53
7/25/2019 Cherubs http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 1/53 ` በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል ኪሩቤሎች 

Cherubs

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 1/53

`

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል 

ኪሩቤሎች 

Page 2: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 2/53

ኪሩቤሎች  2016 

2www.tlcfan.org

በታቦቱና በመጋረጃው ላይ 

የመጀመሪያ እትም 

የሁለተኛ እትም 

መብቱ የተጠበቀ ነው፦ 

ኪሩቤሎች 

Page 3: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 3/53

ኪሩቤሎች  2016 

3www.tlcfan.org

 

ርዕስ ገጽ 

1. መግቢያ ........................................................................................................ 3

2. ኪሩቤል ....................................................................................................... 7

3. የነበልባል ስይፍ .......................................................................................... 15

4. የቅድስተ ቅዱሳን ኪሩቤሎች ...................................................................... 21

5. በመጋረጃውና በታቦቱ ላይ ......................................................................... 25

6. ኪሩቤልና ሃሳብ ........................................................................................... 29

7. ኪሩቤል፣ አዳምና ሉሲፈር ......................................................................... 34

8. የክርስቶስ ሃሳብ (ኪሩብ) ............................................................................. 43

9. የእግዚአብሔር ክብርና ኪሩቤሎች ............................................................. 51

Page 4: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 4/53

ኪሩቤሎች  2016 

4www.tlcfan.org

መግቢያ 

“አዳምን አስወጣው፦ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ

ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የሚገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔደን ገነት ምሥራቅ

አስቀመጠ” (ዘፍ. 3፥24)

ኪሩቤል ልክ እንደ አዳማዊ ባሕሪ የማይጨበጡ መንፈሳዊ ነገር ግን ልክ እንደአዳማዊ አዕምሮ ከሰው ልጆች ጋር የቀረበ ግኙኝነት ያላቸው ፍጥረት ናቸው። ይሁን እንጂ

በመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢያን ዘንድ ፈጽሞ ግንዛቤ ውስጥ ያልገባ ሊጠኑ የተገባቸው ፍጥረቶች

ሲሆኑ የራሳቸው የሆነ ደግሞ ሚስጥራዊ ትርጉምና ትምህርት የያዙ ናቸው። ዓለም እነዚህን

ፍጥረት በገነት የሚበሩ ብሎም በፍቅር ቀስት የሰዎችን ልብ በፍቅር እንዲወድቁ የሚወጉ

አድርገው ያምናሉ። 

ብሉይ ኪዳንን የሚያውቁ አማኞች ደግሞ ከዓለም የተለየ ሐሳብ አላቸው።

ይሁን እንጂ ወደ እውነቱ እንብዛም አልቀረቡም። ምክንያቱም ማንኛውም መጽሐፍ ቅዱስ

አማኝ እግዚአብሔርን የሚያመልኩና የሚጋርዱ ገናና መላዕክት አድርገው ያምናሉ። ይህ

በአንድ መልኩ እውነታ ያለው ነገር ሲሆን ነገር ግን አሁን እኛ በእግዚአብሔር መንፈስ

መሪነት ቃሉን ስንመረምር ኪሩቤል ምን? ማን? ለምን? እንደ ሆኑ ሲገባን በጣም

እንደነቃለን። የእግዚአብሔርን ሚስጥር በመረዳት ከእግዚአብሔር ብዙ ነገሮችን

እንደምንጨምር እርግጠኛ ነኝ። ይህም መለኮታዊ የኪሩቤልን ጥላነት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ

እንማራለን። 

መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ስለ ኪሩቤሎች በዝርዝር ብዙ አያወራም። ይሁን እንጂ

ስለ እነርሱ ለመረዳት የሚያስችል በቂ ነገር እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ አስቀምጦልናል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኪሩቤል የምናገኘው በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ ሦስት ላይ ነው።

ዔደን ገነት  ጋር የተገለጡበትን አላማ እግዚአብሔር በግልጽ አስቀምጦልናል። ይህም

አላማቸው በአጭሩ ሰው ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይደርስ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን

መንገድ ለመጠበቅና ሰው እንዳይገባ ለመከልከል የገነትን በር ለመጋረድ ነው። 

Page 5: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 5/53

ኪሩቤሎች  2016 

5www.tlcfan.org

ይህን አላማቸውን ብቻ ማወቅ በራሱ እግዚአብሔርን እንድንባርከው ያደርገናል።

እግዚአብሔር ከዓለም ጠቢባንና አዋቂዎች ሚስጥሩንና ጥበቡን መደበቁ ርቆና አሻግሮ ማሰቡ

ደስ ያስኘዋል። እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔር እንዳቀደውና

እንደወሰነው በራሱ ክፍል ቆሞ እንደሚገባ የተወሰነበትንና የተሰጠውን ሥራ ያከናውናል። 

እግዚአብሔር በቀደመ እውቀቱ መጽሐፍ ቅዱስን ራሱ ለሚስጥሩ መደበቂያ

አድርጎ ይጠቀምበታል። እግዚአብሔር ያልፈቀደለት ሚስጥሩን ሊረዳና ሊመለከት ፈጽሞ

አይችልም። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ራሳቸው በቀጥታ በትክክል እንደሚገባው

አለመተርጎማቸው ሚስጥሩን እግዚአብሔር በቀደመ እውቀቱ ለሚስጥሩ መደበቂያ አድርጎ

በመጠቀሙ ጭምር ነው ብዬ አምናለሁ። 

እግዚአብሔር በተሳሳተ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ውስጥ ሳይቀር ሚስጥሩን

ይደብቃል። ይህም በክርስቶስ ያሉ ሚስጥሩን በመንፈስ መግለጥ ይረዱት ዘንድ ነው። ”

ለእናንተ የመንግስትን ሚስጥር ማወቅ ተስጥቷችኃል” ይህም የእግዚአብሔር ሚስጥር

በመንፈስ መገለጥ ብቻ የሚታወቅና የሚገለጥ ነው። የኛ ክብር ደግሞ ነገርን የተሰወረውን

ሚስጥር ቃሉን አገላብጠን መርመር ነው። 

በማንኛውም አይነት ቋንቋ የተተረጎመ መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የሆነ ስህተት

አለው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳዱ ሰው ሊኖረን የተገባ መጽሐፍ እንደ ሆነ

አምናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ ባይኖር ኖሮ ሰው ምን ይሰራ ነበር ? ያለ እርሱስ እንዴት ሊኖር

ይችላል? ይህ በመንፈስ በመመራት በእግዚአብሔር ሆነ በሰው እጅ የተፃፈ የእግዚአብሔር

ቃል ሰው ወደ ወጣበት ክብሩ እንዴት መመለስ እንደሚችል ያስረዳል። 

የእግዚአብሔር ቃል አሁን ከኛ ጋር መገኘቱ ሰው ከገነትን እንደወጣ የሚያሳይ

በቂ ምስክርም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ መኖሩ በራሱ ሰው እግዚአብሔርን በቀጥታ ማየትንና

መስማትን እንዳጣ በግልጽ ይመሰክራል። ምክንያቱም ሰው እግዚአብሔርን ቢሰማና ቢያይኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ ባላስፈለገ ነበር። ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ቢሰማው ቢያየው ከእርሱ

ከእግዚአብሔር የሚጻፍም ነገር ባላስፈለገው ነበር። 

መጽሐፍ ቅዱስም በተለያየ ትርጉም መተርጎሙ የሚያሳየው ህብረት

ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው ጋር እንደ ተበላሸ ነው። ሰው ሁሉ በአንድ ቋንቋ ቢኖር የተለያየ

ትርጉም ባላስፈለገምው ነበር። ሰዎች መጽሐፍን በተተረጎመላቸው ቋንቋ እየመረመሩ

በመጽሐፍ የዘላለምን ሒወትን ከእነርሱ ይፈልጋሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ 

Page 6: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 6/53

ኪሩቤሎች  2016 

6www.tlcfan.org

“እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኃልና እነርሱን

ትመረምራላችሁ፥ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፥ ነገር ግን ሕይወት

እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።”

(ዮሐ. 5፥39-40)

ኢየሱስ በተገለጠ ጊዜ መርማሪዎች እርሱን መያዝ መንገዱን እውነቱንና

ሕይወቱን መያዝ ተሳናቸው። አልፈው ተርፈውም ተቃወሙት። ወደ ቤት ወደ ወጡበትም

ክብር ለመመለስ ፍላጎት አልነበራቸውም። በዓለም ፍቅር ሁሉ ወደቁ። ቃሉ ከሚመሰክርለት

ከእርሱ ይልቅ የቃል ማስካካትን ማጣመምንና ማቅናትን እርካታ ሕይወት አድርገው

ተቀበሉ። ሥጋዊ አዕምሮዋቸው የቃሉ ፊደሉ ከሚናገርለት ከእርሱ ይልቅ ፊደሉ ላይ አተኮሩ

የሙጥኝ ብለው ፊደሉን ያዙ። የእነዚህ ሰዎች አለ ማወቅ እዕምሮ ቢሱን ማሞ ቂሎን

ትምህታዊ ታሪክ ያስታውሰኛል። መልካም ላማድረግ ፈልጎ መልካም እንዴት እንደሚደረግ

ባለማወቅ ወንድሙን ያጣውን ተረት። እናቴ ልጅ ሆኜ የነገረችኝ ይህን የተረት ታሪክ

አስታውሳለሁ። 

“ወንድሙ በወንዝ ውኃ ውስጥ ወድቆ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ እያለ ሳለ  ፥

በተማረው ሰው ውሃ ውስጥ ሲወድቅ እንዴት ሕይወት ማዳን እንደሚችል የተማረውን

ትምህርት መሰረት እጁን ሰጥቶ እንደ ማውጣት የሕይወት ማዳን መርህ የሚለውን

መጽሐፉን ከቦርሳው አውጥቶ እንዴት ሰው ውኃ ውስጥ ሲውድቅ ማዳን እንደ ሚቻል

ለሚስጥመው ወንድሙ ያነብለታል። ማንበቡን ሳይጨርስ ወንድሙ የለም። ወንድሙ

ሊስምጥ ለመጨረሻ ጊዜ ከማሞ የሰማው ቃል “ከኔ ቀጥለህ ድገመው” የሚል ነበር። በጣም

እስከዛሬ ይገርመኛል የብዙ አስተማሪዎችና ሰባኪዎች አገልግሎት የማሞ ቂሎ አይነት ነው።

ከእኔ ቀጥለህ ደገመው ብለው ሳይጨርሱ ምእመኑ አልቋል። 

ይህ በኢየሱስ ዘመን የነበሩትንና በእኛ ዘመን ያሉትን ሃይማኖተኛ ፈደል

መርማሪዎችን ያሳየናል። ፊደሉን ከ እስከ ሸምድደው አጥንተውታል በቃላቸውም ይዘውታልነገር ግን ፊደሉ የፈጠረላቸው ምንም መልካም ሕይወትና የመንፈስ ፍሬ በሕይወታቸው

የለም። ይህ ሁሉ ሆኖ እነርሱ እንዳጠኑ እኛም የእነርሱን ስህተት እንድንደግም ይፈልጋሉ።

የፈለጉትን ሕይወት በፊደሉ እንዳላገኙት ሊያምኑ እንኳ አይወዱም። እንደ ማሞ ቂሎ ከኔ

ቀጥላችሁ ድገሙት ይላሉ።

Page 7: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 7/53

ኪሩቤሎች  2016 

7www.tlcfan.org

መንፈስ ቅዱስ የቃሉን ፊደል በር ሲከፍት በፊድሉ ውስጥ ጌታን እናያለን። 

ከአዕምሮአችን ያለፈ የመገለጥ ወንዝ በፊደሉ ውስጥና ጀርባ ይፈሳል። የእግዚአብሔር ዔደን

ገነት እንደገና ከነወንዙ ይገለጣል። ከዚያም ወንዝ የሚገኘው ወርቅ መልካም ነው። (ዘፍ.

2፥11-12) በገነት መካከል ያለውን የሕይወት ዛፍ ስናገኝ ጥማታችንና ረሃባችን ይወገዳል።

የሕይወት ዛፍ ኢየሱስ በመቅረዞች መካከለኛ እንደሆነ የገነትም መካከለኛ የሕይወት ዛፍ

እርሱ ነው። ይህን ማየት ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም መያዝ መጨበጥ ማግኘት እንጂ። እነ

ዮሐንስ ይህን አግኝተው ነበር። ለእኛም የሚመክሩንና የሚያስተምሩን ይህን ሕይወት

እንድንይዝ ነው። (1ዮሐ. 1፥1-4)

እግዚአብሔር ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ በኪሩቤል አጥሮታል።ከክርስቶስ መልክ በታች ያልሆነ ወይም ወደ ልጁ መልክ ያልተለወጠ ሁሉ ኪሩቤልን አልፎ

ወደ ዔደን ገነት መግባት አይችልም። ኪሩቤል በእግዚአብሔር ታዘው በመግቢያው ላይ

በጥበቃ በተጠንቀቅ አሁንም አሉ። አብሮአቸውም የሚገለባበጥ የእሳት ስይፍ ከጎናቸው

እየተገለባበጠ አለ። ስለዚህ ወደ ሕይወት ዛፍ ለመግባት የሚፈልግ የግድ ኪሩቤልንና ስይፉን

ማለፍ ይጠበቅበታል። ከወደቀው አዳማዊ ማንነት ሳይላቀቁ  የመልክ ለውጥ ሳያደርጉ

ለመግባት የሚፈልጉ ሁሉ በእሳቱና በሰይፉ የግድ ያልፋሉ። ያለ ለውጥ ሰው ወደ ሕይወት

ዛፍ መመለስ የማይቻል፣  የማይሆን ጉዳይ ነው። ፊተኛው አዳም ፈጽሞ ወደ ዔደን ገነት

ተመልሶ ሊገባ ፈጽሞ አይችልም። 

ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሃሴት አደረገና እንዲህ አለ፦ 

“የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፦ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ልሕፃናት ስል

ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፥ አዎን አባት ሆይ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።”

(ሉቃስ. 10፥21, ሮሜ.11፥33)

ወገኖቼ በክርስቶስ ውስጥ እስካልተጠመቅን ድረስ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ

ካለመጣን በቀር የእግዚአብሔር ቃል በተለያየ ትርጉም ማጥናት ወደ እውነትና ሕይወት

ፈጽሞ አያቀርበንም። ኪሩቤልና ነበልባል ሰይፍ እንዳንገባ ይከለክሉናልና ነው። ስለ ክሩቤል

ስናጠና እግዚአብሔር የህፃን ልብ ይስጠን። እንደ ሙሴ እባብ የሚመስል ነገር እጃችንን

ዘርግተን በእምነት በመውስድ ከግብጽ የምንወጣበት ወደ ክብር የምንገባበት በትር ይሆንልን

ዘንድ ጸሎቴ ነው። የጌታ ቃል ባልጠበቅነው መልኩ ሲገለጥ ምሕታት ሊመስለን ወይም

የአትክልት ቤት ዘበኛ ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን እንደ ማርያም ድምጹን እንደ ጴጥሮስ

ጥራኝ ሳበኝ የምንል እንድንሆን ጸሎቴ ነው። 

Page 8: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 8/53

ኪሩቤሎች  2016 

8www.tlcfan.org

ኪሩቤል 

አሁን እንግዲህ ሃሳባችንን አስባስበን ስለ ኪሩቤል ቀረብ ብለን ከቃሉ በጥልቀት

እንመልከት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኪሩቤል ልዮ የሆኑ የሰማይ ፍጥረታት፣ ሃይልንና

ስልጣንን የተጎናጸፉ እንደ ሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ከዚህ የበለጠ መረዳት ከነዚህ ፍጥረቶች

ጀርባ አለ። ከሁሉ አስቀድመን ክሩቤል የሚለውን ስም ትርጉም በመጀመሪያው በተፃፈበት

ቃል በመረዳት እንጀምራለን። 

כרו

ኪሩብ ማለት የስሙ ትርጓሜ በዕብራይስጡ ሃሳብ የወለደው ስዕል ማለት ነው።

ኪሩቤል ሃሳባዊ ነገር ናቸው። ማለትም በአዕምሮ የሚገኙ ስዕሎች የሚመሰሉም ናቸው።

በጥቅሉ ኪሩብ በእንግሊዘኛው ስናስቀምጠው  (cherubim are IMAGINATIONS)  ኪሩብ

አይነ ህሊናና ሃሳብ ጥላና ምሳሌ ናቸው። በቃል ውስጥ ያሉ የእውነተኛ ሃሳብ፣ የክርስቶስ

አዕምሮና መልክ ጥላ ናቸው። እነዚህ ኪሩቤሎች ክንፍ አላቸው። ሕዝቅየል ይህን በሰማይ

ተመልክቷል ለኛ በቃሉ አስቀምጦልናል። 

ስለ ሰማይ ከእግዚአብሔር የተማረ ወይም ዘፍጥረት በሸመገለው አይን የሚለውንመጽሐፌን ያነበበ ሰው ምን እንደሆነ ያውቃል። ሰማይ ከጭንቅላታችን በላይ ከፍ ብሎ ያለ

ግዑዝ ነገር ሳይሆን በእኛ ውስጥ ላለው ለመንፈሳችንም ጥላ ምሳሌ እንደሆነ ልናውቅ የገባል።

ይህን ስንል ግን መንፈሳዊ አለም የለም ፍጥረታዊ ሰማይም የለም ማለታችን አይደለም። ያ

እንዳለ ሆኖ መንፈሳችን ራሱ ደህሞ የሰማይ ነጸብራቅ ነው። ስለዚህም እነዚህ ፍጥረታት

እየበረሩ ያሉት በሰማይ ብቻ ሳይሆን በእኛም በመንፈሳንም ውስጥ ነው። የመንፈሳችን ምሳሌ

የሆነው ቅድስተ ቅዱሳን ኩሩቤሎችን በውጡ እንደያዘ መንፈሳችንም አሁን እንዲሁ ነው።

መንፈሳችን በውጡ ኪሩቤሎችን ወይም አይነ ሕሊናዎች፣ ሃሳቦችን ይዟል። 

ስማይ ከሆነው ከመንፈሳዊ አዕምሮ የተቀደሰ ሃሳብ የሚመጣው በክንፍ እንደ

ሚበር ፍጥረት ሃሳብ ወደ ህይወታችን እየተወረወረ እየበረረ ይመጣል። እንደ ማይጨበጥ

ሃሳብ  የራሱን ቅርፅና ምስል በመንፈሳችን ውስጥ ሃሳብ አካልን ይይዛል።  ሃሳብ(አዕምሮ)

