7
ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. Ŧ Ɖ፥Ŧ Ɗ 1 ቁጥር - ነሐሴ ፪ሺህ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]m ባለፈው ስርጭት የፊልጵስዩስን መልእክት እንደምንካፈል አመልክቼ ከመልእክቱ በፊት ግን የቤተ ክርስቲያኒቱን ጅማሬ እንድንመለከት ታሪካዊ ዳራውን ወደምናገኝበት ክፍል ወደ ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 16 በመሄድ ተመልክተን ነበር። ከምዕራፍ 15ጥቂት ጨለፍ አድርገን የጳውሎስን ሁለተኛ ጉዞ አነሣስ አይተን ነበር። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ወደ መልእክቱ በመዝለቅ የላኪዎቹን ማንነት እንቃኛለን። አብረንም ተቀባዮቹንም እንመለከታለን። የዚህን መጣጥፍ ርእስ ከላይ እንደተጻፈው ያልኩት ከቅርብ ወራት ወዲህ ሐዋርያ የሚለው ቃልና ሹመት አነጋጋሪም፥ መስተባዕስም (የሚያጣላ) ሆኖ ስላገኘሁትና በዚህ ክፍል ጳውሎስ ስለ ራሱ ከሚናገረው አንጻርም ለማየት ስለወደድኩ ነው። እግረ መንገድ የቃሉን ዘመናዊ አዝማሚያም እነካለሁ። . ላኪዎች የዚህ መልእክት ጸሐፊዎች ጳውሎስና ጢሞቴዎስ ናቸው። ሁለቱንም በጥቂቱና በንጽጽር ብናያቸው የምንማርባቸው ነገሮች አሉ። ጢሞቴዎስ የመጀመሪያ ታሪኩ የሚገኘው በሐዋ. 161-3 የጳውሎስና ሲላስ ወደ ፊልጵስዩስ ጉዞ ላይ ነው። ባለፈው እንዳየነው ጳውሎስና ሲላስ ወደ ደርቤንና ልስጥራን በደረሱ ጊዜ ያገኙት ደቀ መዝሙር ነው። ደርቤንና ልስጥራን በኪልቅያ አውራጃ የሚገኙ ከተሞች ናቸው። ስለ ጢሞቴዎስ ከማየታችን በፊት ስለ ጳውሎስ ጥቂት ነጥቦችን እንይ። - ጳውሎስም ራሱ እንደ ጢሞቴዎስ የኪልቅያ አውራጃ ሰው ነው። በኪልቅያ የምትገኘው የጠርሴስ ተወላጅና ነዋሪ ነበረ፤ በገማልያል እግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 223 እና 2334ይህ ገማልያል በሐዋ. 534 የተጠቀሰው ይሁን ወይም ሌላ አናውቅም። ቢሆንም ባይሆንም ይህ ጳውሎስ በስሩ ሆኖ የተማረው ገማልያል ስመ ጥር አይሁዳዊ ይመስላል። የጳውሎስ አገላለጥ ይህን ያሳያል፤ ገማልያል በሚባል አስተማሪሳይሆን በገማልያል እግር አጠገብነው ያለው። ይህ ገማልያል እውቅ ሰው ይመስላል። ጳውሎስ ስለ ሕግና ስለ አይሁድ ሥርዓት ያለውን የጠለቀ እውቀት ስናጤን ይህ የጳውሎስ አስተማሪ ሊቅ መሆኑን መረዳት አዳጋች አይሆንም። - ጳውሎስ ጌታን ሲያገኝም ሆነ ከጢሞቴዎስ ጋር ሲገናኙ በዕድሜው ስንት መሆኑን አናውቅም፤ ከጢሞቴዎስ ጋር ሲነጻጸሩ አባትና ልጅ ሳይመስሉ አይቀሩም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ቢያንስ ጳውሎስ የበሰለ ሰው ሳይሆን እንደማይቀር ግን መገመቱ ጤናማና ተገቢ ነው። - ዕድሜ ብቻ አይደለም፤ በጣም የተማረ ሊቅም ነው። የአባቶችን ሕግ ጠንቅቆ የተማረ (ሐዋ. 223)ፈሪሳዊ (ሐዋ. 236265ፊል. 35)በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ያለ ነቀፋ የነበረ ሰው ነው (ፊል. 36)ፈሪሳውያን ለሕጉ ጥበቃ ከመጠንቀቃቸው የተነሣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙትን በጠቅላላ 613 ትእዛዛት በብዛት ሸንሽነውና አቅጥነው የሚጠበቁት ምን በማድረግና ባለማድረግ መሆኑን የወሰኑ (ከእንስላልና ከአዝሙድ አስራት የሚያወጡ ዓይነት) ሰዎች ናቸው። ጳውሎስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን ነቀፋ የሌለበት ፈሪሳዊ ነበረ። - ጉልህ ታሪክ ያለው ሰው ነው። ከጌታ በፊት ለአይሁድ እምነት የቀና ፈቃድ የተሰጠው የታመነ አሳዳጅ፥ ያውም አገር አቋራጭ አሳዳጅ ነበረ። - መለወጡና ወደ ጌታ አመጣጡም ትንግርት ነው። የተጻፈውን ስናነብም፥ እርሱ ሲናገርም የሚያስደምም ነው። - ከመጣ በኋላም የተሰጠው ጸጋና የቃሉ መረዳት ልዩ ነው። ከጻፋቸው መልእክቶችና ከተወልን ትምህርቶች የመረዳቱን ጥልቀት ማየት እንችላለን። - አገልግሎቱና መሰጠቱ የሚያስቀናና ፍሬያማ የሆነ ሰው ነው። ጢሞቴዎስስ? ጢሞቴዎስ ልጅ ነው። የተመሰከረለትና የተመሰገነ ደቀ መዝሙር ነው። አዲስ አማኝ ግን አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ ያመነ ሳይሆን ቀድሞም ደቀ መዝሙር የነበረ ሰው ነው። ቀድሞም የጌታ ተከታይ ተማሪ የሆነ ነው። እምነቱ ንጹሕና ግብዝነት የሌለበት ነው። ደግሞም ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ያመነ መሆኑና እናቱና አያቱም አማኞች መሆናቸው ይታወቃል፤ 2ጢሞ. 15ከልጅነቱ፥ እንዲያውም ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው በእምነትና በቃል እየተኮተኮተ ያደገው። ግማሽ አይሁድ ግማሽ ግሪክ የሆነ ሰው ነው። አባቱ ግሪካዊ ነው። በዕድሜው ምን ያህል መሆኑ በትክክል ባይታወቅም ወጣት መሆኑ ይታወቃል፤ 1ጢሞ. 411-12 ላይ ማንም ታናሽነቱን እንዳይንቅ ይነግረዋል። ይህ ታናሽነት’ (νεότητος) የተባለው ቃል ልጅነት፥ ለጋነት፥ አዲስነት፥ ወጣትነት እንደማለት ነው። እነዚህ ሁለት አገልጋዮች የዕድሜ ርቀታቸው፥ የታሪካቸው ልዩነት፥ የእውቀትና የብስለታቸው ጥልቀት መራራቅ አብረው እንዳያገለግሉ አላገዳቸውም። ለለጋው፥ ለትንሹ ከታላቅ ሰው ጋር ማገልገል የሚናፍቁት ነገር ነው። አልፎ አልፎ አንዳንዶች ትልልቆች ግን ንቀት ሊታይባቸው ይችላል። በተለይ ራሳቸውን ረጅም ቆጥ ላይ የሰቀሉ አገልጋዮች ከቆጣቸው ርዝመት የተነሣ ለሎችን በሙሉ የሚያዩት አዘቅዝቀው ስለሆነ እንደ አቻና እኩያ መታየትም ማየትም አይፈልጉም። ጳውሎስ ግን እንዲህ አይደለም። ጳውሎስ፥ ይኼ ውሪብሎ አልናቀውም። በውስጡ ያየው ነገር ነበረ። ጳውሎስ በታወቀው ገማልያል እግር አጠገብ መማሩና ጢሞቴዎስ በእናቱና በአያቱ ስር ሆኖ መማሩ ችግር አልነበረም። ጳውሎስ የሚያኮራው ነገር መኖሩ አላኮራውም። ይህኛው ደግሞ የሚያሳንሰው ነገር ቢኖርም አልተሸማቀቀም። አገልጋዮችን አንድ የሚያደርግ የጌታ መንፈስና፥ የልብ ቅንነትና፥ ጌታን መውደድና ነፍሳትን መውደድ ናቸው። ሁለቱም ተስተካክለው ጌታን አገለገሉ። እንደ ባሪያ። 1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤ ሁለቱም የጌታ ምኖች ናቸው? ባሪያዎች። ባሪያ የሚለውን ቃል አንዳንድ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች አይወዱትም። እንዲያውም እኛ ልጅ ነን እንጂ ባሪያ አይደለንም የሚለውን ቃል ወስደው ይህን ሊጠቀሙበትም አይወድዱም። ቢያስተውሉትማ ኖሮ ያንን ልጅ ነን እንጂ ባሪያ አይደለንምየሚሉትን ቃል (ገላ. 47) የጻፈው ራሱን ባሪያ ብሎ የሚጠራው ጳውሎስ ነው። (እዚያ እየተናገረ ያለው በሕግ ስር መሆን ባርነት መሆኑን ነው)ባሪያ የሚለውን ቃል አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችም አይወዱትም። የአማርኛ ትርጉሞችን ብቻ እንኳ ብንወስድ፥ ለምሳሌ፥ ይህን ፊል. 11ቀለል ባለ አማርኛ 1972 የተተረጎመው አዲሱ ትርጉም፥ ሕያው ቃል የተሰኘው 1977 ትርጉምና አዲሱ መደበኛ አገልጋዮች ባላቸው በምድራዊ መታወቂያቸው ምክንያት አብሮ ለማገልገል አለመቻል የለባቸውም። 1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤ www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!

