27
1 ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል መተዳደሪያ ደንብ ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል መተዳደሪያ ደንብ ሰኔ ወር ፳፻፯ ዓም የቤተ ክርስቲያን አድራሻ: 4907 S. Main Street, Los Angeles, CA. 90037 ስልክ ቁጥር - የጽሕፈት ቤት - (323)234-5828 የካህናት - (323)232-7151 ድረ ገጽ (Website) - www.EthioVirginMary.org Email: [email protected]

መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

  • Upload
    others

  • View
    164

  • Download
    1

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

1

ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋሕዶ ካቴድራል

መተዳደሪያ ደንብ

ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋሕዶ ካቴድራል መተዳደሪያ ደንብ

ሰኔ ወር ፳፻፯ ዓም

የቤተ ክርስቲያን አድራሻ: 4907 S. Main Street, Los Angeles, CA. 90037

ስልክ ቁጥር - የጽሕፈት ቤት - (323)234-5828 የካህናት - (323)232-7151

ድረ ገጽ (Website) - www.EthioVirginMary.org Email: [email protected]

Page 2: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

2

ማውጫ

አንቀጽ ፩ (1) የመጠሪያ ስም እና የዋናው ጽህፈት ቤት

አንቀጽ ፪ (2) ዋና ዓላማ

አንቀጽ ፫ (3) አጠቃላይ ድንጋጌ

አንቀጽ ፬ (4) መግለጫ

አንቀጽ ፭ (5) አባልነት

አንቀጽ ፮ (6) የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ

አንቀጽ ፯ (7) ምርጫዎች

አንቀጽ ፰ (8) የቦርድ አባላት

አንቀጽ ፱ (9) የሂሳብ መርማሪዎች

አንቀጽ ፲ (10) ካህናት

አንቀጽ ፲፩ (11) የቤተክርስቲያን አዛውንት

አንቀጽ ፲፪ (12) ኮሚቴዎች

አንቀጽ ፲፫ (13) የቤተክርስቲያን ንብረቶች

አንቀጽ ፲፬ (14) ሥነሥርዓት (ዲሲፕሊን)

አንቀጽ ፲፭ (15) መዛግብትና ዘገባዎች

አንቀጽ ፲፮ (16) ልዩ ልዩ ጉዳዮች

ማሻሻያ የተፈረመ መዝገብ

Page 3: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

3

አንቀጽ 1.0

የመጠሪያ ስምና ዋና ጽሕፈት ቤት

1.1 ቤተክርስቲያኗ ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል ተብላ ትጠራለች።

1.2 የድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል ዋና ጽሕፈት ቤት በ4907 ሳውዝ

ሜይን መንገድ ላይ በሎስ አንጀለስ ከተማ ካሊፎርኒያ 90037 ይሆናል።

አንቀጽ 2.0

ዋና ዓላማ

2.1 የቤተክርስቲያኗ ዋና ዓላማ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች የአምልኮት አገልግሎቶች መስጠት ነው። በዚሁም መሠረት ቤተክርስቲያኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዕምነት፥ ሕግጋትና ሥርዓት፥ የባህልና፥ የትምህርት አገልግሎት ትሰጣለች።

አንቀጽ 3.0

አጠቃላይ ድንጋጌ

3.1 ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሎስ አንጀለስ ከተማ የካሊፎርኒያ

ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ለመንፈሳዊ አገልግሎት የተቋቋመች የሃይማኖት (Spiritual Unit) ድርጅት ናት። ከዚህ በኋላ በዚህ ሰነድ ውስጥ ካቴድራሏ ቤተክርስቲያን ተብላ ልትጠራ ትችላለች።

3.2 የቤተክርስቲያኗ አወቃቀርም ሆነ አስተዳደር የዩናይትድ ስቴትስ አገር ውስጥ ገቢ ደንብ (United

States Internal Revenue Code) የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይንም አትራፊ ያልሆኑ አክስዮን

ማሕበራትን አሠራር በሚመለከት ባወጣው ህግ ክፍል 501 (C) (3) መሠረት ይሆናል። ቤተክርስቲያኗ ለትርፍ በሚደረጉ ሥራዎች ሆነ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አትገባም።

3.3 የቤተክርስቲያኗ ተመራጮች በማንኛውም ሁኔታ ደሞዝ ወይንም ሌሎች የገንዘብ ክፍያዎች አያገኙም። የገንዘብ ክፍያ የሚደረገው ግለሰቡ የቤተክርስቲያኗን ጉዳይ በማስፈጸም ረገድ ላዋለው ወጪ ብቻ ይሆናል።

3.4 ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ቁጥራቸው ሁለት ሶስተኛ (2/3) በሚሆን የቤተክርስቲያኗ አባላት ከፀደቀ የቤተክርስቲያኗ የአስተዳደር እና የኣሠራር ሥርዓት ቋሚና ዋና መመሪያ ይኖናል። የቤተክርስቲያኗ አባላት በሙሉ ይህንን መተዳደሪያ ደንብና ወደፊትም ሊጨመሩ የሚችሉ ማሻሻያዎችን ማክበርና መመሪያ ማድረግ አለባቸው።

Page 4: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

4

3.5 ማንኛውም የቦርድ አባል ወይንም የኮሚቴ ተመራጭ በተናጠልም ሆነ በጋራ የቤተክርስቲያኗ የአባላት ጉባዔ ሳይፈቅድና ሳይስማማ መተዳደሪያ ደንቡን የመለወጥ የመተርጎም ወይንም የማሻሻል ሥልጣን አይኖረውም። ደንቡን በሚመለከት የትርጉም አለመግባባት ቢፈጠር የቦርዱ ሊቀመንበር ለጠቅላላ ጉባዔው ማቅረብና ውሳኔ ማስገኘት አለበት።

3.6 ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና እንዲሁም አባሎችዋ ቤተክርስቲያኗን ወክለው በማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አይገቡም። ለመንግሥት

(ለፖለቲካ) ሥልጣን በእጩነት ለሚወዳደሩ ድጋፍ አይሰጡም። የቤተክርስቲያኗ ገንዘብም ሆነ ሌሎች ንብረቶች ለማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ አይውሉም።

==================================================

አንቀጽ 4.0

መግለጫ

4.1 ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ አካል እንደመሆኗ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ሕግጋትን፥ ስነ ርዓትን፥ የአምልኮና የባህል ሥርዓቶችና አገልጎሎቶችን ሙሉ በሙሉ ትከተላለች። ቤተክርስቲያኗ የሃይማኖት አገልግሎቷን በግዕዝና ባማርኛ ቋንቋዎች ታካሂዳለች። አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለትምህርት አሰጣጥ መጠቀሚያ ሊሆን ይችላል።

4.2 ክርስትና ሃይማኖት ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ልምድ የሚመነጨው መጽሐፍ ቅዱስንና የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት በመከተል ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በክርስቲያኑ ዓለም

ከሚገኙ ጥንታዊ አብያተክርስቲያናት አንዷ ናት። በመሆኑም በሶርያ፥ በእስክንድርያ (ግብፅ)፥ በአርመን፥በሕንድ ከሚገኙ የኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ጋር እህታዊ ግንኙነት አላት።

4.3 ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገንዘብን እና አስተዳደርን በሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላትም።

4.4 ቤተክርስቲያኗ የአስተዳደርና የገንዘብ ነክ ጉዳዮችን የምታካሂደው በዚህ መተዳደሪያ ደንብ በተደነገገውና በተወሰነው መሠረት ብቻ ነው።

================================

Page 5: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

5

አንቀጽ 5

አባልነት

5.1 አባል፥ ማንኛውም ግለሰብ ለአባልነት ብቁ ለመሆን የሚከተሉትን ሟሟላት ይጠበቅበታል።

5.1.1 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን፥ የአምልኮ ሥነሥርዓትና ሕግጋትን ሁሉ የሚያምንና የተቀበለ

5.1.2 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተጠቀሱትን ደንቦች የተቀበለ እና የሚያከብር

5.1.3 በአባልነት ቅጽ ተመዝግቦ በአባላት መዝገብ ውስጥ ስሙ በአግባቡ የተመዘገበ

5.2 ተሳትፎ፥

አባላት ቤተክርስቲያኗ በምታደርጋቸው ዝግጅቶች ላይ በሚችሉት መስክ መሳተፍና ማገልገል ይጠበቅባቸዋል። ብቁ የሆኑ አባላት ለአገልግሎት ሥራ ለምርጫ የመወዳደርና የመመረጥ መብት አላቸው።

5.3 በፈቃደኝነት ኃላፊነትን መልቀቅ፦

ማንኛውም ግለሰብ ለሥራ አመራር ቦርዱ በቃል ወይንም በጽሁፍ በማስታወቅ ከአባልነት ራሱን ሊያገል ይችላል። ቦርዱ አስፈላጊ መስሎ ካገኘው አባሉ ራሱን ያገለለበትን ምክንያት በመመርመር አስፈላጊና ጠቃሚ መስሎ የታየውን እርምጃ ይወስዳል።

5.4 ከአባልነት መወገድ፦ አንድ አባል በመተዳደሪያ ደንቡ የተዘረዘሩትን ደንቦችና የቤተክርስቲያን ደንብና ሥነ ሥርዓትን ካጓደለ ወይንም ከጣሰ ከአባልነት ሊወገድ ይችላል።

5.5 ወደ አባልነት መመለስ፦

በፈቃዱ የለቀቀ ወይንም ከአባልነት የተወገደ አንድ ግለሰብ ወደ አባልነት ለመመለስ ከፈለገ ይህንኑ በጽሁፍ ለቦርድ ሊያቀርብ ይችላል። ቦርዱ የግለሰቡን ማመልከቻ ከመረመረ በኋላ ተገቢውን ውሳኔ ያደርጋል።