ሰውም ሆነ እግዚአብሔርም አላቸው። ስለዚህ ምንም ጥርጥር የለውም እነዚህ ስእላዊ ሃሳቦች

ከሰው ወይም ከእግዚአብሔር ሊመጡ ይችላሉ። ነገር ግን ልናውቀውና ልናተኩረው

የሚገባው በሚታየው ዓለም የተገለጡ በዙራያችን የምናያቸው ነገሮች ቁሳቁሶች ሁሉ

የመነጩት መጀመሪያ ከአዕምሮ ከሚገኘው ሃሳብ መሆኑን ነው። 

Page 9: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 9/53

ኪሩቤሎች  2016 

9www.tlcfan.org

ሃሳብ ከቃልም ይቀድማል። ሰው ሆነ እግዚአብሔር በመጀመሪያ አስበው

ይናገራሉ። እግዚአብሔር ሁሉን በፍጥረት ወቅት በቃሉ ከሃሳቡ አውቶታል። ይህን እውነት

ደግሞ የነገሮች ሁሉ ምንጭን ከሚናገረው የዘፍጥረት መጽሐፍ ሁሉን በቅደም ተከተል

ልንመለከት እንችላለን። 

“እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ 

የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥

በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም

ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤

ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።” (ዘፍ. 1፥27-28)

ይህ መልክ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ተስለም)

צלם

መልክ የሚለው ቃል ማለትም በዕብራይስጡ ተስለም ተብሎ የተጻፈው ኪሩብ

ከሚለው ቃል ጋር አንድ አይደለም። ይሁን እንጂ የሁለቱ ቃል ትርጉም የሚሰጠው

ተመሳሳይ መልዕክት ነው። ኪሩብ ማለት ከላይ እንዳየነው ስዕላዊ ሃሳብ ማለት ነው። ተስለም

በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ መልክ ተብሎ የተጻፈው ሃሳብን የሚወክል ነው። ይህ ከሆነ

ሰው የእግዚአብሔር መልክ ነው ሰንል እግዚአብሔርን እንደሚያስብ ማሰብ የሚችል ነው

ማለት ነው። የማሰብ ብቃት ካለው ሰው ደግሞ የራሱ የሆኑ በመንፈሱ ውስጥ ያሉ እንደ

እግዚአብሔር ስዕላዊ ሃሳቦች ወይም (ኪሩብ) አሉት። 

ይህ ደግሞ ኪሩቤሎች ከእግዚአብሔር ሆነ ከሰው ሊነጠሉ የማይችሉ በቅርበት

ከሰውም ሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ያሉ መሆናቸውን ያስረግጥልናል። ኪሩቤሎች ስዕላዊ ሃስብ

ወይም መልክ ከሆኑ እግዚአብሔር ካሰበ ሰውም ካሰበ እነዚህ ስዕላዊ ሃሳቦች ኪሩቤሎች

በውስጣችንም አሉ ማለት ነው።

Page 10: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 10/53

ኪሩቤሎች  2016 

10www.tlcfan.org

ኪሩቤሎች መቼም ጊዜ ከእኛም ፈጽሞ ሊነጠሉ አይችሉም። ኪሩቤል

የሚያድሩበትና የሚበሩበት ሰማይ ወይም መንፈስ በእግዚአብሔርም በሰውም ውስጥ አለ።

ይህ ሁሉ ይሁን እንጂ ኪሩቤሎች አንዱ ከአንዱ ልዪነት አላቸው። ልዪነታቸው የሚታወቀው

ከምንጫቸውና ከመልካቸው ነው። 

እግዚአብሔርም ሆነ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ  የማሰብ ብቃት እንዳላቸው 

እናገኛለን። ከዚህ የተነሳ ደግሞ እግዚአብሔርም ሆነ ሰው የመፍጠር ችሎታ አላቸው። ነገር

ግን የወደቀው ሰው የሚፈጥረው ከወደቀ ማንነት ነው። ይህ የሰው የመፍጠር ችሎታ ስንል

የእግዚአብሔርን ያህል ሳይሆን በልቡ ውስጥ ያሰበውን ነገር በሚታይ ሁኔታ መግለጡን

ለማሳየት ነው። ይሁንና ሰው በወደቀው ማንነቱ የሚፈጥረው ነገር የሚጠቀመውእግዚአብሔር የፈጠረውን ነገር በመጠቀም አዲስ ፍጥረቱን ይገልጣል። ለምሳሌ ከዛፍ

ወንበር፣ ጠረቤዛና አልጋ...ወዘተ። የወደቀው ሰው ልብ እጅግ ክፉ ሲሆን የእግዚአብሔር

ልብ ግን ፍጹም ንጹህ ነው። (ኤርሚያስ.17፥9) ሰለዚህ በወደቀው ማንነት ስዕላዊ ሃሳብ ውስጥ

የተዛባ ነገር እንዳለ እናውቃለን። 

መጽሐፍ ቅዱስ ከመስመር የወጣ ወይም የእግዚአብሔር ሃሳብ የሚቀይር

አይደለም። ሃሳቡን እርሱ እንደ ፈቀደ የሚያሳይ የሚያስተምር እንጂ። ማንም በራሱ ሃሳብ

የሕይወት ዛፍ የራሱ ሊያደርግ ወይም በራሱ መንገድ ሊሄድና ወደ ገነት ሊገባ ቢጀምርበመንገዱ የማያሳልፈው ኪሩብ መንገዱን ዘግቶበት ይቆማል። የእግዚአብሔር ቃል ይህን

እውነት በቃሉ ያስረግጣል። ኢየሱስም በራሳቸው ሃሳብ ለሚመሩ ፈሪሳዊያን ያስተማራቸው

ይህን ነው። 

“እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኃልና T INK እነርሱን

ትመረምራላችሁ፥እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፥ ነገር ግን ሕይወት

እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።” 

(ዮሐ. 5፥39-40)

ፈሪሳዊያን ስላለፈውና ስለሚመጣው የቃሉን ፊደል መርምረዋል። የዘላለም

ሕይወት እንዳላቸው ያሰባሉ።  እነርሱ ያሰቡትና የተረዱት ሕግና ቃሎች

ለእነርሱ የሕይወት ዛፍ መንገድ ቁልፍ አድርገው ያሰባሉ። 

Page 11: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 11/53

ኪሩቤሎች  2016 

11www.tlcfan.org

ፊደሉንም መመርመር የሕይወት ዛፍን ፍሬ እንደሚያስበላቸው አድርገው

ያስባሉ። ፈሪሳዊያን በመንፈሳዊ ትምህርትቤታቸው፣ በቤተ ክርስቲያናቸው፣ በጉባኤያቸው፣

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸው፣ በሰንበት ትምህርታቸው በፈጠሩት ሃሳብ ጎርፍ ጭልጥ ብለው

ተወሰዱ። እነዚህ ሁሉ ጥናታቸው ወደ እውነት እውቀት እንብዛም አላመጣቸውም። (2ጢሞ.

3፥7) እየተማሩ እውነትን (ክርስቶስ ኢየሱስን) ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ አልቻሉም። 

ይሁንና በዚህ ዘመን የምንገኝ እኛ እራሳችን የእነርሱን ስተት እየደገምን ከእነርሱ

በላይ የፈሪሳዊያን ስፍራ ወረስነው። ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ቀን ከሌሊት ፈደሉን

እንመረምራለን። በቃላችንም ሸምድደን እንይዛለን። ለምን ? ወደ ጌታ ለመምጣት ካልሆነ

እንደ አባቶች ለኛም ቃል በቃል ላይ መጨመር ፈጽሞ አይጠቅመንም። 

እግዚአብሔር አንዳዶች ግን ባለንበት ዘመን የቃሉ ፈደል የእኛ ቃል መረዳት

የሕይወት መንገድ፣ እውነትና ሕይወት እንዳልሆነ በመንፈስ

ተረድተናል። ኢየሱስ ብቻ ሕይወት ነው። እርሱ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነው። ቃሉ

ይመስክርለታል ቃሎቹ ፊደሎቹ ግን ያን ሕይወት አይደሉም። 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ዔደን ገነት ሃብት ብዙ ነገር በዝርዝር እናገኛለን።

ነገር ግን በሕወታችን ካልተረጎምነው ምንም መንፈሳዊ ጥቅም በጌታ ያለውን ሕይወት

ለመኖር ከቃሉ ጥቅምን አያስገኝልንም። ወደ እዚህ ሃብት እንዳንገባ ኪሩቤሎች (ሃሳቦች)

ይከለክሉናል። ክርስቶስ መንገድ እስከ ሚሆነን ድረስ የግድ የሕይወት

መንገዳችንን የዘጉ ኪሩቤሎች አሉ። 

ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ከሺ በላይ የሚሆን የቃላት ስህተቶች ስላላቸው

ብዙ መጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ወደ ዕብራይስጡና ግሪኩ መንፈሳዊ እውነታዎችንና

ነገሮችን ለማሰባሰብ ዞር ብለዋል። ይሁንና ይህም መሆኑ ላለንበት ችግር የመፍትሄ መልስ

አይደለም። ምክንያቱም ቃሉ እንዳስረዳን ኪሩቤሎችና ወዲያና ወዲህ የሚገለባበጥ የእሳትሰይፍ በሰው አዕምሮ ውስጥ ሁሌ አሉ። ያለ ክርስቶስ ቅባት ወደ ሕይወት ዛፍ ለመግባት

ከሞከርን እነዚህ የሚገድሉ ደግሞም የሕይወትን መንገድ የሚዘጉ ፈደሎች

ናቸው። 

የዕብራይስጡ፣ አረማይኩና ግሪኩ የጠሩ መጽሐፍ ቅዱሶች ናቸው ተብሎ

ይታመናል። ምክንያቱ ዋና ቅጂዎች ናቸው። ይሁን እንጂ እነዚህም ቃሎች ኪሩቤልን

አያስወግዱም።

Page 12: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 12/53

ኪሩቤሎች  2016 

12www.tlcfan.org

ኩሩቤሎች በቅድስትና በቅድስተ ቅዱሳን መካከል ባለው መጋረጃ ላይም አሉ።

ነገር ግን ጳውሎስ በቆሮንጦስ ላይ እንዳስተማረን ይህ መጋረጃ እንዲወሰድ ወደ ጌታ ዞር

ማለት ይገባል። (2.ቆሮ.3፥15-18) ቃሉን በእነዚህ ቅጂዎች ብናጠና አሁንም የምንረዳው

ማንም ስጋዊ ስው እንዳይገባ ኪሩቤል እንደ ሚጠብቁ ማንም ወደ ውስጥ ለመግባት ቢመጣ

በሰፍ ወይም በቃል እንደ ሚዋጉ ነው። ውጊያው ሰማይ በሆነው በአዕምሮአችን ውስጥ ነው።

ምሽጉም ከፍ ባለው በእግዚአብሔር ሃሳብ ላይ የሚነሳው ሃሳባችን እርሱ ኪሩቤል ነው።

ይህን ሁሉ ዕብራይስጡም ሆነ ግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል። 

ኪሩቤል በሰማይ በመንፈሳዊው ግዛት ቢኖሩም ባይኖሩም እኛ ግን የምናተኩረው

በውስጣችን ስላሉት ኪሩቤሎች ነው። እነዚህ በውስጣችን ያሉ ኪሩቦች የሕይወት መንገድእንደ ተዘጋ በሃሳባችን ይጋርዱናል።  ስለዚህም ሰው ወደ እውነት እውቀት ወይም ወደ

ሕይወት ቃል ሳይለወጥ ሊመጣ አደማይችል ያስረግጣሉ። የቃል እውቀት ያለ ሕይወት

ሰዎች ሊሰበስቡ ይችላሉ። ነገር ግን እውቅት ያለ ሕይወት ትርፍ የለውም ቢኖረውም ትርፉ

ትዕቢት ብቻ ነው። ለትዕቢተኛው ደግሞ ሕይወት ፈጽሞ ከእነርሱ የራቀ ነው። 

የምናነባቸው ማንኛውም አይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በኪሩቤሎችና

በእሳት ሰይፍ የታጠሩ ናቸው። በውስጣቸው በቃሉ ውስጥ መጋረጃ አለ። ከኪሩቤል መጋረጃ

ጀርባ የተደበቀው ቃል ወይም የወርቁ ኪሩቤል እንዳይገለጥ ኩሩቤሎች የቃሉን ደጆችጋርደው ይገኛሉ። እነርሱ እስካልተወስዱ ድረስ ወደ ሕይወት ዛፍ መድረስ ፍጽሞ

አይቻልም። ኪሩቤሎች ከነመጋረጃው ሊቀደዱ ይገባል። 

ሕይወት የሚገኘው በቃሉ መንፈስ ውስጥ እንጂ በቃሉ ፊደል ውስጥ አይደለም።

ሥጋዊው ሰው ከላይ ካልተወልደ በቀር መንግስቱን ሊያይ አይችልም። በተጨማሪም ይህ

አይነቱ ሰው ገብቶ የሕይወትን ዛፍ ሊበላና ሊኖር ስልጣን የለውም። (ዮሐ.3፥3) ዳግም

ያልተወለደ ሰው በቃሉ ደጅ ውስጥ መግባት የማይታሰብ ነው። ምክንያቱም እርሱን

እንዳይገባ ለመከልከል ኪሩቤል ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን የሕይወትን መንገድ መዝጋትሥራ እየተወጡ ስላለ ነው። 

ጌታችን በተቀበረበት የአትክልት ስፍራ በመቃብሩ ላይ የተገጠመው ድንጋይ

የሕግ ጥላ ነው ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም ሕጉ የተጻፈው በድንጋይ ላይ ነው። ይህ ብቻ

አይደለም። ሕይወትን በውስጥ አሸገው፣ ደበቀው፣ ለሦስተ ቀንና ሌሊት በውስጡ ሸሸገው።

ይህ ነው ሚስጥሩ ድንጋይ ወይም ሕጉ ሲፈታ ወይም ሲገጥ በሕጉ ውስጥ የተሰወረው

ሕይወት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይገለጣል።

Page 13: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 13/53

ኪሩቤሎች  2016 

13www.tlcfan.org

ክርስቶስ ከሕጉ ጀርባ በትንሳኤው ጉልበትና መልክ ይገለጣል። ጳውሎስ ስለዚህ

ድንጋይ ምን እንዳለ እንመልከት፦ 

“እናንተም በሕያው በእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፦ ሥጋ በሆነ

በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፦ በእኛም የተገለጠ የክርስቶስ 

መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።” 

(2ቆሮ. 3፥3)

ሕጉ በልባችን ላይ የሚጻፍ ነው። ካልተፈታ ግን ኢየሱን ማየት አንችለም። ነገር

ግን የሕግ ወይም የድንጋይ ልብ በጥሬው እስካለ ድረስ ክርስቶስ ፈጽሞ አይገለጥም። 

ክርስቶስ ራሱ ከውስጥ ጥሶ ወጥቶ በመቃብሩ አትክልት ሰፍራ ካልተገለጠ ሁላችን ባዶ፣

ጨለማና ያለ ሕይወት ነን። እግዚአብሔር ያቀደው ሰዓት ሲደርስ የሕይወት መንገድ ሲገለጥ

መቃብሩን የሚጠብቁ ኪሩቤሎች ስይፋቸውን ይዘው ይተኛሉ። የታተመው ድንጋይ

ይንከባለላል። 

ክርስቶስም በክብርና በድል ከውስጥ ይነሳል። በምናነበው ቃል ውስጥ ሳይቀር

ሕያው ሆኖ ከውስጥ ይወጣል፣ የገለጣል። እርሱ ደግሞ ሕይወት

የሌለው የማይጠቅም ሃሳብ ከፊደል መውስድና መመገብ ይቀራል። ያኔ የሚገድል ፊደል

የለም ሕይወትን የሚስጥ መንፈስ ከቃሉ ይወጣል። ቃሉም ወደ ሰማይ ወጥቶ ሕይወትን

ይስጣል። በሙታን መካከል አይገኝም በሰማያችን በእኛ በሕያዋን ውስጥ ገብቶ ለዘላለም

ይኖራል። በሰማይ እናገኘዋለን በሕይወትም እንኖራለን። ዳግም የተወለደው በሕይወት

መኖር የሚጀምረው በመንፈሱ ውስጥ ክርስቶስ ሲገባ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ እንዳለ

እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ በመንፈስ የሰማይ ምሳሌ በሆነው በመንፈሳች ውስጥም ከመንፈሳችን

ጋር አንድ ሆኖ ይኖራል። 

የመጀመሪያው አዳም በዔደን ገነት ውስጥ ሞተ ሁሉን ይዞ ወደ መቃብር ገባ

ነገር ግን ሁለተኛው አዳም ሁሉን የዞ የመቃብር ስፍራ በሆነው ያትክልት ስፍራ ተነሳ።

እርሱም በመጀመሪያው አዳም የሞተውን ሁሉ ሰው በውስጡ ይዞ ወደ አባቱ ገባ። 

Page 14: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 14/53

ኪሩቤሎች  2016 

14www.tlcfan.org

የመጀመሪያው አዳም ሕይወትን አወደመ፣  አጠፋ የሁለተናው አዳም ደግሞ

ሞትን አወደመ አጠፋ። ይህ ደግሞ ምንኛ የሚደንቅ የሰው ልጆች ሁሉ ተስፋ ነው። ሮሜ

5፣ 1.ቆሮ.15፥21-23 ምንም እንኳ የያዝነው መጽሐፍ ትርጉም  ብዙ የቃላት ስህተት

ቢኖሩበትም የተራቡ ሰዎች የእግዚአብሔር ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት  ሰዓት ሲመጣ

ይሰማሉም፣ ይኖሩማል። ምክንያቱም ሁሉ በራሱ ተራ ይሆናልና ነው። 

በሌላው አንጻር ደግሞ ምንም እንኳን ቃሉን በግሪክና በዕብራይስጥ ቢመረምሩ

ወደ ክርስቶስ ዞር ካላሉና ከላይ ካልተወልዱ ድናጋዪና መጋረጃው በአዕምሮአቸው ሁል ጊዜ

ይኖራል። ይህም መጋረጃ ኪሩቤልን ያሳያል። መጋረጃውም በመቅደስ ውስጥ ተጋርዶ ወደ

ሕይወትን እንዳንቀርብ ያርቀናል ይጋርደናል። የእሳት ስይፍም ሆነ ኪሩቤል መጋረጃውእስከ አለ ድረስ ሁሌም በልባችን ወደ ሕይወት እንዳንደርስ ሊከለክሉን አሉ። 

“ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና ፥ 

በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና፣ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት

በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፥ 

ወደ ጌታ ግን ዞወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወስዳል።” 

(2ቆሮ. 3፥14-16)

ሕግ በጥሬው ወይም ፊደል ብቻ ሲሆን ይገድላል። የሕጉ መንፈስ ግንሕይወትን ይሰጣል። (2ቆሮ. 3፥3-6, ዮሐ. 6፥63)

“የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፦የሚሰራም 

፦ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ

ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፦ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅላጥምንም

እስኪለይ ድረስ ይወጋል፦ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፥እኛን

በሚቆጣጠር በእርሱ አይኖቹ ፊት ሁሉ የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ ፦

በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።” (ዕብ. 4፥12-13)

Page 15: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 15/53

ኪሩቤሎች  2016 

15www.tlcfan.org

ፊደል የእግዚአብሔር እውነት ሲደብቅ ሕያው የሚሰራው የቃሉ መንፈስ ደግሞ

ይገጠዋል። መንፈስ ሁሉን ይከፍታል፣ ይገልጣል፣ ነፍስን ከመንፈስ ይለያል። የመንፈስ

ሰይፍ አለ የሥጋ ሰይፍ ደግሞ አለ። ሕይወት የሚሰጥ ቃል አለ። ሞትንም የሚሰጥ ቃል

አለ። በአንድ በኩል ሕያው ቃል በሥጋ ውስጥ የተደበቀውን ምድረበዳ ሲገልጥ። ሕያው

ያልሆነ ቃል ደግሞ በዚያው ሰው ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ገነት በሚፈጥረው