The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

  • Upload
    others

  • View
    2

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 1

ቁጥር ፮ - ነሐሴ ፪ሺህ ፪ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]

ባለፈው ስርጭት የፊልጵስዩስን መልእክት እንደምንካፈል አመልክቼ ከመልእክቱ በፊት ግን የቤተ ክርስቲያኒቱን ጅማሬ እንድንመለከት ታሪካዊ ዳራውን ወደምናገኝበት ክፍል ወደ ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 16 በመሄድ ተመልክተን ነበር። ከምዕራፍ 15ም ጥቂት ጨለፍ አድርገን የጳውሎስን ሁለተኛ ጉዞ አነሣስ አይተን ነበር። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ወደ መልእክቱ በመዝለቅ የላኪዎቹን ማንነት እንቃኛለን። አብረንም ተቀባዮቹንም እንመለከታለን። የዚህን መጣጥፍ ርእስ ከላይ እንደተጻፈው ያልኩት ከቅርብ ወራት ወዲህ ሐዋርያ የሚለው ቃልና ሹመት አነጋጋሪም፥ መስተባዕስም (የሚያጣላ) ሆኖ ስላገኘሁትና በዚህ ክፍል ጳውሎስ ስለ ራሱ ከሚናገረው አንጻርም ለማየት ስለወደድኩ ነው። እግረ መንገድ የቃሉን ዘመናዊ አዝማሚያም እነካለሁ።

ሀ. ላኪዎች የዚህ መልእክት ጸሐፊዎች ጳውሎስና ጢሞቴዎስ ናቸው። ሁለቱንም በጥቂቱና በንጽጽር ብናያቸው የምንማርባቸው ነገሮች አሉ።

ጢሞቴዎስ የመጀመሪያ ታሪኩ የሚገኘው በሐዋ. 16፥1-3 የጳውሎስና

ሲላስ ወደ ፊልጵስዩስ ጉዞ ላይ ነው። ባለፈው እንዳየነው ጳውሎስና ሲላስ ወደ ደርቤንና ልስጥራን በደረሱ ጊዜ ያገኙት ደቀ መዝሙር ነው። ደርቤንና ልስጥራን በኪልቅያ አውራጃ የሚገኙ ከተሞች ናቸው። ስለ ጢሞቴዎስ ከማየታችን በፊት ስለ ጳውሎስ ጥቂት ነጥቦችን እንይ።

- ጳውሎስም ራሱ እንደ ጢሞቴዎስ የኪልቅያ አውራጃ ሰው ነው። በኪልቅያ የምትገኘው የጠርሴስ ተወላጅና ነዋሪ ነበረ፤ በገማልያል እግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና 23፥34። ይህ ገማልያል በሐዋ. 5፥34 የተጠቀሰው ይሁን ወይም ሌላ አናውቅም። ቢሆንም ባይሆንም ይህ ጳውሎስ በስሩ ሆኖ የተማረው ገማልያል ስመ ጥር አይሁዳዊ ይመስላል። የጳውሎስ አገላለጥ ይህን ያሳያል፤ ‘ገማልያል በሚባል አስተማሪ’ ሳይሆን ‘በገማልያል እግር አጠገብ’ ነው ያለው። ይህ ገማልያል እውቅ ሰው ይመስላል። ጳውሎስ ስለ ሕግና ስለ አይሁድ ሥርዓት ያለውን የጠለቀ እውቀት ስናጤን ይህ የጳውሎስ አስተማሪ ሊቅ መሆኑን መረዳት አዳጋች አይሆንም።

- ጳውሎስ ጌታን ሲያገኝም ሆነ ከጢሞቴዎስ ጋር ሲገናኙ በዕድሜው ስንት መሆኑን አናውቅም፤ ከጢሞቴዎስ ጋር ሲነጻጸሩ አባትና ልጅ ሳይመስሉ አይቀሩም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ቢያንስ ጳውሎስ የበሰለ ሰው ሳይሆን እንደማይቀር ግን መገመቱ ጤናማና ተገቢ ነው።

- ዕድሜ ብቻ አይደለም፤ በጣም የተማረ ሊቅም ነው። የአባቶችን ሕግ ጠንቅቆ የተማረ (ሐዋ. 22፥3)፥ ፈሪሳዊ (ሐዋ. 23፥6፤ 26፥5፤ ፊል. 3፥5)፥ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ያለ ነቀፋ የነበረ ሰው ነው (ፊል. 3፥6)። ፈሪሳውያን ለሕጉ ጥበቃ ከመጠንቀቃቸው የተነሣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙትን በጠቅላላ 613 ትእዛዛት በብዛት ሸንሽነውና አቅጥነው የሚጠበቁት ምን በማድረግና ባለማድረግ መሆኑን የወሰኑ

(ከእንስላልና ከአዝሙድ አስራት የሚያወጡ ዓይነት) ሰዎች ናቸው። ጳውሎስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን ነቀፋ የሌለበት ፈሪሳዊ ነበረ።

- ጉልህ ታሪክ ያለው ሰው ነው። ከጌታ በፊት ለአይሁድ እምነት የቀና ፈቃድ የተሰጠው የታመነ አሳዳጅ፥ ያውም አገር አቋራጭ አሳዳጅ ነበረ።

- መለወጡና ወደ ጌታ አመጣጡም ትንግርት ነው። የተጻፈውን ስናነብም፥ እርሱ ሲናገርም የሚያስደምም ነው።

- ከመጣ በኋላም የተሰጠው ጸጋና የቃሉ መረዳት ልዩ ነው። ከጻፋቸው መልእክቶችና ከተወልን ትምህርቶች የመረዳቱን ጥልቀት ማየት እንችላለን።

- አገልግሎቱና መሰጠቱ የሚያስቀናና ፍሬያማ የሆነ ሰው ነው።

ጢሞቴዎስስ? ጢሞቴዎስ ልጅ ነው። የተመሰከረለትና የተመሰገነ ደቀ መዝሙር ነው። አዲስ አማኝ ግን አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ ያመነ ሳይሆን ቀድሞም ደቀ መዝሙር የነበረ ሰው ነው። ቀድሞም የጌታ ተከታይ ተማሪ የሆነ ነው። እምነቱ ንጹሕና ግብዝነት የሌለበት ነው። ደግሞም ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ያመነ መሆኑና እናቱና አያቱም አማኞች መሆናቸው ይታወቃል፤ 2ጢሞ. 1፥5። ከልጅነቱ፥ እንዲያውም ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው በእምነትና በቃል እየተኮተኮተ ያደገው። ግማሽ አይሁድ ግማሽ ግሪክ የሆነ ሰው ነው። አባቱ ግሪካዊ ነው። በዕድሜው ምን ያህል መሆኑ በትክክል ባይታወቅም ወጣት መሆኑ ይታወቃል፤ በ1ጢሞ. 4፥11-12 ላይ

ማንም ታናሽነቱን እንዳይንቅ ይነግረዋል። ይህ ‘ታናሽነት’ (νεότητος) የተባለው ቃል ልጅነት፥ ለጋነት፥ አዲስነት፥ ወጣትነት እንደማለት ነው።

እነዚህ ሁለት አገልጋዮች የዕድሜ ርቀታቸው፥ የታሪካቸው ልዩነት፥ የእውቀትና የብስለታቸው ጥልቀት መራራቅ አብረው እንዳያገለግሉ አላገዳቸውም። ለለጋው፥ ለትንሹ ከታላቅ ሰው ጋር ማገልገል የሚናፍቁት ነገር ነው። አልፎ አልፎ አንዳንዶች ትልልቆች ግን ንቀት ሊታይባቸው ይችላል። በተለይ ራሳቸውን ረጅም ቆጥ ላይ የሰቀሉ አገልጋዮች ከቆጣቸው ርዝመት የተነሣ ለሎችን በሙሉ የሚያዩት አዘቅዝቀው ስለሆነ እንደ አቻና እኩያ መታየትም ማየትም አይፈልጉም።

ጳውሎስ ግን እንዲህ አይደለም። ጳውሎስ፥ ‘ይኼ ውሪ’ ብሎ አልናቀውም። በውስጡ ያየው ነገር ነበረ። ጳውሎስ በታወቀው ገማልያል እግር አጠገብ መማሩና ጢሞቴዎስ በእናቱና በአያቱ ስር ሆኖ መማሩ ችግር አልነበረም። ጳውሎስ የሚያኮራው ነገር መኖሩ አላኮራውም። ይህኛው ደግሞ የሚያሳንሰው ነገር ቢኖርም አልተሸማቀቀም። አገልጋዮችን አንድ የሚያደርግ የጌታ መንፈስና፥ የልብ ቅንነትና፥ ጌታን መውደድና ነፍሳትን መውደድ ናቸው። ሁለቱም ተስተካክለው ጌታን አገለገሉ። እንደ ባሪያ።

1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤

ሁለቱም የጌታ ምኖች ናቸው? ባሪያዎች። ባሪያ የሚለውን ቃል አንዳንድ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች አይወዱትም። እንዲያውም እኛ ልጅ ነን እንጂ ባሪያ አይደለንም የሚለውን ቃል ወስደው ይህን ሊጠቀሙበትም አይወድዱም። ቢያስተውሉትማ ኖሮ ያንን ‘ልጅ ነን እንጂ ባሪያ አይደለንም’ የሚሉትን ቃል (ገላ. 4፥7) የጻፈው ራሱን ባሪያ ብሎ የሚጠራው ጳውሎስ ነው። (እዚያ እየተናገረ ያለው በሕግ ስር መሆን ባርነት መሆኑን ነው)።

ባሪያ የሚለውን ቃል አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችም አይወዱትም። የአማርኛ ትርጉሞችን ብቻ እንኳ ብንወስድ፥ ለምሳሌ፥ ይህን ፊል. 1፥1ን ቀለል ባለ አማርኛ በ1972 የተተረጎመው አዲሱ ትርጉም፥ ሕያው ቃል የተሰኘው የ1977 ትርጉምና አዲሱ መደበኛ

አገልጋዮች ባላቸው በምድራዊ መታወቂያቸው ምክንያት አብሮ ለማገልገል አለመቻል የለባቸውም።

1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤

www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!

