24
Ze-Habesha Newspaper July . 2013 No.53 612-226-8326 በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ የአድራሻ ለውጥ አድርገናል የአድራሻ ለውጥ አድርገናል የአድራሻ ለውጥ አድርገናል ለሠርግ፣ ለምርቃት፣ ለማንኛውም ግብዣ የኬተሪንግ አገልግሎት አለን 2812 university Ave, Mpls, MN 55414 Tel: (612)770-3270 www.aklogasfawinsurancemn.com $10 Home selling and buying is easy when you list with Demissie AMERICAN REALTY GROUP Call the guy that knows how to make It happen! በመተባበር፣ በመመካከር አብረን እንክበር 651-214-2584 ወይም 651-489-9220 ቤት መግዛት ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው፤ ህልምዎን ለማሳካት ከጅምሮ እስከ ፍጻሜው አብሬዎት እሠራለሁ Mulugeta Mikael Big Real Estate 1561 Selby Ave St.Paul, MN ሐምሌ 2005 ቅጽ IV ቁጥር. 53 ዕውነትን እንጽፋለን፤ ዕውነት ያሸንፋል!! OFF. (763) 951 2931 Cell (612) 644 7665 Fax (763) 432 5069 [email protected] ተፈጥሯዊ የቡግር ማጥፊያዎች (ገጽ 16 ላይ ይመልከቱ) የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ (ዘ-ሐበሻ) የሚኒሶታ Department of Public Safety ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው መኪና መንዳት የሚያስተምሩ ሰዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና እነዚህ ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው ገንዘብ እያስከፈሉ የሚያስተምሩ ሰዎች የሃገሪቱን ሕግ በመጣሳቸው እንደሚቀጡ አስታወቀ። ዲፓርትመንቱ ዘ- ሐበሻን ጨምሮ በየኮምዩኒቲው ለሚገኙ ሚዲያዎች በላከው ማሳሰቢያ በአሁኑ ወቅት በግዛቷ በሕግወጥ የመኪና አስተማሪዎች ሳቢያ የሚደርሰው የመኪና አደጋ ብዛት እየጨመረ በመሆኑ ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተልና ማህበረሰቡም በጥቆማ እንዲተባበር ጠይቋል። (የሚኒሶታ .. ወደ ገጽ 12 የዞረ) (651)-646 6900 or 1-877-302-3347 1821 university Ave. w. Suit 143 St. Paul, MN 55104 አሜሪካንን ጠላኋት + ወደኳት (ገጽ 18 ላይ ይመልከቱ) መዝ. ዳዊት 68:31 ዘወትር አርብ በአዲሱ አድራሻችን ከምሽቱ 6-8 ሰዓት 1901 Portland Ave. South Minneapolis, MN 55404 በእግዚአብሔር የመጎበኘት ወር ! ልባችንና እጆቻንን ወደ እግዚአብሄር በመዘርጋት የእግዚአብሄርን መለኮታዊ መነቃቃትና ፈውስ እንቀበል። ለዚህ ወር ከ10 እስከ 12 የጸሎት ፕሮግራም ጀምረናል። ፒያሣ ገበያ ውስጥ ፒያሣ ትራቭል ኤጀንሲ ሥራውን ጀምሯል ወደየትኛውም ሃገርና ከተማዎች ለመብረር ሲፈልጉ የዓየር ትኬት በተመጣጣኝ ዋጋ እናገኝልዎታለን 512 N Snelling Ave St Paul, MN 55104 (651) 645-7488 (ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ህንፃ ማሰሪያ የተዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫና የርምጃ ውድድር ባለፈው ቅዳሜ ጁላይ 20 ቀን 2013 በፌለን ፓርክ ተደረገ። ዝግጅቱም ሆነ ውጤቱም ስኬታማ እንደነበር ታወቀ። 500 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት በዚሁ የሩጫና የርምጃ ውድድር ዋነኛ ዓላማው ገቢ ለህንፃ ማሰሪያ ለማስገኘት ይሁን እንጂ ማህበረሰቡን በስፖርት ጤንነቱን እንዲጠብቅ በማስተማር ደረጃ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በውድድሩ የተሳተፉ ወገኖች (መድሃኔዓለም... ወደ ገጽ 17 የዞረ) (ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ድራማዎች ላይ ዝነኝነትን ያተረፉት አርቲስቶች መሠረት መብርሃቴ፣ ትዕግስት ንጋቱ፣ ነፃነት ወርቅነህ እና አበባየሁ ታደሰ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት ትያትር እንደሚያሳዩ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። በገመና ድራማ፣ ከዚህ ቀደም በጉዲፈቻ እና በሻማ እምባ ፊልሞች፤ በተጨማሪም የመዝሙር ሲዲ በማውጣት ለገዳም ገቢ ያዋለችው ተወዳጇ አርቲስት መሠረት መብራቴ ወደ ሚኒሶታ መጥታ በመድረክ ላይ በፍሬሽማን ትያትር ላይ ትወናዋን ታሳያለች። ከርሷ በተጨማሪም በሚሰጣት ገፀባህሪዎች ብዙዎችን በሳቅ ማዕበል ውስጥ የምትከተውና ከመስከረም በቀለ ጋር ቋንቋ በተሰኘው የኮሜዲ ፊልም ላይ የሠራቸው አርቲስት ትዕግስት ንጋቱም በዚሁ ፍሬሽማን ትያትር ላይ ለመተወን ሚኒሶታ ትመጣለች። በFBI ፊልም ላይ የሚታወቀው አስቂኙ (ፍሬሽማን ትያትር... ወደ ገጽ 10 የዞረ) ከዝነኛ ድምጻዊያን ጀርባ ያለ ታላቅ ሰው አማኑኤል ይልማ (ገጽ 15 ላይ ይመልከቱ)

Call the guy that knows how to የአድራሻ ለውጥ አድርገናል It happen! · ገቢ ያዋለችው ተወዳጇ አርቲስት መሠረት መብራቴ ወደ ሚኒሶታ

  • Upload
    others

  • View
    11

  • Download
    2

Embed Size (px)

Citation preview

Ze-Habesha Newspaper July . 2013 ᴥ No.53 612-226-8326

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

የአድራሻ ለውጥ አድርገናልየአድራሻ ለውጥ አድርገናልየአድራሻ ለውጥ አድርገናል

ለሠርግ፣ ለምርቃት፣ ለማንኛውም ግብዣ

የኬተሪንግ አገልግሎት አለን

2812 university Ave, Mpls, MN 55414

Tel: (612)770-3270 www.aklogasfawinsurancemn.com

$10

Home selling and

buying is easy

when you list with

Demissie

AMERICAN REALTY GROUP

Call the guy that

knows how to

make

It happen!

በመተባበር፣ በመመካከር አብረን እንክበር

651-214-2584 ወይም 651-489-9220

ቤት መግዛት ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው፤ ህልምዎን

ለማሳካት ከጅምሮ እስከ ፍጻሜው

አብሬዎት እሠራለሁ

Mulugeta Mikael Big Real Estate 1561 Selby Ave St.Paul, MN

ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53 ዕውነትን እንጽፋለን፤ ዕውነት ያሸንፋል!!

OFF. (763) 951 2931 Cell (612) 644 7665 Fax (763) 432 5069 [email protected]

ተፈጥሯዊ የቡግር ማጥፊያዎች

(ገጽ 16 ላይ ይመልከቱ)

የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ

(ዘ-ሐበሻ) የሚኒሶታ Department of Public Safety ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው መኪና መንዳት የሚያስተምሩ ሰዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና እነዚህ ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው ገንዘብ እያስከፈሉ የሚያስተምሩ ሰዎች የሃገሪቱን ሕግ በመጣሳቸው እንደሚቀጡ አስታወቀ። ዲፓርትመንቱ ዘ-ሐበሻን ጨምሮ በየኮምዩኒቲው ለሚገኙ ሚዲያዎች በላከው ማሳሰቢያ በአሁኑ ወቅት በግዛቷ በሕግወጥ የመኪና አስተማሪዎች ሳቢያ የሚደርሰው የመኪና አደጋ ብዛት እየጨመረ በመሆኑ ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተልና ማህበረሰቡም በጥቆማ እንዲተባበር ጠይቋል። (የሚኒሶታ .. ወደ ገጽ 12 የዞረ)

(651)-646 6900 or 1-877-302-3347 1821 university Ave. w. Suit 143

St. Paul, MN 55104

አሜሪካንን ጠላኋት + ወደኳት

(ገጽ 18 ላይ ይመልከቱ)

መዝ. ዳዊት 68:31

ዘወትር አርብ በአዲሱ አድራሻችን ከምሽቱ 6-8 ሰዓት

1901 Portland Ave. South Minneapolis, MN 55404

በእግዚአብሔር የመጎበኘት ወር

ኑ! ልባችንና

እጆቻንን ወደ እግዚአብሄር በመዘርጋት የእግዚአብሄርን መለኮታዊ መነቃቃትና ፈውስ እንቀበል። ለዚህ ወር ከ10 እስከ 12 የጸሎት ፕሮግራም ጀምረናል።

ፒያሣ ገበያ ውስጥ ፒያሣ ትራቭል ኤጀንሲ ሥራውን ጀምሯል

ወደየትኛውም ሃገርና ከተማዎች ለመብረር ሲፈልጉ የዓየር ትኬት በተመጣጣኝ ዋጋ

እናገኝልዎታለን 512 N Snelling Ave St Paul, MN 55104

(651) 645-7488

(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ህንፃ ማሰሪያ የተዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫና የርምጃ ውድድር ባለፈው ቅዳሜ ጁላይ 20 ቀን 2013 በፌለን ፓርክ ተደረገ። ዝግጅቱም ሆነ ውጤቱም ስኬታማ እንደነበር ታወቀ።

500 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት በዚሁ የሩጫና የርምጃ ውድድር ዋነኛ ዓላማው ገቢ ለህንፃ ማሰሪያ ለማስገኘት ይሁን እንጂ ማህበረሰቡን በስፖርት ጤንነቱን እንዲጠብቅ በማስተማር ደረጃ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በውድድሩ የተሳተፉ ወገኖች (መድሃኔዓለም... ወደ ገጽ 17 የዞረ)

(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ድራማዎች ላይ ዝነኝነትን ያተረፉት አርቲስቶች መሠረት መብርሃቴ፣ ትዕግስት ንጋቱ፣ ነፃነት ወርቅነህ እና አበባየሁ ታደሰ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት ትያትር እንደሚያሳዩ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።

በገመና ድራማ፣ ከዚህ ቀደም በጉዲፈቻ እና በሻማ እምባ ፊልሞች፤ በተጨማሪም የመዝሙር ሲዲ በማውጣት ለገዳም ገቢ ያዋለችው ተወዳጇ አርቲስት መሠረት መብራቴ ወደ ሚኒሶታ መጥታ በመድረክ ላይ በፍሬሽማን ትያትር ላይ ትወናዋን ታሳያለች። ከርሷ በተጨማሪም በሚሰጣት

ገፀባህሪዎች ብዙዎችን በሳቅ ማዕበል ውስጥ የምትከተውና ከመስከረም በቀለ ጋር ቋንቋ በተሰኘው የኮሜዲ ፊልም ላይ የሠራቸው አርቲስት ትዕግስት ንጋቱም በዚሁ ፍሬሽማን ትያትር ላይ ለመተወን ሚኒሶታ ትመጣለች። በFBI ፊልም ላይ የሚታወቀው አስቂኙ (ፍሬሽማን ትያትር... ወደ ገጽ 10 የዞረ)

ከዝነኛ ድምጻዊያን ጀርባ ያለ ታላቅ ሰው

አማኑኤል ይልማ (ገጽ 15 ላይ ይመልከቱ)

June 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 52 ሰኔ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 52

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Ze-Habesha Newspaper is Legally

Registered in state of Minnesota -

USA

Founded in December 2008 Publisher :-

ZeHabesha LLC

ዋና አዘጋጅ:- ሔኖክ

ዓለማየሁ ደገፉ

Editor in

Chief:-

Henok A.

Degfu e-mail:- [email protected]

[email protected]

አዘጋጆች:- ሊሊ ሞገስ፣

[email protected] ሮቤል ሔኖክ፣

[email protected] ቅድስት አባተ ዘላለም ገብሬ (ቺካጎ) [email protected]

አማካሪ፡- ዶር ዓብይ ዓይናለም

Ze-Habesha newspaper Address:-

6938 Portland Ave,

Richfield MN 55423

612-226-8326

www.zehabesha.com

www.facebook.com/zehabesha

www.twitter.com/zehabesha “Journalism can never be silent: that is its greatest virtue and its greatest fault. It must speak, and speak immediately, while the echoes of wonder, the claims of triumph and the signs of horror are still in the air.”

Henry Anatole Grunwald

በሚኔሶታ - አሜሪካ የተቋቋመ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው

ዓላማው የማህበረሰባችን የወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ መገኛ መሆን ነው።

ዘ-ሐበሻ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ድርጅት፣ ጎሳ፣ ያልወገነ፣ ነጻ ጋዜጣ ነው፡፡

ዓብይ መልዕክት

ከሶሊያና ሽመልስ (በዘ-ሐበሻ ድረገጽም ይህ ጽሁፍ ይገኛል) ከጥቂት ጊዜያት በፌት አንድ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ላይ

ተገኝቼ ነበር፡፡ መጽሐፉ “ፌኒክሷ ዛሬም፣ ሞታም ታንቀላፋለች” ሲሆን ጸሐፊዋ የቀድሞው የሕወሓት አባልና አመራር የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ወ/ሮ ውብማር ናቸው፡፡ በዳሰሳው ወቅት በትግል ጊዜ ለምን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እንዳልፈቱ ሲጠየቁ ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው መልሰው ነበር፡፡ “ደርግን የሚያህል ጠላት ከፊት ለፊታችን እያለ እንዴት እርስ በርስ በመጣላት ጊዜ እናባክናለን? ነጻ ስንወጣ የሕወሓት ፖሊሲና ፕሮግራም ሁሉንም ነገር ይፈታዋል::” ብለን ተውነው ይላሉ፡፡

በኋላ ላይ ደግሞ ሕወሓትን ስለመለወጥ ሲጠየቁ ‹‹ሕወሓት ከዚህ በኋላ የሚለወጥ ድርጅት አይደለም አርጅቷል፡፡ 40 ዓመት በኋላ የድርጅት ባሕሪይ አይቀየርም›› ሲሉ ይከራከራሉ፡፡

የትኛው ጠላት? የትኛው ትልቁ ዓላማ? አሁንም ሕወሓት ሥልጣን ከያዘ ከ20 ዓመት በኋላም ቢሆን

የዋናው ጠላት ወይም “ትልቁ ዓላማ” ክርክር እንደ መተባበርያ እና እነደመቻቻያ ሰበብ እንዲሁም እንደአለመተቺያ ምክንያት ይነሳል፡፡ ተቃዋሚዎች እንዲተባበሩ የሚጠየቁት “ዋናውን ጠላት” ለማንበርከክ ነው፡፡ የትልቁ ጠላት መኖር አገራዊ የፖለቲካ ክርክራችንንም ሆነ የፓርቲ ፖለቲካችንን የሚበጠብጥ ትልቅ ችግራችን እየመሰለኝ መጥቷል፡፡ መንግሥት/ገዥው ፓርቲ የተሰኘውን ይህንን ጠላት ለማባረር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ለትልቁ ዓላማ ተብሎ የምናጣቸውን ነገሮች ሳናስተውል የምናልፍበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ምሳሌ እናንሳ ብንል ለትልቁ ዓላማ ሲባል የማይተች ጋዜጠኛ አለን፣ ለትልቁ ዓላማ ሲባል የተቃዋሚ ፓርቲ አይነካም፣ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ውስጠ ፓርቲ ልዩነቶች ይታፈናሉ (ሲፈነዱ የሚያመጡት አደጋ መባሱ ላይቀር)፡፡ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ሐሳብን በነጻነት መግለጽ መብትን የሚያፍኑ ሌሎች ትንንሽ ጨቋኞችን ማበረታታት የተለመደ ሆኗል፡፡ ለትልቁ ዓላማ ሰበብ ሲባል ጋዜጠኞች ላይ የጥላቻ ፓሮፖጋንዳ ይነዛል፡፡ ትልቁ ዓላማ ሁላችንም ስህተቶቻችንን የምንሸፍንበት አገራዊ የተቃውሞ ሰበብ ሆኖልናል፡፡

“ትልቁ ዓላማ”ና ትርጉሙ አብዛኛው ተቃዋሚ ፓርቲዎች/ግለሰቦች ዓላማቸው

ቢጠየቁ ሃገሪትዋ አሁን ካለችበት ሁኔታ በሁሉም መልኩ ተሻሽላ እንድትገኝ ማድረግ እንደሆነ ቢያንስ በግርድፉ ይናገራሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ አሁን ላለን የፖለቲካዊ ሁኔታ ትኩረት እንሰጣለን የምንል ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች በቋንቋ ብንለያይም፣ ብንጠየቅ የምንናገረው ሐሳብም ከዚህ የተለየ አይሆንም የሚል ግምት አለኝ፡፡ (የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች አሁን ባለችው ኢትዮጵያ እንደሚስማሙና እንደማይመለከታቸው ባስብም ኢሕአዴግም ራሱ በተቃዋሚዎች ቦታ ቢሆን የተሻለ አቅም እንደማይኖረው በመገመት ይህንን ውይይት ወደራሳቸው ቢተረጉሙት አልጠላም፡፡) ነገር ግን አሁን ያለውን ነባራዊ የፓለቲካ ሁኔታ ከመቀየር ረገድ እየሠራን ነው የሚሉት አካላት ሁሉ የሚስማሙበት የሚመስለው ሌላው ነገር ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት መቀየር የሚለውን አካሄድ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ሠላማዊዎቹንም ነፍጥ ያነሱ ቡድኖችንም የሚያስማማ ሁለተኛው የጋራ ሐሳብ መሆኑ ነው፡፡ እንግዲህ ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ የሚስማሙት ተቃዋሚዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መንግሥት ለመቀየር የሚያደርጉትን ጥረት ባለማስተባበር ሲታሙ ኖረዋል፡፡ “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” ተብለው ሲተቹ ከርመው ቢተባበሩም ደግሞው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሰባበር አላመለጡም፡፡

እኔ እንዳስተዋልኩት ተቃውሞው ጎራ ያሉ አብዛኛው ቡድኖች ከሚስማሙባቸው ጉዳዮች አንዱ መንግሥት ማንኛውንም ተቃራኒ ድምፅ ለማፈን ጥረት ማድረጉን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይህንን ስርዓት ለመቀየር (ትልቁ ዓላማ) ሲባል እርስበርስ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን መተው/ማለፍ

እንደሚገባ ነው፡፡ ይህ ያልተጻፈ የመግባቢያ ሐሳብ በሕዝቡም በፓርቲዎችም በግለሰቦችም ውስጥ ሰርፆ በተቃውሞ ቡድኖች መካከል ልዩነቶች በተፈጠሩ ቁጥር ሕዝቡንም የሚያስከፋው “እነዚህ እርስ በርስ መስማማት ያልቻሉ እንዴት ነገ መንግሥት ይሆናሉ?” “ እንዴት በዚህ ጊዜ እንኳን ለትልቁ ዓላማቸው ሲሉ ችግሮቻቸውን አያመቻምቹም?” የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ጉዳዩን ከላይ ከላይ ያየነው እንደሆነ የሚረባ ጠንካራ ፓርቲ አለማግኘት የማንኛውም ሕዝብ የተስፋ መቁረጥ ምንጭ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ስለዚህ ጠንካራ ፓርቲዎችን ለማየት መመኘትና ደካማ የሚያስመስሉ ችግሮችን መሸሽም ተገቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ ትልቁ ዓላማችን አገራችንን ዴሞክራያዊ የተሻለች አገር ማድረግ ነው ወይስ መንግሥትን መቀየር ብቻ? መንግሥትን መቀየር የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት አስፈላጊ ነው ብዬ ባምንም ይህንን የምናደርገው ለወደፊትዋ ዴምክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚስፈልጉ እሴቶችን በመሸርሸር መሆኑ ግን ያሳስበኛል፡፡ ከነዚህ መ ሸ ር ሸ ሮ ች አንዱ ደግሞ ልዩነትን እንደ አማራጭ ያለመ ቀበል አዝማሚያ ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ባለን የተዛባ የመቻቻልና ተስፋ ያለማስቆረጥ ጽንሰ ሐሳብ ከቀጠልን እንደአገር በዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ውስጥ የምናጣው ነገር ከመብዛቱም በተጨማሪ የሚመጣው ስርዓት የተሻለ ለመሆኑ ማረጋገጫ አይኖረንም ብዬ እከራከራለሁ፡፡

መተባበሮች ለምን ይፈርሳሉ? ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል ቅድሚያ የሚሰጣቸው

የማይመስሉ ነገሮችን መሸፋፈን ባሕላችን እስከዛሬ ውጤታማ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ይህ የአለባብሶ የማረስ ትብብር በአረም ሲያስመልሰን ብዙ ጊዜ አስተውለናል፡፡ እየተሸፋፈኑ የማለፍ ፖለቲካ ከውስጥ ፓርቲ ጀምሮ እስከ አገሪትዋ ወሳኝ የፖለቲካ ጊዜያት ድረስ ብዙ ጊዜ ዋጋ ሲያስከፍለን ቆይቷል፡፡ እነዚህ ያልተተቹ ያልተፈተሹ እርስ በርስ መተባበሮች መካከል በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለምርጫ 97 ውድቀት አስተዋእፆ ማድረጉ የሚታወስ ነው:: ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የሚደረጉ ያልተጠኑ መስማማቶች “ለትልቁ ዓላማ” ሲባል የታለፉ ልዩነቶች ምርጫ 97ትን የሚያህል ስኬት ለማጣት አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ስለዚህ ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የሚታለፉ ልዩነቶቸ መጨረሻውን ውጤት ስኬታማነት ስለሚቀንሱት ለምንድነው የምንተባበረው? ከነማንጋር ነው አብረን መሥራት የምንችለው? የሚለውን ነገር ማጣራትና ልዩነትን በግልጽ ማስቀመጥ ከማይዘልቅ መተባር የተሻለ ለወደፊቱ ለፓለቲካ ባሕል ጥቅም ይኖረዋል፡፡ አሁን ባለን አካሄድ የመተባበር ሙከራዎቹ ችግሩንም ጭንቀቱንም ከመቀነስ አንጻር የሰጡት ጥቅም አይታየኝም፡፡ እነደውም ደካማ ተስፋ እየሰጡ እርሱንም በአጭሩ እያከሰሙት ብልጭ ድርግም የምትለው የተቃውሞ ፓለቲካ ላይ ተስፋ ለማሳጣት ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡

የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ምንድነው?

በባሕል ደረጃ ሊገለጽ የሚችል የፖለቲካ ልምድ ባይኖረንም እነደአገር ለምናደርገው የመማር ሒደት መታሰብ ያለበት የምናሳድገውና የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ምን ይሆናል የሚለውንም ጭምር ነው፡፡ አሁን ባለን ሁኔታ የፖለቲካ ባሕላችን በጠላትና በወዳጅ ልዩነት ብቻ የተወሰነ ሲሆን መሐል ላይ የሚቀመጥ ግራጫ ባሕሪይ የለውም፡፡ ይህ መሐል ያለመቀመጥ ችግር ፖለቲካ ፓርቲዋችን በግድም ቢሆን ወደተለባበሰ መተባበር ሲገፋቸው ይታያል፡፡ ልዮነቶችን የምናተናግድበት መንገድ የንግግር ባሕልን፣ ልዩነትን የማክበርን ሳይሆን ጎራ የመለየትን ከሆነ ለመጪው ትውልድም ቢሆን የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ደካማ ይሆናል፡፡

እንደአገር ከ50 ዓመት በፌት የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ያልቻልን ሕዝቦች ጥያቄዎቹን ለለመለስ የምንጠቀማቸው መንገዶች እንዲህ ደካማ መተባበሮች ላይ የተመሠረቱ ሆነው ከቀጠሉ ችግሮቹን ብቻ ሳይሆን ለመተባበር ሲባል ብቻ የሚነሱ ደካማ ውሕደቶችንም እንደ ባሕል አስተላልፈን ልናልፍ እንቸላለን

የሚል ስጋት አለኝ፡፡ እነዚህን ኃላፊነቶች ከግምት ውስጥ ያላስገባ የፓለቲካ ተቃውሞም እስካሁን ውሕደት/አብሮ

የመሥራት ችግሮች ምክያትን ሲያጠናም ሆነ ለመፍታት ሲሞክር አይታይም፡፡ የኅብረቶችን መፍረስ በሌላ ኅብረት በመተካት መፍታት የፓለቲካ ባሕሉ ሳይሻሻል እንዲቀጥል ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ ጥቃቅን ልምዶችን (መፍረስ መደራጀት) ችላ ማለት የተበላሸና ለማስተካከል ጊዜ የሚፈጅ የፖለቲካ ባሕል ይዘን እንድንቀር እንደማያደርገን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡

ለ”ትልቁ ዓላማ “ ሲባል መሰረታዎ እሴቶችን መጨፍለቅ

ልናመጣቸው የምንከራከርላቸው ሰው ልጆች መብት፣ ፍትሕ፣ እኩልነት እሴቶችን ራሳችን ለትልቁ ዓላማ በመቆርቆር ስያሜ እንደረምሳቸዋለን፡፡ ይህንን ለመረዳት ከፖለቲካ ፓርቲ እስከ ሚዲያ ከግለሰብ እስከ ብሎግና ማኅበረሰብ ሚዲያ አይቶ መመስከር ይቻላል፡፡ በዚህ ባህሪያች የተነሳ በየቀኑ የምንጥሳቸው እሴቶች ብዙ ሰዎችን ገፍተው ዓላማ ሲያስቱም አስተውለናል፡፡ (መቼም ትችቴን ተቹብኝ እንደሰበብ ተቀባይነት ባይኖረውም ተፅዕኖውን ዕውቅና መስጠቱ አስፈላጊ ነው) “ትልቁ ዓላማ” የሚባለው ሰበብም የእሴቶች እሴት ሆኖ ሁሉም ንግግር የመብት ጥያቄና ትችት ከሱ በታች ካልሆነ በስተቀር የማናተናግድበት ባሕል ፈጥረንና

ብዛኛዎቻችን ተስማምተን ተቀምጠናል፡፡ ምን ነካት/ው? ለዚህ ሲል ምናለ ቢያልፈው? ይሄንን መናገሪያ ጊዜ አሁን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይነሳሉ፡፡

የአብዛኛዎቹ የዚህ ክርክር ደጋፊዎች የምናስቀድመው “ትልቁን ዓላማ” መሆን አለበት ከማለት በተጨማሪ ጊዜንና ቅድሚያ አሰጣጥን እንደተያያዥ ምክንያች ያነሳሉ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች በቂ ሆነው ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ የግለሰቦች መብት በቀላሉ ይጣሳል፡፡ ይህ ባሕል ደግሞ በየቦታው የምናነሳቸውን እሴቶች ተቃራኒ የመሆንን እና ተደራራቢ መመዘኛዎችን የመጠቀም ያጋልጠናል፡፡ የምንቆምላቸው እሴቶች ለእኛ ዓላማ ሲሆን የሚሸረፉ፣ ሌሎች ሲያደርጉት የሚያስወቅሱ ከሆነ ምኑን ቆምንላቸው?

ትንንሽ አምባገነኖች ማሳደግ ዛሬ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ዝምታን የምንመርጥባቸው ጥቃቅን

መሳይ ጉዳዮች የምናፈራቸው መሪዎች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖም መገመት (ለትልቁ... ወደ ገጽ 11 የዞረ)

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ከክንፉ አሰፋ ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች

ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። "ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።" ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የብዙ ባህል፣ የብዙ ቋንቋና የበርካታ እምነት ሃገር ስብስብ በመሆንዋ ታሪኳን ጠለቅ እያልን ለማወቅ በሞከርን ቁጥር ሊወሳሰብ ስለሚችል እጅግ ብዙ ጥናት ማድረግ ይገባል ለማለት ነው። ጸሃፊው ለረጅም ጊዜ በቆየ ቁጥር የሚጽፈው ጠፍቶት ሳይሆን ግራ ተጋብቶ መጻፉን ያቆማል።

በያዝነው የበጋ ወር፡ ዲሲ ላይ ያጋጠመኝ ችግር ይኽው ነበር። ስለ-30ኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌስቲቫል በበርካታ ርዕሶች ዙርያ ለመጫጫር ፈለግኩ። ነገር ግን በርዕሶቹ ላይ ጠለቅ እያልኩ ስሄድ ግራ በመጋባት ላለመጻፍ ወስኜ ነበር። የአትላንታው ዳዊት ከበደ ኢ.ኤም.ኤፍ. ላይ በሚጽፋቸው ገጠመኞች ለማብራሪያው እኔን እየጠቃቀሰ 'ሼም' አስያዘኝ። በበአሉ መክፈቻ እለት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የህዝብ ግንኙነቱ ፋሲል አበበ በር ላይ አግኝተውን ሞቅ ያለ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ፋሲል አበበ፣ '...አንተ ሳትኖር ይህ በዓል አይደምቅም።' ያለኝም ታወሰኝ። ከዚህ ቀደም ፌዴሬሽኑን እየተቸን የጻፍናቸውን በማንሳትም ወደፊት ገንቢ ትችት እንድናቀርብ አበረታች ሃሳብ ነበር። አሁንም የታዘብኩት ነገር አለ። ይህንን ወደኋላ እመለስበታለሁ።

30ኛው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲቫል እንደተጠናቀቀ ወዳጆቼን ሸኛኝቼ ዲሲን መቃኘት ያዝኩ። በዲሲ ያለ ኢትዮጵያዊ ልዩ ነው። በዲሲ ከማህበራዊነት ይልቅ ግለኝነት በስፋት ይንጸባረቃል። እዚህ የግል ነገር ይበዛል።

የግል ንግድ፣ የግል ራዲዮ፣ የግል ጋዜጣ፣ የግል ፓርቲ፣ የግል ቤተ-ጸሎት፤ ... አዎ የግል ቤተ-ክርስቲያን። በዚህም ቤተ-ክርስትያን የሙሴ ጽላት ያለበት ታቦት አለ። የግል ታቦት። የሚገርመው ታዲያ በዚህ ሃላፊነቱ ባልተወሰነ የግል ቤተ-ክርስቲያን ምእመናን እየሄዱ መሳለማቸው፣ ማስቀደሳቸውና ምጽዋት መክፈላቸው ብቻ አይደለም፣ የቤተ-ክርስቲያኑ አገልጋይ ቄስ ከተገኘ ተከፍሎት ይቀድሳል፡ ከሌለ ደግሞ ቅዳሴው ለምእመናኑ በቴፕ እንዲተላለፍ ይደረጋል።

አሜሪካ የእድል ሃገር ናት (ላንድ ኦፍ ኦፖርቹኒቲ) የሚባለው እንዲህ አይነቱን እድልም ይጨምራል ማለት ነው። ታዲያ አንዳንድ የዲሲ ነዋሪ ኢትዮጵያዊ ባልጠፋ ጸሎት ቤት ወደግሉ ቤተ-ክርስቲያን እየሄደ የሚሳለመው ለምን ይሆን? ትሉ፡ይሆናል። ይህ የኔም ጥያቄ ነው። መልስ የሚሰጠኝ ግን

አላገኘሁም። በግምቴ ካልተሳሳትኩ ገሚሱ በፍርሃት ሌላው ደግሞ በአንጃነት የሚሄድ ይመስለኛል። አንጃ የሚለውን ቃል በመጨረሻ የወዳጄ ሼክስፒር ታሪክ ላይ አነሳዋለሁ።

በዲሲ የግል ራዲዮ ያለው ሰው በጣም ነው የሚፈራው። በራዲዮ የሚደረግ ዘመቻ አንድን የንግድ ተቋም ከምድረ አሜሪካ የማጥፋት ሃይል እንዳለው ተገንዝቤያለሁ። እጅግ ደማቅ የነበረው የአቦነሽ አድነው (አቢቲ) የባህል ምሽት ቤት እንዲዘጋ የአንዲት ሰዓት የራዲዮ ዘመቻ ብቻ በቂ ነበር። አቢቲ በደረሰባት አደጋ አቤት የምትልበት አጣችና እንባዋን ወደ ፈጣሪዋ ፈነጠቀች። አሁን ምሽት ቤትዋን ዘግታ፥ ዘፈኑንም ትታ መንፈሳዊ መዘምራን ሆናለች።

ኤፍ.ኤም. ራዲዮዎችን በጅምላ መንቀፉ ተገቢ አይደለም። ገንቢ እና እጅግ በጣም ድንቅ የሆነ ስራ እያከናወኑ ያሉ የራድዮ ጣቢያዎች እንዳሉ ሁሉ፡ አፍራሽ የግል ጣቢያዎች በህብረተሰቡ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ መፍጠራቸው በግልጽ ይታያል። በዲሲ፥ አንድ ኤፍ.ኤም. ጣቢያ ያለው እና ጥሩ ተናጋሪ ሰው ራሱን የቻለ መንግስት ሊሆንም ይችላል።

ጭብጨባ፤ ሌላው የታዘብኩት የዲሲ ኢትዮጵያውያን ህብረተሰብ ባህርይ ነው። መድረክ ላይ ያለ አንድ ተናጋሪ

በጭብጨባ ይጀምርና በጭብጨባ ታጅቦ ከመድረክ ይወርዳል። አንዳንዴም የሚናገረውን አረፍተ-ነገር ገና ሳይጨርስ ይጨበጨብለታል። በሄድኩባቸው ስብሰባዎች ሁሉ ይህ ነገር አጋጥሞኛል። ማጨብጨብ ለተናጋሪው የሞራል ድጋፍ መስጠት ይረዳል። ሲበዛ ግን ያስፈራል። ተናጋሪውንም ወደማይፈልገው ትእቢተኝነትና ስሜታዊነት ይገፋፋዋል። ፈረንጆች ሲጨበጨብላቸው በጣም ይፈራሉ። እነሱ እንደሚሉት፥ ሰዎች አንድን ሰው ሲያደንቁና ሲያጨበጭቡለት፤ ለዚያ ሰው ስራ እየሰጡት ነው። ከሰውየው ብዙ የሚጠብቁት ነገር እንዳለ ማመላከቻ መልዕክት። በምክንያት ሳይሆን ይልቁንም በስሜት የሚደረግ ጭብጨባ ግን አደጋ አለው። የሚጨበጨብላቸው ስዎች ታዲያ በዚህ አይነቱ ሞብ ከመኮፈስ ይልቅ የበለጠ ስራ ለመስራት ቢተጉ ይበጃቸዋል። በጭብጨባ ብቻ እየተካቡ ሰማይ ላይ የደረሱ ሰዎች ከጊዜ በኋላ ካሉበት ስፍራ ሲፈጠፈጡ ከቀድሞ ተሞክሮ አይተናል። ክርስቶስን በቤተልሄም እያጨበጨቡና ቄጠማ እያነጠፉ የተቀበሉት ሰዎች ግዜው ሲደርስ ራሳቸው "ይሰቀል! ... ይሰቀል!" ብለው ተነሱበት። ሕዝብ በብዙ ምክንያቶች ስሜታዊ ይሆናል። ይህንን ሞብ ለማስቆም ይከብዳል።

ወደ 30ኛው የኢትዮጵያ ስፖርት እና ባህል ዝግጅት ልውሰዳችሁ። በዓሉ እስካሁን ከነበሩት ዝግጅቶች ሁሉ እጅግ የደመቀና፡ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ ነው ከማለት ውጭ የምጨምረው የለኝም። ታዲያ በዚህ ደማቅ እና ግዙፍ ዝግጅት አንዳንድ እንግዳ ነገሮች ቢኖሩ አይደንቁንም። አንዳንዶቹ ችግሮች በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ነበሩ።

አርብ እለት የኢትዮጵያ ቀን ሲከበር ሼክ ሱለይማን ነስረዲን የተሰኙ የሙስሊም እምነት ተወካይ ንግግር አድርገው ነበር። በሜዳው የነበረውን ሕዝብ ከዳር እስከዳር ያነቃነቀ ንግግር። ሼክ ሱለይማን ስለ ሙስሊም እምነት ብቻ ሳይሆን ስለ ክርስትና እምነትም ሰብክዋል፡ በተለይ ደግሞ ስለ ክርስቶስ እናት ስለ ቅድስት ማርያም ብዙ ብለዋል። በበዓሉ መክፈቻ ላይ ያልነበሩ ሰዎች ግን አንዳንድ ጥያቄዎች ማቅረባቸው አልቀረም፡ "ሼኩ ሁለቱንም እምነት ወክለው ነው እንዴ እዚህ የተገኙት?" "የክርስትና እምነት ተወካይስ ለምን አልተጋበዙም?" የሚሉ ጥያቄዎች።

የክርስትና እምነት ተወካይ ያለመገኘትን በተመለከተ መልሱ ቀላል ነው። የበዓሉ መክፈቻ ላይ የክርስትና እምነት አባት ተጋብዘው ሲናገሩ የሙስሊም ተወካይ ተረስተው ነበር። በሙስሊም ምዕመናን ጥያቄ መሆኑ ነው ሼክ ሱለይማን ነስረዲን በአምሰተኛው ቀን እንዲገኙ የተደረገው። ይህ እንግዲህ የዝግጅቱ አንደኛ ጉድለት መሆኑ ነው።

ከነጋዴው መብዛት አንጻር ይከሰት የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ሌላው ሊገታ ይችል የነበረ ችግር ነበር። በተለይ የኢትዮጵያ ቀን ሲከበር የሙዚቃ መሳሪያው ለበርካታ ጊዜ መቆራረጡ የህዝቡን ስሜት በእጅጉ ጎድቶታል። በርካታዎችም ሜዳውን እየለቀቁ ወጥተዋል።

የፕሬስ ካርድ አለማዘጋጀት፡ በየአመቱ ሊቀረፍ ያልቻለው የፌዴሬሽኑ ችግር ነው። በርካታ ጋዜጠኞች በዚህ ምክንያት ሲጉላሉ አይተናል። ከፌዴሬሽኑ አመራር ጋር ከዝግጅቱ በፊት በዚህም ጉዳይ ላይ ተወያይተን መፍትሄ ተገኝቶለት የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ ግን አልሆነም። ለፌዴሬሽኑ ህልውና የሜዲያው ሚና ቀላል እንዳልሆነ ያውቁታል። እነሱ ለፕሬሱ ከሚሰጡት አክብሮት ጋር ግን አይመጣጠንም። ዘንድሮ ይባስ ብሎ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሜዳ መግባት አልቻለም። ሜዳው ሞልቶ ሳይሆን ያንን ሁሉ ህዝብ (ከ40 ሺህ በላይ) ለማስትናገድ ፌዴሬሽኑ ቅድመ-ዝግጅት ስላላደረገ ነበር።

አርብ እለት የኢትዮጵያ ቀን ሲከበር ቀድሞ ፕሮግራም ላይ ያልነበረው ጃ ሉድ ዘው ብሎ መድረክ ላይ ተገኘ። ከመድረኩ ፊትለፊት ጢም ያለውን ህዝብ ሲያይም ገራ ገባው። የባንዱ ሙዚቃ እየሄደ ነው። ጃ ሉድ ማይኩን ያዘና "ቬኑስ እንገናኝ ተብዬ ነበር የመጣሁት። (ዲሲ.... ወደ ገጽ 20 የዞረ)

ፎቶ በክንፉ አሰፋ

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ራስ ሬስቶራንት የፖሊስና የታጠቁ ጥበቃዎችን (ሴኩሪቲ)

አጠናከረ ዛሬ ራስ ሬስቶራንት ውስጥ ጸብ አለ ብሎ የሚያወራ ከተገኘ ሞኝ

መሆነ አለበት። ይህ የሆነበር ምክንያት ፕሮፌሽናል የሆኑ የታጠቁ በቂ ሴኩሪቲዎች(ጥበቃዎች) መኖራቸውና ከራስ ሬስቶራንት ጋር የሚሰሩ

የሴንት ፖል ፖሊሶች ከበር ላይ ሆነው ሁኔታዎችን ስለሚከታተሉ ነው። ከዚህም በላይ በተለያየ ጊዜ ከሰው ጋር የሚጋጩ የነበሩ ወንድሞቻችን በትዳር፣ በልጅና በብስለት ማደግ ምክንያት ፍጹም ጨዋ በመሆናቸው ሁኔታዎች እንዲለወጡ አድርጓል። ስለዚህ ከማናቸውም ክለቦች ውስጥ ፍጹም የተረጋጋ ሰላም በአሁኑ ሰዓት ያለው ራስ ሬስቶራንት ብቻ ነው።

ጋምቤላ ላውንጅ ተመርቆ

አገልግሎት ጀመረ “ጋምቤላ” ላውንጅ የሚል ስያሜ

የተሰጠው የራስ የታችኛው ላውንጅ ሙሉ እድሳቱ ተጠናቆ አገልግሎት

መስጠት ጀመረ። በውስጡ ሙሉ ባር አሟልቶ የያዘው የጋምቤላ ላውንጅ

ለሠርግ፣ ለልደት፣ ለምርቃት፣ ለማንኛውም የግል ፓርቲ

ልትጠቀሙበት እንደምትችሉ እንገልጻለን።

ቁርጥ ሁሉ ቁርጥ አይደለምና ቅዳሜና እሁድ ወደ ራስ ብቅ ብለው ቁርጥዎን ከድራፍትና ቢራ ጋር ይመገቡ

ከረምቡላና ፑል

ቢንጎ በቅርብ ቀን እንጀምራለን

ዘወትር እሁድ የሬጌ ባንድ

የሙዚቃ ዝግጅት ሊጀመር ነው

በከተማችን ተወዳጅነቱን አጠናክሮ

የቀጠለው ራስ በየሳምንቱ እሁድ የሬጌ ላይቭ የሙዚቃ ባንድ ዝግጅቶችን ለደንበኞቹ

ሊያቀርብ መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነው።

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ጓደኛሞች በህብረት በራስ ሬስቶራንት ሲቀመጡ ወንድማማች ይሆናሉ አሁን የገንዘብ ጉዳይ አይደለም ዓላማችን -

ጓደኛሞችን ወንደማማች ማድረግ እንጂ። በራስ ሬስቶራንት ፓዲዮ ላይ የባርብኪው ጊዜ የዝልዝል ጥብስና በርገር በታደሰና በደረጀ ተዘጋጅቶ ዘወትር እሁድና ሰኞ ከ5 ሰዓት ጀምሮ ይጠብቃችኋል።

ዋጋው $5 ብቻ ነው።

ከ50 ዓመት በላይ ያገለገለው የራስ ሬስቶራንት ኤየር ኮንድሺነር (የአየር ማቀዝቀዣ) በአዲስ ዩኒት

ተቀይሮ ሥራ ጀመረ

እየሞቀም እየቀዘቀዘም ቤታችንና እኛን በመውደድ ያለምንም ቅሬታ አብራችሁን ለተጓዛችሁ ወገኖቻችንና

ወንድሞቻችን ታላቅ ምስጋና እያቀረብን አዲሱ AC

Unit ሥራ የጀመረ መሆኑን እየገለጽን የሚኒሶታን ሙቀት ወደ ራስ ብቅ በማለት ቀዝቀዝ ብለው

በመዝናናት እንዲያሳልፉት እንጋብዛለን።

ከቤተ ክርስቲያን

መልስ የራስ ሬስቶራንት ሁልጊዜ እሁድ የነጻ የቡና ሴሪሞኑ

ለቤተክርስቲያን ተመላሾች ማዘጋጀቱን እየገለጸ የሚፈልጉትን የጠርሙስና የብርጭቆ ድራፍት በ$3 ብር ብቻ

እየተጎነጩ ጣፋጭ ምግባችንን እንዲመገቡ

ጥሪ ያቀርባል።

ጌም (Game) በራስ ሬስቶራንት የተለያዩ ጌሞች እየቀረቡ

በመሆኑ መጥተው ከነቤተሰብዎ እንዲዝናኑ ተጋብዘዋል።

ዲ አፍሪክ ባንድ በየወሩ የመጨረሻው ቅዳሜ

የሚያቀርባቸውን ጣዕመ ዜማዎች ቀጥሏል

በሚኒሶታ ልጆች የተቋቋመው ዲ

አፍሪክ ባንድ ከ ዲጄ I&I ጋር በመሆን በራስ ሬስቶራንት በየወሩ

የመጨረሻው ቅዳሜ የሚያቀርበውን የሙዚቃ ድግስ

እንደቀጠለ ነው። የፊታችን ቅዳሜ ጁላይ 27 በራስ ዝግጅቱን የሚያቀርበው ይኸው ባንድ

ተወዳጅ ድምጻዊያንን እና ታዋቂ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾችን የያዘ

እንደሆነ ይታወቃል። በየወሩ የመጨረሻው ቅዳሜ በዲአፍሪክ

ባንድ ይዝናኑ።

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

The Minnesota Department of Public Safety (DPS) licenses driver training instructors

who work for properly licensed driver training schools. A driver training school and

their instructors are required to be licensed when they charge a fee for driving instruc-tion.