ኪሩብ ( ሃሳብ) ይዘጋዋል። 

በመቅደሱ ውስጥ ሁለት ኪሩቤሎች እናያለን። አንደኛው በመጋረጃው ላይ

የተጠለፉት ሲሆን ሁለተኛዎቹ ደግሞ በምሕረት መክደኛው ላይ ያሉ ሙሉ ለሙሉ ወርቅ

የሆኑት ናቸው። መጋረጃው ላይ ያሉት ኪሩቦች ሊቀደዱ ሲገባቸው ምሕረት መክደኛውላይ ያሉትን ግን ልንመስላቸው ይገባል። መጋረጃው ላይ ያሉት አዳማዊ ሳብንና መልክን

ሲያመለክቱ ቅድስተ ቅድሱሳን ውስጥ ያሉት የክርስቶስን አዕምሮ፣ ሃሳብና መልክ

ያመለክታሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር በቅድስተ ቅዱሳን እንዳሉት ኪሩቤሎች እንድንሆን

አማኞችን ይጠብቅብናል። ይህም የልጁ መልክ ነው። ሕዝ.1-10

Page 16: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 16/53

ኪሩቤሎች  2016 

16www.tlcfan.org

የነበልባል ስይፍ 

“አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ

ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።” 

(ዘፍ. 3፥24)

ይህ በዔድን ገነት ምሥራቅ የተቀመጠ ሰይፍ በብዙ ሰዎች የእግዚአብሔር ሕያው

ቃል ነው ተብሎ ተተርጉሟል። ይህ ግን በቃሉ የእውነት ብርሃን ውስጥ ፍጽሞ የተሳሳተ

መረዳት ነው። እውነት ነው ስይፍ የሚወክለው ቃልን፣ ድምጽንና ንግግርን ነው። ነገር

ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ የምናገኘው ሁሉ ሰይፍ የሕይወትን ቃልን አይወክልም።

ምክንያቱም ሞትን የሚያመጣ ቃል ወይም ሰይፍ አለ። 

ዕብራውያን 4፥12 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፦ የሚሰራም፣ሁለትም አፍ

ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው። ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ

ድረስ ይወጋል። የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል። እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ አይኖቹ

ፊት ሁሉ የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ነገር የለም። እንደሚል

የእግዚአብሔር ቃል በሰው ልብ ያለውን ነገር ሲገልጥ በምስራቅ ዔደን ገነት የተቀመጠው

ግን የሕይወትን ቃል መንገድ ይዘጋል። ወደ እርሱ የሚቀርበውን ሰው ሁሉ ይገድላል።

ሰው ወደ ገነት መግባት ቢፈልግ ስይፉ ይከለክለዋል። በክርስቶስ ካልሆኑ በቀር ይህን ስይፍማለፍ አይቻልም። የቃሉ ፊደል ይገድላል። መንገድንና አዕምሮን ያጨልማል። ነገር ግን

እግዚአብሔር ይመስገን ሕያው ቃል የተፈታ ቃል ደግሞ ሕይወትን ይሰጣል።

መንገዳችንንና አዕምሮአችንን ያበራል። “የቃልህ ፍቺ ያበራል።” “ሕግህ ለመንገዴ ብርሃን

ነው።” 

“ነፍሴን ከሞት እግሮቼን ከመውደቅ አድነሃልና፦በሕያዋን ብርሃን 

እግዚአብሔርን ደስ አስኘው ዘንድ።” (መዝ. 56) ፥13)

“ሕግህ ለእግሬ መብራት ነው፣ ለመንገዴ ብርሃን ነው።” ((119)፥105)

Page 17: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 17/53

ኪሩቤሎች  2016 

17www.tlcfan.org

“ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርህራኄ

ምክንያት ነው፥ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት

ያበራል እግሮቻችንም በሰላም መንገድ ያቀናል።”(ሉቃ.1፥78-79)

ከለይ ከተመለከትናቸው ቃሎች እንደምንረዳው የእግዚአብሔር ሕያው ቃልየሚሰራው ስራ ፈጽሞ በዔደን ገነት በር ላይ ከተቀመጠው ስይፍ ይለያል። ምክንያቱም

በገነት በር ያለው የያዘው ሞት ብቻ ነው። በውስጡም ሊሰጠው የሚችል ሕይወት የለውም። 

ይህ በዔደን ገነት በር ላይ ያለው የሚገለባበጠው ሰይፍ ፊደልን ይወክላል።

በስጋዊ አምሮ ስልጥኖ የግብረ ገብ ስርአት አቅጣጫ ሊያሳየው ሁሌ ወደ ዔደን ገነት

ሳይለወጥ ለተጠጋ አማኝ ሁሉ ሊገድለው ሁሌ እየተንቀሳቀሰ እየሰራ ይኖራል። ነገር ግን

ሕይወት በውስጡ የለውም ፊደል ይገድላል። ምክንያቱም የሚያገለግለው እንደዚህ ሰይፍ

ሞትን ነው። ማንም ወደ እርሱ ቢቀርብ ስይፉ ፈደሉ ይገድለዋል። (2 ቆሮ.3፥7፣1ቆሮ.15፥56)

በምስራቅ ዔደን ገነት ያለው ሰይፍና ኪሩቤል ዋና አላማ ሰውን ከሕይወት

ለማራቅ መሆኑን በጣም ልናውቅ ይገባል።  ነበልባሉ ሰይፍ ሞትን እንጂ ሕይወትን

አያገለግልም። ይህ ሰይፍ የሞት ስይፍ ነው። የመንፈስ ቃል አይደለም ፈደል ቃል ፍጥረታዊ

እውቀት፣ አዳማዊ ድምጽና ሃሳብ ነው። 

ነበልናሉ ስይፍ ፊደል  ወደ እግዚአብሔር መንገድ አይወስድም ደግሞእግዚአብሔርንም አያሳይም። ወደ ሕይወትም አይመራም አያስገባም። ነገር ግን

ሃጢያተኛና አዳማዊ አዕምሮ የያዘ ሰው ወደ እግዚአብሔርና ወደ ሕይወት ዛፍ መገኘት

እንዳይመጣ በእግዚአብሔር ታዞ መንገድ ይዘጋል። 

ሰው በሕጉ ፊደልና ሕጉን በማድረግ እንደማይጸድቅ ሰው በዔደን ገነት ባለው

የፊደል ሰይፍ ውስጥ ወደ ሕይወት ከቶ አያመጣም። አሁን ባለንበት ዘመን ቤተክርስቲያንን

የሞላው ይህ ስይፍ ወይም ፊደል ነው። 

Page 18: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 18/53

ኪሩቤሎች  2016 

18www.tlcfan.org

ሁሉ ሲመዝ የሚታየው ይህንኑ ሰይፍ ወይም ፊደል ነው። በነበልባሉ ሕዝቡ

እያሟሟቀ ሕይወትን ከመስጠት ፋንታ ይገድላል። አማኝ በአድርግ አታድርግ ፈጽሞ ወደ

ሕይወት አይመጣም። (ቆላ. 2፥20-23) የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆይ ስማ!!! በቤተክርስቲያንህ

ያለ የፊደል ሕግ ሆነ ማንኛውም ሰው ሰራሽ ሕግ፣ ስርአትና ሃይማኖታዊ ልምምድ ወግ

ምንም ለውጥ በሕይወታችን አያመጣብንም ሕይወትንም አሰጠንም። የመንፈስንም ፍሬ

ፈጽሞ እንድንወልድ አያደርገንም። ሁሉ ወግና ስርዓቶች የሞት ቃሎች የሚገድሉ የሚያጠፉ

ናቸው። በነበልባሉ ሙቀት እንዳንታለል እንጠንቀቅ። 

በሌላ መልኩ ደግሞ ሕያውና በመንፈስ የተፈታ ቃል ደግሞ ብርሃንን በመስጠትበሕይወት እድትኖር ያደርግሃል። እንዳትገባ ሰማይ በሆነው አዕምሮህ ወዲያና ወዲህ እየበረሩ

የሚከለክሉህን ኪሩቤሎችህን  ሃሳብህን ያስወግድልሃል። የእግዚአብሔር ቃል

ሕያው ነውና፣ የሚሰራም ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው። ነፍስንና

መንፈስንም ጅማትንና ቅላጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል። የልብንም ስሜትና አሳብ

ይመረምራል፥ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ አይኖቹ ፊት ሁሉ የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ

በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። 

የእግዚአብሔር ሕያው ቃል ሥጋዊ የሆነውን መንፈሳዊ ከሆነው ይለያል። ሁሉነገር ወደ መኖር የመጣው በዚህ ሕያው የእግዚአብሔር ቃል ነው። በነበልባል ሰይፍ

የሚያልፍ ሥጋን ሁሉ ይበላል፣ ይቆረጣል ብሎም ይሞታል የገደላል። 

እግዚአብሔር፦  “ሃሳቤ እንደ ሃሳባችሁ መንገዳቸሁም እንደ መንገዴ አይደለም

ይላል።” (ኢሳ. 55፥ 8)

እግዚአብሔር ከገነት ባያስወጣን ኖሮ በስጋዊ አዕምሮ በዔደን እንኖር ነበር።የሕይወትንም ዛፍ በልተን በወደቀ ማንነት ለዘላለም እንኖር ነበር። እግዚአብሔር በዔደን

ሰይፉንና ኪሩቤልን ያስቀመጠው ያልተለወጠ በሕይወት እንዳይኖር ነው። ፊተኛው አዳም

ፈጽሞ አይገባም። ሁለተኛው አዳም ግን በዚህ ነበልባልም ስይፍ በኩል ቢሆን አልፎ ይገባል።

የሕይወትንም ዛፍ እንዲበላ ስልጣን አለው። ለስጋው የሞተ ደግሞ አይሞትም ስለዚህ

በመጋረጃው ላይ ያለው ኪሩብ በሞተ ሰው ላይ ሃይል የላቸውም። (ራእይ. 22፥14)

Page 19: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 19/53

ኪሩቤሎች  2016 

19www.tlcfan.org

ኪሩቤልና ስይፉ /ሃሳብና የቃሉ ፈደል/ በዔደን ገነት በር በእግዚአብሔር

እንዲቆሙ ተደርገዋል። ባይቆሙ መልካም አልነበረም። እስከ መጨረሻው ባያሳልፉ ኖሮም

ጥሩ አልነበረም። ክርስቶስና የክርስቶስን መልክ የያዘ ሁሉ ግን እነርሱና ስይፉን ያልፋል። 

በሃሳብ  /በኪሩቤል/ የተሞላው ስማያችን/አዕምሮአችን/ የቃሉን ፊደል ይወስድና

የራሱ የሆነ ስዕላዊ  አለምና ስዕላዊ ሃሳብ ይፈጥራል። ይህ ሁሉ ቅዠት እንጂ እውነታ

የለውም። እግዚአብሔር በኪሩቤሎች እጅ ያለው ይህ ነበልባል ስይፍ ይህን አይነቱን ስዕላዊ

ቅዠት በሰው አዕምሮ ይፈጥራል። ይህ ውጤቱ ሞት ነው። በዕብራይስጡ ነበልባል የሚለው

ቃል ላሃት  ተብሎ ተጽፎ ይገኛል። ለሃት ደግሞ ማለት አስማት ማለት ነው። H3858

 

 ל ט –ነበልባል(ላሃት) /    ̣

ዘፍ.3፥24

ይህ ቃል በዕብራይስጡ በዘፀአት ሰባት አስራ አንድ ላይ እናገኘዋልለን።

“ፈርኦንም ጠቢባንና መተተኞችን ጠራ፥ የግብፅም ጠንቋዬች በአስማታቸው 

እንዲሁ አደረጉ። 

ስለዚህ በዕብራይስጡ ትክክለኛ ትርጉም መሰረት ላሃት የሚለው ቃል አስማት

ማለት እንደ ሆነ ተመልክተናል አስማታዊ ሃሳብ በሰው አዕምሮ ውስጥ እንደ ነበልባል ነው።

ለዚህ ነው ማነው ክርስቶስን ከአይናችሁ ፊት የወሰደባች ምትሃት፣ አስማት፣ አዚም

ያረገባችሁ ማነው ብሎ የገላትያ ሰዎችን ጳውሎስ የሚጠይቀው። ገላ.3 

ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ የተጻፈው ነበልባል የሚለው ቃል ምትሃት ተብሎአይተረጎምም።  መጽሐፍ ቅዱስ ስናነብ የማናገኘውን ሁሉ ነበልባል አስማት ብለን

እንዳንተረጉም አስጠነቅቃለሁ። ትክክለኛውን ትርጉም ለማግኘት እያንዳዳችን ቃሉን

በዕብራይስጡም ሆነ በግሪኩ በመጀመሪያ ልንመረምር ይገባል። የአንዱ ቃል ትርጉም ለሁሉ

ይሆናል ብለን ከተረጎምን እንስታለን። ምክንያቱም ለሃት የሚለው ቃል ከሌላ ቃል ጋር

ሲጻፍ የራሱ የሆነ ሌላ ትርጉም ይይዛል። ነገር ግን በዘፍጥረት 3፥24 የሚገኘው ግን ነበልባል

በቃሉ መሰረት አስማት፣ ምትሃትና አዚህም  ተብሎ

ይተረጎማል።

Page 20: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 20/53

ኪሩቤሎች  2016 

20www.tlcfan.org

ይህ አይነቱ የአስማታዊ  ሃሳብ ወይም መረዳት በፊደል ተጠቅሞ ወደ ዔደን

ለመግባት የሚመጣ  ሰው ሁሉ ይገደላል። “አስማተኛይቱን በሕይወት እንድትኖር

አትፍቀድላት።” ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች ሲጽፍ አዚም ይለዋል። 

ለቆሮንጦስ ስዎች ደግሞ ፊደል ይገድላል መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል

አላቸው። 2ቆሮ.3፥6 አሁን

ደግም ስለ ስይፍ እንመልከት። ሰይፍ ማለት በዕብራይስጡ ኬሬብ  ማለት ነው። 

חר

 

የቃሉ ምንጭ የሆነው ካራብ የሚለው ቃል ሲሆን ካራብ ማለት ደግሞ መውጋት፣

ለማስወገድ መቁረጥ፣ ማጥፋትና መግደል ማለት ነው። ምንም እንኳ ሰይፍ የእግዚአብሔርን

ቃል ቢወክልም ሰይፍ ምን እንደሚሰራ ልንዘነጋ አይገባም። ስይፍ የጦርነት መሳሪያም

ነው። በእግዚአብሔር ቃል ሰይፍ ብዙውን ጊዜ የሚገለጠው ከጦርነትን፣ ከፍርድንና

ከጥፋትን ጋር ተያይዞ ነው። ለምሳሌ (ኢሳ.1፥20, 49፥2፥ ኤፌ.6፥17 ,ዕብ. 4፥12፥ ራዕይ.

1፥16, 19፥12,21) ይመልከቱ። 

ኢየሱስ ምንም እንኳ የሰላም ንጉስ ቢሆን እንዲ አለ፦ 

“በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ ሰይፍን 

እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።” ማቴ.10፥34

ልናየው የሚፈለገው ነጥብ ሰይፉ በማን እጅ እንዳለ ነው። ሰይፉ የሚያመጣው

ነገር የሚወሰነው በያዘው ሰው እጅ ማንነት ነው። የፈደል ሰይፍ በሚወድቀው ሰው ሁሉ

ላይ ሞትን ያመጣል፣ ይገድላል። ይህ የሰይፉ ተፈጥሮው ነው። ለነፍስ ድርቀትን ያመጣል። 

ማንም ሰው ሕያው ቃልም ሆነ የሚገድል ፊደል ከአፉ ሲወጣ ለራሱም ሆነ

ለሚሰሙት የሚያስተላልፈው የሚናገረውን ነገር አለ። ምክንያቱም ሰይፍ በሁለት በኩል

የተሳለ ስለሆነ ነው። ከሕይወት ቃል ሕይወትን ከሚገድል ቃል ሞትን ሰው በአንደበቱ

ሊያስተላልፍ ይችላል። 

Page 21: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 21/53

ኪሩቤሎች  2016 

21www.tlcfan.org

“የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፦ከንፈሩም የሚያፈራውን ይጠግባል፣ ሞትና ሕይወት

በምላስ እጅ ናቸው። የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።” ምሳሌ. 18፥20-21, 2ጢሞ. 2፥8

“ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ፣ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፥

በሰይፍም የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል።” 

በራዕይ 13፥9-10

እግዚአብሔር ማንም ስው በፊደል እንዲሞት አይፈልግም። ደግሞም በፈደል

የሚሰሙትን የሚገድል ሰው እርሱ እራሱ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በፈደል እንዲሞት

ይደረጋል። ዛሬ ባለንበት ዘመን ብዙዎች ፊደልን አጣጥመው በማጣቀስ ሰዎችን የመግደል

ሳምንጣዊ ፕሮግራሞች አሏቸው። ይህ አውቀው ወይም ሳያውቁ ሊሆን ይችላል። ነገር ግንውጤቱ ግን ያው ሞት ነው። 

የሕይወትን ቃል ካገለገልክ በሕይወት ትኖራለህ ፊደልን ካገለገልክ አንተም ሆንክ

የሚሰማክ ሰው በፊደል ትሞታላችሁ። ይህ የእግዚአብሔር መለኮታዊ መርህ ነው።

እንደውም ፊደልን የሚያገልግል በቀዳሚነት ሞትን የሚቀበል ራሱ ነው። (2ጢሞ. 2፥8)

ከላይ ያሉትን ጥቅሶች ደጋግመው ያንብቡት። ደግሞ በሰይፍ የሚገድል ራሱ በሰይፍ

ይወድቃል። 

ስለዚህም ምክንያት ኪሩቤልና የምትገለባበጠው ነበልባል ሰይፍ ፍሬ ሞት ነው።

እነሱም በታማኝነትና በትጋት ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ ፍሬ ማንም ሰው እንዳይደርስ

መንገዱን ይዘጋሉ።  በብሉይም ሊቀ ካህኑ ሲገባ እግሩ የሚያሰረው መጋረጃውን ያለፈ

ተመልሶ መውጣቱ አይታወቅም። ነገር ግን የሚወጣበት ጊዜ ካለፈ ሞቷልና በገመዱ ተጎትቶ

ይወጣል። ይህም ማንም ገብቶ ስለማያወጣው ነው። ተጎትቶ ለመውጣትም ገመዳችን ባማረ

ስፍራ ልትወድቅ ይገባል። ያኔም ለሕይወት መንገዱ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን

እናውቃለን። 

ከላይ ባየናቸው ጥቅሶችና ትምህርቶች ኪሩቤሎች እንዴት የእግዚአብሔር ነገርና

የሕይወትን ዛፍ ከሰው እንደ ሚጠብቁ አየተናል። ማንኛውም አይነት ሰው ወደ ሕይወት

ዛፍ ፍሬ እንዳይደርስ እንደሚከለክሉና አልፎም ተርፎ ማንም ሊያልፍ በራሱ ፍቃድ ቢመጣ

ከመሞት እንደማያመልጥና የእነርሱ ማንነትና ትርጉማቸውን በእግዚአብሔር ቃል

ተመልክተናል። እግዚአብሔር ሙሴን በተራራው ላይ እንዳሳየው መሰረት በቅድስተ

ቅዱሳንም ውስጥም ሁለት በወርቅ የተሰሩ ኪሩቤሎች ይገኛሉ። እነዚህን ደግሞ

በእግዚአብሔር ቃል እንመልከት። 

Page 22: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 22/53

ኪሩቤሎች  2016 

22www.tlcfan.org

የቅድስተ ቅዱሳን ኪሩቤሎች

 

“ሁለት ኪሩቤልክ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፦በስርየት መክደናው ላይበሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ።”  (ዘጸ. 25፥18-21)

በመቅደሱ መጋረጃ ላይ የሚገኙት በመርፌ ተሰፍተው የተጠለፉት ኪሩቦች

የሚያሳዩት የሰውን አዳማዊ ሃስብ  ነው። መጋረጃ በቃሉ በሥጋም የተመሰለ  ነው።

ዕብራውያን.10፥19-20 ከአዳም የተወለደ ሁሉ ሥጋ ነው። ዮሐንስ.1፥13, 3፥6 ኪሩቤሎች

ያሉት መጋረጃው ላይ ነው። መጋረጃው እስካልተወገደና እስካልተቀደደ ኪሩቤሎችም

በመጋረጃው ላይ ለዘላለም ይኖራሉ። 

ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ሲያነብ ቃሉ እንኳ እንዳይገለጥላቸው

የሚጋርድ መጋረጃ በቃሉና በነፍሳችን (ልብ) ላይ አለ። (2ቆሮ. 3፥14-18) ይህም የሆነው

እግዚአብሔር ሚስጥሩን ከባለ አእምሮዎች ለመጠበቅ ነው። የሰው ነፍስ (አእምሮ፣ ስሜት፣

ምርጫ፣ ህሊና፣ንቃተ ህሊና ወይም ራስን ማወቅ) ጠቅልሎ የያዘ ነው። ሰው በነፍሱ ጉልበት

ቃሉን ቢመረምር ምንም ሚስጥር ፈጽሞ አያገኝም። ሚስጥር ሊገለጥ የሚችለው በኢየሱስክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። 

ቃሉ ያሰፈልገናል ነገር ግን ኪሩቤልን ልናልፍ ይገባል። አንዳንድ ሰዎች በጥቂት

እውቀት ይሞሉና በኪሩቤሎቻቸው ስተው መጽሐፍ ቅዱስ አይስፈልግም

ይላሉ። ምክንያታቸው ፈደል ይገድላ በማለት የሚል ነው። ነገር ግን በጣም ተሳስተዋል

ፊደሉ በራሱ ችግር የለውም ምክንያቱም በፊደሉ መሃል የሚገኘው ሕጉ ነው። ሕጉ ደግሞ

ቅዱስ፣ ጻድቅና በጎም ናት። (ሮሜ. 7፥12)

ችግሩ ያለው ሕጉ ላይ ሳይሆን ሰው በራሱ ሥጋ ፍቃድ፣ ጥረትና ስራ ሕጉን

ለመፈጸም መሞከሩ ነው። ይህም ፈጽሞ የማይቻል ነው። ሰው ሁሉ በራሱ ጥረት መጠበቅ

ያቃተው ሕግ የሚገኘው በቅድስተ ቅዱሳን በምስክሩ ታቦት ውስጥ ነው። እግዚአብሔር

የሰጠውን ስፍራ ተመልከቱ። ይህም ለእግዚአብሔር ቅዱስ ይሆን ዘንድ ነው። 

Page 23: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 23/53

ኪሩቤሎች  2016 

23www.tlcfan.org

በውጭ ሳይሆን በውስጥ ያለውን ሕጉን ልናውቅና ልንረዳ ይገባል። ምክንያቱም

ሳይገባው ሕጉን የሚያይም ሆነ የሚነካ ይሞታል። ታቦቱ ወደ እስራኤል በተመለሰ ጊዜ ወደ

ታቦቱ ውስጥ ማለትም ሕጉን ከውጭ ሲመለከቱ ተቀሰፉ። ሕጉን ከውስጥ ወደ ውጭ እንጂ

ከውጭ ወደ ውስጥ ባንመለከት መልካም ነው። ምክንያቱም ውጤቱ ሞት ነው። 

ሕጉ ለሥጋዊ አዕምሮ ከባድ፣ ጽኑና ሞትንም የሚያገለግል ነው። ሕጉ

በፍጥረታዊው ሰው ላይ ሲመጣ ይገድለዋል። ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን ፈጽሞ ወርቅ

በሆነው በምሕረት መክደኛ ሲከደንና ሲሸፈንና በልብ ድላት ላይ ሲጻፍ ሕይወትን ይሰጣል

በወርቅ የተሰሩት ኪሩቤሎች በምሕረት መክደኛው አሻግረው ሁሌ አይናቸውን በሕጉ ላይ

ይተክላሉ። ሕግ ደግሞ ወደ ክርስቶስ መልክ ያመጣናል። ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣንሞግዚት አሳዳጊ ነው። ጳውሎስ እንዲህ አለ፦ 

“ ከሥጋ የተነሳ ስለደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፦እግዚአብሔር የገዛ ልጁን 

በሃጢያተኛ ሥጋ ምሳሌ በሃጢያትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፥ እንደ መንፈስ

ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግን ትእዛዝ

ይፈጽም ዘንድ ሃጢያትን በሥጋ ኰነነ።”

(ሮሜ. 8፥3-4)

ሕጉ በራሱ ምንም ችግር የለውም።  ነገር ግን የሚቀበለው ሰው አቀባበልና

አሰማም ወሳኝ ነው። ከውስጥ ወይስ ከውጭ ሊሆን ይገባዋል። ይህ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር

ሕጉን ሰውን ለማጽደቅ አልሰጠውም። ሕግ ማንኛውንም አይነት ሰው አያጸድቅም፣ ነገርግን የጸደቀውን ሰው ወደ ክርስቶስ መልክ እንዲመጣ ይቀድሰዋል።

ሕግ ሃጢያት ምን እንደሆነ ያሳያል። ደግሞም ስለ ክርስቶስና ስለሚመጡ

ዘመኖች ሁሉ ይተነብያ። ሕግ ለሰው ልጆች አዳኝ እንደ ሚያስፈልጋቸው አስረግጦ ያሳያል።

ይህ ብቻ አይደለም ሰው በክርስቶስ በቀር በሌላ ማንኛውም አይነት መንገድ ወደ ሕይወት

እንዳይደርስ ይከለክላል። በዔደን ገነት ምስራቅ የተቀመጡት የኪሩቤልም ሥራ ከሕጉ ምንም

አይለይም። ሰው በራሱ ጥረትና ሥራ ወደ ሕይወት እንዳይደርስ መከልከል ነው። 

Page 24: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 24/53

ኪሩቤሎች  2016 

24www.tlcfan.org

በዕብራይስጡ ትርጉም መሰረት በዘፍጥረት. 3፥24 ላይ (ለመጠበቅ) የሚለው

ቃል በንቃት ዘብ መቆም፣ ከውጭ ወደ ውስጥ ማንም እንዳይገባ በንቃት መከላከል፣ ማገድ፣

ማሰወገድ፣ በውጭ ማስቀረት የሚሉትን ቃላቶች ሁሉ ይይዛል። ይህ ደግሞ የሚያሳየው

ምን ያህል ቢጥር ፍጥረታዊው ሰው ወደ ሕይወት ዛፍ እንዲደርስ እግዚአብሔር

እንደማይፈልግና ለሕይወት ዛፍ ምን ያህል እግዚአብሔር እንክብካቤ እንደሚያደርግ

የሚያመለክት ነው። 

H8104-

-  - shamarשמר shaw-mar' (ለመጠበቅ)  በዕብራይስጡ ሳሃማር ማለት

ነው። (

ይህ የእግዚአብሔር ፍላጎት ብቻ አይደለም። በታቦቱ የላይ በምሕረት መክደኛው

ላይ ያሉት የወርቅ ኪሩቤሎችም አላማ፣ ፍላጎት፣ ተግባርና መንፈሳዊ ሥራ ነው። ታቦቱ

ላይ የምንመለከታቸው ኪሩቦች ሙሉ በሙሉ ወርቅ እንደ መሆናቸው መጠን ሙሉ

የእግዚአብሔርን መልክ እንደያዙ ያሳያል። ከወደቀው ስው ጋር ምንም የሚያገናኝ ባሕሪ

የላቸውም። የወደቀውን ሰው ሊወክሉ አይችሉም። የወደቀው ስው ክብር፣ የወርቅ ማንነትየለውም። የወደቀው ሰው ልብሱ አፈር ነው። እነዚህ ኪሩብ ግን ወርቁን ክርሰቶስን በውስጥም

በውጭም ለብሰዋል ማንነታቸው በሙሉ ወርቅ ነው። 

ሰለዚህ በቅድስተ ቅዱሳን ያሉት ኪሩቦች የሚያመለክቱት አዲሱን ሰው ነው።

እነዚህም ኪሩቤሎች የእግዚአብሔር ልጆች አምሳል ናቸው። ማንነታቸው ንጹህ ወርቅ ነው።

ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊውን ሰውን ይወክላሉ። አሮጌው ሰው ሊሆኑ ፈጽሞ አይችሉም።

ምክንያቱም እግዚአብሔር የፍጥረታዊ ሰው ኪሩብ ሃሳብ  በቅድስተ ቅዱሳን

እንዲሆን አይፈቅድምና ነው። 

እዚህ ላይ ጥንቃቄ ልናረግ የሚገባው በመጋረጃ ላይ ያሉ ኪሩቦችና በታቦቱ ላይ

ያሉት ኪሩቦች ፈጽመው እንደሚለያዩ ነው። በታቦቱ ላይ ያሉት ለታላቅ ሥራ ለሕይወት

ስራ ነው። አይናቸው ያረፈው እንደ እግዚአብሔር ልጆች በደሙ ላይ ነው። እግዚአብሔር

በመሃላቸው ወይም በውስጣቸው ነው። እነዚህ የወርቅ ኪሩቦቹ ዙፋን ከእግዚአብሔር ዙፋን

ጋር ነው። እንደ እግዚአብሔር ልጆች ከጌታ ጋር አብረው የተቀመጡ ናቸው። 

Page 25: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 25/53

ኪሩቤሎች  2016 

25www.tlcfan.org

የእግዚአብሔር ድምፅ የሚሰማው ከእነርሱ መካከል ነው። የምድራዊው ሰው

ሆነ ሃሳብ በእግዚአብሔር ዘንድ ስፍራ የለውም። ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር የተነሳ እርሱ

ክብርን ይወርሳል። እነዚህ የወርቅ ኪሩቦች አይናቸው ሁሌ በምህረት መክደኛው ላይ ነው።

ይህ የምህረት መክደኛ ምሕረት በፍርድ ላይ እንደሚመካ የሚያውቁበት ነው። የወርቅ

ኪሩቤሎች መሰረታቸው ምሕረት ነው።

የኩሩቤሎቹ አይን ያረፈው ሊቀ ካህኑ ስለሁሉ ሃጢያት ስርየት ባፈሰሰው ደም

ላይ ነው። ስለዚህም እነዚህ ኪሩቤሎች የሚያዮት ደም ከአደባባይ ከፈሰሰው ደም ይልቅ

የሚናግረን ደም ነው። ይህም ደም የሚናገረው ሁሉ ሰው ሃጢያቱን በእግዚአብሔር ይቅር

መባሉን ነው። 

እነዚህ የወርቅ ኪሩቤሎች ጥበብ በተሞላ ሰው በእሳት ተነጥረው በመዶሻ

ተቀጥቅጠው የተሰሩ ናቸው። እነዚህ ትክክለኛ የክርስቶስ መልክ ላይ የመጡና በክርስቶስ

ያለው ሃሳብ በእነርሱም ላይ የሆነባቸው ድል ነሺ አማኞች ናቸው። የድል ነሺ አማኝ ፍጻሜ

ከአደባባይ ተነስቶ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ነው። ይህም የኪሩቤሎቹን መልክ ይይዝ

ዘንድ ነው። ዛሬም ለቅድስተ ቅዱሳን የሚበቁ ኪሩቦች ለመሆን ከውጭ ወደ ውስጥ

በእግዚአብሔር በግና በር በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እንግባ። 

Page 26: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 26/53

ኪሩቤሎች  2016 

26www.tlcfan.org

በመጋረጃውና በታቦቱ ላይ

እስቲ ቀረብ ብለን በመጋረጃው ላይ ያሉትን ኪሩቤሎችና በታቦቱ ላይ ያሉየሁለቱን ኪሩቦች ልዩነት እንመልከት፦ 

“መጋረጃውንም ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ

ከጥሩ በፍታም አድርግ፥ ብልህ ሰራተኛ እንደሚሰራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ የሁኑ።”

ዘጸአት. 26፥3

ከላይ እንዳየነው በታቦቱ ላይ ያሉት ኪሩቦች በወርቅ ተቀጥቅጠው የተሰሩ ሲሆን

በመጋረጃው ላይ ያሉት ግን አሰደሳችና ለአይን የሚስቡ መስለው ተሰለው የተጠለፉ ናቸው።

መጋረጃ የሚያሳየው እኔነትን፣ ሥጋንና የአሮጌውን ሰው አዕምሮ ነው። ይህ ደግሞ ኪሩብ

ከሰው የሚነጠል ነገር እንዳልሆነ እግረ መንገዳችንን እንማራልን። መጋረጃውና ኪሩብ

አይነጣጠሉም አንድ ናቸው። 

አማርኛው “ብልህ ሰራተኛ እንደሚሰራ” የሚለውን  በእንግሊዘኛው 

በዕብራይስጡ ደግሞ  (ካውሻብ) ይባላል።  ትርጓሜውም፦  חש

የውበት ሥራ፣ ብልጥ፣ የሚያስደስት፣ የተቀናበረ፣ የተመረተ፣ የታሰበ፣ አጥብቆ

የተመለከት ዋጋ የተሰጠው……… ወዘተ የሚሉት ትርጉሞች ይይዛል። ይህ የመጋረጃ ኪሩብ

አስራሩ ስንመለከተው ልክ ነፍስ የምትሰራው ሥራ አይነት ነው። መጋረጃው ያለው

በአዕምሮአችን ነው። 

ስለዚህ ኪሩብም ተሰለው፣ ተነድፈውና ተጠልፈው ያሉት በአዕምሮአችን ባለው

መጋረጃ ላይ ነው። በክርስቶስ አዕምሮ ሳይሆን በሥጋዊ አእምሮ የምንገልጠው ልክ

የኪሩቦቹን አሰራር ነው። ይህም በሰው የተቀናበረ የታሰበ ነገር ብቻ ነው። 

Page 27: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 27/53

ኪሩቤሎች  2016 

27www.tlcfan.org

በታቦቱ ላይ ያሉት ግን የተሰሩት በመጋረጃው ላይ እንዳሉት አይደለም። ነገር

ግን የተሰሩት በእግዚአብሔር ባሕሪ ማለትም በንጹህ ወርቅ ነው።  የሦስተኛ ሰማይ

የሦስተኛው መቅደስ ክፍል ፍጥረቶች ናቸው። የሚገኙት በመጋረጃው ላይ ሳይሆን በቅድስተ

ቅዱሳን ውስጥ ነው። 

የመጋረጃው ኪሩብ ግን ያሉትና የሚታዮት በከቅድስት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን

ውሰጥ ስንገባ ነው። በቅድስተ ቅዱሳን ያሉት በወርቅ የተሰሩ የክብር እቃዎች እግዚአብሔር

ራሱን የሚገልጥባቸው ናቸው። ጳውሎስ ለዚህ ነው የሮማን ሰዎች በአዕምሮአቸሁ መታደስ

ተለወጡ ያለው። (ሮሜ.12፥2)

በታቦቱ ላይ ያሉት ኪሩቦች የታደሱ የተለወጡ ተቀጥቅጠው በእሳት ቀልጠው

የተሰሩ ናቸው። የእግዚአብሔር አዕምሮ የእርሱም አዕምሮ ነው። የምሕረት መክደኛውና

ኪሩቦቹ የታነጹበት የተሰሩበት ማንነት አንድ አይነት ነው። ይህም ንጹህ ወርቅ ነው።

(ዘጸአት. 37፥6-7) በባሕሪና በሃሳብም አንድ ናቸው። 

የምሕረት መክደኛ፣ መደምደሚያ፣ ማስተሰሪያ ከሆነው ከክርስቶስ በመንፈስም

ሆነ በአቋም አንድ ናቸው። ከእርሱም ላይ በክብር ይነሳሉ። (ዕብራውያን. 9፥5) በታቦቱ ላይ

ያሉት ኪሩቦች ሁለት ይሁኑ እንጂ አንድ አይነት ወጥ መልክ ያላቸው ናቸው። ነገር ግን

የእግዚአብሔር ሃሳብና የእኛ ሃሳብ የእግዚአብሔር ፈቃድና የእኛ ፈቃድ፣ የእግዚአብሔር

አላማና የእኛ አላማ አንድ መሆኑን ያሳያሉ፣ ያመለክታሉ፣ ይመሰክራልሉ። ሁለት በራሱ

የምስክርነት ቁጥር ነው። 

በሁለቱ የወርቅ ኪሩብ መለያየት ፈጽሞ የለም ክንፋቸው እርስ በእርሱ የተያያዘ

ነው። በኪሩብ ማንነት ውስጥ ሰውና እግዚአብሔር አንድ ሆኑ። የእርሱ አእምሮ የእኛ

አዕምሮ መሆኑን በይበልጥ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች እንመልከት። (ፊል. 2፥5-6, 4፥2,

ሐዋ.ሥ. 2፥1, ሮሜ. 15፥6፥ ዕብ.8፥10 በይበልጥ ይህን ደጋግመን እናንብበው፦ (1ቆሮ.6፥

17) እግዚአብሔር የሚፈልገው የእርሱ ሃሳብና አዕምሮ በእኛ እንዲሆን ነው። 

Page 28: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 28/53

ኪሩቤሎች  2016 

28www.tlcfan.org

ከክርስቶስ ጋር የሚተባበር አንድ መንፈስ ነው። የወርቁ ኪሩቦች እርስበእራሳቸውም አንድ ሃሳብ አላቸው። አንድ ናቸው። እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ደግሞም

የሰርየት መክደኛ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር የተጣበቁ ፣ የተሳሰሩ፣ የተገጣጠሙ ናቸው። አንድ