5.6 የአባልነት ክፍያ፦

5.6.1 ገንዘብ ክፍያ፥

የአባልነት የገንዘብ ክፍያ መጠን ቦርዱ በሚወስነውና ጠቅላላ ጉባዔው በሚያፀድቀው መሠረት ይሆናል። ወርሃዊ ክፍያውን ለአራት ተከታታይ ወራት ላላሟላ ግለሰብ ከቦርዱ ማሳሰቢያ ይሰጣል። ቦርዱ ልዩ አስተያየት ካላደረገ በስተቀር ለስድስት ተከታታይ ወራት ወርሃዊ ክፍያ ላላሟላ ግለሰብ ድምፅ የመስጠት መብቱ ይታገዳል። እንዲሁም ለአስራ ሁለት ወራት ወርሃዊ ክፍያውን ያላሟላ አባል ከቤተክርስቲያኗ አባልነት ይሠረዛል።

Page 6: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

6

5.6.2 ቃል መግባት፦

አንድ አባል በራሱ ፈቃድ የገባበትን የገንዘብ አስተዋፅዎ ክፍያ ጊዜውን ጠብቆ መስጠት ይጠበቅበታል።

5.7 ከክፍያ ነፃ መሆን ከችግር የተነሳ፦

አንድ አባል ወርሃዊ ክፍያ ማድረግ ካቃተው ቦርዱ ጉዳዩን አጥንቶ ከአንድ ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የአባልነት ወርሃዊ ክፍያ እንዳያደርግ ልዩ አስተያየት ሊያደርግለት ይችላል።

5.8 የክብር አባልነት፦

በቦርዱ አቅራቢነት በጠቅላላ ጉባኤው አፅዳቂነት ለቤተክርስቲያኗ ደህንነት ዕድገት እጅግ ልዩና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገ ግለሰብ የክብር አባልነት ይሰጠዋል።

5.9 መታወቂያ፦ እያንዳንዱ አባል የቤተክርስቲያኗ የአባልነት መታወቂያ ወረቀት ይኖረዋል።

5.10 ድምፅ የመስጠት መብት፦

ማንኛውም አባል በማንኛውም ስብሰባ ላይ ድምፅ የመስጠት መብት አለው። ድምፅ ለመስጠት

ማንኛውም አባል እድሜው 18 ዓመት የሞላና ቢያንስ ለ6 ወራት የቤተክርስቲያኗ አባል ሆኖ መገኘት አለበት።

====================================

አንቀጽ 6.0

የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ

6.1 ትርጉም፦ የአባላት ጠቅላላ ስብሰባ ማለት በአንቀፅ 5.1 በተጠቀሰው መሠረት የተመዘገቡት አባላት ቤተክርስቲያኗን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለመምከርና ለመወሰን የሚሰበሰበው አካል ነው።

6.2 መመሪያዎች፦ የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መመሪያዎች መሠረት ይካሄዳል።

6.2.1 የስብሰባ ጥሪና አጀንዳ ፦ ማንኛውም ስብሰባ ከመደረጉ ከሁለት ሳምንታት በፊት የስብሰባ ጥሪ መደረግ አለበት። የስብሰባ ጥሪና አጀንዳ ለአባላት በሚከተሉት መንገዶች፣ ቢያንስ በአንዱ መገለፅ አለበት።

6.2.1.1 በደብዳቤ ፣

6.2.1.2 በቦርድ አባላት ወይንም በካህኑ አማካይነት ቤተክርሲቲያኗ ውስጥ በሚተላላፍ የቃል ማስታወቂያ ፣

6.2.1.3 በቤተክርስቲያኗ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚደረግ የጽሑፍ ማስታወቂያ

6.2.2 ቦታ ፦ የስብሰባው ቦታ በቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ወይንም በሌላ አማካይ ቦታ ሊሆን ይችላል።

6.2.3 የተካፋዮች መዝገብ፦ ለስብሰባ የሚገኙ አባላት በሙሉ ስማቸውን መዝገብ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

Page 7: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

7

6.2.4 ምልዓተ ጉባኤ ፦ ቁጥራቸው ከግማሽ በላይ (50 %+1) አባላት ከተገኙ አብዛኛው ተሰብሳቢ

እንደተገኘ ይቆጠራል። በመጀመሪያው ስብሰባ ምልዓተ ጉባኤው ካልሞላ ሁለተኛ ስብሰባ በሁለት ሳምንት

ጊዜ ውስጥ ይጠራል። በሁለተኛው ስብሰባ ከተገኙት አባላት አብዛኛው በተቃውሞ ካልወሰኑ በስተቀር

የተገኙት አባላት ምልዓተ ጉባኤውን እንዳሟሉ ይቆጠራል።

6.2.5 ድምፅ አሰጣጥ፦

6.2.5.1 ይህ መተዳደሪያ ደንብ በሌሎች አንቀጾች ከተገለጸው በስተቀር ሁሉም የስብሰባ ውሳኔዎች ሕጋዊም ሆነ ተግባራዊ የሚሆኑት ከተገኙት አባላት አብዛኛዎቹ ሲስማሙባቸው ነው። በማንኛውም ስብሰባ ድምፅ ያልሰጡ አባላት ብዛት መመዝገብ አለበት።

6.2.5.2 የስብሰባው ሊቀመንበር እጅ በማውጣት ድምፅ መስጠት በቂ መስሎ እስካላገኘውና ለዚሁም ተቃውሞ እስካልቀረበ ድረስ የድምፅ አሰጣጡ ሥነሥርዓት ምስጢራዊ ይሆናል። የምርጫው ውጤት በስብሰባው ሊቀመንበር ይገለጻል።

6.2.5.3 ማንኛውም አባል በአገልግሎት ላይ የሚገኙትን ጨምሮ አንድ የድምፅ ምርጫ ይኖረዋል።

6.2.6 ቃለ ጉባዔ፦ ለማንኛውም ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መያዝ አለበት። በስብሰባ የተገኙ አባላት ዝርዝር ከቃለ ጉባኤው ጋር ተጣምሮ መቀመጥ አለበት።

6.3 የስብሰባዎች ሥነ ሥርዓት

6.3.1 ማንኛውም ስብስባ የሚካሄደው ይህ መተዳደሪያ ደንብ በሚገልፀውና በሚፈቅደው መሠረት ይሆናል። የስብሰባዎች ሂደት የተለመደውን የፓርላማ ደንብና ሥርዓት የተከተለና የጠበቀ ይሆናል።

6.3.2 ስብሰባዎች የሚካሄዱት በስብሰባው ሊቀመንበር መሪነት ነው።

6.3.3 ማንኛውም ስብሰባ በአጀንዳ መሠረት ይካሄዳል። የስብሰባው ሊቀመንበር የአጀንዳውን ነጥቦች ያስተዋውቃል። አዲስ የአጀንዳ ነጥቦችን በዕለቱ አጀንዳ ላይ ለመጨመር አስተያየት ሊደረግ ይቻላል።

6.3.4 የስብሰባ ቃለ ጉባኤ በተመደበው ግለሰብ ይመዘገባል። ያለፈው ቃለ ጉባኤ ዘገባ በዕለቱ ስብሰባ በቅድሚያ ይነበባል።

6.3.5 የሊቀመንበሩ ኃላፊነትና ተግባር የሚከተሉት ናቸው።

6.3.5.1 ስብሰባው መጀመሩን ማስታወቅ

6.3.5.2 ስብሰባውን በሥነ ሥርዓትና ባጀንዳው መሠረት ማካሄድ

6.3.5.3 የምርጫ ውጤትን ማስታወቅ

6.3.5.4 ሁኔታዎች ሲያስገድዱ ስብሰባውን ለጊዜው እንዲቆም ወይም እንዲተላለፍ ማድረግ።

6.3.5.5 የዕለቱን ስብሰባ ማቆም

Page 8: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

8

6.4 ዓመታዊ ስብሰባ

6.4.1 የዓመታዊ ስብሰባ ዋና ዓላማ በበጀት ዓመቱ በተደረጉት አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች፥ የሥራ ውጤቶችና ክንውኖች ላይ ለመነጋገር ሲሆን በተጨማሪ የመጪውንም ዓመት በጀት የሥራ ዕቅዶችና ፕሮግራሞችን ለመመልከት ይሆናል።

6.4.2 የበጀት ዓመት January አንድ (ጥር) እስከ December 31 (ታህሳስ) ድረስ ባለው ውስጥ ይሆናል።

6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ይቀርባል።

6.4.4 የመጪው ዓመት በጀት ለዓመታዊ ስብሰባ ቀርቦ እንዲፀድቅ ይደረጋል።

6.4.5 ያጭርና የረጅም ጊዜ የሥራ እቅዶች ለስብሰባው ቀርበው እንዲፀድቁ ይደረጋል።

6.5 ልዩ ስብሰባዎች

6.5.1 እንደጉዳዮቹ ክብደትና ሁኔታ ልዩ ስብሰባዎች እንደአስፈላጊነቱ ሊጠሩ ይችላሉ።

6.5.2 ልዩ ስብሰባዎችን መጥራት አግባብ የሚኖረው ከሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ሲሟላ ነው።

6.5.2.1 ቦርዱ ልዩ ስብሰባ መጥራት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኝው፥

6.5.2.2 ከሶስት አንድ እጅ (1/3) የሚሆን አባላት ስለስብሰባው አስፈላጊነት በጽሑፍ ሲጠይቁ፥

6.5.2.3 ከቤተክርስቲያኑ ካህናትና አዛውንት አብዛኛው የስብሰባውን አስፈላጊነት በጽሑፍ ሲጠይቁ፥

6.5.2.4 በበጀት ውስጥ ያልተጠቀሰ ከ$5,000 (አምስት ሺህ ዶላር) በላይ ወጪ ለማስፈቀድ ሲፈለግ፥

===========================

Page 9: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

9

አንቀጽ 7.0

ምርጫዎች

7.1 ማንኛውም ምርጫ የሚካሄደው በጠቅላላ ያባላት ጉባኤ ይሆናል።

7.2 በስብሰባ ላይ ያልተገኘ አባል ፈቃደኝነቱን በጽሑፍ እስካረጋገጠ ድረስ ለምርጫ ዕጩ ሆኖ መቅረብ ይችላል።

7.3 አብዛኛውን ድምጽ ያገኘ ዕጩ አሸናፊ ይኖናል። አብዛኛውን የመራጮች ድምፅ ባለማግኘት ብቸኛ አሸናፊ ካልተገኘ ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት ሁለት ተወዳዳሪዎች መካከል እንደገና ምርጫ ይካሄዳል። ሁለቱ ተወዳዳሪዎች እኩል ድምፅ ካገኙ ደግሞ በሁለቱ ተወዳዳሪዎች መካከል አሸናፊው በዕጣ ይወሰናል።

