16
በየ3 ወሩ ተዘጋጅቶ ለብሉስታር አባል ክሊኒኮች በነጻ የሚታደል Issue 3, November,2015 3. ኮከብ የብሉ ስታር እንግዳችን 1. የብሉ ስታር መልዕክት 2. ባለሙያው ምን ይላል?

MSIE Newsletter Dec 21_2

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: MSIE Newsletter Dec 21_2

ለብሉስታር አባል ክሊኒኮች በነጻ የሚታደል-በየ3 ወሩ የሚዘጋጅ

Issue 2, OCTOBER- 2015

በየ3 ወሩ ተዘጋጅቶ ለብሉስታር አባል ክሊኒኮች በነጻ የሚታደል

Issue 3, November,2015

3. ኮከብ የብሉ ስታር እንግዳችን

1. የብሉ ስታር መልዕክት

2. ባለሙያው ምን ይላል?

Page 2: MSIE Newsletter Dec 21_2
Page 3: MSIE Newsletter Dec 21_2

የብሉ ስታር መልዕክትውድ የተከበራችሁ የብሉ ስታር ጤና አውታር አባል አጋሮቻችን ከሁሉ

በፊት በማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ መላው ሠራተኞች ስም

የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ድርጅታችን ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከግሉ

የጤና ዘርፍ ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚፈልገው እና እየሰራ ያለው

የግሉ ጤና ዘርፍ ካለው እምቅ አቅም አኳያ የእናቶቻችን ጤና

ለማሻሻል እና አማራጭ የስነ ተዋልዶ ጤና ለማህበረሰቡ ለማድረስ

እየተደረገ ባለው አገራዊ ጥረት ውስጥ ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና

እጅግ በጣም የገዘፈ እንደሆነ ስለምናምን ነው፡፡ ከዚህ አንፃር

ድርጅታችን ከእናንተ ስልታዊ አጋሮቻችን /Strategic Part-

ners/ ጋር በመስራታችን አማራጭ የስነ ተዋልዶ ጤና እና

የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች በማድረስ በኩል እያሳየን

ያለው ዉጤት እጅግ በጣም የሚያበረታታ ነው፡፡ ለአብነት ያህል

በ2007 ዓ.ም ብቻ ድርጅታችን ከብሉ ስታር የጤና ማዕከላት ጋር

በመስራት ቁጥራቸው ከ524,201 ለሚልቁ ዜጎች የተለያዩ የስነ

ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተችሏል፡፡

በዚህ በያዝነው ዓመት (2015 እ.ኤ.አ) ድርጅታችን በዓለም አቀፍ

ደረጃ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት እ.ኤ.አ 1976 ጀምሮ 100

ሚሊዮን ተገልጋዮችን /100 Million Clients/ የአገልግሎት

ተደራሽ ያደረገበት አመት በመሆኑ ድርጅታችን በሚሰራባቸው አገሮች

ቡፖ|1

Page 4: MSIE Newsletter Dec 21_2

ዉስጥ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ ይህ እለትም በማሪስቶፕስ

ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በኩልም በድምቀት ተከብሮ አልፏል፡፡ በዚህ

የስኬት ሃዲድ ዉስጥ አብረውን የሚሰሩ የግል ክሊኒኮች አስተዋፅኦ

ከፍተኛ እንደሆነም የሚታወቅ ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ዉስጥ አገልግሎት