DPS has become aware that there may be people in the community who are providing driving instruction without being properly licensed. People who charge a fee for driving

instruction when they are not licensed are violating Minnesota Law.

People who are not licensed by the DPS as driving instructors do not have the: -

Proper training and experience to provide quality-driving instruction. They may be putting drivers at risk by not providing proper training.

Vehicle safety equipment that is required of licensed instructors. These peo-

ple have no method of stopping or controlling the vehicle if mistakes are made by the drivers.

Proper insurance coverage and their liability could be very large if a crash oc-

curs that involves injuries. Before agreeing to begin driving instruction, DPS advises you to:

Ask the driving instructors to show you their instructor license issued by DPS to verify that they are properly licensed. Licensed instructors have all com-pleted an extensive training program and are tested and evaluated by DPS before they are issued a driver training instructor’s license.

People who are not licensed driving instructors may not provide driving instruction to people who are required to complete driver’s training. Driver examiners are not prop-

erly licensed.

Driver examiners will be asking for instructor licensed from people who frequently

bring drivers to the stations for road tests. Information on these people will be for-

warded to the Department of Revenue for investigation.

DPS would like to make everyone aware that you may be paying someone to teach

you hot to driver, but you may not be receiving the proper instruction to help you pre-pare for the driving test and become a safe driver. It is very important that you see

the instructor license of the person who is providing behind the wheel training.

Te see a list of the licensed commercial driver training schools in Minnesota, you may

go to the Driver and Vehicle Services website at https://dps.mn.gov/divisions/dvs/

locations/Pages/Course-Lists.aspx. If you suspect that a person may be providing driving instruction without being licensed, please contact Driver and Vehicle Services

at 651-284-1234, to report this person. You should provide the person’s name, and a

description of the training vehicle, including the license plate number.

EQUAL OPPORTUNITY EMPLOYER

ከስቴቱ ፈቃድ ሳይወስዱ መኪና ለሚያስተምሩና ፈቃድ በሌላቸው የመኪና አስተማሪዎች የሚማሩ ሰዎችን በሚመለከት ከሚኒሶታ ዲፓርትመንት ኦፍ ፐብሊክ ሴፍቲ የተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ

በልጅነትህ ምን መሆን ትፈልጋለህ ስትባል ምላሽህ ምን ነበር?

ያደግኩት ፊት በር አካባቢ ነው። ይህ ሰፈር ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ በርካታ የደሀ ሰፈሮች አንደኛው ነው። ያደግነውም ሆነ የምንጫወተው በቡድን ነበር። ልጅ ሆኜ ሁሌም ማታ ማታ አባቴ ጋዜጣ ገዝቶ ስለሚመጣ ቡና እየተፈላ ጋዜጣ እንዳነብላቸው ያበረታታኝ ነበር። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል እያለሁ ለቤተሰቡ ጋዜጣ ማንበብ የዘወትር የማታ ተግባሬ ነበር። ታላቅ ወንድሜ ቢኖርም አባቴ የሚያስነብበኝ እኔን ነበር። ትምህርት ቤትም ክፍል ውስጥ አነብ ነበር።

አባትህ ማንበብ አይችሉም? ይችላል። እስከ ዘጠነኛ ክፍል ተምሯል። በኃይለ ሥላሴ

ጊዜ እስከ ዘጠነኛ ክፍል መማር ከአሁን ጋር ሲነፃፀር ያው እንደምታውቁት ነው። [ሳቅ]

ጋዜጣ ማንበቤ፣ ጋዜጠኛ እንድሆን አድርጎኛል እያልክ ነው?

አነብ ነበር እንጂ ጋዜጠኛ እሆናለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። አድጌ መሆን እፈልግ የነበረው መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ገብቼ እስከ ጄኔራል ማዕረግ መድረስ ነበር።

የሆንከው የማትፈልገውን ነው ማለት ነው? ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ጋዜጠኛ በመሆኔ በእጅጉ ደስተኛ

ነኝ። ሁለትም፣ ሦስትም ሰዎች ቢሆኑ እኔ በምሠራው ሥራ ደስተኛ በመሆናቸው ደስ ይለኛል። በልጅነታቸው የተመኙትን ሲያድጉ የሚሆኑ ጥቂቶች ናቸው። የምንኖረው ደግሞ የተመኘነውን ሳይሆን የተጻፈልንን ነው። እናንተም ቢሆን ጋዜጠኛ እንሆናለን ብላችሁ ተመኝታችሁ እንደማታውቁ እገምታለሁ። [ጠያቂዎቹ የፈለጉትን እንደሆኑ ተናግረዋል።]

በልጅነትህ ቶሎ ደምህ የሚሞቅ፣ ከኪስህ ጩቤ የማይጠፋ የፍልውሃ እና የአራት ኪሎ የታወቅክ ተደባዳቢ መሆንህን ሰምተናል። ትክክል ነን?

[በጣም ሳቀ] አ… ማለት… እእእ… እንትን ነው… ወሬው ትንሽ ግነት አለው ብዬ አስባለሁ። እንደ ማንኛውም ልጅ ሰፈር ውስጥ ስትውል ‹‹ሰፈሬን አላስደፍርም›› ከሚል እሳቤ ፀብ አይጠፋም። በእኛ ጊዜ ደግሞ የቡድን ፀብ ፋሽን ነበር። ጩቤ ይዤ የምዞር ተደባዳቢ ግን አልነበርኩም።

ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በሰጠሀቸው ቃለ-ምልልሶች ላይ እንደተናገርከው ወደ ጋዜጠኝነቱ ያመጣህ የሙያው ፍላጎት ሳይሆን ከ1997 ዓ.ም. በኋላ መንግሥትን የሚሞግቱ ጠንካራ ጋዜጦች አለመኖር አስቆጭቶህ እንደሆነ ገልጸሀል። አመጣጥህ መንግሥትን ለመቃወም ወይም ተቺ ፖለቲካዊ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ብቻ አይመስልም?

አይመስልም ሳይሆን ነውም፤ ይህ ግምት ሳይሆን እውነታ ነው። ቅድም እንዳልኩት ጋዜጠኛ የሆንኩት ተጽፎልኝ አይደለም። የጋዜጠኝነት ስሜቱም እንደነበረኝ እርግጠኛ አይደለሁም። ያመጣኝ ጎርፉ ነው። እንደ ማንኛውም ሰው አገሬን እወዳለሁ። በማንኛውም ቀዳዳ፣ በምችለው መልኩ ለአገሬ የሆነ ነገር ማበርከትን አስብ ነበር። 1997 ዓ.ም. የተፈጠረው ማዕበል፣ ያመጣበት ጎርፍ ያደናገጠው ኢሕአዴግ

በርካታ ጋዜጦችን ከጥቅም ውጪ አደረጋቸው። ከዚያ በኋላ የተፈጠሩት ጥቂት ጋዜጦች ደጋግሜ እንደምለው አቅሙ ቢኖራቸውም ከኢሕአዴግ ባሕሪ አኳያ ‹‹ዶማን ዶማ፣ አካፋን አካፋ›› ከማለት ይልቅ ቅኔ ለበስ ያደርጉት ነበር። ስለዚህም ይህን የፍርሃት ቆፈን ለመግፈፍ መሞከር አለብኝ በሚል እንጂ ጋዜጠኛ ለመሆን ስወድቅ ስነሣ ቆይቼ አልመጣሁም። የ97 ጎርፍ ባይመጣ ኖሮ እሆን የነበረው ጋዜጠኛ ሳይሆን ኦዲተር ነበር፤ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ የውጪ ኦዲተር ነበርኩ።

ፍትሕ ምን ዓይነት ጋዜጣ ነበረች? የፖለቲካ ጋዜጣ! አንድ ጋዜጣ፣ ጋዜጣ ለመባል

ሊያሟላቸው የሚገባቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የዓምድ ስብጥር ነው። በሙሉ ወይም በከፊል ፍትሕ ይህን ይዛ ነበር ብለህ ታስባለህ?

አይ …. እንደሱ ብዬ ላስብ አልችልም። ምክንያቱም የአገራችን ሚዲያ ገና እያደገ ስለሆነ እኛም አንድ ጋዜጣ ሊያሟላ ያስፈልገዋል ወደሚባለው ደረጃ ለመድረስ ሌት ተቀን እየሠራን ባለንበት ሁኔታ ነው ጋዜጣዋ እንድትቆም የተደረገው እንጂ እጅግ በጣም ብዙ እንደሚቀረን እናውቃለን።

በአገራችን ያሉ ጋዜጦች አቋማቸው፣ የገጽ ብዛታቸውና የዓምድ መጠናቸው ቢለያይም የሚይዟቸው ነገሮች አሉ። ለምሣሌ ጤና የአገሪቷ ትልቅ ችግር ነው። በዚያ ዙሪያ የሚደረጉ ወንጀሎች፣ ሙስናዎች፣ በግል ሕክምና ተቋም የሚካሄዱ ሕጋዊ የሚመስሉ ዘረፋዎች… ብቻ ብዙ ናቸው። የምትሠሩት ለሕዝብ እስከሆነ ድረስ በቀጥታ ከመንግሥት ጋር የተገናኘው ፖለቲካ ላይ ከማተኮር ባለፈ ሌሎች ችግሮችን ወደ ማጋለጥ ለምን አታተኩሩም?

ኢትዮጵያ ውስጥ በወባ በሽታ ከሚሞተው ይልቅ በፖለቲካ ጦስና ችግር የሚጎዳው በቁጥር ይልቃል። ለዚህ ነው ከወባው ይልቅ ለፖለቲካው ቅድሚያ የሰጠነው።

[ሳቅ] ፍትሕ ጋዜጣ፣ አዲስ ታይምስ መጽሔት እና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ከ12 ሰዎች በላይ የግል ሃሳባቸውን ይገልጹበታል፤ ከድርጅታችሁ ሠራተኞች ብዛት ይልቅ የዓምደኞቻችሁ ቁጥር ይልቃል። ይሄ ደግሞ የጋዜጣውን ኤዲቶርያል ሐሳብ ለማንሸራሸር ዕድል አይፈጥርም። ሁሉም አገሪቷ ላይ ያሉ ችግሮችን አስቦ መጥቶ ይተነፍሳል እንጂ ‹‹ሳምንታዊ አጀንዳችን እነዚህ ናቸው›› ተብለው የመሠራት ዕድላቸው አናሳ ነው።

ይሄ የሚታየው ከጋዜጣው አሠራር አኳያ ነው። ኤዲቶሪያላችን የሚያስቀምጠው ነገር አለ። ሃይማኖትን የተመለከቱ በጣም ስስ የሆኑ ነገሮች አሉ። ከዚያ በተረፈ

ጋዜጣው ሙሉ በሙሉ ሐሳብን በነፃነት መግለጽ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ስላልን ከርዕስ አንቀጻችን ውጪ ሁላችንም የተለያየ ሐሳብ የምናንፀባርቀው ከዚያ ተነሥተን ነው። ከላይ እንደገለጽኩት ፍትሕ የተመሠረተችው የጋዜጠኝነት ሙያ ባንገበገባቸው ወይም ባቃጠላቸው ሰዎች ሳይሆን ጭራሽ ጋዜጠኛ እንሆናለን ብለው ባላሰቡት ነው።

የሆነ ሆኖ ትልልቅ አገራዊ አጀንዳዎች ሲኖሩን ኤዲቶሪያል ቡድናችን ተነጋግሮ በጋራ የሚሠራበት አጋጣሚ አለ። አዲስ ታይምስ ላይ በ‹‹አባይ ግድብ›› ዙሪያ የሠራነውን መጥቀስ ይቻላል። ልዕልና ላይ ወቅታዊውን የሚዲያ ሁኔታ በተመለከተ ሠርተናል። ፍትሕ ላይም ደጋግመን ኤዲቶሪያላችን ወስኖ የሠራናቸው አጀንዳዎች አሉ። ስለዚህም ከሞላ ጎደል የጋዜጣዋን ኤዲቶሪያል ሐሳብ ማንሸራሸር ችለናል ብለን መናገር እንችላለን። አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት አናጣላም፤ በብሔርም እንደዚሁ ነው። ከእነዚያ ውጪ የሚከለክለን/የማይከለክለን ኤዲቶርያል አቋም አለን ብለን የምንራቀቅበት ሁኔታ የለም። የጋዜጣው ዋነኛ የማዕዘን ድንጋይ

ፍርሃትን መግፈፍ ስለሆነ አሁን የምንከተለው ስልት ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ።

ይህ ምን ያህል ተሳክቶልናል ብለህ ታስባለህ? ይሄንንም የምናገረው በግምት ነው እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ

የተደረገ ወይም ያካሄድነው ጥናት የለም። ነገር ግን የተሻለ ነገር አምጥተናል ብዬ አስባለሁ። ሌላ ሰው መጥቶ ‹‹ይሄን ... ይሄን ፍትሕ የፈጠረችው አይደለምን?›› እስከሚል ድረስ ማለት ነው። የመምህራን ተቃውሞ፣ የፀረ- መጅሊስ እንቅስቃሴ የመሳሰሉት ‹‹ስትነጠቅ እምቢ በል›› የሚለው ፍትሕ የፈጠረችው ለውጥ እና መነቃቃት ነው ብዬ አስባለሁ። በሁለቱም በኩል ፍትሕን እንደሞዴል አንሥተው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጽፈው አይተናል።

ስትፅፍ ሐሳብን ገልጸህ መገላገልህን ነው ወይስ የሚያስከትለውን ውጤት (Consequence) ታሰላዋለህ?

ጋዜጠኝነት አርበኝነት አይደለም፤ ጦር ይዘህ ጠላትን ስታይ የምትወረውረውርበት/የምትሰካበት ተግባር አይደለም። ጋዜጠኛ ከሆንክ የምታነሣቸው ትችቶች እውነትን መሠረት ያደረጉ እና ሕዝብ ሊያውቃቸው ይገባል የምትላቸውን ነው። መፍትሄ ማግኘት አለባቸው ያልናቸውን ጉዳዮች እናነሣለን። ገዢው ፓርቲ እየሄደበት ያለውን ስሕተት መጠቆም እና የተሻለ መንገዶችን ማሳየት ላይ አተኩራለሁ። ኢሕአዴግ ብልጥ አምባገነን ነው። የእኛ ጋዜጣ (ፍትሕ) ታተኩር የነበረው የኢሕአዴግን የብልጠት ሴራዎችን ለሕዝብ በማሳየት እና በማጋለጥ ላይ ነው። የእኔም ጽሑፎች የሚቃኙት በዚሁ መልኩ ነው።

‹‹ተቃዋሚ›› ከሚባሉት ከአንዳንድ ፓርቲዎች በተሻለ መንግሥትን በጽሑፎችህ ለመገዳደር ትሞክራለህ። መጣጥፎችህም የጋዜጠኛ ሳይሆን የአርበኛ ወይም የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ዓይነት ናቸው።

እንደምታውቁት አደባባያችን ጭር ብሏል። ጠንካራ ተቃዋሚ የለም፤ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት በዘለለ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ያሉ አማራጭ የትግል ስልቶችን አንዱንም አይጠቀሙም። ተቃዋሚዎች ትልቅ ነገር አደረጉ ከተባለ መግለጫ ማውጣት ነው። መሪያቸው ሲታሰር፣ አቧራ የሚያስነሣና ለትችት የሚዳርግ ፖሊሲ ሲወጣ የእነሱ ሥራ መግለጫ ማውጣት ነው እንጂ በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ አማራጮችን አይጠቀሙም። ወደ እኛ ስትመጣ አንድ ጋዜጠኛ ሊያደርጋቸው የሚገቡ አማራጮችን ሁሉ በመጠቀማችን ከፓርቲዎቹ የተሻለ ግምት አስይዞልን ‹‹አርበኛ›› ሊያስብለን ይችላል። ይህን የሚያመጣው የአርበኝነት ሚና መጫወት የነበረባቸው ፓርቲዎች ጭርታን በመፍጠራቸው እና አንተ የድርሻህን በመወጣትህ ነው። እኔ ግን ከጋዜጠኝነት የዘለለ ሚና አለኝ ብዬ አላስብም።

ፍትሕ ላይ አስፍረኸው የነበረውን ‹‹የፈራ ይመለስ›› የሚለውን ጽሑፍህን ለአብነት ማንሣት ይቻላል። [ጠያቂው ጋዜጣውን ገልጦ እያሳየው] በሰላማዊ መንገድ ቢሆንም ‹‹መብትህን ለማስከበር ውጣ፣ ተንቀሳቀስ›› የሚል ጥቅል ሐሳብ አለው። (ተመስገን... ወደ 22 የዞረ)

ትያትር ማየት ናፍቆዎታል?

ፍሬሽማን ትያትር ሚኒሶታ መጣ፤ ተወዳጅ ተዋንያኖች ሁሉ ሚኒሶታ

ይመጣሉ ኦገስት 10 እና ኦገስት 11 እንዳይቀሩ

BISRAT ALEMAYEHU

& ASSOCIATES Meet your Friendly and Experienced professionals

@

The Center for Multi-Services

Tax, Insurance, Real Estate, Notary,

Application Forms,Translation and

More ታክስ፣ ኢንሹራንስ፣ ሪል እስቴት፣ ኖታሪ፣

ውክልና፣ትርጉምና በርካታ ተዛማጅ አገልግሎቶች

TaaksInshuuraans. Riil Esteet.

Nootarii. Bikka bu'aa. Hiika

afaanii fi Tajaajiloota Heduu kana

fakkaatan

WISER INSURANCE

AGENCY, St. Paul More Insurance Companies, More Price Choices!

[Auto. Home. Life. Health. Business]

Address: 1821 University Ave. W. Suite S-301 Saint Paul, MN 55104

Tel: 651 649 0644 / 651 209 6077 Fax: 651 649 0620

- ተመስገን ደሳለኝ [ጋዜጠኛ] “ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት? “በተሰኘውና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታትሞ በገበያ ላይ በዋለው መፅሀፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰጠው ቃለ - ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ‹‹ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ሳይሆን የፀረ-ኢሕአዴግ ፖለቲካ አቀንቃኝ ነው›› ሲሉ ጋዜጠኛነቱ ላይ ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል ከብዙ ፓርቲዎች በተሻለ ገዢው ፓርቲን በብዕሩ የታገለ፣ ጋዜጣ አንባቢው ኅብረተሰብ ከፖለቲካዊ ፍርሃት

እንዲላቀቅ በጽናት የጣረ፣ የቁርጥ ቀን ጋዜጠኛ መሆኑን ምስክርነት የሚሰጡለትም አሉ። አራት ዓመት ገበያ ላይ በቆየችው ፍትሕ ጋዜጣ፣ ታይተው በጠፉት አዲስ ታይምስ መጽሔትና ልዕልና ጋዜጣ ላይ ባሰፈራቸው መጣጥፎቹ የመነጋገሪያ ርዕስ የነበረው ተመስገን ለእሱ በተሰጡ ቀጣይዎቹ ገጾች ላይ ከእዚህ መጽሐፍ አዘጋጆች የቀረቡለትን ሞጋች ጥያቄዎች በመመለስ የ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› መጽሐፍ አካል ሆኗል።

የፎቶ ግራፍ ምንጭ፡ CPJ

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Two Location

5103 University Ave, NE,

5104Columbia Heights, MN 55421 2929 university Ave. SE

Minneapolis, MN 55414

የኢሳያስ ከበደ ምክር፡- ውድ ጠያቂያችን የተቸገርክበትን ጉዳይ አንሰተሃል፡፡ እኛም ተመልክተናል፡፡ በረከት ያሉ አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ችግርም በመሆኑ ጉዳዩን ሃገር ቤት ካለው ኑሮ ጋር በማያያዝ ለመመለስ እሞክራለሁ። የማትፈልጋቸውና አንተን የሚያስደስቱ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ተደጋግመው እንደተከሰቱ ገልፀሃል፡፡ አይዞህ አትከፋ፣ ችግሩ አንተ ካለህ አስተሳሰብና ባህሪ የመጣ እንጂ እድለ ቢስ ወይም እጅህ አመድ አፋሽ ስለሆንክ አይደለም፡፡ ምላሹን በሚከተለው መልክ ለማብራራት ሞክረናል፤ ለሌሎች አንባቢያንም ያስተምራል ብለን እናምናለን፡፡

አንዳንዶች የማይፈልጉትን ነገር የበለጠ ያስባሉ፡፡ አንድን ስራ ሊጠሉት ይችላሉ፡፡ ለሰዎችም ምን ያህል እንደሚጠሉት ይናገራሉ፡፡ ለዚህ ስራ ያላቸው ስሜትም የሚረብሻቸው አይነት ነው፡፡ እንዲሁም ማየትና ማግኘት የማይፈልጓቸው ሰዎች አሉ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ስም በተነሳ ቁጥር ወይም ደግሞ ድንገት በመንገድ ላይ በተመለከቷቸው ቁጥር ውስጣቸው ብቻ ሳይሆን ውጫቸውም ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ስለዚህም ሰዎች እንዴት

እንደሚጠሏቸው ሳይቀር ለሌሎች ያወራሉ፡፡ እነዚህ የጠሏቸው ሰዎች የስራ አለቆቻቸው ወይም ደግሞ የተጣሏቸው ጓደኞቻቸውና የፍቅር አጋሮቻቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማየትና በቦታው መገኘት የማንፈልጋቸው አካባቢዎችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህንም በዚያው ልክ ልናማርራቸው እንችላለን፡፡

የትኛውም ውጫዊ ዓለም ነገር የተገነባው ከኳንተም ፓርቲክሎች እንደመሆኑ መጠንና የኳንተም ፓርቲክሎችም በውስጣችን ያለውን ተደጋጋሚ ምልክታ ተከትለው የምንፈልገውን አይነት ቅርፅ የሚዙ በመሆናቸው ዋናው ነገር ጥላቻና ፍቅራችን ሳይሆን ተደጋጋሚ ምልከታችን ነው፡፡ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚፈጥረው፡፡ አንድን ነገር የበለጠ ደጋግመን ባፈቀርነው ወይም ደጋግመን በጠላነው ቁጥር የኳንተም ፓርቲክሎች ነገርየው ለእኛ ይጠቀመን ወይም ይጉዳን የሚያውቁት ጉዳይ የለም፡፡ በመሆኑም ሁልጊዜ ደጋግመን የጠላነውን ወይም ደጋግመን ያፈቀርነውን ነገር ቅርፅ ሰጥተው ያሳዩናል፡፡

ደጋግመን የጠላናቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ ልንሆን ወይም

ከእነሱ ላንርቅና መልሰን ልንፋቀር እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ተደጋጋሚ ምልከታው (Hate based ob-servation) ስለእነሱ በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ ደጋግመን ያፈቀርነውን ነገር (Love based observation) የበለጠ ተከስቶ እናየዋለን፡፡

በመሆኑም በህይወታችን እንዲከሰቱና እንድናያቸው የማንፈልጋቸውን ነገሮች ማስወገድ የምንችለው ተደጋጋሚ ጥላቻን በማንፀባረቅ ሳይሆን ለዚያ ነገር የሚኖረንን ምልከታ ዜሮ በማድረግ ነው፡፡ ልክ አንድ ስለማናውቀው ሁሉ በህይወታችን ልናያቸው ስለማንፈልጋቸው ሰዎችም ሊኖረን የሚገባው ስሜት ምንም መሆን መቻል አለበት፡፡ ስለ አንድ ነገር የሚኖረን ምልከታ (observation) ምንም በሆነ ቁጥር የኳንተም ፓርቲክሎች የሚኖራቸው ክስተት ፓርቲክላዊ መሆኑ ይቀርና ሞገዳዊ መሆን ይጀምራል፡፡ በሞገድ ክስተት ውስጥ ደግሞ ምንም ነገር ልንመለከት አንችልም፡፡ ወይም የክስተት ዕድላቸው (probability of predictability) በእጅጉ ያንሳል፡፡ ነገር ግን ተደጋጋሚ ትኩረታችን (በፍቅርም ይሁን በጥላቻ) በአንድ ነገር ላይ በተደጋጋሚ በተንፀባረቀ ቁጥር የኳንተም

ፓርቲክሎች የሚኖራቸው የክስተትና የሚይዙት የቦታ (position) እና በዕድል የመወሰን ሁኔታዎች (predictability) የላቀ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የምንጠላው ወይም የምናፈቅረው ነገር የበለጠ ሊከሰት ይችላል፡፡ በህይወታችን ልናያቸውና እንዲኖሩን በምንፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያ የፍቅራዊ ትኩረትንና ቋንቋን ተግባራዊ ማድረግ ሲጠበቅብን በህይወታችን ተከስተው እንድናያቸው በማንፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያ ደግሞ ሊኖረን የሚገባው ስሜት መሆን ያለበት ዜሮ ነው፡፡ ወይም ምንም ነው፡፡ የፍቅር ተቃራኒ ምንነት ነው ወይም ደግሞ ‹‹indifferent›› መሆን ነው እንጂ የጥላቻ ስሜት አይደለም፡፡ የጥላቻ ስሜት ራሱን የቻለ ስሜታዊ ትኩረት (observation) ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተራው የኳንተም ዓለሙን ተፅዕኖ ውስጥ በመክተት የጠላነው እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ ‹‹የጠሉት ይወርሳል፤ የፈሩት ይደርሳል›› እንደሚባለው ነው፡፡

የሰው ልጅ በህይወቱ እንዲገጥሙት የሚፈልጋቸው የተለያዩ ገንቢ ውጤቶች አሉ፡፡ ሰዎች የሚወዱትና የሚያከብሩት (በትዳሬ... ወደ ገጽ 11 የዞረ)

እኔ የ38 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ ስሆን ፈጣሪዬ የተመሰገነ ይሁንና እስካሁን ጤናዬን አልነሳኝም፡፡ ቤተሰብ መስርቼ ህይወትን እየመራሁ ብገኝም እስካሁን አሳካሁት የምለው የለኝም፡፡ ያስደስተኝ ነገርም የለም፡፡ እንደውም የምፈልገውን ሳይሆን የማልፈልገው ነገር ነው እየሆነ ያለው፡፡ በትዳሬም ሆነ በስራዬ ደስተኛ አይደለሁም፡፡ የተከፋሁ ሰው ነኝ፡፡ ታዲያ ምን ይሻለኛል? ትላላችሁ፡፡ ወይስ እድሌ ይሆን?

ስሜ አይገለፅ

የዛሬው ጥያቄዬ ስለ እንቅልፍ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ መተኛት እየፈለኩ አይሳካልኝም፡፡ የተሟላ ኑሮ ያለኝ ነኝ፤ በጣም አሪፍ መኝታ ክፍልና አልጋ አለኝ፡፡ እንደውም 35 ሺ ብር የተገዛ አልጋ ላይ ነው የምተኛው፡፡ ግፋ ቢል ከ4 ሰዓታት የዘለለ እንቅልፍ የለኝም፡፡ ይሁን እንጂ ድሮ መደብ ላይ ከምተኛው ጋር ሲነፃፀር አሁን አሁን እንቅልፌ እየቀነሰ መጥቶ ጭራሽ ሊጠፋ ችሏል፡፡ እናም፣ በአጭሩ እንዴት ችግሬን ልፈታ እንደምችል ከእናንተ ምክር እሻለሁ አመሰግናለሁ፡፡

እምሩ ነኝ መልስ፡- በደብዳቤህ ለመግለፅ እንደሞከርከው ውዱ አልጋህ

እንቅልፍን ሊገዛልህ እንዳልቻለ ገልፀሀል፡፡ በቅድሚያ እስኪ ስለ እንቅልፍ ምንነት ትንሽ እንበልና ወደ መፍትሄው እናምራ፡፡

እንቅልፍ ለሰው ልጅ ከመሰረታዊ ፍላጎቶች አንዱ ነው፡፡ አዕምሮ (አንጎል) ከአድካሚ የቀን ስራው አረፍ የሚለውና የሚታደሰው በማታው እንቅልፍ ነው፡፡ ይህን የተነፈገ፣ አዕምሮ ነጭናጫ ይሆናል፣ ይቆጣል፣ ማገናዘብ (ማሰላሰል) ይከብደዋል፣ ለአደጋ የተጋለጠ ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ ግለሰቡ እንደ ጭንቀትና ሰው ጥርጣሬ ያሉ የአዕምሮ ህመም ምልክቶች ሊታዩበት ይችላሉ፡፡

የአንድ ሰው እንቅልፍ ጤናማ ነው የሚባለው መቼ ነው? ምን ያህል ሰዓትስ ሲተኛ ነው? የሚሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ይፈልጋሉ፡፡ እንቅልፍ አዕምሮ ላይ እና በተቀረው የሰውነት ክፍል ላይ ከሚያሳያቸው (ከሚያሳድርባቸው) ለውጦች በሁለት መሰረታዊ ክፍሎች ይከፋፈላል፡፡ ሁለቱም የእንቅልፍ ክፍሎች ከ90-100 ደቂቃዎች ይፈጃሉ፡፡ የመጀመሪያው የእንቅልፍ ክፍል ግለሰቡ ወደ አልጋ ከሄደበት ደቂቃዎች እስከ ድብን ያለ እንቅልፍ የሚወስድበት ጊዜ ነው፡፡

ይህ የእንቅልፍ ክፍል አራት መሰረታዊ ደረጃዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎች ግለሰቡን ከንቁነት ወደ እንቅልፍ የሚመሩ ሲሆን የመጨረሻዎቹ ሁለት ደረጃዎችን በተለይም አራተኛው ደረጃ ግለሰቡ ድብን ያለ እንቅልፍ የሚሰድበትና በቀላሉ የማይቀሰቀስበት ደረጃ ነው፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ግለሰቡ የመታደስ ስሜት አይሰማውም፡፡ ይህ የእንቅልፍ ክፍል ሁለተኛው የእንቅልፍ ክፍል የሚታወቅበት የአይን በጎን ወደ ጎን መንቀሳቀስ ጎልቶ ስለማይታይበት አይን የማይንቀሳቀስበት የእንቅልፍ ክፍል (Non Rapid eye movement sleep phase) ይባላል፡፡

ሁለተኛው የእንቅልፍ ክፍል አይን በፍጥነት የሚንቀሳቀስበት እና መላው ሰውነት እንደ በድን የሚሰንፍበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ ክፍል አይን የሚንቀሳቀስበት (ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው የሚሮጥበት) የእንቅልፍ ክፍል ይባላል፡፡ ጡት ለጓደኞቻችን የምንተርከው ህልም የሚታየውም በዚህ የእንቅልፍ ክፍል ነው፡፡ በአንድ ሌሊት አንድ ግለሰብ ከመጀመሪያው የእንቅልፍ ክፍል (አይን በማይንቀሳቀስበት) ወደ ሌላ አይን የማይንቀሳቀስበት የእንቅልፍ ክፍል ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ በጥቅሉ በአማካይ የአዋቂ እንቅልፍ ከ70-75 በመቶ በመጀመሪያው የእንቅልፍ ክፍል የተያዘ ሲሆን የተቀረው 25 በመቶ ደግሞ አይን በሚንቀሳቀስበት (ህልም በማታይበት) የእንቅልፍ ክፍል የተያዘ ነው፡፡ አንድ ግለሰብ ተኝቶ ታድሶ እንዲነሳ የመጀመሪያውን የእንቅልፍ ክፍል ሳይቆራረጥበት (አራተኛውን ደረጃ) መጨረስ ይኖርበታል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለረጅም ሰዓት ተኝተው ሲነሱም ራስ ምታት እና ድካም የማይለያቸው እንቅልፍን መጨረስ ስለማይችል የመጀመሪያውን የእንቅልፍ ክፍል አራቱን ደረጃዎች ሳይጨርስ

ቶሎ ቶሎ እንዲነቃ ስለሚያደርገው ጧት ላይ ምንም ሳይተኛ እንዳደረ እንደከበደው ይነሳል፡፡

ብዙዎች ለእንቅልፍ የመደቡት ሰዓት (ጊዜ) ልክ ይሆን ብለው ይጨነቃሉ፡፡ የሰው ልጅ ሁሉም እንቅልፍ የግድ የሚያስፈልገው ቢሆንም ለእንቅልፍ የምንሰጠው ዕድሜ እንደ ግለሰቡ ተፈጥሮ፣ ፆታ እና ዕድሜ ይለያያል፡፡ አዲስ የተወለደ አራስ ህፃን ከቀኑ 24 ሰዓት ውስጥ 20 ሰዓቱን ቢተኛበት የሚጠበቅ ነው፡፡ ህፃኑ እያደገ ሲሄድ ይህ የእንቅልፍ ረሃቡ እያነሰ ይሄዳል፡፡ ህፃናት እያደገ ሲሄድ ይህ የእንቅልፍ ረሃቡ እያነሰ ይሄዳል፡፡ ህጻናት በቀን ውስጥ ከ8 ሰዓት እስከ 14 ሰዓት ድረስ ሊተኙ ይችላሉ፡፡ የአዋቂዎች አማካይ ቀን እንቅልፍ ከ7-8 ሰዓት ነው ተብሎ ቢነገርም ለሶስት ሰዓት ብቻ ያህል ቢተኙ የማቃቸው አሉ፡፡ እንዲሁም በቀን ውስጥ እስከ 12 ሰዓት ያህል መተኛት የሚያስፈልጋቸው ይኖራሉ፡፡ ዋናው ነጥብ ምን ያህል ሰዓት ተኛን ሳይሆን በተኛነው እንቅልፍ ታድሰን ተነስተናል ወይ? የሚለው ነው፡፡ አራት ሰዓት ያህል ብቻ ተኝቶ ሙሉ ለሙሉ የሚነቃና አዕምሮው የታደሰ የመሰለው ግለሰብ ለምን ስምንት ሰዓት አልተኛሁም ብሎ ሊጨነቅ አይገባቸውም፡፡ በተጨማሪም ዕድሜያቸው ከ35 ያለፈ ሴቶች በአማካይ ከወንዶች ረዘም ላለ ሰዓት እንደሚተኙ ይታወቃል፡፡