7.4 አስመራጭ ኮሚቴ

7.4.1 ጊዜያዊ የአስመራጭ ኮሚቴ የቦርድ አባላትን ለማስመረጥ በጉባኤው ይቋቋማል።

7.4.2 አስመራጭ ኮሚቴው በጉባኤው የተመረጡ (6) ግለሰቦችና ዋናው ቄስ በአባልነት የሚገኙበት ይሆናል።

7.4.3 አስመራጭ ኮሚቴው ከመካከሉ ሊቀመንበር ይመርጣል።

7.4.4 የአስመራጭ ኮሚቴው በሚከተሉት መመሪያዎች መሠረት ኃላፊነቱን ይወጣል።

7.4.4.1 ለመምረጥም ሆነ ለተመራጭነት ለመወዳደር የሚችሉ አባላትን ያጣራል ያጠናል።

7.4.4.2 አስፈላጊውን ጥናትና ቃለ መጠይቅ ካደረገ በኋላ ማጣሪያውን ያለፉ አሥራ አንዽ (11)

ተወዳዳሪዎች ይመርጣል። አጠር ያለ የሥራ ልምድና ሙያቸውን የሚገልጽ ጽሑፍ (resume) ይሰበስባል።

7.4.4.3 አስመራጭ ኮሚቴው የመረጣቸውን 11 እጩዎች ለአባላት ጉባኤ ለምርጫ ያቀርባል።

7.4.4.4 አስመራጭ ኮሚቴው እያንዳንዱን እጩ ለጉባኤው ያስተዋውቃል። እጩዎችም ራሳቸውን ለጉባኤው እንዲያስተዋውቁ ያደርጋል።

7.4.4.5 የአስመራጭ ኮሚቴው ሊቀመንበር ከ 11 ተወዳዳሪዎች መካከል በከፍተኛ ድምፅ

ያሸነፉትን (7) አባላት በሚቀጥለው ሳምንታዊ ስብሰባ ላይ ለጉባኤው ያቀርባል።

7.4.4.6 በቦርድ ሽግግር ወቅት አዲስ ከተመረጡት የቦርድ አባላት መካከል በአጋጣሚ ምክንያት ለማገልገል የማይችሉ ከሆነ ከ (7) ተመራጮች ቀጥሎ ከፍተኛ ድምፅ ብልጫ ያላቸው ተተክተው እንዲሰሩ ያደርጋል።

7.4.4.7 አስመራጭ ኮሚቴው ለተመረጡት 7 እጩዎች የመጀመሪያ ስብሰባቸውን እንዲያደርጉ ያደርጋል። አዲስ የተመረጠው የሥራ አመራር ቦርድ በመጀመሪያ ስብሰባውና አስመራጭ ኮሚቴው በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥ ምክትል ሊቀመንበር፥ ዋና ፀሐፊ፥ የሂሳብ ሹምና የገንዘብ ያዥ ይመርጣል።

Page 10: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

10

7.4.4.8 አስመራጭ ኮሚቴው አዲሱን የቦርድ ሊቀ መንበር ለቤተክርስቲያኑ አባላት ያስተዋውቃል። የቦርዱ ሊቀመንበር የሥራ አስኪያጅ ቦርዱን አባላት ለቤተክርስቲያኗ አባላት ያስተዋውቃል። የቦርድ አባላት የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት በዋናው ቄስ አማካይነት ይፈፅማሉ።

7.4.4.9 አስመራጭ ኮሚቴው በአገልግሎት ላይ የነበረው ቦርድ የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን፥ ሰነዶችንና ሌሎችንም መዛግብት ሁሉ ለአዲሱ ቦርድ ማስረከቡን ያረጋግጣል።

7.4.4.10 የሚያስፈልጉትን ሠነዶች ርክክብ በሁለቱም ቦርዶች በኩል በፊርማ መደረጉን የአስመራጭ ኮሚቴው ሊቀመንበር፥ ዋናው ቄስና አንድ የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ባሉበት መፈጸሙን ያረጋግጣል።

7.4.4.11 ምርጫውን የሚመለከቱ ሠነዶችና መዝገቦችን ሁሉ ለተመረጠው ቦርድ ያስረክባል።

7.4.5 የአስመራጭ ኮሚቴው ሥራውንና ኃላፊነቶቹን ለማቀላጠፍ እንዲረዳው የሚከተሉትን የጊዜ ገደቦች ይከተላል።

7.4.5.1 የአስመራጭ ኮሚቴው ምርጫ August (በነሐሴ) ወር የመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ ይደረጋል።

7.4.5.2 የቦርዱ እጩዎች November (በሕዳር) ወር አጋማሽ ላይ ይቀርባሉ።

7.4.5.3 የአዲሱ ቦርድ አባላት ምርጫ November (በሕዳር) ወር መጨረሻ ይካሄዳል።

7.4.5.4 የአዲሱ ቦርድ የትውውቅና የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት December (በታህሣሥ) ወር መጀመሪ ይደረጋል።

7.4.5.5 የሠነዶች ርክክብ በዲሴምበር (በታህሳስ) ወር መጨረሻ ይደረጋል።

7.4.5.6 አዲሱ ቦርድ መደበኛ ሥራውን January (በጥር) ወር ይጀምራል።

7.4.5.7 የአስመራጭ ኮሚቴው ምርጫውን የሚመለከቱ ሠነዶችን February (በየካቲት) አንድ ቀን አዲስ ለተመረጠው ቦርድ ያስረክባል።

===============================

Page 11: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

11

አንቀጽ 8.0

የቦርድ አባላት

8.1 ምርጫ በአንቀፅ 8.11.2 ከተደነገገው በስተቀር የቦርድ አባላት የሚመረጡት በጠቅላላ ጉባኤው ነው።

8.2 ቦርዱ በጠቅላላው ጉባኤው ሥር የሚገኝ ከፍተኛው የስራ አመራር አካል ነው።

8.3 ብቁነት፦ ለ12 ተከታታይ ወራት የቤተክርስቲያን አባል የሆነና የክብር አባል ያልሆነ ወይንም ወርሃዊ ክፍያ እንዳያደርግ አስተያየት የተደረገለት ግለሰብ በቦርድ አባልነት እጩ ሆኖ መቅርብ ይችላል።

8.4 በሥራ ላይ ያሉ የቦርድ አባላት ለሁለተኛ ዙር ምርጫ መወዳደር ይችላሉ። ከሁለት ተከታታይ የኃላፊነት ዘመን በላይ በቦርድ አባልነት መሥራት አይቻልም።

8.5 የሥራ ዘመን፦የቦርዱ የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል። January (ጥር) አንድ የአገልግሎት ጊዜው የሚጀመርበት ቀን ይሆናል።

8.6 ብዛት፦ የቦርድ አባላት ቁጥር ሰባት ይሆናል።

8.7 ኮሚቴዎች፦ቦርዱ የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ኮሚቴዎች ከጠቅላላ ጉባኤው መካከል ማቋቋም ይችላል።

8.8 ክፍያ፦የቦርዱ አባላት ለገቡበት የሥራ ኃላፊነትም ሆነ ለሚሰጡት አገልግሎት የገንዘብም ሆነ ሌላ ክፍያ አያገኙም።

8.9 ተግባርና የሥራ ኃላፊነት፦

የቦርዱ መሠረታዊ ተግባር ለቤተክርሲቲያንዋ አባላትና ለማህበረሰቡ የሚደረጉትን ልዪ ልዩ አገልግሎቶች፣ አስተዳደርና ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን ማቀድ፣ በተግባር ማዋልና መቆጣጠር ይሆናል። ቦርዱ የሥራ ተግባሩን የሚፈጽመው ይህን መተዳደሪያ ደንብና፥ የካሊፎርንያና የአሜሪካን የፌደራል ሕግን መሠረት በማድረግ ይሆናል።

የቦርዱ የሥራ ተግባሮችና ኃላፊነቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ።

8.9.1 አስተዳደር፦ ቦርዱ የቤተክርስቲያኗን የአጭርና የረጅም ጊዜ ሥራዎችን ያቅዳል፤ ያካሂዳልም።

8.9.2 አገልግሎት፦ ሃይማኖት ትምህርትና የህብረተሰብ ነክ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲቻል አስፈላጊውን መመሪያ ይሰጣል።

8.9.3 ገንዘብ ነክ፦ ቦርዱ ለሚከተሉት ተግባራት ኃላፊነት ይኖረዋል።

8.9.3.1 መዋጮ፣ ስጦታ፣ ሙዳየ በረከት እና ሌሎችንም እርዳታዎችን መሰብሰብ፣

8.9.3.2 የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችንና የአገልግሎት ክፍያዎችን መተዳደሪያ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት ማከናወን፣

Page 12: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

12

8.9.3.3 ዓመታዊ በጀትና የገንዘብ አቋምን የሚገልጹ ዘገባዎችን አዘጋጅቶ ጠቅላላ ጉባዔው እንዲያፀድቀው ማቅረብ፣

8.9.3.4 ደረሰኞችን፣ የባንክ መግለጫዎችን፣ ወርሃዊ ክፍያዎችን፣ እንዲሁም ሌሎች ገንዘብ ነክ ሠነዶችን ባግባቡ መጠበቅ፣

8.9.3.5 የውሥጥ የሂሳብ እና የገንዘብ ቁጥጥር ማድረግ፤የሒሳብ መርማሪዎች ሥራ እንዲቀላጠፍ አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ፤

8.9.3.6 የገንዘብ ወጭና ገቢዎች በትክክለኛው መንገድ እንዲወራረዱና በገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም ሳቢያ ሊነሱ የሚችሉ ጉድለቶችን ለማስወገድ አስፈላጊውን መመሪያ ማውጣት፤