መንፈስ ናቸው። ይህ ብቻ አይደለም፦ ሕጉ በእምሮቸው ማጥናት ማውጣት ማውረድ

አያሰፍልጋቸውም። ሕጉ ላይ የቆሙ ማለት በሕጉ የሚራመዱ ሕጉ በልባቸው የተጻፈ ናቸው

ማለት ነው። ሳጥኑ የሚያመለክተው ልባቸውን ነው። በተጋጠሙበት በታቦቱ ውስጥ ሕጉ

ተጽፎ ይገኛል እንዲሁም ድል በሚነሱ አማኞ። ከውጭ ምንም ሕግ አያስፈልጋቸውም። 

ሕጉ በኪሩቢል ውስጥ በአዕምሮአቸው ውስጥ ትክክለኛ ስፍራውን ይዟል። ታቦቱና በታቦቱ

ውስጥና በታቦቱ ላይ ያሉ ሁሉ አንድ ናቸው። እውነተኛ አንድነት የሚታየው በዚያ ስፍራ

ነው። 

“ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፦ የስርየት መክደኛውንም

በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፦ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፥

የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ።” 

(ዘጸአት.25፥22)

ይህ የነዚህ ኪሩቦች የክብር ማንነት ባህሪ ነው። ነገር ግን ዛሬ ብዙዎች በመስተዋት

በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። ዛሬስ ከእውቀት ከፍለን

እናውቃለን በዚያን ጊዜ ግን እኛ ደግሞ እንደተታወቅን እናውቃለን። (1ቆሮ. 13፥12) በዚያን

ጊዜ የተባለው እንደ ኪሩብ ሆነን በወርቅ ተቀጥቅጠን ተሰርተን የምናበቃበት ጊዜ ነው። ያኔ

እንደ ኪሩብ ፊት ለፊት እናያለን። 

የኪሩብ አይን በሰርየት መክደኛው እንደ ሆነ የኛም አይን ያኔ በክርስቶስ ላይ

በደሙ ብቻ ላይ ይሆናል። አይናችን ፈጽሞ በምሕረቱ ላይ የተከላል። ይህ ያልሆነለት የሰው

ልጆችን ሁሉ መዳናቸውን መመልከት ፈጽሞ አይችልም። እርሱ ግን ሁሉን በምሕረቱ

ዘግቷል። ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል። ይህም የምሕረት መክደኛ ሕጉን በታቹ ገጥሞ

እንደያዘ ፣ የተመካ ማለት ነው። ያቆብ.2፥13 

Page 29: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 29/53

ኪሩቤሎች  2016 

29www.tlcfan.org

“እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።”

(ሮሜ. 11፥32)

የኪሩቤልን እይታ ከዚህ ወደ ሌላ ማንም አይወስደውም አይኖቻቸው በምሕረቱ

ላይ ተተክሏል። በክንፋቸውም ምሕረቱን አቅፈው ይዘዋል። የዚህ ሰፍራ ሚስጥር ገና

በአለም ላሉ ሕዝብና የሰው ልጆች ገና አልተበሰረም። ምክንያቱም ወደ ወርቅ ማንነት

ያልመጣ ሁሉ ይህን ማወቅ እንዳይችል እግዚአብሔር ራሱ ስለዘጋው ነው። ዘመኑ ስላልሆ

ነው። ደግሞም ወደ ቅድስተ ቅዱስን ሕይወት ያልገባ ይህን ሚስጥር ማወቅ አይችልም።

አንብቦ የሚገኝ ሳይሆን በመሆን የሚመጣ ነው። 

ወርቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንን እንደሚወክል ብዙዎቻቸን እንናውቃልንይህም እግዚአብሔርን ራሱን ነው። ኪሩብ የተሰሩት ከተቀጠቀጠ ወርቅ ነው። ኢየሱስም

ለእኛ የተቀጠቀጠ ነበር። እርሱ የእኛ ሂወት መሰራያም  ነው።  እርሱንም ልንለብስና

ልንሞላው ይገባል። በእርሱ እንደ እርሱ ያልተስራ የቅድስተ ቅዱሳንንና በውስጡ ያለውን

ነገር ሚስጥር ማወቅ፣ ማየት ወይም መግባት ፈጽሞ አይችልም። 

Page 30: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 30/53

ኪሩቤሎች  2016 

30www.tlcfan.org

ኪሩቤልና ሃሳብ 

ከዚህ በፊት በዝርዝር ኪሩብ የሚለውን ቃል በዕብራይስጡ ምን ማለት እንደሆነተመልክተናል። ኪሩብ ማለት ሃሳባዊ ስዕል ወይም ሃሳብ  ማለት

ነው። እነርሱም በዕምሮአችን እንዳሉም ምሳሌነታቸውን አይተናል። ነብዩ ኢሳያስ በመንፈስ

ተመርቶ እንዲህ ብሎ ጻፈልን፦ 

“አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፦ 

ይላል እግዚአብሔር።” (ኢሳ. 55፥8)

ሕጉ በራሱ ምንም ችግር እንደሌለው ሃሳብም በራሱ ምንም ችግር የለውም።

ምክንያቱም ሁሉ ነገር የሚጀምረው ከማሰብ ነውና። በአእምሮ ውስጥ አሁን ተጨባጭ

ያልሆኑ ነገር ግን ተጨባጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሃሳቦች አሉ። ችግር የሚመጣው ሃሳቡ

ከሚፈልቅበት ምንጭ ነው። ሃሳብ ከአዳምም ሆነ ከክርስቶስ ሊፈልቅ ይችላል። እግዚአብሔር

ግን በእርሱ ሃሳብ ላይ የሚነሳውን የአዳምን ሃሳብ ፈጽሞ ይጠላዋል። ስለዚህም ይህን ሃሳብ

ባገኘው ጊዜ ሁሉ ያፈርሰዋል። 

“የሰውንም (አዳማዊ) ሃሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሳውን፥ 

ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን..።”

(2ቆሮ. 10፥5)

ሁሉ ሃሳቦች ስተት ናቸው ብለን ልናስብ ፈፅሞ አይገባም። እንዲህ ካሰብን ግን

እግዚአብሔር እንዲያሰብ አድርጎ የፈጠረው ሰው መልካም አይደለም እያልን ነው። ማስብ

ችግር የለውም እንድናስብ በእግዚአብሔር ተፈጥረናል። ይህም እግዚአብሔር የሰጠን መልኩ

ነው። 

Page 31: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 31/53

ኪሩቤሎች  2016 

31www.tlcfan.org

እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው እንደ እርሱ እንዲያስብ በእራሱ በእግዚአብሔር

ሃሳብ ነው። መልክ የሚለው ከላይ እናዳየነው ተስለም በሚለው በዕብራይስጡ ቃል ሲተካ

ሃሳብ ማለት ነው። የእግዚአብሔር መልክ ሃሳቡ ብሎም ከሃሳቡ የሚመነጨው ባህሪው ነው።እግዚአብሔር ደግሞ ሰውን በእንዲህ ያለ ሁኔታ መፍጠሩ በጣም አሰደስቶታል። (ዘፍጥረት.

1፥26-27,31)

እኔ የዘፍጥረት አፈጣጠር እንዲ በመንፈስ እረዳልሁ። መጀመሪያ በእግዚአብሔር

አዕምሮ ሃሳብ ነበርን ከዛም እርሱ እንዲህ አለ ፦ በእኔ ውስጥ ባለው በማይታየው ሃሳቤ

የማየው ሰው የሚታይ ሆኖ ይውጣ እርሱም ሲወጣ የማይታይ ሃሳብ እንደ እኔ ያለው ነገር

ግን እኔ ከማይታየው ሃሳቤ የሚታይን እንዳወጣሁ እርሱም እንደ እኔ ይሁን፦ እግዚአብሔር

የመፍጠር መጀመሪያው ኪሩብ ወይም ሃሳብ ነው። ሃሳብ ሁሉን ይቀድማል። 

ከዛም ተጨባጭና የሚታይን ነገር በቃሉ ሃሳቡን በመናገር ይገልጣል።

እግዚአብሔር ሰውን አሰበ ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ሊገልጠው አሰበ በቃሉ በመናገር

ፈጠረው። አካልን ደግሞ ከምድር አፈር አበጀለት። ይህም በቃሉ ለተፈጠረው ሰው ነው። 

በታቦቱ ላይ ያሉት የወርቅ ኪሩቦች በዔደን ገነት ምስራቅ ካሉት ኪሩቤሎች ጋር

ፈጽመው የተለያዩ ናቸው። በታቦቱ ላይ የተሰሩት የወርቅ ኪሩቦች እግዚአብሔር ሰውን

ሃሳብ ከራሱ አፍልቆ እንደገለጠው እነዚህም ኪሩቦች ከእርሱ ሃሳብ የፈለቁ ናችው። ከውድቀትየተነሳ ይህን ስራ የተቀብሉ ናቸው። በማደሪያው ድንኳን የተሰሩት የወርቅ ኪሩብ

በመንፈሳዊው አለም የሚገኙ የሌሎች ኪሩቦች ምሳሌ ናቸው። (ዕብራውያን. 8፥5, 9፥5)

እነዚህ ኪሩቦች በመንፈሳዊው አለም ከክርስቶስ ጋር በሰማያዊው ስፈራ የተቀመጡ

የእግዚአብሔር ልጆችም ምሳሌ ናቸው። የምሕረት መክደኛው ክርስቶስ እንደ መሆኑ መጠን

መሰረታቸው እርሱ ነው። የሚመለከቱትም የእምነታቸው ጀማሪና ፈጻሚ የሆነውን እርሱ

ነው። የወረቁ ኪሩብ የእግዚአብሔር ልጆችን ሁለተኛውን አዳም ክርስቶስን ሲያሳዩ፥

በምስራቅ ዔደን ገነት የቆሙት የወደቀውን አዳም እሰከ ሃሳቡ ያሳያሉ፣ በጥላነትምያመለክታሉ።

ሰዎችን ቃሉን ሊመረምሩ ይችላሉ ነገር ግን አንዱንም አይረዱትም። ቃሉ

የተፃፈው በእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው። ቃሉ በራሱ ለስጋዊ አዕምሮ እንዳይገለጥ

የሚያደርገው ባህሪ አለው። ፍጥረታዊ ሰው በመንፈስ የተነገረን ነገር ማወቅ አይችልም።

(ዮሐ.5፥ 39, 2ጢሞ. 3፥16, ሉቃ. 18፥34፥ 1ቆሮ.2፥14,16) ኪሩቤሎች ደግም ይህን

የተገለጠውን ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ሥጋዊ እንዳያገኘው ፈጽመው ይጠብቃሉ። 

Page 32: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 32/53

ኪሩቤሎች  2016 

32www.tlcfan.org

ጳውሎስ እንዳለው እግዚአብሔር እርሱን ለሚወዱ ማለት ለሚታዘዙ ያዘጋጀውን

የሰው አይን አላየውም፣ የሰውም ጆሮ አልሰማውም። ነገር ግን እግዚአብሔርን ለሚወዱ

እንደ ሃሳቡም ለተጠሩ ይህ ሚስጥር በመንፈሱ ይገለጥላቸዋል። ምክንያቱም መንፈስ ሁሉን

ነገር ይመረምራል። የእግዚአብሔር የሆዱ ጉርጆች አንኳ በመንፈስ የሚገለጡ ናቸው።

(1ቆሮ. 2፥9-10)

የሰው ልጆችን ሁሉ መዳን የሚያበስር የመንግስቱ ወንጌል ተሰጥቶናል። (ዮሐ.

12፥32) ነገር ግን በእያንዳንዱ ሰው አዕምሮ ያለው የኪሩብ መጋረጃ ካልቀደደ ወደ ሕይወት

ዛፍም ሆነ ወደ እግዚአብሔር ድግስ መግባት አይቻልም። ሰዎችን በትምህርት ወደ ክርስቶስ

ዞር አያደረጉ ይህን መጋረጃ የሚያስወግዱ በየዘመኑ እግዚአብሔር ባሪያዎች አሉት። ይህፀጋ ለጳውሎስ ተሰጥቶት ነበር። ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ የሚያደርጉ ለትሁታን

ይህ ፀጋ አሁንም ይሰጣል። (ያቆ. 4፥6) 

“ ፍለጋ የሌለውን የክርሰቶስን ባለጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፦ሁሉንም በፈጠረው

በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የሚስጥር ሥርአት ምን እንደ ሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ

ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ…”

(ኤፌ. 3፥9) 

ሰዎች በእግዚአብሔር ጸጋ ሳይሆን በቃል ሽምደዳ፣ በሰዋዊ ጥበብ ይህን ሚስጥርለመግለጥ ይሞክራሉ። ነገር ግን የራሳቸው ሃሳብ /ኪሩብ/ መጋረጃ ሚስጥሩን

አንዳይገልጡ ይከለክላቸዋል። ከዘመናት በፊት በእግዚአብሔር ከትውልድ ሁሉ የተሰወረው

ይህ ሚስጥር ለቅዱሳኑ ተገልጧል። ሚስጥሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ

ውስጥ መኖሩ ነው። ደግሞም በዘመን ፍጻሜ ያለው እግዚአብሔር የሚፈጽመው ሃሳቡን

የፍቃዱን ሚስጥር አስታውቆናል ይህም ሁሉ የሰው ልጆች በክርስቶስ ለመጠቅለል ወይም

ለመውረስ ነው። ሁሉን ከእርሱና ለእርሱ ናቸውና በመጨረሳም ሁሉን ይወርሳል። (ቆላ.1፥

26-27)

የፈለገ የመጠቀ ሰዋዊ አዕምሮ ቢኖር መጋረጃውን ሊያልፍ በራሱንም አዕምሮ

መጋረጃ ሊያልፍ ፈጽሞ አይችልም። እግዚአብሔር መጋረጃውን ቀድዶ አፈር የሆነውን

ሰው ወደ ተቀደሰው ስፍራ አልጋበዘም። ለሰዋዊም ጥበብ እግዚአብሔር ተስቦ የለውም።

ሰጋዊ ሰውና ሥጋዊ አዕምሮ በእርሱ ዘንድ ስፍራ የላቸውም። (አቤልና ቃየን) የሚለውን

መጽሐፌን ያንብቡት። ጳውሎስ ስለዚህ ሥጋዊ አዕምሮ ምን ያህል ክርስቶስንና የእርሱን

ሚስጥር ወደ ውስጥ እንዳይገባ እንደ ሚከላከል ሲናገር፦ 

Page 33: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 33/53

ኪሩቤሎች  2016 

33www.tlcfan.org

“ የጦር እቃችን ሥጋዊ አይደለምና ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ

ነው፥ የሰውንም አስብ /መጋረጃ/ ኪሩቤል በእግዚአብሔር እውነት ላይየሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አዕምሮን ሁሉ

እንማርካለን።” (2ቆሮ. 10፥4-5)

እግዚአብሔርን በዔደን ምስራቅ ኪሩቤሎችን ስላስቀመጠ እጅግ አድርጌ

አመስግነዋለሁ። በዚያ ብቻ አይደለም፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥና በሰው ሁሉ አዕምሮ

ስለተቀመጡት ኪሩቦች እግዚአብሔር የተመስገነ ይሁን። አዎ ከአዋቂዎችና ከጠቢባን

ሚስጥሩን ለመከልከል ሰለሰራው ድንቅ ስራ ሁላችን ድል ነሺዎች ይህን መጽሐፍ እንኳን

ለመረዳት የቻልን ልናመሰግነው ይገባል። 

አሁን ግን እኛ ባሪያዎቹና ቅዱሳን ጥልቅ በሆነው ጥበቡ እግዚአብሔር ኪሩቦችን

በፊደሉ፣ በሰው አዕምሮ፣ በሕግ ውስጥ ሚስጥሩን ከሥጋዊ አዕምሮ ለመጠበቅ እንዳስቀመጠገለጠልን። ይህ ብቻ አይደለም፦ ደካማ፣ ሞኝ፣ ትሁት የሆነውን ደግሞ መርጦ ይህን

ሚስጥር መጋረጃውን በመቅደድ ለሰው ሁሉ እንዲያደርስ ጸጋን ይሰጠዋል። 

በይበልጥ ደግሞ እግዚአብሔርን ከምሕረት መክደኛው ላይ ሰለ ሚነሱት ሙሉ

በሙሉ ወርቅ ስለ ሆኑት በውስጣቸው እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር ድምፅ ለሚገልጡት

በመልኩና በአምሳሉ ሰለ ተነሱት ቤቱን በክብር በክርስቶስ ሰለ ሚሞሉት ኪሩቦች ማለትም

ድል ነሺ ስለሆኑት / የእግዚአብሔር ልጆች/ አመሰግነዋለሁ። 

“እግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ ቤቱም በደመና

ተሞላ።” (ሕዝ.10፥4) 

“አብን አሳየን…እኔን ያየ አብን አይቶአል።” (ዮሐ. 14፥8) 

Page 34: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 34/53

ኪሩቤሎች  2016 

34www.tlcfan.org

ኪሩቤሎች በሰው ሦስቱም ክፍሎቹ ይገኛሉ። መንፈስ፣ ነፍስና ሥጋ። ኪሩቤሎች

በአንድ በኩል እግዚአብሔርና ሚስጥሩን ሲገልጡ በሌላው በኩል ደግሞ ሲከለክሉና ሲጋርዱ

እናገኛቸዋልን። ከላይ እንዳየነው ክብር በውስጥ እንጂ በውጭ አይደልም። 

እግዚአብሔር ክብር በማደርይያው ድንኳን ውስጥ በሁሉም ክፍል አለ። ሃሳብም

እንዲሁ ነው። የክብሩ መጠን ግን ይለያያል። እግዚአብሔር ሙሉ ክብሩ ያለውና

የሚገለጠው በምሕረት መክደኛው ላይ ባሉት ኪሩብ ውስጥ ነው። ይህም ውስጠኛው ክፍል

ቅድስተ ቅዱሳን በመንፈስ ውስጥ ነው። 

የእግዚአብሔር ሙሉ ክብሩ ሊገለጥ የሚችለው ከመንፈስ ሲመጣ ብቻ ነው።

ክብሩ ግን ከውስጥ ወጥቶ መድረኩን ሥጋ ላይ ሁሉ ሊታይ ይችላል። ይህ የቅዱሳኑ መንፈስ

ከክርስቶስ መንፈስ ጋር በመዋሃድ የሚመጣ ነው። ከክርስቶስ ጋር የሚተባበር ሁሉ አንድ

መንፈስ ነው። እንዚህ ኪሩቦች የተሰሩት ከላይ እንዳየነው በንጹ ወርቅ ነው። ይህም ወርቅ

የእግዚአብሔር ባህሪ ጥላ ነው። እግዚአብሔር የሚመኝልን ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር አንድ

እንድንሆን እርሱን ብቻ እንድናንጸባርቀው ነው። 

Page 35: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 35/53

ኪሩቤሎች  2016 

35www.tlcfan.org

ኪሩቤል፣ አዳምና ሉሲፈር

 

ከዚህ በመቀጠል የምንመለከተው ትምሕርት በብዙ የሃስት አስተማሪዎች ሰይጣንተብሎ በመተርጎሙ የብዙ የተሳሳቱ ሃይማኖታዊና ዶክትሪኖች እንዲፈልቁ ያደረገ ሃሰት

ትምህርትን በማፍረስ ነው። ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነትና በዕብራይስጡ

