4
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት .108 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Corporate Communication and Public Relations Directorate Bi-monthly News Letter No.108 ገጽ ህዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም. 8ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት አጭር ቅኝት .ከ 150 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጪ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምርት እና አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ለኢንድስትሪ ልማት ዕድገት እና ለንግድ ስራ መስፋፋት ላቅ ያለ ሚና ያለውን 8ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያን ይግዙ በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 25-29 ቀን 2008ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ 150 የአገር ውስጥ እና ከሳውዲ አረቢያ፣ ከቱርክ እና ከሶማሊላንድን የመጡ ኩባንያዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የውጪ ኩባንያዎች የሚተሳተፉበት ለአገራችን የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች የልማት ዘርፎች ዕድገት ጠቃሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች የቀረቡበት ሲሆን በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ዘርፉን ከምርምር እና ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የጎላ ሚና ተጫውቷል፡፡ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ዕውቅና ያገኙ የኢትዮጵያውያን ምርጥ የፈጠራ ስራዎች እና የንግድ ጽንሰ ሀሳቦች የቀረቡበት ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 8ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ለተሳታፊዎች የገበያ ትስስር፣ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጥምራት እና በአገር ውስጥ እና በውጪ አምራቾች / አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መካከል አድራሻ ፋክስ: - +251-011-5517699 ኢ.ሜይል: [email protected] ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ዓላማውን አሳክቷል፡፡ በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የንግድ ሚንስትሩ አቶ ያዕቆብ ያላ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድ ሚንስቴር ጋር በመተባበር አመቺ የንግድ ስርዓትን ለመዘርጋት በንግድ ስርዓቱ ውስጥ እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን ለማስወገድ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮችን በጋራ በማዘጋጀት በርካታ ተግባራትን ማከናወን ችለዋል በመሆኑም በቅርቡ በዴንማርክ ኮፐን ሀገን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ጉባኤ ከ54 ሀገሮች ጋር በመወዳደር ሀገራችን አንደኛ በመውጣት የክብር ተሸላሚ ሆናለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ በበኩላቸው ምክር ቤታችን ንግድና ኢንቨስትመንትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ከሚጠቀምባቸው ተግባራት አንዱ የሆነው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ለአገራችን የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች የልማት ዘርፎች ዕድገት ጠቃሚ የሆኑ የልምድ ልውውጦች የሚከናወኑበት የሀገራችን ምርቶች የእድገት ደረጃ ለመላው ዓለም የሚቀርብበት መድረክ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠውና በየዓመቱ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡ ለአምስት ቀናት ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ጎብኚዎች ሲጎበኝ የነበረው የንግድ ትርዒቱ ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ethiopian, Chamber - Bi-monthly News Letter No.108 ኛው …ethiopianchamber.com/Data/Sites/1/e-newsletter/eccsa-108.pdfEthiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Corporate

  • Upload
    others

  • View
    5

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: Ethiopian, Chamber - Bi-monthly News Letter No.108 ኛው …ethiopianchamber.com/Data/Sites/1/e-newsletter/eccsa-108.pdfEthiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Corporate

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.108 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Corporate Communication and Public Relations Directorate Bi-monthly News Letter No.108

ገጽ

ህዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም.

8ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ

ትርዒት አጭር ቅኝት

.ከ 150 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጪ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል

የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምርት እና

አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ለኢንድስትሪ ልማት ዕድገት እና ለንግድ

ስራ መስፋፋት ላቅ ያለ ሚና ያለውን 8ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም

አቀፍ የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያን ይግዙ በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት

25-29 ቀን 2008ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል

ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

150 የአገር ውስጥ እና ከሳውዲ አረቢያ፣ ከቱርክ እና ከሶማሊላንድን

የመጡ ኩባንያዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የውጪ ኩባንያዎች

የሚተሳተፉበት ለአገራችን የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች የልማት ዘርፎች

ዕድገት ጠቃሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች የቀረቡበት ሲሆን በተጨማሪም

የኢንዱስትሪ ዘርፉን ከምርምር እና ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የጎላ ሚና

ተጫውቷል፡፡ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ዕውቅና ያገኙ

የኢትዮጵያውያን ምርጥ የፈጠራ ስራዎች እና የንግድ ጽንሰ ሀሳቦች

የቀረቡበት ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 8ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት

ለተሳታፊዎች የገበያ ትስስር፣ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጥምራት እና በአገር

ውስጥ እና በውጪ አምራቾች / አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መካከል

አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

ኢ.ሜይል: [email protected]

ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ዓላማውን

አሳክቷል፡፡

በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት

የንግድ ሚንስትሩ አቶ ያዕቆብ ያላ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ

የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድ ሚንስቴር ጋር

በመተባበር አመቺ የንግድ ስርዓትን ለመዘርጋት በንግድ ስርዓቱ

ውስጥ እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን ለማስወገድ የመንግስትና

የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮችን በጋራ በማዘጋጀት በርካታ

ተግባራትን ማከናወን ችለዋል ፤ በመሆኑም በቅርቡ

በዴንማርክ ኮፐን ሀገን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ

የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ጉባኤ ከ54 ሀገሮች

ጋር በመወዳደር ሀገራችን አንደኛ በመውጣት የክብር ተሸላሚ

ሆናለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ በበኩላቸው ምክር ቤታችን ንግድና

ኢንቨስትመንትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ከሚጠቀምባቸው

ተግባራት አንዱ የሆነው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ

ትርዒት ለአገራችን የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች የልማት

ዘርፎች ዕድገት ጠቃሚ የሆኑ የልምድ ልውውጦች

የሚከናወኑበት የሀገራችን ምርቶች የእድገት ደረጃ ለመላው

ዓለም የሚቀርብበት መድረክ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት

የሚሰጠውና በየዓመቱ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡

ለአምስት ቀናት ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ጎብኚዎች ሲጎበኝ

የነበረው የንግድ ትርዒቱ ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

Page 2: Ethiopian, Chamber - Bi-monthly News Letter No.108 ኛው …ethiopianchamber.com/Data/Sites/1/e-newsletter/eccsa-108.pdfEthiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Corporate

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.108 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Corporate Communication and Public Relations Directorate Bi-monthly News Letter No.108

ገጽ

ህዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም.

በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡

በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይ የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ

አቶ ታደሰ ሐይሌ የክብር እንግዳ በመሆን የተገኙ ሲሆን የንግድ

ትርዒቱ መዘጋጀት ለሀገራችን የኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት

የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ የሚያጎላ ንግግር አድርገዋል፡፡

በእለቱ በአቀራረባቸው ላቅ ያለ ዝግጅት በማድረጋቸው አሠናፊ የሆኑ

የኤግዚብሽኑ ተሳታፊዎችና እንዲሁም የንግድ ትርዒቱን ስፖንሰር

ያደረጉ ድርጅቶች ተሸልመዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከ

140ሚሊዮን ብር በላይ የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት

ተፈራረመ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከስዊድን ዓለም

አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ(SIDA) ጋር ለአምስት ዓመታት

የሚቆይ ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ የፕሮጀክት ፋይናንስ ድጋፍ

ስምምነት ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ተፈራረመ፡፡

በሒልተን ሆቴል በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ እንደተገለፀው

የተገኘው ይህ በምክር ቤቱ ዘላቂ የአቅም ግንባታ ላይ ያተኮረው

የፕሮጀክት ፋይናንስ ድጋፍም የአቅም ግንባታ፣ የጥናት እና

የአድቮኬሲ ዋና ዋና ተግባራት ማስፈጸሚያነት የሚውል ይሆናል፡፡

ይህ የዘላቂ አቅም ግንባታ የፕሮጀክት ድጋፍ ዋንኛ አላማም ለግሉ

ዘርፍ እድገት ምቹ የሆነ የንግድ ስራ ከባቢን በመፍጠር ለአገሪቱ

የኢኮኖሚ ልማት ገንቢ አስተዋጽኦ ማበርከት ሲሆን

አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

ኢ.ሜይል: [email protected]

ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

ውጤታማ የሆነ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የውይይት

መድረኮችን ማዘጋጀት የሚያስችሉ ጥናቶችን በማካሄድ እና

ለመንግስት በማቅረብ ለንግድ እና ኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑ

የህግ እና የፖሊሲ ለውጦችን በማምጣት ውጤታማ እና ሁሉን

አቀፍ የምጣኔ ሃብት ዕድገት እንዲፈጠር ማስቻል ነው፡፡

በግሉ ዘርፍ ማበልጸጊያ ማዕከል(PSD Hub) ሶስተኛ

ምዕራፍ ማስፈጸሚያ የሚውለውን እና በዚህም የምክር ቤቱን

አባላት ብሎም መላውን የንግዱን ህብረተሰብ ተጠቃሚ

የሚያደርገውን ይህን ስምምነት የተፈራረሙት ከምክር ቤቱ

በኩል የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ሲሆኑ

ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ(SIDA)

በኩልም በኢትዮጵያ የስዊድን ኤምበሲ ሚኒስትር ኮንሱለር

ሚ/ር አኒካ ከኑትሰን ናቸው፡፡

የስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ(SIDA)

ለግሉ ዘርፍ ማበልጸጊያ ማዕከል(PSD Hub) አማካኝነት

የሚሰጠው የፕሮጀክት የፋይናንስ ድጋፍ እ.ኤ.አ ከ 2005

ጀምሮ መተግበር የጀመረ ነው፡፡

ከእለቱ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሀን የተወጣጡ ጋዜጠኞች ስነ

ስርዓቱን የተከታተሉ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው

ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Page 3: Ethiopian, Chamber - Bi-monthly News Letter No.108 ኛው …ethiopianchamber.com/Data/Sites/1/e-newsletter/eccsa-108.pdfEthiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Corporate

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.108 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Corporate Communication and Public Relations Directorate Bi-monthly News Letter No.108

ገጽ

ህዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም.

ከፍተኛ የፖላንድ የንግድ ልዑካን አዲስ አበባ

ሊገባ ነው

ከፍተኛ የፖላንድ የንግድ ልዑካን ህዳር 10 ቀን 2008ዓ.ም. ወደ

ኢትዮጵያ በመምጣት ከኢትዮጵያ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር የአቻ ለአቻ

ውይይት እንደሚያደርጉ በኢትዮጵያ የፖላንድ ሪፐብሊክ አምባሳደር

ሚስተር ጃሴክ ጃንኮውስኪ ገለፁ፡፡

አምባሳደሩ ይህንን የተናገሩት ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ

የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት

አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ጋር ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

እንደ አምባሳደሩ ገለፃ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት የፖላንድ ባለሀብቶች

በኢነርጂ፣ በአግሪካልቸር፣ በማሽነሪ ምርት፣ በፋርማሴውቲካል፣

በኬሚካልና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ዓለም አቀፍ

ኩባንያዎች ናቸው፡፡

ህዳር 10 ቀን በሸራተን ሆቴል እንደሚካሄድ የተገለፀው የሁለቱ ሀገራት

የአቻ ለአቻ ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና

ዳይሬክተር አቶ ፍፁም አረጋ እና የፖላንዱ አቻቸው መድረኩን

እንደሚመሩት ከወዲሁ የተያዘው ጊዜያዊ ፕሮግራም ያመለክታል፡፡

በዚህ አጋጣሚ በፕሮግራሙ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ የሀገራችን

ኩባንያዎች የምክር ቤቱን የንግድ ማስተዋወቅ መምሪያን በማነጋገር

መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በምክር ቤቱ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ

ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ይገልፃል፡፡

አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

ኢ.ሜይል: [email protected]

ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

8ኛው የኢትዮ-ቻምበር የንግድ ትርዒት የመክፈቻ ፕሮግራም

Page 4: Ethiopian, Chamber - Bi-monthly News Letter No.108 ኛው …ethiopianchamber.com/Data/Sites/1/e-newsletter/eccsa-108.pdfEthiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Corporate

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

በየ15 ቀኑ የሚዘጋጅ ዜና-መጽሔት ቁ.108 Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Corporate Communication and Public Relations Directorate Bi-monthly News Letter No.108

ገጽ

ህዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም.

8ኛው የኢትዮ-ቻምበር የንግድ ትርዒት የመዝጊያ ፕሮግራም

አድራሻፋክስ: - +251-011-5517699

ኢ.ሜይል: [email protected]

ደረ-ገጽ፡- www.ethiopianchamber.com

ምክር ቤቱ ከሲዳ (SIDA) ጋር ደረገው የ140 ሚሊዮን ብር ስምምነት