8.9.3.7 ዓመታዊ የሒሳብ ምርመራ ዘገባ ጊዜውን ጠብቆ ፤ለአባላቱ እንዲዳረስ ማድረግ፤

8.9.3.8 የካሊፎርንያ ሕግ አትራፊ ያልሆኑ አክስዮን ማህበራትን በሚመለከት በሚፈቅደው መሠረት የቤተክርስቲያኗ ገንዘብ የሚያድግበትን መንገድ መፈለግ፤

8.9.4 ንብረት፦ ቦርዱ የቤተክርስቲያኗን ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ይጠብቃል ይንከባከባልም።

8.9.5 ሕግ ነክ ስራዎች፦ ቦርዱ ቤተክርስቲያኗን የሚመለከቱ ወይንም ሕግ ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ያካሂዳል። የቤተ ክርስቲያኗን መብት በሕግ ፊት ያስከብራል። በማንኛውም ሕግ ነክ ጉዳዮች ቤተ ክርስቲያኗን ወክሎ ይቀርባል። ቦርዱ ማንኛውንም ዓይነት ውሎችና የግዢና የሽያጭ ጉዳዮችን የሚያከናውነው በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ነው።

8.9.6 የቤተ ክርስቲያኗ ሠራተኞች (አገልጋዮች) ቦርዱ የቤተክርስቲያኗን ሠራተኞችና ካህናት ጨምሮ የመቅጠርና የማሰናበት ሥልጣን አለው። ከካህናቱ መካከል አንዱን ማሰናበት የሚችለው ከዋናው ቄስ ጋራ በጉዳዩ ከመከረ በኋላ ነው። ስለ ዋናው ቄስ ከአገልግሎት ማሰናበት ወይንም ለአገልግሎት ማግኘት ጉዳይ የሚወስነው ጠቅላላ ጉባኤው ሲያፀድቅ ብቻ ነው።

8.9.7 መዛግብት፦ ቦርዱ የቤተክርስቲያኗን ሠነዶችና መዛግብት ይጠብቃል።

8.9.8 ማኅተም፦ቦርዱ የቤተክርስቲያኗን ማኅተም ይይዛል፣ ይጠቀምበታልም። ማኅተሙ ቅዱስ መስቀል፣ የእመቤታችን የቅድስት ማርያምን እና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምስል የያዘ ይሆናል። የቤተ ክርስቲያኗን ስም በአማርኛና በእንግሊዝኛ የሚገልፅ ይሆናል።

8.9.9 ተወካይነት፥ ቦርዱ በተለያዩ ስብሰባዎችና ዝግጅቶች ላይ ቤተክርስቲያኗን ሊወክል ይችላል።

8.9.10 ውሳኔዎች፥ ቦርዱ ጠቅላላ ጉባኤው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በሥራ ላይ ያውላል።

8.10 ገደቦች፦ በጠቅላላ ጉባኤው ካልተፈቀደ በስተቀር ቦርዱ የሚከተሉትን የሥልጣን ገደቦች የማስተዋል ኃላፊነት ይጠበቅበታል።

8.10.1 በዓመታዊ በጀት ውስጥ ያልተመደበ $5000 (አምስት ሺህ ዶላር) በላይ ወጪ ለማድረግ የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ ይጠይቃል።

8.10.2 ከ$500 (አምስት መቶ ዶላር) በላይ ውሎ አበልና ከመቶ አምስት (5%) በላይ የደሞዝ ዕድገት ለማድረግ ሲፈለግ ጠቅላላ ጉባኤው ማፅደቅ አለበት።

Page 13: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

13

8.10.3 ቦርዱ ከዓመታዊ ባጀት ከመቶ አስር (10%) በላይ ወጭ ለማድረግ ተገቢነቱን ለጠቅላላ ጉባኤው በጽሑፍ ማስረዳት አለበት።

8.10.4 ፈራሚዎች፦

የቦርዱ ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበርና፣ ዋና ገንዘብ ያዥ በቼኮችና በገንዘብ ነክ ሰነዶች ላይ መፈረም ይችላሉ። እያንዳንዱ ሰነድ ቢያንስ ከሶስቱ የሁለቱን ፊርማ መያዝ አለበት።

8.11 ክፍት ቦታ መሙላት፦

8.11.1 ከቦርዱ አባላት አራቱ በተለያዩ ምክንያቶች በአንድ ወቅት ኃላፊነታቸውን መወጣት ካልቻሉ ወይንም በፈቃዳቸው ከአገልግሎታቸው ከለቀቁ ቦርዱ ሕጋዊ ሰውነት አይኖረውም። የዚህ ዓይነት ሁኔታ ከተከሰተ የአባላት ልዩ ስብሰባ ተጠርቶ የውስጥ መተዳደሪያ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት አዲስ የቦርድ አባላት ምርጫ ይደረጋል።

8.11.2 ቦርዱ ለእያንዳዱ ክፍት ቦታ ሁለት እጩዎችን ለጠቅላላ ጉባኤው ለምርጫ ያቀርባል።

8.12 ስብሰባ፦ቦርዱ ቢያንስ በወር አንድ ቀን ስብሰባ ያደርጋል። ስብሰባዎችን የሚያካሂደው መተዳደሪያ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት ይሆናል።

8.13 ከአገልግሎት መገለል፦ ከቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል አንድ ሶስተኛው (1/3) በጽሁፍ ጥያቄ ካቀረበና በጠቅላላ ጉባኤው ከመቶ ሃምሳ በላይ በሆነ ድምፅ ከወሰነ የቦርድ አባል ከሥልጣን ሊገለል ይችላል።

8.14 ከምድብ ሥራ ኃላፊነት መወገድ፦ከቦርድ አባላት ሁለት ሶስተኛው (2/3) በአንድ የቦርድ አባል ምድብ ሥራ አያያዝ እምነት ቢያጡ እሱን አንስተው በዚያ ምድብ ቦታ ላይ ሌላ የቦርድ አባል መተካት ይችላሉ።

8.15 ለሚነሱ አለመግባባቶች ግጭቶች መፍትሔ:

በቦርዱ አባላት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈቱት በቦርዱ ውስጥ ነው። ቦርዱ ለጉዳዩ መፍትሔ ሊያገኘለት ካልቻለ ለአዛውንት ኮሚቴ ጉዳዩን ያቀርባል። የአዛውንት ኮሚቴ ለጉዳዩ መፍትሔ ካላገኘ የቦርዱ ሊቀመንበር ለጉዳዩ መፍትሔ እንዲሰጥ ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርብና ያስፈፅማል።

8.16 የቦርዱ የሥራ መዋቅር፦ የቦርድ የሥራ መዋቅር እንደሚከተለው ይሆናል።

ሀ. ሊቀመንበር

ለ. ምክትል ሊቀመንበር

ሐ. ዋና ጸሐፊ

መ. ዋና የሒሳብ ሹም

ሠ. የገንዘብ ያዥ

ረ. የቀሩት ሁለት የቦርድ አባላት

Page 14: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

14

8.16.1 ሊቀ መንበር

8.16.1.1 የሊቀመንበሩ ኃላፊነት በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ቦርዱን መምራት ነው።

8.16.1.2 ሊቀመንበሩ መተዳደሪያ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት ስብሰባዎችን ይመራል።

8.16.1.3 የስብሰባ አጀንዳ ዝግጅቶችን ያቀነባብራል፤ አባላትን ለመደበኛና ልዩ ስብሰባዎች ይጠራል።

8.16.1.4 ቤተክርስቲያኗን በመወከል ከተለያዩ ድርጅቶች ጋራ ለሚደረጉ ውሎች፣ ስምምነቶችና፣ ድርድሮች ለመፈጸም ያብዛኛውን የቦርድ አባላት ድጋፍ ማግኘት አለበት።

8.16.1.5 በቦርዱ ስም ለጠቅላላ ጉባኤው ረፖርትና ገለጻዎችን ያቀርባል።

8.16.1.6 በሁሉም ስብሰባዎችና ውሳኔዎች ላይ አንድ ድምፅ ብቻ ይኖረዋል።

8.16.1.7 ሥራ ላይ እንዲውሉ ሀሳብ የቀረበባቸው ተግባሮች ሁሉ መፈጸማቸውን ማረጋገጥ አለበት።

8.16.2 ምክትል ሊቀመንበር

8.16.2.1 ሊቀ መንበሩ በማይኖርበት ጊዜ በምትኩ ሆኖ ይሠራል።

8.16.2.2 እንደ ማንኛውም የቦርድ አባል አንድ ድምፅ ብቻ ይኖረዋል።

8.16.2.3 የተለያዩ ሥራዎችና (ፕሮጀክቶችን) በኃላፊነት እንዲያካሂድ ይመደባል።

8.16.3 ዋና ፀሐፊ

8.16.3.1 የቦርድ ስብሰባዎችን እና ጠቅላላ ጉባኤዎችን በፀሐፊነት ያገለግላል።

8.16.3.2 ዓብይ ውሳኔዎችን በተግባር የመዋል ሂደት በቅርብ ይከታተላል።

8.16.3.3 አስፈላጊ የሆኑ መግለጫዎችንና ማስታወቂያዎችን ለምዕመናኑና ለቦርድ አባላት ያስተላልፋል።

8.16.3.4 የቦርዱንና የጠቅላላ ጉባኤውን የስብሰባ አጀንዳ ያዘጋጃል፤ የስብሰባውን ሂደትቃለ ጉባኤ ይይዛል።

8.16.3.5 ሊቀመንበሩና ምክትል ሊቀመንበሩ በማይኖሩበት ጊዜ ስብሰባዎችን ይመራል።

8.16.4 ዋና የሂሳብ ሹም

8.16.4.1 ብቁነት፦ ዋና የሂሳብ ሹም የሂሳብ አያያዝ መሠረታዊ ዕውቀት ያለው ቢሆን ይመረጣል። የሒሳብ ሹሙ የዚህ ዓይነት እውቀት ያለው ግለሰብ ካልሆነ በሙያው ብቁ በሆነ ሰው ሊረዳ እንዲችል ቦርዱ ፈቃደኞች ባለሙያዎች እንዲያግዙት ያደርጋል።

8.16.4.2 ዋናው የሒሳብ ሹም በተለመደው የገንዘብ አያያዝ ዘዴና አሰራር መሠረት የቤተ ክርስቲያኗን ሃብትና ዕዳ የሚገልፁ መዛግብትን ይይዛል።