መስጠት ከጀመረ እነሆ 25 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህንንም የ 25

አመታት ጉዞአችንን በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን።

በዚህ በ25 ዓመታት ጉዞአችን ዉስጥ በድርጅታችን በኩል እየተሰጡ

በሚገኙ ዘርፈ ብዙ የጤና አገልግሎቶች ምክንያት አያሌ ዜጎች

ተጠቃሚ ከመሆናቸውም ባሻገር በስነተዋልዶ ጤና መረጃ እና

አገልግሎት ተደራሽነት ውስንነት ምክንያት በሴቶች ወገኖቻችን ላይ

ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና መታወኮችን ከመከላከል አኳያም ጉልህ ሚና

መጫወት እንደቻልን እናምናለን፡፡ ከዚህ ጉልህ ሚና እና ከተገኙ

ውጤቶች በስተጀርባ በመንግስት በኩል እየተደረገልን ባለው እገዛ

ከእናንተ ከብሉስታር አባል ክሊኒኮች ጋር በቅርብ መስራታችን እና

ከሁሉም በላይ ደግሞ በምንሰጠው የስነ ተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ

እቅድ አገልግሎት እንዲሁም የእናቶች እና ህጻናት ጤና አገልግሎት

ዙሪያ ዘወትር አስተያየት በመስጠት የተሻለ እና ጥራቱን የጠበቀ

አገልግሎት እንድንሰጥ የሚያተጉን የተገልጋዮች /Client/ ሚና

ታላቅ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

በቀጣዩ ዓመት 2016 (እ.ኤ.አ) ድርጅታችን ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል

ኢትዮጵያ በመንግስት በኩል የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት፣ የእናቶች እና

ህጻናት ጤና አገልግሎትን ለማዳረስ በዘረጋው እቅድ መሰረት ከብሉ

ስታር ክሊኒኮች ጋር በመተባበር በቀጣይነትም ገንቢ ሚና ለመጫወት

በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡

በመጨረሻም አጋር የብሉ ሰታር ክሊኒኮች ጥራቱን የጠበቀ እና

ተገልጋዮችን ሊያረካ የሚችል የስነተዋልዶ ጤና እና የቤተሰብ

እቅድ አገልግሎት በመስጠት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ በቀጣይነትም

እንድታበረክቱ እየጠየቅኩኝ በአገልግሎት አሰጣጣችሁ ዙሪያ እየታዩባችሁ

ያሉትን ድክመቶች ለማሻሻል እና እያሳያችሁት ያለውን ጠንካራ ጎን

ለማጎልበትም በምታደርጉት ጥረት ዉስጥ ድርጅታችን በቀጣይነትም

ከጎናችሁ በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እና እገዛ የሚያደርግ መሆኑንም

በመጠቆም ነው፡፡

ሰላም ቆዩ!

አበበ ሽብሩ

ምክትል ካንትሪ ዳይሬክተር እና

የስትራቴጂ እና ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተር

ቅምጥሏቅምጥል አፍቅሬ፣

ለሷ ተቸግሬ፣

ኩሽና እንዳትገባ ካልጋ እንዳትነሳ፣

ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ባስብላት ለሷ፡፡

የእንጀራ ጫፍ ጣቷን እንዳይቆርጣት ብዬ፣

አጉራሽም ቀጠርኩኝ አሳቢ መስዬ፡፡

ቅምጥሏን ፍቅሬን ድንገት ቢያስነጥሳት፣

ይማርሽ የምትል ሌላም ቀጠርኩላት፡፡

የሞልቃቃ ነገር፣

መጨረሻው አያምር፣

ቅጥ ያጣውን ፍቅሬን ውስጤን ስላየችው፣

ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ብላኝ አረፈችው፡፡

በሰለሞን ወልዴ

ቡፖ|2

Page 5: MSIE Newsletter Dec 21_2

ዶ/ር ነጋ ተስፋው በማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የጥራትና

የክሊኒካል አገልግሎቶች ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ዛሬ ከእርሳቸው ጋር

በሚኖረን ቆይታ በሚከተሉት ሀሳቦች ዙሪያ ተወያየን፤ እናንተ

ደግሞ አንብባችሁ ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኙ ዘንድ እንደሚከተለው

አቅርበነዋል፡፡

ብሉስታር ፦ የብሉ ስታር ክሊኒክ (የጤና እንክብካቤ ተቋማት)

ጥራት ወይም (Health- Care Quality) ስንል ምን ማለታችን

ነው?