Page 2: The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 2

ቁጥር ፮ - ነሐሴ ፪ሺህ ፪ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]

ትርጉም ‘አገልጋይ’ ሲሉ ተርጉመውታል። ቃሉ ባሪያዎች (δοῦλοι) ሲለው እነርሱ ግን አገልጋይ ያሰኙታል። ስሕተት ነው። በአገልጋይና በባሪያ መካከል ልዩነት አለ። አገልጋይ ለጉልበቱ፥ ለሰዓቱ፥ ለእውቀቱ የሚከፈለው ሠራተኛ ነው። ለመኖር ሲል ለአሠሪው ይሰራል፤ አልሠራም ካለም ግዴታ የለበትም። መኖሪያ ገንዘብ ካለው የራሱ ሰው ነው፤ ከሌልለው ደግሞ ሌላ መሥሪያ ቦታ ሄዶ፥ ሌላ ሥራ ፈልጎ ይሠራል። ባሪያ ግን እንዲህ አይደለም። በዚህ ዘመን ባሪያ ስለሌለ ባሪያ የሚለውን ቃል በዚህ ዘመን ባለው እንተካ ብለን የትርጉም ሥራን ቀሊል አድርገን የግብር ይውጣ ሥራ መሥራት ስንፍና ነው። ቃሉ በዘመኑ እንዲህ የመሰለ ነገር ነው ብሎ ከማስታወሻ ጋር ማስቀመጡ ተገቢ ነበር። አገልጋይ ለሚለው ቃል አዲስ ኪዳን የተጻፈበት ቋንቋ ሌላ ቃላት አሉት። አንዱን ወደ ኋላ እንመለከተዋለን። ይህ ቃል ግን ባሪያ ነው።

በዚህ ዘመን ባሪያ አይተንም ሰምተንም አናውቅም። በዚያን ዘመን ግን ባርነት የተለመደ ሥርዓት ነው። ዛሬ ሠራተኛ ሆነን እንቀጠራለን ወይም አሠሪ ከሆንን እንቀጥራለን እንጂ የሚሠራልንን ወይም የሚያገለግለንን ሰው ገበያ ሄደን እንደ በግ ወይም እንደ ልብስ አንገዛም። ያኔ ግን ባሪያ ማለት ይህ ነው፤ ከገበያ ስፍራ በጨረታ ወይም ያለጨረታ የሚገዛ፥ በገንዘብ የተሸመተ ሰው ነው። ስለዚህ አገልጋይ ብቻ አይደለም፤ የተገዛ አገልጋይ ነው። ንብረት ነው። ሴት ከሆነች ዕድሜዋና ጤንነቷ፥ ወንድ ከሆነ ጥንካሬው፥ ጉልበቱ፥ ትከሻው፥ ባቱ፥ ጥርሱ ታይቶ ይገዛል። ያ ባሪያ ይባላል። ያ ባሪያ ከዚያ በኋላ የሰውየው ንብረት ነው። አንዳንድ የባሪያዎች ጌቶች በባሪያዎቻቸው ሰውነት ላይ የጥብሳት ወይም የንቅሳት ምልክትም ያስከትባሉ። የተገዛ ንብረት ነውና ያንን ባሪያ ከገዥው በቀር ‘የኔ’ የሚለው ሌላ ሰው የለም። ራሱም እንኳ፥ ‘እኔ የኔ ነኝ’ ማለት አይችልም። ‘እኔ የጌታዬ ነኝ’ ነው የሚለው። በየትም አገር ቢኖር የአገሩ ዜግነት የለውም። መብትም የለውም። ጌታው ከፈለገ ነፃ ሊያወጣው ይችላል፤ ከፈለገ ምግብ ሊከለክለው ይችላል፤ ከፈለገ ሊገድለውም ይችላል። ሕግ ሳይጠይቀው ሊገድለውም እንኳ ይችላል።

ጳውሎስ ራሱንና ጢሞቴዎስን ምን አለ? የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ። በሌላ ሹመት ወይም በሌላ ማዕረግ አልጠራም። ዛሬ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ባሪያ ወይም አገልጋይ በሚል ቃል አይጠሩም። አቡን፥ ጳጳስ፥ ሊቀ ጳጳስ፥ ሐዋርያ፥ ቄስ፥ መጋቢ፥ ወዘተ፥ ይባላሉ። መጋቢ ወይም እረኛ የምትባለው የአማርኛ ቃል ብዙም አትጥማቸውምና ‘ፓስተር’ የምትለዋን ቃል ይወዷታል፤ እንዲያውም እንዲያ ተብሎ ለመጠራት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የሌለ ብዙ ቀጣፊዎች አሉ። ያልተማረውን ስነ መለኮት እንደተማረ አድርጎ ዋሽቶ እንዲመግብ የተሾመ ሰው አውቃለሁ። ቅጥፈት ነው። ይህ ሲታወቅበት ከመንጋው ገምሶ እዚያው ከተማ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ጀመረ። ጥሪና ጸጋው ሳይኖረው አለኝ ብሎ ፓስተር ተሰኝቶ መንጋውን ያመሰና ቤተ ክርስቲያንን ያመሳቀለ ሰው በከተማችን አውቃለሁ። ቅጥፈት ነው። በገዛ ጉልበቱ የጀመረው ሥራ ጉልበቱ ሲነጥፍበት ‘አገልግሎቱን’ በገዛ እጁ ጥሎ ወደ መዝገብ ያዥነት ሥራው ተመለሰ። በኩረጃ መጋቢ የሚሆኑ ሰዎችም አሉ። ከአለባበስ እስከ ድምጽ አወጣጥና እጅ አወዛወዝ ሳይቀር ይኮርጃሉ። ጸጋ ሳይጠፋ፥ ለጋስ አምላክ ሳለ ኩረጃ አሳፋሪ አገልግሎት ነው።

አንዳንዶች በዓለ ሢመት (የሹመት በዓል) ተዘጋጅቶ ሐዋርያ ተብለውም ሲሾሙ ይታያል። ሹመት ያዳብር አንዳይሉት ግራ የሆነ ነገር ነው። ሢመት ወይም ሹመት መሆኑ ነው የከፋው። ጌታ ሲጸልይ አድሮ አሥራ ሁለቱን መርጦ “ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው” ይለናል ወንጌሉ፤ ሉቃ. 6፥13። ሥልጣንንን ሰጥቶአቸዋልና ይህ ይሆን ሹመት ያሰኘው? ቃሉ

‘ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው’ (ἀποστόλους ὠνόμασε) ሲል

ሐዋርያት አላቸው፥ ብሎ ጠራቸው ነው እንጂ ሾማቸው አይደለም። ሕያው ትርጉም ሾማቸው ይለዋል፤ ቃሉ እንደዚያ ስለማይል ሌላ ስሕተት። ሐዋርያ ወይም ሐዋርያነት ሹመት አይደለም። እንኳን ዛሬ በ2002፥ ያኔ በጌታችን አገልግሎት ዘመንም ሹመት አልነበረም። ሹመት ነው ቢባልም እንኳ ከ12ቱ በኋላ ያልተደገመ ነውና አያከራክርም።

ለ. ሁለት ዓይነት ሐዋርያት ሐዋርያት ሁለት ዓይነት ናቸው። ስለዚህ ‘ሐዋርያ’ የሚለው ቃል 12ቱን ጌታ የሰየማቸውን የሚያመለክት ቃል ብቻ አይደለም። እርግጥ እነዚያ አሥራ ሁለቱ በተለየ፥ በጌታ በራሱ የተጠሩ፥ አብረውት የቆዩ፥ አብረውት ወጥተው የገቡ፥ ትምህርቱን በስማ በለው ሳይሆን በቀጥታ የሰሙ፥ ተአምራቱን ያዩ፥ ከአገልግሎቱ መጀመሪያ እስከ ሞቱና ትንሣኤው ድረስ የተከተሉት የዓይን ምስክሮችም ናቸው። የአስቆሮቱ ይሁዳ ከሞተ በኋላ በምትኩ ማትያስ የተመረጠበትን መስፈርት እነዚህ የኋለኞቹ ሆነው እናገኛቸዋለን። ሐዋ. 1፥21-22 እንዲህ ይላል፥ ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል። አሥራ ሁለተኛ ሐዋርያ መምረጥ ለምን እንዳስፈለጋቸው አናውቅም። በጎዶሎ ቁጥር ላለመጀመር ይሆናል። ይሁን እንጂ መለኪያው ጥብቅ ሆኖ ይታያል። ከዚህ ክፍል ሳንወጣ የይሁዳ ምትክ ማትያስ ከተመረጠበት ክፍል ሦስት ጉልህ አሳቦችን ማየት ጥሩ ነው።

ሐዋ. 1፥17 ከእኛ ጋር ተቈጥሮ ነበርና፥ ለዚህም አገልግሎት ታድሎ ነበርና። ከዚህ ጥቅስ ይህ ሐዋርያነት መታደልና አገልግሎት እንደሆነ ጴጥሮስ መናገሩን እናስተውላለን። ጌታ ስለመረጣቸው ከራሳቸው የሆነ የውስጣዊ ብቃት ኩራት ሊኖራቸው አይችልም። ይህ መታደል ነው፤ ድንቅ እድል ፈንታ ነው። ሐዋርያነት ደግሞም አገልግሎት ነው። ሥራና ተግባር ሆኖ ዝቅታና ትኅትናም ያለበት ነው።

ሐዋ. 1፥20 በመዝሙር መጽሐፍ። መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባትም አይኑር፤ ደግሞም፦ ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት ተብሎ ተጽፎአልና። እዚህ ሹመት የሚል ቃል ተጽፎአል። በሚቀጥለው ጥቅስም ሹመት ተሰኝቶአል። ጥቅሱ ከመዝሙረ ዳዊት ከሁለት ቦታዎች ተወስዶ የተሠራ ነው (መዝ. 69፥25 እና 109፥8) ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤ ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ። የሚሉ ናቸው። ሐዋርያነትን እንደ ደጃዝማችነት ያለ ሹመት ሳይሆን አደራና ኃላፊነት መሆኑን ቃሉን

በቦታው እንይ። ሹመቱን የሚለው ቃል τὴν ἐπισκοπὴν αὐτοῦ ‘ቴን ኤፒስኮፔን አውቱ’ የሚል ነው። ከቃሉ ድምጽም እንደምንረዳው ሳይተረጎም ቃሉ እንደተሰጠን ይህ ኤጲስ ቆጶስ የሚለው ቃል ነው። ቃሉ

በዕብራይስጥ ሹመት ፕቁዳህ ሲሆን (ሹመቱ ፕቁዳሁ פקדתו) ሆኖ ትርጉሙ ጉብኝት፥ ኃላፊነት፥ አደራ፥ ከላይ ሆኖ መመልከት፥ መቁጠር ወይም መቆጣጠር ማለት ነው። ብሉይ ኪዳንን አዲስ ኪዳን በተጻፈበት የግሪክ ቋንቋ የተረጎመው የሰብትዋጅንት (ሰባ ሊቃናት) ትርጉም ይህን

ቃል ἐπισκοπὴν ይለዋል። ከአዲስ ኪዳኑ ቃል ጋር አንድ ነው። ኤጲስ ቆጶስ (አጻጻፉ መሆን የነበረበት ኤጲ እስቆጶስ ነው) ኤጲ ከላይ መሆንን እስቆጶስ ማየትን፥ የሚያይ መሆንን የሚገልጡ ናቸው። ኤጲስ ቆጶስ ማለት ከላይ ሆኖ የሚያይ ማለት ነው። ሐዋርያነትንም ሆነ ሌሎቹን አገልግሎቶች ዘመናዊውን ሹመት ወይም ሥልጣን ያስመሰለው ይህ አሳብ ሳይሆን አይቀርም። ኤጲስ ቆጶስ የሚለው ቃል በዚህ በምናጠናው በፊል. 1፥1ም የተጻፈ ሲሆን በአዲስ ኪዳን በሌሎች ሦስት ስፍራዎች ተጽፎአል (1ጢሞ. 3፥1-2 እና ቲቶ 1፥7)። በሐዋ. 20፥28 ጳጳሳት የሚለው ቃልም ጳጳሳት ሳይሆን ይህ ኤጲስ ቆጶስ የሚል ቃል ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ ከላይ ሆኖ የሚያይ ኃላፊ እና ባለአደራ ማለት

የጌታ አገልጋይ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እንደ ጸጋው በሌላ ስያሜ ሊጠራም ይችላል። ነገር ግን አገልጋይ ነው። አገልጋይ ባሪያ ነው።

www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!