8.16.4.3 የገንዘብ ነክ ሠነዶችን በአግባቡና ሥርዓት ባለው ሁኔታ መያዛቸውን ያረጋግጣል።

Page 15: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

15

8.16.4.4 ገንዘብ ነክ ሰነዶች ሁሉ ለሚፈቀድላቸው አባላትና የሂሳብ መርማሪዎች ሊቀርቡ በሚችሉበት ሁኔታና ሥርዓት ይይዛል።

8.16.4.5 በተመደበው በጀት መሠረት ክፍያዎች ወቅቱን ጠብቀው መከፈላቸውን ያረጋግጣል።

8.16.4.6 ለቤተክርስቲያኗ ገቢ መሆን ያለባቸውን ክፍያዎችና የሚሰበሰቡ ገንዘቦች ገቢ መሆናቸውንና ደረሰኝ መሰጠቱን ያረጋግጣል።

8.16.4.7 ቦርዱ ለጠቅላላ ጉባኤው የሚያቀርበውን የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ የገንዘብ ሪፖርት ያዘጋጃል።

8.16.4.8 ለሂሳብ መርማሪዎች የሚያስፈልጉትን የገንዘብ ሰነዶች በሚገባ አዘጋጅቶ ያቀርባል።

8.16.4.9 የሂሳብ መርማሪዎች ገንዘብ አያያዝን በሚመለከት የሚያቀርቡትን አስተያየት በሥራ ላይ ያውላል።

8.16.4.10 ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ውሎችና የቼኮች ክፍያ አግባብ ባላቸው የቦርድ አባላት በትክክል መፈረማቸውን ያረጋግጣል።

8.16.4.11 የባንክ መግለጫዎችን በየወሩ በማስተካከልና በማወራረድ ለቦርዱ አቅርቦ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል።

8.16.5 ገንዘብ ያዥ

8.16.5.1 ገንዘብ ያዡ የቤተክርስቲያኗን ንብረቶች መዛግብትና ሠነዶችን በበላይ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት አለበት።

8.16.5.2 ከቦርዱ ሊቀ መንበርና አግባብ ካላቸው አገልጋዮች ጋር በመመካከር ለቦርዱ ቀርቦ ከታየ በኋላ ሰጠቅላላ ጉባኤ የሚቀርብ ዓመታዊ በጀትን ያዘጋጃል።

8.16.5.3 ጥሬ ገንዘብና ቼኮችን በቤተክርስቲያኗ የባንክ ሒሳብ ውስጥ ሳይዘገይ ያስገባል።

8.16.5.4 ለጥቃቅን ወጪዎች በቦርድ የተመደበውን የጥሬ ገንዘብ (petty cash) በአግባቡ ይዞ ይጠቀማል።

8.16.5.5 የቤተክርስቲያኗን መዋዕለ ንዋይ (investment) እንዲሁም የገንዘብ ሁኔታዎችን (cash

flow) ገቢዎች አካሂያድ ያቅዳል ይቆጣጠራል።

===========================

Page 16: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

16

አንቀጽ 9.0

የሂሳብ መርማሪዎች (ኦዲተሮች)

9.1 የሒሳብ መርማሪዎች የሚመረጡት በጠቅላላ ጉባኤው ሆኖ በምርጫው ቦርዱ አስፈላጊውን ትብብር ያደርጋል።

9.2 የሂሳብ መርማሪዎች ተጠሪነታቸው ለጠቅላላ ጉባኤ ነው።

9.3 የሒሳብ መርማሪዎች በሙያው የሠለጠኑ መሆን አለባቸው። ለሚሰጡት አገልግሎት ክፍያ ሊደረግላቸው ወይንም ደግሞ በበጎ ፈቃድ ያለክፍያ የሚሠሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ያለክፍያ የሚሠሩ ከሆኑ ብዛታቸው ከሁለት መብለጥ የለበትም።

9.4 ጠቅላላ ጉባኤው ለውጥ ለማድረግ እስካልወሰነ ድረስ የሒሳብ ምርመራ የሚካሄደው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ ይሆናል።

9.5 የቤተክርስቲያኗን የሂሳብ ምርመራ ካጠናቀቁ በኋላ የሂሳብ መርማሪዎች የሥራቸውን ውጤት ለጠቅላላ ጉባኤው ከማቅረባቸው በፊት ከቦርዱ ጋር በውጤቱ ላይ ይነጋገራሉ።

9.6 የበጀት ዓመቱ ባለቀ በሶስት ወራት ውስጥ የሂሳብ ቁጥጥር ውጤት ለጠቅላላ ጉባኤው መደበኛ ወይንም ልዩ ስብሰባ ይቀርባል።

9.7 የሂሳብ መርማሪዎች ከቦርዱ ጋር በመተባበር የሂሳብ ሪፖርቱን ውጤትና ዘገባ ግልባጭ ለጠቅላላ ጉባኤው አባላት ያሰራጫሉ። ስለውጤቱ ተጨማሪ መግለጫ ወይንም ማብራሪያ እንደአስፈላጊነቱ በቦርድ ተዘጋጅቶ ከሪፖርቱ ጋር ሊቀርብ ይችላል።

=========================================

አንቀጽ 10.0

ካህናት

10.1 “ካህናት” ተብሎ የሚጠራው አካል የድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ዋና ቄስ፣ ሌሎች ቄሶችን፣ ዲያቆኖችንና ሌሎች በመንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በአባልነት የሚገኙበት ነው።

10.2 ካህናቱ አስተዳደርን በሚመለከት ተጠሪነታቸው ለቦርዱ ይሆናል።

10.3 ካህናቱ ይህን መተዳደሪያ ደንብ ማክበርና በዚሁም መሠረት መተዳደር ይኖርባቸዋል።

10.4 ካህናቱ በሙሉ የመንፈሳዊ እና የዕምነት አገልግሎታቸውን የሚያበረክቱት በዋናው ቄስ ኃላፊነትና ተቆጣጣሪነት ነው።

10.5 የካህናቱ ኃላፊነትና ተግባር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሲኖዶስ ሕግጋትና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የመንፈሳዊና የኃይማኖት አገልግሎቶች መስጠት ይሆናል። ካህናቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያካትት ነገር ግን በነዚህ ያልተወሰነ ተግባራትና ኃላፊነት ይኖራቸዋል።

Page 17: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

17

10.5.1 የቤተክርስቲያኗን የቅዳሴ፥ የጋብቻ፥ የሥርዓተ ቀብር፥ የውዳሴና ሌሎችም አገልግሎቶችን መስጠት

10.5.2 የጥምቀትና፥ የጋብቻ እንዲሁም ተመሳሳይ ምስክር ወረቀቶችን ማፅደቅ

10.5.3 ምዕመናኑን መጎብኘት፥ የታመሙትን፥ በኃዘን ላይ ያሉትንና የተቸገሩን ማጽናናት

10.5.4 የቤተክርስቲያኗን አባላት ቁጥር በመጨመርም ሆነ ለአጠቃላይ ዕድገቷ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ መሳተፍ።

10.5.5 የኦርቶዶክስ ዕምነትን ለማስፋፋት አስፈላጊውን አመራር መስጠት

10.5.6 ከትምህርት ጉዳዮች ኮሚቴ ጋራ በመተባበር የሃይማኖት ትምህርትን መስጠት

10.6 ዋናው ቄስ ቦርዱ በእጩነት ካቀረባቸው ሁለት ተወዳዳሪዎች መካከል የጠቅላላ ጉባኤውን ሁለት

ሶስተኛ (2/3) ድምፅ በማግኛት ይመረጣል። ቦርዱ ለዋና ቄስነት የሚያገለግሉ ብቃትና ችሎታ ያላቸው ካህናት በሚፈልግበትና በሚመርጥበት ጊዜ የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚቴውን ትብብር ሊጠይቅ ይችላል።

10.7 ከዋናው ቄስ በስተቀር ሌሎች የካህናቱ አባላት የሚመረጡት ቦርዱና ዋናው ቄስ አስፈላጊውን ግምገማና ጥናት ካደረጉ በኋላ በሚደርሱበት የጋራ ስምምነትና ውሳኔ መሠረት ይሆናል። የተደረሰበት ስምምነትም ተመዝግቦ ለጠቅላላ ጉባኤው ይቀርባል። ለእያንዳንዱ ክፍት ቦታ ለውድድር የሚቀርቡት እጩዎች ከሁለት ማነስ የለባቸውም።

10.8 የማንኛውም ካህን አባል ብቃት ችሎታና ማዕረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነትና ሕግጋት መሠረት ይሆናል። የተመራጩ ካህን የብቃት መረጃዎች በቦርዱ ጽሕፈት ቤት ይቀመጣሉ።

10.9 የቦርዱን ስምምነት ካገኙ ዋናው ቄስ በሃይማኖት በዓላት፥ ዝግጅቶችና ሴሚናሮች ላይ የድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያንን መወከል ይችላሉ። እንዲሁም ሌሎቹ ካህናትም የቦርዱንና የዋናውን ቄስ ስምምነት ካገኙ ቤተክርስቲያኗን ወክለው ሊገኙ ይችላሉ።

10.10 ዋናው ቄስ

10.10.1 ካህናቱን መቆጣጠርና መምራት የዋናው ቄስ ኃላፊነት ነው ።

10.10.2 ቤተክርስቲያኗ ለምታስተዳድራቸው ትምህርት ቤቶች፥ ሌሎች ድርጅቶች፥ ማሕበራትና ኮሚቴዎች የመንፈሳዊ አመራር ይሰጣሉ

10.10.3 በአንቀጽ 10.5.2 ለተጠቀሱት የምስክር ወረቀቶች ፈቃድና ፊርማ ኃላፊ ይሆናሉ።

10.10.4 በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ሕግጋትና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት መንፈሳዊ ጉዳዮችን በሚመለከት የዳኝነት ውሳኔ የመስጠት ተግባር የዋናው ቄስ ይሆናል። ሆኖም ቦርድ፥ የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚቴ፥ የቀሩት የካህናት አባላትና አንዳንድ ምዕመናን በአጥጋቢ ምክንያት በዋናው ቄስ ዳኝነት ወይም ውሳኔ ካልተስማሙ፥ ዋናው ቄስ ውሳኔያቸውን እንዲያነሱ በቦርድ አቀነባባሪነት ይጠየቃሉ። ዋናው ቄስ ይህን ጥያቄ ተቀብለው ውሳኔ ካልሰጡ ጉዳዩ በቦርድ አማካይነት ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ ይወሰናል።