መጽሐፍ ቅዱስ አጋዥነት በሕዝቅኤልና ኢሳያስ ላይ የተጠቀሰው ኪሩቤል አዳም መሆኑን

በግልጽ እንመለከታለን። 

“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጥበብን የተሞላህ ውበትህም የተፈጸመ

መደምደሚያ አንተ ነህ፣ በእግዚአብሔር ገነት በኤደን ነበርህ፥ የከበረ ዕንቁስ ሁሉ፣ ሰርድዮን፣

ቶጳዝዮን፣ አልማዝ፣ ቢረሌ፣ መረግድ፣ ኢያስጲድ፣ ሰንፔር፣ በሉር፣ የሚያብረቀርቅዕንቁ፣ወርቅ፣ልብስህ ነበረ፣ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ። በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው

ነበር። አንተ ልትጋርድየተቀባህ ኪሩብ ነበርህ።

 በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ

አኖርሁህ። በእሳት ድንጋዮች መካከልን ተመላለስክ። ከተፈጠርክ ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ

ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ። በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢያትንም ሰራህ፥ ሰለዚህ

እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፥ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፦ ከእሳት ድንጋዮች

መካከል አጠፋሁህ። በውበትህ ምክንያት ልብህ ኮርቶአል፥ ከክብርህ የተነሳ ጥበብህን አረከስህ፥

በምድር ላይ ጣልሁህ የዩህም ዘንድ በተገሥታት ፊት ሰጠሁህ። በበደልህ ብዛት በንግድህም

ኃጢያት መቅደስህን አረከስክ፣ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አምጥቻልሁ እርስዋም በልታሃለች፦ 

በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለው። በውኑ በገዳይህ ፊት፦ እኔ አምላክ ነኝ

ትላለህን? ነገር ግን በገዳይህ እጅ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። 

(ሕዝቅኤል. 28፥12-18, 28፥9)

Page 36: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 36/53

ኪሩቤሎች  2016 

36www.tlcfan.org

“4፤ ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ እንዲህም ትላለህ። አስጨናቂ እንዴትዐረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ! 5፤6፤ አሕዛብንም በመዓትና በማያቋርጥ መምታት

የመታውን፥ አሕዛብንም ባልተከለከለ መከራ በቍጣው የገዛውን የኀጥኣንን በትር

የአለቆችንም ዘንግ እግዚአብሔር ሰብሮአል። 7፤ምድርም ሁሉ ዐርፋ በጸጥታተቀምጣለች እልልም ብላለች። 8፤ ጥድና የሊባኖስ ዝግባ። አንተ ከተዋረድህ ጀምሮ

ማንም ይቈርጠን ዘንድ አልወጣብንም ብለው በአንተ ደስ አላቸው። 9፤ ሲኦልበመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፥ የምድርን ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተአንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች። 10፤ እነዚህ ሁሉ።አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን? ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደሲኦል ወረደ፤ 11፤ በበታችህም ብል ተነጥፎአል፥ ትልም መደረቢያህ ሆኖአል ብለው

ይመልሱልሃል። 12፤ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ!አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ! 13፤ አንተን

በልብህ። ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍአደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ 14፤ ከዳመናዎችከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። 15፤ ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ

ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ። 16፤ የሚያዩህ ይመለከቱሃልና። በውኑ ምድርንያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥ 17፤ ዓለሙን ሁሉ ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችንምያፈረሰ ምርከኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።18፤ የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ በየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል። 19፤ አንተ ግን

እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፥ ተገድለውም ወደጕድጓዱ ድንጋዮች የወረዱት ከድነውሃል፤ እንደ ተረገጠም ሬሳ ሆነሃል። 20፤ ምድርህንአጥፍተሃልና፥ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤

የክፉዎች ዘር ለዘላለም የተጠራ አይሆንም። 21፤ እንዳይነሡም፥ ምድርንምእንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ

ሞትን አዘጋጁላቸው። 22፤ በእነርሱ ላይ እነሣለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ከባቢሎን ስምንና ቅሬታን፥ ዘርንና ትውልድንም እቈርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር። 23፤የጃርት መኖርያ የውኃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 24፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎምሎአል። እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።”

ኢሳ.14 

አዳም በእግዚአብሔር ሃሳብ (ኪሩብ) የተፈጠረ ነው። ዔደን ገነትን እንዲጠብቅ፣እንዲያበጅና እንዲሸፍናት ከጠላት ከሰይጣን እንዲከልላት ነው። ከዛም ምድርን ሁሉ እንዲገዛ

በሁሉ ላይ ስልጣን ተሰጠው። ይህም የገነትን ወንጌልና ጸጋ ይዞ ነው። በዚያ ሕግ እንዲበዛና

ምድርን ሁሉ እንዲ ሸፍን ገነትንም በምድር ሁሉ እንዲያሰፋ ነበር። ነገር ግን መጽሐፍ

ቅዱስ ብርሃን ሰጪ (የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮኮብ)፣ የሚጋርድ ኪሩብ፣ በእግዚአብሔር

መንግስት ተራራ እንደ ነበር ብቃቱንና ችሎታውን ቢነገርለትም  አዳም ይህን

እግዚአብሔርያዊ ተልኮ አልፈጸመም። 

Page 37: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 37/53

ኪሩቤሎች  2016 

37www.tlcfan.org

አዳም የተሰጠውን ገነት በደንብ አልጋረደም። ይልቁንም መቅደሱን አረከሰ።

ሃጢያትንም ሰራ ራቁቱንም ተገኘ። ጥበቡ የሆነው ክርስቶስን የሕይወት ዛፍን አረከሰ

አቀለለ። ከዚህም የተነሳ የሚጋርድ የተቀባ ኪሩብ መሆኑ ቀርቶ፥ ቅባት፣ መንፈስ፣ እሳት

የሌለው ኪሩብ ሆነ። ብርሃን የሌለው ሆነ። ሊሸፍን ቀርቶ እራሱን ሊሸፍን ተገባው።

እግዚአብሔር የተሻለውን ልብስ እስከሚያዘጋጅለትና ዘመኑን ጠብቆ እስከሚሰጠው በቆዳ

ሊሸፈን ግድ ሆነ። የተሻለው ልብስ ባሪያዎቹ የሚያውቁት ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። እርሱ

የጽድቅ ልብሳችን ነው። 

የእግዚአብሔር የተቀባ አንባሳደር በእፍረት ከመቅደሱ፣ ከተራራው (ከገነት)

ተባረረ ይንንም ስፍራ በንቃት ለመጠበቅ በምስራቅ ዔደን ገነት ኪሩቤልንና ወዲያና ወዲህ የሚገለባበጥ ነበልባል ሰይፍን አስቀመጠ። (ዘፍጥረት. 3፥24) በሰው ውስጥ ያለው

የእግዚአብሔር ገነት መጠበቅ ተገባው። አንድ ቀን አዳም በወደቀ ማንነቱ ተንሰቶ እንዳገባ

መግባትም እንዲሳነው ኪሩቦችን ጠባቂ አድርጎ እግዚአብሔር በገነት መግቢያ መንገድ ላይ

አቆመ። 

ይህን ያድርግ እንጂ እግዚአብሔር የሰው ልጆች በአዲስ ፍጥረት ሆነው

የሚገቡበትን መንገድ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አዘጋጅቶም  ነበር። ሰለዚህም ሥራው

እግዚአብሔር ልናመሰግነው ይገባል። እግዚአብሔር በምስራቅ ገነትም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስቃል ውስጥ ኪሩብን ስላስቀመጠ የተባረከ ይሁን። (2ቆሮ.3፥6)

ዮሐንስ በእግዚአብሔር መንፈስ መገለጥ ስለ ሰይጣን በሃሪ ሲጠቅስ ሉሲፈር

Lucifer

  የሚለውንም ስም በዚህ ስፍራ ማጣቀስ ነበረበት ግን አላጣቀሰውም። ለምን?

የሰይጣንን የመጀመሪያ ስም እንኳን አሰቀምጦ እንዴት ይህን ተወው? ወይስ ሉሲፈር ብለን

የምንለው የሰይጣን ስም አይደለም? ሰይጣን ሉሲፈር አይደልም። 

Page 38: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 38/53

ኪሩቤሎች  2016 

38www.tlcfan.org

ብዙዎቻችን ሉሲፈር ሲባል ሰምተናል። እግዚአብሔር የሚጋርድ መለዓክ፣ በጣም

ውብ የሆነ የመላዕክት ሁሉ አለቃ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት

ያደረገ፣ እራሱን እንደ እግዚአብሔር አደርጋለሁ እመለካለሁ ያለ፣ ሙዚቃ በመጫወት ሆነ

በድምጽ የሚስተካከለው የሌለ፣ ኩሩብ እንደሆነ፣ 1/3 መለዓክ አብሮ በእግዚአብሔር ላይ

እንዳሳበረ፣ እስካሁን ከእግዚአብሔርና ከሰው ልጆች ጋር በውጊያ ላይ ያለ. . . ወዘተ።

ዝርዝሩ አያልቅም በጥቅሉ ግን የዘመኑ እጅ የሰጠችው ቤተክርሲያንም የምታምነው ይህንን

ስህተት ትምህርት ነው። 

በራእይ መዕራፍ 12 ላይ ያለው ታሪኩ ወደፊት ስለሚሆን የተነገረ ሆኖ ሳለ

ቤተክርሲያን ሰለ ሉሲፈር መውደቅ ከአዳም መፈጠር በፊት የሆነ ነገር አድርጋ እንዴትልታስተምረው ደፈረች? በእውነት እግዚአብሔር የሰራውን ያማያውቃ መቆጣጠር የማይችል

አምላክ ነውን? እንደዚያ ከሆነ አሁንስ ይህ ነገር በመንግስቱ እንዳይደገም ምን ማረጋገጫ

አለን? እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ለመንግስቱ እስኪያባርረው ድረስ የሚያሰጋው

ነውን? እስቲ ይህን ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጠለቅ ብለን ገብተን እውነቱን

በእግዚአብሔር ቃል እንመርምር። 

ሉሲፈር በአማርኛው የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ፣ ክሩብ፣ ተብሎ በመጽሐፍ

ቅዱስ ላይ የተቀመጠው ነው። ከላይ ያየናቸው ሰዎችና በአሮጊቶች ተረት የተሞሉየሚሏቸውና የሚሰብኳቸው ናቸው። ብዙዎች ይህ ሊሲፈር የሚለው ቃል በመድሐፍ ቅዱስ

ውስጥ ስንት ጊዜ እንኳን እንደተጻፈ አያውቁም። ብዙዎች ልክ እንደ ሰይጣን ተደጋግሞ

በቃሉ የሚገኝ ይመስላቸዋል። በምጽሐፍ ቅዱስ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው ብላችሁ

ይደንቃችኋል? ይህም በትንቢት ኢሳያስ ላይ ምዕራፍ 14፥12 ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን።

ያውም በላቲኑ ቩልጌት ትርጉምና ከእርሱ ብዙ ትርጉሞችን ካከኙ እንደ ኪንግ ጀምስ አይነት

የመጽሐፍ ትጉሞች ላይ ብቻ ይገኛል። 

ይህ አንድ ስፋር ተጽፎ የሚገኝ ቃል ግን የዚህን ሁሉ የክርሲያን እምነት መሰረትሆኖ ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲሁን ስለ ኩሩቦች ያለውን ሚስጥ እንዳናው ጋርዶን ኖሯል።

ይህም ሰይጣን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብተን እውነተኛ ማንነታችንን አወቀን ከእግዚአብሔር

ፍጹም ሕብረትንና የቅድስና ሕይወት እንዳናመጣ እኛን ለመቃወሚያና ለማድከሚያ

ይጠቀመዋል። አማርኛችን የዕብራይስጡን መጽሐፍ መሰረታዊ እውቀት ያላቸው

ስለተረጎሙት በትክክለኛ ቃል የክጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ብለው ትክክለኛ ትርጉሙን

አስቀምጠውልናል። 

Page 39: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 39/53

ኪሩቤሎች  2016 

39www.tlcfan.org

ሉሲፈር፣ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ማለት በጥቅሉ ትርጉሙ። ብርሃንን

የሚሸከም፣ ብርሃንን ተሞልቶ የሚያንጸባርቅ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ፈጽሞ ሰይጣል ሊሆን

አይችልም። በእርሱ ዘንድ ፈጽሞ ከመጀመሪያውም ብርሃን አልነበረም ሊኖርም አይችልም።

በዝርዝር እየገባን ስንሄድ የበለጠ ይህ ስህተት ትምህርታቸው እየጎላ ይሄዳል። አንድ ነገር

ግን እንድታውቁ የምፈልገው እኔ ስይጣን እና አጋንት የሉም እያልኩ አለመሆኑንና ሉሲፈር

የተባለው ኪሩብ ማለት የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ የወደቀው ሰው አዳም እንጂ ሰይጣን

አለመሆኑ እንድታውቁ ነው። 

ይህ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ደግሞ በ2.ጴጥ.1፥19 እና በራእይ.22፥16

ለኢየሱስ ክርስቶስ መልክ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። ታዲይ እንዴት አድርገን ነው ይህንየምናስታርቀው? ኢየሱስ ሉሲፈር ነውን? ወይስ የመጀመሪያውን አዳም የንጋት ልጅ

አጥቢያ ኮከብ ስፍራ ወስዶ ሁለተኛው አዳም የሆነው የእኛ መልክና ምሳሌ? ይህ ሊሲፈር

የሚባለው ቃል ከክርስቶር በኋላ በሶስተኛ ክፍለ ዘመን የጀመረ ከዚያ በፊት የማይታወቅ

እንደሆነ ታላልቅ የሃማኖት መሪዎች በታሪክ ተሞርኩዘው የሚያምኑት እውነት ነው። ይህ

የማይታወቅ መጤና ሰዎችን ለማስፈራራት ብሎም የእግዚአብሔር ሃይል ለማቅለል ታስቦ

የተቀናጀ ከሰይጣን የመነጨ ስህተት ትምህርት ነው። 

እንግዲህ ይህ ሉሲፈር የተባለው የንጋር ልጅ አጥቢያ ኮከብ የወደቀው ሰይጣንካለሆነ ማን ነው? ኢሳያስ የሚያወራው ስለ ባቢሎንና ስለ ወደቀው አንድ ሰው ነው። ይህም

እኔ እንደማምነው የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ስለ ወደቀው አዳም ነው። “አንተ የንጋት

ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥

እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ?” 

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያሳየው ከኢየሱስ በፊት ከውድቀት በኋላ ማንም

የሚያበራና ብርሃን የተሸከመ ከአዳም ውጪ በዚህ ክብር የታየ ሰው አናገኝም። በቃሉ

ኢየሱስ እዳሰተማረን ደግሞ ሰይጣን ከመጀመያም ደግሜ እላለሁ ከመጀመሪያ አንስቶ

ሲፈጠርም ተኮለኛ፣ ነፍሰ ገዳይና የሐሰት አባት ነበር። አዳም ግን በእግዚአብሔር መልክና

ምሳሌ የተፈጠረ ብርሃንን ልክ እንደ አምላኩ የተሸከመና የሚያንጸባርቅ ነበር። እግዚአብሔር

ደግሞ ብርሃን ነው። (1.ዮሐ.1፥5፣ ያቆብ.1፥17) 

Page 40: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 40/53

ኪሩቤሎች  2016 

40www.tlcfan.org

ሰዎች ይህን የኢሳያስንና የሕዝቅኤልን ደግሞም ራእይ አስራ ሁለትን በመጥቀስ

ከሰማይ የወደው ሰይጣን ነው ይሉናል። ነገር ግን ስይጣን አሁንም ከሰማይ አልወደቀምእስካሁን በሰማይ ይገኛል። ራእይ 12 የሚያሳየው ይህንን እውነት ነው። ብቸኛው የመላእክት

አለቃ ሚካኤል የተዋጋው ሰይጣን ያለው በሰማይ ነው። ኢየሱስን ይህን በምድር በነበረበት

ወቅት በመንፈሱ ተምልክቶታል። ሉቃ.10፥18 

ይህ ደግሞ በጥላው 70ዎቹ ደቀመዛሙርት ሁለት ሁለት ሆነውም በተላኩ ጊዜ

ከመሰዎች ሰማይ ላይ አጋንት በመውደቅና ከሰዎች በመውጣት የእግዚአብሔር መንግስት

መምጣት መጀመሯን አብስሯል። ሰይጣን በሰዎች መንፈስ (ሰማይ) ላይ ይዞት የነበረውን

ስፍራ እንዲለቅ በኢየሱስ ስም ተደርጓል። ይህ ደግሞ በእርሱ ባርነት ተይዘው ለነበሩመፈታትና ጤናን አምጥቶላቸዋል። ሰለዚህ ኢየሱስ እዚህ ጋር ያየው ወደፊት ስለሚሆን

ነገር እንጂ ከሺዎች አመታት በፊት ስለሆነ ነገር ወይም አፈ ታሪክ አይደለም። 

ሰይጣን እንደ ብርሃን የብሎ የጠቀሰ ጥቅስ እንግዲ ይህ ኢየሱስ ካየው ትንቢት

ባሻገር በ2 ቆሮ.11፥14 ላይ ጳውሎስ ሰይጣን እራሱን እንደ ብርሃን መላእክት ይለውጣል

ይላል። ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ ላይ የሚገኙት ሁለት ጥቅሶችም ስለ ሰይጣን

ከብርሃን ጋር መያያዝ የሚያመለክትቱ እንደ በማለት መሆኑን ልናውቅ ይገባል። እንደ

ብርሃን ፣ እንደ መብረቅ ካለ መብረቅም ሆነ ብርሃን አይደለም ማለት ነው። ስለዚህ ኢሳያስላይ ያለው ጥቅስ ስለ ሰይጣን እንደማያወራ በዚህም ቃል ደግመን እንመለከታለን። 

የንጋት ልጅ የሚለው ቃልም ራሱ የቻለ ለሰይጣን እንዳልተነገረ የሚመሰክር

ቃል ነው። በዕብራይስጡ ልጅ ማለት “ቤን” ማለት ነው። ይህ ደግሞ የሚያመክተው አባት

እንዳለው የዘር ግንጽ እንዳለውና የተወለደ እንደሆነም ነው። ሰይጣን ይህ ሁሉ የለውም።

ሰይጣን ፍጡር እንጂ ልጅ አይደለም። አዳም ግን ከውድቀቱ በፊት የንጋት ልጅ የብርሃን

ልጅ ነበር። ኢየሱስ ደግሞ ሁለተኛ አዳም ሆኖ መጥቶ። ይህን ስም ለራሱ አውጇል ይህም

ነገሩ መገልበጡን የእግዚአብሔር ሃሳብ እንደ መጀመሪያው መጽናቱን ለማሳየት ነው። “እኔየዳዊት ስር ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።” ራእይ.22፥16 

እንግዲህ አዳምም ሆነ ኢየሱስ ተወልደዋል። አዳም ሆነ ኢየሱስ ብርሃንን

ተሸክመዋል አንጸባርቀዋል። ስለዚህ አዳም ከሰማይ የቀደቀው የመጀመሪያው የሚጋርደው

ኪሩብ እርሱ ነው። በመጀመሪያው አዳም በሃጢያት ምክንያት ያጣነውን ይህን የኪሩቤል

መልክና ክብር የንጋት ልጅነት በኢየሱስ ክርስቶስ በሁለተኛው አዳም መልሰን አግኝተነዋል።

ለዚህም በድፍረት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብተን ስፋራችንን እንድንይዝ መጋረጃው