ዶ/ር ነጋ ፦ የብሉ ስታር የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት ስንል

የተቋሙን ደንበኞች ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ፤ በአግባቡና ጥንቃቄ

በተሞላበት ሁኔታ ዘመናዊ ግኝቶችን በመጠቀም የሚሰጥ የጤና

አገልግሎት ማለታችን ነው፡፡ ይህ አይነቱ የጤና አገልግሎት አነስተኛ

ጥራትን፣ ደግሞ መስራትንና ብክነትን የሚቀንስ ሲሆን ጥራት አለው

እንላለን፡፡

ብሉስታር ፦ የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት መሟላት

የሚያስገኛቸው ጥቅሞች ምን ምን ናቸው?

ዶ/ር ነጋ ፦ የጤና እንክብካቤ ተቋማት ጥራት ከሚያስገኛቸው

ጥቅሞች መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ውጤታማ፣ በደንበኞች ፍላጎት

ላይ የተመሰረተ፣ ጊዜውን የጠበቀ፣ ሁለገብ፣ በቀላሉ የሚገኝ

በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እና እሴቶችን የመጨመር አቅም ያለው

የጤና አገልግሎት ይገኝበታል፡፡

ብሉስታር ፦ የብሉ ስታር የጤና እንክብካቤ ተቋማት አገልግሎት

አሰጣጥ በማንኛውም ጊዜ ሊተገበሩ የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው

ይላሉ?

ዶ/ር ነጋ ፦ የብሉ ስታር ተቋማት ጥራትን ለማሟላት የደንበኞችን

መብት ሊያከብሩ ይገባቸዋል፡፡ የደንበኞች መብት ስንል ደንበኛው/ዋ

ሰብአዊ መብቱ/ትዋን በጠበቀ መልኩ መረጃን የማግኘት መብት፣

የአገልግሎቶች ተጠቃሚነት መብት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ

የአገልግሎት ምርጫ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት፣ ምስጢሩ

የተጠበቀ የደንበኛ አገልግሎት፣ ምቾቱ የተጠበቀና ቀጣይነት ያለው

አገልግሎት ማለታችን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ

ለድንገተኛ ህክምናዎች ዝግጁ መሆን እና ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር

ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን መተግበር ተገቢ መሆኑን ሊገነዘቡ

ይገባል፡፡

ባለሙያው ምን ይላል?

ቡፖ|3

Page 6: MSIE Newsletter Dec 21_2

ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል

እንችላለን?

• እጅን በመታጠብ

• ጓንቶችን፣ ገዋኖችንና

መነጽሮችን በመጠቀም

• ባክቴሪያ የሚገድሉ አንቲሴፕቲኮችን

በመጠቀም

• በቀዶ ህክምና ወቅት ተገቢ

ጥንቃቄዎችን በመውሰድ

• የህክምና መሳርያዎችን በንጽህናና

በጥንቃቄ በመጠቀም

• ቆሻሻን በአግባበቡ በማስወገድ

ብሉስታር፦ በብሉ ስታር ክሊኒኮች ውስጥ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች

ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚኖራቸው ድርሻ ምን

ያህል ነው ይላሉ?

ዶ/ር ነጋ፦ የዚህ የብሉስታር መጽሄት ተደራሽ አካላት በብሉ ስታር

ክሊኒኮች ውስጥ የሚገኙ የጤና ሰራተኞችና የህክምና ባለሙያዎች

ናቸው፡፡ እናም ሁሉም የጤናው ተቋማት ባለሙያዎች ደረጃውን

የጠበቀ የህክምና እርዳታን የመስጠት ብቃት ማሟላት፣ የተቋሙን

አስተዳደራዊ አደረጃጀት ምቹ ማድረግ፣ በየጊዜው ተገቢውን

ስልጠና መውሰድ እንዲሁም ለባለሙያው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች

መሟላታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል

ኢትዮጵያ በይበልጥ ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል

በደንበኞች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት አሰጣጥና የተሟላ

የምክክር አገልግሎት ተደራሽነት ይገኙበታል፡፡ ይህንንም ተግባራዊ

ማድረግ የጤና ባለሙያዎቹ ድርሻ ነው ማለት ነው።

ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ክሊኒኮች ከማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል

ኢትዮጵያ የሚያገኙት ድጋፍ ምን ይመስላል?

