4
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት .75 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Communication and International Relations Department Bi-monthly News Letter No.75 ገጽ የካቲት 15 ቀን 2006ዓ.ም. በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የኢኮኖሚ ሚንስትር የሚመራ የንግድ ልዑክ ሊመጣ ነው በተባበሩት የአረብ ኤሜሬት የኢኮኖሚ ሚንስትር የሚመራ ከፍተኛ የንግድ ልዑካን ቡድን እ.አ.. ማርች 14 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሊመጣ ነው፡፡ የካቲት 14 ቀን 2006ዓ.ም. በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዱባይ የንግድ አማካሪ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ዋሊድ ሃሬብ አል ፋላሂ እንደተናገሩት ወደኢትዮጵያ የሚመጣው የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንትና የንግድ እድሎችን ለማጥናት ፣ በግልም ሆነ በእሽሙር ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ለመስራት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ከመንግስትና ከግል ከተወጣጡ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አማካሪው “በሀገራችን ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በኢትዮጵያ የሚመረቱ በርካታ ምርቶች መኖራቸው መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው” በማለት በሸራተን ሆቴል በሚከናወነው የኢትዮ- አረብ የንግድና ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ተገኝተው ቢዝነስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮሚዩኒኬሽንና አድራሻ ፋክስ: - +251-011-5517699 ኢ.ሜይል: [email protected] ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ አዲሱ ተክሌ በበኩላቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ትኩረት የሰጣቸውን የኢንቨስትመንት መስኮች ያብራሩ ሲሆን በነዚህ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች እንዲገኙ በደረግ የተሻለ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ በሸራተን ሆቴል ለሚደረገው ኮንፈረንስ ምክር ቤቱ የሀገሪቱን የንግድ ማኅበረሰብን በመጥራትና በማስተባበር የበኩሉን ሀላፊነት እንደሚወጣ አቶ አዲሱ አያይዘው ተናግረዋል፡፡ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን በዝርዝር ያስረዱት ሥራ አስኪያጁ የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሸራተን ሆቴል በሚካሄደው የንግድና ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የንግድ ልዑካን የአቻ ለአቻ ውይይት እንደሚያደርጉ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የቻይና የንግድ ልዑካን በመጋቢት ወር መጨረሻ ሊመጡ ነው ቁጥራቸው ከ20 እስከ 25 የሚጠጉ የቻይና የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት ለማድረግ እና እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማየት በመጋቢት ወር መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የቻይና የሳይንስና ኢንግነሪንግ ኮሌጅ ልዑክ

Bi-monthly News Letter No.75 በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ...ethiopianchamber.com/Data/Sites/1/yek-15(74).pdfበዚህም ምክንያት ግብር ከፋዩ በታክስ

  • Upload
    others

  • View
    1

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

  • በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ

    በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.75 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

    Communication and International Relations Department Bi-monthly News Letter No.75

    ገጽ

    የካቲት 15 ቀን 2006ዓ.ም.

    በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የኢኮኖሚ

    ሚንስትር የሚመራ የንግድ ልዑክ ሊመጣ

    ነው

    በተባበሩት የአረብ ኤሜሬት የኢኮኖሚ ሚንስትር የሚመራ ከፍተኛ

    የንግድ ልዑካን ቡድን እ.አ.. ማርች 14 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ

    ሊመጣ ነው፡፡

    የካቲት 14 ቀን 2006ዓ.ም. በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት

    ምክር ቤት በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዱባይ የንግድ

    አማካሪ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ዋሊድ ሃሬብ አል ፋላሂ

    እንደተናገሩት ወደኢትዮጵያ የሚመጣው የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ

    ያለውን የኢንቨስትመንትና የንግድ እድሎችን ለማጥናት ፣ በግልም ሆነ

    በእሽሙር ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ለመስራት እንደሆነ

    ተናግረዋል፡፡

    በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ

    ከመንግስትና ከግል ከተወጣጡ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር

    ቃለ ምልልስ ያደረጉት አማካሪው “በሀገራችን ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው

    በኢትዮጵያ የሚመረቱ በርካታ ምርቶች መኖራቸው መልካም

    አጋጣሚ የሚፈጥር ነው” በማለት በሸራተን ሆቴል በሚከናወነው

    የኢትዮ- አረብ የንግድና ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች

    ተገኝተው ቢዝነስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

    የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮሚዩኒኬሽንና

    አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

    ኢ.ሜይል: [email protected]

    ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

    አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ አዲሱ ተክሌ

    በበኩላቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ትኩረት የሰጣቸውን

    የኢንቨስትመንት መስኮች ያብራሩ ሲሆን በነዚህ ዘርፎች ላይ

    የተሰማሩ ባለሀብቶች እንዲገኙ በደረግ የተሻለ ውጤት

    ማግኘት እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡

    በሸራተን ሆቴል ለሚደረገው ኮንፈረንስ ምክር ቤቱ የሀገሪቱን

    የንግድ ማኅበረሰብን በመጥራትና በማስተባበር የበኩሉን

    ሀላፊነት እንደሚወጣ አቶ አዲሱ አያይዘው ተናግረዋል፡፡

    በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን

    በዝርዝር ያስረዱት ሥራ አስኪያጁ የኢኮኖሚ ትብብራቸውን

    ለማጠናከር ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

    በሸራተን ሆቴል በሚካሄደው የንግድና ኢንቨስትመንት

    ኮንፈረንስ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የንግድ

    ልዑካን የአቻ ለአቻ ውይይት እንደሚያደርጉ ለመረዳት

    ተችሏል፡፡

    የቻይና የንግድ ልዑካን በመጋቢት

    ወር መጨረሻ ሊመጡ ነው

    ቁጥራቸው ከ20 እስከ 25 የሚጠጉ የቻይና የንግድ ልዑካን

    ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የአቻ ለአቻ ውይይት ለማድረግ

    እና እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት

    እድሎችን ለማየት በመጋቢት ወር መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ

    እንደሚመጡ የቻይና የሳይንስና ኢንግነሪንግ ኮሌጅ ልዑክ

  • በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ

    በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.74 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

    Communication and International Relations Department Bi-monthly News Letter No.74

    አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

    ኢ.ሜይል: [email protected]

    ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

    ገጽ-3

    የካቲት 15 ቀን 2006ዓ.ም.