Page 3: The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 3

ቁጥር ፮ - ነሐሴ ፪ሺህ ፪ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]

ነው። የሐዋርያትን አመራረጥ ሹመት ነው ብንለው እንኳ መሠልጠንና ገዥነት አልታየባቸውም። ደግሞም ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያው እርከንና በጌታ የተደረገ ነውና ያልተደገመ ሹመት ነው።

ሐዋ. 1፥24-25 ሲጸልዩም፥ የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፥ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው አሉ። ሹመው የሚለው ቃል የመረጥኸውን ግለጠው፥ አሳየው

የሚል ነው። ቃሉ ἀνάδειξον ግልጥ መውጣትን መታየትን አመልካች ነው። ደግሞም ዕጣ ሊጣል ነውና ጸሎታቸው ይህ ግልጥነት ነበረ። ከነዚህ ከሁለቱ አንዱን ግለጠው፥ አሳየው፥ ገሃድ አድርገው ነው ያሉት።

የመጀመሪያዎቹን ሐዋርያት እንዲህ ካየን ሐዋርያ የሚለውን ቃል ሁለተኛ ትርጉም እንመልከት። ሐዋርያ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው። ሐዋርያ የሚለው የአማርኛ ቃል ሖረ ወይም ሐወረ (ሄደ) ከሚለው የግዕዝ ስር የወጣና የሄደ፥ እንዲሄድ የተደረገ፥ የተላከ፥ ማለት ነው። ይህ በጥሬው የቃሉ ትርጉም ነው። በአዲስ ኪዳናዊ ትርጉሙ ደግሞ ጌታ የላከው፥ ወንጌል አስይዛ ቤተ ክርስቲያን የላከችው፥ ከኃላፊነት፥ ከአደራ ጋር ዓላማና ግብ ባለው ተልእኮ የተሰማራ መልእክተኛ ማለት ነው። ሐዋርያ ማለት ወንጌል ወዳልተነገረበት ስፍራ የምሥራቹን እንዲሰብክ የተላከ ሰው ነው። በቃ ይኸው ነው። ሌላ ትርጉም የለውም። ጌታ የሰየማቸው 12ቱ ከስያሜው በኋላ ሲልካቸው፥ ሲሄዱና ሲሰብኩ ነው የምናነብበው። ስያሜውና ሥራው የተከታተሉትም ስለዚያ ነው። በአዲስ ኪዳን ይህ ስጦታ ከሌሎች የጸጋ ስጦታዎች ጋር ተጽፎ ይገኛል፤ ሮሜ. 1፥5፤ 1ቆሮ. 12፥28-29፤ ኤፌ. 4፥11። እነዚህ ባለሥልጣኖችና ሹሞች ሳይሆኑ አዋጅ ነጋሪዎች ናቸው። የምሥራቹን ቃል ወንጌሉን አብሳሪዎች ናቸው። ይህ ስጦታ እንደ ሥልጣንና አገዛዝ ሳይሆን እንደ ጸጋና እንደ ስጦታ ዛሬም አለ፤ በቤተ ክርስቲያን ዘመንም ሁሉ ይኖራል።

የዘንድሮ ሐዋርያት የሆሩ ወይም የሐወሩ ሐዋርያት፥ የሄዱ መልእክተኞች፥ ቤተ ክርስቲያን ወንጌል አስጨብጣ፥ መርቃ፥ ወንጌል ወዳልሰሙት የሰደደቻቸው ከሆኑ እሰይ ነው። መልካም ተግባር፥ ውብ ስጦታ፥ ድንቅ ጥሪ፥ ትልቅ ሸክምና ኃላፊነትም ነው። ግን እንደ ጀነራል ወይም ሊቀ መንበር የመሰለ ሹመት ሲሆንና የበዓለ ሢመት ድግስ ሲደገስ ያ ሰው መልእክተኛ ሳይሆን ሌላ ነገር መሆኑ ነው። በነዚህ ዓመታት በምስል ያየኋቸውና ያደመጥኳቸው የዘመናችን ‘ሐዋርያት’ ብለው በራሳቸው እጅ ራሳቸውን የቀቡ ሰዎች ግን እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት በካህናት ላይ ከፍ ሊሉ የሚወዱ፥ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ብቸኛ ቶምቦላ የወጣላቸው የሚመስላቸው፥ በአገልጋዮችና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ሊሰለጥኑ በኩራት የሚራመዱ ባለ ልዩ ማዕረግተኞች ሲመስሉ ታዝቤአለሁ። አንዳንድ አላስተዋይ አገልጋዮችና የዋህ ምእመናንም ሐዋርያነትን ከመጋቢነት ወይም ይህን ከመሰለው አገልግሎት ከፍ ያለው ደረጃና እርከን አድርገው ተቀብለውታል። ልክ መጋቢ ዲፕሎማ ከሆነ ሐዋርያ ዲግሪ እንደሆነ አድርገው አይተውታል።

ጳውሎስን የመሰለ ሐዋርያ በቃሉ ውስጥ አላየሁም። የላከችው የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ግን መለከት አስነፍታና ቃለ አዋዲ አስነግራ፥ ጉባኤ አስጠርታና ድግስ ደግሳ ሳይሆን ጸልያ፥ እጅ ጭና ነው የላከችው፤ ሐዋ. 13፥1-3። ተልእኮውን ሲፈጽምም ወደዚያችው ወደላከችው አጥቢያ ተመልሶ ዘገባ ያቀርብ ነበር፤ ሐዋ. 14፥26-28። ጳውሎስም ራሱን ሐዋርያ፥ መጋቢ፥ አስተማሪ ብሎ ጠርቷልና እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሐዋርያ፥ መጋቢ፥ ጳጳስ፥ ወዘተ፥ የሚባሉት ስሞች ከኃላፊነት ጋር ተቋጥረው ከሆነ ክፋት የለበትም። መመጻደቂያና እንደ ቃሉ ትርጉም የሆነ አገልግሎት ካልሆነ ግን ችግር አለበት። አገልግሎት ሳይሆን ሥልጣን ከሆነ ደግሞ ችግር ብቻ ሳይሆን ክፋትም አለበት።

ጳውሎስ ጥቂት ባልሆኑ መልእክቶቹ፥ ራሱን ሐዋርያ (ማለትም መልእክተኛ) እያለ ጠርቶአል። እዚህ ለፊልጵስዩስ ምእመናን ግን ባሪያ ማለቱ በምን ምክንያት ይሆን? ራሱን እንዲህ ሐዋርያ እያለ ከጠራባቸው ቦታዎች ቦታዎች መካከል እነዚህ ይገኛሉ፤ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ (ሮሜ. 1፥1)፥ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ (1ቆሮ. 1፥1)፥ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ (2ቆሮ. 1፥1)፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ (ገላ. 1፥1)፥ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ (ኤፌ. 1፥1)። ታዲያ እዚህ ስለምን ራሱን ባሪያ አለ?

ባለፈው መግቢያውን (ሐዋ. 16ን) ስንመለከት ፊልጵስዩስ የሮም ቅኝ ከተማ መሆኗን አይተን ነበር። ይህ ማለት ከተማዋ ወይም የከተማዋ ሕጋዊ ነዋሪዎች ነፃነትና የሮም ዜግነት ከሙሉ መብቱ ጋር የተሰጣቸው ሰዎች ናቸው። ፊልጵስዩስ የሮሜ ዜግነት በቅኝነቷ ምክንያት በሮሜ መንግሥት ቸርነት እንዲያው የተሰጣት ከተማ ናት። የከተማዋ ሕጋዊ ነዋሪ ሁሉ ባሪያ ተብሎ የማይጠራባት፥ በዜግነቱ፥ በመብቱ የሚኮራባት ከተማ ናት። እንደዚህ ባለች ከተማ ለሚኖሩ አማኞች፥ ባርነት ጸያፍና ነውር በሆነበት ሥርዓት ባሪያ ብሎ ራስን ማስተዋወቅ ያሳፍራል። ግን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች ብሎ ጻፈ።

ደግሞም ሐዋ 16ን ስናይ ራሱም የሮሜ ዜጋ ሳለ የሮሜ ዜግነቱን እንዳልተጠቀመበትም ተመልክተናል። በተደበደበ በማግስቱ ግን አንድ ቤተ ሰብ በግሩም ወደ ጌታ ከመጣ በኋላ ዜጋ መሆኑን ተናገረ። በመብትና በነፃነት በሚኩራሩ ሰዎች መካከል ኃላፊነትና ግዴታን የሚያውቅና የሚያሳውቅ ሰው መኖሩ አስፈላጊ ነው። ጌታ ያላቸው፥ ባለቤት ያላቸው፥ የወደደውን የሚያደርግ፥ ወደፈለገበት የሚልክ፥ ሲፈልግ ተነሡ፥ ሲፈልግ ተቀመጡ የሚል ባለቤት ያላቸው ባሪያዎች ናቸው ጳውሎስና ጢሞቴዎስ።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስናነብብ ጳውሎስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሐዋርያትም ራሳቸውን እንደ ባሪያ አስተዋውቀዋል። ለምሳሌ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ (2ጴጥ. 1፥1)፤ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥ (ራእ. 1፥1)። ያዕቆብና ይሁዳም እንዲሁ ብለዋል፤ የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ (ያዕ. 1፥1)፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ (ይሁ. 1)።