ከላይ እንደተገለፀ አንድ ሰው በቂ እንቅልፍ ያላገኘ ከመሰለውና ከተለመደው የእንቅልፍ ጊዜው የተለየ ሁኔታ እንቅልፍ ያጣ ከመሰለው እንቅልፍ ማጣት (Insomnia) አጋጥሞታል ማለት ነው፡፡ እንቅልፍ ማጣት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ምክንያቱን ለማወቅ በሚያስችል ሁኔታ በአራት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው እንቅልፍ መውሰድ አለመቻል (sleep onset Insomnia)ነው፡፡ እነዚህ እንቅልፍ አልወስድ

ብሏቸው ሌሊቱ የሚጋጭባቸው ሲሆን በአዕምሯቸው የሚብላላ ሀሳብ ወይም የሚያስጨንቃቸው ጉዳይ ያለባቸው ላይ ይበረታል፡፡ ሁለተኛው አይነት የእንቅልፍ ማጣት ደግሞ እንቅልፋቸውን መጠበቅ የማይችሉ (ቶሎ ቶሎ የሚነቁ) (Sleep maintenance insolanio) ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅልፍ የመውሰድ ችግር ያለባቸውም ይልቁኑ ቶሎ ቶሎ መንቃት ይስተዋልባቸዋል፤ ይህ ጠጪዎች ላይ ጎልቶ የሚታይ ችግር ነው፡፡ ሶስተኛው የእንቅልፍ ማጣት አይነት ደግሞ ሌሊት (ንጋት) ላይ ቀድሞ መንቃት ሲሆን ድብርት እና ጭንቀት የበዛባቸው ሰዎች ላይ በስፋት የሚታይ ችግር ነው፡፡ እንዲሁም ተኝተው የማይታደስ (Non restorative sleep) የሚኖራቸው አሉ፡፡

እንቅልፍ ማጣት አሳሳቢ ችግር ከመሆኑ አንፃር ከምክንያቶቹ ይልቅ መፍትሄዎቹ ይበልጥ ይፈልጋሉ፡፡ ከላይ ምክንያቶቹን ለመዘርዘር የተሞከረው ምክንያቶቹን ፈልገው ለማግኘት የሚረዱ ጠቋሚ ምልክቶች በመሆናቸው ነው፡፡ ወደ መፍትሄው ስንመጣም እንዲሁም የእንቅልፍ ማጣቱን በጊዜ (ቆይታ) መከፋፈል አስፈላጊ ነው፡፡ ከመፍትሄ አንፃር የእንቅልፍ ማጣት ችግር በሶስት ተከፍሎ እንደ ደረጃው የተመጠነ ህክምና ይሰጠዋል፡፡ ይህ ክፍል እንቅልፍ በማጣት የተቸገሩ ሁሉ አጥብቀው የሚሹት በመሆኑ በዝርዝር ማየቱ ጠቃሚ ነው፡፡

1. ጊዜያዊ የእንቅልፍ ማጣት (Transient Insomnia) ይህ ጊዜያዊ የሆነና ለጥቂት ቀናት ብቻ የሚቆይ የእንቅልፍ

ማጣት ነው፡፡ የመኝታ አካባቢን መቀየር እና ከአንዲት የጊዜ ክልል (Time zone) ወደ (ውድ አልጋ... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

የዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምክር፡ ውድ ዓለም፡- ጉንፋን ሲያጓድዱት በሽታ ይሆናል- ባያጓድዱትስ? ለነገሩ የት ሊደርስ! ይሁን እንጂ ተጠቂ ለሆነ ግለሰብ የበሽታ ትንሽ የለውም፡፡ ያልተነካ ግልግል ያውቃል እንደሚባለው ላልተነካ ሰው ጉንፋን እንደበሽታ ላይቆጠር ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ የህመም ቀላል የለምና ጉንፋንም በቀላሉ ሊታይ አይገባም፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት በመዲናችን አዲስ አበባ እየታየ ያለው ጉንፋን ከተላላፊነቱና ክብደቱ አንፃር ሲታይ ይሄ ነገር ‹‹ጉንፋን ነው ወይስ በርድ ፍሉ?›› የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ዳድቶናል፡፡ ለማንኛውም መንስኤውንና መፍትሄ ያልነውን እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

ጉንፋን ተብሎ የሚጠራው በጥቅሉ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ የላይኛው የመተንፈሻ አካላችን ኢንፌክሽን ሲሆን፣ በዓለማችን በአጠቃላይ በተላላፊ ኢንፌክሽንነትና የዕለት ተዕለት ተግባራችን በብቃት እንዳንወጣ በሚፈጥረው ሳንካ፣ ቁጥር አንድ ተጠቃሽ በሽታ ሆኗል፡፡

እነዚህ ቁጥራቸው ከ200 ያላነሰ የቫይረስ አይነቶች ከብዛታቸው የተነሳ ሰውነታችን ለነዚህ የሚሆን የመከላከያ አይነት አምርቶና አዘጋጅቶ ሙሉ በሙሉ ሊቋቋም አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ የሰው ልጅ በዕድሜው በገፋ ቁጥር ከሞላ ጎደል በጉንፋን የመያዝ ዕድሉ እየቀነሰና በጉንፋን ሳቢያ የሚመጡትንም ስሜቶች የመቆጣጠር ሁኔታው እየጨመረ ይሄዳል፡፡

በአጠቃላይ በጉንፋን ቫይረስ ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ 75 በመቶ የሚሆኑት ስሜቱን የሚቋቋሙ ሲሆኑ 25 በመቶ ደግሞ የጉንፋን ስሜቶችና ህመሞች የሚጎሉባቸው ናቸው፡፡ በአማካኝ ቤት የሚውሉ ህፃናት ከ6-10 ጊዜ፣ በመዋዕለ ህፃናት የሚውሉ ልጆች ከ10-12 ጊዜ እንዲሁም ወጣቶችና ጎልማሶች ከ2-5 ጊዜ በዓመት የጉንፋን ተጠቂዎች ይሆናሉ፡፡

ይህ የጉንፋን ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በዋነኛ የሚተላለፍባቸው መንገዶች፣ በጉንፋን የተያዘ ሰው ሲያወራ፣ ሲያስል፣ ወይንም ሲያስነጥስ፣ በአማካኝ ሁለት ሜትር ርቀት አካባቢ ሆነን ቫይረሱ የያዘውን አየር ወደ ውስጥ ስንስብ፣ ጉንፋን የተያዘን ሰው በእጃችን

ጨብጠን ወይንም የተጠቀመበትን (በእጁ የያዘውን) ማንኛውም ዕቃ ነክተን አይናችንን አፍንጫችንን ወይንም አፋችንን የያዝን እንደሆነ ነው፡፡

ይህ ቫይረስ በአብዛኛው ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ጉንፋን በተያዘ በመጀመሪያው ከሁለት እስከ ሶስት ባሉት ቀናት ውስጥ ሲሆን በጥቅሉ ግን እስከ ሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥም ሊተላለፍ የሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡

ጉንፋን በአብዛኛው በክረምት (በብርድና ዝናባማ ወቅት) በዝቶ ሚታይበት ምክንያት በተለምዶ እንደሚባለው፣ ብርድ መትቶን፣ በቅዝቃዜ ወቅት ልብስ ሳንደርብ ወጥተን፣ ድራፍት መትቶን ወይንም በቅዝቃዜ በእርጥብ ፀጉር ከቤት ወጥተን ሳይሆን፣ የጉንፋ ቫይረሶች ቀዝቃዛ አየር ለመራባት አመቺ ስለሚሆንላቸውና እንዲሁም በክረምት ወቅት ከቤት ያለመውጣትና ቤት ውስጥ አብሮ የመቀመጥ ሁኔታ የጉንፋንን የመተላለፍ እድል ስለሚጨምረው ነው፡፡

በጉንፋን የመያዝ ምልክቶችስ ምን ምን ናቸው? የጉንፋን ቫይረስ እንደ ብዛቱ ሁሉ ሰዎች ላይ የሚያስከትለው

ስሜትም የተለያየ ቢሆንም፣ በላንቃችንና በጉሮሮአችን አካባቢ የመከርከር ስሜት ብሎም በሚወጡበት ጊዜ የህመም ስሜት መሰማት፣ የአፍንጫችን መደፈንና ከአፍንጫ የሚወጣው ቀጭንም ሆነ ወፍራም ፈሳሽ መብዛት፣ ማስነጠስ፣ ማሳል፣ የራስ ህመም መሰማት፣ በትንሹ የትኩሳት ስሜት መሰማት፣ ድካም ድካም ማለት፣ ቁርጥማት መሰማት፣ እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ ከሞላ ጎደል ይጠቀሳሉ፡፡ አንድ ሰው በጉንፋን ቫይረስ ከተያዘ በኋላ ከሁለት እስከ ሶስት ቀናቶች ባሉት ጊዜ ውስጥ የጉንፋን ስሜት ሊጀምረው ይችላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በአብዛኛው የጉንፋን ስሜት ያለው ሰው በአማካኝ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሊሻለው ቢችልም እስከ ሶስት ሳምንታት ያክል የሚቆይበት አጋጣሚ አለ፡፡

በጉንፋን ላለመያዝ የመከላከል እርምጃ በጉንፋን ከተያዘ ሰው በተቻለ (ጉንፋን... ወደ ገጽ 12 የዞረ)

በጋው በመጣ ቁትርም ሆነ በክረምት ጉንፋን ይደጋገምብኛል። ሌሎች የቤተሰብ አባላቶቼን ወዲያው ሲተዋቸው እኔን ግን አፍንጫዬን እንደዘጋኝ አልፎ አልፎም ከባድ የአፍንጫና የጉሮሮ ፈሳሽ ያከታትልብኛል፡፡ ጉንፋን በመጣብኝ ቁጥር ምን ባደረገው ሊተወኝ ይችላል? እባካችሁን መላ በሉኝ፡፡

ዓለም ተስፋ እኔ የ30 ዓመት ወጣት ስሆን ትዳር ከያዝኩ አራት ዓመቴን ይዣለሁ፡፡ እስካሁንም አልሃምዱሊላ የሶስት ልጆች አባት ለመሆን በቅቻለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ከባለቤቴ ጋር በልጆች አስተዳደግ ብዙም ልንስማማ አልቻልንም፡፡ እሷ ገጠር ነው ያደገችውና ልጆቹን ልክ በድሮው ባህል ለማሳደግ ትሞክራለች፡፡ እኔ ደግሞ ዘመናዊውን ባህል መከተል አለብን የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ እኔ በአንድ በኩል ልጆቹን ስመክርና ስቆጣ እሷ ደግሞ በተቃራኒው ነው የምታደርገው፡፡ እኔን ስለሚፈሩኝ ነው እንጂ የሚሰሙት እናታቸውን ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንዴት ማሳደግ እንዳለብኝ ብንመካከርም የሚያስማማን ሀሳብ ግን አላገኘንም፡፡ ልጆችን እንዴት ማሳደግ እንዳለብን መፅሐፍ ካለ ብዬ ብጠይቅም አጣሁ፡፡ እባካችሁ በልጆቻችን የተነሳ ቤታችን ሰላም አጣ፤ ከመለያየታችንም በፊት አስታራቂ መላ ካላችሁ ብዬ ነው፡፡

መሀመድ ነኝ

የኢሳያስ ከበደ ምክር፡- ከኢሜልህ ለመረዳት እንደተሞከረው ገና ስትጀምር የ30 ዓመት ወጣት እንደሆንክ ገልፀሃል፡፡ ይህ መስተካከል አለበት፡፡ የ30 ዓመት ጎልማሳ እንጂ ወጣት ባለመሆንህ፡፡ ጎልማሳ ስልህ ግን ጎረምሳ ያልኩህ እንዳይመስልህ፡፡ የበሰለ ወጣት ለማለት ነው፡፡ እንዲህ አይነተ ጥያቄን መጠየቅ በራሱ ብስለትህን የሚገልፅ ነውና፡፡ በተረፈ ግን በዚህ አጭር የትዳር ዘመን ውስጥ ሶስት ልጆች ማፍራትህን ስንመለከት እንዴት ነው እናንተ አካባቢ የእርግዝና መከላከያ የለም ወይ? እንድንል ይዳዳናል፡፡ ያው የአሜሪካን ኑሮ በራሱ ‹‹ውስን ነገር ግን የበለፀገ ቤተሰብ›› በሚል የሚገድብ በመሆኑ። ይሁን እንጂ አቅሙ ካለህ ግን ወይም ከአቅሙ በተጨማሪ ጊዜያዊም ካልሆነ ግን ምርጫው ያንተ ነው፡፡ በርታ!

ወደ ጥያቄህ ስመለስ ታዲያ የብዙ ወላጆችን ችግር የያዘ ሆኖ ይታያል፡፡ እንደምታውቀው ብዙ ወላጅ ልጁን የሚያሳድገው በነሲብ ነው፡፡ በነሲብ በመሆኑም የልጁ የወደፊት ማንነት ነሲባዊ ይሆናል፡፡ እንዳጋጣሚ ካልሆነ በቀር ልጅ ልጅ

የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው፡፡ አንዳንድ ወላጅ ልጁ ስኬታማ ሆኖ እንዲወጣለት ይፈልጋል፤ ይሁን እንጂ ልጁን እያሳደገበት ያለው አካሄድ ሲታይ ግን ወላጅ ራሱ ከመወለዱ በፊት እንደ ልጅ ማደግ አለበት ያሰኛል፡፡ አንዳንድ ወላጆች ከልጅ ያልተናነሰ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ ራሳቸው ወላጆቹ አሳዳጊ የሚያሰፈልጋቸው አይነት ማለት ነው፡፡ የሚናገሩትን መሆን የማይችሉ፣ ልጃቸውን የምክር መዓት የሚያሸክሙ እነሱ ግን የሚመክሩትን በተግባር ማሳየት የማይችሉ ናቸው፡፡ እንዲህ አይነት ወላጅ ልጅ ቢወጣለት ነው የሚገርመው፡፡ በእንደነዚህ አይነት ወላጅ ማደግና ሎተሪ መቁረጥ የመውጣትና ውጤታማ ዕድሉ ተመሳሳይ ነው፡፡ ትልቁ ነገር ልጆች እንዲሆኑ የምንፈልገውን ነገር በተግባር ማሳየት መቻል ነው፡፡ አሪፍ ምግብ ማብላቱንና ማሞላቀቁ እንዲሁም አሪፍ ትምህርት ማስተማሩ ብቻውን ለውጥ አያመጣም፡፡

አንዳንድ ወላጅ ራሱ በልጅነቱ ያደገበትን የአስተዳደግ ስርዓት እንደገና በሚወልደው ልጅ ላይ የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ (በልጅ ... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

ከዳንኤል ክብረት Danielkibret.com

አንዳንዱ የሞተበት ቀን የድል ቀን ተብሎ ይከበርበታል፤ ሕዝብ የመሞቻውን ቀን የሚናፍቁለት ሰውም አለ፡፡ አንዳንዱ እንኳን ተወለደ ሳይባልለት እንኳን ሞተ ይባልለታል፡፡ አንዳንዱ እንዲሞት ይጸለይለታል፤ ሌላው እድሜው እንዲያጥር ይረገማል፡፡ ከዚህ የተለየ ነው ማንዴላ፡፡

ሚሊየኖች እንዳይሞት የሚጸልዩለት፤ ሚሊየኖች እንዲኖር የሚመኙለት፤ ሚሊየኖች ከእድሜያቸው ተቀንሶ ቢሰጠው የሚፈቅዱለት፤ ሚሊየኖች እነርሱ ሞተው ሊያኖሩት የሚሹት፤ ሚሊየኖች በየቀኑ የጤናውን ሁኔታ ከራሳቸው ጤና በላይ የሚከታተሉለት ሰው ነው ማንዴላ፡፡

አፍሪካ አያሌ መሪዎችን በቅርብ ዘመናችን አስተናግዳለች፡፡ አያሌ የነጻነት ታጋዮችን አይታለች፡፡ እንደማንዴላ ታሥረው የታገሉ ነበሩ፡፡ እንደ ማንዴላ ድርጅት አቋቁመው የተዋጉ ነበሩ፤ እንደ ማንዴላ ሕዝባቸውን ለነጻነት ያበቁ ነበሩ፤ እንደ ማንዴላም ከነጻነት በኋላ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የሆኑም ነበሩ፤ እንደ ማንዴላ ከሀገር ተሰደው የኖሩ ነበሩ፤ ታድያ ማንዴላን ምን ልዩ አደረገው?

ማንዴላ የታገለው ለፍትሐዊነት ነው፡፡ ደጋግሞ ይናገር እንደ ነበረው ‹‹እኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው›› ይል ነበር፡፡ በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከነጻነት ትግል በኋላ ጭቆና አልቀረም፡፡ ነገር ግን ነጭ ጨቋኞች በጥቁር ጨቋኞች ተተክተዋል፡፡ በነጮች ተይዞ የነበረው የገዥነት ቦታ ለሥልጣን በበቁት ታጋዮች ፓርቲዎችና ጎሳዎች ተተካ፡፡ የነጻነት ተዋጊዎች የፍትሕና እኩልነት አስፋኞች ሳይሆኑ አዳዲሶቹ ገዥ መደቦች ሆነው ብቅ አሉ፡፡ በነጮች ተይዞ የነበረውን ሀብት ነጻ አውጭ ግንባሮችና ፓርቲዎች ወረሱት፡፡ ስለዚህም ሕዝቡ በትግሉ ጨቋኞችን በሌሎች ጨቋኞች ተካቸው እንጂ ፍትሕና እኩልነትን ለማግኘት አልታደለም፡፡

ማንዴላ ይህንን ነበር የተዋጋው፡፡ እንደተመረጠ ብዙዎች የነጮች መሬት ተቀምቶ ለጥቁሮች እንዲሰጥ፣ ነጮች ከሀገሪቱ እንዲባረሩ ይፈልጉ ነበር፡፡ እርሱ ግን አላደረገም፡፡ ‹መሬቱ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲዳረስ እንጂ መሬት አልባ ነጮች የመፍጠር ዕቅድ የለንም› አለ፡፡ ጥቁሮች ይበልጥ ነጻ የሚወጡት የበለጸገች ደቡብ አፍሪካ ስትኖር እንጂ በደኸየች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አይደለም ብሎ አመነ፡፡ ለዚህ ደግሞ የብዙ ዘመን ሀብትና ልምድ ያላቸው ነጮች ወሳኞች መሆናቸውን ተገነዘበ፡፡ ለዚህም ነበር በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ያየነው ምስቅልቅል በደቡብ አፍሪካ ያልተከሰተው፡፡

ማንዴላ የዕርቅና የፍቅር ሰው ነበር፡፡ በነጮችና በጥቁሮች መካከል ለዘመናት በአፓርታይድ የተፈጠረውን መከፋፈል፣ መጠላላትና መገፋፋት በዕርቅና በይቅር ባይነት እንጂ በመሣሪያና በበቀል ሊጠፋ እንደማይችል የተረዳ መሪ ነው፡፡ አፓርታይድ ሲገረሰስ የይቅርታ ኮሚሽን ተቋቁሞ፣ ነባር የሕዝብ ለሕዝብ ችግሮች በተቻለ መጠን በይቅርታና በዕርቅ እንዲወገዱ ሠርቷል፡፡ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ከነጻነት በፊት የነበሩ ገዥዎችና አበሮቻቸው ወደ እሥር ቤት ሲወረወሩና ወደ ውጭ ሲሰደዱ፤ በደቡብ አፍሪካ ግን የከፋ ወንጀል ካልፈጸሙና ይቅርታ ለመጠየቅም ከፈቀዱ ችግሩን በዕርቅና በይቅርታ ለመፍታት ተችሏል፡፡ በዚህም ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ብቻ ሳይሆን ሀገርን አፍርሶ ከመሥራት አባዜ ነጻ እንድትወጣ አድርጓታል፡፡

ማንዴላ ለሰዎች ልጆች ሁሉ የቆመ መሪ ነበረ፡፡ ከዊኒ ማንዴላ ጋር ያፋታቸው ዋነኛው ምክንያት ዊኒ ማንዴላ በነጻነት ትግሉ ወቅት ‹ለነጻነት ትግሉ› ሲባል ፈጽመውታል የተባለው ኢ ሰብኣዊ ድርጊት በእርቅና ይቅርታ ኮሚሽኑ መጋለጡ ነበር፡፡ ምንም

እንኳን ለነጻነት ትግሉ ሲባል ቢደረግም፣ ምን እንኳን ዊኒ ማንዴላ ቢሆኑም ማንዴላ ግን ሊታገሡት አልቻሉም፡፡ የነጻነት ታጋይ ድርጅቱ ኤ ኤን ሲ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ የፈጸማቸው ኢሰብአዊ ድርጊቶች ካሉ ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ አለበት ብለው የሚያምኑት ማንዴላ በዚህ ምክንያት ከዊኒ ጋር ተለያይተዋል፡፡ ከነጻነት በኋላ አያሌ የነጻነት ታጋይ ድርጅቶች በትጥቅ ትግላቸው ወቅት የፈጸሙት ኢሰብአዊ ድርጊት፣ ወንጀልና ግፍ ተሠውሮ እንዲቀር ሲደረግ ማንዴላ ግን ኤ ኤን ሲ ይቅርታ እንዲጠይቅ አድርገዋል፡፡

ማንዴላ ሰላማዊ መንገድን ብቻ ይመርጥ የነበረ መሪ ነበር፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ምንም እንኳን የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረውን ኤ ኤን ሲ የመራ ቢሆንም ሰላማዊ የትግል መንገድ ከማንኛውም የትግል መንገድ ሁሉ ቅድሚያ እንዲያገኝ ሲታገል የኖረ ሰው ነው፡፡

ይህ ትግሉ ከአፓርታይድ መሪዎች ጋር ብቻ ሳይሆን በኤ ኤን ሲ ውስጥ ከነበሩ ሌሎች አመራሮች ጋርም ጭምር ነበር፡፡ የጠመንጃ ትግል ለሰላማዊ ትግል፣ ለድርድርና ለውይይት የተዘጋውን በር ማስከፈቻ እንጂ ሰላማዊ መንግሥት የመመሥረቻ መንገድ አይደለም ብሎ ያምን ነበር፡፡ በአፓርታይድ የመጨረሻዎቹ ዘመናት እነ ፒተር ቦታ ከኤ ኤን ሲ መሪዎች ጋር ለመደራደር ያቀረቡትን ጥያቄ አንዳንድ የድርጅቱ አመራሮች አልቀበል ሲሉ ‹እኔ ብቻዬንም ቢሆን እደራደራለሁ› እስከ ማለት አቋም ወስዶ ነበር፡፡ ከአፓርታይድ ጋር የሚደረገው ትግል በጠመንጃ አሸናፊነት ሳይሆን በሃሳብ አሸናፊነት መጠናቀቅ አለበት የሚል አቋም ነበረው፡፡

በደቡብ አፍሪካ ሁሉንም ያሳተፈ የመጀመሪያ ምርጫ በተደረገ ጊዜ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ሕገ መንግሥቱን ብቻውን ለማጽደቅ የሚያስችለውን ድምጽ አላገኘም ነበር፡፡ ይሄንን አጋጣሚ ማንዴላ በደስታ ነበር የገለጠው ‹‹ሁሉንም ሕዝብ የሚመራ ሕገ መንግሥት ብቻችንን ማጽደቅ የለብንም፤ ይህ አጋጣሚ መልካም ነው፤ ከሌሎቹ ጋር ተማክረን፣ ተደራድረንና ተስማምተን እንድናጸድቅ ያደርገናል› ብሎ ነበር፡፡

ማንዴላ ሥልጣን መያዝን ብቻ ሳይሆን መልቀቅንም ያስተማረ ሰው ነው፡፡ ማንዴላ ደቡብ አፍሪካን ለአንድ ዙር ብቻ ነው የመራው፡፡ በቀጣዩ ምርጫ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ዘመናት በሚደረጉ ምርጫዎችም የማሸነፍ ዕድል ነበረው፡፡ ነገር ግን በቃኝ አለ፡፡ እየተወደደ፤ እየተመሰገነና እየተከበረ በቃኝ አለ፡፡ በደቡብ አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ብሎም በመላው ዓለም ‹አይከን› የመሆንን ጸጋ ተጎናጸፈ፡፡ የነጻነት፣ የጽናትና የትዕግሥት፣

የሰላምና የዕርቅ፣ የይቅር ባይነትና ከጥላቻ ውጭ የሆነ ፖለቲካ ‹አየከን› ሆነ ማንዴላ፡፡ በመላው ዓለም ሕዝብ ልብ ውስጥ ማንም ሊነቅለው የማይችል ዛፍ፣ ማንም ሊያፈርሰው የማይችል ሐውልት ሆነ ማንዴላ፡፡

ለዚህ ይመስለኛል ማንዴላን ዓለም በሙሉ የሳሳለት፤ ለጤናውም ሆነ ለእድሜው የጸለየለት፤ የተጨነቀለትና ልቡን ከልቡ ጋር ያስተባበረለት፡፡ እንደ እርሱ ዓይነት ሰዎች እንደ ሄሊኮሜት በዘመናት አንድ ጊዜ ብቅ የሚሉ ናቸው፡፡ ተወደው ሥልጣን ላይ የሚቀመጡ፣ ተወደውም ከሥልጣን የሚወርዱ፤ ተወደውም ያለ ሥልጣን የሚኖሩ፡፡ እንደ ማንዴላ ዓይነት ሰው እንኳን ሌላው የአፍሪካ ሀገር ራሱ ኤ ኤን ሲም ዳግም ሊያገኝ አልቻለም፡፡ መከፋፈል ዕጣ ፈንታ የሆነውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡

መሪነትና ባለ ሥልጣንነት ምን ያህል እንደሚለያዩ ማንዴላ

አንድ ማሳያ ናቸው፡፡ ማንዴላ ባለ ሥልጣን አልነበሩም፤ መሪ እንጂ፡፡ ባለ ሥልጣን በሰው ገንዘብ ውስጥ እንጂ በሰው ልብ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ባለ ሥልጣን ይፈራል እንጂ አይከበርም፤ ባለ ሥልጣን ቢሮ አለው እንጂ ሀገር የለውም፤ ባለ ሥልጣን የሚላላኩት ሠራተኞች እንጂ የሚጸልዩለት ወገኖች የሉትም፡፡ ባለ ሥልጣን የሚያዘው ሰው እንጂ የሚያፈቅረው ሰው አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ፊርማውን የሚፈልግ እንጂ እድሜውን የሚፈልግ የለም፤ ባለ ሥልጣን ብዙ ገንዘብ እንጂ ብዙ ልቦች አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ከሥልጣን ወዲህ እንጂ ከሞት ወዲያ ተዝካር የለውም፡፡

ማንዴላ ከሞት በኋላም ይኖራል፡፡ በብዙ ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡ መቃብር እርሱን ሊያስረሳ አይቻለውም፡፡ እርሱ ከመቃብር በላይ የሆነ ተግባር አለውና፡፡ ማንዴላ የአንድ ሀገር መሆኑ ቀርቶ የዓለም ሆኗል፡፡ መሬት ላይ የሚቆም ሐውልት አያስፈልገውም፤ እርሱ በሕዝቦች ልብ ውስጥ የማይፈርስ ሐውልት በሕይወት እያለ ሠርቷልና፡፡ ብዙ ባለ ሥልጣናት በሕይወት እያሉ በሰው ልብ ውስጥ ሐውልት መሥራት ስለማይችሉ፣ ከሞቱ በኋላ የድንጋይ ሐውልት ይሠራላቸዋል፡፡ ነገር ግን ሐውልታቸው መልእክት አልባ ሐውልት ይሆናል፡፡ እንደ ማንዴላ ያሉ መሪዎች በመሬት ላይ ሐውልት ሲተከልላቸው ደረቅ ሐውልት አይሆንም፤ መልእክት ያለው ሐውልት እንጂ፡፡

ማንዴላ አይሞትም፤ ጀግና አይሞትምና፤ የማንዴላ አይረሳም፤ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ሰው አይረሳምና፤ ማንዴላ አያልፍም፣ በጎ ሥራ አያልፍምና፡፡

ዋጋ እናወዳድራለን፤ ሌላ ቦታ ውሰዱ በተባሉበት ዋጋ እንሸጥልዎታለን

617 Cedar Ave S Minneapolis, MN 55454

612-332-7020

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page June 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 52 ሰኔ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 52

ከሰሞኑ ግብይት የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ

24ቱ የሃገር ቤት

ኦርጋኒክ ቢራ በማይታመን

ዋጋ

አክሱሚት እና ጉደር ሁለቱ 15$ ብቻ የሃገር ቤት ጠጦችን ይዘዙን በተመጣጣኝ ዋጋ እናደርሳለን።

ምንዛሪ ግዢ ሽያጭ

የአሜሪካን ዶላር 18.6299 19.0025

ፓውንድ 28.7813 29.3569

ስዊዝ ፍራንክ (100) 2005.5900

2045.7018

የስዊድን ክሮነር(100) 282.9700 288.6294

የኖርዌይ ክሮነር(100) 310.8800 317.0976

የዳኒሽ ክሮነር (100) 329.7900 336.3858

የጅቡቲፍራንክ(1000) 103.5000 105.5700

የህንድ ሩፒ (100) 31.4270 32.0555

የኬንያ ሽልንግ (100) 21.6500 22.0830

የጃፓን የን (100) 19.0704 19.4518

የካናዳ ዶላር 17.9272 18.2857

የአውስትራሊያ ዶላር 17.1917 17.5355

የሳዑዲ ሪያል 4.9674 5.0667

የኤመሬትስ ድርሃም 5.0721 5.1735

ዩሮ 24.5971 25.0890

የደቡብ አፍሪካ ራንድ 1.8211 1.8575

- ቡና - እንጀራ

- ጌሾ - ጧፍ

- የፊት ቅባት - የቤተክርስቲያን

ጃንጥላ - ቁሌት - መሶብ - ጀበና

- የቡና ብረትምጣድ - ረከቦት

- የስልክ ካርዶች - የለስላሳ መጠጦች

- የጸጉር ቅባቶች - ከሃገር ቤት

- የክትፎ ማቅረቢያ ሸክላ

- የሸክላ ድስቶች - የሃበሻ ቀሚስ - የሃበሻ ቁምጣ

- ፌጦ - ቀበሪቾ - ሰፌድ

-የባህል ጌጣጌቶች

- ጤፍ

በሚኒሶታ የባህል ልብሶችንና እቃዎችን ከግሮሰሪዎች ጋር የያዘ

ትልቁ ገበያ

1569 Sherburne Ave. St. Paul, MN 55104

(651) 203-0146

Addis Market አዲስ ማርኬት

የሃገር ባህል ልብሶችን፣ ቅመማቅመሞችን፣ ጤፍ፣ እንጀራ፣ የስልክ ካርድ፣

ኦርጂናል ሲዲዎችን፣ ሁሉን ነገር ሲፈልጉ ወደ ሴንት ፖሉ አዲስ

ማርኬት ብቅ ይበሉ

የፎቶ ግራፍ ምንጭ፡ history.com

ልብስ መስፋት ጀምረናል

የሃበሻ ቀሚሶችን ጨምሮ ማንኛውንም ልብስ እናጠባለን፤ እናሰፋለን፤ የተቀደደ

እንጠግናለን። ባላገሩ የልብስ መስፊያ ቀጠሮ ያከብራል

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

መብት የተሰኘው አምዳችን በአሜሪካን ሃገር እየኖርን ሕግን ሳናውቅ ብዙ ነገሮችን ለምናጣ ወገኖቻችን ትልቅ ትምህርት ሰጪ አምድ ነው። በአምዱ ላይ በአሜሪካ ሕጎች ዙሪያ ጥያቄዎቻችሁን ተቀብለን እዚሁ ከሚገኙ

የሕግ ባለሙያዎች መልስ እናሰጣችኋለን። ጥያቄዎቻችሁን ላኩልን።

ይህ አምድ በአሜሪካ የኢትዮጵያውያንን ኑሮ በትዝብት መልክ አቅርቦ እንደንማማርበት ታስቦ የተከፈተ ነው። ሁሉም የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ አንባቢ በዚህ አምድ ላይ ትዝብቱን ማስፈር ይችላል። ታዲያ ትዝብቱ መስተማርን አንግቦ ቢቀርብ ለኮምዩኒቲያችን ትልቅ ትምህርትን ይሰጣል ብለን እናምናለን። ተሳተፉበት።

ከኢሳያስ ከበደ የወሲብ ስሜት የሞራል ደንቦችን ሲፈታተን ከዘመን ዘልቋል፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን በልቅ የወሲብ ድርጊቶች ምክንያት

ሰዎች ለማህበረሰብ ደንቦች ተገዢ እንዳይሆኑ ጋሬጣ የሚሆኑ አማራጮች በሰፊው የሚዳረስበት ጊዜ ነው፡፡ ልቅ የወሲብ ድርጊት አሁን አሁን ስርጭቱ በዓለም ዙርያ ይናኝ እንጂ ከጥንት አንስቶ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ሰዎች የወሲብ ስሜታቸውን በተለያዩ የጥበብ ስራዎች እንደገለፁ ታሪክም በመዝገቡ አስፍሯል፡፡ ልቅ የወሲብ ድርጊት (ፖርን) ዛሬ ላይ እንደ ኢንዱሰትሪ ከመንሰራፋቱ በፊት የጥንት ዘመን ሰዎች የወሲብ ስሜታቸውን በግብራቸው ሳይሆን በቅርፃ ቅርፅ፣ በስዕል እንዲሁም በስነፅሁፍ ለቀጣይ ትውልድ አስተላልፈዋል፡፡ ለዚህ አይነቱ ድርጊት እማኝ ለመሆን የታሪክ መዘውር ጥንታዊቷ የሮም ግዛት ወደነበረችው ፖምፔይ ይጠቁማል፡፡ ፖምፔይ ከአቅራቢያ ካለው ተራራ በፈነዳ እሳተ ጎመራ መርዛማ አመድ ተውጣ የወደመች ከተማ ናት፡፡ ውድመቱ ካለፈ ከዘመናት በኋላ አርኪዮሎጂስቶች በከተማዋ ፍቅር የሚሰሩ ቅርፃ ቅርፆች እንዲሁም የወሲብ ስሜት ቀስቃሽ ስዕሎች ለማግኘት ችለዋል፡፡ እነዚህ ግኝቶች ለ200 ዓመታት ከሰፊው ህዝብ እይታ ተከልክለው የቆዩ ሲሆን አሁን ላይ በካሊፎርንያ በሚገኝ ሙዝየም ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡

አዳም ሄዋንን ካወቃት ዘፍጥረት አንሰቶ እስከ አሁን ሰው በማህበረሰብ የከለከለውን ልቅ የወሲብ ስሜት በተለያዩ ስራዎች አስፍሯል፡፡ ይህም አካሄድ ካለንበት ጊዜ አንስቴ እስከ ምፅአት ቀን እንደሚቀጥል እርግጠኛ የሚያደርገን ደግሞ ኢንተርኔት ዓለምን የመቆጣጠሩ እውነታ ነው፡፡ የኢንተርኔት ግኝት የፓርን ኢንዱስትሪው ትርፋማ እንዲሆን አስችሎትል፡፡ ከልቅ የወሲብ ድርጊት ሽያጭ የሚገኝ ገቢ እንደ ስፖርት ካሉ መዝናኛዎች ከሚገኝ ገቢ በመጠን ይስተካከላል፡፡ እ.ኤ.አ በግንቦት 2001 ዓ.ም የታተመው የኒውዮርክ ታይም መፅሔት ከልቅ የወሲብ ድርጊት ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ‹‹ ወደር የሌለው›› በማለት ገልፆታል፡፡ ፖርን በዓለም ዙሪያ ወደ 54 ቢሊዮን የሚጠጋ ዓመታዊ ትርፍ እንደሚያስገኝ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማል፡፡ ምንም አይነት ማህበረሰባዊ ቁጥጥርን አሻፈረኝ ካለው ፖርኖግራፊ ጋር የእይታ ትውውቅ የሚደረግበት አማካኝ ዕድሜ 11 ዓመት ነው፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢንተርኔት ባለበት ሁሉ ልቅ የወሲብ ድርጊቶችን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡ ኢንተርኔት ለፖርን

ኢንዲስትሪው አስተዋፅኦ ቢያደርግም የድርጊቱ ውጥን ሀሳብ ጥንትም ቢሆን በሰዎች ልቦና ተቀብሮ ነበር፡፡ በጥንታዊቷ ፖምፔይ የተገኙት የወሲብ አነቃቂ ቅርፃ

ቅርፆች እና ስዕሎች ሁሉንም የማወቅ ጉጉት ያለው የሰው ፍጥረት ልቅ የሆነ የወሲብ ፍላጎት ድሮም ቢሆን አሁን በውስጡ እንዳለ

አመላካቾች ናቸውና፡፡

የልቅ ወሲባዊ ድርጊት ታሪካዊ ጉዞ ከ16ኛው እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በወቅቱ ይከለከል የነበረውን የወሲብ ገደብ በመጋፈጥ ሰዎች የወሲብ ስሜታቸውን

በስነፅሁፍ ይገልፁ ነበር፡፡ ለዚህም ጥንታዊት ሮም እና ፈረንሳይ ግንባር ቀደም ሀገራት ናቸው፡፡ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፖርኖግራፊ

አቀንቃኝ ወደሆነችው አሜሪካም ወሲብን የሚያነቃቁ ድርሰቶች መግባት የጀመሩት እ.ኤ.አ በ1780 ዓ.ም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1789 ዓ.ም የፈረንሳይ አብዮት

ፖለቲካዊ ፖርኖግራፊን ይዞ ብቅ አለ፡፡ አብዮቱ ከመቀስቀሱ በፊት የፈረንሳይ ፖለቲከኞች እና ሹማምንቶች የፖርኖግራፊ ተጠቃሞዎች ስለበሩ በወቅቱ የነበረውን የሉዊ 14ኛ ንጉሳዊ አገዛዝ ለማስወገድ የፈረንሳይ ተቃዋሚዎች ንግስት ማርያ አንቶኔት አፀያፊ ወሲብ ስትፈፅም የሚያሳይ በራሪ ወረቀቶችን ያሰራጩ ነበር፡፡ የፈረንሳይ አብዮተኞች ፖርኖግራፊን የንግሥቲቱን ስም ለማጥፋት ተጠቅመውበት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ ይህንን ተክትሎ በፖርኖግራፊ ታሪክ ትልቅ አስትዋፅኦ ያደረገው ፈረንሳዊ ማርከስ ዴሳዴ የፖርኖግራፊን ገፅታ ከፖለቲካው መድረክ በማውረድ ልቅ ወሲብን ሁሉንም አይነት የሞራል መሰረት መዋጊያ መሳሪያ አደረገው፡፡ ሳዴ በፃፋቸው መፅሐፍቶችም ሰው በተገኘው አጋጣሚ እርካታን በአካሉ መሻት እና ማግኘት እንዳለበት ገልጧል፡፡ የሳዴ እርካታን የመሻት ሂደትም አካላዊ እንግልት እንዲሁም ሰዎችን በማሰቃየት የሚገኝ ደስትን ያካትታል፡፡ ከሳዴ ስምም በመነሳት በ1780 በኋላ የወሲብን እርካታ በአካላዊ እንግልት እንዲሁም በስቃይ ማግኘት የሚፈልገው ሰው ሳዲስት (saddest) በመባል ይጠራ ጀመር፡፡ ሳዴ ይሰብካቸው የነበሩት የወሲብ ሀሳቦች ለዛሬዎቹ የፖርን ፊልሞች ጭብጥ መሰረቶች ናቸው፡፡ ሳደም ፓርኖግራፊን መሰረታዊ የሞራል ደንቦች በገሀድ ለመፃረር የተጠቀመ የመጀመሪያው ሰው ነው፡፡ በማህበረሰብ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተፅዕኖ ከቁጥር በማስገባት ከ18ኛ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የሳዴ ስራዎች ከብዙሀኑ ተሸሽገው ኖረዋል፡፡

የወረቀት መመረትን ተከትሎ ፖርኖግራፊ የህትመት ስራዎች መሰራጨት ጀመረ፡፡ እኤአ በ1970 ዓ.ም ፖርኖግራፊ የዶክመንተሪ ይዘት ባለው ፊልም ተዘጋጅቶ ከሀገረ ዴንማርክ ብቅ አለ፡፡ የአሜሪካውያንን የሞራል ገደብ በመጣስ ‹‹የወሲብ ነፃነት በዴንማርክ›› የሚለው ፊልም በሀገረ አሜሪካ ለእይታ በቃ፡፡ ዴንማርክም ለፖርኖግራፊ እውቅና የሰጠኝ ግንባር ቀደም ሀገር ሆነች፡፡ ቀጥሎ ወጥ ታሪክ ባላቸው የሆሊውድ ፊልሞች ውስጥ ወሲብን ልቅ በሆነ መልኩ ፊልም ውሰጥ ማካተት አስደንጋጭነቱ እየቀነሰ መጣ፡፡ ከ1980 አንስቶ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ ፓርኖግራፊ አስገራሚ እድገትን አስመዘገበ፡፡ እኤአ በ1985 ‹‹የእርቃን›› እና የልቅ ወሲብ ገበያው በዓለም አቀፍ ደረጃ 75 ሚሊየን ዶላር ሲያስገባ እኤአ በ2009 ገቢው ወደ 4.9 ቢሊየን ዶላር አሻቀበ፡፡ ፓርኖግራፊም እንደ ፓሜላ አንደረስን ያሉ አሜሪካዊ እንስቶችን በወሲብ ልቅነታቸው በዓለም ዙርያ ዝነኛና ከበርቴ አደረገ፡፡ በኢንተርኔት ዘመን ከሙዚቃ፣ ከመፃህፍት፣ እንዲሁም ከአገልግሎት ሰጪ ድረገፆች ይልቅ የፖርን ድረገፆች በእጥፍ ይጎበኛሉ፡፡

ባለፉት 500 ዓመታት ማህበረሰብ ለፖርን ያለው አመለካከት መቀየሩ፣ የቴክሎጂ እድገትን ተከትሎ ድርጊቱ መስፋፋቱን እንዲሁም የሞራል መሰረቶች ፖርኖግራፊን ለመቆጣጠር እንደተሳናቸው ታሪክ ያስረዳል፡፡ የወሲብ ልቅነት አስደንጋጨ ዕድገት ታሪክ ምን ቢያወሳ እና የሚያስገባውን አህዛዊ ትርፍ መረጃዎች ቢጠቁሙም፣ ፖርኖግራፊ ልንክደው የማንችል አሉታዊ ገፅታ በማህበረሰብ ላይ ያሳድራል፡፡

የልቅ ወሲባዊ ድርጊት አሉታዊ ገፅታዎች የሀሳብ፣ የድርጊት እንዲሁም የምርጫ ነፃነት የካፒታሊዝም መገለጫዎች ናቸው፡፡ የነፃነት ሀሳብ በወሲብ ስሜት ሲገለፅ ያለ ከልካይ ስሜትን በሚያስተናግደው ፓርኖግራፊ ጣሪያውን ይነካል፡፡ በኢንተርኔት ፖርን ብለው ፍለጋ ቢያደርጉ ከ2ሚሊየን በላይ ድረገፅችን ያገኛሉ፡፡ በሀገራችን እነዚህ ድረገፆች ለሰዎች ተደራሽ እንዳይሆኑ የሚደረግ ቁጥጥር ባለመኖሩ ህፃን፣ ወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ እንዲሁም ጤናማ ማህበረሰብ ከመፍጠር አኳያ የሚያበረክተውን አሉታዊ ተፅእኖ ከቁጥር በማስገባት ፓርኖግራፊን ማውገዝ የእያንዳንዳችን ፋንታ ነው፡፡ ካፒታሊዝም የምርጫ ነፃነትን ይሰጣልና፡፡

ከናዖድ ቤተሥላሴ - ከሀገረማርያም (ሜሪላንድ

www.naodlive.com

ሰሞኑን ዚመርማን የሚባል አንድ ክልስ ነጭ ጎረምሳ፤ ሌላ ጥቁር ጎረምሳን በሽጉጥ ገድለሃል ተብሎ የተመሰረተበት ክስ ተዘረዘለት፡፡ ክሱ የተሰረዘለት፤ ነጩ ጎረምሳ፤ ጥቁሩን ጎረምሳ፤ ስላልገደለው አይደለም፡፡ ነጩ ጥቁሩን በጥቁርነቱ ፈርጆ፤ ሌባ ነው ብሎ ደምድሞ፤ ተከታትሎ ነው የገደለው፡፡ ገዳይም ይሄንን ብዙ አልካደም፡፡ ክሱ የተሰረዘለት፤ ነጩ ጥቁሩን የገደለው ራሱን ለመከላከል ነው በሚል የሕግ አግባብ እንጂ፡፡ ይሄ ፍርድ ታዲያ ጥቁሮችን ያናደደ፤ ነጮችን ደግሞ የልብ ልብ የሰጠ ክስተት በመሆኑ የሰሞኑ የሚዲያ ወሬ ነው፡፡ እና ዛሬ ጠዋት፤ በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ፤ አንድ ነጭ እንዲህ የሚል አስተያየት ሲሰጥ ሰማሁት…..