ተቀዷል። 

Page 41: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 41/53

ኪሩቤሎች  2016 

41www.tlcfan.org

በይበልጥ ደግሞ ለመረዳት የሰይጣንን ማንነትና ምንጭ ተመክተን ከእነዚህ

በኢስያስ፣ በሕዝቅኤልና በራእይ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅስ ጋር እናነጻጽር። ምንም እንኳን

ኢየሱስ ስለ ሰይጣን ጨለማነት የተናገረው ቃል ሁሉን መመልስ ብቁ ቢሆንም በሃይማኖትና

በአሮጊቶች ተረት የጠወለገ አይምሮ ከተኛበት ለመንቃት ብዙ ጥሶችና ፍቺዎች

ስለሚያስፈልጉት ይህን ሃሳብ በዝርዝር እናየዋለን። 

ኢየሱስ ሰይጣንን አንድም ቦታ የወደቀ ኪሩብ ወይም የብርሃን መልዓክ ነው ብሎ

ሲያስተምር አናገኝም። ኢየሱስ ያስተማረውን ትምሕረት ብቻ ይምናምንና የምንቀበል

ከሆንን እንግዲ ቃሎቹን በቅርበት እንመልከት። ሰይጣን ከመጀመሪያ ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ

እንደሆነና በእውነትም ፈጽሞ እንዳልቆመ አስተማረ። 

“44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ

ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ

ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ

የሐሰትም አባት ነውና።” (ዮሐ.8፥44)

ኢየሱስ የሚወደው ሐዋርያ ዮሐንስ ስለ ሰይጣን ከኢየሱስ የተማረውን

ሲያስተምር። ሰይጣን ከመጀመሪያው ሃጢያትን ያደጋል ብሎ አስተማረን። (1.ዮሐ.3፥8)

ዘፍጥረት የጻፈ ሙሴ በዘፍጥረት ሶስት አንድ ላይ እግዚአብሔር ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉየቀደመው እባብ በኋላ ዘንዶና ዲያቢሎስ ሰይጣን የተባለው ከመጀመሪያውኑ ተንኮለኛ እንደ

ነበር ያተምረናል።  (ኢዮብ.12፥16, ኢሳ.45፥1-7, ሮሜ።11፥32-36 ቆላ.1፥15) በእነዚህ

ጥቅሶች መሰረት ፈጽሞ ሰይጣን በኢይሳስም ሆነ በሕዝቅኤል ላይ ለሰይጣን መውደቅ

ከሚጠቀሰው ጥቅስ ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ነው። 

ሰይጣን ከመጀመያ ጀምሮ ነፍሰ ገዳይና ያጢያትን የሚያደግ ከነበረ። ሕዝቅኤል

በደል እስኪገኝብ ድረስ በዔደን ገነት ነበርክ የሚለው ለአዳም እንደሆነ በግልጽ

እንመልከታለን። ሰው በሰይጣን ተፈትኖ በእግዚአብሔር ሊመሰል የፈለገና መልካምና ክፉን

ዛፍ ፍሬ የበላ ነው። ሰው እንጂ የትም ቦታ ሰይጣን በእግዚአብሔር ሊመሰል ሲሞክር

አናገኝም። የባቢሎን ንጉስ የሆነው ናቡ ከደነዖርም የዚህ የአዳም ምሳሌ ነው። በሕይወቱ

የተፈጸመውን ከእነዚህ ጥቅሶች ጋር አያይዘን ብናየው ይህ ከክብሩ የወደው ራሱን ከፍ ከፍ

ሊያደግ የሞከረውና ከዔደን ገነት በደል ሲገኝበት ወደ መቃብር የተጣለው ሰው ነው። 

Page 42: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 42/53

ኪሩቤሎች  2016 

42www.tlcfan.org

ሰይጣን መንፈስ ነው። አመድም ሆነ አፈር ሊሆን አይችልም። ሰይጣን እንደ

ሰው አካል የለውም ስለዚህም ሊበሰብስ፣ ሊተላና ወደ መቃብር ሊወርድ ወደ ሲዖል ሊወርድ

ፈጽሞ አይችል። ሰይጣንና መላዕክቱ የተዘጋጀላቸው የእሳት ባሕር ነው። ሰይጣንን ወደመቃብር ወይም ወደ ሲዖል ግባ ማለት ሞኝነት ቃሉን በሚገባ ካለማወቅ የሚመጣ

ሃማኖተኝነት ነው። አጋንትን እንዴት እንደምለይና ከሰው እንዴት እንደምናስወጣ

“ሃይለኛውን ማሰር” የሚለውን መጽሐፌን አብቡ።

ሰይጣን ደግሞ የወደቀ መላዕክ አይደለም። የወደቊ መላዕክትና ሰይጣን ፈጽሞ

የተለያዮ ናቸው። ሰይጣን በእግዚአብሔር የተፈጠረ ፈታኝ፣ ተቃማሚ፣ ከሳሽ ሲሆን።

ኢየሱስ ሳይቀር በሰይጣ ይፈተን ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ወደ ሰይጣን ፈተና ውስጥ

በእግዚአብሔር ገብቷል። ፈተናውንም አሸንፎ ከምድረበዳ ወጥቷል። በሕዝበ እስራኤልምዘመን ሆነ በኢዮብ ዘመን ሰይጣንን የምናገኘው ሲፈትን፣ ሲቃወምና ሲከስ ነው።

ሰይጣን እግዚአብሔር ካፈቀደለትና እኛ ቅጥራችንን ካላፈረስን ሊነድፈን ሆነ ወደ

እኛ ዝም ብሎ ሊቀርብ አይችልም። የኢዮብ ታሪክና ሰይጣን ኢየሱስን የጠየቀው ጥያቄ

ለዚህ በቂ ምስክራችን ነው። ሰይጣን ደቀመዛሙርቱን እንደ ስንዴ ሊያበጥራቸው ኢየሱስን

ለመነ። እየሱስን ግን ገና በእመንት ስላልጠነከሩ ወደ ፈተና እንዳይገቡ እግዚአብሔር ለምኑ

ብሎ ጸሎት አስተማራቸው። ደግሞ ሰይጣንን እንዲያበጥራቸው የጠየቀውን ፍቃድ

ከለከለው። 

የወደቁ መላዕክት እግዚአብሔር ስለ ስንፍናቸው የሚከሳቸው ናቸው። የቀደቁ

መላዕክት በስንፍናቸው በሰሩት ስራ ምክንያት እስከ አሁን በእስር ላይ ይገኛሉ። የወደቁ

መልዕክት ከሰይጣን የሚለዮበት ዋናው ሰይጣን እስከ አጋንቱ እስካሁን ተፈቶ የሚንቀሳቀስ

ሲሆን የወደቁ መላዕክት ግን ፈጽመው እስከ ታላቁ የነጩ ዙፋን ፍርድ ቀን ድረስ በእስር

ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሉሲፈር ለወደቁ መላእክትም ሆነ ለሰይጣን ስም አድርገን ልንሰጠው

ፈጽሞ አልችልም። ይህ የእግዚአብሔር ቃልን መቃወም ነው። ስለ ወደቁ መላዕክትና

ስንፍናቸው ምን እንደነበር ለማወቅ ከፈለጉ “የወደቁ መላዕክትና የእግዚአብሔር ፍርድ”

የሚለውን መጽሃፌን ያንብቡት። 

እንግዲህ ወንድምና እህቶቼ እነግራችኋለሁ አዳም ከመውደቁ በፊት የተቀባ ኪሩብ

ነበር። ድል ነሺዋ ቤተክርሲያ በጨረሻው ዘመን በራእይ ላይ የምትገለጥበት ልብስ

ብንመልከተው ከሞላ ጎደል በኪሩብ በነበር በአዳም ላይ የነበረው ልብሱ ነው። ነገር ግን

የሁለተኛው ቤት አካል ክብር ከመጀመሪያው ስለሚበልይ የከበሩ ድንጋዮች በድል ነሺዎች

ቤተክርስቲያን ላይ ስሞችን ጨምሮ ተጨምሮባታል። 

Page 43: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 43/53

ኪሩቤሎች  2016 

43www.tlcfan.org

አሁን ይህን መረዳትና የእውነት ብርሃን ይዘን የኢሳያስን 14 ና የሕዝቅኤልን

28 ደግመን አንድ በአንድ እንድናበርው አበረታታለሁ። በእነዚህ ቃል ውስጥ ያሉት ነገሮች

ትኩረት አድርጋችሁ እንዳታይዋቸው እፈልጋለሁ። አንተ ሰው ነህ፣ በልዑል እመሰላለው

አልክ፣ ምድርን ያስጨክ ሰው፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብለሃን አንተ ግን ሰው ነህ፣

መደምደሚያ አንተ ነህ (የሰው ልጆች መሰረት ወይም መጀመሪያ ፍጥረት ማለት ነው።)፣

በደል እስከሚገኝብህ ድረስ፣ በመንገድህ ፍጹም ነበርክ፣ . . . ይህን የመሳሰሉ ቃሎችን

በውስጣቸው እናገኛለን። 

እንግዲህ ሰይጣን ማን እንደሆነና ከመጀመሪያ ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ እንደ ነበር

የኢየሱስ ክርስቶስን ትምሕርትና የሐዋርያትን ትምህርት ካመንን ይህ ሁሉ ቃል ስለ አዳምእንጂ ስለ ሰይጣን ወይም ስለ ወደቁ መላዕክት እንዳማይነገር እናውቃለን።

ኪሩብ የልጁ መልክና ክብር ነው። ሕዝ.1-10 እኛም የተጠራነው ይህን መልክ

እንድንመስል ነው። ድል ነሺዋም ቤተክርሲያን የምትመስለው በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ

ያሉት በእሳት ቀልጠው በመዶሻ ተቀጥቅጠው የተሰሩትን የወርቅ ኪሩቦች ነው። 

Page 44: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 44/53

ኪሩቤሎች  2016 

44www.tlcfan.org

የክርስቶስ ሃሳብ (ኪሩብ)  

ምንም እንኳ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ክብር ሆኖ ሊገለጥ በምድር ቢመጣም

ተሸፍኖም ነበር። ይህ የሆነው በማርያም ማህፀን ውስጥ ሲገባ የእርሷ የሥጋ መጋረጃ

ሸፈነው። ይሁን እንጂ ለዘላለም አይደለም ዘጠኝ ወር ሲደርስ እንደ ህጻን በበረት ተገለጠ።

የእግዚአብሔር ክብር በብቸኛው ልጁ ተገለጠ። ነገር ግን የራሱ ሥጋ  (አካል) ደግሞ

የእግዚአብሔር ታልቅ ክብር ሸፈነ እስከ በዓለ ሃምሳ ብሎም አካሉ እስከ ሆነችው ባለ ብዙ

ብልት ቤተ ክርስቲያ ዘመን ቆየ። በተራራው ላይ ለሶስት ደቀመዛሙር ያለ መጋረጃ

የገለጠላቸው። የእነርሱ መጋረጃ ግን ገና ስላልወደቀ ይህን ክብር የተቀበሉበት ሆነ

የተመለከቱበት መመልከት ያመጣባቸው ሃሳብ ትክክል አልነበረም። 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ክብርና ባህሪ መንጸባረቅ ቢሆነም ይህ ክብር

እንዳያንጸባርቅ የራሱ ሥጋ ብሩህ የሆነውን ክብር ሸፈነ። እርሱ የአለም ሁሉ የመዳን

መንገድና ብርሃን ነው። ነገር ግን ብዙዎች ሊያዩት ሊያገኙት አልቻሉም። ምክንያቱም

በሥጋው ላይ ያለው ማለት በመጋረጃው ላይ የተሰፉት ኪሩቤሎች ናቸው። 

ይህን ክብር ያየ በአዲስ ኪዳን ቀዳሚው ሰው ሽማገሌው ስምኦን ነው። (ሉቃስ. 2፥

25-33) ዩሴፍና ማርያም አብረውት ቢኖሩም፥ መልአኩ ቢነግራቸውም ክብሩ ለእነርሱሳይቀር የተሸፈነ ነበር። (ሉቃስ. 2፥49-50) ምክንያቱ የተባለውን እየሰሙ ይደነቁ ነበር።

እነርሱም የተናገራቸውን ነገር አላስተዋሉም። ስምኦን ግን እነርሱ ያላዩትን ክብር አየ።

ለሽማገሌው መንፈስ በእርሱ ላይ ስለ ነበር የኢየሱስ ኪሩቦች ተቀደዱለት የክብሩን ነጸብራቅ

ተመለከት። ከዚያም በኃላ ለ30 አመት የኢየሱስ ክብር አልተገለጠም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ

ምንም ቦታ መታየቱን አይገልጽም። 

ነገር ግን በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኃላ ኢየሱስ በሄደበት ሁሉ የእግዚአብሔር

ክብር የገልጥ ነበር። ሆኖም ክብሩ በራሱ ኪሩቦች ሥጋ መጋረጃ ተሸፍኖ ነበር። ከዚህምየተነሳ ታምር ቢያደርግ፣ የሞተ ቢያስነሳ፣ ጥበቡን በትምህርት ቢገልጥ ፈሪሳዊያን ከጠራቢ

ልጅ ያለፈ ነገር አልስጡትም። ምክንያቱም እንዳያዮ በእርሱም ሆነ በራሳቸው መጋረጃ

ተጋርደው ነበር። 

እግዚአብሔር ካልሰጠው በቀር የሚሰራቸውን ነገሮች ማንም እንደማይሰራ

ያውቃሉ። ኒቆዲሞስ ይህን መስክሩአል። (ዮሐ. 3፥2) ነገር ግን ማንና ምን እንደ ሆነና ከየት

እንደ መጣ አያውቁም ነበር። በጎ ነገር ከማይወጣባት ከናዝሬት እንደ መጣ ያስባሉ።

ታምሮቹ እጅግ ድንቅ ናቸው። 

Page 45: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 45/53

ኪሩቤሎች  2016 

45www.tlcfan.org

እግዚአብሔር ክበር በእርሱ ያያሉ ነገር ግን እጅግ የበለጠው ክብር በኪሩቦች

ተሸፍኖ ነበና ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ ፥ ከላይም እንደ ተወለደ አያውቁም። (ማቴ.16፥

16) ጴጥሮስ አይኑ እንደ ተከፈተ አይናቸው ተከፍቶ ኪሩቤልን አልፈው ክርስቶስ

የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ አላዩም ነበር። በአደባባይ የሚቀርበው ንጹህ የእግዚአብሔር

መስዋእት አንደሆነ፥ የአባቱን ሥራ ሊሰራ በሁሉ ላይ ጌታ ለመሆን እንደ መጣ አላወቁም

ነበር። የሚመለከቱት አንድ ነገር ቢኖር ጨለማ ብቻ ነው። አመጸኛ አድርገው ነበር

የሚያዩት። 

በመቃብር ውስጥም ክብሩ ተሸፍኖ ነበር። በሥጋዊ አእምሮ የሚመሰለው ድንጋይ

ክብሩን ሸፍኖት ነበር። ጠባቂዎቹ ማለትም በምስራቅ ገነት የተቀመጡትን ኪሩቦችየሚያሳዩትም ፈጽመው ሕይወት፣ ክብር እንዳይገለጥ ሸፍነው ማንም ቀርቦ የሕይወት ዛፍ

እዳይወስድ ጋርደው ነበር። ይሁንና ሥጋዊ አዕምሮም ሆነ ኪሩቦች ክብሩን ለዘላለም ሊሸፍኑ

አይችሉም። ከሶስት ቀን በኃላ እንደ ገና ክብሩ ተገለጠ ታየ። በመጀመሪያ ለወታደሮቹ

ከዚያም ለመቅደላዊት ማርያም ከዛም ለደቀመዛሙርቱ፣ ከዛም በ40 ቀናት ውስጥ ብዙዎች

ተመለከቱት። በመጨረሻም በእርገቱ ላይ ለነበሩ ሰዎች ሁሉ በክብሩ ታየ። 

አንድ ሰው ከትንሳኤ በኃላ ኢየሱስ በቀላሉ ይታወቃል ይገለጣል ለሁሉ በክብር

ይታያል ብሎ ሊያስብ ይችላል። ነገር ግን ይህ አልሆነም። የትንሳኤው አካል እራሱ ክብሩንሽፍኖት ነበር። የሰዎች አይን ሲከፈት ብቻ የሚታይ ነው። የታወቀው እንኳ የእጁን ሚስማር

የገባበት ቀዳዳ አሳይቶ፣ እንጀራ ቆርሶ አብልቶ፣ አሳ የሚገኝበትን ቦታ አመላክቶ፣ በስም

ተጣርቶ…. ነው። ከዚህ መገለጥ በኃላም በኪሩቦች ተሸፈነ። 

ከአርባ ቀን በኃላ እንደ ገና ይህ ክብር ተሸፈነ። ይህም የሆነው ጥቂት ደመና

ከአይናቸው ሰወረው። (ሐዋ. 1፥9) ደመና ሰወረችው። ከዛም ሙሉ ሰማይ የእርሱ መሸፈኛ

ሆነ። ለአስር ቀናትም ከሰዎች እይታ ተሽፈነ። ከዛም በኃላ በተነሳ በሃምሳኛው ቀን ልክ

እንደ ሄደ እንደዚሁ በደመና ተመልሶ ከሰምይ በመንፈስ መጣ። 

በዚያም ጊዜ የተቀበሉት ደመናዎች ብዛት መቶ ሃያ በላይኛው ክፍል ነበር። ከዛም

ይህ ደመና እያደገ ሄደ በበአለ ሃምሳ ቀን 3,000 ደመናዎች ተጨመሩ። (ሐዋ.ሥ. 2፥41)

5,000 ከዚያም በኃላ (በሐዋ.ሥ.4፥4) ከዛም ደመናው ማደጉን መብዛቱን አላቆመም። ከዚህ

ድንቅ ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ክብሩን መግለጡን አላቆመም። አሁን እነዚህ የሚመስሉ

የምስክር ደመናዎች በምድር ላይ እየገለጡት ይገኛሉ። 

Page 46: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 46/53

ኪሩቤሎች  2016 

46www.tlcfan.org

ነገር ግን የራሳቸው ኪሩቦች ስላላቸው ለተከፈተ አይን ወጋረጃው ወደ ጌታ ዞር

በማለት ለተወሰደለት ሰው ብቻ ይታያሉ። ኢየሱስ ሊቀ ካህን የሆነውን ቀያፋን እንዲህ

አለው፦ 

“..ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በሃይል ቀኝ ሲቀመጥ

በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው።” 

(ማቴ. 26፥64)

