁጥጥር ባለስልጣን
ሠ) ደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
ረ) የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ
6) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ተጠሪ ይሆናል
ሀ) ግዢ ኤጀንሲ
ለ) የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ
ሐ) የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን፣
7) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተጠሪ ይሆናል
ሀ) ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
ለ) የፍትህ አካላት ማሰልጠኛና የሕግ ምርምር ማዕከል
8) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
ሀ) የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ/ፅ/ቤት
ለ) የከተሞች ፕላን ኢንስቲዩት
ሐ) የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ
መ) የኮንስትራክሽን ባለስልጣን
ሠ) የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ኤጀንሲ
ረ) የተቀናጀ የመሬት መረጃ ስርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት
9) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የውሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ተጠሪ ይሆናል
ሀ) የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ
ለ) የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ
41
10) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ይሆናል
ሀ) የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና መገናኛ ኤጀንሲ
ለ) የገጠር ቀበሌ አስተዳደር መዋ/ማጠ/ፕሮ/ ጽህፈት ቤት
ሐ) አመራር አካዳሚ
መ) የልዮ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
11) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን
ተጠሪ ይሆናል
ሀ) የቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ
ለ) የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
ሐ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን
መ) ደቡብ ዲዛይን ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ
ሠ) የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት ድርጅት፣ ‹‹
12) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት የቴክኒክና ሙያ፣ ትምህርትና ሰልጠና ቢሮ ተጠሪ
ይሆናል፡፡
ሀ) የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት
ለ) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
13) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት ለትራንስፓርትና መንገድ ልማት ቢሮ ተጠሪ ይሆናል፡፡
ሀ) የመንገዶች ባለስልጣን
ለ) ለትራንስፓርት ባለስልጣን
14) የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት ለእንስሳት እና አሳ ሃብት ልማት ቢሮ ተጠሪ ይሆናሉ
ሀ የእንስሳት ሃብት ልማት ኮሚሽን
ለ የአርብቶ አደር ኮሚሽን
15) የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ተጠሪነቱ ለጤና
ቢሮ ይሆናል
16) የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ማኑፋክቸሪንግ ልማት ኤጀንሲ ተጠሪነት
ለኢንተርፕራይዞችና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ይሆናል፡፡
17) ስፓርት ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለባህል፣ ቱሪዝምና ስፓር ቢሮ ይሆናል፡፡
42
18) የደቡብ ብሄር በሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት
ተጠሪነት ለክልሉ ምክር ቤት ይሆናል፡፡
ክፍልል ስድስትስድስት
የአየአስፈፃሚ አካላት መሥሪያስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤቶች ቤቶች መዋቅር እና ኃላፊዎችመዋቅር እና ኃላፊዎች
3311.. የአስፈፃሚ አካላት መሥሪያየአስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤቶች በየቤቶች በየደረጃው የሚቋቋሙ ስለመሆኑደረጃው የሚቋቋሙ ስለመሆኑ
1) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 መሠረት የተቋቋሙ አስፈጻሚ አካላት መሥሪያቤቶች
እንደሁኔታው በዞን፣ በልዩ ወረዳ፣ በወረዳ፣ በከተማና በክፍለከተማ ደረጃ ሊቋቋም
ይችላል፡፡ ዝርዝሩ በመስተዳድር ም/ቤቱ ይወሰናል፡፡
2) የአስተዳደር ምክር ቤት አባል የሆኑ በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙ የአስፈፃሚ
አካላት መስሪያ ቤቶች ተጠሪነት ለአስተዳደሪውና ለአስተዳደር ምክር ቤቱ
እንዲሁም በየደረጃወው ላሉ የአስፈፃሚ አካላት መስሪያ ቤቶች ይሆናል፡፡
3) ለአስፈፃሚ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር በየአስተዳደር
እርከን ላሉት መስሪያ ቤቶች እንደአስፈላጊነቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
4) እያንዳንዱ የአስፈፃሚ አካላት መስሪያ ቤቶች ኃላፊና እንደአስፈላጊነቱ ምክትል
ኃላፊዎች፤ እንዲሁም የሥራ ሂደት ባለቤቶች እና ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡
5) ተቀራራቢ ተግባር ያላቸው የአስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤቶች አንድ የድጋፍ ሰጪ
ማዕከል በጋራ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
6) በየደረጃው ያሉ አስፈጻሚ መሥሪያቤቶች በየአስተዳደር ዕርከኑ እንደ-አስፈላኒነቱ
ተቀናጅተው ወይም ተጣምረው ሊደራጁ ይችላሉ፡፡
3322.. የአስፈፃየአስፈፃሚ አካላት ሚ አካላት መስሪያመስሪያ ቤት ኃላፊዎች ተጠሪነት፣ ቤት ኃላፊዎች ተጠሪነት፣ ሥልጣንና ተግባር
1) የመስየመስተዳድር ምክር ቤት አባላት የሆኑ የአስፈፃሚ አካላት መሥሪያ ቤቶች
ኃላፊዎች ለርዕሰ መስተዳደሩ እና ለመስተዳደሩ ምክር ቤት ተጠሪ ይሆናሉ፡፡
2) እያእያንዳንዱ የአስፈፃሚ መሥሪያ ቤት ኃላፊ፡-
43
ሀ/ ለመሥሪያ ቤቱ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ መዋሉን
ያረጋግጣል፣
ለ/ መሥሪያ ቤቱን ይወክላል፤ ያስተዳድራል፣
ሐ/ ሥራንና ሠራተኛን ይመራል፣
መ/ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲðpድም ሥራ ላይ ያውላል፣ አፈፃፀሙንም
ለመስተዳድር ምክር ቤት ሪፖርት ያደርጋል፣
ሠ/ በሕግ ለመሥሪያ ቤቱ የተሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
3) የዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች እንደ አግባብነቱ በየደረጃው
ለሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች ተፈፃሚ ሊሆን ይችላል፡፡
ክፍል ክፍል ሰባትሰባት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
33. አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ስለማደራጀት
የመስተዳደር ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደንብ በማውጣት፣ ማንኛውም አስፈጻሚ
አካል እንዲታጠፍ ወይም ከሌላ አስፈጻሚ አካል ጋር እንዲዋሃድ ወይም እንዲከፋፈል
ወይም ተጠሪነቱ ወይም ሥልጣንና ተግባሩ እንዲለወጥ ወይም አዲስ አስፈጻሚ አካል
እንዲቋቋም በማድረግ የክልሉን መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የማደራጀት ሥልጣን
በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል፡፡
3344.. ደንብና መመሪያ የማውጣት ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣንሥልጣን
1) ይህንይህን አዋጅ ለማስፈፀም የሚረዱ ደንቦችን መስተዳድር ምክር ቤት ሊያወጣ
ይችላል፡፡
44
2) ይህን አዋጅና አዋጁን ለማስፈፀም የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈፀም የሚረዱ
መመሪያዎችን የመስተዳደር ምክር ቤት አባል የሆኑ አስፈፃሚ አካላት መስሪያ
ቤቶች ሊያወጡ ይችላሉ፡፡
3355.. የተሻሩ ሕጐችየተሻሩ ሕጐች
1) የተየተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ
አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 161/2008
በዚህ አዋጅ ተሽሯል፡፡
2) ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ደንብ፣ መመሪያ ወይም አሠራር በዚህ
ደንብ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
36. መብትና ግዴታዎች ስለማስተላለፍ
1) የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ቢሮ እና የአርብቶ አደርና ጉዳዮችን የሚለከት
የአርብቶ አደርና ልዮ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ
ለተቋቋመው ለእንስሳት ቢሮ ተላልፏል፡፡
2) ልዮ ድጋፍን የሚለከተው የአርብቶ አደርና ልዮ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ መብትና
ግዴታ ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ተላልፏል፡፡
3) ወጣቶችን የሚመለከቱ የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ መብትና ግዴታ በዚህ አዋጅ
ለተቋቋመው ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ተላልፏል፡፡
4) የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መብትና ግዴታ ለርዕሰ መስተዳድሩ
ለሚቀቋቋመው ሴክሬተሪያት ይተላለፋል፡፡
5) ስፓርትን የሚመለከቱ የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ መብትና ግዴታ በዚህ አዋጅ
ለተቋቋመው ባህል፣ ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ተላልፏል፡፡
6) ፍትህ ቢሮን የሚመለከቱ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው ጠቅላይ
አቃቤ ህግ ተላልፏል፡፡
7) የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ መብትና ግደቴዎች በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው ሴቶች፣
ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ተላልፏል፡፡
45
8) የባህልና ቱሪዝም ቢሮ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው ባህል፣ቱሪዝና
ስፓርት ቢሮ ተላልፏል፡፡
9) የኢንዱስትሪ ዘርፍን የሚመለከቱ የንግድና ኢንዱስትሪና ቢሮ መብትና ግዴታዎች
በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው ለኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ተላልፏል፡፡
10) የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና የሚመለከቱ የስፓርትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ
እና የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው
የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኮሚሽን ተላልፏል፡፡
11) የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽኅፈት ቤት መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው
የፕሬስ ሴክሬተሪያት ተላለፏል፡፡
12) ስልጣንና ተግባራት መካከል ህትመትን የሚመለከቱ ለሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት
የተላለፉ ሲሆን ሌሎች ስልጣንና ተግባራት በዚህ አዋጅ ለተቀቋመው ለፕሬስ
13) የኮንስትራክሽን ቢሮ መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለከተማና ኮንስትራክሽን ልማት
ቢሮ ተላልፏል፡፡
አዋጁ ተፈፃሚ የሚሆንበት ጊዜአዋጁ ተፈፃሚ የሚሆንበት ጊዜ
ይህይህ አዋጅ ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
ሀዋሣሀዋሣ /2011 ዓ.ም
ሚሊዮሚሊዮን ማቲዎስን ማቲዎስ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት
ርዕሰ መርዕሰ መስስተዳድር ተዳድር
1
ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLL
mNGST db#B nU¶T Uz@È DEBUB NEGARIT GAZETA OF THE SOUTH
NATIONS, NATIONALITIES AND PEOPLES’ REGION STATE
አዋጅ ቁጥር-------/2011 ዓ.ም
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች
ክልልመንግስት ጠቅላይ ዓቃቤን ሕግ ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ
ሕገ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን
እንዲሁም የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር፤ ወጥነት
ያለው ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ፤
የሕዝብንና የመንግስትን ጥቅም በተሟላ ሁኔታ
የሚያስጠብቅ አንድ ጠንካራ ሕግ አስከባሪ የዓቃቤ
ሕግ ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሕዝብ ተአማኒነት ያለው፣ በተሟላ ተቋማዊና
ሙያዊ ነፃነት የሚያገለግል እንዲሁም ለሙያዊ፣
ተቋማዊና ሕዝባዊ ተጠያቂነት የሚገዛ፣ በግልጽነትና
በአሳታፊነት የሚሰራ የዓቃቤ ሕግ ተቋም ማቋቋም
በማስፈለጉ፤
በተለያዩ ተቋማት ተበታትኖ የሚሰራው የዓቃቢያነ ህግ
ስራ በአንድ ተቋም ስር ተደራጅቶ መሰራት እንዳለበት
PROCLAMATION No. ------/2018
A DRAFT PROCLAMATION TO PROVIDE FOR
THE ESTABLISHMENT OF THE ATTORNEY
GENERAL OF THE THE SOUTH NATIONS,
NATIONALITIESAND PEOPLES’ REGION STATE
WHEREAS, it has been found necessary to
establish one strong law enforcement public
prosecution institution which can comprehensively
protect public and government interest and deliver
uniform, effective and efficient service as well as
enforcing the constitution and constitutional
systems and the supremacy of law;
WHEREAS, it has been found necessary to re-
organize institution which enforces rule of law and
ensures that laws are properly organized and
government works are conducted in accordance
with the law;
WHEREAS, it has been believed that the public
prosecution activity to be performed at various
organizations shall be performed by organizing
under sole institution;
bdb#B B/@éC½B/@rsïC ?ZïC KL§êE
mNGST Mክር b@T ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ›mT q$_R (((((¼2011
hêú qN 2011 ›.M
Year No Hawassa /2018
2
በመታመኑ;
በ1994 ዓ ም በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕገ-መንግስት አንቀፅ
51 ንዑስ አንቀፅ 3 (ሀ) መሰረት የሚከተለው
ታውጇል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር --------/2011” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
በዚህ አዋጅ ውስጥ የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም
የሚያሰጥ ካልሆነ በስተቀር፤
1. “ክልል” ማለት “የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና
ህዝቦች ክልል ነው፤
2. “ምክር ቤት” ማለት በደቡብ
ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት በየእርከኑ የሚገኙ የህግ አዉጭ
አካል ነው፡፡
3. “መስተዳድር ምክር ቤት” ማለት በተሻሻለው
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 65 መሠረት
የተገለጸው ሆኖ የክልሉ ከፍተኛ የአስፈፃሚ
አካል ወይም ካቢኔ ነው፡፡
4. “አስተዳደር ምክር ቤት” ማለት በደቡብ
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት በየእርከኑ የሚገኙ አስፈፃሚ
መስሪያ ቤት ሀላፊዎች በአባልነት የሚገኙበት
NOW, THEREFORE, in accordance with the sub
article 3 (a) of Article 55 (1) of the 2002 revised
Constitution of the Southern Nations,Nationalities
and Peoples’ Region State, it is hereby Proclaimed
as follow;
PART ONE
GENERAL
1. Short Title
This Proclamation may be cited as the “South
Nations, Nationalities and Peoples’ Region
State Attorney General Establishment
Proclamation No. ---- ------- /2018”.
2. Definition
In this Proclamation unless the context
otherwise requires:
1. “region” means the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Region;
2. “council” means a legislative organ in
each administration of the South Nations,
Nationalities and Peoples’ Region;
3. “executive council” means a Supreme
Executive Organ or cabinet us defined
under urticle 65 of the revised
Constitution of the South Nations,
Nationalities and Peoples’Region;
4. “administration council” means an
executive organ, which heads of each
level executive organization are
members, in the Southern Nations,
3
አስፈፃሚ አካል ነዉ፡፡
5. “የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች” ማለት
ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ሙሉ በሙሉ ወይም
በከፊል በክልሉ መንግስት በጀት የሚተዳደሩ
አካላት ሆነው የክልሉ መንግስት የልማት
ድርጅቶችንም ይጨምራል፡፡
6. ““ሕግ” ማለት በፌደራል መንግስቱ ህግ
አውጪ ወጥተው በክልሉ ውስጥ ተፈጻሚነት
ያላቸው የሕግ ማእቀፎችን፣ በክልሉ ሕግ
አውጪ አካላት የወጡ አዋጆችን፣ ደንቦችን
እና ስልጣን በተሰጣቸው የክልሉ መንግስት
አካላት የወጡ መመሪያዎችን ያጠቃልላል፡፡
7. “ሕገ-መንግስት” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ
ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ እና የተሻሻለው
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
ሕገ-መንግስትን ያጠቃልላል፡፡
8. “የወንጀል ሕግ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ
ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት የተደነገገ የወንጀል ሕግ ነው፡፡
9. “ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” ማለት “የደቡብ ብሄሮች
ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ነው፤
10. “ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” ማለት “በደቡብ
ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት
በርዕሰ መስተዳድር አቅራቢነት በክልል ምክር
ቤት የተሾመ የክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ ነው፤
11. “ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” ማለት
Nationalities and Peoples’ Region;
5. “offices of the regional state” means
organs with legal personality relay
wholly or partly on the Regional State
budget to be administered, encluding the
developmental organizations of the
Regional State;
6. “law” means legal packages that are
applicable in the Region, issued by the
Federal Government’s legislative organ;
Proclamations and Regulations issued by
the Regional Legislative organ and
encludes Directives issued by the
empowered Regional State’ organs;
7. “constitution” means the Constitution of
the Federal Democratic Republic of
Ethiopia and encludes the revised
Constitution of the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Region;
8. “criminal law” means the criminal law
provided by the House of Peoples’
Representatives of the Federal
Democratic Republic of Ethiopia;
9. “Attorney General” means Attorney
General office of the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Regional
State;
10. “chief Attorney General” means a chief
head of the Regional Attorney General
office submitted by excutive council and
appointed by the South Nations,
Nationalities and Peoples’ Regional
Council;
11. “deputy Attorney General” means a
4
“በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት ርዕሰ መስተዳድር የተሾመ የክልል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ምክትል
ኃላፊ ነው፤
12. “ዓቃቤ ሕግ” ማለት በመስተዳድር ምክር ቤት
በሚወጣ ደንብ መሰረት የሚቀጠር ወይም
የሚመደብ እና የሚተዳደር የሕግ ባለሙያ
ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 7 መሠረት
የተሾሙ ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉን፣ ምክትል
ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግን እና በየእርከኑ ያሉት
የዓቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችንም
ይጨምራል፤
13. “ፖሊስ” ማለት ስልጣን ያለው የክልል ወይም
የፌደራል ፖሊስ ነው፡፡
14. “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤
15. የፆታ አገላለፅ፤ በዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ
ፆታ የተገለፀው ሴትንም ይጨምራል፡፡
ክፍል ሁለት
መቋቋም፣ተጠሪነት፣ሥልጣን እና ተግባር
3. መቋቋም
“የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት ከዚህ
በኋላ “ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ” እየተባለ የሚጠራ
ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው የመንግስት
መስሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፡፡
4. ዋና መስሪያ ቤት
የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዋና መስሪያ ቤት በሀዋሳ
deputy head of the Regional Attorney
General office appointed by the Chief
Executive of the South Nations,
Nationalities and Peoples’ Region State;
12. “public prosecutor” means a lawyer
employed or assigned and administered
under Regulation that is issued by the
Executive Council and includes the Chief
Attorney General, the deputy Attorney
General and heads of Attorney General
office in each level which are appointed
in accordance with Article 7 of this
Proclamation;
13. “police” means federal or regional police
with legal Power;
14. “person” means a natural person or a
body with legal personality;
15. Gender expression; for the purpose of
this Proclamation, expression in the
masculine gender includes the feminine.