‹‹እኔ›› አለ ነጩ አስተያየት ሰጪ ‹‹በወጣትነቴ ለጥቁሮች ነጻነት ታግያለሁ፤ ተሰልፌያለሁ፤ የዘረኝነት ፖሊሲዎች እንዲጠፉ ታግያለሁ፤ ወዘተ….አሁን ያ ዘመኔ አልፎ፤ ሽማግሌ እና የወጣት ልጆች አባት ነኝ፡፡ ወጣቶች ዘረኝነትን ይማሩታል እንጂ በተፈጥሮአቸው ውስጥ የለም እንደሚባለው የእኔም ልጆች እንዲሁ ናቸው፡፡ ሁሉም ሰው ጓደኛቸው ሊሆን የሚወዱ እና የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ቢሆንም…ቢሆንም….ልጆቼ ከአንድ ጥቁር ጋር ጓደኝነት ሲመሰርቱ ሳይ ‹‹ተው! አይሆንም!›› ባልላቸውም፤ አንድ ቃል ግን መሰንዘሬ አይቀርም፡፡ ያም ቃል ‹‹ Becareful! ›› የሚል ነው፡፡››

ቀጠለና ወደ ጥያቄያዊ ማብራሪያው ገባ፡፡ ለምን ‹‹ Becareful! ›› እንደሚል ሲገልጽም፤ ‹‹75 ፐርሰንት የጥቁር ልጆች ወይ አባት የላቸውም ወይ ከአባታቸው ጋር አይኖሩም ወይም ሙሉ የቤተሰብ ባህል እና ቅርጽ ባለው ሕይወት እያደጉ አይደለም፡፡ እኒህ ልጆች፤ እንደ እኔ ልጆች በቤተሰብ ሥርዓት እና ባህል ካደጉ ልጆች ጋር የማይጣጣሙበት ብዙ የአስተሳሰብ እና የልማድ ጉዳዮች እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ጥቁሮች ሕጋዊ እኩልነታቸውን ባከብርም፤ የልጆቼ ጓደኞች እንዲሆኑ ለመፍቀድ ግን እቸገራለሁ፡፡ እና… ይሄ ዘረኝነት ነውን?›› አለ

የሬዲዮ አስተናጋጁ፤ ነጭ ነው፤ ሲመልስለትም ‹‹ሁላችንም በየቤታችን የምናሰላስለው የወላጅነት ጥያቄ እንጂ ዘረኝነት ነው ብዬ አልወስደውም›› አለ፡፡ ቀጥሎም ‹‹ ዘረኝነት ተፈጥሮአዊ ስሜት ነው፡፡ ሕገወጥ እና መጥፎ የሚሆነው፤ ምርጫው እና አድልኦው ተቋማዊ እና ሕጋዊ መልክ ሲይዝ ይመስለኛል፡፡›› ብሎ ወሬውን ደመደመው እና ወደ ሌላ ርዕስ ሄደ፡፡

እኔ ግን ቃለ ምልልሱ ልቤ ውስጥ ቀረ….የሰውዬውን የ‹‹Becareful! ›› ሎጂክ ሳስበው ጊዜ፤ እኔም በአቅሜ ዘረኛ ነኝ ማለት ነው ብዬ አሰብኩ፡፡ ወይስ አይደለሁም፤እንጃ!

አንዱ ኑዛዜዬ ለምሳሌ ይሄውላችሁ፡፡ ቤት ለመከራየት ባሰብኩ ቁጥር መጀመርያ የማየው በአቅራቢያ ያለውን ትምህርትቤት ነው፡፡ ስለ ትምህርትቤቱ የማየው፤ የትምህርትቤቱን ደረጃ እና ነጥብ ብቻ አይደለም፤ የተማሪዎቹን የዘር ስብጥርም እንጂ፡፡ እውነቴን ነው፡፡ ነጭ ልጆች የበዙበት ትምህርት ቤት ላግኝ ብልም አላገኝም፤ እንደ እውነቱም ከሆነ ደግሞ፤ ልጆቼን በነጭ ትምህርትቤት አስገብቼ፤ ብቸኛ ጥቁር ሆነው፤ አዕምሮዋቸው በበታችነት ሲጎሳቆል ማየት አልፈልግም፡፡ በተቃራኒውም፤ ልጆቼን ጥቁር የሞላበት ትምህርት ቤት ማስገባት አልመርጥም፡፡ እኔ ባለሁበት ከተማ ያሉ ጥቁሮች፤ ከላይ ነጩ የጠቀሰውን የኑሮ እና የቤሰብ ባሕል የሚያሟሉ ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቶቹም፤ በአሜሪካ ስታንዳርድ፤ ውዳቂ ወይም ባጣ ቆየኝ አይነት ናቸውና፡፡ ስለ ብዙ ምክንያት፤ ጥቁር እና ጥበብ ብዙ ወዳጅነት አያሳዩም፡፡ ለእኔ የሚሆነኝ ትምህርትቤት ብዬ የማምነው ‹‹የተለያዩ ዘሮች ያሉበት (ከቻይና፤ ህንድ፤ ስፓኒሽ፤ አፍሪካ፤ ኢትዮጵያ ወዘተ…) እና ነጣ ያሉ መምህራን የበዙበት ነው፡፡

ፈረንጁን ሰውዬ አልኩ እንጂ፤ እኔም እንደ አቅሜ ታዲያ ቢኬርፉል የምል አባት ነኝ፡፡ የምልበት ምክንያት ግን ለየቅል ነው፡፡ ልጆቼ ከፈረንጅ ልጅ ጋር ሲጫወቱ ሳይ ‹‹ቢኬርፉል›› እላለሁ፡፡ ምክንያቱም፤ ልጆቼ ነጩን ልጅ ያስለቀሱት እንደሆን፤ እናቱ

ፍርድ ቤት ትገትረኛለች፡፡ ፈረንጅ ሳይ የሚታየኝ ‹‹ክስ›› ነው፡፡ ሕግ ስለሚያውቁ፤ መብታቸውን ማስከበር ይቀላቸዋልና፡፡ ልጆቼ ከጥቁር ልጅ ጋር ሲጫወቱ ሳይም ‹‹ቢኬርፉል›› እላለሁ፡፡ ነጩ አባት የሰጋውን አይነት ስጋት እኔም ስላለብኝ፡፡ ልጆቼ ከስፓኒሽ ልጅ ጋር ሲጫወቱ ሳይ ‹‹ቢኬርፉል›› እላለሁ፡፡ በስድብ አፋቸውን እንዳይፈቱ፤ ሁሉን ነገር መብላት

እንዳይለምዱ ብዬ ቢኬርፉል የማልልው ልጆቼ ከሀበሻ ልጅ ጋር ሲጫወቱ ብቻ መሰለኝ፡፡ ዘመድ ከዘመዱ…ዘርም ከዘሩ፡፡ የሬድዬ አስተናጋጁ

እንዳለው፤ የቢኬርፉል ምክር በቤተሰብ ውስጥ መኖሩን ማስቀረት አይቻልም፤ ነገሩ ኢ-ተፈጥሮአዊ የሚሆነው፤ ዘረኝነት ተቋማዊ፤ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ መልክ ይዞ፤ የጅምላ ፍረጃ ሲጀምር መሰለኝ፡፡

ቢኬርፉል!

Pornography

is

moral cancer

ፎቶ ምንጭ፡ ጎግል

ፍሬሽማን ትያትር.. ከገጽ 1 የዞረ

አርቲስት ነፃነት ወርቅነህም እንዲሁ የዚሁ ትያትር አካል ነው።

በሚኒሶታ ለ2 ቀናት ቅዳሜ ኦገስት 10 እና እሁድ ኦገስት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ሚኒያፖሊስ ሪቨርሳይድ አቬንዩ ላይ በሚገኘው ኦግስበርግ ኮሌጅ ከምሽቱ 5:30 ጀምሮ እንደሚታይ የተገልጸው ፍሬሽማን ትያትር በኢትዮጵያ በተለያዩ ቲያትር ቤቶች ውስጥ የታየና በአስቂኝነቱም የተመሰከረለት እንደሆነ ታውቋል። በሚኒሶታ በመድረክ ላይ ራሳቸው ተዋንያኖቹ መጥተው ሲተውኑ ብዙ ጊዜ የማይታይ በመሆኑ ብዙዎች ይህን ትያትር ለማየት እንደጓጉ ከደረሱን አስተያየቶች ለመረዳት ተችሏል።

በተለይ በፊልምና በድራማ ላይ የሚታወቁትን አርቲስቶች በአካል አግኝቶ ሲተውኑ ማየት በሚኒሶታ ውስጥ ያልተለመደ በመሆኑ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ትያትሩን እንደሚያየው ይጠበቃል።

ተዋንያኖቹ ከኢትዮጵያና ከዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም ከካሊፎርኒያ የሚመጡ በመሆናቸው ትያትሩን በሚኒሶታ ለሁለት ቀናት ለማሳየት አዘጋጆቹ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ማውጣታቸውን ገልጸው የመግቢያ ዋጋውም ብዙዎችን በማይጎዳ መልኩ $30 እንደሚሆን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያን በሚኒሶታ የ እረፍት ቀናቸው የተለያየ በመሆኑ አርቲስቶቹን በማስፈቀድ ትያትሩ ቅዳሜም እሁድም የሚታይበትን መንገድ አዘጋጆቹ ያመቻቹ ሲሆን ማህበረሰቡ ቅዳሜ ኦገስት 10 ያልቻለ፤ እሁድ ኦገስት 11 በመገኘት በሳቅ እንዲንበሸበሽ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ፍሬሽማን አስቂኝ የመድረክ ድራማ የሚታይበት አድራሻ፡

Augsburg College፡ 2211 Riverside Avenue South,

Minneapolis, MN 55454 ሲሆን ለበለጠ መረጃ 612-986-0557 ወይም 612-226-8326 መደወል

እንደሚቻል አዘጋጆቹ አስታወቀዋል። አዘጋጆቹ እንዳሉት የመድረክ ሥራው ካለቀ በኋላ

የአርቲስቶቹ አድናቂዎች ፎቶ መነሳትና ፊርማ መቀበል ለሚፈልጉ ሰዓት ይመቻቻል።

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ታዋቂው የኢንሹራንስ ባለሙያ ኤፍሬም በጥሩ ዋጋ ጥሩ የኢንሹራንስ ከለላ ለመኪናዎ፣

ለቤትዎና ከፈለጉም ለጤናዎ ያስገኝልዎታል

651–233-8256

በቦሌ ሃዋላ እና በመኒ ግራም በመጠቀም ወደ ሃገር ቤት ገንዘብዎን

በፍጥነት እናደርሳለን

አርክቴቸር ኤርሚያስ መኮንን ሃገር ቤትም ሆነ አሜሪካ ቤትና ንግድ ቤት ለሚሰሩ የዲዛይን ያወጣልዎታል። በተጨማሪም ለቤት እድሳትና

ቤት ለመግዛት ኤርሚያስ በኢንስፔክሽን አገልግሎት ያግዝዎታል።

763-807-2989

የበግ፣ የበሬና የዶሮ ሥጋ አለን፤ ለቁርጥ የሚሆነውን ጊርጊሮ ሥጋችንንም ይጠይቁን ለሠርግ፣ ለቀለበት፣ ለልደት እና

ለማንኛውም ድግስ በትዕዛዝ በፈለጉት ዲዛይን እናቀርባለን

ለትልቁ ዓላማ... (ከገጽ 3 የዞረ)

ቀላል ሥራ አይደለም፡፡ ዛሬ እሴቶች እና መርሕዎቸ ሲሸራረፉ ዝም ማለታችን በትንሽ ሥልጣን ትንሽ አምባገነንነትን ሊያበረታታ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፡፡ ይህ ትንንሽ አምባገነኖችን የማበረታታት አዝማሚያ ነገ ትልቅ ሥልጣን ላይ ትልቅ አማባገነንነት ላለመፍጠሩ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ የአመራር ብቃትና ባሕርይ ማጣት ችግር በሰፊው የሚታይበት የተቃውሞ ፓለቲካ ከገዥው ፓርቲ ከሚደርስበት ጫና በተጨማሪ የሚጋፉት ችግሮች አንዱ አመራሩ አለመገራቱ እና በገዥው ፓርቲ ስም ለስህተቶችቹ በቀላሉ የማርያም መንገድ ማግኘቱ ነው፡፡ ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የምናልፋቸው ስህተቶች ሌላ አምባገነን መሪዎችን መፍጠር አደጋ ውስጥ ገብተን እንዳይሆን አሁንም ቢሆን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የመንግሥት ተቃውሞውን የማዳከም ተፅዕኖ አሳንሶ ማየት አይደለም፡፡ እንደኽዝብ የምንፈልገውን በግልጽ ማወቅና ለዚያ መሽራትና መኖርንና መለማመድ እንደአንድ የክርክር ሐሳብ ለማቅረብ ብቻ ነው፡፡ ለ”ትልቁ ዓላማ” የሚደረጉ ማመቻመቾችም የት ድረስ መሄድ አለባቸው? የምናጥፋቸውና የማናጥፋቸው መርሕዎች የትኞቹ ናቸው? የትኛው ላይስ ማስተካከያ መውሰድ ይገባናል?

የሚለውን ለመለየትና ከአሁኑ እርምጃ መውሰድ ካልቻልን “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” የሚለው የአበው ምሳሌ እንዳይደርስብን ከመጨነቅ የመነጨ ነው፡፡ የሐሳብ ልዩነታቸውን ተከትሎ ብቻ “ትልቁ ዓላማ” አልተከተላችሁም በሚል ሰበብ ያጣናቸውና የምናጣቸውን ሰዎችም እያሰብኩ እንደጻፍኩት ይታሰብልኝ፡፡

በትዳሬ... ከገጽ 8 የዞረ

እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ የፍቅርና የትዳር አጋሩ ታማኝነት አፍቃሪ እንድትሆንለት ይፈልጋል፡፡ ሴቷም ይህንኑ ትፈልጋለች፡፡ ጤናማ እሱነት እንዲኖረው፣ ወጣትነትን የተላበሰ ውበት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ በገንዘብ ህይወቱ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝና ስኬታማ ቢዝነስ እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ሰላማዊና ደስተኛ የሆነ አኗኗር እንዲኖረውም ፍላጎቱ ነው፡፡ በመሆኑም በኳንተም ፊዚክስ ህግ እነዚህ መልካም የሆኑ ውጤቶችን ግለሰቡ ይመለከትና በተግባርም ለእንዲህ መሰል ህይወቶች የታደለ ይሆን ዘንድ ከልቡ መመልከት ይሆናል ብሎ በማመን ውስጥ መታዘብ ያለበት (observation) ይህንኑ ውጤት ሊሆን ይገባል፡፡

የምንፈልገው የትኛውም አይነት ውጤት በገሃድ ይከሰት ዘንድ ከልባችን በሚገባ ልንመለከትና ልንታዘብ የሚገባው ይህንኑ ውጤት መሆን መቻል አለበት፡፡ ስሜታዊ ምልከታችን

በዚሁ ላይ የተነጣጠረ መሆን መቻል አለበት፡፡ ውስጣዊ እምነታችንም ይህንኑ የሚያንፀባርቅ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ሁል ጊዜም ቢሆን ለመመልከት መጣር ያለብን የምንፈልገውን ነገር ነው ሊሆን የሚገባው፡፡ ከሰዎች የምንፈልገውን አይነት ባህሪ ልናገኝ እንደምንችል በውስጣዊ እምነታችን ውስጥ ማስረፅና ይህንንም በሚገባ ለመመልከት መሞከር ይጠበቅብናል፡፡ በህይወታችን ውስጥ የገንዘብ ብልፅግናና ሙላት እንደሁም ስኬታማ የቢዝነስ ህወይት ሊኖረን እንደሚችል ከውስጣችን በሙሉ እምነትና ስሜት ውስጥ ደጋግመን ለማየት መጣር ይኖርብናል፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ውስጣዊ ሰውነታችን ጤናማና በጤናማ የአሰራር መንፈስ ውስጥ የሚሰራ አድርገን ማድመጥና ማመን ይኖርብናል፡፡ ሌሎች በህይወታችን እንዲሆኑልን የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ በዚህ መልክ የማየት ብቃትን ልናዳብር ይገባናል፡፡

እናም ስለራሳችንም ሆነ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንዲሁም ስለሰዎችም በአጠቃላይ መልካም ነገሮችን ባሰብንና ክስተታቸውንም ከልባችን በተመኘን ቁጥር የበለጠ በገሃድ ተከስተው የማየት እድላችን የላቀ መሆን ይጀምራል፡፡ እንደሚታወቀው የትኛውም አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ አስተሳሰባችን የአመለካከት አቅጣጫችንን ይወስናል፡፡ ይህም በተራው ደግሞ የንግግርም ሆነ የድርጊት ቋንቋችንን ይወስናል፡፡ ይህም የንግግርና የድርጊት ቋንቋ በተራው

ውጤታችንን ይወስናል፡፡ ድርጊታችንና ውጤታችንም በተደጋጋመ ቁጥር የኑሮ ዘይቤያችንና ዕጣ ፈንታችን ሆኖት ያርፋል፡፡

በመሆኑም በህይወታችን ተከስቶ ማየት በምንፈልገው ጉዳይ ላይ ደጋግመን ባሰብን፣ ባመንን፣ በቋንቋም በገለፅነውም ሆነ በድርጊት ክዋኔ ውስጥ ባረጋገጥነው ቁጥር የምንፈልገው ነገር በትክክልም ተከስቶ የማየት እድላችን በእጅጉ የላቀ መሆን ይጀምራል፡፡ በመሆኑም የኳንተም ዓለሙን በእኛ ተፅዕኖ ውስጥ ባረጋገጥነው ቁጥር የምንፈልገው ነገር በትክክልም ተከስቶ የማየት እድላችን በእጅጉ የላቀ መሆን ይጀምራል፡፡ በመሆኑም የኳንተም ዓለሙን በእኛ ተፅዕኖ ውስጥ ለመክተት ምን ጊዜም ቢሆን የመጀመሪያው ህግ የምንፈልገውን ገንቢ ውጤት ማወቅ፣ በምንፈልገው ዙሪያ ማሰብ፣ ከልባችን ተሳክቶ ማየት እንደምንችል ማመን፣ ውስጣዊ ስሜታችን በምንፈልገው ነገር ዙሪያ የተቃኘና የተጣጣመ ማድረግ የሚጠበቅብን ሲሆን የምንፈልገው ነገር እንደሚሳካም ይጠበቅብናል፡፡ ይህ መሰል የሀሳብ፣ የእምነት፣ የስሜት፣ የቋንቋና የድርጊት ትኩረታዊ ሂደት ኳንተማዊውን ክስተት በእጅጉ የሚያፋጥነው ኃይል ጥበብ ነው፡፡ ውድ ጠያቂያችን ከረጅሙ በአጭሩ አጠቃላይ የምላሹ መንፈስ ይህን ይመስላንና ራስህን በዚህ መልክ አስተካክል፡፡

Zehabesha.com

ፒያሣ ገበያ ውስጥ ፒያሣ ትራቭል ኤጀንሲ ሥራውን ጀምሯል

ወደየትኛውም ሃገርና ከተማዎች ለመብረር ሲፈልጉ የዓየር ትኬት

በተመጣጣኝ ዋጋ እናገኝልዎታለን::

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ጉንፋን... ከገጽ 8 የዞረ

መጠን መራቅ፣ እጅ አለመጨበጥ፣ ምክንያቱም ጉንፋን የተያዙ ሰዎችን መጨበጥ በጉንፋን የመያዝ ዕድልን በ70 በመቶ ስለሚጨምር ነው፡፡ ነገር ግን ጉንፋን የተያዘን ሰው ከጨበጡ ወይንም የነካውን ዕቃ

ከያዙ በቶሎ ከ15 ሰከንድ ባላነሰ ጊዜ ውስጥ እጅዎን በውሃና በሳሙና መታጠብ ይኖርበታል፡፡ በህዝብ አገልግሎት መስጫዎች ወይንም ጉንፋን የያዘው ሰው ባለበት አካባቢ ለዕጅ ማድረቂያ ከፎጣ ይልቅ ሶፍት መጠቀም ጥሩ ነው፡፡ ጉንፋን የያዘው ሰው የተጠቀመበትን ብርጭቆ ወይንም የመመገቢያ

ማንኪያና ሹካ አለመጠቀምና ጤነኛ አመጋገብና የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ የሰውነትን ህመም መከላከያ አቅም መገንባት ትልቅ የመከላከያ ዘዴ ነው፡፡ በተጨማሪም እርስዎ ጉንፋን በሚይዝዎት ጊዜ በተቻለ መጠን ቤት መቀመጥና ወደ ሰው ላለማስተላለፍ

መጠንቀቅ፣ የሚጠቀሙበትን ሶፍት ቶሎ ቶሎ (ወዲያው ወዲያው) ማስወገድና በተገቢው ቦታ መጣል፣ እንዲሁም በመሀረብ ከመጠቀም ይልቅ በተቀያሪ ሶፍት መጠቀም፡፡ በሚስሉበት ወይንም በሚያስነጥሱበት ወቅት እጅዎን በአፍዎና

በአፍንጫዎ ላይ መሸፈንና እጅን ተጠንቅቆ መታጠብ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በፊት ጉንፋን ቢይዝዎትስ? ጉንፋን በእርግጥ መድሃኒት የሌለውና በሂደትም በራሱ የሚጠፋ

ወይም የሚድን ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው በጉንፋን ከተያዘ በኋላ ስሜቶቹን ለማቅለል የህመሙን የቆይታ ጊዜ ለማሳጠርና እንግልቱን ለመቀነስ የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይችላል፡፡ - ውሃና ሌሎች ፈሳሾችን በብዛት መውሰድ ከሰውነታችን በአፍንጫ

ፈሳሽና በላብ መልክ የሚወጣውን ፈሳሽ በመተካት የሰውነታችንን የውሃ ድርቀት ከመከላከሉም በላይ፣ ለአፍንጫችን መደፈንና ለሚከተለው የራስ ህመም ምክንያት የሆነውን ወፍራም ፈሳሽ

በማቅጠን ስሜቶቹን ይገታል፡፡ ጉሮሮን ለብ ባለ ውሃና ጨው በመጉመጥመጥ የጉሮሮ መከርከርንና ተጓዳኝ ስሜቶች መቀነስ፣ ውሃ አፍልተን እንፋሎቱን በመታጠን የመተንፈሻ አካላችን እንዳይደርቅ መከላከል፡፡ ውሃ መታጠን ወይም እንደ ‹‹ስቲም ባዝ›› መጠቀምም በድርቀት ሳቢያ ለሚመጡ ስሜቶች መፍትሄ ከመሆንም አልፎ ለቫይረሱ መራቢያ ምቹ የሆነውን የደረቅ አየር ሁኔታ ይቀይራል፡፡ ሰውነታችንን በማሳረፍ የሰውነታችንን የመከላከያ ብቃት

መገንባትና ማር በመብላት ለሰውነታችን ኃይል መስጠት፣ እንደ ብርቱካንና ሎሚ የመሳሰሉትን የቫይታሚን ሲ ምንጮችን በመውሰድ ሰውነታችን ትግሉን እንዲያበረታ ማገዝ፣ ከዶሮ የተሰራ ሾርባ መጠጣት የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል ብቃት ሊያጎለብት በተጨማሪም ትኩስ፣ ኃይል ሰጪና፣ ፈሳሽ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት ያከናውናል፡፡ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን በአማራጭነት መጠቀምዎም እንደ ራስ ምታትና መሰል የሰውነት ህመሞችን ይገታሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን ስሜቱ የበረታ እንደሆነና ጊዜው የረዘመ

ከሆነ፣ የትንፋሽ ማጠርና የደረት ውጋት ከጀመረ፣ የአክታ መብዛት፣ ሀይለኛ ትኩሳት፣ ማስመለስ፣ እንዲሁም የጉሮሮ ህመም በርትቶ አላስውጥ ያለ እንደሆነ ወደ ሐኪምዎ በመሄድ መፍትሄ ማግኘት እንደልብዎ አይዘንጉ፡፡ ውድ አንባብያን ዓለም ላይ የተጠቀሱትን መፍትሄ ያልናቸውን

መንገዶች በመጠቀም ችግር ለመቅረፍ መሞከር መልካም ነው፡፡ እናም በሂደት ያለውን ለውጥ ማየት ነው፡፡ ሁኔታው በዛው ከቀጠለ ግን ሌላም ተያያዥ ችግር ሊኖር ስለሚችል ወደ ሐኪም መሄድ ያዋጣል ነው የእኛ ምክር፡፡ ሰላምና ጤና ለሁላችን ይሁን፡፡

ማሳጅ... ከገጽ 13 የዞረ

እርግዝና ያጋልጣል፡፡ በሌላም በኩል ኤሮቲክ ማሳጅ በተደጋጋሚ ከተደረገ ሱስ የሚያስይዝ ባህሪ ያለው ነው፡፡ ይህም ማለት ወንድም ሆነ ሴት ከትዳር (ከፍቅር) ተጣማሪ ጋር ወሲብን ከመፈፀም ይልቅ ሁሉንም ነገር ኤሮቲክ ማሳጅ

በሚሰጥባቸው ቦታዎች በመጨረስ ግንኙነታቸው ወደ ችግር እንዲያመራ ያደርጋል፡፡

በማሳጅ ቤቶች የሚሰጠው ኤሮቲክ ማሳጅ ተፈጥሮአዊ ሂደቱን በጣሰ መልኩ የሚፈፀም በመሆኑ ውስጣዊ ኦርጋኖችን ያዳክማል፡፡ በሂደትም የግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካላት ስሜት አልባ እንዲሆኑም ያደርጋቸዋል፡፡ ስለሆነም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ኤሮቲክ ማሳጅ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ወሲብ ሳይፈፀም የመርካት ሂደት ያለው በመሆኑ ፍቅርን ሰጥቶ ፍቅርን የመቀበል ጉዳይን ወደ ጐን በመግፋት የአካል እና የአዕምሮአዊ ጤና መቃወስን ወደሚያስከትል ችግር ሊያስገባ ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ ከስነ ምግባር ያፈነገጡ ለምሳሌ፡- የአፍ ውስጥ ወሲብ፣ ሌዝቢያንነትና ሌሎች ጤናማ ያልሆኑ የወሲብ ድርጊቶች እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡

ማህበረሰባዊ ባህልን ከማናጋት አንፃር የሚያስከትለው ጉዳትም በቀላሉ የሚታይ አይሆንም፡፡ በመሆኑም የኤሮቲክስ ማሳጅን ጥቅምና ጉዳቱን አመዛዝኖ በተገባው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል በማለት እንወዳለን፡፡

የሚኒሶታ... ከገጽ 1 የዞረ

ዲፓርትመንቱ በማሳሰቢያው ላይ እንዳለው “ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው መኪና መንዳት የሚያስተምሩ ሰዎች፡-

1ኛ. ጥራት ያለው የመንዳት ትምህርት ለመስጠት ባግባቡ የሰለጠኑ እና ልምድ ያላቸው አይደሉም፤ በመሆኑም ተማሪውን ለአደጋ ያጋልጣሉ፤

2ኛ. ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው አስተማሪዎች ያላቸውን ዓይነት የተለማማጁንም ሆነ አስተማሪውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል "Veh ic le sa fety Equipment"

አልተገጠመላቸውም። በመሆኑም ስህተት ቢፈጠር፣ መኪናውን ለማስቆምም ሆነ ለመቆጣጠር የሚያስችል ሁኔታ የለም።

3ኛ በሰውነት ላይ የሞትም ሆነ የመቁሰል አደጋ ቢፈጠር የኢንሹራንስ "ዋስትና" ተጠያቂነቱ መጠን በጣም ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።” ብሏል። ማሳሰቢያው ጨምሮም ማንኛውም የመኪና መንዳት ለመማር የሚፈልግ ሰው መኪና ለመንዳት ከመጀመሩ በፊት፣ አስተማሪዎ ፍቃድ ያለው መሆኑን መጠየቅ እንዳለበት አሳስቧል።

“ካሁን በኋላ የDMV መኪና መንዳት ፈታኞች፤ አዘውትረው ተፈታኞችን ወደ ፈተና ቦታ ይዘው የሚመጡ ሰዎችን ፈቃድ ይጠይቃሉ።” ያለው የዲፓርትመንቱ ማሳሰቢያ “የነዚህም ሰዎች ስም ዝርዝር ወደ (Department of Reve-nue) ይተላለፋል። ስለዚህ መኪና ለመንዳት ከመስማማትዎ በፊት፣ አስተማሪዎ ፍቃድ ያለው መሆኑን ማወቅ በጣም ይጠቅማል።” በማለት የተማሪውን ግዴታ አስቀምጧል።

“ መኪና አስተምራለው ብሎ የቀረበዎት ሰው ካለ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው የሚያስተምር ሰው መሆኑን ከተጠራጠሩ፣ ለሚኒሶታ Department of Public Services, Driver and Vehicle Services ስልክ ቁጥር 651-284-1234 ደውለው፣ የግለሰቡን ሰም፣ የመኪናውን ዓይነት እና ቀለም፣ ሰሌዳ ቁጥር እንዲያሳውቀም” ዲፓርትመንቱ ማህበረሰቡን ጠይቋል።

በህገወጥ መንገድ ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚያስተምሩ ወገኖችም፤ የሚገባውን የአስተማሪነት ትምህርት ወስደው ፈቃድ እንዲያወጡ ዲፓርትመንቱ መክሯል።

የሚኒሶታ ዲፓርትመንት ኦፍ ፐብሊክ ሴፍቲ በ እንግሊዘኛ ቋንቋ ለማህበረሰቡ እንዲደርስ ለዘ-ሐበሻ የላከው ደብዳቤ በገጽ 6 ላይ ቀርቧል። ይመልከቱት።

(ፍሬሽማን ትያትር በሚኒሶታ ኦገስት 10 እና 11 ይታያል)

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Phone:- 651-641-0931 2147 university avenue west suite 117 . St. Paul, MN 55114

www.gobena-law.com

Law Practice with Passion!

GOBENA & ASSOCIATES Attorney At Law

“let our family fight for your family”

የኮዲ ቤተሰብ ጠበቃዎች ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር አብረው በመሥራትና ጥብቅና በመቆም የረዥም ልምድ አላቸው!!