ዶ/ር ነጋ፦ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለብሉ ስታር

ክሊኒኮች የሚሰጠው ድጋፍ የምስረታ አባልነት ድጋፍ አንስቶ፦

የመሳሪያዎች ስልጠና እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ክትትል፣ የጥራት

ቴክኒክ እገዛና ቁጥጥር ድጋፍ ናቸው፡፡ ይህም የሚደረገው ጥራትን

በዘላቂነት ጠብቆ መጓዝና በየጊዜው አገልግሎቶች ላይ መሻሻል

ማድረግ የብሉ ስታር ክሊኒኮች ልዩ መለያ በመሆኑ ነው፡፡

ቡፖ|4

Page 7: MSIE Newsletter Dec 21_2

ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል

እንችላለን?

• እጅን በመታጠብ

• ጓንቶችን፣ ገዋኖችንና

መነጽሮችን በመጠቀም

• ባክቴሪያ የሚገድሉ አንቲሴፕቲኮችን

በመጠቀም

• በቀዶ ህክምና ወቅት ተገቢ

ጥንቃቄዎችን በመውሰድ

• የህክምና መሳርያዎችን በንጽህናና

በጥንቃቄ በመጠቀም

• ቆሻሻን በአግባበቡ በማስወገድ

የሰራተኝነት ብቃትዎን ይፈትሹከዚህ በታች የሚገኙት ጥያቄዎች ምን አይነት ሰራተኛ ነዎት የሚለውን

ይፈትሻሉ፡፡ እስቲ ጊዜ ወስደው ጥያቄዎቹን ለራስዎ በታማኝነት

ይመልሱ፡፡ ዉጤቱን በገጽ 12 ይመልከቱ::

1. ስራ ላይ በስራ ሰዓትዎ ይገኛሉ?

o አዎ እገኛለሁ

o አልገኝም

2. በስራ ላይ ከተመደበልዎት ስራ ውጪ ተጨማሪ ነገሮችን ይሰራሉ?

o አዎ እሰራለሁ

o አልሰራም

3. ከስራ ባልደረቦችዎ ጋር ሌሎች ሰራተኞችን ወይም ደንበኞችን

የማማት ልማድ አልዎት?

o አዎ አለኝ

o የለኝም

4. በስራዎ ሁልጊዜ ደስተኛ ነዎት?

o አዎ ነኝ

o አይደለሁም

5. የስራ ባልደረቦችዎንና ደንበኞችን በተለያዩ ነገሮች ለመርዳት

ምንጊዜም ዝግጁ ነዎት?

o አዎ ዝግጁ ነኝ

o ዝግጁ አይደለሁም

6. በስራ ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን የመፍታት አቅም አለኝ ብለው

ያምናሉ?

o አዎ አለኝ

o የለኝም

7. የተሰጥዎትን ስራ ምንጊዜም በተመደበልዎ ጊዜ ያጠናቅቃሉ?

o አዎ አጠናቅቃለሁ

o አላጠናቅቅም

8. የስራ ተነሳሽነት አልዎት?

o አዎ አለኝ

o የለኝም

ቡፖ|5

Page 8: MSIE Newsletter Dec 21_2

9. በቡድን የመስራት ልምድና ፍላጎት አለዎት?

o አዎ አለኝ

o የለኝም

10. ጊዜ ወስደው ከስራ ባልደረቦችዎ ጋር ለመተዋወቅና ለመግባባት

ይሞክራሉ?