10.10.5 ከቦርዱ ጋር በመሆን በመንፈሳዊ የሥልጣን መዋቅር መሠረት የካህናቱን የደረጃ ዕድገት ወይንም ሽረት የማቀነባበር ኃላፊነት ይኖራቸዋል።

Page 18: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

18

10.10.6 ከገንዘብ ያዡ ጋር በመተባበር የቤተክርስቲያኗን የመንፈሳዊና የሃይማኖት አገልግሎት ንዋዬ ቅዱሳት ዕቃዎችን ይጠብቃሉ።

10.11 ማንኛውም የካህናቱ አባል ከአገልግሎቱ ሊወገድ ወይንም ሊሰናበት የሚችለው ቦርዱ ዋናውን ቄስ አማክሮ ጉዳዩን ለጠቅላላ ጉባኤው አቅርቦ ሲያስፈቅድ ነው።

10.12 ዋናውን ቄስ ከአገልግሎት ማሰናበት ወይንም ማስወገድ የቦርዱ ኃላፊነት ሲሆን ጉደዩ ለጠቅላላ

ጉባኤው ቀርቦ በሁለት ሶስተኛ (2/3) ድምፅ ሲፀድቅ ተፈፃሚነት ይኖረዋል።

========================

አንቀጽ 11.0

የቤተ ክርስቲያን አዛውንት

11.1 ዓላማ፦ የቤተክርስቲያን አዛውንት ተብሎ የሚጠራው አካል የተመሠረተበት ዓላማ ከቦርዱ ጋር በመተባበር የቤተክርስቲያኗን ህልውናና አንድነት ለመጠበቅና ለማራመድ ይሆናል።

11.2 ምርጫ፦ ጠቅላላ ጉባኤው ከመካከሉ የቤተክርስቲያን አዛውንት ይመርጣል።

11.3 የምርጫ ሂዳት፦ቦርዱ የምርጫውን ሂደት ያከናውናል። አምስት አባላት የሚገኙበት ልዩ

የአስመራጭ ኮምቴ ከቦርዱ ጋር በመተባበር ለጠቅላላ ጉባኤው 12 እጩዎችን ለምርጫ ያቀርባል። ምርጫው ከተደረገ በኋላ የቦርዱ ሊቀመንበር የተመረጡትን አዛውንት ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል። አዛውንቱ ከመካከላቸው ሊቀመንበር ይመርጣሉ።

11.4 ብዛት፦ የአዛውንት ብዛት 7 ይሆናል

11.5 የአገልግሎት (የሥራ) ዘመን፦ የአዛውንት ኮሚቴው የሥራ ዘመን ለሶስት ዓመት ሆኖ ሥራውንም

የሚጀምረው ጁን (ሰኔ)ወር መጀመሪያ ይሆናል።

11.6 ለአዛውንት ኮሚቴው የሚቀርቡ እጩዎች የቤተክርስቲያኗ አባል መሆን አለባቸው፣ የኢትያጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ሥርዓትና ሕግጋት እውቀት ያላቸው ቢሆን ይመረጣል። በቤ ክርሲቲያኗ ዝግጅቶች ላይ አገልግሎቶችና በቂ ተሳትፎ ያደረጉ፣ በቤተክርስቲያን ሥራዎች ላይ በኃላፊነት ተመድበው በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው፣ በሥነምግባራቸው በአስተዋይነትና በዕምነታቸው ጠንካራ የሆኑ መሆን አለባቸው።

11.7 ኃላፊነት፦ የአዛውንት ኮሚቴው ዋና ኃላፊነት የቤተክርስቲያኗን ሕልውና መጠበቅ ይሆናል።

11.8 ተግባራት፦ የአዛውንት ኮሚቴው ተግባራት የሚከተሉት ናቸው ፣

11.8.1 በምዕመናን፣ በቤተሰብ፣ በተመራጮች፣በቦርዱና በካህናቱ መካከል ሊነሱ የሚችሉ ግጭቶችና ውዝግቦችን መሸምገልና ማስታረቅ።

Page 19: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

19

11.8.2 ይህ መተዳደሪያ ደንብ አለመጣሱን ማረጋገጥ

11.8.3 ቤተክርስቲያኗን በሚመለከቱ ዓበይት ጉዳዮችን በማንሳት አስፈላጊውን ሐሳብ በጽሑፍ ለቦርዱ ማቅረብ

11.8.4 ለቤተ ክርስትያኗ ጥንካሬና ዕድገት ሊውሉ የሚችሉ ሃሳቦችና ጥቆማዎችን ለቦርዱ ማቅረብ

11.8.5 ቦርዱ በአንድ ምክንያት መሥራት የማይችልበት አጋጣሚ አስቸኳይ ሁኔታ ተፈጥሮ የቤተክርስቲያኗ የሥራ እንቅስቃሴ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሰ የአዛውንት ኮሚቴ የቦርዱን ሥራ ተረክቦ የቤተ ክርስቲያኗን አስተዳደር በጊዜያዊነት ያከሂዳል።

11.8.6 ምእመናን ወይም አባላት በተመራጮች፥ በካህናት ወይም በሌሎች አባላት ላይ ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ወይም የሥራ ኃላፊነት አያያዝ ጉድለት ቢያቀርቡ የአዛውንት ኮሚቴ ጉዳዩን መርምሮ መፍትሔ ይፈልጋል።

11.8.7 በቦርዱ በሚጠየቁበት ጊዜ አዛውንቱ ቤተክርስቲያኗ ከሌሎች ቤተ ክርስቲያኖች እና ድርጅቶች ጋር ያላትን ግንኙነቶች በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ቦርዱን ወክለው ያገለግላሉ።

11.9 በአንቀጽ 11.8.1 የተመለከቱትን ለመሳሰሉ ግጭቶችና ውዝግቦች በአዛውንት ኮሚቴ በኩል መፍትሄ ቢታጣ እና በዚሁም ምክንያት ችግሩ ለቤተክርስቲያኗ ህልውና እና ለምዕመናኗም አንድነትና

ህብረት አሳሳቢ ሲሆን ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ በሁለት ሶስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናል። ጉባኤው የሚጠራው በቦርድ ሲሆን ጉዳዩ ለጉባኤው የሚቀርበው በአዛውንት ኮሚቴ ይሆናል። በተጨማሪም በቦርድና በአዛውንት ኮሚቴ መካከል ችግር ቢፈጠር ጉዳዩን በቦርድ ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ ውሳኔ ይሰጥበታል።

11.10 ክፍት ቦታ፦በአዛውንት ኮሚቴ ክፍት የአባል ቦታ ሲፈጠር አዛውንቱ ለእያንዳዱ ከፍት ቦታ ዕጩዎችን ለጠቅላላ ጉባኤው አቅርቦ ያስመርጣል።

11.11 እንደገና መመረጥ፦ የአዛውንት ኮሚቴ አባላት ሰሁለተኛ ዙር ምርጫ መቅረብ ይችላሉ። ከሁለት ተከታታይ የአባልነት ዘመን በኋላ ለምርጫ መቅረብ አይፈቀድላቸውም።

11.12 ከሥራ መገለል፦ከቤተክርስቲያኗ አባላት በአንድ አራተኛው (1/4) ጥያቄ በጽሑፍ ቀርቦ ጠቅላላ ጉባኤ ከመከረበትና በአብዛኛው ድምፅ ከተወሰነበት የአዛውንት ኮሚቴ አባል ከአባልነት መገለል ይችላል።

================================

Page 20: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

20

አንቀጽ 12.0

ኮሚቴዎች

12.1 ኮሚቴዎችን ስለማቋቋም፦ስራዎችን ለማቀላጠፍም ሆነ ኃላፊነቱን ለመወጣት ቦርዱ የተለያዩ ጊዜያዊና ቋሚ ኮሚቴዎችን ማቋቋም ይችላል።

12.2 ተጠሪነት፦እያንዳንዱ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለቦርዱ ይሆናል። በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረትም ሥራውን ያከናውናል።

12.3 መዋቅር፦ የቦርድ አባል ወይንም በቦርዱ የተወከለ ግለሰብ በሰብሳቢነት ወይንም በተጠሪነት ያገለግላል። እያንዳንዱ ኮሚቴ ፀሐፊና እንደአስፈላጊነቱም ሌሎች የሥራ ምድብ ቦታዎች ይኖሩታል። ሁሉም የኮሚቴ አባላት የሚመረጡት ከቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል ብቻ ይሆናል።

12.4 የሥራ ዘመን፦ የኮሚቴ አባላት የሥራ ዘመን ከቦርድ አባላት የሥራ ዘመን ጋራ አብሮ ያበቃል።

12.5 የቤተ ክርስቲያኗን ሥራዎች ለማስፈጸም በቋሚነት የሚያስፈልጉት ኮሚቴዎች የሚከተሉት ይሆናሉ።

12.5.1 የትምህርት ጉዳይ ኮሚቴ

12.5.1.1 የትምህርቱ ጉዳይ ኮሚቴ በቦርዱ የሚሰየም አካል ነው።

12.5.1.2 የቦርዱ ምክትል ሊቀ መንበር የትምህርት ጉዳይ ኮሚቴውን በኃላፊነት ይመራል።

12.5.1.3 የትምህርት ኮሚቴው ከምዕመናንና ከካህናቱ የተውጣጣ ይሆናል።

12.5.1.4 የትምህርት ኮሚቴው የሃይማኖት፣ የቀለምና የባህላዊ ትምህርቶችና አገልግሎቶችን ለሕፃናት፣ ለወጣቶች እንዲሁም ለአዋቂዎች እንዲደርስ ያስተባብራል ያዘጋጃል።

12.5.2 የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚቴ

12.5.2.1 የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚቴ በቦርዱ የሚሰየም አካል ነው።