የኮዲ ሕግ ጠበቃዎች ቡድን በሥራ ቦታ አደጋ፣ በመኪና አደጋ፣ በራስ ላይ

በሚደርስ ማንኛውም አደጋ የሰዎችን መብት በማስከበር ማግኘት የሚገባቸውን

ጥቅም በማስገኘት የታወቀ ነው። እርስዎም ምርጫችሁ እኛ እንሁን።

Phone: 651.294.0994 Fax: 651.292.4955 Email: [email protected]

Our Location: 359 Commerce Court Vadnais Heights, MN 55127 www.codylawgroup.com

በልጅ... ከገጽ 8 የዞረ

ድሮ እሱ ወይም እሷ ያደጉበት ሂደት ትክክል ስለሚመስላቸው በዚያም መንፈስ ልጄ ካላደገ ሞቼ እገኛለሁ የሚሉ ናቸው፡፡ በአንተና በእሷም መካከል ያለው ውዝግብ ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ ምናልባት እሷ ወይም አንተ ትክክል ናችሁ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ሁለታችሁም ትክክል ላትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህ ትክክለኛ የወላጅ ባህሪና የአስተዳደግ አቅጣጫ ምን መምሰል አለበት ስንል የሚከተሉትን 25 የስኬታማ ወላጆች ባህሪያት እናገኛለን፡፡

25ቱ የብቁ ወላጅ ባሀሪያት (የብቁ እናትና አባት ባህሪያት) 1. ለልጁ የሚመክረውን በተግባር የሚያደርግና የሚያሳይ 2. ከየትኛውም አይነት ሱስ ነፃ መሆን የቻለ 3. ውበቱንና አለባበሱን የሚጠብቅና ፅዱ 4. ቃል የሚገባውን በትክክል የሚተረጉም 5. እውነትን የሚናገርና የሚታመን 6. ደስተኛ፣ ፈገግተኛና ማራኪ መንፈስን የተላበሰ 7. ከልጆቹ ጋር በግልፅ የሚነጋገርና ልጁን የሚያዳምጥ 8. የልጁን ባህሪያት የሚከታተልና ጥሩ ባህሪያትን

ሲመለከት የሚሸልም፣ ጥሩ ያልሆኑ ባህሪያትን እንዲያርም ሽልማትን የሚነሳ

9. የትምህርት ብቃቱን የተሰጠውን የቤት ስራ መስራቱን የሚከታተል

10. አባት ከልጁ እናት ጋር በመሆን እናትም ከልጁ አባት ጋር በመሆን ስለልጁ አዎንታዊና አሉታዊ ነገሮች መገምገም ይኖርባቸዋል፡፡

11. ከትምህርት ቤት መምሀራን ጋር በመሆን ስለልጁ አሉታዊና አዎንታዊ ነገሮች የሚገምግም

12. ልጁ ሲያጠፋ የሚመክርና የሚያበረታታ፣ ከጥፋቱም እንዲማር የሚያደርግ

13. ፍቅርና እንክብካቤን ለልጁ የሚሰጥ፣ ለእናቱም ሆነ ለራሱ ይህንኑ በተግባር የሚያሳይ

14. ለልጁ ሙሉ ኃላፊነትን የሚወስድና ከማንም ሳይጠብቅ ለልጁ መልካሙን ሁሉ ማድረግ የሚችል

15. ልጁን ከተለያዩ አደጋ አምጭ ነገሮች የሚጠብቅና የሚንከባከብ

16. ልጁን የተለያዩ ችሎታዎች እንዲኖሩት የሚያስተምር፣ የሚያሳይና የሚያበረታታ

17. የልጁን እናት የሚያከብር፣ የሚንከባከብና የሚያፈቅር 18. ራዕይ ያለውና ራዕዩን መኖር የሚችል 19. ጤናማ አኗኗርን፣ አመጋገብን፣ አስተሳሰብን፣ የአካል

ብቃት እንቅስቃሴንና ጥንቃቄን የሚተገብር፣ ይህንኑም ለልጁ የሚያሳይ

20. የገንዘብ ቁጠባ ባህሪን የሚተገብር፣ ሀብት ፈጣሪ

መሆን የሚችልና ይህንንም የገንዘብ ልዕልና በፅንሰ ሀሳብም ሆነ በተግባር ማሳየት የሚችል፡፡

21. በፈጣሪ የሚያምን፣ ፈጣሪን በፍቅር የሚያመልክና የሚያመሰግን፣ የፈጣሪን ፍጡራን በመላ ያለልዩነት የሚያፈቅር፣ የሚያመሰግንና የሚያከብር (ራሱንም ጭምር)

22. በልጁ አዕምሮ ውስጥ አዎንታዊ ስሜት፣ በራስ የመተማመን ስሜት፣ የመታመን ስሜት፣ የራዕይ እምነትና፣ የማመን ስሜትና የገንዘብ ሀብት ስሜት በአዕምሮው ውስጥ የሚገነባ (Positive emotional bank accounts)

23. ለልጆቹ ጊዜ የሚሰጥ፣ ልጆቹን የሚያዝናና፣ ማታ ወደ ቤት በጊዜ በመግባት ልጆቹን የሚጎበኝ

24. ሲሳሳት ወይም ሲያጠፋ ልጆቹን ይቅርታ የሚጠይቅ 25. ችግሮችን በብቃት የሚፈታና የችግሮችን አፈታት

ብቃትም ለልጆቹ በተግባር ማሳየት የሚችል መሆን አለበት፡፡ ውድ ጠያቂያችን፡- በመሆኑም ሁለታችሁም ከላይ ያሉትን

ዝርዝር የስኬታማ ወላጅ ባህሪያት በጋራ ማንፀባረቅ ይጠ በቅባችኋል፡፡ እናንተ እነዚህን ባህሪያት ከተላበሳችሁ ልጆቻችሁ የእናንተን ባህሪ ነው የሚሆኑትና የሚቀስሙት፡፡ ስለ ልጅ አስተዳደግ ራሳችንን ስንጠይቅ በቅድሚያ እኛ ትክክለኛ የወላጅ ባህሪያት አሉን ወይ? የሚለው ሊያስጨንቀን ይገባል፡፡ እነዚህን ባህሪያት ለመላበስም ራሳችሁ ደጋግማችሁ ተለማመዷቸውና ሆናችሁ ተገኙ፡፡ መልካም ትዳርና ስኬታማ የልጆች አስተዳደግ እየተመኘን ምላሻችንን እዚህ ጋር እናብቃ፡፡

ማሳጅ... ከገጽ 14 የዞረ

ስርዓታቸው የተነቃቃና ካላስፈላጊ ውጥረቶች የተላቀቁ እንዲሆኑ፣ ሚዛንን የጠበቀ ስሜትና ዘና ያለ መንፈስ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ኤሮቲክ ማሳጅ የወሲብ አካላትን ያነቃቃል እንጅ ከተቃራኒ ፆታ ጋር የሚደረግን የግብረሥጋ ግንኙነት ይተካል ማለት አይደለም፡፡

ኤሮቲክ ማሳጅ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች ይህ አይነቱ ማሳጅ በቤት ውስጥ ጥንዶች የሚፈፅሙት

(የሚተገብሩት) ቢሆንም ዛሬ ግን በሐገራችን እየሆነ ያለው በተቃራኒው ነው፡፡ እንደ አንድ የቢዝነስ ሴክተር በአደባባይ የሚፈፀምና የገንዘብ ማግኛ ወደመሆን ተሸጋግሯል፡፡ የሚገርመው ደግሞ የኤሮቲክ ማሳጅ የሚሰጡ ሰዎች ስለ ሰዎች ተፈጥሮአዊ አካላትም ሆነ ስለማሳጅ ጥበብ የተማሩና እውቀቱ ያላቸው አይደሉም፡፡ በመሆኑም የኤሮቲክ ማሳጅ ገንዘብ ማግኘትን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ በመሆኑም ሴቶችም ሆነ ወንዶች በተለያዩ ጤና ነክ ችግሮች የሚጋለጡበት ሁኔታ ሰፊ ነው፡፡ ውስጣዊና ውጫዊ የመራቢያ አካሎች ጤና በከፍተኛ ሁኔታ ይጐዳል፡፡ ማሳጅ የሚደረገውም ሞያዊ ስነ ምግባር ከሚጠይቀው ውጪ በፓንትና ርቃን ተጋልጦ በመሆኑ ጥንቃቄ ለጐደለው ወሲባዊ ድርጊት የመጋለጥ እድልም ሰፊ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ ኤች.አይ.ቪን ጨምሮ በተለያዩ አባላዘር በሽታዎችና ለአልተፈለገ (ማሳጅ... ወደ ገጽ 12 የዞረ)

Hours: 6:00am - 10:00pm Monday-Sunday Play Ground Nutritious Breakfast, Lunches, for kids Languages Spoken: English, Amharic, Oromo,

Somali & Arabic Excellence in Education &

Child Development

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

በተለያዩ ዲዛይኖች ፋሽን የሆኑ ሹሩባዎችን

ኪስን በማይጎዳ

ሂሳብ እንሰራለን

ውድ አልጋ... ከገጽ 8 የዞረ

ሌላ የጊዜ ክልል በአይሮፕላን መጓዝ (Jet lap) ምሳሌ ይሆናሉ፡፡ ይህ አይነቱ የእንቅልፍ ማጣት ችግር ጊዜዊ በመሆኑ ሰውነት ራሱን እስኪያላምድ መታገስ ይገባል፡፡ አጣዳፊ ስራ ካለና የግድ መተኛቱ አስፈላጊ ከሆነ ብቻ የእንቅልፍ ኪኒን መውሰድ ይቻላል፡፡

2. አጭር ጊዜ እንቅልፍ ማጣት (Short term insomnia) ከጥቂት ቀናት እስከ ሶስት ሳምንት የሚቆይ የእንቅልፍ

ማጣት ነው፡፡ ከመጀመሪያው የእንቅልፍ ማጣት ይበልጥ አብሮ የሚቆይ መሆኑ ውስጣዊ ምክንያቱ ከመጀመሪያው የበለጠ ጫና መኖር መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ለአጭር ጊዜ በስራ ቦታ ላይ የሚኖሩ ውጥረቶች፣ መታመም ወይም ከህመም ማገገም ወዘተ... ለሳምንታት ሊዘልቅ የሚችል እንቅልፍ ማጣት ሊፈጠር ይችላል፡፡ እንዲህ አይነቱ የእንቅልፍ ማጣት በእንቅልፍ ኪኒን ቢረዳ ጥሩ ለውጥ ያመጣል፡፡ ዳያዜፓም የሚባለውን ኪኒን አምስት ሚሊ ግራም ወደ አልጋ ከመሄድ በፊት ለቀናት ወይም ለሳምንት ያህል መውሰድ የእንቅልፍ ማጣቱን ችግር ሊያስወግደው ይችላል፡፡ ሎሪዜጋም (500 ማ.ግ) እንዲሁ አማራጭ መድሃኒት ነው፡፡

3. የከረመ እንቅልፍ ማጣት (Chronic Insomnia) ለወራት እና ለዓመታት የሚቆይ የእንቅልፍ ማጣት ነው፡፡

በዚህ አይነቱ እንቅልፍ ማጣት ከሚጨነቁት ውስጥ የተወሰኑት ሰዎች ምክንያት እንቅልፍ የመተኛት ጉጉት ነው፡፡ እንቅልፍ

አይወስደኝም የሚል ጭንቀት አእምሮን ሲቃወም እንቅልፍ አልመጣም እንዲል ሊያደርገው ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ውጫዊ ምክንያቶች አዕምሮን ለረጅም ጊዜ ለአዕምሮ እንቅልፍ ሊነሱ ይችላሉና የሚወዱትን ፍቅረኛ ማጣት፣ ቤተሰብ ወዳጅ በሞት መለየት፣ በከፋ ህመም መሰቃየት ወዘተ... መጥቀስ ይቻላል፡፡ አልኮል መጠጥ አዘውታሪነትና እኔ ደናርኮሌፕሲ (Narcolepsy) ያለ የእንቅልፍ ሕመም ምክንያት ሊሆኑም ይችላሉ፡፡

ለዚህ አይነቱ የእንቅልፍ ማጣት የእንቅልፍ ኪኒን መፍትሄ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ችግሩ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በመሆኑና የእንቅልፍ ኪኒኖችን ከሳምንታት ጊዜ በላይ አከታትሎ መውሰድ ስለማይችል ነው፡፡ ይልቁኑም የእንቅልፍ ማጣቱን ውስጣዊ ምክንያት ድብርት፣ የእንቅልፍ ባህሪ ማዳበር ይመከራል፡፡ ጤናማ የእንቅልፍ ባህሪ (sleep hygiene) ውጤቱ በአንድ ሌሊት የማይታይ ቢሆንም ቀስ በቀስ እየጎላ የሚመጣ ውጤታማ መንገድ ነው፡፡

ውድ ጠያቂያችን በአጠቃላይ ስለ እንቅልፍ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዳገኘህ ይሰማናል፡፡ በተረፈ ግን የእንቅልፍ እጦትን ለማቆምና በቂ እረፍት ለማግኘት የሚከተሉትን ምክሮች ተግባራዊ አድርጋቸው፡፡

1. በየምሽቱ ለእንቅልፍ ወደ አልጋ የሚሄድበትን ሰዓት መወሰን እና ተመሳሳይ የእንቅልፍ ሰዓት መልመድ

2. የመኝታ ቤትን ፀጥ ያለ እንዲሁም ብርሐን ያልበዛበት ማድረግ

3. አልጋ ላይ ወጥተው እንቅልፍ ካልመጣ ለመተኛት ከመታገል ይልቅ ተነስቶ እንደ መፅሔት፣ ጋዜጣ፣ መፅሐፍትን ማንበብ ወይም ሙዚቃ ማዳመጥ

4. በእንቅልፍ ሰዓት እንደ ቡና፣ ሻይ እና ኮካ ያሉ አነቃቂ መጠጦችን አለመውሰድ

5. ከመኝታ በፊት በሙቅ ውሃ ሻወር መውሰድ ጥሩ እንቅልፍ እንድትተኛ ይረዳሉ፡፡

6. ለውጥረት የሚዳርጉ ችግሮችን አንድ በአንድ የመፍታት አቅም ይኑርህ፡፡

7. ስራ የመደራረብ ሳይሆን ስራን የማቅለልና የመወከል ልማድ ይኑርህ፤ ሁሉንም ስራ አንተ ብቻ መስራት አይጠበቅህም፡፡

8. በእዝነ ህሊናህ ውስጥ ጥሩ እንቅልፍ እንደሚኖርህ አስብ ወይም ተመልከት፡፡

የተሰጠህ ምላሽ በቂ ነው ብለን እናምናለን፤ መልካም እንቅልፍ እንመኝልሃለን፤ ሰላም!

ማሳጅ... ከገጽ 16 የዞረ

- የአንገት አከርካሪ ህመም - በዲስክ መንሸራተት ምክንያት የሚከሰቱ የወገብ

ህመሞችን - ከመቀመጫ እስከ ውስጥ እግር ድረስ የተዘረጋው

ነርቭ ጤናው ከታወከ በማሳጅ ማስተካከል ይቻላል፡፡ ከውስጥ ህመሞች አንፃር - ኃይለኛ የጨጓራ ህመምን፤ - የጨጓራና የአንጀት

ቁስል፤ - የአልሰር በሸታን ፤ - የሆድ ድርቀትን፤ - የጉበት ህመምን፤ - ከፍተኛ የደም ግፊትን፤ - የልብ ህመምን ፤ - የአንጀት ህመምን፤ - በጨጓራና በአንጀት አካባቢ የሚፈጠሩ የነርቭ ህመሞችን፤ - የስንፈተ ወሲብ ችግሮችን፤ - የፊት ከፊል ሽባነት፤ - በጎድኖች አካባቢ የሚከሰቱ ነርቭ ህመሞችን፤ -

ከወገብ በታች ሽባነት ሲከሰት፤ - ኃይለኛ ራስ ምታት ከተፈጠረ፤ - የእንቅልፍ እጦት፤ - የመገጣጠሚያ ህመሞች ችግር፤ - የሐሞት ከረጢት ህመም እና፤ - በማህፀን አካባቢ ህመሞች ከአሉ አኩፓይንት ማሳጅ ከፍ ያሉ ጤና ነክ ጥቅሞችን ያስገኛል፡፡ በአጠቃላይ ጤና ነክ ማሳጅ ሰዎች የተፈጥሮ መከላከያ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ፣ ጤንነታቸውን እንዲያጐለምሱ፣ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ አካሎቻቸው በአግባቡ እንዲሰሩ እና በሰውነት ውስጥ የሚፈጠሩ መርዛማ ነገሮች እንዲወገዱ የማድረግ ጥቅሞች ያሉት ነው፡፡

* ኤሮትክ ማሳጅ (Eretic massage) ከምንነት እስከ ጥቅሞቹ ኤሮቲክ ማሳጅ ስሜት ቀስቃሽ ሲሆን ሁለት ጥንዶች

በሚፈፅሙት ወሲብ የተሟላ ደስታን ለማግኘት የሚያስችላቸውን መንቃት ለማግኘት እርስ በእርስ የሚተገብሩት የማሳጅ አይነት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ማሳጅ ከ10ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ይተገበር የነበረ ሲሆን፤ ቻይናንና ታይላንድን ጨምሮ በኤዥያ ሐገሮች በስፋት የሚካሄድ ነው፡፡

የሴቶችንም ሆነ የወንዶችን የግብረ- ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካላት በማነቃቃት፣ የነርቭ ስርዓታቸው የተስተካከለ እንዲሆን በተጨማሪም ፍቅረኛሞችም ሆኑ በትዳር ውስጥ ያሉ ጥንዶች ውጤታማ የወሲብ ግንኙነትን እንዲፈፅሙ ለማድረግ ኤሮቲክ ማሳጅ ያግዛል፡፡ ይህ ማለት ኤሮቲክ ማሳጅ የተሳካ ግብረ ሥጋ ግንኙነትን ለመፈፀም የሚያስችል ተጨማሪ ኃይልን ይሰጣል ማለት ግን አይደለም፡፡

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሁለቱ ጥንዶች በቤታቸው ውስጥ የሚያካሂዱት አሮቲክ ማሳጅ የተሟላ ደስታን እንዲያገኙ፣ የነርቭ (ማሳጅ... ወደ ገጽ 13 የዞረ)

ዘርፈ ብዙ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነው፡፡ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የሙዚቃ ፕሮዲውሰር፣ የቪዲዮ ክሊፕ ፕሮዲውሰርና የፊልም ተዋናይ! አማኑኤል ይልማ፡፡

ለጌዲዮን ዳንኤል፣ ኃይልዬ ታደሰ፣ ሸዋንዳኝ ኃይሉ፣ አለማየሁ ሂርጶ፣ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ብርሃኑ ተዘራ፣ ጸሐይ ዮሐንስ፣ ኤፍሬም ታምሩ፣ ማቲያስ ተፈራ፣ ጥበቡ ወርቅዬ፣ ግርማ ተፈራ፣ አቦነሽ አድነው፣ ፋሲል ደመወዜና ሌሎችም በርካታ ድምፃዊያን በአልበማቸው ውስጥ በግጥም፣ በዜማና በቅንብር ተሳትፎ አለው፡፡ እንዲሁም የተለያዩ ድምፃዊያንን ሙሉ አልበም አቀናብሮ ፕሮዲውስ አድርጓል፡፡ በቅርቡ ‹‹ዜማ አማን›› በሚል ኃይለየሱስን፣ ትዕግስትን፣ ህብስትን፣ ብዙአየሁን፣ ግርማ ተፈራን፣ ገረመውንና ፀጋዘአብን ያካተተ ኮሌክሽን አልበምም በፕሮዲውሰርነት አቅርቧል፡፡ በሚዲያዎች ራሱን ለማስተዋወቅ እንብዛም ግድ የሌለውን አማኑኤል ይልማን አነጋግረነዋል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- በኢትዮጵያ ሚሊኒየም ጊዜ የነበረውን በአል ለማክበር ከ50 በላይ ድምፃዊያን የተለያዩ ሙዚቃዎችን አውጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን ከሁሉም ጎልተው የወጡት አንተ ያቀናበርካቸው የቴዲ አፍሮ ‹‹ጊዜ ለኩሉ›› እና የብርሃኑና ማዲንጎ ‹‹አንበሳው አገሳ›› ነበሩ፡፡ ያ እንዴት ሊሆን ቻለ?

አማኑኤል፡- እንዳልከው የ2000 በአልን ለማክበር ህዝቡን ለማንቀሳቀስ ብዙዎች ዘፈኖችን ሰርተዋል፡፡ በዚያ አጋጣሚ አንዱ ሆኜ እንደዜማ ደራሲና እንደ አቀናባሪ ተሳትፌ ነበር፡፡ ዕድለኛ ያደረገኝ እኔ የሰራሁት ዘፈን ህዝቡ የተቀበለው ሆነ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የቴዲ አፍሮ ‹‹ጊዜ ለኩሉ›› ወይም ‹‹አበባ አየህ ወይ›› የሚለው ዘፈን ሲሆን፣ ከዛ በመቀጠል ‹‹አንበሳው አገሳ›› የሚለው በብርሃኑ ተዘራና ማዲንጎ አፈወርቅ የተዜመው ነው፡፡ በጊዜው በታዋቂ ድምፃዊያን ጭምር የተሰሩ ብዙ ዘፈኖች ውድድሩ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከእነዛ ውስጥ ግን በተለይ ‹‹አበባአየህ ወይ›› በአንድ ጊዜ ሒት ሆኖ ወጥቷል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የምነግርህ ያኔ ከቴዲ ጋር ብዙ አብረን ስንጓጓዝ ‹‹ቴዲ አትዘፍንም ወይ?›› እያሉ ይጠይቁት ነበርና በጣም የተጨነቀበት ወቅት ነበር፡፡ ምን ይዤ ልምጣ? ብሎ በተጨናነቀበት ወቅት ሌሎች ስራዎችን ስንሰራ ቆይተን አበባአየህ ወይን ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ነበር የጀመርነው፡፡ ወደ 11፡00 ሰዓት ላይ ጨረስነው፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም ግጥም አልጨመረም፡፡ ድጋሚም አልዘፈነውም፡፡ አንዴ ስቱዲዮ ውስጥ የተሰራ ስራ ነው፡፡ ዜማና ግጥሙ የቴዲ አፍሮ ነው፡፡ ቅንብሩ ከእነሚክሲንጉና ማስተሪንጉ የእኔ ነው፡፡ ከዛ በኋላ

የብርሃኑና የማዲንጎ ‹‹አንበሳው አገሳ›› ወጣ፡፡ (ዜማው የህዝብ፣ ግጥሙ የመሰለ ጌታሁን ሲሆን ቅንብሩ ሙሉ በሙሉ የእኔ ነው) ሁለቱም ላይ የሰቀሉ ዘፈኖች ነበሩ፡፡ እኔን የሚሊኒየሙ ዕድለኛ ያደረገኝ ሁለቱም ዘፈኖች ዓመት በዓል በመጣ ቁጥር የምንሰማቸው ማለትም ድሮ ከነበሩት ከእነጥላሁን ገሠሠ፣ ከእነ ብዙነሽ በቀለ የአመት በአል ዘፈኖች ጋር በማይተናነስ መልኩ እየተሰሙ ዘመን ተሻጋሪነታቸውን በማስመስከራቸው ነው፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- በተለይ የቴዲ አፍሮን ‹‹ጊዜ ለኩሉ›› ቢዮንሴ አዲስ አበባ መጥታ በሰራችው ኮንሰርት መድረክ ላይ ተጫውተው ደንሳበታለች፡፡ ያ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ብታጫውተኝ?

አማኑኤል፡- በወቅቱ እኔም እዚያው ሚሌኒየም አዳራሽ ነበርኩ፡፡ እና ሰርፕራይዝ ያደረገች ጊዜ እንደማንኛውም አድማጭ ደንግጫለሁ፡፡ በጣም አሪፍ ነበር፡፡ ሙዚቃውን

የመረጠችው ሳውንድ ማኗ ናት የሚል ነገር በኋላ ሰምቻለሁ፡፡ እርግጥም በዚያን ጊዜ የሳውንዱ ግሩቭ (Groove) በጣም ሒት ነበረ፡፡ ብዙ ጊዜ እንደ አጋጣሚ ሆኖ እንደዚያ አይነት ሚክሲንግ አልተሰራም ነበር፡፡ በመሆኑም ሳውንድ ማኗ ወደደችው፡፡ በሳውንድ በኩል በጣም ብዙ የሚጠበቅብን ነገር ያለ ቢሆንም በወቅቱ ግን ያ ሳውንድ በቂ እንደነበረ አምናለሁ፡፡ በተጨማሪም ያን ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ ይለቀቅ የነበረው ይህ ዘፈን ነበር፡፡ ህዝቡ ያብድበት የነበረ በመሆኑ የቴዲ አዘፋፈንም ምርጥ ስለነበረ መርጠውታል፡፡ በአጠቃላይ በዚያ የሚሌኒየም ወቅት ለቢዮንሴ ይመጥን የነበረ ሙዚቃ ስለሆነ ነው ብለን ብንወስደው ደስ ይለኛል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- ብዙ ጊዜ በግጥምና ዜማ ስራዎችህ ላይ እውነተኛ ታሪኮችን ወደ ሙዚቃ እየቀየርክ እንደምታቀርብ ይሰማል፡፡ ይህን ስታይል የመረጥከው ለምንድን ነው?

አማኑኤል፡- ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ትንሽ ወደኋላ መለስ ብዬ ልጀምርልህ፡፡ ከያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የተመረቅኩበት መሳሪያ ደብል ቤዝ ይባላል፡፡ ፒያኖ ማይነሬ ሲሆን፣ በባህል መሳሪያ ማሲንቆን ተጫውቻለሁ፡፡ ማሲንቆ በጣም ዜመኛ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ውጭ ደግሞ የአዝማሪ ግጥሞችን መስማት በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ረጅም ጊዜ እየሄድኩኝ የእነሱን ስራዎች

እከታተላለሁ፡፡ አንድ የአዝማሪ ስራንም ፕሮዲውስ አድርጌያለሁ፡፡ እንደነዚህ አይነት በድሮ ጊዜ የሚሰሩ ነገሮች ሪያሊቲ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ከድሮ ድምፃዊያን የማደንቀው የጋሽ ባህሩ ቀኜ ግጥሞችን ነው፡፡ በዚህ ዘመን ‹‹አንጣላ›› ብሎ የሚዘፍን የለም፡፡ ልቤን ጅብ በበላው ባወጣው አጥንቱ፣ ተጣልቶ መታረቅ አይሆን እንደ ጥንቱ፡፡ የመሳሰሉ ግጥሞች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ቀድመው የሚነግሩህ ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት ፍልስፍና ውስጥ ስትገባና ይህን እያዳበርከው ስትሄድ፣ ላይፍን ወደ ሙዚቃ አምጥተህ የሰውን ታሪክ ስትፅፍ ከዛ የበለጠ ቀድመህ ሁሉ መድሃኒት ታዘጋጃለህ፡፡ እኔ ደግሞ ፊት ለፊት ያሉኝን ችግሮች ወደ እውነተኛ ታሪክ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ዘመን እሰራቸው የነበሩት ስራዎች በአብዛኛው አፍቅሮ የተጎዳ ሰው ላይ ያመዝን ነበር፡፡ የተወሰኑትን ብጠቅስልህ ‹‹እንዳረከኝ አድርገኝ፣ ሳታመሀኝ ብላ፣ ኋላ እንዳይቆጭሽ፣ በአይኔ ላይ ዋልሽሳ በአይኔ፣ የማታ ማታ...››

ሌሎችም አሉ፡፡ በሴት ደግሞ የነፃነት አየለ ‹‹ላያገባኝ›› አለ፡፡ ማለትም እንዴት ይሄ ሁሉ ጊዜ አልፎና ዛሬ ከእኛ አልፎ ለሰው ተርፎ፣

ለካ ይሄን ሁሉ ጊዜ እያለፋኝ ነበረ ለካ ሳያገባኝ እያለች የምትጫወተው ማለት ነው፡፡ ይህም አንዲት ሴት ረጅም ዓመት አንድ ወንድ ይዟት ሄዶ

ጊዜዋን ሁሉ ገድሎ በመጨረሻ ሳያገባት ሲተዋት ያመላክታል፡፡ የብዙ ሴቶችን፣ ችግር ያሳየሁበት ነው፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- በጎሳዬ ተስፋዬ የተዘፈነውን ‹‹ሳታመሀኝ ብላ›› ግጥም የፃፍከው ከእውነተኛ በምታውቀው ሰው ላይ ከደረሰ አጋጣሚ ተነስተህ መሆኑም ይነገራል፡፡

አማኑኤል፡- ልክ ነህ፡፡ ‹‹ሳታመሀኝ ብላ›› ትልቅ ታሪክ ነው፡፡ በአንድ የቅርብ ጓደኛዬ የደረሰ ታሪክ ነው፡፡ አንድ ሰው የሚወደውን ጓደኛውን በምን መንገድ እንደሚያጣው፣ ሚስቱን

ደግሞ በጓደኛው እንዴት እንደሚያጣ የሚገልፅ ነው፡፡ የክሊፑ አለመሰራት ዘፈኑን በውስጥ ደረጃ አስቀረው እንጂ ትልቅ ታሪክ ያለው ነው፡፡ የሚገርምህ ከዚህ ዘፈን ጋር በተያያዘ ብዙ ገጠመኝ አለኝ፡፡ ለምሳሌ ‹‹እንዴት ሰውን ጅብ ትላለህ?›› ያሉኝ ሰዎች ነበሩ፡፡ እኔ ግን ‹‹ጅብ›› ስል በልመናና በጨዋነት ነበረ የገለፅኩት፡፡ አንቺም ትዳሬ ነሽ እሱም ጓደኛዬ፣ ጥፋቱ የማን ይሆን ስሄድ አንችን ጥዬ፣ አወይ ክፉ ዘመን ልቤ አዘነብሽ እሱም ተሳሳተ የእኔ እናት አንቺም አልታመንሽ ታማኝ ያንቺ ገላ ያለኔም አያውቅም ምነው ደከመሳ አነሰው ወይ አቅም ስደተኛ ታርገኝ ደሞ ብላ ብላ ጅብ ረሃብ አይችልም ብለህ ወንድሜ ሳታመሀኝ ብላ አየህ ‹‹ወንድሜ›› ነው ያልኩት፡፡ ጭካኔ የለውም፣ ግን መልዕክቱ ሃያል ነው፡፡ በጓደኛዬ ላይ የደረሰው ህመም ነው ያንን እንድፅፈው ያደረገኝ፡፡ ብዙዎች ይህ የእኔ ስራ መሆኑን ሲያውቁ የኔ ታሪክ መስሏቸው ደውለው ሀዘናቸውን የገለፁልኝ አሉ፡፡

ሌሎች ደግሞ ‹‹የእኔን ታሪክ ነው የሰራህልኝ›› ያሉኝም አሉ፡፡ ዘ-ሃበሻ፡- አንተ በጥሞና ዜማውን የሰራኸውና ኤፍሬም

ታምሩ የተጫወተው ‹‹ኋላ እንዳይቆጭሽ›› ሙዚቃም እውነተኛ ታሪክ ነው አይደል?

አማኑኤል፡- ኋላ እንዳይቆጭሽ እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ የሰራሁት ስራ ነው፡፡ ታሪኩን በዝርዝር ባልነግርህም የዚያን ጊዜ የተፈጠሩት ‹‹ኋላ እንዳይቆጭሽ››፣ የጌዲዮን ዳንኤል ‹‹እንዳደረግከኝ አድርገኝ››፣ የፀሐዬ ዮሐንስ ‹‹ፍቅርሽ እንደ ጥላ፣ አንድ በይኝ...›› ወዘተ እውነተኛ ታሪክን መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- አማን አንተ ሌላ የምትታወቅበት ‹‹ለታናሿ ልስጋ››

በሚለው የሙዚቃ ቪዲዮ ነው፡፡ ይህንን ቪዲዮ ግጥምና ዜማ ሰርተህ ከማቀናበርህም በላይ ራስህ ፕሮዲውስና ዳይሬክት አድርገህ ያቀረብከው መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ለመሆኑ ይህን ስራ ለማቅረብ እንዴት ተነሳሳህ? ከአድማጭ ያገኘኸው ምላሽስ?

አማኑኤል፡- የምር ለመናገር ደራሲ ስትሆን፣ በሰው ችግር ውስጥ ማለፍ ስትጀምር፣ ዘፈኖችን ወደ ሪያሊቲ ስታመጣና ወደ እውነተኛው በሄድክ ቁጥር አርቱም ይሳካልሃል፡፡ የምትፅፈው ነገር ይሳካል፡፡ ዳይሬክት የምታደርገው ነገር ሁሉም ወደ እውነት ይቀርብልሃል፡፡ ከቅንነት ከተነሳህ ማለት ነው፡፡ እና የሚገርምህ ነገር በቡና ቤት ሴቶች ላይ፣ በጎዳና ተዳዳሪዎች ላይ፣ በአላቻ ጋብቻ ላይ እንደዚህ አይነት ነገሮችን ለመስራት እያሰብኩ ባለሁበት ሰዓት ወደ ገጠር ውስጥ እየሄድኩ፣ በቀንም በማታም ያለውን ሁሉ እያየሁ እየቀረብኩ እፅፍ ነበር፡፡ እና በዚህን ወቅት አንዲት ልጅ በጣም አዝና አየሁኝ፡፡ ያቺ ልጅ በሀዘን አገጯን የያዘች፣ ከንፈሯ የሚንቀጠቀጥ፣ እንባ ያቀረረችና ደንግጣ የተቀመጠች ነበረች፡፡ እኔም የፃፍኩት ያንኑ ነው፡፡ ግጥሙንም ስፅፈው፤-

እንባ አዝሎብኝ አይኖቿ፣ መዳፏ አልፎ ከጉንጮቿ እንባዋ ይፈሳል ሳያባራ ብቻውን ያወራል ከንፈሯ እያልኩ ጀመርኩት፡፡ ከዚያ ይህችን

ህፃን ሊድሯት፣ ቤተሰቦቿም ፈረዱባት፣ እያልኩ ዘፈኑን እየሰራሁት ይህን ዘፈን በደንብ ሊጫወተው የሚችለው ማነው? የሚለው ውሳኔ የኔ ነበር፡፡ ጎሳዬን መረጥኩት፡፡ እንደውም ለጎሳዬ ክፍያ ስከፍለው ‹‹እንዴት እንደዚህ አይነት አይዲያ?›› ሲለኝ ግድየለህም ብዬ አስጀመርኩት፡፡ ከዚያ ቡሬ አንድ ጥጃ አጠገቧ ስለነበረች ‹‹ቡሬ ቡሬ ቀናችን አይደለም እኔና አንቺ ዛሬ፣ አለጊዜው ታርደሽ አለጊዜው ተድሬ›› የሚለው በመስታወት አራጋው ተቀረፀ፡፡ ታገል ሰይፉም ገባበት፡፡ በእንደዚህ አይነት ተቀረፀ፡፡ ዘፈኑን ከቀረፅን በኋላ የዚህን እውነተኛ ታሪክ ሰው ጭፈራ ይመስለዋል፡፡ ምክንያቱም ሲሰማው እንደዘፈን የሚያደምጠው ነው፡፡ ስለዚህ ክሊፑን በመስራት መልዕክቱን ህዝቡ እንዲረዳው ማድረግ ያስፈልግ ነበር፡፡ የዚህንም ሪስክ ወስጄ ወደ 50 ሺ ብር በማውጣት ክሊፑን አሰርቼዋለሁ፡፡ እዛ ውስጥ ያለ ሁሉ ድምፃዊ፣ አንባቢ ተከፍሎታል፡፡ ይሄ ሁሉ አልፎ እስካሁን ከሰራኋቸው በርካታ ስራዎችና ሙዚቃዎች በላይ በየሄድኩበት ዓለም ሁሉ ‹‹ለታናሿ ልስጋ›› ነው የሚሉኝ፡፡ ምክንያቱም በህዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ያገኘሁበት በዚህ ስራ ነው፡፡ እንደምታውቀው የአላቻ ጋብቻን በተመለከተ ብዙ ወረቀቶች፣ ብዙ ወርክሾፖች፣ ብዙ ስብሰባዎች ተደርገዋል፡፡ ግን በሰባት ደቂቃ አንድ የሙዚቃ ክሊፕ ብዙ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል መሆኑን ብዙዎች መስክረውለታል፡፡ ሰውን እያዝናና ለቀጣዩዋ ለታናሿ ደግሞ ይታሰብበት በሚል መንገድ የቀረበ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓም፣ በአሜሪካም፣ በካናዳም አውስትራሊያም፣ አረብ አገር ጭምር ያሉት የወደዱትና እንዲዘፈን ደጋግመው ያዩት ክሊፕ ሊሆን ችሏል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- በቅርቡም ሌላ ይህን መሰል ክሊፕም ሰርተሃል? ይህኛውስ?

አማኑኤል፡- አዎ፣ በቅርብ ጊዜ ድጋሚ ከጎሳዬ ጋር ሰርቻለሁ፡፡ ያቀናበረው አበጋዝ ነው፡፡ ግን ዜማውም ግጥሙም የእኔ ነው፡፡ ‹‹ፍጥረትን እንደቀላል›› የሚል ነው፡፡ ይህኛው ደግሞ ህፃናቶችን ብዙ ጊዜ ከገጠር እያመጡ ዘመድ ጋ ይቀመጡ በሚልና በተለያየ መንገድ በማምጣት ትልልቅ ስራ ከአቅማቸው በላይ ያሰሯቸዋል፡፡ እኔም የሰራሁት ያንን በመቃወም ነው፡፡ ይህም ስራ አስተማሪ፣ ትልቅ ተቀባይነት ያገኘና ማህበረሰቡን የሚነካ፣ ለውጥና ዕድገትን የሚያመጣ የህፃናትን ኃላፊነት እኛ መውሰድ እንዳለብን የሚያስገንዘብ ሆኗል፡፡ እንደ አጋጣሚ ይህን ያሰራኝ አንድ ድርጅት ነው፡፡ ለታናሿ ልስጋን አይተው በዚያ መንገድ እንዲሰራላቸው ፈልገው ጠይቀውኝ ቦታው ድረስ ሄጄ፣ እንዴት ሽመና

እንደሚያሸምኗቸው እህል እንዴት እንደሚያስፈጯቸው ከባባድ ስራ ሲያሰሯቸው አይቼ በጣምም እንዳይከፉ አድርጌ ቀለል አድርጌ የሰራሁት ነው፡፡ ግን ያለው ሁኔታ በዚህ መንገድ ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን ሁለትና ሶስት እጥፍ የበለጠ መገለፅ የሚችል ነው፡፡ እኔ ግን የማምነው ማንኛውንም አይነት ችግር ነገሮችን በማቅለል ማህበረሰቡ በሚረዳበት መንገድ ማስተማርና ማዝናናት እንዳለብን ነው፡፡ በመሆኑም ያቀረብኩት በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ ከሁለቱ ስራዎቼ በተጨማሪ በቀጣይነት እንደዚህ አይነት ስራዎችን ማለትም ማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ችግር እየፈለፈልኩ የማውጣት አቋም አለኝ፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- እስቲ ስለዜማ ላሰታስ ባንድስ እናውራ፡፡ እንዴት ተቋቋመ? እንዴትስ ሊፈርስ ቻለ?

አማኑኤል፡- እኔ ዜማ ላስታስ ባንድ ለሙዚቃ ዕድገት አንድ መሰረት ነው ብዬ የማምንበት ነው፡፡ ከያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የተመረቅን ልጆች ማለትም ኤልያስ መልካ፣ ሁንአንተ ሙሉ፣ ሚካኤል መላኩ፣ ምስጋናውና እኔ ሆነን ያቋቋምነው ሲሆን፣ ስንጀምር ድምፃዊዎች ትዕግስት በቀለ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ እዮብ መኮንን፣ ኃይሌ ሩትስ ባንዱ ውስጥ ነበሩ፡፡ ባንዱ ትልቅ የሳውንድ ለውጥ ይዞ የመጣና አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነበር፡፡ ባንዱ ሊፈርስበት የቻለው ዋንኛ ምክንያት ሁላችንም ወደየስራችን ስቱዲዮ መበታተናችን ነው፡፡ መጀመሪያ ኤልያስ መልካ፣ ቀድሞን የራሱን ስቱዲዮ ሲከፍት ሁንአንተ ተከተለው፡፡ ከዚያ እኔም ወደ ስቱዲዮ ገባሁ፡፡ ከዚያ የየራሳችንን የስቱዲዮ ስራ ስንሰራ ወደ ባንዱ ለመስራት ስላልቻልን ሊፈርስ ችሏል፡፡ ይሁንና ባንዱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዓለማየሁ እሸቴ፣ የባህት ገ/ህይወት፣ የፍቅር አዲስና የመሳሰሉትን የድሮ ሙዚቃዎች አምጥተን በጥሩ ሁኔታ ቀርፀን ሰው በሚገርም ሁኔታ ተቀብሎታል፡፡ በዚያ ሳውንድም ባንዱ በጣም አሪፍ ከሚባሉት ባንዶች ስሙን አስቀምጦ ለማለፍ ችሏል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- አንተ በሙዚቃ ስራ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለመዞር የቻልክ ነህ፡፡ የአቡጊዳ ባንድ ውስጥ ተካተህም ከቴዲ አፍሮ ጋር ብዙ መድረኮች ላይ መስራትህን አውቃለሁ፡፡ የሙዚቃ ጉዞህን በተመለከተ እናውራ?

አማኑኤል፡- የሚገርምህ ከታዋቂ ድምፃዊያን ጋር ወደ ውጭ አገራት ከመሄዴ በፊት ከያሬድ ት/ቤት እንደተመርቅኩኝ አንድ ‹‹ፎርኤቨር ያንግ›› የሚል የባህል ቡድን አቋቁሜ ነበር፡፡ ከዚያ ቡድን ጋር ሀኖቨር የባህል ኤክስፖ በተዘጋጀበት ወቅት ከዛሬ 13 ዓመት በፊት በመሄድ ጀምረን በተከታታይ ለአንድ 6 ዓመታት የተለያዩ ቦታዎች ሰርተናል፡፡ ከዚያ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከእነፍቅር አዲስ፣ ኃይልዬ፣ ይርዳው፣ ህብስት ቴዲ አፍሮን

ጨምሮ ራሴ ፕሮሞተር እየሆንኩኝ ከአገር ውስጥ እስከ አረብ አገሮች እሰራ ነበር፡፡ የመጨረሻ ጉዞዬን ያደረግኩት ደግሞ ከቴዲ አፍሮ አቡጊዳ ባንድ ጋር በመቀላቀል ነው፡፡ ከአቡጊዳ ጋር ከ24 ሾው በላይ ሰርቻለሁ፡፡ ይህም በመላ አውሮፓ፣ አረብ አገራት፣ እንዲሁም አሜሪካና ካናዳ ዞሬያለሁ፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- ምንም አልበም ሳይኖረው በመላው ዓለም ታዋቂ ለመሆን የበቃው ጃኪ ጎሲ (ጎሳዬ ቀለሙ) ከዚህ ቀደም በዚሁ ዘ-ሃበሻ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ ሲያደርግ አንተን አመስግኗል፡፡ ከስኬቱ በስተጀርባ ያለህ ቁልፍ ሰው መሆንህንም ተናግሯል፡፡ ለመሆኑ ከጃኪ ጋር የነበራችሁ የስራ ግንኙነት ምን ይመስላል?