PART TWO
Establishment, Accountability,
Powers And Duties
3. Establishment
The South Nations, Nationalities and Peoples’
Region State Attorney General (hereafter
called the “Attorney General”) is hereby
established as an autonomous government
office, which has its own legal personality.
4. Head Office
5
ከተማ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በክልሉ በተለያዩ
ቦታዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ወይም
ምድብ ጽህፈት ቤቶች ሊኖሩት ይችላል፡፡
5. ተጠሪነት
1. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ለርዕሰ
መስተዳድሩ እና ለመስተዳድር ምክር ቤት
ይሆናል፡፡
2. በዞን እና በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ያሉ የዓቃቤ
ህግ መምሪያ እና በልዩ ወረዳ ያሉ የዓቃቤ ህግ
ፅ/ቤቶች ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ እና
በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ዋና አስተዳዳሪ
ወይም ካንቲባ እና አስተዳደር ምክር ቤት
ይሆናል፡፡
3. በወረዳ፣በከተማ አስተዳደር እና በሀዋሳ ከተማ
ክፍለ ከተማ ያሉ የዓቃቤ ህግ ፅ/ቤቶች
ተጠሪነታቸው ለዞን፣ለልዩ ወረዳ ወይም
ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ህግ መምሪያ
ሀላፊ እና በየአስተዳደር እርከኑ ለሚገኙ ዋና
አስተዳዳሪ ወይም ካንቲባ ወይም ስራ አስፈፃሚ
እና አስተዳደር ምክር ቤት ይሆናል፡፡
4. በክልሉ በየትኛውም ደረጃ ለሚገኝ ዓቃቤያነ ሕግ
የበላይ ኃላፊ ጠቅላይ ዓቃቤ-ህግ ነው፡፡
5. በዚሁ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 4 የተጠቀሰው
እንደተጠበቀ ሆኖ በየትኛውም ደረጃ ያለ ዓቃቤ
ህግ ለበላይ ኃላፊያቸውና ለተመደቡበት የስራ
ዘርፍ ኃላፊዎቻቸው ተጠሪ ይሆናሉ፡፡
6. ሥልጣንና ተግባራት
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሚከተሉት ሥልጣንና
The head office of the Regional Attorney
General shall be in Hawassa and may have
branch or allocate offices in different area of
the region, as may be necessary.
5. Accountability
1. The Regional Attorney General shall be
accountable to the Chief Executive and
Executive Council;
2. The departments of public prosecutors in
zone and Hawassa City administration and
public prosecutor offices in especial woreda
shall be accountable to the Regional
Attorney General and to the chief
administrater or Mayor found at each
administration level;
3. The public prosecutor offices in woreda and
sub city of Hawasssa city shall be
accountable to the public prosecutor
departments of Zone, especial woreda or
Hawassa city administration and to the chief
administrater or Mayor or Executive found
at each administration level and
administration council;
4. Chief Attorney General shall be a head of
public prosecutors found at every level in
the Region;
5. Subject to Sub Article 4 of this Article,
public prosecutor at every level shall be
accountable to their principal heads and to
the division heads they are assigned;
6. Power and duties
6
ተግባራት ይኖሩታል፤
1. በሕግ ጉዳዮች የክልል መንግስት ዋና አማካሪ
እና ተወካይ ሆኖ ይሰራል፤
2. በፌደራል መንግስት ተዘጋጅቶ የጸደቀውን
የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ በክልሉ ውስጥ
ተግባራዊ እንዲሆን ያስተባብራል፣
ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
3. የወንጀል ፍትሕ መረጃዎችን መሰብሰብ፣
ማደራጀት፣ መተንተንና ማሰራጨት
የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስፈፅማል፡፡
4. በፌዴራልና በክልሉ ሕገ-መንግስታት እና
በሌሎች ሕጎች የተደነገጉ የግልና የቡድን
መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች
መከበራቸውን ያረጋግጣል፣
5. የወንጀል ጉዳይን በተመለከተ፤
ሀ) በክልሉ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር በሚወድቁ
በማናቸዉም የፀረ-ሙስና እና የታክስ ህጎችን
በመጣስ በሚፈፀሙ የወንጀል ጉዳዮች
እንዲሁም ከባድና ውስብስብ በሆኑ ሌሎች
የወንጀል ድርጊቶች የወንጀል ምርመራ
ከፖሊስ ጋር አብሮ ያጣራል፣ምርመራውን
በበላይነት ይመራል፡፡
ለ) በሕዝብ ጥቅም መነሻ ወይም በወንጀል
የማያስጠይቅ ሁኔታ መኖሩ በግልፅ ሲታወቅ
የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ ወይም
የተቋረጠው የወንጀል ምርመራ እንዲቀጥል
ያደርጋል፤ ማናቸውም የወንጀል
ምርመራዎች በሕግ መሰረት መከናወናቸውን
ያረጋግጣል፤ አስፈላጊውን ህጋዊ ትእዛዝ
ለሚመለከተዉ አካል ይሰጣል፤
The Regional Attorney General shall have the
following power and duties:
1. works as principal advisor and
representative of the Regional government
regarding law;
2. coordinates, follows up and ensures the
implementation of the criminal justice
policy, prepared and ratified by Federal
government, in the Region;
3. Develop the system enables to collect,
organize, analyze and distribute the
informations of criminal justice; execute the
same;
4. Ensure if basic right and liberties of the
individual and group stated in federal and
Regional Conistitutions and in other
laws,are respected;
5. regarding criminal matters:
a) Investigates tough and complex criminal
cases as well as every criminal cases
committed by violating the anti-
corruption and tax laws, with police,
which are falling under the jurisdiction
of Regional courts,direct investigation
principally.
b) Effects the discontinuation or restart of
discontinued investigation on the basis of
public interest or when it is clearly
known that there could be no criminal
liability, ensures that investigation is
conducted in accordance with the law,
gives the necessary instruction to the
7
ሐ) ምርመራቸው በፖሊስ በተጀመረባቸው
መካከለኛ፣ ቀላል እና በግል አቤቱታ
በሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ
በአግባቡ ስለመከናወኑ በቅርበት ክትትል
ያደርጋል፤ በተጀመረ የወንጀል ምርመራ
አስመልክቶ ፖሊስ ለዓቃቤ ህግ ማሳወቁን
ያረጋግጣል፤
መ) በወንጀል መዝገብ ላይ የተሰጠ የዓቃቤ
ሕግና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን
ለሚመለከተው ፖሊስ ያሳውቃል፣ የወንጀል
ምርመራ መዝገቦችን አስመልክቶ በየደረጃው
ባሉ ዓቃቤያነ ሕግ በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ
በፖሊስ የሚቀርቡ አቤቱታ ተቀብሎ ውሳኔ
ይሰጣል፤
ሠ) የተጠናቀቁ የምርመራ መዝገቦችን ከሕግና
ከማስረጃ አንፃር መርምሮ በሥነ-ሥርዓት
ሕግ መሰረት የተቀመጡ መመዘኛዎች
ሲሟሉ የ’አያስከስስም’ ወይም የ’ተዘግቷል’
ውሳኔ ይሰጣል፤
ረ) የጥፋተኝነት ድርድር ይወስናል፣ ድርድር
ያደርጋል፣ አማራጭ የመፍትሄ እርምጃ
እንዲወሰድ ይወስናል፣ ተግባራዊነቱን
ይከታተላል፤
ሰ) መንግስትን በመወከል የወንጀል ጉዳዩች ክስ
ይመሰረታል፣ ይከራከራል፣ ለህዝብ ጥቅም
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ክስ ያነሳል፣
የተነሳ ክስ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡
ሸ) የወንጀል ድርጊት ጠቋሚዎችና ምስክሮች
በህግ መሰረት ጥበቃና ከለላ እንዲያገኙ
concern body;
c) effects immediate follow up if a
criminal investigation of medium, simple
and perivatly presented petition issues
which has been started by the police are
conducted appropriately; ensures if the
police notify regarding criminal
investigation to the public prosecutor.