12.5.2.2 የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚቴ አንድ የቦርድ አባል፣ ጥቂት ካህናትና፣ ከቤተ ክርስትያኗ አባላት መካከል ከተመረጡ ምዕመናን የተውጣጣ ይሆናል።

12.5.2.3 ዋናው ቄስ ወይንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት እና ሥርዓት ጠንቅቆ የሚያውቅ ግለሰብ የሃይማኖት ጉዳይ ኮሚቴውን በሰብሳቢነት ይመራል።

12.5.2.4 የኮሚቴው ኃላፊነቶችና ተግባራት

ሀ. በአንቀጽ 2.0 እና በአንቀጽ 10.0 በተጠቀሰው መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የሃይማኖት ሕግጋትና አገልግሎቶች በሚገባ መቅረባቸውን ይከታተላል።

ለ. በሃይማኖት ነክ ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ አለመግባባት እና ግጭቶችን በሰላም ይፈታል ይሸመግላል።

ሐ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን ያራምዳል፣ ያስፋፋል።

Page 21: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

21

መ. ከትምህርት ጉዳዮች ኮሚቴ ጋር በመተባበር የሃይማኖት ትምህርትን መመሪያ ይነድፋል ያዘጋጃል።

ሠ. ከምእመናኑ መካከል ቄሶችና ዲያቆኖች ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን ለትምህርት፣ ለሥልጠና፣ እንዲሁም ለክህነት ያቀርባል።የቤተክህነት ትምህርትን አጠናቀው ሊያገለግሉ የሚችሉበትን ዕቅድ ይነድፋል ያዘጋጃል።

ረ. የቤተክርስቲያኗ ካህናት ለመንፈሳዊ ሃላፊነታቸው ብቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል።

ሰ. በሥራ መልቀቅ፣ መሰናበት፣ ወይንም በመወገድ ምክንያት ከካህናቱ መካከል አንዱ ቢለዩ ኮሚቴው ቦታውን ለመተካት አስፈላጊውን በማድረግ ይተባበራል።

ሸ. ከካህናቱ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥርዓትንና ይህንን መተዳደሪያ ደንብ ሳያከብር ቢገኝ፣ ስለጉድለቱ መወሰድ የሚገባውን እርምጃ የሃይማኖት ኮሚቴ አጥንቶ ለቦርድ ያቀርባል።

12.5.3: የእርዳታ ኮሚቴ

12.5.3.1: የእርዳታ ኮሚቴው በቦር.ዱ የሚሰየም ይሆናል።

12.5.3.2 ኮሚቴው አንድ የቦርድ አባልና ከምእመናኑ መካከል የተመረጡ አባላት ይገኙበታል።

12.5.3.3 የኮሚቴው ኃላፊነቶችና ተግባራት የሚከተሉት ይሆናሉ፣

ሀ. በሃዘን፣ በሞትና በችግር ጊዜ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች ወገኖች አስፈላጊው

እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ይፈልጋል።

ለ. ኮሚቴው ቤተ ክርስቲያኗ ካላት አቅም አንፃር ምን ዓይነት እርዳታዎችን ለማድረግ

እንደምትችል ጥናት ያደርጋል።

ሐ. ከእርዳታ፣ ከመንግስታዊና ከሌሎችም አግባብ ካላቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት

በመፍጠርና በመዋዋል የቤተ ክርስቲያኗን የእርዳታ ማግኘት ሥራዎች ለማሳደግና

ለማመቻቸት የሚያስችሉትን መንገዶች ይቀይሳል።

መ. ከተለያዩ የርዳታና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር የሃይማኖት ዕምነት ልዩነቶችን

ሳይመለከት ግንኙነቶች ይመሰርታል።

ሠ. ልዩ ልዩ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብ በሎስ አንጀለስ እና በአካባቢው ለሚገኙ

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እርዳታ ያደርጋል።

12.5.4 የወጣቶች ጉዳይ ኮሚቴ

12.5.4.1 የወጣቶች ጉዳይ ኮሚቴ በቦርዱ የሚሰየም አካል ነው።

Page 22: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

22

12.5.4.2 የወጣቶች ጉዳይ ኮሚቴ ከትምህርት ጉዳይ ኮሚቴ ከሕዝብ ግንኙነትና ማኅበራዊ ጉዳይ ኮሚቴ፣ አንድ የቦርድ አባልና ከቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል የተመረጡ ሶስት ወጣቶች የሚገኙበት ይሆናል።

12.5.4.3 ኮሚቴው በቦርድ አባሉ ይመራል። ከኮሚቴው አባላት አንዱ ኮሚቴውን በፀሐፊነት ያገለግላል።

12.5.4.4 የኮሚቴው ኃላፊነትና ተግባራት የሚከተሉት ይሆናሉ፣

ሀ. በጥንታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ሥርዓትና ባህል መሠረት በመንፈሳዊ ሞራል ነክ ሁኔታዎች እንዲታነጹ ተገቢውን ጥረት ማድረግ።

ለ. የወጣት ማኅበራት፥ የወጣቶች ክበብ፥ መዘምራን እና የመሳሰሉት እንዲመሠረቱ አስፈላጊውን ጥረት ያደርጋል።

ሐ. የተለያዩ ስልቶችና ፕሮግራሞችን በመጠቀም ወጣቶች ቤተ ክርስቲያኗ በምታደርጋቸው የተለያዩ ዝግጅቶችና ተግባራት ላይ እንዲሳተፉ ያደርጋል።

መ. ከአስፈላጊ ኮሚቴዎች ጋር በመተባበር የትምህርትና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በተለያዩ የዕድሜ ክልል ላሉ ወጣቶች ያቀርባል።

ሠ. ለወጣቶች መመሪያ ይሰጣል፥ ምክርና ሃሳብ ያካፍላል::

ረ. የሞራልና የቁሳቁስ እርዳታ በማድረግ ወጣት መዘምራንን ክለቦችንና ማህበሮችን ይረዳል።

ሰ. ወጣቶች ራሳቸውን በማደራጀት በዲሞክራሲያዊ ሂደትና አሠራር መሠረት የአመራር ችሎታቸውን

(leadership) እንዲያሳድጉና እንዲያዳብሩ የበኩሉን ድርሻ ያደርጋል።

ሸ. የቤተክርስቲያኗን የገቢ ምንጭ ለማሳደግ በሚደረጉ የገንዘብ አሰባሰብ (fundraising) ዝግጅቶች ላይ ወጣቶች እንዲሳተፉ አስፈላጊውን ቅስቀሳ እና ማበረታቻ ያደርጋል። የድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያንና ሌሎችም ቤተ ክርስቲያኖች በሚያደርጉዋቸው የሃይማኖትና ማህበራዊ ዝግጅቶች ላይ እንዲሳተፉ ያበረታታል።

ቀ. ወጣቶች በሃይማኖት ነክም ሆነ በማህበራዊ ኑሮ ሥራ ላይ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍ እንዲል ያደርጋል።

12.5.5 የሕዝብ ግንኙነትና የማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ

12.5.5.1 የሕዝብ ግንኙነትና የማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ በቦርዱ የሚሰየም አካል ነው።

12.5.5.2 የኮሚቴው አባላት ከቤተ ክርስቲያኑ አባላት መካከል ይመረጣሉ።

12.5.5.3 የኮሚቴው ስብሰባ በቦርዱ አባል ይመራል።

12.5.5.4 የኮሚቴው ኃላፊነትና ተግባር የሚከተሉት ይሆናሉ፦

ሀ. በምዕመናን መካከል የጠበቀ ግንኙነትና መቀራረብ እንዲዳብር ማበራታታት

Page 23: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

23

ለ. ምዕመናኑ በቤተ ክርስትያኗ ዝግጅት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር የተለያዩ ዕቅዶችንና ፕሮግራሞችን በመቀየስ መርዳት

ሐ. በሎስ አንጀለስ፣ በአካባቢዎቿና በሌሎች ከተሞች የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን የድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የምታደርገውን መንፈሳዊ እንቅቃሴ እንዲሁም አንድነትና ሕብረት እንዲሰፍን ያላትን በጎ አቋም እንዲያውቁና እየመጡም በአገልግሎት እንዲጠቀሙ አስፈላጊውን ማድረግ።

መ. የተለያዩ ሃሳቦችን በማመንጨት፥ በመንደፍና በሥራ ላይ በማዋል የቤተክርስቲያኗ የአባላት ቁጥር እንዲያድግ ማድረግ

ሠ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት፥ ባህል፥ ታሪክና ሕግጋትን በአስፈላጊው መንገድ ለህብረተሰቡ ማሰራጨት

ረ. ለሃይማኖት ዝግጅቶች፥ ለዓመት በዓላት እንዲሁም ሌሎች የቤተክርስቲያን ሥራዎች አስፈላጊ ጽሑፎችን፥ በራሪ የጥሪ ወረቀቶችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት

ሰ. የቤተክርስቲያኗን እንግዶች፣ ጎብኝዎች መቀበል እና ለምዕመናኑ ማስተዋወቅ

ሸ. የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴው በሚያደርጋቸው የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅቶች በመካፈል ለውጤቱ መሳካት አስፈላጊውን ትብብርና እገዛ ማድረግ።

ቀ. ምዕመናንን የሚመለከት የህመም፥ የሞትና እንዲሁም ልዩ ልዩ ማህበራዊ ሁኔታዎችንና ዝግጅቶችን ለአባላት ማስተዋወቅ።

12.5.6 የሂሳብና የገንዘብ አሰባሰብ ኮሚቴ

12.5.6.1 የኮሚቴው አባላት በቦርዱ ይሰየማሉ

12.5.6.2 ከቤተክርስቲያኗ አባላት መካከል የተመረጡ ግለሰቦች ኮሚቴውን በአባልነት ያገለግላሉ።

12.5.6.3 የቦርዱ ገንዘብ ያዥ የኮሚቴው ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል።

12.5.6.4 የኮሚቴው ኃላፊነትና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው።

ሀ. ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር ግንኙነት በመመስረት የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ እንዲያደርጉ መጠየቅ።