ጳውሎስ በዚህ በፊልጵስዩስ መልእክቱ ስለ ጌታችን እንኳ ሲናገር (ፊል. 2፥7) ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ ይላል። የጌታን የባሪያ መልክ በገለጠበት መልእክት ራሱን እንደ ባሪያ ባያቀርብ ስሕተት ስለሚሆን ብቻ ሳይሆን በእርግጥም በዋጋ የተገዛ ባሪያ መሆኑን ስላወቀ ነው ይህን ባሪያ የሚል ቃል የተጠቀመው። የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ያስተማረው ራሱ ጌታችንም አገልግለን ስናበቃ፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ አለ፤ ሉቃ. 17፥10። እንግዲህ ሐዋርያ ባሪያ ነው።

ሐ. ተቀባዮች

ላኪዎቹ ባሪያዎቹ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ ሲሆኑ ተቀባዮቹ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ ናቸው። የሐረጉ ኃይለ ቃል ያለው የመጨረሻው ቃል ላይ ነው። ተቀባዮቹ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱሳን ሆነው አብረው ተቀባዮቹ ኤጲስ ቆጶሳቱና ዲያቆናቱ ናቸው።

ቅዱሳን የሚለው ቃል ሰፊ ነው። ቅዱስ ማለት በጥሬ ትርጉሙ የተለየ ማለት ነው። ቅድስና ሦስት ደረጃዎች አሉት። በቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ጭብጥ ሳስተምር ለመያዝና ለማስታወስ እንዲረዳ ሦስቱን ደረጃዎች በ

ሐዋርያነት ለወንጌል ሰባኪነት የተላኩ መሆን ነው እንጂ ባለ ሥልጣንነት ወይም ሹመት፥ ማዕረግ አይደለም።

www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!

Page 4: The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 4

ቁጥር ፮ - ነሐሴ ፪ሺህ ፪ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]

‘ፍ’ በሚጀምሩ ቃላት አስቀምጫቸው አስተምሬ ነበር። ፍልሰታዊ፥ ፍኖታዊ፥ ፍጹም። ያለ ሰፊ ትንታኔ ሦስቱንም በጥቂት ላብራራ።

ፍልሰታዊ ቅድስና ስፍራዊ ለውጥ የሚያመጣው ቅድስና ነው። ቀድሞ በዓለም ነበርን፤ አሁን ከዓለም ወጥተን በክርስቶስ ሆንን። ይህ በአካል ከዓለም መውጣት ሳይሆን በመንፈስ ከዓለማዊነት መውጣት ነው። ከሰይጣን ግዛትና አገዛዝ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት ፈለስን። ይህ ፍልሰታዊ የቦታ ለውጥ ቅዱሳን አድርጎናል። ስለዚህ ማንም ጌታን የተቀበለ ሰው ወደ ክርስቶስ ሲገባ በክርስቶስ ሲሆን ቅዱስ ይባላል። ደካማ ቢሆን ብርቱ፥ ታታሪ አገልጋይ ቢሆን ወይም ውዝፍ ግን ቅዱስ ነው። ጳውሎስ የፊልጵስዩስን ምዕመናን ቅዱሳን ሲል ይህን ማለቱ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ ነው ያለው፤ እናም በእርሱ በክርስቶስ ላሉት፥ በእርሱ ውስጥ ላሉት በማለት ስፍራቸውን፥ ቦታቸውን መናገሩ ነው። እነዚህ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ውስጥ ሆነዋልና ቅዱሳን ናቸው። ይህ ስፍራዊ ቅድስና ግን የክርስትና ድምዳሜው አይደለም። ሌሎች ሁለት ደረጃዎችም መረገጥ አለባቸው።

ፍኖታዊ ቅድስና የጉዞ፥ የአመላለስ፥ የአካሄድ ቅድስና ነው። ፍኖት ማለት ጎዳና፥ መንገድ፥ መመላለሻ ማለት ነው። ፍኖታዊ ቅድስና ፍልሰታዊ ቅድስናን መከተል ይጠበቅበታል። አንድ ሰው ክርስቲያን ከሆነ በኋላ በመንገዱ ላይ (የቀጠነ መንገድ ይላታል ጌታ) የሚመላለስ ሊሆን ተገቢ ነው። ይህ አመላለስ ለጌታ እንደሚገባ የተባለ አመላለስ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የመደገፍና በእርሱ ቁጥጥር ስር የመሆን ኑሮ ነው። ክርስቶስን ለመምሰል መንጠራራት ወይም መዘርጋት ነው።

ፍጹም ቅድስና ወደፊት ጌታን ስናየው የምንሆነው ሁኔታ ነው። በዚህች ምድርና በዚህ ሥጋ ውስጥ ሆነን ፍጹም ለመሆን እንተጋለን እንጂ ሆነን አናበቃም። ግን ጌታ ይመስገን፥ አንድ ቀን ፍጹም ቅድስናን እንቀዳጅና ለዘላለም ቅዱሳን ሆነን እንኖራለን።

በመልእክቱ ውስጥ የቅድስናን ኑሮ እንዴት መኖር እንዳለባቸው በርካታ ተግባራዊ ምክሮችን ሰጥቶአቸዋል። ሆኖም ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ምእመናን ቅዱሳን ብሎ ሲጽፍላቸው የመጀመሪያውን በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆናቸው የሆኑትን ቅድስና መጥቀሱ ነው።

ጳውሎስ የጻፈላቸው የደብዳቤው ተቀባዮች የፊልጵስዩስ ቅዱሳን ሆነው የተቀበሉት ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር ነው። ኤጲስ ቆጶስ የሚለውን ቃል ቀደም ሲል ስላየነው እዚህ ማብራራቱ ድግግሞሽ ነው። ዲያቆን ማለት የጉልበትም፥ የአእምሮም፥ የጥበብም ሥራ የሚሠራ ሠራተኛ ወይም አገልጋይ ማለት ነው። ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አንጻር ስናየው የአገልግሎቱ ግብ በመንፈሳዊው አገልግሎት ዘርፍ፥ በተለይም ቃሉን በማስተማር የሚተጉት በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ሥራዎችና ተግባራት እንዳይጠመዱ ከትከሻቸው ይህንን የተግባር ኃላፊነት መውሰድና ማቅለል ነው። በቤተ ክርስቲያን የአገልግሎቱን ጅማሬ የምናየው በሐዋ. 6 ነው። በሐዋ. 6፥2-4 አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው። የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም። ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤ እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን ይላል። በጥቅሱ ውስጥ

ያሰመርኩበት ሐረግ διακονεῖν τραπέζαις (ዲያኮኔዪን ትራፔዛይስ ጠረጴዛ እናገለግል ዘንድ) የሚለው ዲያቆን የሚለው አገልግሎትና ስያሜ በቤተ ክርስቲያን ጅማሬ ነው። እንግዲህ እነዚህ የተመረጡት ሰባት ሰዎች አገልጋዮች፥ ሠራተኞች፥ ዲያቆናት፥ የቃሉና የጸሎት ሥራ እንዲሮጥ እነዚያን የሚረዱ ረዳቶች ወይም አርድዕት ናቸው።

በፊልጵስዩስ መልእክት ውስጥ ልብ ልንል የሚገባን ሌላ ትልቅ ነጥብ ኤጲስ ቆጶሳቱና ዲያቆናቱ አንድ ሳይሆን ብዙ መሆናቸውን ነው። ይህ የሚያሳየን በቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ ዋና መሪ ሳይሆን የቡድን መሪዎች መኖራቸውን ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው ብቻውን ልፋት

ከሆነ መልፋት፥ ሥልጣን ከሆነም መሰልጠን የለበትም። በእርግጥ መሪ የሚሆን፥ ቀዳሚ፥ ዋነኛ የሚሆን ሰው ማስፈለጉ እውነት ነው። ጤናማ የቤተ ክርስቲያን አመራር ግን አንድ ሰው በአምባ ላይ የሚገንንበት ሳይሆን የቡድን አመራር ነው። የፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን ጳውሎስ መልእክት ከጻፈላቸው ቤተ ክርስቲያኖች ሁሉ በውበትና በደስታ፥ በአገልግሎትና በትጋት፥ በስደትና በመጽናት የተመሰገነች ቤተ ክርስቲያን ናት። ትመራ የነበረውም በአንድ ሰው ሳይሆን በቡድን መሪዎች ነበረ።

የቡድን አመራር ከጥንት ከመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያንም ጀምሮ የነበረ ሁነኛው የአጥቢያ ቤተ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ስልት ነው። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የተመራችው በሐዋርያትና በሽማግሌዎች ነበር። ግዝረትን የተመለከተው የመጀመሪያው የአስተምግሮ ውዝግብ በተከሰተ ጊዜ ሊፈቱ የተቀመጡት እነዚህ ነበሩ፤ ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ፤ ሐዋ.15፥6። በጉባኤው ጴጥሮስና ያዕቆብ የጎላ ነገር መናገራቸው ተጽፎአል። የጴጥሮስ ጉልህነቱ ለአሕዛብ ወንጌልን ለመስበክ የመጀመሪያው ሰው መሆኑ እንጂ መሪነቱ አልነበረም። በምዕራፉ መጨረሻ ችግሩ ለተከሰተባት ለአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ደብዳቤ ሲጽፉ ላኪዎቹ ‘ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም’ እንዲሁም ‘እኛና መንፈስ ቅዱስ’ ብለው ነበር የጻፉት፤ ሐዋ. 15፥23-29። የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን አመራርና ከዚያ የተከተሉት አብያተ ክርስቲያናት አመራር (ለምሳሌ ይህች በዚህ ትምህርት የምንመለከታት የፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን አመራር) የነጠላ ሰው ካልነበረ ይህ ልንከተለው የተገባው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ፈለግ ሊሆን ግድ ነው። ቆይቶ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሌሎችም የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያና አስተዳደር ዓይነቶች ቢከሰቱም ጤናማና ፍሬያማ የወንጌል ሥራ የተሠራባቸው አብያተ ክርስቲያናት በግለሰብ የተመሩ እንዳልነበሩ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አስምሮ ዘግቦታል። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሁለቱ ደማቅ የወንጌል ስርጭት የታየባቸው ዘመናት የመጀመሪያው ምዕት ዓመትና 19ኛው ምዕት ዓመታት ናቸው። በነዚህ ሁለት መቶዎች ዓመታት የጎሉ ወንጌል ሰባኪዎችና የወንጌል ሐዋርያት (ወንጌልን ይዘው በከተማም በዱርና በገደልም የተላኩ መልእክተኞች) ቢኖሩም አብያተ ክርስቲያናት የተመሩት በነጠላ ሰዎች አልነበረም።