[
d) informs the relevant police about
decisions given on criminal case files by
the public prosecutor and court; receives
and gives decision on appeals presented
by the police against decisions given at
different level of the public prosecution;
e) provides appropriate legal decision on
completed investigation files based on
evidence and law in accordance with
procedure law;
f) determines guilty plea, conducts plea
bargaining, decides alternative actions to
be taken, follows the implementation;
g) institutes criminal case charges by
representing the federal government,
litigates, withdraws charge when found
necessary in the interest of the public,
resumes withdrew charge.
8
ያደርጋል፡፡
ቀ) በማረፊያ ቤትና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር
ሥር ያሉ ተጠሪጣሪዎችንና ታራሚዎችን
ይጎበኛል፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ
መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፣ ሕገ ወጥ
ተግባር ተፈፅሞ እንደሆነ እንዲታረም
ያደርጋል፡፡ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች
ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ ይወስዳል ወይም
እንዲወሰድ ያደርጋል፤
በ) በዕርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶች
በእርቅ የሚጠናቀቁበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
ተ) ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጡዋቸው
ውሳኔዎችና ትእዛዞች መፈፀማቸውንና
መከበራቸውን ይከታተላል፣ ሳይፈፀሙ ከቀሩ
ወይም አፈፃፀማማቸው ሕግን ያልተከተለ
ከሆነ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት
በማመልከት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ
ያደርጋል፤
ቸ) በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የወንጀል ቅጣቶች
በአግባቡ እንዲፈፀሙ ለማድረግ የሚያስችሉ
ሥርዓቶችን ያደራጃል ወይም መደራጀታቸውን
ያረጋግጣል፤
ኀ) የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ
በኩል እንዲቀርብ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን
ይከታተላል፡፡
6. የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በተመለከተ፤
h) Enacts the criminal act informant and
evidences to have protection and secure
under law;
i) pays visit to suspected and inmates under
custody at police stations and prisons,
ensure their handling and reside is
carried out in accordance with the law,
cause unlawful act to be corrected; take
measures or cause measures to be taken
based on the law against people who are
found to have transgressed the law;
j) facilitates the condition in which
criminal acts that are completed with
settlement to be considered with
settlement;
k) follows the implementation and
enforcement of judgments and orders
given by courts under criminal case,
applies to the court that gave judgments
and orders and makes corrective action
to be taken where they have not been
implemented or their implementation is
contrary to law;
l) organizes or ensures the establishment of
systems for the proper execution of
criminal punishments imposed by the
court of law;
m) causes death penalty decisions to be
submitted to the President of the
Federal Democratic Republic of
Ethiopia through Federal Attorney
General; follow up the execution.
9
ሀ) በክልል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የሕዝብ
እና የክልል መንግስት መብትና ጥቅም ወኪል
ሆኖ ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ እንዲከበሩ
ያደርጋል፣ የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፤
ለ) ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶችን የውል
ዝግጅት እና ድርድር ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር በመሆን ያደርጋል፣ የሕዝብና የክልል
መንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ይጎዳል ብሎ
ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች ውል እና የመግባቢያ
ሰነዶች ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል ወይም
የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤
ሐ) የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶችን በመወከል
የፍትሐብሔር ክስ ይመሰርታል፤ በከሰሱበት
ወይም በተከሰሱበት የፍትሐብሔር ጉዳዮች
ላይ ክርክር ያደርጋል፤ በተጀመረ ክርክር
ተቋማትን ተክቶ በተናጠል ወይም በጋራ
ይከራከራል፣ ወይም በክርክር አመራር ላይ
ለመሥሪያ ቤቶች አቅጣጫ ይሰጣል፣ በሕግ
መሠረት ለተሰጡ ዉሳኔዎች ፍርድን
ያስፈፅማል፤
መ) በክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና በግል
ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች መካከል የሚከሰቱ
የፍትሐብሔር ክርክሮች በድርድር እንዲያልቁ
ጥረት ያደርጋል፤ድርድሩ ካልተሳካ ጉዳዩን
ስልጣኑ ለሚፈቅድለት ፍርድ ቤት አቅርቦ
ይከራከራል፣
ሠ) የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ
በርሳቸው ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር
6. regarding civil matters:
a) litigates, enforces, causes enforcement,
follows and controls the process of
enforcement within the regional
government offices by acting as an agent
of rights and interest of the public and
regional government;
b) advises and participates with concerned
bodies in contract preparation and
negotiation of large government projects;
participates or advises concerned bodies
in other contract and consensuse
document preparation and negotiation
when it believes that public and
government interest could be affected;
c) institute civil suits on behalf of the federal
government office; represent them in civil
litigation where they sue or sued,
represent them in an ongoing civil
litigation by its own or together with
them; gives direction to government
offices on the management of the
litigation; cause execution of judgment on
decision imposed in accordance with law;
d) cause effort on the civil despute arising
among the regional government offices
and non-governmental organizations or
individuals to be completed in
negotiation; litigates presenting the issue
10
ጉዳዩች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት
ውጭ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ
እንዲወሰን ውሳኔ ሀሳብ ይሰጣል፤ በውሳኔው
መሰረት መፈፀሙን ያረጋግጣል፤
ረ) የተመዘበረ የመንግስት ገንዘብ ስልጣን ባለዉ
ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ያስመልሳል፡፡
የሙስና ወንጀል ዉጤት የሆኑት እና በፍርድ
ሂደት ላይ ያሉ ንብረቶችን ያስተዳድራል፤
እንዲወረስ ዉሳኔ የተሰጠባቸዉን ንብረቶች
ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል
ያስተላልፋል፡፡
ሰ) የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም
የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣
ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን
ወክሎ ይከራከራል፤
ሸ) የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ
ተበዳዩች እንዲካሱ መልሰው እንዲቋቋሙ
እንዲሁም ከጉዳቱ የተያያዙ የፍትሐብሔር
ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እነሱን በመወከል
የፍትሐብሔር ክስ ያቀርባል ወይም
ይደራደራል፤
7. የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅ እና ማስረፅ ሥራን
በተመለከተ፤
ሀ). በክልል መንግሥት የሚወጡ ሕጎች የሕግ
ረቂቅ ዝግጅት ስራ ይሰራል፤ የመንግስት
አካላት የሚያዘጋጁት ረቂቅ ህግ ከፌዴራልና
ከክልሉ ሕገ መንግስትና ከሌሎች ሕጎች ጋር
የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፣
to the court eligible if the negotiation fails
e) give decision for settlement of disputes
arising between regional government
offices through judicial means or out of
court alternative dispute settlement
mechanisms, and ensures the execution
of the decision;
f) administers properties that are on the
process of the court verdict and result
from corruption; pass the properties
which are decided to be successes to the
concerned government body; causes the
corrupted government money to be
returned by presenting charge to the court
havig power;
g) conducts litigation by representing
citizens who do not have financial
capacity to institute civil action; specially
women, children, disabled and the elderly;
h) represent victims of crime who do not
have financial means in litigations or
negotiations for their compensation,
reinstitution and protection of their civil
interests emanated from the damage
sustained;
7. regarding legal study, drafting and
decimination activity;
a) perform preparation of draft laws to be
promulgated by the regional
11
ለሚመለከታቸው ክፍሎችም አስተያየት
ያቀርባል፤
ለ) በክልሉ በስራ ላይ ባሉ ህጎች ጥናት በማድረግ
ሕጎች እንዲሻሻሉ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣
ሲደገፍም ለተባሉት ማሻሻያዎች ረቂቆችን
በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት
ያቀርባል፣
ሐ) ሕጐችን የማሰባሰብ፣የማጠቃለልና የኮዲፊኬሽን
ሥራ ይሰራል፤ የክልሉን ህጎች በባለአደራነት
ይይዛል፣ ያሰራጫል፤
መ) ዓቃቤያነ ሕግ ስለ ስራቸው ያላቸውን
አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት በተከታታይ
እና በየደረጃው ለማሳደግ ትምህርት እና
ሥልጠና ይሰጣል፤እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤
ሠ) የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ለማዳበር ለክልሉ
ህብረተሰብ በተለያዩ ዜደዎች የንቃተ ህግ
ትምህርት ይሰጣል፤
8. የጠበቆች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ሲቪክ
ማህበራት እና የሰነድ ማረጋገጥን በተመለከተ፤
ሀ. በክልሉ ፍርድ ቤቶች ለሚከራከሩ ጠበቆች
ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ስራቸውን
ይቆጣጠራል፣ የጠበቆችን ዲሲፕሊን
ጉዳዮች አይቶ ይወስናል፤ በህግ መሰረት
ይሰርዛል፣
ለ) በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያውያን የበጎ
አድራጎት ድርጅቶችንና ማህበራትን
ይመዘግባል፣ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ
ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ስራቸውን
government; ensure that draft laws
prepared by government organs are
consistent with the federal and regional
Constitutions and others laws; provide
legal opinion to concerned bodies;
b) conducts legal studies on the functional
laws in the region and present decision
idea to be reformed; submits to the
concerned bodies by preparing draft for
raised amendement when supported;
c) carry out codification, compilation and
consolidation of laws; hold and dispense
regional laws as atitle holder;
d) provide training or cause provision of
training and education at every level for
continuous development of the attitude,
knowledge and skill of public
prosecutors;
e) Provide legal awareness education in
different methods to the regional society
for the development of their legal
awareness.