አማኑኤል፡- ጃክ ከጥቂት ዓመታት በፊት እኔ ጋር ሊሰራ በአጋጣሚ ወደ ስቱዲዮ መጥቶ ነበር፡፡ ይዞት የመጣው ስታይልም ትንሽ ወጣ የሚል ነው፡፡ ማለት ከአማርኛ ሙዚቃዎች ወጣ ያለና እንደ ሒፕ ሆፕ አይነት ነገር ነበር፡፡ እና የሒፕ ሆፕ ስታይሉን በሚያሰማኝ ጊዜ ልጁ አንድ ቃናና በጣም የሚገርም ድምፅ እንዳለው ተረዳሁ፡፡ ይሄን ድምፁን ደግሞ በእርግጠኝነት የሌላ ዜማ ስታይል ቢሰራበት ጥሩ ይሆናል በሚል ትንሽ ደቂቃ ተነጋገርን፡፡ ልጁም ጥሩና ቅን ስለሆነ ወዲያው ተመለሰ፡፡ ምክንያቱም የዜማ ደራሲ ስትሆን የመጀመሪያው ነገርህ ሰው መፍጠር ነው፡፡ አንድን ድምፃዊ አምጥቶ መስራት እንደማለት ነው፡፡ እንደፊልም ለዚህ ተዋናይ ይህን ካራክተር ብሰጠው ይዋጣለታል ብሎ መቅረፅ ነው፡፡ ስለዚህ በዚያ መንገድ የመጀመሪያውን ‹‹ጭራሽ›› የሚለውን ሰራሁለትና ይዞት ወደ አገሩ ሄደ፡፡ እዛ ከለቀቀ በኋላ አቀባበሉ የሚገርም ሆነ፡፡ እኔ መልዕክቱንም ስፅፈው ውጭ አገር ስላሉ ሰዎች በመለያየትና በመነፋፈቅ ውስጥ እንዴት እንደሚተሳሰቡ በሚያደርግ ስሜት (አማኑኤል.... ወደ ገጽ 20 ይዞራል)

አማኑኤል ይልማ ከአስቴር አወቀ ጋር - ፎቶ ዘ-ሐበሻ

አማኑኤል ይልማ ከማሪቱ ለገሰና ከቴዲ አፍሮ ጋር - ፎቶ ዘ-ሐበሻ

አማኑኤል ይልማ ከኤፍሬም ታምሩ፣ አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታና ሌሎችም ጋር - ፎቶ ዘ-ሐበሻ

የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የሙዚቃ ፕሮዲውሰር፣ የቪዲዮ ክሊፕ ፕሮዲውሰርና የፊልም ተዋናይ!

አማኑኤል ይልማ

Zehabesha.com በየሰዓቱ አዲስ ዜና

የማሳጅ ቴራፒ ምንነት ማሳጅ ቴራፒ ማለት ዘመናዊ በሆነ ሳይንስ

በፊዚዮሎጂ፣ አናቶሚና አቶሎጂ ቴክኒኮችን በመጠቀም በጡንቻዎችና በአጥንቶች ውስጥ ጥልቀታዊ ግፊት በማካሄድ በተመሳሳይ አቅጣጫ የደም ፍሰትን ወደ ልብ የመመለስ ጥበባዊ ሂደት ነው፡፡ በዚህ ሂደት በደም ውስጥ ጤናማ የኦክስጅን ፍሰት እንዲኖር እንደዚሁም ከጡንቻዎች ውስጥ መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድ የሚጠቅም ሁሉ አቀፍ የተፈጥሮ አማራጭ ህክምና ነው፡፡

የማሳጅ ጥበብ እጅንና ከተፈጥሮ ተክሎች የሚቀመሙ ቅባቶችን በመጠቀም በማሸት ምቾት ለመስጠት፣ ጡንቻን ማፍታታት፣ የደምን ፍሰት ጤናማ እንዲሆን መርዳት፣ የነርቭ ስርአትን ማረጋጋት፣ የሊምፎ ስርአትን ማበረታታት፣ የመገጣጠ ሚያዎችን፣ አገናኝ ህብረ ህዋሳትን መዘርጋት፣ የጡንቻ ውጥረትን ማርገብ፣ ጡንቻዎችን ማጎልበት፣ ባክቴሪያና ሌሎች ቆሻሻ ነገሮችን ለማስወገድ የሚረዳ ከመሆኑም በላይ በህብረ-ህዋስና በደም ውስጥ ትክክለኛው የፈሳሽ ሚዛን እንዲኖር የሚያደርግ ተፈጥሮአዊ የአማራጭ ህክምና ዘዴ ነው፡፡

በሌላም በኩል በጡንቻዎች፣ በመጋጣጠሚያዎችና ጅማቶች ውስጥ ዩሪክና ላክቲክ አሲዶች በዝቃጭነት ተከማችተው የህዋሳቶቻችን ኬሚካላዊ እንቅስቃሴን ያውካሉ፡፡ እንዲህ ያለውን መሰረታዊ ችግር በማሳጅ ጥበብ መፍትሄ መስጠት ይቻላል፡፡

ማሳጅ በአንጀቶች፣ በሳንባዎች፣ በኩላሊቶችና ቆዳ ውስጥ የሚፈጠሩትን መርዛማ ነገሮች ከማስወገድ ባሻገር የጠበቁትንና ያጠሩትን ጡንቻዎች በቀላሉ የማዝናናት አቅም ያለው ጥበብ ነው፡፡

ታሪካዊ አመጣጥና እድገቱ ጥንታዊያን ግብፆች ከክርስቶስ ልደት 3000 ዓመት

በፊት ማሳጅን ለጤንነትና ለቁንጅና በሚል በስፋት ይጠቀሙበት እንደነበር ሰነዳዊ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በተለይ መንግስት ክሊዮፓትራ በእራት ግብዣ ጊዜ የእግር

ማሳጅ መጠቀም እንደሚያስደስታት የሚያሳይ ስዕላዊ ማስረጃዎችም ተገኝቷል፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ5ኛው ክፍለ ዘመን ጊዜ ይኖር የነበረው እና የዘመኑ ህክምና አባት ተብሎ የሚጠራው ናፖ ክራትስ ስለማሳጅ የጻፈው መረጃ እንደሚያመላክተው ማሳጅን ከቅባት ጋር በመጠቀም ያላሉትንና ግትር የአሉ የሰ ውነት ክፍሎችን መፍትሄ የመስጠት አቅም ያለው መሆኑን ነው፡፡

በሌላ ታሪካዊ መረጃ ደግሞ ቻይናዊያኖች ለ500 ዓመታት በባህላዊ ህክምና ናቸው ማሳጅን ከእስትንፋስ እንቅስቃሴ ጋር በማዋሃድ ለህመምተኞች በተገቢው መንገድ

ይጠቀሙት እንደነበር ታሪካዊ መጽሐፍቶቻቸውን ጨምሮ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3ኛው ክፍለ ዘመን የተፃፈው ‹‹ዘ-የሎው ኤምፕረ ር ክላሲክ ኦፍ አተርናል ሜዲስን›› በሚለው መጽሐፍ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በህንድ ጥበቡ 3000 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን አዩርቫይ የህይወት ጥበብ በመባልም ይታወቃል፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በህንዳውያን የተጻፉ መጽሐፍ ላይ ማሳጅ ድካምን ይቀጥላልና ጤንነትን ያስገኛል ይላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አውሮፓ በ1517-1590 ይኖር የነበረው ፈረንሳዊው የቀዶ ጥገና

ሐኪም አምብሮስ ፓሬ ማሳጅን አራት ንጉሶችን እንዳከሙበትና በ18ኛውና በ19ኛው ክፍለ ዘመኖች በአውሮፓ ውስጥ ገንኖ ዝናን ያገኘበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ ለዚህም ታዋቂው ስዊድናዊው የሻቦላ ማስተርና የጅምናስቲክ መምህር ፐር-ኸንሪክ ሊንግ (ከ1776-1839) ከፊዚዮሎጅና ከጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ጋር ማሳጅን በማዋሃድ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ለዘርፉ ሳይንሳዊ እድገት መሰረት ጥሏል፡፡ በተለይም ዛሬ ‹ስውዲሽ ማሳጅ› ተብሎ የሚጠራው የማሳጅ ጥበብ የሱ ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ የፕርኸንክ ሊንግን የጥናት ውጤት መሰረት በማድረግ የደቹ ተወላጅ ጆሃን ጆርጅ 1838-1909 መሰረታዊ አስተሻሸቶች መጠሪያ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ በዚህ ሂደትም ዛሬ ማሳጅ ቴራፒ በጤና ማዕከላቶች፣ ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች እንደ አንድ መደበኛ ህክምና ሆኖ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

* የማሳጅ ቴራቲ ዓይነቶች የማሳጅ ቴራፒ አይነቶች ብዙ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ

በዛሬው መሰናዶአችን አኩፓይንት እና ኤሮቲክ የሚባሉትን የማሳጅ አይነቶች ብቻ በመጠኑ ዘርዘር አድርገን ለማየት እንሞክራለን፡፡

አኩፓይንት ማሳጅ አኩፓይንት ማሳጅ የአኩፓንክቸር (የነርቭ) እና

ፕሪፈራል ነጥቦችን በመተነኳኮስ የደም ኡደትንና የሊምፎ ዝውውርን እንዲሁም የህብረ-ህዋሳት ሚታቦሊዝምን በማበልፀግ የአዕምሯችንን፣ የማዕከላዊ ነርቭ ስርዓታችንና

የውስጣዊ አካላት ሥራ እንዲያቀላጥፍ ያስችላል፡፡ በአኩፓንክቸር ነጥቦች ላይ የሚደረገው የማሸት

ተግባር በሰውነት ውስጥ የባዮ-ኤሌክትሪካዊ ስሜትን ምላሽ የሚሰጥና ሰውነታችን ጤናማና እለታዊ ተግባሩን በአግባቡ እንዲያከናውን ያደርገዋል፡፡ አኩፓይንት ማሳጅ ከላይ የተገለፁትን ተንኳሽ ነጥቦች በእጅ ጣቶች አማካኝነት ቴክኒካዊ

ግፊቶች በመጠቀም በሰውነት ውስጥ በሚገኙት ቻናሎች ውስጥ ያሉትን መሰናክሎች የማሳገድ ተግባርን ያከናውናል፡፡ በዚህም በሰውነታችን ውስጥ የደም ፍሰትንና ኦክስጅንን በአግባቡ እንዲዟዟር እና ጡንቻዎች እንዲዝናኑ በማድረግ ጤናማነትን ያጐናፅል፡፡

የሰውነት ውስጥ ቻናሎች ሲባል ለምሳሌ የጉበት፣ የጨጓራ የቆዳ፣ የጡንቻዎች፣ የአጥንት፣ የእጅና የእግሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ በመላ ሰውነት ላይ አንድ መረብ የተዘረጉና እንደ አንድ አካል የሚተባበሩትን ውስጣዊ አካሎች ማለት ነው፡፡

* አኩፓይንት ማሳጅ ቴራፒ ከጤና አንፃር የሚያስገኛቸው ጥቅሞች

ረመድያል ማሳጅ ቴራፒ በሁሉም ሲስተሞች ላይ የሚደርሱትን ጉዳቶች በተገቢው ሁኔታ ማከም የሚያስችል አቅም ያለው ሲሆን ከሚያስገኛቸው ጤና ነክ ጥቅሞች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ * ከነርቭ ችግሮች አንፃር፡- (ማሳጅ... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

ከሊሊ ሞገስ እዚህ ሚኒሶታ አንዳንድ ሴቶች የሞንግ ወይም የቻይና

ገበያ በመሄድ የፊት ሳሙናዎችን እና ቅባቶችን በመግዛት ቡግራችንን እናጠፋለን፤ መልካችንን እናቀላለን በሚል ካለ ሃኪም ትዕዛዝ ይህን ሳሙናና ቅባት በመጠቀም ፊታቸውን ሲያበላሹ አስተውለናል። አንዳንድ ሴቶችም ወደ ዘ-ሐበሻ በመደወል “ሳሙናውና ቅባቱ ፊታችንን አበላሸው፣ አዥጎረጎረን፣ ቡግር አወጣብን” ሲሉ በ እኛ የደረሰው እንዳይደርስ ምክራችንን አስተላልፉልን ብለውናል። የዘ-ሐበሻ የጤና አምድ ሁልጊዜም ሰዎች ሳሙናም ሆነ ፊት የሚያጠራ ቅባት ከመቀባት በፊት ከቆዳ ሃኪም ጋር መነጋገር እንደሚያስፈልግ ስትመክር ቆይታለች። የኤሲያኖች ቆዳ እና የሃበሾች ቆዳ አንድ አይነት አይደለም። እነርሱን ስለጠቀማቸው ሃበሾችን ይጠቅማል ማለት አይደለም። በመሆኑም የዚህ ችግር ስለባዎች ወደ ሃኪም እንዲሄዱ በመምከር ተፈጥሯዊ የቡግር ማጥፊያዎችን እንጠቁማለን። ይህንን ያዘጋጀነውም ለግንዛቤዎ እንዲጠቅም እንጂ ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ነገር ከማድረግ በፊት ሃኪምዎን ማማከርዎን አይርሱ።

ቅባታማ ምርቶችን ያስወግዱ፡- ከፍተኛ የቅባትነት ይዘት ያላቸውን የፀጉር ቅባቶች ጨምሮ የፊት ማውዣዎች (moisturizers) እና ዘይታማ ማጽጃዎችን አይጠቀሙ፡፡

የፊትዎን ንፅህና ይጠብቁ፡- ፊትዎን የእጅዎ መዳፍ ላይ በፍፁም ማሳረፍ አሊያም በተደጋጋሚ ፊትዎን መዳሰስ አይኖርብዎትም፡፡ ፀጉርዎን አዘውትረው በሻምፖ ይታጠቡ፣ ነገር ግን ፊትዎን መንካት የለቦትም፡፡

የአካል እንቅስቃሴ ያዘውትሩ፡- በመካከለኛ ደረጃ የአካል እንቅስቃሴ ማዘውተርዎ የደም ዝውውርን ከማቀለጣጠፉም በላይ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ከሰውነትዎ እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡

ከጭንቀት ነፃ ይሁኑ፡- በርካታ ጥናቶች ጭንቀት ብጉርን ከማባባሱም በላይ የቆዳ ጤንነት ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል ይላሉ፡፡ ጭንቀት ሲያድርብዎ ከወዳጆችዎ ጋር ይማከሩ፣ የሚወዱትን ሙዚቃ ያዳምጡ፣ አሊያም ዘና ለማለት ይሞክሩ፡፡ የእግር ጉዞ ማድረግዎ ዘና እንዲሉ ያደርጋል፡፡ እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ከጭንቀት ነፃ እንዲሆኑ የሚረዱም ነገሮችንም ይከውኑ፡፡

በቂ የፀሐይ ብርሃንና ኦክስጅን፡- የሐይ ብርሃን ቫይታሚን ዲን ለሰውነታችን ይሰጣል፡፡ ይህ ቫይታሚን ለቆዳ ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ንፁህ አየርና የፀሐይ ሙቀት ጭንቀትን በመቀነስ በቆዳ ውስጥ የኦክስጅን መጠን እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ፀሐይ ላይ ለረጅም ጊዜ በመቆየት ቆዳዎ እንዲቆጣ ማድረግ አይኖርብዎትም፡፡

ብጉርን ለመቀነስና ለማጥፋት ይረዳሉ ተብለው የሚመረቱ ዘመናዊ ባህላዊ ቅባቶችና ዘይቶች በርካታ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ለጊዜው ችግሩን ያጠፉ ቢመስሉም ቅባቱ ካለቀ በኋላ ግን ብጉሩ ተባብሶ ሊቀጥል የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ ከባህላዊም ሆነ ዘመናዊ ህክምናዎች ባልተናነሰ ተፈጥሯዊ

የሚባሉት ዘዴዎች ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ ይሰጣሉ፡፡ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ ብጉሮችን በጣትዎ አይነካኩ፡- ፊትዎ ላይ

የሚታዩትን ብጉሮች በጣትዎችዎ መጫን ወይም ማሸት አይገባም፡፡ እንዲህ በሚያደርጉበት ጊዜ የፈሳሹን (sebum ይሰኛል) መጠን እንዲጨምር ከማድረግዎም በላይ ከቆዳዎ ስር ያለው አካል (membrane) እንዲቀደድ ያደርጋሉ፡፡ ኢንፌክሽኑና ፈሳሹ በቆዳዎ ስር በመዛመት ሌሎች ብጉሮች እንዲፈጠሩም ምክንያት ይሆናል፡፡ ከሁሉም በላይ በፊትዎ ላይ የማይጠፉ ጠባሳዎች የመከሰት ዕድልን እንዲጨምር ሊያደርጉ

ስለሚችሉ ፊትዎን በጣትዎችዎ ማሸትን ያስወግዱ፡፡ ፊትዎን በቀን ሁለት ጊዜ በሳሙና ይታጠቡ፡- ፊታቸው

ላይ ብጉር የሚታይባቸው ሰዎች ከሰልፈር (sulfur) የተሰሩ ሳሙናዎችን እንዲጠቀሙ ይመከራል፡፡ ቆዳዎ በተፈጥሮው ባለ ወዝ (oily) ከሆነ benzoyl peroxide የተካተተበት ሳሙና ይጠቀሙ፡፡ ፊትዎን በስፖንጅና በሌሎችም ሻካራ ጨርቆችና ብሩሾች እየሞዠቁ እንዳያጥቡ፡፡

- ብጉሩን ያብሰዋል እንጂ አያጠፋውም፡፡ ፊትዎን ከሁለት ጊዜ በላይ ደጋግመው በማጠብ

እንዳያደርቁት መጠንቀቅ ይኖርብዎታል፡፡ የቆዳ ዕጢዎች ፊትዎ የደረቀ ከመሰላቸው ብዙ sebum እንዲመረት በማድረግ ብጉሩ እንዲስፋፋ ምክንያት ይሆናሉ፡፡

ምግብና ብጉር፡- ለበርካታ ሰዎች የምግብ አለርጂ ለረጅም

ጊዜ የማይጠፋ ብጉር እንዲፈጠርባቸው ሊያደርግ ይችላል፡፡ ብጉር ፊታቸው ላይ የሚታይባቸው ሰዎች ቅባትና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች አብዝተው እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች በወተት ውስጥ የሚገኙ ሆርሞኖችና በባህር ምግቦች ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ የአዮዲን መጠን ብጉርን እንደሚያባብሱ ተደርሶበታል ይላሉ፡፡ ከተቻለ እነዚህ ምግቦች አይወሰዱ፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ስኳር፣ የወተት ተዋፅኦዎች፣ ለረጅም ሰዓት ሲጠበሱ የቆዩ ምግቦች፣ ስጋ፣ የኦቾሎኒ ቅቤ እና የመሳሰሉት ቅባታማና ዘይታማ ምግቦችን ያስወግዱ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው አረንጓዴ ተክሎች፣ የአትክልት ጭማቂና በዚንክ የበለፀጉ ምግቦች ብጉርን ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡

ውሃ ይጠጡ፡- ሲባል በመጠኑ በርከት ያለ መሆን ይኖርበታል፡፡ ጄኒፈር ቶደን የተባሉ የብጉር ኤክስፐርት በቀን ስምንት ብርጭቆ ውሃ በመጠጣት ብጉርን መከላከል እንደሚቻል ይመክራሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ውሃ ቆሻሻን ከሰውነታችን ሲስተም ማስወገድ ስለሚችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሰውነታችን ብጉርን እንዲከላከልና እንዲያድን ይረዳዋል፡፡

ሜክአፖችን አይጠቀሙ፡- የተለያዩ የሜክአፕ ምርቶች ብጉርን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ በተቻለ መጠን ባይጠቀሟቸው ይመከራል፡፡ እነዚህ መኳኳያዎች ብጉር እንዲስፋፋ ያደርጋሉ፡፡ የግድ መጠቀም አለብኝ ካሉ ደግሞ መሰረታቸው ውሃ የሆነ (water based) ሜክአፖችን ምርጫዎ ያድርጉ፡፡ የሜክአፕ ብሩሾችዎን በቋሚነት ያጽዱ፤ እንዲሁም ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ፊትዎንና ሜክአፕ የነካውን አካል ይታጠቡ፡፡

የወይራ ዘይት - የጓሮ አትክልት መንከባከቢያ ቁሳቁሶችን በቀላሉ

ለማጽዳት ያስችላል፡፡ - የቤትና የቢሮ ፈርኒቸር ያሳምራል፡፡ - በቀላሉ ከዓይን ላይ ሜክአፕ ለማስለቀቅ ይረዳል፡፡ - ከማይዝግ ብረት የተሰሩ (stainless steel) ቁሶች

እንዲያንፀባርቁ ያደርጋል፡፡ - የካጄት አሊያም የሱሪዎ ዚፕ ተቀርቅሮ አልንቀሳቀስ ካለ

የወይራ ዘይት ጠብ ያድርጉበት፡፡ - የቆዳዎን ልስላሴ ይጠብቃል፡፡ - ማንኳራፋትን ያስወግዳል፡፡ - የኩራዝ መብራት ሆኖ ማገልግል ይችላል፡፡ - አንዳንድ ስቲከሮች የተዉትን ማጣበቂያ ያስወግዳል፡፡ - ለጉሮሮ ህመም ፈውስ ይሰጣል፡፡ - የጆሮ ህመምን ያስታግሳል፡፡ - ጺምዎን ከተላጩት በኋላ ጥቂት የወይራ ዘይት

ይቀቡት፡፡ ልስላሴው ያስደስትዎታል፡፡ - ጫማዎን ቢጠርጉበት ያሳምርልዎታል፡፡ - ጥሩ የፀጉር ቶኒክ ነው፡፡ - ገላዎን ገንዳ ውስጥ የሚለቃለቁ ከሆነ የወይራ ዘይት

ጠብ ያድርጉበት፡፡

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

በቋንቋ የተነሳ የኮምፒውተር ፈተናውን ማለፍ ተስኖዎታል? በዚህ የተነሳ መኪና መንዳት አልቻሉም? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር

አለ፤ አስተምረን ወስደን እናስፈትንዎታለን።

ልብ ይበሉ የእርስዎን ቋንቋ እንናገራለን

2400 Minnehaha Avenue #204 Minneapolis, MN 55404 (612) 275-0970

በተጨማሪም የትርጉም ድርጅታችን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲኖርብዎ ወይም በማንኛውም ሰዓት የትርጉም ሥራ

ሲያስፈልግዎ ክፍት ነው።

የፎቶግራፍ ምንጭ፡ ኔሃ ክሊኒክ ድረገጽ

ፎቶ ምንጭ፡ upstonchiropractic.com

ቻይናንና ታይላንድን ጨምሮ ከ10ኛ ክ/ዘመን ወዲህ ፈጣን በሆነ መልኩ እየተስፋፋ የመጣው የማሳጅ ጥበብ ዛሬ- ዛሬ በሐገራችን በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት እየተተገበረ ይገኛል፡፡ በሐገራችን ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ማሳጅ ጠቅለል ባለ መልኩ ከተጠቃሚዎች አንፃር ሲታይ ሁለት መልክ ያለው ነው፡፡ በአንድ በኩል ከተለያዩ በሽታዎች ፈውስን ለማግኘት የማሳጅን ህክምና ይጠቀማሉ፡፡ በሌላኛው ደግሞ ወሲባዊ መነቃቃትን (እርካታን) ለማግኘት በሚል የማሳጅ አገልግሎት ወደሚሰጡ ተቋማት ጐራ የሚሉ ሰዎች ቁጥርም በየጊዜው እየተበራከተ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

አኩፓይንት (ረመድያል) የማሳጅ አይነት የነርቭ ስርአትን ከማስተካከል ጀምሮ ለተለያዩ ጤና ነክ ችግር መፍትሄ በመስጠት ረገድ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ብዙዎቹ ይስማማሉ፡፡ ልዩነቱ ያለው በኤሮቲክ ማሳጅ ዙሪያ ነው፡፡ ኤሮቲክ ማሳጅ የሴቶችም ሆነ የወንዶች መራቢያ አካላት ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ፣ እንዲሁም የተሳካ ወሲባዊ ድርጊት ከመፈፀም አንፃር ጠቀሜታ እንዳለው የሚገልፁ ሙያተኞች አሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ተፈጥሮአዊውን የወሲብ መፈፀሚያ ስርዓትን የሚጥቅስና በትዳር ተጣማሪዎች መካከል አለመተማመንን የሚያሰፍን ከመሆኑም በላይ ፍቅርን ሰጥቶ ፍቅርን ለመቀበል የሚደረገውን ተፈጥሮአዊ ሂደት ያውካል ሲሉ የሚከራከሩ ሙያተኞች ቁርጥም በርካታ ነው፡፡ የክርክሩን መቋጫ ለዘርፉ ተመራማሪዎች እንተወው፡፡ ለዛሬ በኤሮቲክ እና በአኩፓይንት ማሳጅ በማሳጅ ጥበብ ምንነት፣ አይነት፣ ፋይዳና መውሰድ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ዙሪያ ሙያዊ ማብራሪያ ለመስጠት ይሞክራል፡፡

አዘጋጅ፦

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

መንስኤው ምንድን ነው? የአንጐል የአሰራር ሂደት እንዲዛባ ሊያደርጉ

የሚችሉ ሁኔታዎችን ስንመለከት ከሁለት ምንጮች ይነሳል፡፡ እነዚህም አንደኛው በተፈጥሮ ሌላውም ከአካባቢ በሚነሱ ተጨማሪ ነገሮች ነው፡፡ አንድ ሰው በተፈጥሮ ዲፖሚን የተሰኘው ኬሚካል የሚያመነጭ ሲሆን ይህ ኬሚካል በራሱ ጊዜ መጠኑ ሊዛባ ይችላል፡፡ በሌላው በኩል ከአካባቢያችን የምንወስዳቸው አነቃቂ መድሃኒቶች፣ አልኮል፣ ሃሺሽ እና የመሳሰሉት የኬሚካላዊ ይዘቱን በመቀየር አእምሮአዊ የማገናዘብ ሁኔታን ሊያዛባ (ሊያዘበራርቀው) ይችላል፡፡ ለዚህም ነው የአእምሮትን መረዳት እና ያለውን ሃቅ ማጣጣም የሚያቅተን፡፡

መረሳት የሌለበት ትልቅ ጉዳይ ሀሉሲኔሽን እራሱን የቻለ የስነ አእምሮ ህመም

ሳይሆን የስነ አእምሮ ህመሞች መገለጫ ምልክት ነው፡፡ አንድ ሰው ለቲቢም ሆነ ለታይፎይድ አልያም ለሌላ በሽታ ሲጋለጥ በመጀመሪያ ደረጃ የሚያያቸው አንድ አይነት ምልክት አለው፡፡ ለምሳሌ ራስ ምታት (ትኩሳት) የአብዛኛዎቹ ህመም የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶች ይሆናሉ፡፡ ልክ እንደዛው ሁሉ ብዙዎች የአዕምሮ ህመሞች የሌሉ ነገሮች እንዳሉ አድርጐ የመገንዘብ ሁኔታን እንደ መገለጫቸው ምልክት ሆኖ የሚወሰድ የስነ አእምሮ ጤና ችግር ነው፡፡ እስኬዞፌርኒያ መደበት (ዲፕሬሽን) ሳይኮሊስ እና ብዛት ያላቸው መሠል የአዕምሮ ህመሞች በሚኖሩበት ጊዜ እነዚህ በሽታዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ያሳዩናል፡፡

ሌላው እነዚህ ምናባዊ ሁነቶች ለችግሩ ተጋላጭ ሰዎች ትክክለኛ ናቸው፡፡ ለጤነኛው ሰው ግን አይታወቁም (ከብዙሃኑ ጋር አለመጋራቱን ነው ህመሙ እንደነ የሚያስረግጥልን)

በአእምሮአዊ መዛባቱ ወቅት የሚገለጡት ምን አይነት ምልክቶች ናቸው?

እነዚህ ምልክቶች የተለያዩ ናቸው፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው ማንኛቸውም በስሜት ህዋሳቶቻችን የሚመጡ መረጃዎችን አእምሮ በተለየ ሁኔታ መገንዘቡ ነው፡፡

ከማየት ጋር የተያያዘው የሃሉሲኔሽን ችግር ለሰዎች የማይታዩ ነገሮችን ማየታቸውን ህሙማኑ ይረዳሉ፡፡ በቦታው የሌለሰውን አጠገባቸው እንዳለ መቁጠርና ማናገር ለተለያዩ ድምፆች ምላሽ መስጠት የሚረብሽ ድምፅ የሰሙ ሲመስላቸው ጆሮአቸውን መድፈን፣ ብቻቸውን መሳቅ ወይም በማልቀስ ሃዘናቸውን ይገልፃሉ፡፡ ከእንቅስቃሴና ንክኪ ጋር በተገናኘ ከአጠገባቸው ሰው እየሠራ እንደሆነ በማሰብ እርዳታ ለመስጠት አልያም ለመቀበል መሞከር እና ምግብ ሳይኖር የመመገብ እንቅስቃሴ እና ጣዕሙን ለይቶ የመግለፅ ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ለጊዜው ትክክል ያለመሆናችን ልንነግራቸው ብንሞክረም ሊረዱን አይችሉም፡፡ ያሉበት ሁኔታው አይፈቅዳላቸውም፡፡ የህመሙ ባህሪ በመሆኑ ልንፈርድባቸውም አይገባም፡፡ እነሱን ለማስረዳት ከመሞከር ይልቅ ወደ ህክምና ቦታዎች በማድረስ ሊያገኙ የሚገባቸውን ህክምና በጊዜው እንዲያገኙ በማስቻል ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ከባድ

የአዕምሮ ህመም ልንከላከልላቸው ይገባል፡፡ ስሜታቸውን በሚገልፁበት ጊዜም መረዳታቸው ከጉዳት

እየሸሹ እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡ ለምሳሌ ከማሽተት ጋር መጥፎ ጠረኖች እንዳሉ በማሰብ አፍንጫቸውን ሊይዙ ይችላሉ፤ ከመስማት ጋር በተያያዘም ረቂቂ ድምፆችን እንደ የደም ዝውውርን የማዳመጥ ጥቃቅን ድምፅችን የማጉላትና ትርጉም የመስጠት ከስኪዘፌርኒያ ከተሰኘው አዕምሮአዊ ህመም ጋር እንደሚያያዝ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ከማየት ጋር በተያያዘም በማይግሪንና መሠል ህመሞች ሳቢያ የሚኖር ስነ አእምሮ መታወክ የሚመጣ ሲሆን ለዚህም መከሰት መጠጥና አደገኛ መድሃኒቶች አብይ ሚና ይጫወታል፡፡ አጠቃላይ የስሜት ለውጦችም በአካል የሚኖሩ ሲሆን የአካል ጉዳቶች እንዳሉ በማሰብ የስቃይ ስሜቶችን ማሳየትና ከጥቃት ለማምለጥ የሚደረጉ እንቅስቅሴዎች ሲያደርጉ ይስተዋላሉ፡፡ የአእምሮ ማዛባት ችግር ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በእኩል ደረጃ የሚያጠቃ የአእምሮ በሽት መለያ ነው፡፡

ጥንቃቄ የበሽታ ምልክት እንጂ እራሱን የቻለ በሽታ ባለመሆኑ ምንም

አይነት የተለየ ጥንቃቄ ለማድረግ ያስቸግራል፡፡ ሆኖም የስነ አዕምሮ ህመሞች ውስጥ የአንዱ መገለጫ ሊሆን ስለሚችል የስነ ልቦና ጉዳዮች ከሚያጋልጡ አጠቃላይ ሁኔታዎች መራቅ ይገባል፡፡ በተለይም እንደ መነሻ ምልክት በመሆኑ የከፋ የአዕምሮ ችግር ውስጥ ከመግባታችን በፊት የህክምና እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ በተለይም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች ትክክለኛውን ነገር ስለማይለዩት ካሉበት ችግር እስኪላቀቁ ድረስ

የቅርብ ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዓለማቀፍ ደረጃ በተካሄደ ጥናት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1996-1999 39 በመቶ የሚሆኑ ህዝቦች የአእምሮ መዛባት ችግር ሰዎች አጋጥሟቸው እንደማያውቅ ከዚህም ውስጥ 27 በመቶ በቀን ውስጥ የሚስተዋሉ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ የአዕምሮ ችግር ያለባቸው ብዙዎች በተፈጥሮ ከሚመጣው የአእምሮ መዛባት ጋር የተገናኘ ሲሆን መጠናቸው በርከት ያሉ ሰዎች ከማሽተትና ከመቅመስ ጋር የተዛባ ያለመረዳት ችግር እንዳጋጠማቸው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ በአገራችን ከሚስተዋሉት የስነ ልቦና ችግሮች አንፃር ቁጥሩን ለማወቅ የታካሚዎች የግልፅነትና የስነ ልቦና ህመሞችን መለየት ካለመቻልም ባሻገር ጠለቅ ያለ ጥናት አለመከናወኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ምርመራው ምርመራው የሚሰጠው በስነ አዕምሮ (ስነ ልቦና) ባለሙያ ሲሆን ይህም ቃላዊ (ኦራል ዲያግኖሲስ) በማድረግ የተለያዩ ቴክኒካዊ፣ ሙያዊ መጠይቆችን በማድረግ ያለፉ ታሪኮችን በማጥናት እና በማገናዘብ ሣይንሳዊ መንገዶችን ተከትሎ የሚደረግ ሲሆን የባለሙያው ምልከታዎች የታማሚውን አካላዊና ስነ ልቦናዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የማድረግ ፍተሻዎችን በማድረግ ይህ ችግር በምን እንደተፈጠረና እንዴት ሊቀረፍ

እንደሚባው ይወስናል፡፡

ምን አይነት ሕክምና አለው? የተወሰኑ ተመሳሳይ ህክምናዊ እንክብካቤዎች በተለያዩ

ምክንያቶች ላጋጠሙ የስነ ልቦና መዛባት ችግሮች የሚደረግ ሲሆን በዚህም የውስጥ የአእምሮ ህመሞች ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጠውን አይነት በሳይኮሎጂስቶች ወይም በሳይካትሪስቶች የስነ አእምሮ እና ስነልቦና የምክርና እንደየደረጃውም የማገገሚያ እንክብል መድሃኒቶችን እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ ያሉትን እውነታዎች ከተጨባጭ ሂደት ጋር ባገናዘበ በአእምሮ መዛባት ሳቢያ የተከሰተውን የምናብ ዓለም ገጠመኝ ከነባራዊ ሀቅ ጋር እንዲያገናዝቡት የማድረግ ሙያዊ እገዛዎችን ያደርጋሉ፡፡ በሌላው በኩል አንቲ ሳይኮቲክ እና ታይፒካል አንቲሳይኮቲክ በሆኑ እና በሳይንስ ተቀባይነት ያላቸውን ሃሉጄኒክ መድሃኒቶችን በመጠቀም የአእምሮ ጭንቀት መጠናቸውን ለመቀነስ፣ ጤናማ አስተሳሰብ እንዲኖራቸውና እንቅልፍ እንዲወስዳቸው የሚረዱ እንክብሎች እንዲወስዱ በማድረግ የስነ ልቦና መረጋጋት እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡ ለማጠቃለል ያህል የአዕምሮ ህመም አይነቶች ብዙ ናቸው፡፡ የተለያዩ መገላጫዎችም አሉት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዲ ሃሉሲኔሽን የአእምሮ መዛባት ችግር ነው፡፡ ሁሉም ሰው እንደሌላው በሽታዎች ምልክትነቱን ተገንዝቦ የተጠቃውን ሰው መንከባከብና ህክምና እንዲያገኝ በማድረግ ትብብር ሊያደረግ ያስፈልጋል፡፡

ቸር እንሰንብት፡፡

ሃሉሲኒሽን የተለያዩ የስነልቦና ችግሮች (የአእምሮ ህመሞች) በሚያጋጥሙበት ወቅት እንደ መነሻ ምልክትነት ይወሰዳል፡፡ ይህ የስነ ልቦና ችግር በተለያየ መልኩ የሚገለፅ ሲሆን በንቃተ ህሊና ውስጥ ያልተከወኑ ነገሮችንና ያልተፈጠሩ ሁነቶችን እንደተፈጠሩ አድርጎ አዕምሮ እንዲቀበል የሚያደርግ ሂደት ነው፡፡ የችግሩ ተጋላጮች የሚያሳዩት ባህሪ ኖርማል እንደሆነ በማሰብ ስሜታዊ ማረጋገጫቸው በሰውነት ስሜት ህዋሳቶች ሲሆኑ አዕምሮ በምናብ ያለን ነገር ልክ እንደ እውነት ተቀብሎ ምላሽ ይሰጣል፡፡ ዶ/ር ዳዊት ሲገልፁ አዕምሮአችን የራሱ የሆነ የአሠራር ዘዴ አለው፡፡ ሥራውም በነርቭ አማካይነት ይከናወናል፡፡ አንዲ ነርቭ ከሌላው ነርቭ ጋር በሚኖረው ግንኙነት በመፍጠር አጋዥ በሆኑ ኬሚካላዊ ኡደቶች እንዲታገዝ ይደረጋሉ፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲገኙ አንድ ሰው አካባቢውን በመቃኘት ያለበትን ሁኔታ በትክክክል እንዲገነዘብ ያደርገዋል፡፡ ማንኛቸውም እንቅስቃሴዎች በሚኖሩበት ሰዓት መልእክት በማስተላለፍ የነርቭና የስሜት ህዋሳት ቅንጅታዊ ሥራ እንዲኖር በማስቻል የመረዳት አቅም ይፈጥራል፡፡

አንጐላችን ከአካባቢ የሚመጣለትን መረጃ በተሳሳተ መልኩ እንዲረዳ የሚያደርገው የኬሚካሎች መጠን መዘበራረቅ ነው፡፡ ሰዎች የስሜት ህዋሳቶቻቸውን ተከትለው በሚመጡ መረጃዎች ላይ የተሳካ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሚታይ፣ የሚሰማ፣ የሚዳሰስ፣ የሚሸት እና የሚቀመስ ነገር ባልኖረበት አጋጣሚ ውስጥ እንዳለ አድርጐ አዕምሮአቸው ስለተቀበለው ቀጥተኛ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ብቻቸውን ያወራሉ፡፡ እንቅስቅሴ እና ስሜታዊ ለውጦችንም ያስተናግዳሉ፡፡ ይህን ድርጊት ከነሱ ውጭ ሌላ ሰው ሊገባውና ሊረዳው ይከብደዋል፡፡

የአንጐላችን ጤናማ አስተሳሰብ መዛባቱም ለሎች የስነልቦና ህመሞች መጋለጣችንን ጠቋሚ በመሆኑ በጊዜ ወደ ስነ ልቦና እና አእምሮ ህክምና ቦታ መሄድ ይገባል፡፡

ፎቶ ኡስማን አርት

ከደራሲና ገጣሚ መኳንንት ታዬ ሚኒሶታ በአንድ ወቅት የምድር አራዊትና

የሰማይ አእዋፋት ወገን ለወገንህ ተባባሉና ሁሉም ከእያሉበት ተጠራርተው ሲያበቁ በአንድ ችግር ላይ መወያት ጀመሩ። ይኸውም በአራዊቱ እና በአኢዋፍቱ ዘንድ ችግር እንዳለና እራሳቸውንም ማስከበር እንዳለባቸው ይመክሩ ጀመር ። በአእዋፋቱ ዘንድም አራዊቱ ዘንድ ችግር እንዳለ እና ደኑን ተማምነው ያልተገባ ነገር እያደረጉ እንደሆነ እንደሚጠራጠሩ ለዚህ ደሞ መፍትሄው ጦርነት ብቻ እንደሆነ እየተነጋገሩ እያሉ የለሊት ወፍ መጣች። ሁሉም በድንጋጤ ቢያያትም ቅሉ የማን ወገን ናት በሚል መልኩ እርስ በእርሳቸው ቢተያዩም ደፍሮ ግን ሊጠይቃት የወደደ ግን ስላልነበር እርሷም የማንነቷን ገልፃ አልተናገረችም። ብቻ ግን አንድ ነገር አስባለች፤ ጦርነቱ ሲጀመር ብዙም ወደሰማይ ከፍ ሳትል ብዙም ወደ መሬት ሳትቀርብ በረራዋን ለማድረግ።

ይሁን እና በዚህ መሃል ጉባዬው ጋር ለመገኘት የረፈደባቸው ይቅርታ እየጠየቁና ያጋጣማቸውን እየነገሩ ተቀላቀሉ። የእለቱ ፀሃይ በጣም የሚያቃጥል ቢሆንም ከህልውና የሚበልጥ የለም በሚል ይመስላል በሁለቱም ወገን ምክከሩ የአሰላለፍ አካሄዱ የ እለቱን ውሎ በሚመለከት ተነጋገሩ። ከአእዋፍ ወገን ፤ እነ- እርግብ ፤ እነ-ንስር ፤እነ -ጥንብ አንሳ እነ- አሞራ ብቻ ሁሉም ከያሉበት ተጠራርተው የመገናኘታቸውን ያህልም ፤ ጦሩን ማን ይምራ የሚለውም ነገር ብዙ ካነታረካቸው በሓላ፤ በስተመጨረሻ ንስር የጦሩ መሪ ሊሆን ተማምለው ባሉበት ሠኦት ፤ የለሊት ወፍ ፈንጠር ብላ ተቀምጣ ነበርና ፤"አንቺ የማን ወገን ነሽ?ሲል ንስር በቁጣ ቃል ጥያቄ አቀረበላት። እርሷም ፈጠን ብላ "ምን ጥያቄ አለው

ክንፌን ስታይ የማን እመስልሃለው ብላ ጥያቄውን በጥያቄ መለሰችለት። በዚህ ሁኔታ እያሉ የአራዊቱን አሰላለፍ ማን ይሰልል እያሉ አእዋፋቱ ሲነጋገሩ ይህቺው የለሊት ወፍ "እኔ ብሄድስ? ምክንያቱም ጡት ስላለኝ አጥቢ ናት እና ከእኛ ወገን ነች ብለው ስለሚያስቡ ያለውን ነገር ሁሉ በሚገባ አጤነዋለው" ብላ እንደጨረሰች የሁሉም ሃሳብ አንድ ሆነና የለሊት ወፍ ተላከች።

እዛም እንደደረሠች አራዊቱ በመልክ በመልክ ተሰብስበው ይወያያሉ። ሁሉም አሉ፤ አንበሳ ፤ ነብር አያጅቦ፤ ተኩላ እነ ዝሆን ብቻ አራዊቱ ወገን የቀረም የለ። ይሁንና በውይይታቸው መሃል እንዳሉ የለሊት ወፍ ደረሰች ። ሁሉም አፈጠጡ፤ አንበሳ ነበርና የጦሩ አበጋዝ "ምን ፈለግሽ?’’ ሲል አፈጠጠባት። የለሊት ወፍም ምንም እንዳልተፈጠረ በመቁጠር ለማርፈዷ ይቅርታ ጠይቃ ለመቀላቀል ስትሞክር አንበሳ ጠንከር ባለ ንግግር "የማን ወገን ነሽ?" ሲል አፈጠጠባት። የለሊት ወፍም ፈጠን ብላ ምን ጥያቄ አለው !