ስለ አስተዳደር ዓይነቶች መተንተን የዚህ መጣጥፍ ግብ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ፍሬያማ አመራሮች የቡድን አመራሮች መሆናቸው ሁነኛውን የአስተዳደር ዘይቤ ያመለክታል። በቤተ ክርስቲያን ታሪክና በተለይም ከቅርብ ዓመታትና ዐሠርታት ወዲህ በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ቤተ ክርስቲያንን አጋር ድርጅቶች ውስጥ በሥልጣን የሚባልጉና ከንዋይ ላይ እጃቸው እንዳይነሣ የሚፈልጉ ሰዎች መፍላታቸው ገሃድ ሆኖአል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ አሃዳዊ መሪነትን ወይም የአንድ ሰው ብቻ መሪነትን ለአደጋና ለውድቀት የሚዳርግ ክፍት በር ተደርጎ የሚታይ የመሪነት ስልት አድርጎታል። ብቸኛ መሪነት ባለበት ስፍራ መሪው ባይወድቅም እንኳ የሚወድቅበት ገደል ሣይርቅ እንደሚከተለው እርሱም እኛም ልንገነዘብ ያስፈልጋል።

በቤተ ክርስቲያን የጸጋ ስጦታዎችን አሰባጥሮና በአካል እንደሚገኙ ብልቶች ድርሻ አድርጎ ጌታ የሰጠው ያለ ዓላማ አይደለም። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ራስ የሆነ ሰው የለም፤ የቤተ ክርስቲያን ራስ አንድ፥ እርሱም ክርስቶስ ነው። ብልቶች ብቻ የሆኑ ሰዎች የሆኑትን ብልትነት ትተው ያልሆኑትን ራስነት ሲቀዳጁ የሆኑትን እያልሆኑና ያልሆኑትን ሊሆኑ እየሞከሩ ነው፤ ደግሞ በቅዱሳን ላይ ሊሠለጥኑ እየተንጠራሩ ናቸው። የፊልጵስዩስ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ነጠላ መሪ የምትመራ ቤተ ክርስቲያን ሳትሆን ኤጲስ ቆጶሳት ከዲያቆናት ጋር የሚያስተዳድሩአት ቤተ ክርስቲያን ነበረች።

እግዚአብሔር ከአርያም ይባርካችሁ። © ዕዝራ የስነ ጽሑፍ አገልግሎት / ዘመ

ሁነኛ የቤተ ክርስቲያን አመራር ነጠላ ሳይሆን የቡድን አመራር ነው።

www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!

Page 5: The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 5

ቁጥር ፮ - ነሐሴ ፪ሺህ ፪ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]

‘የተቀባ አገልጋይ’ ወይም ‘የተቀባ አገልግሎት’ የሚሉትን ሐረጎች ሳንሰማቸው ቀናት ቢያልፉ ሳምንት አያልፍም።1 ይህ ቃል አሁን አሁን ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ለአገልግሎቶችና ለነገሮችም እየዋለ ይደመጣል። የተቀባ መዝሙር፥ የተቀባ ስብከት፥ የተቀባ ይህ፥ የተቀባ ያ ይባላል። ቅባትን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናት ሳይሆን ሰብዓዊ ልምምድ የገነነባቸው ስብከቶችና መጽሐፎች አደባባይ ወጥተዋል። ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ተወዳጅ ሰባኪዎቻቸውን የሚያምኑና የሚቀበሉ ምእመናንም በዚህ ብቻ ሳይሆን በምንም ርእስ የሚሰሙትን ስብከት በቃሉ መርምሮና መዝኖ ከመቀበል ሰባኪያቸውን በድፍኑ ማመን ይቀልላቸዋል።

ከጥቂት ዓመታት በፊት በቤተ ክርስቲያናችን የአዲስ አበባ ቀጣና መሪዎች ስልጠና ላይ አንድ ስሙ የገነነ ሰባኪ ‘የቅባት አገልግሎት’ በሚል ርእስ አስተማረ። በትምህርቱ ውስጥ የቅባት ዓይነቶችና አምስት የቅባት ደረጃዎች ብሎ የከፋፈላቸውን እርከኖችም አስተማረ። የሚያሳዝነው የተባሉት የቅባት ዓይነቶችና ደረጃዎች በቃሉ ውስጥ የተጠቀሱና የሚገኙ አልነበሩም። ይህን ትምህርት ተከትሎ ከሚያስተምሩት አንዱ እኔ ነበርኩ። የተሰጠኝ ርእስም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሚገኙ የስሕተት ልምምዶችና ተቀባይነት ያገኙ የስሕተት ትምህርቶች ነበር። ሰባኪውን መጥቀስና መንካት አንዳንዶችን ሊያስቆጣ እንደሚችል ባውቅም ይህ የቅባት ትምህርት ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆን ስላመንኩ ስሕተቱን እንደ ስሕተት ገለጥኩ። ከጠበቅሁት ባለፈ ሁኔታ ለጊዜው መቆጣት ብቻ ሳይሆን ያንን ጉባኤ ያወኩና ለዘለቄታው ያኮረፉም ነበሩ።

ሰባኪዎች ከሚሰበከው የጌታ ቃል በላይ ተአማኒ በሆኑበት አሳች ዘመን ላይ የምንገኝ መሆናችንን ያ ጉባኤ በግልጽ እንድረዳ አደረገኝ። በቃሉ መቃ ሲለኩ ጠማማና ወልጋዳ ብቻ ሳይሆኑ ከቃሉ ጋር የተጣሉ የስሕተት ትምህርቶችና ልምምዶች በታዋቂና በባለዝና ሰባኪዎች ሲሰበኩ እውነት መምሰል ከጀመሩ ከርመዋል። ለመሆኑ ቅባት ምንድርነው? ቃሉስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት ነው የተስተማረው?

1 የዚህን ጽሑፍ አንኳር የወሰድኩት በ1989 (1996) ከታተመው መንፈስ ቅዱስና ካሪዝማዊ ቀውሶች ከተሰኘ መጽሐፌ (ገጽ 162-170) ነው። መጽሐፉን ለማንበብ ወይም ወደ ኮምፒዩተር ለመጫን http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=107 ይጎብኙ።

ቅባት በብሉይ ኪዳን በመጀመሪያ ቃሉና አሳቡ በብሉይ ኪዳን እንዴት እንደተገለጠ እንይ። በብሉይ ኪዳን ግዑዛን ቁሳቁሶችም ይቀቡ ነበር። የተቀቡት ነገሮች ግዑዛን ቁሳቁስ ከሆኑ የተቀቡት ነገር ዘይት ወይም ቅባት፥ ደም ወይም ቀለም ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፥ ጋሻ፥ መሠዊያ፥ ቤት፥ ሐውልት፥ የመስዋዕት ቂጣ፥ እንዲሁም በማደሪያው ድንኳን ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች ከተቀቡ ነገሮች መካከል ይገኛሉ። የመገናኛውን ድንኳን ንዋየ ቅድሳት በተመለከተ ይህ ቅባት ወይም መቀባት የሚያመለክተው እነዚህ ነገሮች የተለዩ፥ የተቀደሱ ለእግዚአብሔር የተሰጡ መሆናቸውን ነው። ግዑዛን ከሆኑት ነገሮች ሌላ የተወለደ ሕጻን፥ የታመመ ሰው፥ እንዲሁም የሞተ በድን እንደተቀቡ ወይም እንደሚቀቡ ተጽፎአል።

ከዚህ ባለፈ ቅባትና ሰዎች አብረው የተጠቀሱት ከሹመትና ሥልጣን ጋር ሆኖ ይገኛል። በዚህ ሁኔታ በብሉይ ኪዳን በብዙ ቦታዎች ‘የተቀቡ’ተብለው ሲጠሩ ወይም ሲቀቡ የምናያቸው ነገሥት ናቸው፤ 1ሳሙ. 2፥4፤ 10፥1፤ 12፥3-5፤ 16፥13፤ 24፥6-10፤ 26፥9-23፤ 2ሳሙ. 1፥14-16፤ 19፥21፤ 1ነገ. 1፥39፤ 19፥15-16፤ 2ነገ. 11፥12፤ 23፥30፤ 2ዜና 29፥22 ወዘተ። ንጉሥ ከተቀባ በኋላ ‘በእግዚአብሔር የተቀባ’ ተብሎም ይጠራል። ሹመቱ ከላይ ከእግዚአብሐር ዘንድ የመነጨ የመሆኑ ምልክት ነው። ምንም ሥልጣን ከላይ ካልተሰጠ በቀር እንዲያው የሚቀዳጁት አይደለምና ይህ ቅባት የዚህ አመልካች ነው።

የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናትና ካህናት ሲካኑ ይቀቡ ነበር፤ ዘጸ. 29፥7፤ 30፥22-33፤ 40፥15፤ ዘሌ. 8፥12፤ 16፥32፤ 21፥10-12፤ ወዘተ። ነቢይ ሲቀባ ግን ከአንድ ጊዜ በቀር አናይም፤ ያም ነቢዩ ኤልሳዕ የተቀባበት ነው፤ 1ነገ. 19፥16። ብሉይ ኪዳን በተጻፈበት የዕብራይስጥ ቋንቋ ቅባትና ዘይትን ለግል ጉዳይ መቀባትና መለኮታዊ ለሆነ ጉዳይ መቀባት በተለያዩ ቃላት ተገልጠዋል። ለግል፥ ማለትም፥ ለመውዛት፥ ለጌጥ፥ ወዘተ፥

መቀባት ሱቅ (סוּך) ሲሰኝ ለእግዚአብሔር መቀባት ደግሞ ማሻኽ

ይባላል። በዚህ ቋንቋ መሺያኽ የሚባለው መሢሕ የሚለው (משׁח)

ስያሜ የመጣው ከዚህ ነው። እንግዲህ እነዚህ የብሉይ ኪዳን ቅባቶችና የተቀቡ ሰዎች ወደ አዲስ ኪዳን የሚጠቁሙ አመልካቾች ናቸው። ያም አንድ ቀን ነቢይም፥ ሊቀ ካህናትም፥ የነገሥታት ንጉሥም የሆነው መሢሕ ክርስቶስ እንደሚመጣ የሚያመለክት የናፍቆት ገላጭ ነው።

ቅባት በአዲስ ኪዳን

አዲስ ኪዳን በተጻፈበት የጽርዕ ቋንቋ ክሪኦ (χρίω) መቀባት ማለት

(2ቆሮ. 1፥21 እንደሚገኘው) ሲሆን ክሪዝማ (χρίσμα) ደግሞ (በ1ዮሐ.