o አዎ እሞክራለሁ

o አልሞክርም

11. በስራ ቦታ አለባበስዎ ለስኬት የሚያዘጋጅና ደንብን የተከተለ

ነው?

o አዎ ነው

o አይደለም

12. በስራ ላይ ከሚጠበቅብዎ በላይ እጅግ በላቀ መልኩ ተሽለው

ለመገኘት ጥረት ያደርጋሉ?

o አዎ እጥራለሁ

o አልጥርም

አገባሽ ነበረየቁመቴን ማጠር የመልኬን ማስከፋት፣

ከጉዳይ ባትቆጥሪው የገፄን ደም ግባት፣

ኮልታፋ አንደበቴን ሸካራውን ድምጼን፣

ሰምተሸ ባትንቂያቸው ለዛ አልባ ቃላቴን፣

ፍፁም ድህነቴን አምነሽ ብትቀበይ፣

ፍቅርን ብታስበልጭ ከዚች ምድር ሲሳይ፣

አገባሽ ነበረ እሽ ብትይ አንቺ፣

በተለይ በተለይ ባልሽን ብትፈቺ፡፡

ዘላለም ምህረቱ

ቡፖ|6

Page 9: MSIE Newsletter Dec 21_2

አቶ አበራ አያና ይባላሉ፡፡ በበቆጂ ከተማ የብሉ ስታር አባል የሆነው

የአበራ መለስተኛ ክሊኒክ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤

በዚህ ዓመት በማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የብሉ ስታር

የክሊኒካል አገልግሎቶች ምዘና 98% በማስመዝገብ የከፍተኛ

ውጤት ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ አቶ አበራ ከዚህ በተጨማሪ

የ3 ዋንጫዎችና የተለያዩ ሰርተፊኬቶች ተሸላሚ ሲሆኑ በበቆጂ

ከተማ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ደንበኞችን

በማስተናገድ ድንቅ ውጤትን እያስመዘገቡ የሚገኙ የጤና ባለሙያ

ናቸው፡፡ የአበራ መለስተኛ ክሊኒክ ለዛሬ በአርአያነት ያቀረብነው የብሉ

ስታር ክሊኒክ ነው፡፡ ከአቶ አበራ ጋር ያደረግነውን ቃለምልልስ እነሆ።

ብሉስታር፦ በቅድሚያ የዚህ አስደሳች ውጤት ባለቤት በመሆንዎ

እንኳን ደስ አልዎት፡፡ የብሉ ስታር አባል የሆኑት መቼ ነበር?

የአባልነት ጊዜዎንስ እንዴት ይገልጹታል?

አቶ አበራ፦ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ አበራ ክሊኒክ በብሉ ስታር አባልነት

የተመዘገበ ክሊኒክ ነው፡፡ በኔትዎርኩ የአባልነት ጉዞዬ እጅግ በጣም

አስደሳች ነው፡፡ ክሊኒኩ ጥሩ ስም የነበረው ሲሆን አባል ከሆንን

ጀምሮ በይበልጥ በራሴ እንዲሁም በአካባቢው ዘንድ ከፍተኛ የሚባሉ

ለውጦችን በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዙሪያ ለመፍጠር በመቻሌ

በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ኔትወርክን ከተቀላቀሉ ጀምሮ እስካሁን በዚህ

ዙሪያ በበቆጂ ምን ምን ለውጦች ተስተውለዋል?