8. regarding advocates, charity organizations,
civic societies and ;document certification;
a) supervise advocates practicing at
regional courts and services provided by
them; license, renew, revoke the license
in accordance with the law; determines
by overtaking disciplinary issues of
advocates;
b) recored the Ethiopian charity
12
ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፣ በሕግ መሰረት
ይሰርዛል፣
ሐ) አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ሰነዶችን
ይመዘግባል፣ ያረጋግጣል፣ ይሽራል፣
ይሰርዛል፣
መ) ነፃ የሕግ ድጋፍ አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን
ይቀርፃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ በመስኩ
የሚሰማሩ አካላትን ያስተባብራል፤
9. ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀግብር
መነሻ በማድረግ ክልላዊ ሰብአዊ መብት የድርጊት
መርሀ ግብርን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በመሆን ያዘጋጃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
በክልል ደረጃ የሚመለከታቸውን አካላት
ያስተባብራል፣ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት
ያቀርባል፤
10. የዓቃቤ ሕግ የውሳኔ አሰጣጥ እና የፍቅደ ሥልጣን
አጠቃቀም ወጥነትን ለማረጋገጥ በጠቅላይ ዓቃቤ
ሕግ የፀደቀ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን
ያረጋግጣል፤
11. በዓቃቤያነ ሕግ የሚሰጡ ውሳኔዎች በሕግ
መሰረት መከናወናቸውን የሚያረጋግጥ
የኢንስፔክሽን ክፍል ያደራጃል፣ ጉድለቶችን በጥናት
አስደግፎ ይለያል፤ በግኝቱ መሠረትም እንዲታረሙ
ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ ይወስዳል
ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፣ መልካም
ተሞክሮዎችን ይቀምራል፤ ያስፋፋል፤
12. የክልሉን ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
ሥራዎች በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
organizations and companies working in
the Region; issue legal personality
assurance certificate; supervise their
work; ensure; revoke by law;
c) record, ensure, repeal, and revoke
document under pertinent law;
d) design strategy for provision of free legal
aid, follow up implementation of same,
coordinate bodies engaged in the sector;
9. prepare regional human right action plan
together with the concerned bodies based
on national human rights action plan,
follow up implementation of same,
coordinate the concerned bodies at national
level; submit report to the relevant bodies;
[
10. ensure that the directive issued by the
Attorney General with the view to ensure
consistent application of discretion and
provision of decision of the public
persecutors is enforced;
11. organize inspection department and
investigate that decisions passed by public
prosecutors are in accordance with the law,
identify defects based on studies and take
corrective measures on the bases of findings
to rectify the problems; when necessary, take
measure or cause measures to be taken;
compute, scale up good practices;
13
ያስተባብራል፤የህግ ታራሚዎች ይቅርታ
የሚያገኙበትን ስርዓት ይዘረጋል፡፡
13. የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር
በሚወስነው አዋጅ የመስተዳድር ምክር ቤት አባል
ለሆኑ አስፈፃሚ አካል መስሪያ ቤቶች የተሠጡ
የወል ሥልጣንና ተግባርን ሥራ ላይ ያውላል፤
14. የንብረት ባለቤትና የይዞታ ባለመብት ይሆናል፣
ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
15. በሕግ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ወይም
ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን
ያከናውናል፡፡
7. ሹመት
1. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ በርዕሰ መስተዳድሩ
አቅራቢነት በክልል ምክር ቤት ይሾማል፡፡
2. ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በክልሉ ርዕሰ
መስተዳድር ይሾማል፡፡
3. በዞን፣በልዩ ወረዳ እና በሀዋሳ ከተማ
አስተዳደር ያሉ የዓቃቤ ህግ መምሪያ ኃላፊዎች
በየአስተደደር እርከኑ ዋና አስተዳዳሪ/ካንቲባ
አቅራቢነት በየእርከኑ ባሉ ምክር ቤቶች
ይሾማሉ፡፡
4. በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደር እና በክፍለ ከተማ
በየእርከኑ ያሉ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በየአስተደደር
እርከኑ ዋና አስተዳዳሪ/ካንቲባ/ ወይም ስራ
አስፈፃሚ አቅራቢነት በየእርከኑ ባሉ ምክር
ቤቶች ይሾማሉ፡፡
12. lead, follow up, coordinate principally the
activities of Regional prisonss administration
commission, develop the system in which
legal inmates acquire pardon;
13. exercise the common powers and duties
provided for, the offices of executive organ
and member of the Executive Council, under
the Definition of Powers and Duties of the
Executive Organs of the Southern Nations,
Nationalities and Peoples’ Regional State
Proclamation;
14. own and possess property, enter into
contracts, sue or be sued in its own name;
15. perform other activities that help to achieve its
objectives or carry out its power and duties
given by law.
7. Position
1. A chief Attorney General shall be appointed
by Council of the region up on the
recommendation of the Executive Council.
2. A Deputy Attorney General shall be
appointed by the Executive Council.
3. The heads of public prosecutor offices in
Zone, especial woreda and Hawassa City
administration shall be appointed at Council
of their level by approval of their
administrative level administrater/mayor.
4. The heads of public prosecutor offices in
woreda, urban center administration and sub
city levels shall be appointed at council of
their level by approval of their administrative
14
5. በየትኛውም ደረጃ የሚሾም የዓቃቤ ህግ
መስሪያ ቤት ሀላፊ በህግ ትምህርት እውቅና
ካለው ተቋም የተመረቀ መሆን አለበት፡፡
8. የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቋም
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣
1. አንድ ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና ምክትል
ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግ፤
2. የሥራ ዘርፎች፤
3. የማኔጅመንት ኮሚቴ፤
4. የክልል ዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ፤
5. በዓቃቤ ሕግ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት
የተቀጠሩ/የተመደቡ ዓቃቢያነ ሕግ፤ እና አስፈላጊ
ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡
9. የዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥልጣንና ተግባር
1. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የጠቅላይ ዓቃቤ
ሕግ የበላይ ኃላፊና የካቢኔ አባል በመሆን
በሙያውና በሕግ መሠረት ጠቅላይ ዓቃቤ
ሕግን ይመራል፣ ያስተዳድራል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፤
ሀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 የተመለከቱትን
ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ
ያውላል፤
ለ) በክልል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና
ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ 142/2004፣
እንዲሁም በተሻሻለው የገቢዎች
level administrater/mayor or executive.
5. The head of public prosecutor to be
appointed at every level shall be a graduate in
legal education from recognized institution.
8. Organization of the Attorney General
The Attorney General shall have:
1. a chief Attorney General and Deputy
Attorney Generals;
2. line divisions;
3. Management Committee;
4. Regional Public Prosecutors
Administration head Council;
5. Public prosecutors employed/assigned in
accordance with the public prosecutor
administrative Regulation; and necessary
staffs.
9. Powers and Duties of the ChiefAttorney
General
1. The Chief Attorney General shall be the
head of the Attorney General and a
member of cabinet; and lead and
administer the Attorney General
professionally and in accordance with the
law.