2፥20 እና 27 እንደሚገኘው) ቅባት ማለት ነው። ከዚህ ስርወ ቃል

የወጣው ክርስቶስ (Χριστός - ክሪስቶስ) የተቀባ ማለት ነው። የብሉይ

ኪዳኑ መሺያኽ እና የአዲስ ኪዳኑ ክርስቶስ በትርጉም አንድ ናቸው። በአዲስ ኪዳን ‘የተቀባ’ የሚል ብቸኛ ስያሜ ያለው ጌታ ብቻ ነው። ከክርስቶስ ሌላ የተቀቡ ወይም ቅባትን የተቀበሉ የተባሉም አሉ። ሆኖም ይህ ስያሜአቸው አይደለም። እነርሱም ከክርስቶስ የተነሣና መንፈስ

www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!

Page 6: The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 6

ቁጥር ፮ - ነሐሴ ፪ሺህ ፪ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]

ቅዱስ በውስጣቸው ከመኖሩ የተነሣ ማንም ከማንም ሳይለይ ወይም ምንም ልዩነት ፈጽሞ ሳይኖር የተቀቡት አማኞች ሁሉ ናቸው።

በአዲስ ኪዳን የተቀባና ያልተቀባ ክርስቲያን ወይም የተቀባና ያልተቀባ አገልጋይ የሚባል መደብ የለም። ክርስቲያኖች ሁሉ የተቀቡ ናቸው፤ ያልተቀቡ ከሆኑ ደግሞ ቀድሞም ክርስቲያኖች አይደሉም ማለት ነው። ከሆኑ የተቀቡ አይደሉም ማለት አይቻልም።

በአዲስ ኪዳን ቅባትና መቀባት የተባለው ቃልና አሳብ 30 ጊዜያት ያህል ሲጠቀስ ከነዚህ ወደ 20 ያህሉ በአካል ላይ የሚፈስ ወይም የሚቀቡትን ንጥረ ነገር ሲያመለክቱ ከነዚህ ከ20ው ግማሽ ያህሉ ክርስቶስና አማኞች የተቀቡበትን ሁኔታ ያመለክታል። ከእነዚህ ክርስቶስን በተመለከተ የተጻፉት የሚከተሉት ናቸው፤

ሉቃ. 2፥26 በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።

ሉቃ. 4፥17-20 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።

ሉቃ. 9፥20 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።

ሐዋ. 4፥26-27 የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቆችም በጌታና በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ ብለህ የተናገርህ አምላክ ነህ። በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።

ሐዋ. 10፥38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤

ዕብ. 1፥9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል።

ከእነዚህ ክርስቶስን የሚመለከቱ ጥቅሶች ናቸው። ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስ ብለን ነው የምንጠራው። ኢየሱስ የዕብራይስጥ ስሙ ሆኖ አዳኝ ማለት ሲሆን ክርስቶስ የግሪክ ቃል ሆኖ ከላይ የተመለከትነው መሢሕ ማለት ነው። ቅቡዕ ወይም የተቀባ ማለት ነው። ጌታን ስሙን በአማርኛ ተርጉመን የምንጠራው ቢሆን ኖሮ “የተቀባው አዳኝ” ብለን ነበር የምንጠራው። በብሉይ ኪዳን መቀባት መሾምን፥ ሥልጣንን፥ ማዕረግን፥ አብሮት የተያያዘውንም ክብር የጨበጠ ነው። የጌታ ቅቡዕነት የተለየ ነው። ቅባት ያካተተውን ክብርና ምማዕረግ ሁሉም የያዘ ነው። በአይሁድ ይጠበቅ የነበረው መሢሕ፥ ሰው የሆነ አምላክ፥ ሥጋ የሆነ ቃል፥ ሊያማልድ ለዘላለም የሚኖር ሊቀ ካህናት፥ ቃልን የገለጠ ነቢዩ ኢየሱስ እርሱ ሰማያዊው ሹም ነው።

አማኞችን በተመለከተ ከቅባት ጋር የተያያዙት የአዲስ ኪዳን ጥቅሶች ብዙ አይደሉም። የሚከተሉት ናቸው፤

2ቆሮ. 1፥21 በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው።

1ዮሐ. 2፥20 እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።

1ዮሐ. 2፥27 እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ

እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።

ከነዚህ የምንረዳው ትልቅ እውነት በዚህ መጣጥፍ መጀመሪያ እንደተመለከትነው ያለ ‘የተቀባ’ እና ‘ያልተቀባ’ የሚባል መደብ ፈጽሞ ያለመኖሩን ነው። የቅባት ደረጃና ክብደትም የለም። ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምዕመናን ሲጽፍ እኛና እናንተ ብሎ በመለየት ሳይሆን ‘ከእናንተ ጋር. . . የቀባን’ ነው ያለው። ያገለገሉአቸው እነ ጳውሎስም የቆሮንቶስ ምእመናንም በእግዚአብሔር የተቀቡ ናቸው።

ዮሐንስ በጻፈው መልእክት ደግሞ አማኞች ሁሉ ከቅዱሱ ቅባትን መቀበላቸውን ነው በግልጽ የጻፈው። እዚህ ቅባት ተብሎ የተጠቀሰው የራሱ የመንፈስ ቅዱስ ኅልውና ሲሆን ቅዱሱ የተባለው ደግሞ ጌታ ነው። አምኞች ከጌታ መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ የአገልግሎት ማዕረግ ወይም ሹመት መቀበላቸው ሳይሆን ትክክለኛ ትምህርትን ትክክለኛ ካልሆነው ለይቶ ማወቅን፥ ማስተዋልን፥ መረዳትን የሚሰጠውን፥ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራውን መንፈስ ቅዱስን መቀበላቸውን መግለጡ ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ የሚያድር አማኝ ሁሉ ከቅዱሱ ቅባትን ተቀብሎአል። መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ መኖር የጀመረው መቼ ነው? በመንፈስ ቅዱስ በተጠመቀ ጊዜ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቀው መቼ ነው? የክርስቶስ አካል ብልት በሆነ ጊዜ ነው። የዚህ አካል ብልት የሆነውስ መቼ ነው? ባመነ ጊዜ ነው። 1ቆሮ. 12፥13 እንዲህ ይላል፥ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል። ስለዚህ የአካሉ ብልቶች ስንሆን የቅባቱ ተቀባዮች ሆነናልና ይህ ልዩነት የለም።

ዱሮ ‘አንድ ጥያቄ አለኝ’ ወይም ‘ይድረስ ለጳውሎስ ኞኞ’ የሚባል የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዓምድ ነበረ። ማንም ሰው ምንም ጥያቄ ይጠይቃል፤ ጋዜጠኛ ጳውሎስም ይመልሳል። የሚመልሳቸው መልሶች ያልጣመው አንድ ጠያቂ፥ “የምትመልሳቸው መልሶች ሁሉ ደረቆች፥ ወዝ የሌላቸው፥ ለዛቢሶች ናቸው” ብሎ ጻፈለት። ጳውሎስም፥ “ወዝ እንዲኖራቸው አምበርጭቃ ቀባቸው” ብሎ መለሰለት። አምበርጭቃ መቀባት ጋዜጣውን ያወዛው እንደሆነ እንጂ የመልሱን ለዛ እንደማይቀይረው ግልጽ ነው። እንደዚሁም ከጸጋ ስጦታና ከጥሪ ያልተቋጠረ እንዲያው ‘የተቀባ’ መሰኘት አገልግሎትን አያወዛም። ‘የተቀባ’ የምንለውስ ምኑን ነው? ሰውየውን? አገልግሎቱን? ጥሪውን? ስጦታውን? ምኑን? ከሆነ እነዚህን ነገሮች የተቀቡ ያልተቀቡ የሚያሰኙአቸው ምንድርናቸው?

እገሌ የተቀባ አገልጋይ ነው ስንል እገሌ ደግሞ የተቀባ አይደለም ማለታችን መሆኑን አንዘንጋ። ካልን ቅባት ወይም መቀባት ለሚለው አሳብ የራሳችንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የግል ትርጉም መስጠታችን ነው። ልንል የፈለግነው በጸጋ ስጦታው ወይም ያለጸጋ ስጦታው እያገለገለ ስላለ አገልጋይ ከሆነ የተቀባ ወይም ያልተቀባ ከማለት ይልቅ ሌላ ቃል መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል። በእርግጥ ያለስጦታቸው የሚያገለግሉ ኮራጆች ወይም ያለ ጥሪያቸው የተሰማሩ ሞያተኞች ይኖራሉ። እነዚህም የሚያስፈልጋቸው የጸጋ ስጦታቸውን መዝነውና ጥሪያቸውን ፈትሸው መሰማራት ነው እንጂ መቀባት አይደለም። ከላይ እንደተመለከትነው በአዲስ ኪዳን ትምህርት እንደ ብሉይ ኪዳን ዘመን የመሰለ ዘይት ወይም ቅዱስ ቅብዓት የመቀባት ሥርዓት ባለመኖሩ የቅቡዓንና የቅባት-አልባዎች መደብ የለም። የታመሙ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ጠርተው፥ እነርሱም ዘይት ቀብተው እንዲጸልዩላቸው

www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!