አቶ አበራ፦ ብሉ ስታርን ከተቀላቀልን ጀምሮ በበቆጂ ብዙ ለውጦች

ታይተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በዛ ያሉ ክሊኒኮች በኔትወርኩ

መታቀፋቸው፣ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው፣ ማሪ ስቶፕስ

በዞናዊ አስተዳደር ከተዋቀረ በኋላ ደግሞ ከሃላፊዎች ጋር በቀላሉ

ለመገናኘት መቻላችንና የረጅም እርቀት አድካሚ ጉዞና ድካምን

ማስቀረቱ፣ የአገልግሎቱ ተደራሽነትና የአገልግሎት ዓይነቶች መጨመርና

በአካባቢው ዘንድ በቤተሰብ እቅድ ላይ ያለው ግንዛቤ መቀየርና

የመሳሰሉት የታዩ ድንቅ ለውጦች ናቸው፡፡

ኮከብየብሉ ስታር እንግዳችን

ቡፖ|7

Page 10: MSIE Newsletter Dec 21_2

ብሉስታር፦ እንደ ጤና ባለሙያ በበቆጂ ከተማ በቤተሰብ እቅድ ላይ

ያለው የአስተሳሰብ ለውጥ ምን ይመስላል? መጀመሪያ የብሉ ስታር

ጽንሰ ሃሳብ ሲተገበርና አሁን ያለውስ ለውጥ ምን ያህል ነው?

አቶ አበራ፦ ለውጡ ከፍተኛ ነው፡፡ በፊት ሴቶች የቤተሰብ እቅድ

አገልግሎት ለማግኘት ወደተቋማችን የሚመጡት ተደብቀው ነበር አሁን

ግን በተደረጉ ቅስቀሳዎችና ግንዛቤ መፍጠሪያ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች

በነጻነትና በግልጽነት እንዲሁም ከባለቤቶቻቸውና ከቤተሰብ አባሎች

ጋር አብረው በመምጣት የሚገለገሉበት ሁኔታ እየተስተዋለ ነው፡፡

በዚህም የተነሳ የሚፈጠሩ አደጋዎች እየቀነሱና ክሊኒኩ በቀን ውስጥ

የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቁጥርና የአገልግሎት

አይነቶች ከበፊቱ በእጅጉ ከፍ እንዲሉ ለማድረግ ተችሏል፡፡

ብሉስታር፦ አበራ ክሊኒክን ለዚህ ከፍተኛ ውጤት ያበቁት ነገሮች

ምንድን ናቸው ብለው ያስባሉ?

አቶ አበራ፦ ለዚህ ከፍተኛ ውጤት መገኘት ዋነኛ ምክንያት ብዬ

የማስቀምጣቸው ነገሮች የተለያዩ ስልጠናዎችን መውሰዴና መተግበሬ፣

በክሊኒኩ ከሚገኙት የጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበርና በመተጋገዝ

መስራቴ፣ ለአካባቢው ህብረተሰብ ጥሩ ውጤት ያስመዘገበና ጥራቱን

የጠበቀ አገልግሎት በመስጠታችን፣ ልዩ ልዩ የምክክርና የደንበኛ

ክትትል ስራን በመስራት ከደንበኞቻችን ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር

መቻላችን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ቡፖ|8

Page 11: MSIE Newsletter Dec 21_2

ብሉስታር፦ የክሊኒካል ጥራት (clinical quality and

infection prevention) ለእርስዎ ምን ማለት ነው?

በክሊኒክዎ ውስጥስ ምን ዓይነት ድርሻ አለው?

አቶ አበራ፦ የመጀመሪያው የህክምና ህግ ንጽህና ነው፡፡ ንጽህና

ከተጠበቀ የሚደርሱ ጉዳቶች እጅጉን ይቀንሳሉ፡፡ በክሊኒኩ ውስጥ

ማንኛውንም የምንጠቀምበት እቃ ንጽህናው የተጠበቀ መሆኑን

በሚገባ እናረጋግጣለን፤ ባለሙያውም እጁን በሚገባ መታጠቡንና

ጓንቶች መጠቀሙን እናረጋግጣለን፡፡ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ፣

ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ጥንቃቄ መውሰድና ቁስልን በሚገባ ማጠብ

ስቴሪያላይዘር፣ አልኮል፣ አዮዲን፣ ሀይድሮጅን ፐር ኦክሳይድና

የመሳሰሉትን መጠቀም ለክሊኒካል ጥራት ወሳኝነት አላቸው፡፡

ብሉስታር፦ የብሉ ስታር ኔትወርክ አሰራር ላይ ቢደረጉ የሚሉት

ማሻሻያዎች ወይም የበለጠ ለስራችን ጠቃሚ ይሆናሉ የሚልዋቸው

ጥቆማዎች ካሉ?