ከአራዊቱ ወገን ለመሆኔ ጡቴን ማየት ብቻ አየበቃም? ስትል በማፍጠጥ በመመለሷ ሁሉም በይሁንታ ተቀብሉዋት። ስለሚያደርጉት ጦርነት እና የቦታ አያያዝ ብሎም ማን ፊት አውራሪ እንደሚሆን እና ማን ጦር መሳሪያ አቀባይ እንደሚሆን ፕላኑን አውጥተው ከጨረሱ በሓላ ፤ አንበሳ ወደ ለሊት ወፍ ዞር ብሎ ፡አጅሪት እስቲ ሂጅና ያለውን ነገር ሰልለሽ ያላቸውን ሃይልና እና የታጠቁትን የጦር መሳሪያ አይነቱን ንገሪን አላት። መላኩ ያስደሰታት የለሊት ወፍ ስትበር ሄዳ ‘የአራዊቱን አቅም ምን ያህል ደካማና በአሰላለፍም ከኣኢዋፍቱ እንደማይበልጡ አፏን እያጣፈጠች ነገረቻቸው። በሁኔታው የተደሰቱት አእዋፍቱም በፍጥነት ጦርነቱን ቢጀምሩ አራዊቱ ካለቸው ብቃት ማነስ ጋር ተጨምሮ በድንጋጤ ሊረበደበዱ እንደሚችሉ ነግራ ፤ ለመጀመር እየተዘጋጁ ባሉበት ሰዐት ለፊት አውራሪው ንስር ጠጋ ብላ “ምንም እንኳን ሁኔታው ባይመችም ቅሉ ጦርነቱ ባሸናፊነት እንዲወጡ እርሷ ለአስር ደቂቃ ፀሎት አድርጋ መምጣት እንደምትፈልግ አሳምናው በራ ወደ አራዊቱ ዘንድ በመሄድ ለእነኛ የነገረቻቸውን ሁሉ ለእነዚህም ነግራ ጦርነቱን አስጀመረች። በሁለቱም ወገን ከባድ ውጊያ ሆነ። የለሊት ወፍም ከፍ ብላ በበረረች ግዜ ኣኢዋፍቱን በርቱ እንጂ

መጠቃታችን ነው ስትል ዝቅ ብላ አራዊቱን በርቱ እንጂ መጠቃታችን ነው፤ እያለች ቀኑን ስታዋጋ ዋለች። ከሁለቱም በኩል በጣም ብዙ ሰራዊት ወደቀ። ሬሳ በሬሳ ላይ ተደራረበ። የሚገርመው በእለቱ ከሁለቱም ወገን የጦርነቱ ሚስጠር ያልገባቸው እንዲሁ በየወገንህ ሲባል ብቻ ሰምተው የተሰለፉም ነበሩበት። ባላወቁትም የሞት ሰለባ ሆኑ። ግና በዚህ ሁሉ ምሀል ስትሽሎኮለክ የነበረችው የለሊት ወፍ የምታደርገውን ንስር ከሩቅ ሆኖ ይመለከት ነበርና ሳታስበው አደጋ ጥሎ ከሙታን ጋር ቀላለቀላት።

በዚህ ሁሉ መሃል አንበሳ በድንገት ዞር ብሎ ቢያይ የለሊት ወፍ የለችም። ከሓላው ይከተለው ለነበረው ወታደር በቁጣ “የለሊት ወፍ የታለች ?” ብሎ ጠየቀው። ወታደሩም ፈጠን ብሎ ከንስር በተጣለ ቦንብ ስትጋይ አይቻታለሁ አለ።” ለነገሩ እኔም ላጋያት ነበር የፈለኳት ብሎ ጦርነቱ እየመራ ቀጠለ። በዚህ ሁኔታ ሆዱን መሸከም ያቃተው አያ ጅቦ ከሞቱት ወገኖች መሃል የሞተውን (እርሙን) ሊበላ ወደሓላ ቀረ። ከአእዋፍቱም ወገን እንዲሁ እነ ጥንብ አንሳ ሆን ብሎ እጁን በመስጠት ከተማረከ በሓላ የሞተውን መብላት ጀመረ። በስተመጨረሻ ጦርነቱን የሰሙት የቤት እንሰሳት በገላጋይነት በመግባት “ለሊቱን ለአራዊት ቀኑን ለአእዋፋት” ብሎ አምላካችሁ ከፍሎ ሰጥቶአችሁ እያለ ውጊያው ምንን በተመለከተ ነው? ሲሉ በዝርዘር የውጊያው አላስፈላጊነት አስረዱአቸው። በሆነውም ከልብ እንዳዙኑ ገልፀው ሁሉን አሳምነው ሲያበቁ በጦርነቱ ወቅት ችግር ፈጣሪ እና ታማኝታቸውን በአቅም ማጣት ምክንያት እና በመምሰል ለመሆን የሞከሩትን ጦር ወንወጀለኞች፤ እንደ ለሊት ወፍ ያለው ከሁለቱም ወገን እንዳትገባ፤ ጥንብ አንሳና ጅብ ዜግነታቸው ተነጥቆ በቁም አስር እንዲቆዩ ተወስኖ፤ ከእንግዲህ የሰላም አገር መስርተው ሊኖሩና የጋራ ጠላታቸውን በጋራ እንደሚከላከሉ ተስማምተው ሊስታርቋቸው የመጡትንም አመስገኑ::

በስተመጨረሻም ለአስታሪቀነት ከመጡት አንዷ እመት በግ ተነስታ “እስቲ የጦርነቱን መንስሄ ከሁለቱም ወገን ብታስረ ዱን“ ስትል ሁሉንም አይን አይናቸውን እያየች ጠየቀች። በሁለቱም ወገን ይሄ ነው ብሎ ምክንያት የሚሰጣት በመጥፋቱ

አፍረው አንገታቸውን በደፉበት ግዜ አሞራ ከሩቅ ሆኖ”መሳሪያ ሻጮች ናቸው የሚያጣሉን” ሲል ሁሉም በምክንያቱ ተገርመው ሳቁ። በግም በነገሩ ተገርማ ስታበቃ ”ይገርማል የሚያፈስ ጣራ ያላት ሃገር ይዘን ብዙ ግዜ የምንጣላው ለአጥር በሚሆን እንጨት በሚደረገው ፍለጋ ስለሆነ ነው። ነገር ግን መጀመሪያ መቅደም የነበረበት ጣራን መሸፈን ነው ወይስ አጥር? ብላ ሁሉንም አፍጣ ጠየቀች። ሁሉም በአንድነት አሱማ ጣራ ይቀድማል አሉ። አዎ አንዲህ ስላችሁ አጥር አትጠሩ ማለቴ ሳይሆን ከጦርነት በፊት ለምን የሚል ቃልና ትርፉስ የሚለውን አስተሳሰብ አትርሱ። በማለት የእለቱን የማስታረቂያ ንግግር ስታደርግ ሁሉም ተመስጠው በመስማት አድንቀው ሲያበቁ ከዚህ በሓላ ስለሁሉም በማሰብ ስልጣኔን አየር እየዛቁ ለሃገር ለወገን በሚሆን ነገር ላይ በማተኮር ዘመናቸውን እንደሚኖሩ ተነጋግረው ተሳስመው ተለያዩ።

ቸር እንሰብት

መድሃኔዓለም... ከገጽ 1 የዞረ

ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል። ውድድሩ በስኬት መጠናቀቁንና ማህበረሰቡን በማቀራረብ

ደረጃ ዓይነተኛ ሚና እንደሚቻወት የገለጹት አንዳንድ በውድድሩ የተሳተፉ ወገኖች ይህ የሩጫና የርምጃ ውድድር በኢትዮጵያውያን በሚኒሶታ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ በመሆኑ ወደፊትም እንዲለመድና እንዲቀጥል ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ “በሃገራችን ታላቁ ሩጫ እየተባለ በየዓመቱ ይደረጋል። በሚኒሶታም በመድሃኔዓለም ቤ/ክ አማካኝነት ይህ መጀመሩ የሚያስደስት ነው። ኢትዮጵያውያንን የሚያቀራርብ ሩጫ በመሆኑ የየትኛውም እምነት ተከታዮች በመምጣትና አብሮ በመሮጥ ውድድሩን ወደፊት ትልቅ ማድረግ ይቻላል” ሲሉ ተናግረዋል።

“በዚህ ሩጫ ላይ በመሳተፌ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው የመታሁት” የምትለው ወጣት ደግሞ “ከማላውቃቸው ወገኖቼ ጋር የመተዋወቅና አብሮ በመሮጥም እህትና ወንድሞች እስከማፍራት ደርሼበታለሁ። ይህን ውድድር አስበው ላዘጋጁትም ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ” ብላናለች።

አሜሪካንን... ከገጽ 23 የዞረ

በየተራ እየተመለከትኩዋቸው… ቀለብለብ የምትለው… “ስራ ምን ያደርጋል…” እንዴ ታዲያ እንዴት ትኖራላችሁ ? አልኩዋት በግርምታ… “እነ ቢልዬ…ኪርዬ እና ራይድዬ የት

ሄደው…” ማሙዴ ሳቁን ለቀቀው… አልገባኝም አልኩዋት… ማሙዴ ፈጠን አለ… “ኪርዬ ቤት ኪራይ ይከፍላል…ቢልዬ ቢል

ይዘጋል…ራይድዬ ደግሞ የተፈለገበት ቦታ ያደርሳል ይመልሳል…ያመላልሳል…”

በድጋሚ ሳቁን ለቀቀው… እኔ እና ጉዋደኛዬ በ አግራሞት ተያየን… “አሁንስ ገባሽ ጀለሴ…” አለኝ… አሁንም አንገቴን ነቀነቅኩለት። ማሙዴ ተቁነጠነጠ … “በቃ ፍሬንዶች ስልካችሁን ይዣለሁ

እደወልላችሁዋለሁ አሁን እቸኩላለሁ…” ብሎን ጥሎን እብስ አለ። እኛም ሰአታችንን ተመለከትን ልጆቹን

ተሰናብተናቸው ወጣን። ዩ ስትሬትን እየተዙዋዙዋርን ቃኘን። የሚያሳሱ አንዳንድ ፍሬ ልጆች በአስራዎቹ እና በሃያዎቹ መግቢያ የሚገኙ ወጣቶች ይተራመሳሉ ከክለብ ክለብ…ከቦታ ቦታ ከሰው ሰው ይቀያየራሉ ይራወጣሉ ይጋፋሉ …ያጩዋጩሃሉ…ይጠራራሉ…ይሰዳደባሉ። ፖሊስ እዛም እዚም መብራት እያበራ ሳይረን ያሰማል። የሃገሬ ህዝብ ነቅሎ መጥቶዋል አልኩት ለጉዋደኛዬ።

በነገራችን ላይ ዲሲ እና አካባቢዋን የቃኘሁበት ጽሁፍ በዚህ አያበቃም ስለሁለተኛው ሳትለን ስለሶስተኛው አትበሉኝ እና በቅርብ ለንባብ ከሚበቃው መጽሃፌ በሁዋላ የሚከተለው ሶስተኛው የመጽሃፌ ክፍል “አሉንባኮት” የትኩረት አቅጣጫው አሜሪካ እና የስደት ህይወት በሃበሻውያን ላይ አጠቃላይ ሁኔታ ዙሪያ በመሆኑ እመለስበታለሁ።

ግን ግን ዩ ስትሬትን እና 9 ስትሬትን ስመለከት በ እውነት ነው የምላችሁ ካዛንቺስ ከነ አቡዋራዋ ትምጣብኝ ብያለሁ በቃ ቁርጥ የ አዲስ አበባውን ቺቺኒያ። እንዳውም ካዛንቺስ እና ቺቺኒያ ምስጋና ይጡ። ይሄን ብቻም አይደለም የሃገሬ ህዝብ እንደዚያ በተዘበራረቀ ባልተጠበቀ የ አኑዋኑዋር ሁኔታ ውስጥ ሳየው የኮሜዲያን ደረጀ ሃይሌን የሞባይል ቀልድ አስታውሼ እኔም ተበታትነናላ…ተበታትነናላ እያልኩ ከጉዋደኛዬ ጋር ወደማረፊያችን ወደ ሜሪላንድ ኮሌጅ ፓርክ እብስ

አልን። ሰላም።

ሳቅ በሳቅ የምታደርጋችሁ አርቲስት ትዕግስት ንጋቱ

ሚኒሶታ በመምጣት የምትተውንበት “ፍሬሽማን”

ትያትር ሚኒያፖሊስ ኦግስበርግ ኮሌጅ ኦገስት 10 እና ኦገስት 11

2013 ይታያል። እንዳያመልጣችሁ።

ለበለጠ መረጃ፡ 612-226-8326

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page

Ethiopian Community in

Minnesota (ECM)

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሚኒሶታ

ከዳንኤል ገዛኽኝ በአትላንታ የዘ-ሐበሻ ወኪል ለኢትዮጲያ የስፖርት እና የባህል ፌዴሬሽን ምስጋና

ይግባው እና በአንድነት እያሰባሰበ በየ አመቱ ደስ የሚል አይነት ትዝታ ያለው አጋጣሚ እንድናሳልፍ። በተለያዩ ስቴቶች እንዲሁም በተለያዩ አህጉሮች ከሚገኙ ከናፈቅናቸው…ከናፈቁን ጋርም እንዲሁ ተገናኝተናል። ይህ እንዲሆን ደግሞ ስለሚያደርገን በድጋሚ ፌዴሬሽኑን እናመሰግነዋለን ከነ ችግሮቹም ቢሆን።

ዘንድሮ እንዳለፉት አመታት ሁሉ ከሙያ ጉዋደኛዎቻችን ጋር ደስ የሚል አጋጣሚ አሳልፌያለሁ። የሆነው ሆኖ ለዲሞክራሲያዊትዋ ሃገረ-አሜሪካ ምስጋና ይድረሳት። ይህቺ ሃገር ዲሞክራሲያዊት ባትሆን ኖሮ በዲሲ የተመለከትኩት የሰዎች ህይወት እውን ባልሆነ ነበረ። ያም ሆኖ ግን በ ኢኮኖሚ የአለም መሪ በምትባለው በዚህች ሃገር በ አሜሪካ የመንግስትዋ መቀመጫ በሆነችው ግዛት በዋሽንግተን የተመለከትኩት ህይወት በጣም አሳዛኝ እና ስሜት የሚያደፈርስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በተለይም ደግሞ የዚህ ጽሁፌ የትኩረት አቅጣጫ የሚሆነው የዋሽንግተኑ ዩ ስትሬት የ ኢትዮጲያውያኑ ኑሮ ልቤን በሃዘን ሞልቶት ሃዘኔን አብዝቶታል በ እውነት ውስጤ አልቅሶዋል። እንደ እኔ እሳቤ ነው አካባቢው ከመጨናነቁ የተነሳ ነው መሰል በ ፊደል አልፋ ቤት እና በቁጥሮች የተሰየመ ነው አካባቢው። ከሁሉ ሁሉ ግን 7ስትሬት…9ስትሬት እንዲሁም ዩ ስትሬት አካባቢ የሚታየው የምሽት ትዕይንት አስገራሚ ነው።

በአካባቢው የ ኢትዮጲያውያን መዝናኛዎች እና ምግብ ቤቶች በርከት ብለው ይታያሉ። በተለይም ማራኪ…ሃበሻ…ዱከም ሬስቶራንት ከሁሉም ደንበኛ ያላቸው እና ግርግር የሚበዛባቸው ናቸው። ሌላው 7 ስትሬት እና 9 ስትሬት አክባቢ በስፋት ያሉት የሺሻ ዲጄ ምሽት ቤቶች ናቸው። ሙዚቃው በአጫዋቹ በዲጄው ይቀልጣል የሚደንሱ አጫጭር ቀሚሶች የለበሱ ሴቶች እና ወንዶቹም በተመሳሳይ ከሰውነታቸው ላይ የተጣበቁ ጂንስ ሱሪ አብዛኛዎቹ በተመሳሳይ የለበሱ ጥንድ ጥንድ አንዳንድ ጊዜም በቡድን እየሆኑ ጭፈራውን ልበለው ዳንሱን ያስነኩታል።

የኢትዮጲያውያንን ቀን ጁላይ 5 በበርድ ስታድየም ካከበርን በሁዋላ ያመራነው ወደ ሜሪላንድ ጆርጂያ ጎዳና ላይ ወደሚገኘው አንድ ታዋቂ ሬስቶራንት ነበረ። በዚያ ሬስቶራንት ሞገስ መብራቱን እና ከዝነኛዎቹ ደግሞ እንደ ኤሊያስ ተባባል አይነት ታዋቂ ድምጻዊ ከ አንድ ኪቦርድ ጋር ተቀናጅቶ ማሲንቆውን እየገዘገዘ ከመድረኩ ላይ ቆየት ያሉ ዜማዎቹን ይጫወታል። ሞገስ መብራቱ በድምጽም በኪቦርድ ተጫዋችነትም ያጅባል።

ሌሎችም ብዙ ታዋቂ ያልሆኑ ድምጻዊያን የምሽቱን ታዳሚያን ያዝናናሉ። ሆኖም ግን በድምጻዊያን አካባቢ በተለይ በሃገራችን በውጪም ሲኖሩ ሆነ በሃገር ቤት አንድ የተለመደ ነገር አለ። ባለሞያው ህይወቱን የሚመራበት ከሙያው ውጪ የሆነ ቢዝነስ በመክፈት ታላላቅ መድረኮች ላይ ሲጋበዝ ስራዎቹን ማቅረብ እና አመታቶችን ጠብቆ አዳዲስ ስራዎችን በአልበም መልክ አሳትሞ ለአድማጭ ማቅረብ ሲሆን ይህ ሲሆን ታዲያ በየምሽት ክለብ መጫወት ያቆማል ማለት ነው። ነገር ግን ገቢው ካልተሻሻለ የራሴ የሚለው ነገር ከሌለው ግዴታ ምሽት ክለቦች እየሄደ እየተጫወተ በሚያገኘው ገቢ ኖሮውን ይደጉማል ማለት ነው። አንጋፋውን የራስ ቲያትር ቤት ያፈራውን ድምጻዊ ተወዳጅ እና ቁምነገር አዘል ስራዎች በመስራት የሚታወቀውን ኤሊያስ ተባባል ዛሬም እንደ ጥንቱ ማሲንቆ እየገዘገዘ መጠጥ እየጠጡ ለሚዝናኑ ሰዎች በአንድ ተራ ምሽት ቤት ሲያቀነቅን ሳየው በ እውነት ስለ ሃገራችን ድምጻዊያን አዘንኩ። እርግጥ ነው ድምጻዊያኖቻችን ደረጃቸው እና ገቢያቸው ሁሉ ነገራቸው ይለያያል። ቢሆንም ኤሊያስ ግን አሳዘነኝ። ቢሆንም ህይወት ነው እና ምን ይደረግ።

ስንቅነሽ ከሚባለው የሜሪላንዱ የሃበሻ ሬስቶራንት በ አስጎብኚያችን ማሙዴ አማካኝነት ወደ ዋሽንግተን ዩ ስትሬት በረርን። ማሙዴ ጨዋታ የጀመረው ከምንጉዋዝበት የ2014 ፎርድ-ቶሬዝ መኪና በመጀመር ነው። ማሙዴ አይፎርሽም ያለማቁዋረት ያወራል። ንግግር ከጀመረ አያቆምም።

“ይሄን የመሰለ ዘመናዊ የልጥጥ መኪና ይዘህ አይደለም ካምሪ እንኩዋን ብትነዳ ተከታይህ ብዙ ነው እንዴ ጀለሴ እንዳው ለመድሃኒትም ቢሆን አንድ ቺክ መጫን ነበረባችሁ

ወይ ፍሬንዶች ተሸውዳችሁዋል በጣም ትገርማላችሁ…” የማሙዴ ነገር እኔንም ጉዋደኛዬንም አስፈገገን። መካከለኛ ቁመት አለው ጠቆር ይላል…የፊት ጥርሶቹ

መበለዝ ብቻም አይደለም ተሸራርፈዋል። የጥርሶቹ መበለዝ ታዲያ የናዝሬት የአዋሳ የመተሃራ ልጆች አይነት ከለር አይደለም ጠይቄዋለሁ “ሲጋራ እና ጫት ነው” የሚል መልስ ሰጥቶኛል። የት እንደሚሰራ ጠየቅኩት ማሙዴ ሊያወራ ሲል ሳቅ ሳቅ ፈገግ ፈገግ ይላል እንደልማዱ ሳቅ እያለ ንግግሩን ቀጠለ…

“ባይገርምሽ እኔ ከአምስት በላይ ዲግሪዎች አሉኝ…” ሲለኝ አቁዋረትኩት እና የምን ዲግሪ ነው ይሄ ሁሉ ?… ማሙዴ አሁንም ሳቅ አለ… “የውልሽ እኔ ሸራተን ሆቴል ውስጥ የታወኩኝ ሃውስ

ኪፐር ነኝ በጣም ይወዱኛል የየ አመቱ ኮከብ ተሸላሚ ነኝ ከአምስት አመት በላይ ሰሰራ በየ አመቱ ኮኮብ ተሸላሚ እየተባልኩ እሸለማለሁ በተሸለምኩ ቁጥር ሆቴሉ ዲግሪዬን ይሰጠኛል…”

ታዲያ እሱ እኮ የ እውቅና ወይንም የምስጋና በለው ወይ ደሞ ለስራ ልምድነት የሚያገለግል ወረቀት ነው እንጂ ዲግሪ ይባላል እንደ ?

የኔ ጥያቄ ነበረ… “ሞኝ ነሽ መሰለኝ ! ያው እኮ ነው እንዳውም ከዲግሪም

በላይ ነው እሱን አሳይቼ ዲግሪ አለን ከሚሉ ሰዎች በላይ በተፈላጊነት እቀጠራለሁ…”

አሁንም እየሰራህ ነው ? “አሁን እንኩዋን አቁሜያለሁ” ለምን አቆምክ? አስከትዬ ጠየቅኩት… “ሃገሬን ማየት ፈልጌ ነበር እና ፍቃድ ሰጡኝ

አልኩዋቸው አንፈቅድም አሉኝ ትቼላቸው ወጣሁ…” ታዲያ ሃገር ቤት ሄድክ ? “አይ በቅርቡ እሄዳለሁ…አሁን እዚህ ስታድየም ውስጥ

ከሃይሌ ኩዋሴ ጋር ቢዝነስ እየሰራን ነው በቅርቡ ሃግሬን ሄጄ አይቼ እመለሳለሁ…”

ማሙዴ ደስተኛ ቢጤ ነው ምንም የሚያስጨንቀው ነገር እንደሌለ ነው ሁኔታው የሚያሳብቅበት። አስከትዬ ጥያቄ ወረወርኩለት።

ግን እንዴት ነው እነዚያ ዩ ስትሬት አካባቢ ያየሁዋቸው ሰዎች ወጪ የሚኖሩት ?

“ምን ምርጫ አላቸው አንዳንዱ የገቨርንመንት እርዳታ ጥሞት የሚኖር አለ ሌላው ደግሞ ከምኑም የሌለ አለ በቃ አይተሃቸዋል አይደል በጣም ያሳዝናሉ በይበልጥ ደግሞ ከ9 እና ከዩ ስትሬት የትም አይሄዱም እዛው ናቸው በቃ እዛው ይፈልጣሉ…እዛው ይቀፍላሉ እዛው ለሽ ይላሉ…”

አልገባኝም ? አልኩት… “ነፍሴ ሳይሽ ሃሪፍ ነገር ነሽ ወይንስ አውቀሽ ፋራ

ለመምሰል ነው በቃ አይገባሽም እንዴ እዛው እየለመኑ እዛው ያድራሉ ላይፋቸው ይሄ ነው…ያረጁትን ያቺን አሮጊትዋን አይተሃታል ሼባውንም አይተኽዋል ሼባው እንዳውም ዲግሪ ሁሉ አለው እንዳውም አንተ ከመጣህበት ስቴት ነው ወደ ዲሲ ሙቭ አድርጎ እዚሁ በድራግ እና በመጠጥ ህይወቱ ተበላሽቶ ዩ ስትሬት የወደቀው…ወጣቶች አሉልህ 24…27 ዓመት የሚሆናቸው ወላ ሴቶች ወላ ወንዶች እንዴት ያሳዝኑሃል መስለህ…”

አለ እና አንገቱን ነቀነቀ። “ግን ጀለሴ ይህንን ሁኔታ አይታችሁ ዝም አትበሉ እስቲ

ኮምዩኒቲው ዜጎቹን ከዚህ እንዲያወጣቸው የበኩላችሁን ትረት አድርጉ…እዚህ ማንም ስለማንም አይገደውም…”

ማሙዴን ቀስ ብዬ አየት አደረግኩት። ፊቱ ክስል ብሎዋል በጣም ጠቁሮዋል ድምጹ ዝግትግት ያለ ነው። ድምጹ ከተፈጥሮው ለወጥ ያለ መሆኑ ያስታውቃል ይሄ ደግሞ መጠጥ ዕና አንዳንድ ነገር ከማዘውተር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገምቻለሁ። መኪና ውስጥ ባለማጨሱ ተጨናንቆዋል ብዙ ረጅም ባይባልም ከ አርባ ደቂቃ በላይ መንዳት አለብን ዩ ስትሬት ለመድረስ።

ማሙዴ ጨዋታው የሚያልቅ አይደለም…እንዲያው ግን ማሙዴ ይቅርታ አድርግልኝ እና ቨርጂኒያ…ሜሪላንድ…ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እንዳው እንደ ናሙና ስታያቸው እንዴት ነው ምን ይመስሉሃል ላንተ ?

አልኩት… ማሙዴ እንደ ልማዱ ፈገግ… ሳቅ አለ እና…ንግግሩን

ቀጠለ… “አባ ምን እንዳለ ታውቂያለሽ ሜሪላንድ አካባቢ እንዳው

ለኩዋሱ ከመጣው ከ እንግዳው ህዝብ ባሻገር ስታያቸው በ እድሜገፋ ያሉ ሴቶች እና ወንዶች የተሰባሰቡበት ነው…ቨርጂኒያን ደሞ ስታያት እዚያ ያሉት በአብዛኛው የተማሩ ምሁራኖች…አርቲስቶች…ታዋቂ ሰዎች የተሰባሰቡበት ነው…ወደዲሲ ስትመጣ የኔ ቢጤዎች ችሰታዎች የሚበዙበት ነው… ብዙዎቹ ህይወቱን የሚወዱትም የማይወዱትም የተማረሩ ዲሲን እንዴት ብለን እንልቀቃት የሚሉ ከሃገራቸው ከሃያዎቹ አመታት በፊት ወጥተው ወደሃገራቸው እና ወደ ቤተሰቦቻቸው ዞረው ማየት ያቃታቸው ናቸው። ምክንያቱም ዲሲ ጠዋት ማታ ጭፈራ ጠዋት ማታ መጠጣት መዝናናት የሚበዛባበት አካባቢ ነው…ባይገርምሽ መንግስቱም ይህንን ሁኔታ ያወቃል መኖሪያ ቤቶቹ እንኩዋን የተጨናነቁ እና አንድ ክፍል ውስጥ ለአራት ለአምስት ነው የሚኖሩባቸው ይሄ የሆነው ደግሞ ኑሮ ውድም

ስለ ሆነ ነው…” የ ማሙዴ አገላለጽ ግምገማው አስገራሚ ነው።

እንደምንም ከግማሽ ሰአት ያላነሰ ጉዞ አድገን ዲሲ ከተቃጠለው ሰፈር ደረሰን። ሆኖም ግን መኪናችንን ፓርክ የምናደርግበት ቦታ አጥተን ቦታ ፍለጋ ስትሬቶቹን ሁሉ ስንዞር ቆየን። የአካባቢው ፖሊስ ስራ በዝቶበታል። በድንገት ታዲያ መኪናችንን እንዳቆምን አንድ ለየት ያለ ቀልባችንን የሚስብ ጉዳይ አጋጠመን። አንድ የሰው አካል ከመንገዱ ጥቂት ሜትሮች ወጣ ብሎ ተመለከትን ሰውየውን ጠጋ ብዬ ተመለከትኩት። በትክክል እንቅልፍም አይደለም ሰውየው እስከ ወዲያኛው አሸልቦዋል። ዝርግትግት ብሎ ወድቆዋል። ከኛ እይታ በሁዋላ ለአካባቢው ሰዎች ለሚዝናኑት ሁሉ ብዙም ትኩረት ያልሳበው የወደቀው ሰው ወዲያው የፖሊሶችን ትኩረት ሳበ እና ፖሊሶች ከበቡት። አክባቢው ከነበረው ትርምስ የበለጠ በትርምስ ተሞላ። እኛም ብዙ አልቆየንም ቦታውን ተተን በአስጎብኚያችን በማሙዴ መሪነት ወደ ማራኪ አመራን።

ማራኪ ጠባብ ቤት ነች። ነጭ ሸሚዝ እና ጥቁር ሱሪ የለበሱት አስተናጋጆች አቅላቸውን እስኪስቱ ከወዲያ ወዲህ እያሉ ባልኮኒ እና በተለምዶ ባለጌ ወንበር እያልን የምንጠራው መቀመጫ ላይ የተቀመጡ ደንበኛዎቻቸውን ያስተናግዳሉ። ብዙዎቹ ባልኮኒውን ታኮ ባለው ባለጌ ወንበር ላይ ሆነው ሺሻ ወይንም ሁካቸውን ያንቦለቡሉታል ከእያንዳንዱ አፍ የሚወጣው ባለ ረጅም ጭስ እየወጣ እየሄደ ይበተናል። የኔም ሃሳብ ከጭሶቹ ጋር እየተከተለ ብትን ይላል። ሆ! አልኩ ለራሴ የሰውም ሃሳብ እንደዚሁ ብትን ይላል አልኩ ለውስጤ።

“ያቺውትልህ ያቺውትልህ…የምታሳዝን የሃያ አራት አመት ወጣት ናት መንግስት ይረዳታል ግን በቃ ኑሮዋ እዚሁ ዩ ስትሬት አካባቢ ነው ያጠመደ ሰው ከናይን ስትሬት እና ከዩ ስትሬት አያጣትም ታሳዝናለች…”

ማሙዴ የረሳው ነገር እንዳለ ሁሉ ከደረት ኪሱ የተጨማደደች የሲጋራ ፓኮ …ከሱሪ ኪሱ ደግሞ ላይተር አውጥቶ ከፓኮው የመዘዛትን ሲጋራ ከ አፉ ጫፍ ለጎማት እና አቀጣጠላት። ሲጋራዋን አከታትሎ ምጎ በ አፉ የሳበውን ጭስ ሙሉ ለሙሉ አውጥቶ ሳይጨርስ በችኮላ መናገር ጀመረ…

የ ኔ አይን አንዴ ከማሙዴ አንዴ ዥንጉርጉር የተጨማደደ ቀሚስ ለብሳ ቀይ ትልቅ ቦርሳ ከትከሻዋ ላይ ካንጠለጠለችው ልጅ ላይ አነጣጥራለሁ። ጆሮዎቼ የማሙዴን ንግግር እየተጠባበቁ ነው…ልጅትዋ ከጭኖችዋ ላይ ከተንጠለጠለችው የተጨማደደች ቀሚስ በታች ጥቁር ታይት ሱሪ ለብሳለች በቀኝ እጅዋ ተጭሳ ግማሽ የደረሰች ሲጋራ በጣቶችዋ ሰክታለች…ጠባብዋን ማራኪን አቁዋርጣ ወደ አነስተኛዋ ፎቅ ዘለቀች።

ሌሊቱ ተጋምሶዋል ታይተው ገብተው…ወጥተው የማያልቁ የሰከሩ…የሚጣደፉ…የሚጉዋተቱ የሚያማምሩ ወጣት ሴት እና ወንዶች ይታያሉ ብዛታቸው አይጣል ነው። አንድ ወጣት ሴት ቀልቤን ሳበችው የትነው የማውቃት በሚል ሃሳብ ተወጠርኩኝ። አዎ አወቅኩዋት በ አንድ ወቅት በቴሌቪዥን ድራማዎች የማውቃት ወጣት አማተር ተዋናይት። ከቲቪ እይታ ከጠፋች ቆይታለች። ወይ ዲሲ ወይ አሜሪካ ውጣ አስቀርታት ነው አልኩ በውስጤ። አይታዬን ከወዲያ ወዲህ ቀጠልኩ… በአንድ ወቅት በአንድ በተለያዩ የሙዚቃ ክሊፕ ውስጥ የታየች በሞዴሊስትነት ትሰራ የነበረች ሌላ ወጣት ነይልኝ…ነይለት በሚለው የዘፈን ክሊፕ ከማውቃት የበለጠ በግንባር አውቃት የነበረች ወጣት ሞዴሊስት…አንድ ወጣት ወንድ እጅዋን ይዞ እየጎተታት ማሙዴ እንደነገረኝ ከማራኪ ባር ውስጥ ካለው የሺሻ እና የዲጄ ጭፈራ ከሚቀልጥበት አነስተኛ ፎቅ ደረጃ እየወረደች ከጭኖችዋ ላይ ከተጣበቀው ቁምጣ ጋር አየሁዋል። የሚጎተታትን ወጣት እየተከተለች ከማራኪ ወጣች።

እውነት ነው የምለው ብዙ ሰዎች ተመለከትኩኝ። ግን በተለየ አለም ውስጥ ናቸው ያሉት። ማሙዴ ጨዋታውን ቀጥሎዋል።

“ታውቂያለሽ እኔ ራሴ ሃያ አመታት አስቆጥሬያለሁ አሁን ግን ወስኛለሁ ሃግሬ መሄድ አለብኝ በቃ ዲሲ አልለቅ ብላኛለች አሁን ግን እፋታታለሁ…”

አልወለድክም ?…አላገባህም ?… አከታትዬ ጠየቅኩት… “እንዴት ያለች ሚስት አለችኝ መሰለህ ሚስቴ ነጭ ነች

ከወደ ሚሺጋን ነች ግን አልወለድኩም መውለድ አትችልም እስዋ ምክንያቱም ማይሌጅዋ ሄዶዋል…”

አነጋገሩ ግራ (አሜሪካንን... ወደ ገጽ 23 የዞረ)

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያኑ ካሳንቺስ

ድንገተኛ አይንዎን ከአደጋ ይጠብቁ

በቸልታ ወይም ባለማወቅ ከአይንዎ ላይ በምትደርስ ትንሽና ቀላል አደጋ ነገሩን አድበስብሰው ሊያስቀሩት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ለወደፊት የአይንዎ መዳክም ወይም መሰል ህመም መሰማት ለወደፊቱ እይታዎ እክል መግጠም አስተዋፅኦ ሊኖረው እንደሚችልስ ያውቃሉ? እንግዲያውስ በአደጋ ጊዜ ምን አይነት እንክብካቤ ማድረግ እንደሚችሉ ከወዲሁ ይወቁ፡፡

አይንዎ ውስጥ ኬሚካል ከገባ ለ15 ደቂቃ ያህል ለሰስ ያለ ውሃ በጣትዎ ያፍሱበት፡፡ አይንዎንም ፈፅሞ አይሹት፡፡

አይን፣ ከተጠነቆለ፣ ከተወጋ ግን ይህን መንገድ ይከተሉ - በጀርባዎ መንጋለልና መተኛት - ለመረጋጋት መሞከር - አይን ውስጥ የገባው ነገር እዚያው ውስጥ ካለ ለማውጣት አይሞክሩ፣ ይታገሱ፡፡ - የጭንቅላት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ያድርጉ - በአይንዎ ላይ ምንም አይነት መጫን እና ማሸትን ሳያደርጉ ወደ ሐኪም መሄዱ ይመረጣል፡፡

ይህን እንዲያውቁ የአዕምሮ ውጥረትና ጫናን

ማስወገድ ቢፈልጉ የህይወታችን መዘውር ጫናና ውጥረት እንደሚፈጠርበት ጥርጥር የለውም፡፡ ግን አንዳንድ ሰዎች ከሌሎቻችን በተሻለ መልኩ ለምን ውጥረትን መቋቋም ቻሉ? ተመራማሪዎች ቀለል ያሉትን የመቋቋሚያ ዘዴዎች እንዲህ ጠቁመዋል፡፡ - በአእምሮ ውጥረትና ለመቋቋም ከማስብዎ በፊት ረጋ ብለው ቅድሚያ ስለሚሰጡት ነገር ያስቡ፡፡ በህይወትዎ ውስጥ አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው? ልጅ ማሳደግ፣ ወላጆችዎን መጦር፣ ቤት መግዛት፣ ለብቻዎ ጊዜ ማሳለፍ ወይስ ትምህርትዎን የማጠናቀቅ አላማ? - በመቀጠልም ጭንቀትዎ ምን እንደሆነ መወሰን ይችላሉ፡፡ ውጥረቶች እንደየሰዉ ይታያሉ፡፡ ተስፋ የቆረጡበትን ሰዓታት ያስታውሱ፡፡ ወደ ከባድ ችግር የጣልዎ ጊዜስ መቼ ነው? ደክሞዎት፣ እርቦዎት፣ ደብሮዎት ወይም ሀሳብዎ ተበታትኖ ቀረ? እነዚህን ጥያቄዎች በተቃራኒው ይውሰዷቸው፡፡ እናም ለመዝናናት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ራስዎን ይጠይቁ፡፡ ሰውነትዎ ምን ያስፈልገዋል? አዕምሮዎ ምን? - ከባድ ፈተና ራስን መንከባከብ ነው፡፡ እርዳታ ሊያስፈልግዎ ይችላል፡፡ ቤተሰብዎ፣ ባልደረቦችዎ፣ ጎረቤትዎ፣ ወይስ ጓደኛዎ? ለሰዎች ችግርን መተንፈስ ስሜትን ያቀላል፡፡ ከማን ጋር እንደሚወያዩ ከአሁኑ ያስቡበት፡፡ - የሰው ልጅ የማወቅ ጉጉት ያለው ፍጡር ነው፡፡ ሌላኛው የጭንቀት መሸተኛ ደግሞ መማር ነው፡፡ ትምህርት መማር፣ መፅሐፍት ማንበብ፣ ድሪገፆችን መጎብኘት ከሌሎች ሰዎች ጋር በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ወይም መከራከር ሀሳብዎን ያስረሳዎታልና ችላ አይበሉት፡፡

ጥቂት ስለውፍረት የሰዎች አካላዊ ውፍረት ሶስት ገፅታዎች ሲኖሩት፣ ለቁመት ያልተመጠነ ክብደት፣ በወጣትነትና በታዳጊነት ዕድሜ የሚከሰት የቦርጭ አደገኛ ውፍረትና የወገብ ወይም የመቀነትዎ ዙሪያ ያለመጠን መስፋት ናቸው፡፡ የሰውነት ክብደትዎ ለቁመትዎ መመጠኑን ወይም አለመመጠኑን ለማወቅ ‹‹ቢኤምአይ›› የሚባል አሀዝ መጠቀም ይቻላል፡፡ በፊት ከነበረዎት የወገብ ስፋት በሶስት/በአራት ሳንቲ ሜትር ጨምረው እንደሆነ ለምሳሌ የበፊቱ 45 ሳንቲ ሜትር የአሁኑ 50 ሳንቲ ሜትር ከሆነ በእርግጥም በአደገኛ ፍጥነት መወፈር ጀምረዋል ማለት ነው፡፡

ምን እንመገብ?