2. Without prejudice to sub-article of this
Article, the Chief Attorney General shall
have the powers and duties to:
a) exercise the powers and duties
stipulated under Article 6 of this
Proclamation;
b) exercise the prosecution powers and
duties given to the organizations in the
15
ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
143/2004 ለተቋማት ተሰጥተው የነበሩ
የዓቃቤ ህግነትን የተመለከቱ ሥልጣንና
ተግባራትን ሥራ ላይ ያውላል፤
ሐ) በምክትል ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግ
እንዲሁም በየእርከኑ ባሉ የዓቃቤ ህግ
መስሪያ ቤት ኃላፊዎች የዓቃቤ ህግ ስራ
አስመልክቶ የተሰጡ ውሳኔዎችን
ያፀድቃል፣ያሻሽላል፣ይለውጣል፣ይሽራል
ወይም ጉዳዩ እንዲጣራ ወይም እንደገና
እንዲታይ ያደርጋል፤
መ) ዓቃቢያነ ህግን በኣቃቢያነ ህግ መተዳደሪያ
ደንብ መሰረት እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ
ሠራተኞችን በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ
ህጎች መሰረት ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፣
በህግ መሰረት ያሰናብታል፤
ሠ) የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን ስትራቴጂክ
ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም በስራ
ላይ ያውላል፤
ረ) ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተፈቀደለት በጀት
እና የሥራ ፕሮግራም መሰረት ገንዘብ
ወጪ ያደርጋል፤
ሰ) ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደርጉት
ግንኙነቶች ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን
ይወክላል፤
ሸ) የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን የሥራ አፈጻጸም
እና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ
ለመንግስት ያቀርባል፤
ቀ) ለሥራ ቅልጥፍናና ውጤታማነት
Regional Ethics and Anti- corruption
Commission under its establishment
Proclamation No 142/2012 and in the
revised Revenues Authority under its
establishment Proclamation No.
143/2012;
c) revoke, change, modify, suspend,
approve the decision given by deputy
Attorney Generals and heads of public
prosecutors office concerning public
prosecutor activity, or refer the case
for re-examination or revision by the
one that has given the decision;
d) hire, administer public prosecutors in
the by laws of public prosecutors and
the supporting staff of the Attorney
General in accordance with the
Regional civil service laws; and
dismiss in accordance with law;
e) prepare strategic plan and budget of
the Attorney General, and implements
same upon approval;
f) effect payment in accordance with the
budget approved and work program of
the Attorney General;
g) represent the Attorney General in
its dealings with third parties;
h) prepare and submit the performance
and financial report of the Attorney
General to the Government;
i) delegate part of his powers and
16
በሚያስፈልግ መጠን ከሥልጣንና
ተግባሩ በከፊል ለምክትል ዋና ጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ፣ ዓቃቤያነ ሕግና ሠራተኞች
በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡
በ) በሕግ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት
ያከናውናል፡፡
10. የምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥልጣንና ተግባር
ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ለዋና
ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ሆኖ፣
1. ለዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ የተሰጡትን
ሥልጣንና ተግባራት በማቀድ፣ በማደራጀት፣
በመምራትና በማስተባበር ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ
ሕጉን ያግዛል፤
2. የሚመደብባቸውን ዘርፎች ይመራል፣
ያስተዳድራል፤
3. በዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ተለይተው
የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
4. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ በማይኖርበት ጊዜ
ውክልና ያልተሰጠ እንደሆነ በሹመት
ቅድሚያ ያለው ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
የዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግነት ሥራን ተክቶ
ይሰራል፤
11. ከሹመት ስለመነሳት
1. ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ እና ምክትል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንደዚሁም በየእርከኑ
የሚገኙ የዐቃቤ ሕግ ሀላፊዎች
ከሹመታቸዉ ሊነሱ ይችላሉ፡፡
duties to deputy chief attorney
general, public prosecutors and
employees to the extent necessary
for effective and efficient
performance of the activities of the
Attorney General;
j) perform other activities given to him
by law.
10. Power and Duties of the Deputy Attorney
Generals
Deputy attorney general shall be accountable
to a chief attorney general, and;
1/ shall assist the Chief Attorney General
in planning, organizing, leading and
coordinating powers and duties given
to a chief Attorney General;
2/ shall lead and administer the line
divisions to which he is assigned;
3/ shall perform specific duties given to
them by the Chief Attorney General;
4/ in the absence of the Chief Attorney
General, without giving delegation, the
senior Deputy Attorney General shall
represent and perform the duties of the
Chtef Attorney General;
11. Removal from position
1. The Chief Attorney General and the
Deputy Attorney General as well as the
public prosecutors at various levels may
be removed from their position.
17
12. የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር
የዓቃቤያነ ሕግ አስተደደር በመስተዳድር ምክር
ቤት በሚወጣ የዓቃቢያነ ህግ መተዳደሪያ ደንብ
ይወሰናል፡፡
13. የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ
1. የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ በዚህ
አዋጅ ተቋቁሟል፤ የጉባኤው ሰብሳቢ ዋና
ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ይሆናል፡፡ የጉባኤውን
አባላት፣ የአሠራር ሥነ-ሥርዓትና ሌሎች
ዝርዝር ጉዳዮች የመስተዳድር ምክር ቤት
በሚያወጣው የዓቃቢያነ ህግ አስተዳደር ደንብ
ይወሰናል፡፡
2. የራሱ ጽህፈት ቤት፣ለስራዉ የሚያስፈልጉ
ዓቃቢያነ ህግ እና በዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ
የሚሰየም የጽህፈት ቤት ኃላፊ ይኖረዋል፡፡
ክፍል ሶስት
ሙያዊ ነፃነትና ተጠያቂነት
14. የዓቃቤያነ ሕግ የሙያ ነፃነት
ዓቃቤ ሕግ ሥልጣኑንና ተግባሩን ሲያከናውን
ከማንኛውም ሰው ወይም አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ
ሆኖ በሕግ መሠረት ብቻ ይፈፅማል፡፡
15. . ተጠያቂነት
በየትኛውም ደረጃ ያለ ዓቃቤ ሕግ በሥራ
አፈፃፀማቸውና በሥነ-ምግባራቸው ለሚታየው
ጉድለት የዲስፕሊን ተጠያቂነቱ በመስተዳድር ምክር
ቤት በሚወጣው የዓቃቢያነ ህግ መተዳደሪያ ደንብ
` 12. Administration of Public Prosecutors
The administration of public prosecutors
shall be determined by by-laws of public
prosecutors which is issued by the Executive
Council.
13. public prosecutors’ administration head
council
1. The Public Prosecutors Administration head
Council is hereby established with this
Proclamation; the chair person of the council
shall be a chief Attorney General. The
members, working procedures and the details
of which shall be determined by public
prosecutors administration regulation to be
issued by the Executive Council.
2. The assembly shall have its own office,
public prosecutors necessary for work, and
head of the office who is assigned by a Chief
Attorney General.
PART THREE
Proffetional Independence And
Accountablity
14. Public Prosecutors’ Professional
Independence
The Attorney General shall discharge its
powers and duties based on law independently
free from any person or body’s interference.
15. Accountability
Public prosecutors in every level shall be
accountable, in accordance with the public
prosecutors’ working Regulation issued by
Executive Council, for defects in their work
18
መሰረት ይሆናል፡፡
16. አቤቱታ የማቅረብ መብት
1. ዓቃቤ ሕግ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ
ያለው ማንኛውም ሰው በየደረጃው ለሚገኙ
የዓቃቤ ሕግ ኃላፊዎች አቤቱታ የማቅረብ
መብት ይኖረዋል፤ አቤቱታ የቀረበለት ኃላፊ
ጉዳዩን በአፋጣኝ አጣርቶ ውሳኔ መስጠት
አለበት፡፡
2. አቤቱታ የቀረበለት ኃላፊ ጉዳዩን ለማጣራት
አግባብ ያላቸውን ባለሙያዎች የሚያካትት
ኮሚቴ ሊያቋቁም ይችላል፡፡
3. አቤቱታውን የመረመረው ኃላፊ የሕግና
የማስረጃ ምክንያቱን በመጥቀስ በበታች ዓቃቤ
ሕግ የተሰጠውን ውሳኔ ለማጽደቅ፣
ለማሻሻል፣ለመለወጥ፣ለመሻር፣ለማገድ ወይም
ጉዳዩን አስቀድሞ አይቶ ወደ ወሰነው ክፍል
ለመመለስ ይችላል፡፡
4. ከላይ በአንቀፅ 3 መሰረት በተሰጠዉ ዉሳኔ
ቅሬታ ያለዉ አካል ቅሬታዉን ደረጃዉን
ጠብቆ እስከ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ድረስ
በየእርከኑ ላሉት የበላይ ሀላፊዎች ማቅረብ
ይችላል፡፡ሆኖም የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ዉሳኔ
የመጨረሻ ይሆናል፡፡
17. ጥቆማ ወይም አስተያየት የማቅረብ መብት
1. ማንኛውም ሰው በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
ሥልጣንና ተግባር ውስጥ የሚወድቅ
ማንኛውም መታረምና መስተካከል አለበት
የሚለውን ጉዳይ ወይም ተፈጽሟል የሚለውን
የሥነ-ምግባርና የሕግ ጥሰት በማናቸውም
መንገድ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲሁም
performance and ethics.