Page 7: The Christian Voice,Beyond Church!ethiocross.com/blogs/media/blogs/a/Ezra-Literature-Mag-Issue-006.pdfእግር ስርም የተማረው በዚያ ነበረ፤ ሐዋ. 22፥3 እና

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 7

ቁጥር ፮ - ነሐሴ ፪ሺህ ፪ ዓመተ ምሕረት AUGUST 2010 [email protected]

ከተነገረው (ያዕ. 5) ሌላ የመቀባባት ሥርዓት የለም። ክርስቲያኖች ክርስቲያኖች ሲሆኑ፥ ማለትም ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን ሲቀበሉ የተቀቡ ሆነዋል።

የቀባኋቸውን አትዳስሱ? የቅባት ችግር ይህ ከላይ የተጠቀሰው በአሳሳች ትምህርቶች የተፈጠረው የመቀባትና አለመቀባት ልዩነት ብቻ አይደለም። ሌላው ችግር ቀቢዎቹም ሆኑ የተቀባን ነን ባዮች መቀባትን ከሥልጣን ጋር አያይዘው አይነኬ፥ አይደፈሬ አድርገው ራሳቸውን ከሌላው ስለሚያግዱ የሚወቅስና የሚያወግዛቸውን፥ ስሕተታቸውን የሚያሳያቸውንና ሥልጣናቸውን የሚፈትሸውን የሚያዳፍኑበት የጥቅስ አዳፍኔ መጨበጣቸው ነው። ይህም ‘የቀባኋቸውን አትዳስሱ’ የሚል ሐረግ ነው።

ከ15 ዓመታት በፊት የሴሚነሪ ተማሪ ሳለሁ አንዲት ቤተ ክርስቲያንንም በማገልገል እረዳ ነበር። በጊዜው የነበረው መጋቢ መጋቢ ብቻ ሳይሆን አስተዳዳሪም፥ የገንዘብ ኃላፊና ተቆጣጣሪም፥ የሽማግሌዎችንና ዲያቆናትን ሿሚና ሻሪም ነበረና ይህ አሠራር እንዳልጣመኝና አገልግሎቱንና ምስክርነቱንም አጠያያቂ እንደሚያደርግ በመንገር ለውጥ እንዲደረግ የመጀመሪያ ሙከራ አደረግሁ። ወዲያውኑ የመለሰልኝ የእርሱ አሠራር እኔ ከመጣሁበት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ስልት የተለየ መሆኑን እና በምትሾምና በምትሽር (በራሱ ቋንቋ hire and fire በምታደርግ) ቤተ ክርስቲያን መሥራት እንደማይፈልግ ነበር። በቀጣዮቹ ሁለት እሁዶች የሰበከው ደግሞ ‘የቀባኋቸውን አትዳስሱ’ በሚል ርዕስ ሆነ። ያደረገው እርሱን መጠየቄ ተገቢ ያልሆነ ተግዳሮት መሆኑን በማሳየት በአፌ ላይ ዝማም ለማኖር ነበር። በዚያ ሁኔታ ማገልገል ስላልፈለግሁ ወደ ትምህርቴ ተሰበሰብኩ። ይህ ሰው ግን በወቅቱ ባለ ዝና ቢሆንም በዚያ አገልግሎቱ ከ1 ዓመት ያልበለጠ ብቻ ነበር የቆየው። ከታቹ ከምዕመናንም ከላዩ ከሚያመልኩባት ቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ጥያቄ ውስጥ በመግባቱ ባልጠበቀው ፍጥነት ከአገልግሎቱ ተሰናበተ። እንደ መሰለው የተቀባ መሆኑ ከተጠያቂነትና ከመፈተሽ አላገደውም።

አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከዐውደ ምንባቡ ፈልቅቀው ከወቀሳና ከተግሳጽ ለመዳን ሲፈልጉ እንደ ባንዲራ የሚያውለበልቡት ይህ ‘የቀባኋቸውን አትዳስሱ’ የሚለው ሐረግ የተወሰደው ከመዝ. 105፥14-15 ነው። ጥቅሱ እንዲህ ይላል፥ የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ። ጥቅሱን ብቻ ሳይሆን ምዕራፉን በመላው በቦታው ስናጠና ይህ ቃል የተጻፈው ወይም የተዘመረው በታሪካዊ ትውስታነት ሲሆን ቃሉ መፈተሽ ስለሌለባቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሳይሆን እግዚአብሔር ተስፋ ስለሰጣቸውና ቃል ስለገባላቸው ስለመጀመሪያዎቹ የአይሁድ አባቶች ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ሐረግ በኋላ በሕጉና በሥርዓቱ ውስጥ የኪዳኑ ሕዝብ መሪዎችና ካህናት ሊሆኑ ስለተቀቡ ሰዎችም እንኳ የተነገረ አይደለም። ይልቁንም ስለ አዲሱ ኪዳን አማኞችና ደቀ መዛሙርት፥ አገልጋዮችና መሪዎችም የተነገረ ከቶም አይደለም። ጥቅስን ያለቦታው መሰንቀር ከትጉህ የቃሉ አስተማሪዎች የማይጠበቅ ነው። ይልቁንም ለራስ ሥልጣን የራስ ጠበቃና ሥልጣን አስከባሪ መሆን ከአገልጋይ የሚጠበቅ ባህርይም አይደለም። በእውነቱ ‘አገልጋይ’ የሚለው ቃል በፍጥነት እየሳሳና ከእይታ ውጪ እየሆነ እየመጣ ነው።

በእርግጥ የእግዚአብሔርን ሕዝብ መሪዎችና አገልጋዮች ማክበር ሊያጠያይቅ የተገባ ወግ አይደለም። በብሉይ ኪዳን ዘመን ይከበሩ ነበር። ለዚህ ክብር ውብ ምሳሌ የሚሆንልን ሰው ራሱም ተቀብቶ የነበረው ዳዊት በዘመኑ ንጉሥ ሆኖ የተቀባውን ሳኦልን ሊያጠፋው ሲችል ነፍሱን ደጋግሞ ያለማጥፋቱ ብቻ ሳይሆን ‘የተቀባ’ እያለ ማክበሩ ነው። ራሱም የተቀባ ሳለ እንዲህ ማድረጉ ሌሎቹ ከዚህም በላይ ሊያደርጉ እንዲጠበቅባቸው ጉልህ አስረጅ ነው።

ወደ አዲስ ኪዳን ስንዘልቅ አገልጋዮች ‘አክብሩን’ ሲሉ ሳይሆን ‘አክብሩአቸው’ ሲባል አናያለን። የጳውሎስ የራሱ አገልግሎት ክብርን ወደራሱ የሚስብ አገልግሎት አልነበረም። ለተሰሎንቄ ምእመናን እንዲህ አለ፥ የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም፤ 1ተሰ. 2፥6። የጳውሎስ ዒላማ አክብሮት ከቶም አልነበረም።

ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ምእመናን ስለ አፍሮዲጡ ሲጽፍ፥ እንግዲህ በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት፥ እርሱን የሚመስሉትንም አክብሩአቸው፤ በእኔ ዘንድ ካላችሁ አገልግሎት እናንተ ስለሌላችሁ የጎደለኝን እንዲፈጽም፥ በነፍሱ ተወራርዶ ከጌታ ሥራ የተነሣ እስከ ሞት ቀርቦአልና ብሎአል፤ ፊል. 2፥29-30። እንዲህ ነፍሳቸውን አስይዘው የሚያገለግሉ አገልጋዮች እንደምን በደስታ ሊከበሩ ይገባል! 1ጢሞ. 5፥17 እንዲያውም ስለ እጥፍ ክብር እንዲህ ይላል፥ በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል። ይህ እውነት ነው። እነዚህ በመልካም የሚያስተዳድሩ፥ በመስበክና በማስተማርም የሚደክሙ ናቸው። መልካም አስተዳዳሪዎች ከሆኑና በመድከም የሚያገለግሉ ከሆኑ እነዚህም እንደምን በደስታ ሊከበሩ ይገባል! እነዚህ ‘አክብሩን’ እያሉ በግንባራቸው ራስ ወርቅ የሚያስሩ ገዥዎች ሳይሆኑ ሌሎች አክብሩአቸው እያሉ የሚናገሩላቸው ሁነኛ መሪዎች ናቸው።

ክብር የተገባ ቢሆንም አክብሩኝ ሲሉ አትድረሱብኝ፥ አትንኩኝ፥ አትድፈሩኝ፥ አትመዝኑኝ ማለታቸው ከቶም መታሰብ የለበትም። ይልቁንም ይህንን አክብሮት በቃሉ ውስጥ ካልተጻፈ የቅብዓት ትምህርት ጋር አቆራኝቶ ማሳት የለባቸውም። አገልጋዮች ፈጽሞ እንደማይሳሳቱ ሁሉ በአመላለስም ሆነ በአስተምህሮ ግልጽ ከመሆንና ከመመርመርም ነጻ መሆን የለባቸውም። አንዳንድ ጊዜ ትልልቅ አገልጋዮችና መሪዎች ብዙ መዘዝ ያለበት ትልልቅ ስሕተት ይሳሳታሉ። የወርቅ ጥጃ የሠራ አሮን ነበረ። ጌታ ስለ ሞቱ ሲናገር ‘ይህ አይሁንብህ’ ያለ ጴጥሮስ ነበረ። እነዚህ ሰዎችና የእነርሱን የመሰለ ስሕተት የሚደግሙ ሰዎች ዝም መባል አለባቸው? ከቶም የለባቸውም። አገልጋይ የአደባባይና የመድረክ ሰው ሲሆን ለመፈተሽ ፈቃደኛ መሆን አለበት። ይልቁንም ለመፈተሽ የማያስቀርቡቱ የበለጠ መፈተሽ አለባቸው። መጠየቅና መገዳደር ነውር በሚመስልበትና ሰዎችን አክባሪና ፈሪ በሆነ የእኛ ዓይነቱ ባህልና ማኅበረ ሰብ ይህ ችግር ይጎላል። ቅባትን ስናስብ ይህን እናስብ። የተቀባን ነን ባዮች ለመፈተሽ የማይፈልጉት ቢፈተሹ የሚገኝባቸው ነገር በመኖሩ ነው። ኬላ ላይ መቆም የማይወዱ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ብቻ ናቸው። በአውሮፕላን ማረፊያ የፍተሻ በር ለመግባት የሚሳቀቁ ጎጂ መሣሪያ የያዙ ብቻ ናቸው። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ዮሐ. 2፥27 እግዚአብሔር ከአርያም ይባርካችሁ። © ዕዝራ የስነ ጽሑፍ አገልግሎት / ዘመ

www.Ethiocross.com The Christian Voice,Beyond Church!