ለ, የገንዘብ አሰባሰብ ስልቶችን መቀየስ፥ ዕቅዶችን መንደፍ እና ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ።

ሐ. የገንዘብ ዕድገት የሚገኝበትን መንገድ ማጥናትና ለቦርድ ማቅረብ።

መ. የቤተክርስቲያኗን የገቢ ምንጭ ሊያሳድጉ የሚችሉ አዳዲስ ተግባራት (ፕሮጀክቶች) ማቀድና ማዘጋጀት።

ሠ. በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስና ለመቆጠብ የሚያስችሉ ዘዴዎችና መንገዶች ማቅረብ።

ረ. መዋጮ ከሚያደርጉ ሁሉ ጋር ከፍተኛና ጠንካራ ዝምድና እንዲኖር ማድረግ ።

Page 24: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

24

አንቀጽ 13.0

የቤተ ክርስትያን ንብረቶች

13.1 የድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ንብረቶች የሚውሉት ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች ብቻ ነው።

13.2 የቤተክህነት መሪዎች ወይም የሥራ አመራር አባላት የቤተክርስቲያኗን ንብረትም ሆነ ገንዘብ ያለ አግባብ ከተጠቀሙ ወይንም ካጓደሉ በሕግ ፊት ይቀርባሉ።

13.3 ከ$5,000 (ከአምስት ሺህ የአሜሪካ ዶላር) በላይ ግምት ያላቸው ተንቀሳቃሽም ሆኑ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሊሸጡ፣ ሊለውጡ ወይም ሊገዙ የሚችሉት ጠቅላላ ጉባኤው ሲመክርበትና ሲስማማ ብቻ ነው።

13.4 ድርጅቱ ከፈረሰ ወይንም ከተበተነ ማንኛውም ዓይነት ንብረት የሚከፋፈለው የካሊፎርንያ ስቴት አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በሚመለከት ባወጣው ሕግና መመሪያ መሠረት ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ የድርጅት መፍረስም ሆነ ንብረት ወይንም ገንዘብ መከፋፈል በግለሰብ ወይን በቡድኖች የሚጀመርም ሆነ የሚፈጸም ሳይሆን ለዚሁ ጉዳይ ተብሎ የተሰበሰበ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ጉባዔ መክሮበት በሶስት

አራተኛ (3/4) ድምፅ ሲስማማበት ነው።

=================================

አንቀጽ 14.0

ሥነ ሥርዓት (ዲስፕሊን)

14.1 በማንኛውም ጊዜ አንድ ምዕመን የቤተክርሰቲያን አባል ተመርጦ የሚያገለግል አባል ወይም ግለሰብ ሥነ ሥርዓት ወይንም ደንቦችን ጥሶ ከተገኘ ቦርዱ በቀጥታ ወይንም በኮሚቴ ጉዳዩን ይመረምራል።

በአንቀጽ 14.2 መሠረት ውሳኔ ይሰጣል ወይም ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል። የጠቅላላ ጉባኤው ካጸደቀው ቋሚ ውሳኔ ይሆናል።

14.2 ቦርዱ ጠቅላላ ጉባኤውን ሳያማክር የሚከተሉትን የዲስፒሊን እርምጃዎች ሊወስድ ይችላላ።

14.2.1 ማስጠንቀቂያ

14.2.2 በቃል ወይንም በጽሑፍ ተግሳፅ/ወቀሳ

14.3 የሚከተሉት የዲስፒሊን እርምጃዎች ግን የጠቅላላው ጉባኤ ውሳኔ ያስፈልጋቸዋል።

14.3.1 በራስ ፈቃድ ሥራውን እንዲለቅ ዕድል መስጠት

14.3.2 ከኃላፊነት ማስወገድ (ማባረር)

14.3.3 ከመመረጥ፥ ከመምረጥና፣ ድምፅ ከመስጠት መብቶች ማገድ

14.3.4 ከአባልነት ማገድ

Page 25: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

25

14.4 የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደበት ግለሰብ ወደ ቤተክርስቲያኗ በመምጣት የሚሰጠውን የመንፈሳዊ አገልግሎት ከመሳተፍ አይነፈግም።

14.5 የቤተክርስቲያኗ ካህናትና የሌሎች አባላት የዲስፕሊን ጥያቄዎች የሚፈቱት በሃይማኖትና ባህላዊ ሕግጋት መሠረት ሲሆን በቦርዱና በሃይማኖት ጉዳይ ኮሚቴ ይካሄዳል። ጉዳዩ ዋናውን ቄስ የሚመለከት ከሆነ ወይም በጣም አሳሳቢ ከሆነ የቤተክርስቲያኑ አዛውንት ጉዳዩን አብረው እንዲፈቱት ቦርዱ ይጠይቃል። ይህ ካልሆነ በጠቅላላው ጉባኤ በአብዛኛው ድምፅ ብልጫ እንዲወሰን ይደረጋል።

===========================

አንቀጽ 15.0

መዛግብትና ዘገባዎች

15.1 ቦርዱ ይህን መተዳደሪያ ደንብ ከነማሻሻያዎቹ እና አትራፊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑን የሚገልፀው የምስክር ወረቀት በቤተክርስቲያኗ ዋና ጽሕፈት ቤት ያስቀምጣል። የውስጥ መተዳደሪያ ደንቡንም ሆነ የምስክር ወረቀቱ አግባብ ባለው የሥራ ጊዜ በአባላት ሊታዩ ይችላሉ።

15.2 የቦርዱና የኮሚቴዎች የስብሰባ ሂደት ቃለ ጉባኤዎች የሚቀመጡት በአንቀጽ 8.0 መሠረት በቤተ ክርስቲያኗ ዋና ጽሕፈት ቤት ወይንም ቦርዱ በመረጠው በቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኝ ቦታ ይሆናል።

15.3 አንድ አባል ጥያቄ ካቀረበና የቀረበውም ምክንያት በቂ ሆኖ ከተገኘ ከላይ የተጠቀሱት ሠነዶችና መዛግብት በአባላት ሊመረመሩና ሊታዩ ይችላሉ። ሆኖም ጉዳዩ የቤተክርስቲያኗን ጥቅም የሚፃረር ሆኖ ካገኘው ቦርዱ የአባሉን ጥያቄ የማሟላት ግዴታ የለበትም።

15.4 የቤተክርስቲያኗ መዛግብት በመዝገብ አያያዝ ሥርዓት መሠረት መደራጀት አለባቸው። ለማንም በተውሶ አይሰጡም።

===========================

አንቀጽ 16.0

ልዩ ልዩ ጉዳዮች

16.1 የመተዳደሪያ ደንቡን በሥራ ማዋል

16.1.1 ይህ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ በጠቅላላ ጉባኤው ሁለት ሶስተኛ (2/3) ድምፅ ከፀደቀ ይጸናል፥ በሥራ ላይ ይውላል።

16.1.2 በመተዳደሪያ ደንብ ላይ የማሻሻያ አንቀጾች ለመጨመር የጠቅላላ ጉባኤው በሁለት

ሶስተኛ (2/3) ድምፅ መጽደቅ አለባቸው።

16.1.3 የዚህ መተዳደሪያ ደንብና የማሻሻያዎቹ ግልባጭ የካሊፎርኒያ ስቴት መንግሥት ሕግ በሚጠይቀው መሠረት ተዘጋጅተው ይቀርባሉ።

Page 26: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

26

16.2 ተጠያቂነትና ካሣ፥ በሽፍጥ እና ሆነ ብሎ በማወቅ ላልፈጸሟቸው ጥፋቶች የቦርድ አባሎች፥ ሌሎች ተመራጮችና የቤተክርስቲያኗ አባሎች እያንዳንዳቸው ለቤተክርስቲያኗ ዕዳዎች ግዴታዎችና ኪሣራዎች በግል ተጠያቂ አይሆኑም። እያንዳንዱ የቦርድ አባል ወይንም ቤተክርስቲያኗን በተመራጭነት የሚያገለግል ሰው በቤተክርስቲያኗ የሥራ አላፊነት ተመድቦ በመሥራቱ ምክንያት ብቻ በማኅበረ ቤተክርስቲያኗ ላይ ለሚቀርቡ የአለኝታ ጥያቄዎች፣ የኪሣራዎች፣ የመቀጫና የቅጣት ጥያቄዎች፣ በግል በአላፊነት ያለመያዝ፣ ወይንም ያለመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል። ሆኖም አውቆ በሰራው የሽፍጥና የወንጀል ድርጊት ተግባሩ አግባብ ባለው ፍርድ ቤት የተበየነበት የቦርድ አባል ወይንም አገልጋይ ከወንጀሉ ነፃ አይሆንም።

16.3 ትርጉም፥

16.3.1 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ “ጉባኤ”፥ “ጠቅላላ ጉባኤ” “የቤተክርስቲያኗ አባላት

ስብሰባ” ወይንም ጉባኤ እየተባሉ የሠፈሩት ቃላት ወይንም ሐረገ ቃላት የቤተክርስቲያኗ አባሎች ጠቅላላ ጉባኤ ለማለት ጠቀሜታ ላይ የዋሉ ናቸው። ይህንኑ ለመግለጽ እንዲመች በተለዋዋጭነት ጠቃሜታ ላይ ውለዋል።

16.3.2 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ ምዕመናን የተባሉት በቤተክርስቲያኗ በየጊዜው እየተገኙ ጸሎት የሚያደርጉ ወይም በቤተክርስቲያኗ የሃይማኖትና የመንፈሳዊ አገልግሎት የሚጠቀሙ አማኞች ናቸው።

16.3.3 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የቤተክርስቲያኗ አባሎች ተብሎ እንደ አንድ ሰውነት ወይም ማህበር ሲነገር ስለ ቤተክርስቲያኗ መናገር ይሆናል። ስለ ቤተክርስቲያኗ ሲነገርም ስለ አባሎቿ መናገር ይሆናል።

====================================================================

Page 27: መተዳደሪያ ደንብ - Virgin Mary Ethiopian ... · 6.4.3 የበጀት ሪፖርት ለዓመታዊ ስብሰባው ... በሌለበት የቦርዱን ሊቀመንበር፥

27