16. Right to Lodge Complaint
1. Any person who has grievance against the
decision of public prosecutor has the right
to lodge complaint to the public
prosecutor’s heads at different levels. A
head received complaint shall urgently
investigate and give decision.
2. A head received complaint may form a
committee containing relevant professionals
to investigate the case.
3. A superior considering the complaint may
suspend, change, modify, revoke or approve
the decision of the subordinate public
prosecutor or return the case to the section
that saw the case previously by stating his
legal and factual reasons.
4. A body that has an appeal on decision set in
accordance with Article three may submit
its appeal to the heads of Attorney General
at each level; whereas the decision by
Attorney General shall be the end,
17. Right to Inform or Present Suggestion
1. Any person may inform or present
suggestion to the Attorney General or to
the public prosecutor’s heads at different
levels in any way on any matter which
falls under the power and duty of the
Attorney General which he believes
19
በየአስተዳደር እርከኑ ላሉት የዓቃቤ ህግ
መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ጥቆማ ወይም
አስተያየት ለማቅረብ ይችላል፡፡
2. በዚህ አንቀፅ በንዑስ ቁጥር አንድ መሰረት
ጥቆማ ወይም አስተያየት የሚቀበሉ አካላት
ጥቆማ፣ አስተያየትና ቅሬታዎችን
የሚቀበሉበትን፣ የሚያጣራበትና የመፍትሄ
እርምጃ የሚወሰድበት እና ለሕብረተሰቡ
የሚገለጽበትን የአሠራር ሥርዓቶች ይዘረጋል፡፡
ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
18. መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ
1. በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት አስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር
ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 161/2008
እና በሌሎች ሕጎች ለፍትሕ ቢሮ ተሰጥተው
የነበሩ ሥልጣንና ተግባራት በዚህ አዋጅ
መሠረት ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተላልፈዋል፡፡
2. በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና
ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 142/2004
እና በሌሎች ሕጎች ለክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-
ሙስና ኮሚሽኑ ተሰጥቶ የነበረ የዓቃቤ
ሕግነት ሥልጣን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
ተላልፏል፡፡
3. በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ
ቁጥር 143/2004 እና በሌሎች ሕጎች ለባለስልጣኑ
ተሰጥቶ የነበረው የዓቃቤ ሕግነት ሥልጣን ለጠቅላ
ይጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተላልፏል፡፡
should be corrected and rectified or his
claim of ethical and legal violation which
has been committed.
2. In accordance with sub article 1 of this
Article, bodies that collect inform and
suggestion shall lay down working system
whereby suggestion and complaints are
received, investigated and corrective
measures are taken and notified to the
public.
PART FOUR
Miscelaneous Provisions
18. Transfer of Rights and Duties
1. The powers and duties given to the Bureau of
Justice under the Definition of Powers and
Duties of the Executive Organs of the
Southern Nations, Nationalities and
Peoples’Regional State Proclamation No.
161/2016 and other laws are hereby
transferred to Attorney General pursuant to
this Proclamation.
2. The public prosecution power given to the
Southern Nations, Nationalities and Peoples’
Regional State Ethical and Anti-corruption
Commission under its establishment
Proclamation No142/2012 and other laws are
hereby transferred to Attorney General.
3. The public prosecution power given to the
Southern Nations, Nationalities and Peoples’
Regional State Revenues Authority under its
establishment Proclamation No. 143/2012 and
other laws are hereby transferred to Attorney
General.
20
4. የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር
እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
161/2008 አንቀፅ 30 ንዑስ አንቀፅ 13 እና
በማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ማቋቋሚያ
ደንብ ቁጥር 137/2008 አንቀፅ 6 ንፁስ አንቀጽ 1
መሰረት የክልሉን ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
አስመልክቶ ለጸጥታና አስተዳደር ቢሮ የተሰጠዉ
ስልጣን በዚህ አዋጅ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ
ተላልፉል፡፡
5. በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር
813/2ዐዐ6 እንዲሁም በሌሎችሕጎች ለንግድ
ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ተሰጥቶ
የነበረው የዓቃቤ ሕግነት ሥልጣን ለክልል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተላልፏ፡፡
6. በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ
ቁጥር 813/2ዐዐ6 እንዲሁም በሌሎች ሕጎች
ለንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን
ተሰጥቶ የነበረው የወንጀል ምርመራ የማድረግ
ሥልጣን ለክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተላልፏል፡፡
7. የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
የፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማዕክል
ተጠሪነት በዚህ አዋጅ ለጠቅላይ ዓቃቤ-ህግ
ተላልፏል፡፡
19. የመተባበር እና የመፈጸም ግዴታ
1. የክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ዓቃቤያነ ሕግ በሕግ
የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር ለመወጣት
4. The power given to the security and
administration bureau, regarding the regional
prisons commission, according to Article 30,
sub Article 13 of the Proclamation
No.161/2016 which is issued to redetermine
the Powers and duties of the executive organs
of the Southern Nations, Nationalities and
Peoples’ Region State and the prisons
administration commission of the region is
accountable to the security and administration
bureau of the region in Article 6, sub Article 1
of Regulation No.137/2016 , is transferred to
Attorney General hereby this Proclamation.
5. The prosecution power given to the Trade
competition and consumers protection
Authority under the proclamation. No
813/2013 and other laws are hereby
transterred to the region state Attorney
General.
6. The crime investigation power to the Trade
competition and consumers’ protection
Authority under proclamation No.813/2013
and other laws are hereby transferred to the
region police commission.
7. The accountability of the Suthern Nations,
Nationalities and Peoples’ Reogion Justs
Organs profesionals traiming center
transferred to Attorney General hereby this
Proclamation.
19. Duty to Cooperate
1. Any person who is requested to cooperate
with the Regional Attorney General and
public prosecutors in the execution of their
21
ትብብር የተጠየቀ ማንኛውም ሰው ከአቅም በላይ
ያልሆነ እና ጉዳት የማያስከትልበት ከሆነ
የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
2. ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በሥራ ላይ የነበሩ
የክልል ፍትህ ቢሮ እና የስር መዋቅር አመራር እና
ሠራተኞች፣የገቢዎች ባለሥልጣን አመራር እና
ሰራተኞች በዚህ አዋጅ መሠረት የሚደረገውን
ሽግግር የመተባበርና የመደገፍ ግዴታ አለባቸው፡፡
3. ማንኛውም የፖሊስ አባል የዓቃቤ ሕግን የመጨረሻ
እና ሕጋዊ ውሳኔ የማክበር እና የመፈጸም ግዴታ
አለበት፡፡
20. የወንጀል ተጠያቂነት
1. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና ዓቃቤያነ ሕግ
ሥራቸውን በነፃነት እንዳያከናውኑ ጣልቃ
የሚገባ ወይም የሚሰጡትን ህጋዊ ውሳኔ
የማያከብርና የማያስፈጽም እንዲሁም
የመተባበር ግዴታውን የማይወጣ ማንኛውም
ሰው አግባብ ባለዉ የወንጀል ህግ ይጠየቃል፡፡
2. ማንኛውም የፖሊስ አባል የዓቃቤ ሕግን
የመጨረሻ እና ሕጋዊ ውሳኔ በመቃወም
ያልታዘዘ እንደሆነ አግባብ ባለው ሕግ
በወንጀል ይጠየቃል፡፡
21. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች
1. በመስተዳድር ምክር ቤት የወጡ ደንቦች፣ በፍትሕ
ቢሮ፣ በክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን እና በክልል
የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የወጡ የጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ ሥልጣንና ተግባር ለማስፈፀም
አግባብነት ያላቸው መመሪዎች እና ማኑዋሎች
በሌሎች ደንቦች፣ መመሪያዎች ወይም ማኑዋሎች
powers and duties has a duty to cooperate if it
is not beyond his capacity and does not cause
danger.