አቶ አበራ፦ እስካሁን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ

ነው፤ ሆኖም በቆጂ ከተማ ውስጥ የቤት ለቤት ቅስቀሳ አናሳ ነው።

ህብረተሰቡ በቤተሰብ እቅድ ዙሪያ ግንዛቤን የሚፈጥሩ ዝግጅቶችን

እንዲታደም ማድረጉ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የጤና በጎ ፈቃደኛ

ሰራተኞች ሰዎችን የማሳመንና የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ

የማስተማር እንቅስቃሴዎችን ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ ህብረተሰቡ

እንዲለወጥና በራሱ ተነሳሽነት ወደ ክሊኒኮቹ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡

ብሉስታር፦ አቶ አበራ በድጋሚ እንኳን ደስ አልዎት! ለመጪው የስራ

ዘመን ደግሞ መልካሙን ሁሉ እንመኝልዎታለን፡፡ ስለነበረን አስደሳች

ቆይታ እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡

አቶ አበራ፦ እኔም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡

ቡፖ|9

Page 12: MSIE Newsletter Dec 21_2

ቡፖ|10

እስቲ ይሞክሩት (የጠቅላላ እውቀትና የማስተዋል ጥያቄዎች)

1.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የብሉ ስታር ሶሻል

ፍራንቻይዚንግ ፕሮግራሙን መቼ የጀመረ ይመስልዎታል?

2.በመላው አለም የብሉ ስታር አጋር የጤና አውታሮች በስንት

ሃገሮች ላይ ያሉ ይመስሎታል?

3.በኢትዮጵያ እንዲሁም በዓለም ላይ ስንት የብሉስታር አባል

ክሊኒኮች ያሉ ይመስልዎታል?

4.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል አገልግሎት መስጠት የጀመረው መቼ

ይመስልዎታል?

5.ማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ከብሉስታር አባል ክሊኒኮች ጋር በመሆን

እስካሁን ለምን ያህል አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሎት የሰጠ

ይመስልዎታል?

6.ከዚህ በታች የምታዩት ምስል ውስጥ ሻማ፣ በክብሪት ሳጥን

ውስጥ ያሉ ክብሪቶችና ስፒሎች በጠረጴዛው ላይ ተቀምጠው

ይታያሉ፡፡ ጥያቄው የበራውን ሻማ በሚታዩት ቁሳቁሶች ተጠቅመው

ከግድግዳው ላይ ማጣበቅ ሲሆን ሻማው ግን በፍጹም

ቀልጦ ጠረጴዛው ላይ እንዳይንጠባጠብ ማድረግ መቻል

ነው፡፡ እስቲ ይሞክሩት፡፡

7. ሁለት እናቶች አና ሁለት ሴቶች ልጆቻቸው አሳ በማጥመድ ላይ

ናቸው፡፡ እናም አንድ ትልቅ፣ አንድ ትንሽ፣ እና አንድ ወፍራም

አሳ አጠመዱ፡፡ የተጠመዱት አሳዎች ሶስት ቢሆኑም ሁሉም

ሴቶች አንድ አንድ አሳ ይዘዋል፡፡ እንዴት ሊሆን ቻለ?