    ሚስ ኩንግ ዚያ ገለፁ፡፡

    ሚስ ዚያ ይህንን የገለፁት በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት

    ምክር ቤት የካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ከዋና ፀሀፊው አቶ ጋሻው

    ደበበ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

    በዕለቱ ዋና ፀሀፊው ስለምክር ቤቱ አደረጃጀት፣ የሥራ ኃላፊነት፣

    ራዕይና ተልዕኮ በዝርዝር ያብራሩ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት

    የንግድ ልዑካን የሚመጡበትን ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ መንግስት

    ትኩረት በሰጠባቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ

    ቢሆኑና በተለይ በኮንስትራክሽን፣ በማዕድን ማውጣት፣ በግብርና

    ማቀነባበሪያ ላይ ቢሆን የተሻለ ይሆናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

    የንግድ ልዑካኑ ወደኢትዮጵያ ሲመጡ ከፍተኛ የቻይና የመንግስት

    የስራ ኃላፊዎች አብረው እንደሚመጡ የተገለፀ ሲሆን በእለቱ

    ከኢትዮጵያዊያን አቻዎቻቸው ጋር የንግድ ለንግድ ውይይት

    እንደሚያደርጉም ለመረዳት ተችሏል፡፡

    በግብር ይግባኝ አቀራረብ እና በቫት ተመላሽ

    አከፋፈል ዙሪያ ዓውደ ጥናት ተካሄደ

    በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የመንግስትና ግሉ

    ዘርፍ የምክክር መድረክ ጽ/ቤጽ ያዘጋጀው በግብር ይግባኝ አቀራረብ

    እና በቫት ተመላሽ አከፋፈል ያሉ ችግሮች ዙሪያ የሚመክር ዓውደ

    ጥናት የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት በደሳለኝ ሆቴል ተካሄደ፡፡

    የግብር ይግባኝ ሥርዓቱ ያሉበት ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች

    እንዲሁም በቫት ተመላሽ አከፋፈል የሚስተዋሉ ችግሮች በሚሉ

    ርዕሶች ዙሪያ የዳሰሳ ጥናቶች ቀርበው ተሳታፊዎች በሰፊው

    የተወያዩበት ሲሆን በውይይቱ የተነሱትን ገንቢ ሃሳቦች

    በማካተት ጥናቶቹ በቀጣይ በሚካሄደው የመንግስትና የግሉ

    ዘርፍ የምክክር መድረክ እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡ የጥናቱ

    አቅራቢዎች እንደተናገሩት የታክስ ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴው

    የስልጣን ወሰን ከታክስ ውሳኔ ጋር ብቻ በመያያዙ ሌሎች የህግ

    ጉዳዮች ሲነሱ ኮሚቴው እነዚህን ጉዳዮች ለማየትና የውሳኔ

    ሀሳብ ለማቅረብ አለመቻሉ በጣም የተወሳሰቡ የታክስ ጉዳዮች

    በአጣሪ ኮሚቴው እንዳይታዩና መፍትሄ እንዳያገኙ በማድረግ

    በታክስ ከፋዮች ላይ መጉላላትን ፈጥሯል ብለዋል፡፡ ይህም

    ችግር የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተጨማሪ

    ቴክኒካል ኮሚቴ የሚባልና ምንም ዓይነት የህግ መሠረት

    የሌለው አካል እንዲቋቋም አስገድዶታል፡፡ ይህም አካሄድ የህግ

    የበላይነትን የሚፃረር ይሆናል ብለዋል፡፡

    በተጨማሪም በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የግብር ውሳኔ

    ቅር የተሰኘ ግብር ከፋይ ቅሬታውን ለአጣሪ ኮሚቴው ማቅረብ

    የሚችለው የግብር ውሳኔው በደረሰው በ10 ቀናት ውስጥ

    ተብሎ በህግ መደንገጉና በተግባርም መተርጎሙ የተለያዩ

    ችግሮችን እያስከተለ መሆኑን የተናገሩት የጥናት አቅራቢዎቹ

    ይህም ቀኑ በጣም አጭር በመሆኑ ግብር ከፋዩ ቅሬታውን

    በአግባቡ እንዳያቀርብ እንደሚያሰናክለውና ይህም ችግር

    የግብር ከፋዩን ቅሬታ የማቅረብና የመሰማት መብት በእጅጉ

    እየጎዳ እንደሆነ ተገልፃል፡፡

  • በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ

    በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.74 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

    Communication and International Relations Department Bi-monthly News Letter No.74

    አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

    ኢ.ሜይል: [email protected]

    ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

    ገጽ-3

    የካቲት 15 ቀን 2006ዓ.ም.

    በዚህም ምክንያት ግብር ከፋዩ በታክስ ሥርዓቱ ላይ ቅሬታ

    እንዲያድርበትና አመኔታ እንዳይኖረው ከማድረጉም በተጨማሪ

    በታክስ አስገቢው ባለሥልጣንና በግብር ከፋዮች መካከል መልካም

    ግንኙነት እንዳይኖር አድርጎታል ብለዋል፡፡

    በቀረቡት ጥናቶች ዙሪያ ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት ያደረጉ

    ሲሆን በታክስ አስገቢው ባለሥልጣናትና በታክስ ከፋዮች

    መካከል የሚነሱት አለመግባባቶች እጅግ ዘርፈ ብዙ

    በመሆናቸው አጣሪ ኮሚቴው ማናቸውንም የታክስ ከፋዮች

    ቅሬታዎችን ለማየትና የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ ይቻላል የሚል

    የህግ ድንጋጌ በታክስ ህጎቻችን ውስጥ በግልፅ መደንገግ

    ያስፈልጋል የሚል ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ የግብር ይግባኝ ጉባዔ

    አባላት የሚመረጡበት ዝርዝር መስፈርቶችን የያዘ መመሪያ

    አለመውጣቱ የታክስህጉ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ያነገበው

    ዓላማ በትክክል ሥራ ላይ እንዳይውል አድርጓል ይህም ሁኔታ

    የግብር ጉባኤ አባላትን አመራረጥና ስብጥር የንግዱ

    ማህበረሰብ በጥርጣሬ እንዲመለከተው አድርጓል ተብሏል፡፡

    በማናቸውም የታክስ ክርክር ጉዳይ የማስረዳት ሸክም ሙሉ

    በሙሉ በታክስ ከፋዩ ላይ እንዲያርፍ መደረጉ ምንም እንካን

    በመርህ ደረጃ ትክክል ቢሆንም በልዩ ሁኔታ ግን በግብር

    አስገቢው ባለሥልጣንም ላይ የሚያርፍበት ሁኔታ እንዲፈጠር

    ህጎቹ በማሻሻል በዚህ ረገድ ግልፅ ድንጋጌዎች ማካተቱ

    አስፈላጊ እንደሆነ ተሳታፊዎቹ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

    የጣሊያን የንግድ ልዑካን ቡድን ከምክር

    ቤቱ አመራሮች ጋር ተወያየ

    የጣሊያን የንግድ ልዑካን ቡድን እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ

    ማኅበራት ምክር ቤት አመራሮች በሁለቱም ሃገራት ስላለው

    የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሁኔታና ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉት

    ሠፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ላይ ተወያዩ፡፡

    በቀረቡት ጥናቶች ዙሪያ ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት ያደረጉ

    ሲሆን በታክስ አስገቢው ባለሥልጣናትና በታክስ ከፋዮች መካከል

    የሚነሱት አለመግባባቶች እጅግ ዘርፈ ብዙ በመሆናቸው አጣሪ

    ኮሚቴው ማናቸውንም የታክስ ከፋዮች ቅሬታዎችን ለማየትና

    የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ ይቻላል የሚል የህግ ድንጋጌ በታክስ

    ህጎቻችን ውስጥ በግልፅ መደንገግ ያስፈልጋል የሚል ሃሳብ

    አቅርበዋል፡፡

    የግብር ይግባኝ ጉባዔ አባላት የሚመረጡበት ዝርዝር መስፈርቶችን

    የያዘ መመሪያ አለመውጣቱ የታክስህጉ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ

    ያነገበው ዓላማ በትክክል ሥራ ላይ እንዳይውል አድርጓል ይህም

    ሁኔታ የግብር ጉባኤ አባላትን አመራረጥና ስብጥር የንግዱ

    ማህበረሰብ በጥርጣሬ እንዲመለከተው አድርጓል ተብሏል፡፡

    በማናቸውም የታክስ ክርክር ጉዳይ የማስረዳት ሸክም ሙሉ በሙሉ

    በታክስ ከፋዩ ላይ እንዲያርፍ መደረጉ ምንም እንካን በመርህ ደረጃ

    ትክክል ቢሆንም በልዩ ሁኔታ ግን በግብር አስገቢው ባለሥልጣንም

    ላይ የሚያርፍበት ሁኔታ እንዲፈጠር ህጎቹ በማሻሻል በዚህ ረገድ

    ግልፅ ድንጋጌዎች ማካተቱ አስፈላጊ እንደሆነ ተሳታፊዎቹ ሃሳብ

    ሰጥተዋል፡፡

  • በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ

    በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.74 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

    Communication and International Relations Department Bi-monthly News Letter No.74

    አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

    ኢ.ሜይል: [email protected]

    ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

    ገጽ-3

    የካቲት 15 ቀን 2006ዓ.ም.

    የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ

    ሙሉ ሰሎሞን እንደተናገሩት በኢትዮጵያ እና ጣሊያን የነበረው የቆየ

    ታሪካዊ ትስስር አሁን ላለው ግንኙነት ጽኑ መሰረት ጥሏል፡፡

    በተጨማሪም ይህ ታሪካዊ ግንኙነት በሁለቱም ሃገራት ሕዝቦች

    መካከል ለተፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ትስስር ዓይነተኛ ምክንያት

    መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቷ በተለይ ብዙ የጣሊያን ኩባንያዎች

    ከኢትዮጵያ ባለሃብቶች ጋር እየሠሩ እንደሆነና ኢትዮጵያ ውስጥ

    በአስመጪ እና ላኪነት፣ በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች

    እንዲሁም በእርሻ ሥራ አብረው እንዲሠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡

    ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ምቹ

    የኢኮኖሚ ለውጥ እና እየዳበረ የመጣው የሁለቱ ሃገራት

    ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የኢኮኖሚ ትስስሩ ይበልጥ እንዲጎለብት እና

    የጣሊያን ባለሃብቶች በአዳዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለምሳሌ

    በመሠረተ-ልማት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል

    ማመንጫ ግድቦች እንዲሁም አግሮ-ኢንዱስትሪ ሥራ ላይ

    እንዲሠማሩ ዕድል መክፈቱን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በሁለቱም

    ሃገራት ያለው የንግድ እና ኢንቨስትመንት ልውውጥ ከዓመት ዓመት

    እየጨመረ መጥቷል፡፡ በ2004 እ.ኤ.አ በሁለቱም ሃገራት የነበረው

    ጠቅላላ የንግድ መጠን 171 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን በ2011 እ.ኤ.አ ወደ

    391 ሚሊዮን ዶላር አድጓል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ ወደ

    ጣሊያን ከላከቻቸው ምርቶች 109 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ስታገኝ

    282 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ምርት ከጣሊያን

    አስገብታልች፡፡ በሁለቱም ሃገራት ያለው የንግድ ሚዛን ልዩነት ሠፊ

    የሚባል ነው ያሉት ወ/ሮ ሙሉ የንግድ ሚዛኑን ለማጥበብ ሁለቱም

    ወገኖች ተባብርው መስራት እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡

    የሁለትዮሽ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ከማሣደግ አንፃር የንግድ

    ማህበረሰቡ ሚና የማይተካ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ የኢንዘማም እና

    ጠቅላላ የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት የሁለቱን ሃገራት

    የንግድ ማህበረሰብ ጥቅም ለማስጠበቅ ከጎናቸው እንደሚቆሙ

    ገልፀውላቸዋል፡፡

    ፎቶ ዜና