ቀያፋ ከሞተ ብዙ ዘመናት አልፋል። ኢየሱስ ዝናብ በሚያዘንበው ደመና ይመጣ

ብለው የሚጠባበቁ ግን ብዙዎች ናቸው። ቀያፋና አብረውት ያሉት ታያላችሁ ከተባሉ

ሳይሞቱ እንደ መጣ ፍጹም ግልጽ ነው። ይህም የመጀመሪያው ዝናብና በሐዋርያት ዘመንየወረደው መንፈስ ቅዱስ ሙላት ነው። 

አንዳንዶች ይህ የሁሉ ትንሳኤ ሲሆን የሚሆን ነገር ነው ይላሉ። ቀያፋና

አብረውት ያሉት በተነሱ ጊዜ ሁሉ አይን በሚመለከተው ጊዜ የሚሆን ነው ይላሉ። ነገር

ግን ይህ ትክክል አይደለም። ነገር ግን ቀያፋና ከእርሱ ጋር ያሉት ሁሉ ደመና በሆኑት

ቅዱሳን ላይ እግዚአብሔር ሲመጣ ተመልክተዋል። ሁሉ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝብ

የሃይል ደመና እንደ ተባሉ ማወቅ ይገባዋል (መዝ. 68፥34-35) ይህ መሰረታዊ መረዳት

ነው። ደግሞም አሁን ከእርሱ ጋር በሰማይ እንደ ተቀመጥን ልናውቅ ይገባል። (ኤፌ. 2፥6)ሰማያዊ ስፈራ የምናየው ስማይ አይደልም፣ መንፈሳዊው ግዛት እንጂ። 

ሰለዚህ እኛ በሰማያዊ ስፍራ የተቀመጥን የእግዚአብሔር ደመናዎች ነን። እርሱ

በኛ ውስጥ አለ። ከእኛ ክብሩ እየወጣ ይታያል። ነገር ግን ኪሩቤሎችን ልዘነጋ አይገባም።

በደመናም ውስጥ ኪሩቦች አሉ። እነርሱም ይሸፍኑታል። ይሁን እንጂ ለእነርሱ የተሸፈነ

አይደለም። ወደ ደመና ለሚመለከቱት እንጂ ምክንያቱም ሥጋዊያን ከሆኑ ሊያዩ ስለማይችሉ

ነው። ጌታ በክብሩ የሚገለጠው በመንፈስ ሙላት ነው። 

እግዚአብሔር የቀጠረላቸው ቀን እስኪደርስ ከምድራዊ የልብ መሻታቸውና

ጨለማ በቀር ምንም አያዩም።  አይኖቻቸው ሲከፈቱ እነርሱም ከእርሱ ጋር በሰማይ

ይቀመጣሉ። በአይን መከፈት ወደ ታልቁ የሕይወት ጉዞ ውስጥ ይገባሉ። በዚህ ባለንበት

ዘመን ከክርስቶስ ጋር በመንፈስ አንድ የሆኑ ክብሩን በአካሉ ማለትም በቅዱሳን ሕይወት

ያያሉ። ይህ ሲሆን ለውጥ ቀርቦአል። 

Page 47: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 47/53

ኪሩቤሎች  2016 

47www.tlcfan.org

“በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በሃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል፣

ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሱ።”

(ሉቃስ. 21፥27-28)

አንዳዶች ይህን በእምነት ብቻ ለመያዝ ያስባሉ። እንደ ደረሱ በእምነት ያውጃሉ

ነገር ግን የክርስቶስ የክብሩ ብርሃን መብራት ሲጀምር አካሉ ትነቃለች፥ በስህተት ውስጥምእንደ ነበሩ በቶሎ ያውቃሉ። ቅዱሳን እውነታው ይህ ነው፦ 

”…አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፣

ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና፥ እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።”

1.ዮሐ.3፥2

መገለጥ ቢመጣ እግዚአብሔር አይናችንን ቢከፍት እርሱ እንዳልተወን ከእኛ ጋር

እንዳለ እንደ መጣ እናየዋለን። መገለጥን በትግስት ልንጠባበቅ ይገባል። እኛ እርሱን ለማየትእንዲህ በኪሩቤሎች ከተቸገርን መንፈስን ያልተቀበሉማ እንዴት ይሆኑ? ኢየሱስን አብን

አሳየን አሉት እርሱም እኔን ያየ አብን አይቶአል ብሎ መለሰላቸው። 

ነጥቡ ይህ ነው መንፈስ አልተስጠም ነበርና ማን እንደ ነበር ሊያውቁት

አልቻሉም። የክርስቶስ ኪሩቦች የአባቱን ክብር ከእርሱ ላይ ሸፍኖ ነበርና ነው። ይህም

በጠያቂዎቹ ውስጥ ያለውን ኪሩቦች ሳንጨምር ነው። በእነርሱ ሥጋ እንዳሉም ልንዘነጋ

አይገባም። ስለዚህም ምክንያት አባቱን ሊያዩ አልቻሉም። ልክ እንደዚሁ በአካሉም

ቤተክርሲያን ሊታይ አልቻለም። ምክንያቱም በመጋረጃው ላይ ያሉ ኪሩቦች በክንፋቸውየክብሩን ጸዳል ስለ ጋረዱ ነው። 

ኢየሱስ በምድር ውስጥ ከተገለጠበት ቀን አንስቶ አባቱን አክብሯል፣ ገልጡአል።

ይህ ለፍጥረታት ምን ያህል በረከት እንደ ሆነ መገመት አይቅትም። ከመገለጡ ጋር በተያያዘ

መሸፈን፣ መጋረድ፣ መከልከልም ነበር። 

Page 48: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 48/53

ኪሩቤሎች  2016 

48www.tlcfan.org

እግዚአብሔር ክብር በግልጥ እንዳይታይ አድርጎታል፣ ከበአለ ሃምሳ ጀምሮ

ታላላቅ ነገሮች ደመና በሆኑት ቅዱሳን ተገልጡአል፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ቅዱሳን ደግሞ

እጹብ ድንቅ የሆነውን የእግዚአብሔር ክብር ለመጋረድ የራሱን ድርሻ ተወጥቱአል፣ 

ሳሙኤል ስለዚህ ጨለማ ሲናገር፦ 

በአንድ በኩል መሰወሪያውን ጨለማ ቅድስተ ቅዱሳን ሲያደርግ በሌላው በኩል

ደግሞ በፊቱም ካለው ብርሃን የተነሳ ፍም ተቃጠለ። ማንም ሰው እግዚአብሔር አይቶ

በአዳማዊ ሕይወት አይኖርም። 

“ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፦ አንድ ልጅም ከአባቱ

ዘንድ እነዳለው ክብር የሆነውን ክብሩን አየን።”(ዮሐ. 1፥14)

በሙሉ ሐይሉ ይህ ሕያው ቃል የአባቱን ክብር ገለጠ። በእዚያው ጊዜ ጨለማ

ደመና ሸፈነው፥ ነገር ገን ይህ የሆነበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው። 

“ማንም ፊቴን አይቶ በሕይወት አይኖርም።”

ዘጸ. 33፥20

እግዚአብሔር በምህረቱ ሰው እንዳይጠፋ ራሱን ከሰው አይን ሸፈነ። እግዚአብሔር

ክብር በልጁ በሙላት ተገልጦ ቢሆን ኖሮ ስለ ክብሩ የሚያወራም አይገኝም ነበር። የእርሱ

ሁለተኛ አዳምነት በእምሮው ያሉት ኪሩብ በሚሄድበት ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋረዱት። ይህ

ስንል በዙሪያው ባሉት ሰዎች ላይ ያለን ጥቅጥቅ ጨለማና አዳማዊ ኪሩባቸውን ሳንጨምር

ነው። እግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅ የተገለጠው ጥቂት በጥቂት ነው። አንዳዶች ይህን

ተለማምደውታል። በተመሳሳይ መልክ እነርሱ አንደ እርሱ እግዚአብሔር አንጸባርቀዋል። 

Page 49: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 49/53

ኪሩቤሎች  2016 

49www.tlcfan.org

ሰማእቱ እስቲፋኖስ የመጀመሪያ ምሳሌያችን ነው። ነገር ግን ኢየሱስን ካዩበት

የበለጠ አልነበረም። እውነት ነው አንድ አንዶች ዮሐንስ በፊጥሞ ደሴት ላይ እንደ

ተመለከተው ክበር ሊያዩ ይችላሉ። 

“ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው

ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ

ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር

የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤

ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል

ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።“

ራዕይ. 19፥10፥22፦9 

መልአክ ማለት በግሪኩ አጊሎስ ማለት ነው። 

ትርጉሙም መልክተኛ፣ 

የተላከ፣  ከሌላው ተቀብሎ ለሌላው የሚያስተላልፈው መልእክት ያለው ማለት ነው።

አምስቱን ቢሮዎችንም ያጠቃልላል።

ከላይ እንዳየነው ጥቅስ መሰረት ዮሐንስ ሁለት ጊዜ መላእክ የጌታን ክብር

ነጸብራቅ ተላብሶ ተገልጦለት ነበር። የጌታን ክብር ከመላበሱ የተነሳ መልአኩን ከጌታው

ለይቶ ማየት ዮሐንስ ተሳነው በመልአኩ ፊት ሊሰግድ ተደፋ። ይህ የሚደንቅና ላማሰብ

የሚከብድ ነው። ዮሐንስን የሚያህል ታላቅ በጌታ የተወደደ፣ ጌታን በቅርብ የተረዳ ሰው

በመልአኩ ያየው ክብር ሊያመልክ አስደፋው። ጌታ ይመስገን የጌታ መልአክቶች ምንም

አይነት የጌታ ክብር በላያቸው ቢንጸባረቅ ስግደት አይፈልጉም። ይህ በላያቸው ላይ ለዮሐንስ

የተገለጠው ክብር የእግዚአብሔር ልጆች ፍጻሜ ከዚህም የሚበልጥ መሆኑን የሚያሳይ ነው።መድረስ የተገባን ሙላት ግን የክርስቶስ መልክ ነው። 

የኪሩቤል ክንፍ የምህረት መክደኛውን መጋረዱ የሚገርም ነው። ይህ ታላቅ

ክብር በኪሩቤሎች መሃከል እንደ ሆነ ዛሬም ይህ ክብር በድል ነሺዎች መካከል ነው። (ማቴ.

18፥20) ይህን ክብር በክንፋቸው ባይሸፍኑት ኖሮ በስህተት ሊመለኩ ይችሉ ነበር። 

Page 50: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 50/53

ኪሩቤሎች  2016 

50www.tlcfan.org

እርሱ በሌላ ስፍራ አይደለም ያለው። እርሱ ራሱ በመካከላቸው ባለው ሰማይ

ነው። ይሁን እንጂ በኪሩብ ተጋርዶአል። ሰዎች ከእርሱ ጋር አንድ የሆኑትን ሰዎች ክብር

ቢያዩ በእርግጥ ሊያመልኩ ይቃጡ ነበር። ነገር ግን እንዳይሞቱ እንዲያዩ አልተፈቀደም።“ 

አዳም ጌታን አይቶ የሚኖር የለም፣ (ዘጸ. 33፦20) ነገር ግን ንጹህ ወርቅ የሆኑት ኪሩቦች ግን 

ያዩታል፣ ልበ ንጹሆች እግዚአብሔር ያዩታል። (ማቴ. 5፦8) 

ምድራዊ ሰው ይህን አይነቱን የገነነ አንጸባራቂ የሆነ ክብር ፈጽሞ አያይም።

ይህም አጠራጣሪ አይደለም። ምክንያቱም ለሰዎችም ለኢየሱስም ለሙሴም ጌታ ባለፈ ጊዜ

የተገለጠው እውነት ይህ ነው። 

“ሙሴ ድንኳኒቱን ሊስራ ሳለ እንደ ተረዳ፦ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን…

.ሕጉ ሊመጣ ላለው ነገር የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና።”

(ዕብ. 8፥5, 10፥1) 

በዕብራዊያን ዘጠኝ አምስት ላይ የተጠቀሱት ኪሩቦች ምንም እንኳ ጥላ ቢሆኑ የክብር

ኪሩቦች ነበሩ። የምሕረት መክደኛውን ሙሉ ክብር በውጣቸው ሸፍነው የያዙ ኪሩቦች ናቸው። ይህ

ደግሞ የመጀመሪያውን አዳም የኪሩብነቱ አገልግሎት የሚያሳዮ ናቸው።

“በዚያም ካንተ ጋር እገናኛለሁ..በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል

መካከል በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ አነጋግርሃለሁ።”

(ዘጸ. 25፥22) 

እግዚአብሔር በኪሩቤሎች የሚገልጠው ትልቅ ክብር አለው። እነዚህ ኪሩቦች

የመልኩ መገለጫ የሆኑ ልጆቹ ምሳሌ ናቸው። እግዚአብሔር ማደሪያ ማን ያውቀዋል?

ክብሩንስ ማን ሊያይ ይችላል? 

በብሉይ ኪዳን መጋረድ የሚለውን አጠላበት ጋረደው ይለዋል። በእንግሊዘኛውብሉይ ሲል አዲስ ኪዳን ደግሞ/ 

 

ይለዋል። የሁለቱ ልዩነቶች

በጥልቀት ለማየት  /የቃልት መዝገብ ዝርዝር/ እንመልከት። 

Page 51: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 51/53

ኪሩቤሎች  2016 

51www.tlcfan.org

ሰዎች ክርስቶስን ብቻ ሲመለከቱ የእርሱን ክብር ብቻ ሲይዙ ክብሩን መገለጥ

ብቻ ሳይሆን ላልተገባቸው ክብሩን ይሸፍናሉ። ጳውሎስ ስለ እያንዳዳቸው ልናገር አሁን

አልችልም። መንፈሳዊ እንደመሆናችሁ ልናገራችሁ አልችልም በማለት የእግዚአብሔርክብሩንና ሚስጥሩን ከሥጋዊያን ይሸፍን ይጋርድ ነበር። (1ቆሮ. 3፥1-3፥, ዕብ. 9፥5) ከላይ

በሕዝቅኤል ላይ እዳየነው ጥቅስ መሰረት ኪሩቤል የሚያመለክተው አዳም ነው እንጂ

ሰይጣንን አይደለም። ራሱ ቃሉ አንተ ሰው ነህ ይላል። ሰይጣን በእግዚአብሔር ለመመሰል

ፈለገ የሚል ቃል አናገኝም። ሰው ግን በሰይጣን ተፈትኖ እግዚአብሔር ለመምስል ሲፈልግ

እናገኘዋለን። 

ዛሬም እኛ አማኞች እውነተኛ ኪሩቦ መሆናችን ገብቶች የክርስቶስን አዕምሮና

መልክ ልናንጸባርቅ ተጠርተናል። ይህ ሲሆን የእግዚአብሔር ሃስብና ፍቃድ በሕይወታችን

ይፈጸማል። ይህ እግዚአብሔር ለእኛ የሚያስበው መላክም ሃሳቡ ነው። 

Page 52: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 52/53

ኪሩቤሎች  2016 

52www.tlcfan.org

የእግዚአብሔር ክብርና ኪሩቤሎች 

“የእግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ፤

ቤቱም በደመናው ተሞላ፥ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ፀዳል

ተሞላ።” ሕዝ.10፥4 

የእግዚአብሔር ክብር የሰለሞንንም መቅደስ ሞልቶርት ነበር ነገር ግን ከዚህ

ከሕዝቅኤል ከተመለከተው የሚለየው የሰለሞን በድቅድቅ ጨለማ ሲሆን የሕዝቅኤል ደግሞበእግዚአብሔር ክብር ጸዳል ብርሃን የተሞላ ነው። በድቅድቅ ጨለማና በጸዳል ብርሃን

መካከል ትልቅ ልዮነት አለ። 

ሕዝቅኤል በራእይዮ እንደተመለከተው (ሕዝ.8፥16) ጀርባቸውን ለመቅደሱ

አድርገው ፊታቸውን ወደ ምስራቅ አድርገው ለጸሐይ ስለሰገዱት ሰዎችን ይነግረናል። ይህ

ደግሞ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የሚያደርገው እርኩሰት ነው። ዛሬም እንዲሁ ነው። ወደ

እግዚአብሔር መቅደስ ገብተን ኪሩቤሎችን መልክ መምሰል ሲገባን በአደባባይ ሆነን ለጸሐይ

እንሰግዳለን። ወደ ውስጠናው ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት እንወድም። ጸሃይፍጥረታዊ እውቀትንና ፍጥረታዊውን አዳማዊ አስተሳሰብ የሚያመልክት ነው። ጸሐይ

የሚገኘው በአደባባይ ወይም ከመቅደሱ ውጨኛው ክፍል ነው። 

ከቅዱስ ቅዱሳን ውስጥ ካለው ብርሃንና ክብር ጋር የሚወዳደር ምንም አይነት ነገር

የለም። ነገር ግን ሰዎች ወደዚህ ክብር ውስጥ ከመግባትና መሰረታቸውን የምሕረት

መክደኛው ላይ ከማድረግ ይልቅ በሌሎች ላይ መፍረድን ለጸሐይ መስገድን ይመርጣሉ። 

አንድ አማኝ ከኪሩም ከመጋረጃው መልክ ወደ ወርቁ መልክ በአዕምሮው መታደስሲለወጥ ወይም ከመጀመሪያው አዳም ወደ ሁለተኛ አዳም ሲለወጥ ወደ ላይ ከፍ ከፍ ይላል።

ከእግዚአብሔር አንድ የሆነ እግዚአብሔር በሚሄድበት ይሄዳል ክብሩ ባለበት ይኖራል።

እግዚአብሔር በእነዚህ በድል ነሺ በሆኑ ኪሩቦች ወይም የእግዚአብሔር ልጆች ላይ

ይቀመጣል። የእነርሱም ክብር ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር በእነርሱና ከእነርሱ ጋር

ይንቀሳቀሳል፣ በእነርሱም ላይ ይከብራል። ስለ እግዚአብሔር ንፋስ ስለ እግዚአብሔር ክብር

የእግዚአብሔር ቃል ብዙ ያስተምረናል። 

Page 53: Cherubs

7/25/2019 Cherubs

http://slidepdf.com/reader/full/cherubs 53/53

ኪሩቤሎች  2016 

“በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ።” መዝ.18፥10 

እግዚአብሔር ቃል እንደሚያሳየን በቀደሙት ምዕራፎች እንዳየነው አዳምየእግዚአብሔር የመጀመሪያ ኪሩብ ነበር። ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ክብር በላዮ ላይነበረው። ሰው የእግዚአብሔር ክብር ባለመታዘዝ ምክንያት አጣው። ሰው ከውድቀት በኋላየወደቀው አዳም ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ተስማምቶ ከእግዚአብሔር ጋር ከመኖር ይልቅየራሱን የሞት መንገድ መረጠ። ይህ ሁሉ ሲሆን እግዚአብሔር ልጆቹ ኪሩቦች ወደ እርሱየሚመጡበትን መንገድ አዘጋጅቶ ነበር። ይህም የእግዚአብሔር በኩር ልጅ የናዝሬቱ

ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። 

ሰው የእግዚአብሔር ድምጽ ሲሰማ ወደ እግዚአብሔር የመለሳል። ዛሬም ድምጹየሰማችሁ ወደ እርሱ ተመለሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በመግባት የተሰጠንን ማንነት እንወርስዘንድ በእግዚአብሔር ሁላችን ተጠርተና። ማራናታ 

……………………………ተፈጸመ……………………………. 

ሌሎች መጽሐፎቼን ለማግኘት ወደ ከዚህ በታች ያለውን ድረ ገጽ ይሂዱ 

www.tlcfan.org