8. የሚመለከቱትን ምስል ወደ አራት ተመሳሳይ ምስልና ቅርጽ

ወዳላቸው ምስሎች ይከፋፍሉ፡፡

Page 13: MSIE Newsletter Dec 21_2

ቡፖ|11

በብሉ ስታር አውታር ክሊኒኮች ውስጥ አባል በሆኑ 622 ክሊኒኮች ላይ ላለፉት 10 ወራቶች (ማለትም እ.ኤ.አ ከታህሳስ 01 እስከ ጥቅምት 31, 2015) ከተከናወኑ አበይት አገልግሎቶች ውስጥ በከፊል፡-

➢ አጠቃላይ የቤተሰብ እቅድና ስነተዋልዶ ጤና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን የተጠቀሙ ተገልጋዮች ብዛት 537,108 ነው።

➢ ከላይ ከተጠቀሰው ቁጥር ውስጥ፡-• የአዩሲዲ (IUCD) ተጠቃሚዎች ብዛት 18,297 ነው።• የተለያዩ አይነት ኢምፕላንቶች (Implants) ተጠቃሚዎች ብዛት 46,972 ነው።• ፖስት አቦርሽን የቤተሰብ እቅድ (Post Abortion Family Planning) አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብዛት 49,974 ነው።

ምርጥ 20 የብሉ ስታር ክሊኒኮች

አይ.ዩ.ሲዲ ኢንሰርሽን ኢምፕላንት

እ.ኤ.አ ከታህሳስ 1 እስከ ጥቅምት 31 ቀን 2015 ድረስ በረጅም ጊዜ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቶች የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የብሉ ስታር አጋር ክሊኒኮች፡ ፡

1359

1040

718 637

590 578

481 435

403 345

328 279

270 168

129 123

431 120

81

24

669

533

173 89

142 94

110 258

115 368

459 273

303 395

436 356

64 335

367 536

0

500

1000

1500

2000

2500

Implant

IUCD Ins

Page 14: MSIE Newsletter Dec 21_2

የማስተዋል ጥያቄዎች ምላሾች1. እ.ኤ.አ በ2008

2. በ18 አገሮች ላይ

3. በኢትዮጵያ ከ620 ክሊኒኮች በላይ ሲሆን በዓለም ላይ

ደግሞ ከ3,600 በላይ ናቸው።

4. እ.ኤ.አ ጥር 1976 በዶክተር ቲም ብላክ

5. ከ100 ሚሊዮን በላይ

6. በክብሪት ሳጥኑ ውስጥ የሚገኙትን ክብሪቶች በሙሉ ካወጡ

በኋላ የክብሪት ሳጥኑን በስፒሎቹ ግድግዳው ላይ ያጣብቁት፤

ሻማውን ይለኩሱና እንዳይወድቅ በቅላጩ የክብሪት ሳጥኑ ላይ

ይለጥፉታል፡፡ ጠረጴዛው ላይ ሻማው እንዳይንጠባጠብ የክብሪት

ሳጥኑ ይከላከላል፡፡

7. ሶስት ሴቶች ብቻ ናቸው አሳ ያጠመዱት፡፡ አንደኛዋ እናትም

የእናትዋ ሴት ልጅም ናት፡፡

8.

የሰራተኛነት ብቃት መፈተሻ ምላሽለጥያቄዎቹ ከሰጡት ምላሾች ውስጥ ከ10-12 የሚሆኑትን ’አዎ’

በማለት ከመለሱ እንኳን ደስ አልዎት፤ ከፍተኛ ብቃት ያልዎት

ሰራተኛ ነዎትና፡፡ ከምላሾችዎ ውስጥ ከ7-9 የሚሆኑት ’አዎ’ ከሆኑ

መካከለኛ የስራ ብቃት ያለዎት ሲሆን ’አዎ’ የሚለው ምላሽዎ 6

እና ከዛም በታች ከሆነ በሰራተኝነት ብቃትዎ ላይ መስራትና ለመሻሻል

ጥረት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ቡፖ|12

Page 15: MSIE Newsletter Dec 21_2

Children by choice not chance

Page 16: MSIE Newsletter Dec 21_2

አስተያየት፣ ጥያቄ ወይም ይዘን እንድንቀርብላችሁ የምትፈልጉት እንግዳ ካለ

በነፃ የስልክ መስመር፦ 8044

ኢሜል፦ [email protected]

ፖ.ሳ.ቁ 5775 ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አዲስ አበባ