2. Leaders and employees of the Regional
Justice Bureau and the subordinate structure,
leaders and employees of the revenue
authority who have been in charge before the
coming into force of this Proclamation have
duty to cooperate with and assist the transition
based on this Proclamation.
3. Any member of the police shall have duty to
respect and execute final and legal decision of
the public prosecutor.
20. Criminal Liability
1. Any person, who does not respect and
execute the authorized decision provided as
well as does not exercise; or interferes
against the Attorney General and public
prosecutors inorder not perform their work
independently, shall be liable by pertinent
criminal law.
2. Any member of the police who resists and
fails to execute the final and legal decision
of the public prosecutor shall be punished in
accordance with relevant law.
21. Transitory Provisions
1. The regulations issued by the Executive
Council, directives and manuals issued by the
Bureau of Justice, Regional Revenues
Authority, Regional Ethics and Anti-
corruption Commission which are relevant
for the enforcement of the powers and duties
of the public prosecution shall be applicable
22
እስካልተተኩ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል፡፡
2. አግባብነት ያላቸው የተሻሻለው የፌደራል የፀረ-
ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ አዋጅ
434/97 (በአዋጅ ቁጥር 882/2007
እንደተሻሻለ)፣የተሻሻለው የፌደራል ስነ ምግባርና
ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
433/2007 (በአዋጅ ቁጥር 883/2007
እንደተሻሻለ)፣የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ
አዋጅ ቁጥር 881/2007 በክልሉ በሚፈፀሙ
የሙስና ወንጀሎች እንደየአግባብነቱ ተፈፃሚ
ይሆናሉ፡፡
3. በክልሉ ፍትህ ቢሮ፣በገቢዎች ባለስልጣን እና
በክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ተቀጥረው ወይም ተመድበዉ በሥራ ላይ የሚገኙና
በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የሚወጡ መሥፈርቶቹን
አሟልተው ወደ ክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መስሪያ
ቤት የሚዛወሩ ዓቃቤያነ ሕግ በዚህ አዋጅ መሠረት
በዓቃቤ ሕግነት ሥራቸውን ይቀጥላሉ፡፡፡
4. በክልሉ ፍትህ ቢሮ፣በገቢዎች ገቢዎች ባለስልጣን
እና በክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ለዓቃቤ ሕግ የሥራ ክፍሎች በድጋፍ ሰጪነት
ሥራ ላይ የሚገኙና በክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
ውሳኔ ወደ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሚዛወሩ
የመንግስት ሰራተኞች በዚህ አዋጅ መሠረት የክልል
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሠራተኞች ሆነው ሥራቸውን
ይቀጥላሉ፡፡
5. በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ
ሆነው ነገር ግን በክልሉ ፍትህ ቢሮ፣የሥነ-
ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ በገቢዎች
ባለሥልጣን ተይዘው በመታየት ላይ የሚገኙ
unless replaced by other regulations,
directives or manuals.
2. The Federal Ethics and Anti-corruption
Commission under its establishment
Proclamation No 433/2005 (as amended by
Proclamation No. 883/2015) and the Revised
Anti-corruption Special Procedure and
Evidence Proclamation No. 434/2005 (as
amended by Proclamation No. 882/2015 and
Proclamation No.881/2015 issued to
determine the Corruption crimes shall be
executed as may be necessary.
3. The Public prosecutors, who are employed or
assigned to worke for Regional Ethics and
Anti-corruption Commission, Revenues
Authority, and Justice Bureau, and
transferred to the Attorney General upon
satisfying the criteria issued by Attorney
General, shall continue their work as public
prosecutors pursuant to this Proclamation.
4. Public servants, working as supporting staff
for prosecution departments, in the Regional
Justice Bureau, Ethics and Anti-corruption
Commission, and Regional Revenues
Authority, and transferred to the Attorney
General by decision of the Regional Attorney
General, shall continue their work as
employees of the Regional Attorney General
pursuant to this Proclamation.
5. The criminal and civil cases, which are
pending under the power of the regional
Justice Bureau, Ethics and Anti-Corruption
Commission, and Revenues Authority but
23
የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች የክልሉ ጠቅላይ
ዓቃቤ ሕግ በአራት ወር ውስጥ እስኪረከባቸው
ድረስ በተጀመሩበት አኳኋን መታየት ይቀጥላሉ፣
እንዲሁም በነዚህ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ዓቃብያነ-
ሕግ እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች አስተዳደር
በነበረበት ሁኔታ ይቀጥላል፡፡
6. በዲሲፕሊን ኮሚቴዎች ወይም በሌሎች የዓቃቤ
ሕግ አስተዳደር ጉባኤዎች በመታየት ላይ ያሉ
የዓቃቤ ሕግ የዲስፕሊን ክስ ጉዳዮች በዚህ አዋጅ
መሠረት ለተቋቋመው የዓቃቤያነ ሕግ አስተዳደር
ጉባኤ ተላልፈዋል፡፡
7. በክልል ፍትህ ቢሮ፣ የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና
ኮሚሽን እና በክልል ገቢዎች ባለሥልጣን እጅ
የሚገኙ ጥቆማዎች፣ የምርመራ እና የዓቃቤ ሕግ
መዛግብትና ሰነዶች እንዲሁም
ኤግዚብቶች፣የተያዙና በክርክር ላይ ያሉ ንብረቶች
ወደ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይዛወራሉ፡፡
8. በክልሉ ስነ ምገባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና
በክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የተጀመሩ
የወንጀል ምርመራዎች ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን
ተላልፏል፡፡
22. በጀት
የክልል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከመንግስት
በሚመደብለት በጀት ይተዳደራል፡፡
droped under the jurisdiction of the Attorney
General, shall be continued in the manner
they were started until the Regional Attorney
General accepts them within four months; the
public prosecutors and supporting staff
administration shall continue as they are.
6. Discipline charge Cases of the public
prosecutors pending under the discipline
committee or other public prosecutors
administration councils shall be transferred to
the public prosecutors administration council
established in accordance with this
Proclamation;
7. The uncovering, investigation found under
the Regional Justice Bureau, Regional Ethics
and Anti- corruption Commission, and
Regional Revenues Authority, and files and
documents of public prosecutors, as well as
showings, seized properties and properties on
dispute shall be transferred to Attorney
General.
8. Criminal investigations that are strated in the
Region Anti corruption Commision and
Revenue Authority are transmitted to the
Region Police Commission
22. Budget
The Regional Attorney General shall be
administered by budget allocated by the
Government.
24
23. የሂሳብ መዛግብት
1. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተሟላና ትክክለኛ የሂሳብ
መዛግብት ይይዛል፡፡
2. የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ
ሰነዶች በክልል ዋና ኦዲተር ወይም በዋና ኦዲተር
በሚሰየም ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡
24. ደንብና መመሪያ የማውጣት ስልጣን
1. የመስተዳድር ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም
የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
2. ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይህን አዋጅ እና በዚህ
አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የወጡ
ደንቦችን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን
ሊያወጣ ይችላል፡፡
3. በህግ መሰረት ለህዝብ ይፋ እንዳይደረጉ
ከተከለከሉ ሚስጥራዊ ሰነዶች በስተቀር
የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በማናቸውም
መንገድ እንዲታተሙ እና እንዲሰራጩ
ይደረጋል፡፡
25. ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች
ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ሕጎች
በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዳዩች ላይ
ተፈፃሚት አይኖራቸውም፡፡
26. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ በክልል ምክር ቤት ከፀደቀበት ቀን
ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
ሀዋሳ …….. ቀን 2011 ዓ.ም ሚሊዮን ማቲዎስ
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር
23. Books of Accounts
1. The Attorney General shall keep complete
and accurate books of account.
2. The books of accounts and financial
documents of the Attorney General shall be
audited annually by the Regional Auditor
General or by an auditor designated by him.
24. Power to Issue Regulation and Directive
1. The Executive Council may issue
regulations necessary to enforce this
Proclamation.
2. The Attorney General may issue directives
necessary for the enforcement of this
Proclamation and regulations issued
pursuant to sub-article (1) of this Article.
3. Except the secret documents banned to
public by law, directives issued shall be
published and disseminated by any means.
25. Inapplicable Laws
No laws, in so far that they are inconsistent
with this Proclamation, shall be applicable
with respect to matters covered under this
Proclamation.
26. Effective Date
This Proclamation shall enter into force on the
date of its approval by regional council.
Hawassa this -------day of 2018
Milion Mathewos
Chief executive of the South Nations,
Nationalities and Peoples Region state
25