የአምስቱ ምግቦች ምስጢር - እንጆሪ፡- ዝቅተኛ የስኳር መጠንና ከፍተኛ የፋይበር ይዘት አላቸው፡፡ የእንጆሪ ዘሮች በምርምር እንደተረጋገጠውም የማስታወስ መጠንን ይጨምራል፡፡ ፀረ-ካንሰር የሆኑ ንጥረ ነገሮችም አሉት፡፡ - ሽንብራ፡- ይህ ደግሞ በዳይቨር ንጥረ ነገር የበለፀጉ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የስኳር ህመምና የደም ግፊትን በመከለካልና የአጥንት ካንሰርን በመዋጋት ተጠቃሽ ነው፡፡ - ለውዝ፡- ለልብ ህመምና መድከም ከ50 ፐርሰንት ድረስ የመከላከል አቅም እንዳለው ይነገርለታል፡፡ በሳምንት ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እንዲመገቡት ይመከራል፡፡ - ሳልመንና ሌሎች የአሳ ዝርያዎች፡- አሳ እርጅና ተዋጊ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ እንደ ሳልመን፣ ተስሮዲንና የማካፈላ ዝርያዎች ትልቅና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘውን ኦሜጋ-3 ይዘው ይገኛሉ፡፡ በቀላሉ ድብርትን በማጥፋትና ስሜትን በመቀየራቸው ይነገርላቸዋል፡፡ - ቀይና ነጭ ሽንኩርት፡- አያሌ ጥናቶች እንደሚመሰክሩላቸው ከጨጓራ፣ የወንዶች መራቢያ አካላትና የመተንፈሻ አካላት ካንሰር በመከላከል ወደር የላቸውም፡፡ በልብ ህመም የሚመጣን ሞት በ2006 ይቀንሳሉ ከሚባሉት የምግብ አይነቶችም የመጀመሪያዎቹ ናቸው፡፡

ትኩረት እንክብካቤ ለፀጉርዎ

- የአመጋገብም ሁኔታ የፀጉርዎን ጤንነት ይወስነዋል፡፡ - ውሃ፣ ባዮቲን፣ ቫይታሚን ኤ፣ ቢ6፣ ቢ12፣ ሲ፣ ኦሜጋ 5 ፋቲ አሲድ፣ ዚንክ፣ ካልሺየም፣ ፋሲክ አሲድ እና ማግኒዚየም ጤነኛ ራስ ቅልና ፀጉር እንዲኖርዎ ስለሚያደርጉ ጠቃሚ ናቸው፡፡ - የፀጉርዎን ቅባት ሲቀቡ በጣቶችዎ ውስጡን ይሹት፡፡ ይህም በራስ ቅልዎ ውስጥ እንዲዋሃድ ያደርገዋል፡፡ - ፀጉርዎን በጥንቃቄ ማበጠሩ የፀጉርዎን ቀዳዳ የደፈኑትን ቅባቶች ይሰባብራል፡፡ ጠዋት ጠዋትም የራስ ቅልዎን ህመም እንዳይሰማዎ በማድረግ በጥንቃቄ መልኩ ያበጥሩ፡፡ - ከፍተኛ የሆነ ንፋስና የፀሐይ ሙቀት ፀጉርዎን እንዳያገኘው ይጠንቀቁ፡፡ - ጠበቅ ያሉ ኮፍያዎች በራስ ቅልዎ ውስጥ የሚካሄደውን ስርዓት ለማስተጓጎል ላብና ቆሻሻ እንዲከማች ያደርጋሉ፡፡ - ህይወትዎ ውጥረት የበዛበት ከሆነም አንዳንድ ሁኔታዎችን ከአሁኑ ያስተካክሉ፡፡ ከፍተኛ ውጥረት ፀጉርን መሳሳትን እንደሚያፋጥን ይታመናል፡፡ - የፀጉር ቀለም ይቀባሉ? መጠኑን ቢያንስ በ2 ወራት አንድ ጊዜ ያድርጉት፡፡ ፀጉርን ቀለም መቀባት የፀጉርን ውበት በተወሰነ መጠን ማውደም እንደሚችል የተረጋገጠ ነው፡፡ - ፀጉርዎ ላይ ጫና አያብዙበት፡፡ ሲያበጥሩ በጥንቃቄ ይሁን፡፡ ሴቶችም ሁል ጊዜ ጉንጉን እንዳይሰሩት ይመከራል፡፡ ምክንያቱም ፀጉሩ ላይ የሚከሰት መወጣጠርን ለመቀነስ ነው፡፡ - በቂ እንቅልፍ ይውሰዱ፡፡ ከፀጉርዎ ሴሎች ጋር የተያያዘ ውጤት አለው፡፡ - በቫይታሚን የበለፀጉ የፀጉር ሻምፖዎችን እንዲጠቀሙም ይመከራል፡፡

ገጽ page July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ይህ አምድ እያዝናኑ የሚያስተምሩ፤ ቁምነገሮች የሚስተናገዱበት ነው። በአምዱ ላይ የአንባቢያን ተሳትፎ ይበረታታል። ምንጭ ጠቅሰው ያስገረመዎትን እውነታ ያካፍሉን

ታዋቂዋና ተወዳጇ አርቲስት መሠረት መብራቴ

ሚኒሶታ በመምጣት

የምትተውንበት “ፍሬሽማን”

ትያትር ሚኒያፖሊስ

ኦግስበርግ ኮሌጅ ኦገስት 10 እና ኦገስት 11 2013 ይታያል።

እንዳያመልጣችሁ። ለበለጠ መረጃ፡ 612-226-8326

በእርግጥም ይህን ዘልማዳዊ አነጋገር ከእውነታው ጋር ሲነፃፀር በእውነትም ሰማያዊ እምነቶች (ሃይማኖቶች) እንደሆኑ በቀላሉ ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ሃይማኖቶቹ ለፈጣሪያቸው አልያም ለአምላካቸው ቅንነታቸውንና ታዛዥነታቸውን የሚገልፁበት የተለያዩ አምልኮታዊ ተግባራት ያላቸው ከመሆኑ ባሻገር እነዚህ አምልኮታዊ ተግባራት በምን መልኩ እንደሚፈፀሙ የሚያመላክት የየራሳቸው የሆነ ሰማያዊ መመሪያዎች አላቸው፡፡ ይህ ሰማያዊ መመሪያቸው በሚያመለክተው መሰረትም የአምልኮ ተግባራቸውን ይፈጽማሉ፡፡

ለዛሬ እንደ ርዕስ የያዝነው በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች እየፈፀሟቸው ከሚገኙት የአምልኮ ተግባራት መካከል አንዱ ስለ ሆነው የረመዳን ፆም አንዳንድ ነገሮችን ለማንሳት ነው፡፡

የፆም ትርጓሜ በኢስላም ሃይማኖት በኢስላማዊው የስነ ቃላት ትርጓሜ መሰረት ፆም ማለት ጎህ ከቀደደበት ጊዜ አንስቶ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ድረስ ባለው

ጊዜ ውስጥ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከወሲባዊ ፍላጎት እና ከሌሎች መሰል ድርጊቶች በልበ ውሳኔ ተነሳሽነት ከአላህ ዘንድ ምንዳ አገኛለሁ በሚል እምነት መታቀብ (መከልከል) ማለት ነው፡፡

በእስልምና ሃይማኖት የተለያዩ የፆም አይነቶች ያሉ ሲሆን እነዚህ የተለያዩ የፆም አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ሀ. ግዴታ የሆኑ ፆሞች ለ. ግዴታ ያልሆኑና በፍላጎት የሚፆሙ ፆሞች - ክልክል የሆኑ ጾሞች ፆም የሚሰጣቸውም ጠቀሜታዎች እንደሚከተለው በአጭሩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ሀ. በመንፈሳዊ ጠቀሜታዎች 1. በልቦና ውስጥ የአላህ ፍራቻ እንዲሰርፅ ከማድረጉ ሌላ ህሊና ወደር የማይገኝለትን የውስጣዊ ደስታ እንዲቀዳጅ

ያደርጋል፡፡ 2. ትዕግስትን ሲያላብስ፣ ፍላጎትን ያጠነክራል፡፡ 3. ማንኛውም ሰው በማናቸውም ክስተቶችና ሁኔታዎች ውስጥ ራሱን እንዲቆጣጠር በማድረጉ ሂደት ፆም ከፍተኛውን ሚና

ይጫወታል፡፡ 4. ፆም የሰው ልጅ ህይወት ስርዓት ባለው መልኩ እንዲጓዝ ያደርጋል፡፡ 5. ፆም አዕምሮ ለትንሽ ጊዜያትም ቢሆን ስለ መልካም ነገሮች እንዲያስታውስ ብሎም የሰው ልጆች አላህን አስበው

እንዲፈሩና ቅን ታዛዥ እንዲሆኑ መንፈሳዊ ስልጠናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ይሰጣል፡፡ 6. ፆም አንደበትንና መላ አካላትን እንዲሁም ስጋዊ ስሜትን በማድከም ሰዎች ለሰይጣን (ዲያቢሎስ) ታዛዥ እንዳይሆኑ

ስለሚከለክል ሰዎች መልካምና ቀጥታውን የኢስላም መንገድ እንዲከተሉና ከትንሣኤ በኋላ ባለው ዘልዓለማዊ ህይወት ተደሳች እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

ለ. ማህበራዊ ጠቀሜታዎች 1. ፆም ሙስሊሞች በአንድነት አንድ ወጥ ለሆነ ስርዓት ተገዢ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ 2. በሰዎች መካከል ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ይረዳል፡፡ 3. ማንኛውም ሙስሊም በመልካም ስነ ምግባር የታነፀና ለሌሎች ሰዎች አርአያነት ያለው ሰው እንዲሆን በማድረጉ በኩል

ፆም ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡ 4. ፆም ማንኛውንም ባለሀብት አላህ የገለሰውንና የቸረውን ሀብቶች በይበልጥ የሚያስታውስበት ልዩ አጋጣሚ ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር የተቸገሩ ወገኖቹን በማስታወስና ህመማቸውን በጋራ በመቅመስ ከጎናቸው እንዲቆም ይረዳል፡፡ ሐ. በጤና መስክ የሚሰጠው ጠቀሜታ 1. ፆም የስኳር ህመምን በመከላከሉ ረገድ የሚሰጠው ጠቀሜታ፡- ሰውነታችን በተመጣጣኝ ሁኔታ ከሚፈልጋቸው ንጥረ ነገሮች መካከል ስኳር አንዱ ነው፡፡ ሰውነታችን የሚፈልገውን ይህን

ስኳር በሚፈለገው መጠን ተዘጋጅቶ በተመጣጠነ ሁኔታ የሚቀርበው በጉበት አማካኝነት ነው፡፡ የስኳር ክምችት መጠኑ ከሚፈለገው በላይ ከሆነ በጤንነት ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ የጤና ችግር እንዳይፈጠር በፆም

ምክንያት የተከማቸው ስኳር በደም ውስጥ በመቀላቀል ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ስለ ሚሰራጭ፣ ፆም የስኳር ክምችት በጤናነት ላይ ከሚያደርሰው የጤና መታወክ ይታደጋል፡፡

2. የልብን ጤንነት በመጠበቁ ረገድ፡- የጤነኛ ሰው ልብ ምት ከ70-80 በደቂቃ ያመለክታሉ፡፡ ነገር ግን ዕድሜ እየጨመረና እየገፋ በሄደ ቁጥር የልብ ምት

ድክመትን እንደሚያመለክትና በአብዛኛው ዕድሜአቸው ከሃምሳ በላይ የሆኑ ሰዎች በልብ ድካም በሽታ እንደሚጠቁ የህክምና መረጃዎች አረጋግጠዋል፡፡ ሆኖም ግን በፆም ጊዜ ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች የሚሰራጨው የደም መጠን ከሚፈለገው መጠን በላይ ስለሚያንስ የልብን ስራ ያቃልላል፡፡ ስለዚህ የልብ ምት መጠን 60 በደቂቃ ይደርሳል፡፡ ይህ ደግሞ ልብ የተወሰነ የስራ ጫናንና መጨናነቅን አስወግዶ ለጥቂት ጊዜ እረፍት እንዲያገኝ ይረዳል፡፡

የረመዳን ፆም የረመዳን ወር ፆም ከዚህ በላይ እንደተመለከትነው ግዴታዊ ፆም ከሚባሉት የፆም አይነቶች አንዱ ነው፡፡

ቤት ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ሲፈልጉ እኔ አብሬዎ

እሰራለሁ።

If you are buying or selling

a property, talk to me,

I can work for you!

በተለያዩ ስታይሎች ተኩስና ሹሩባ እንሰራለን የስፓ አገልግሎታችን ልዩ ነው ሙሽራ እንሞሽራለን የፀጉር ቀለም፣ ቁርጥ፣ ጸጉር መቀጠልና ሌሎችም አገልግሎቶች አሉን

Global Braids Salon፡ 1821 University Ave, Suit 130

St. Paul, MN 551004 651-646-5854

ፀጉር የውበት አክሊል ነውና ወደ ግሎባል ሳሎን በመምጣት ተውበው ይሂዱ

በዓለማችን ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው እምነቶችና ኃይማኖቶች የመገኘታቸው ነገር እሙን ቢሆንም ካላቸው የረዥም ዓመታት ታሪክ፣ ወግ፣ ስርዓትና ባህል አኳያ ኢስላም (እስልምና)፣ ክርስትናና የአይሁድ እምነቶች በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ እምነቶች፡- በተለምዶ ሰማያዊ ሃይማኖቶች ወይም ዋና መሰረተ ምንጫቸው ከሰማይ መለኮታዊ ኃይል ነው የሚባሉ እምነቶች ናቸው፡፡

ፎቶ ምንጭ ኢስላም ወርልድ

ገጽ page July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

Nuru Dedefo, ESQNuru Dedefo, ESQNuru Dedefo, ESQ... Attorney at Law & CounselorAttorney at Law & CounselorAttorney at Law & Counselor

If you have legal issues, If you have legal issues, If you have legal issues,

you need a lawyer who you need a lawyer who you need a lawyer who

fights for your rights. fights for your rights. fights for your rights.

Nuru Dedefo fights for Nuru Dedefo fights for Nuru Dedefo fights for

your rights.your rights.your rights.

--- Car AccidentsCar AccidentsCar Accidents

--- Work place injuriesWork place injuriesWork place injuries

--- ImmigrationsImmigrationsImmigrations

--- Family LawFamily LawFamily Law

--- Criminal LawCriminal LawCriminal Law

If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:

3989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 554213989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 554213989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 55421

(763)(763)(763)---781781781---5254 (office), (6125254 (office), (6125254 (office), (612---559559559---0489) Cell0489) Cell0489) Cell

(763)(763)(763)---781781781---5279 Fax5279 Fax5279 Fax

አስደሳች ዜና ከቲስ ፕሌስ

ሠርግዎንም ሆነ ማንኛውንም ድግስ በሃገር ቤት እና በተወዳጁ የኤሽያ ምግቦቻችን ኬተሪንግ አገልግሎት

መስጠት ጀምረናል። ሕጋዊ ፈቃድ ስላለን በየትኛውም ሆቴል

ኬተሪንግ እናደርጋለን

ዲሲ... ከገጽ 3 የዞረ ... እኔ አላውቅም።" አለና የሞት ሞቱን የርግብ አሞራ...

ማለት ጀመረ። ህዝቡ ግን እንኳን ሊጨፍር ራሱንም አልነቀነቀም ነበር። ጃ ሉድ ትንሽ ሃይ እንደነበር ያስታውቃል። የዚያኑ እለት የነበረው ኮንሰርት አዳራሽ ሙሉ ሰው ሲጠብቀው ጃ ሉድ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ።

እንደዚህ አይነት በርካታ እንግዳ ነገሮችን ታዝበናል። ለግዜው ፈገግ ሊያደርጉን ቢችሉም ችግር መሆናቸው አልቀረም።

በእርግጥ ፌደሬሽኑ ከተገንጣዩ ቡድን ጋር የገባው እሰጥ እገባ ብዙ ጊዜውንና ጉልበቱን ወስዶበታል። ሙሉ ትኩረቱን በ30ኛ አመት በዓል ላይ አለማድረጉ ዝግጅቱ በጥቂቱም ቢሆን መደናቀፉ አልቀረም። የዘንድሮውን በዓል ለየት ያደረገው ሕዝቡ በእልህ እና በቁጭት እንደዘመቻ በመረባረብ ዝግጅቱን ማሳመሩ ነው። ዘንድሮ በዚህ አልፏል። ወደፊት ግን ፌደሬሽኑ ቁጭ ብሎ ማሰብና ብዙ መስራት ይጠበቅበታል። በሙያው የተካኑ ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ ማሰራት ካልቻለ ችግሮቹ አሁንም ለ30 አመታት ይቀጥላሉ።

*** ፌዴሬሽኑን በፖለቲከኝነት ለሚከሱ ወገኖች የምለው

አለኝ። ሃገር ወዳድነት ፖለቲከኝነት አይደለም። በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ ክስተት ወገን ሲጎዳና ለአደጋ ሲጋለጥ እርዳታ ማድረግ ሰብአዊነት እንጅ ፖለቲከኝነት አይደለም። ወገኖቻችን በፖለቲካና በመንፈሳዊ እምነታቸው ምክንያት ያላግባብ ሲሰቃዩ ዝም ብሎ መመልከትም በአንጻሩ ሰብአዊነት አይደለም። ደቡብ አፍሪካ በዘረኛው አፓርታይድ ስርዓት ስር ወድቃ በነበረችበት ጊዜ ቤተ-ክርስትያናትም ለዜጎቻቸው መብት እና ነጻነት ይጮሁ ነበር። ታዲያ እነ ዴዝሞንድ ቱቱ ፖለቲከኞች ናቸው?

ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ያሰባሰበ ተቋም ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ አያገባውም ማለት ከግብዝነትም ያለፈ ይሆናል።

ኢትዮጵያ ላይ እንዲጋልቡ የተፈቀደላቸው ባለሃብቶች፡ በድሃው ህዝብ ላይ እስኪደክሙ ሊጋልቡ ይችላሉ። አትላንቲክን ተሻግሮ በዲያስፖራው ላይ መጋለብ እንደማይቻል ግን የዘንድሮው የዲሲ ዝግጅት በቂ ምስክር ነበር። ከ 3,000,000,000 ዶላር በላይ ወጥቶ 700 ሰራተኞች እና ተጫዋቾች በቅጥር የተሰማሩበት የዲሲው አር.ኤፍ.ኬ ስታዲየም ባዶ ነበር። በቃ ባዶ!... ከኢትዮጵያ የተጋበዙ እንግዶች፡ አትሌቶች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች ሁሉ እዚያኛው ሜዳ ድርሽ አላሉም። ሁሉም፡ የተገዙ ተጫዋቾችም ጭምር፤ ሜሪላንድ በመሄድ ከኢትዮጵያዊው ጋር በዓሉን በፍቅር ማሳለፍን ነበር የመረጡት።

ከቅድም አያቶቻችን የወረስነው አረንጓዴ-ቢጫ-ቀይ ባንዲራችንን ይዞ መገኝት በዘመናችን ገዢዎች ወንጀል እንደሆነ ተነግሮናል። ዘንድሮ በዲሲ ያየነው ደግሞ ትንሽ እንግዳ ነገር ነው። የራሱ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች በንግድ ስፍራዎቻቸው ባለኮከቡን የህወሃት ባንዲራ አውርደው ያልተበረዘውን ባንዲራ ሲሰቅሉ ታዝበናል። በዲሲ አር.አፍ.ኬ. ስታዲየምም ሆነ ተገንጣዮቹ በሚበትኑት ፍላየር ባለኮከቡ ባንድራ አልነበረም። ለግዜው አራዶች መሆናቸው ነው። ለጥቅም ሲሆን ሁሉም በባንዲራችን ይነግዳሉ። ብሄርተኝነት በኢኮኖሚ ጥቅም ይጠፋል ያለው ማን ነበር?...

ሁሉም ግምት ውስጥ የገቡ ይመስላል። እውነታው ግን አንድ ቦታ ላይ ነው ያለው። ገንዘብ ኢትዮጵያዊነትን አላሸነፈውም፣ አልገዛውምም። አንጋፋው ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ ስለዘንድሮው ዝግጅት እንዲህ አለ "የምናውቀው አንድ ድርጅት ብቻ ነው። ነባሩ ፌዴሬሽን። የኢትዮጵያን ህዝብ ለመክፋፈል የሚደረገውን ተንኮል ብልሁ የኢትዮጵያ ህዝብ በመፈቃቀር አክሽፎታል።"... አዲዮስ!

*** "አንጃ" የሚለውን ቃል ቀደም ብዬ ሳነሳ ወዳጄ ዶ/ር

ሼክስፒር ፈይሳ ታወሰኝ። እለተ-አርብ ከኢትዮጵያ ቀን ደማቅ ዝግጅት በኋላ ከሼክስፒር ፈይሳ እና ዳዊት ከበደ ጋር ከግቢ ስንወጣ ሜሮን አሃዱን ከበር ላይ አገኝናት። ሜሮን የአንጋፋው ጋዜጠኛ የአህዱ ሳቡሬ ልጅ ናት። ሼክስፒር የኢትዮጵያዊነት ውርስ እና ቅርስ በሰሜን አሜሪካ ሊቀ-መንበር በነበረ ግዜ በሁለቱ መካከል የተፈጠረ ቅራኔ እንዳለ ብንሰማም እንዲህ የተካረረ ጉዳይ አልመሰለንም ነበር። በመሃል የነበርነው እኔና ዳዊት ግን እንዲታረቁ ገፋፋናቸው። ሜሮን የሼክስፒርን ይቅርታ ጥያቄ አልቀበልም ብላ ብዙ ካንገራገረች በኋላ እኛን በማክበር ለመታረቅ ተስማማች እና ተቃቀፉ።

ከእርቁ በኋላ በጸቡ ዙሪያ መቀላለድ ጀመርን። እኔን ትንሽ ፈገግ ስላደረገኝ ነው እዚህ የምደግምላችሁ።

ጸቡን ያመጣው "አንጃ" የሚል ቃል ያለበት የሼክስፒር ኢሜይል ነበር። "ለመሆኑ አንጃ ማለት ምን እንደሆን ታውቀዋለህ?" ስትል ሜሮን ሼክስፒርን ጠየቀችው። "እኔ ምን አውቅልሻለሁ። ያው ፖሊቲከኞቹ የሚጠቀሙበት ቃል ስለሆነ ነው የጨመርኩት።" ሲል መለሰላት።

ሼክስፒር በሙያው እጅግ የሚደነቅ ችሎታ ያለው ለመሆኑ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። ጨዋታና መዝናናትን ይወድዳል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሀ-ሁ እንጂ ገና አቡጊዳው (shrowdity) ላይ የደረሰ ስለማይመስል ለፖለቲካ የሚሆን ሰው አይደለም።

የሜሮን ኢሜይል ምላሽ አንተ "ግልገል" አንባገነን የሚል ነበር። ሼክስፒር ለፈጸመው ድርጊት ይህ ምላሽ ተገቢ እንዳልነበር ተነጋገርን። በመጨረሻ ግን ግልገል የሚለው ሃረግ ብቻ እንዲነሳ ተስማማን። ሼክስፒርም በዚሁ ተስማማና ወደ ጃኖ ባንድ የምሽት ዝግጅት ተያይዘን አመራን። ... ጃኖዎች መድረክ ላይ በቲቪ እንደምናያቸው ሆነው አልተገኙም።

*** ...በመጨረሻም ዲሲን ተሰናብቼ ወደ ዳለስ አውሮፕላን

ማረፍያ አመራሁ። ከበጀት የተከራየሁትን መኪና የተረከበኝ አንድ ሰውዬ ትኩር ብሎ ተመለከተኝና "ኢትዮጵያዊ ነህ?" ሲል በእንግሊዝኛ ጠየቀኝ። "አዎ" ስለው እሱም ኤርትራዊ መሆኑን ነግሮኝ አንድ ስለመሆናችን የሚደሰኩር ወሬ ብጤ ጀመረ - በተኮላተፈ አማርኛ። አዎ አንድ ነን አልኩት በልቤ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲህ የሚሉ በርካታ ኤርትራውያን አጋጥመውኛል። የሚገርምው ታዲያ ዛሬ እንዲህ የሚሉን፤ ከአመታት በፊት እኛን ለማናገር እንኳን ይጸየፉ የነበሩ ናቸው። ከኢትዮጵያ ለመለየት 99.9 በመቶ ድምጽ ሲሰጡ ምንም አላልናቸውም ነበር። ዛሬ የአፍሪካዋን ሲንጋፖር ሲጠብቁ ኤርትራችን "ሲንግል ኤንድ ፑር" ሆና መቅረትዋ የቆጫቸው ይመስላል። አዎ! ከትላንት ይልቅ ዛሬ አንድ ነን። ሁሉም ነገር ያልፋል፡ ፍቅር ያሸንፋል! ሜሪላንድ፡ ጁን 2013

አማኑኤል... ከገጽ 15 የዞረ

ነበር፡፡ በመሆኑም ውጭ አገር ያሉ ሰዎች በጠቅላላ ወደዱት፡፡ ከዚያ ከስድስት ወር በኋላ ደወለልኝና ‹‹ዘፈኑ በጣም ቡም ብሏል›› አለኝ፡፡ አላመንኩም፡፡ ‹‹እውነትህን ነው?›› አልኩና ዩቲዩብ ላይ ሳየው ደነገጥኩኝ፡፡ የሚገርምህ ወደ 2 ሚሊዮን 800 ሺ ህዝብ አይቶለታል፡፡ በደወለልኝ ጊዜ ሌላ ዘፈን እንዳዘጋጅለት በጠየቀኝ መሰረት ‹‹ደሞ አፌን›› ሰራሁለት፡፡ የመጀመሪያው የባህል ዘመናዊ ሲሆን ይህ ግን ችክችካ አይነት ለመድረክ የሚሆን ነው፡፡ ከዚያ፣ በየኮንሰርቶች ተመራጭ ለመሆንና ለመስቀል ቻለ፡፡ ቀጥሎ ‹‹ሰላ በይ›› የሚለውን በሌላ ስቱዲዮ መጥቶ ሰራው፡፡ እሱም ውጤታማ ሆነለት፡፡ ይሄ ልጅ የተሾመ አሰግድን ‹‹የእኔ አካል›› የሚለውን ድጋሚ በመዝፈን አንድ ዘፈን ጨምሮ በአራት ዘፈን በዓለም ላይ እየተዘዋወረ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

እኔ ለጃክ የመጀመሪያውን ሙዚቃ ግጥምም ዜማም ቅንብርም ስለሰራሁለት ሊያመሰግነኝ ቢችልም፣ እኔ ደግሞ በጣም ብልህ ልጅ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ለምን ብትል በደራሲ ያምናል፡፡ የድሮዎቹን ትልቅ ደረጃ የደረሱት እነ ኤፍሬም ታምሩን ብትመለከት ለረጅም ጊዜ የሰሩት ደራሲዎችን ይዘው በመምጣታቸው ነው፡፡ ልጁ በዚሁ ከቀጠለ ታዋቂዎቹ የደረሱበት ቦታ የማይደርስበት መንገድ የለም፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- ብዙውን ጊዜ የድሮ ድምፃዊያንን በተለያዩ መንገዶች ታነሳለህ፡፡ ለምንድን ነው?

አማኑኤል፡- ያለጥርጥር እኔ የድሮዎቹ ድምፃዊያን አድናቂ ነኝ፡፡ ከ50ዎቹ ጀምሮ የነበሩት በተለይ ባህሩ ቀኜ፣ አሰፋ አባተ፣ ወደዚህ ስትመጣ ጋሽ ይርጋ ዱባለ በጣም ድምፃዊ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሚያገኙት ግጥምም ሆነ ዜማ ያስገርመኝ ነበር፡፡ በተለይ ጋሽ ባህሩ የሚፈጥረው ዜማና ግጥም በጣም ለኢትዮጵያ ሙዚቃ መሰረት የነበረና ለረጅም ዓመት የተደመጠ ነው፡፡ ወደዚህ ስንመጣ ደግሞ የእነ ጥላሁን፣ የእነ ብዙነሽ፣ የእነ ሒሩት ዘመን አለ፡፡ ሲቀጥል ሮሀ ባንድ፣ በ70ዎቹ እነ ኤፍሬም ታምሩ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ አስቴር አወቀ እያልን መዘርዘር እንችላለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ሙዚቃን ለ40 እና 30 ዓመታት ያሻገሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደቀላል አይታዩም፡፡ አሁን የእኛ አገር ሙዚቃዎች ለሶስትና ለአራት ወር ተሰምተው ሲቆዩ እንደትልቅ ነገር የምናይበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ስለዚህ እኔ የዚያን ጊዜ ሰዎች በምን መንገድ ቢሰሩት ነው ቴክኖሎጂ በሌለበት ሰዓት፣ በአናሎግ ሲስተም እየቀዱ፣ ኮምፒውተር ሳያግዛቸው፣ ላይቭ እየቀዱ፣ ወጣቱ በእነሱ ዘፈን እየተማረከ እኛ

እንዴት እንደነሱ መስራት አቃተን? የሚሉ ጥያቄዎች ስላሉኝ ያኛው ትውልድ ይበልጥብኛል፡፡ ይሄ የእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የአድማጭ፣ የህዝብና የአርቲስቱ ጥያቄ ይመስለኛል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- የዚህ መፍትሄው ምንድን ነው ትላለህ? አማኑኤል፡- አንደኛው ነገር ራሳችንን እየሆንን አይደለንም፡፡

ራሳችንን መሆን መቻል አለብን፡፡ ሁሉም በየፊናው የተለያየውን ዓለም ሙዚቃ ይሰራል፡፡ አይስራ አልምም፡፡ በስታይሉ ውስጥ ደግሞ ስራውን በማቅለል ደረጃ በአንድ ሞኖ ስቱዲዮ (ሆም ስቱዲዮ) ውስጥ በመሰራቱ አንድ ሰው ሙዚቃውን እንደፈለገው ማድረግ ጀመረ፡፡ ድምፃዊያኑም ስለቀለለው ገባ፡፡ መአት ድምፃዊያን ተፈጠሩ፡፡ ግን ከዚያ ውስጥ ምን ያህሉ ድምፃዊ ነው? ብለህ ብታስብ ሁሉም አይደሉም፡፡ ስለዚህ ህዝቡንም አሰለቸነው፡፡

እኛ የእኛነት የምትለው ነገር የለም፡፡ ሬጌው ምን ያህል በኢትዮጵያ ሄዷል? ብትል የለም ገና መጀመሩ ነው፡፡ ሒፕ ሆፕ አለ ወይ? ብትል ሒፕ ሆፕ የሚባል ሙዚቃ የት አለ? ሌላው ዓለም መጥቶ ሲሰማን በጣም ያዝንብናል፡፡ በየስቱዲዮው ነጮቹ ጥቁሮቹ መጥተው አይተው የተሰማቸውን ስሜት አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በዚህ ትውልድም እንደድሮው የራሳቸውን ቀለም ይዘው መስራት እንዳለባቸው ይሰማኛል፡፡ ኢንዱስትሪው እንዲያድግና አድማጭ እንዲሰማን ከፈለግን ጥሩ ዜማ፣ ለግጥሙም መጨነቅ፣ ለአሬንጅመንቱም መጨነቅና ጥሩ ድምፃዊም መስራት ያስፈልገናል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የሙዚቃ ቪዲዮ ክሊፕ ዳይሬክተር ፕሮዲውሰር ስለመሆንህ እስካሁን በነበረን ቆይታችን ስናወራ ቆይተናል፡፡ አሁን ደግሞ በፊልሙ ዓለም ስላለህ ተሳትፎ እናውራ፡፡ እንችላለን?

አማኑኤል፡- ይቻላል፡፡ ስለፊልም ካነሳን የመጀመሪያው ‹‹የማያልቀው መንገድ›› ነው፡፡ እንኳን እኔ ኢትዮጵያ ውስጥም ፊልም ገና እየገባ በነበረበት ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ነበረ፡፡ የያኔው ከነበረው ሁኔታ አንፃር ጥሩ ነው፡፡ ወደ አሁኑ ዘመን ስንመጣ ‹‹ፔንዱለም›› እና ‹‹ከመጠን በላይ›› የሚሉ ፊልሞች ላይ ሰርቻለሁ፡፡

የፔንዱለም ፕሮዲውሰር ቶማስ ጠርቶ ሲፈትነኝ ሌሎች ዳይሬክተሮችም ይዞ ነበር፡፡ ከተፈተንኩ በኋላ የተቀረፅኩትን በቪዲዮ ስመለከተው እውነቴን ነው የምልህ ጠላሁት፡፡ እናም ‹‹እኔ መግባት የለብኝም፡፡ እኔ አልሆናችሁም›› አልኳቸው፡፡ ግን ዳይሬክተሩ ለዚህ ቦታ አማን ይሆናል ብሎ ከወሰነ ሪስኩን ይወስዳል፡፡ ስለዚህም ‹‹ይህን ልጅ እለውጠዋለሁ፣ በዚህ አይነት ፎርም አመጣዋለሁ›› ብሎ ስላሰበ ዳይሬክተሩንም አምኜ ገባሁበት፡፡ እውር አሞራ እንደማለት ነው የማታውቀው ነገር ውስጥ መግባት፡፡ በዚህ መንገድ ሰራሁ፡፡ ፊልሙ እስኪያልቅ ድረስ ስቱዲዮ ዘግቼ ነው የሰራሁት፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- የፔንዱለም ፊልም ምርቃት ከተማውን ሁሉ በነቀነቀ ሁኔታ ነበር የተከናወነው፡፡ በዚህ ረገድ የአንተም ወሳኝ ድርሻ እንደነበረበት ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ነው?

አማኑኤል፡- ፊልሙ ከተጠናቀቀ በኋላ በአንዳንድ ቦታዎች ማስታወቂያውን ሰማሁ፡፡ ያኔ ለፕሮዲውሰሩ ቶም ደወልኩለትና መተዋወቅ ያለበት በዚህ አይነት መንገድ አይደለም አልኩት፡፡ ምክንያቱም እንደ አበባዮሽ አይነት እን ደጃኪ አይነት ስዎች ጎልተው ሲወጡ ደስ ይለኛል፡፡ ዘፈን ከተሰራ ጎልቶ መውጣት አለበት፡፡ ፊልምም ቢሆን እንደዚያው ነው፡፡ ስለዚህ የሚዲያውን ስራ ሁሉ ጠቅልዬ ያዝኩት፡፡ እንደውም የማልረሳው ለሳውንድ ትራኩ ብዙአየሁ ብዙ ብር ጠየቀ፡፡ እኔ ‹‹በቃ ራሴ እገዘዋለሁ›› ብዬ አሰራሁትና ጨርሼ ቶምን ሰራሁት፡፡ ቶምም ሲሰማው ዘፈኑን ሳላጋንን ከ30 ጊዜ በላይ ቆሞ ሰማው፡፡ ፊልሙን ግልፅ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ዘፈን ይሄን ያህል ፓወር አለው ወይ? ብሎ ደነገጠ፡፡ ከዚያ ተጀመረ፡፡ ቶም ሁሉንም ወጪ አወጣለሁ በማለቱ ወደ ሚዲያ መጥተን ሬዲዮኑን ተቆጣጠርነው፣ ጋዜጦችን ተቆጣጠርን፡፡ ቀጥሎ የሚሊኒየም አዳራሽ ሀሳብ መጣ፡፡ ቀይ ምንጣፍ ታሰበ፡፡ እኔ ወደ ባንድ መጣሁኝ፡፡ ሔለን በርሄ ገባች፡፡ በዚህ ጊዜ ሰዎችን ሳማክር ‹‹እናንተ እብድ ናችሁ ወይ፤ እንዴት ዘፈንና ፊልም አንድ ላይ ይታያል? በዚያ ላይ ሚሊኒየም አዳራሽ›› ብለው አልተቀበሉኝም ነበር፡፡ ግን ነገሮችን ትልቅም ትንሽም የምታደርገው አንተ ነህና በውጥናችን ገፍተንበት በስተመጨረሻ 14 ሺ ሰው መጥቶ ፊልሙን ሊያየው ችሏል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- ለዚሁ ፊልም ማጀቢያነት ሔለን በርሔ የተጫወተችውን ሙዚቃ በግጥምም በዜማም በማቀናበርም ሰርተሀል፡፡ ይሄ ሙዚቃዋ ደግሞ ከፊልሙም በኋላ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲደመጥ ይታያል፡፡ ሙዚቃውን ስታዘጋጅላት ከፊልሙም ውጭ ይደመጣል ብለህ አስበህ ነበር?

አማኑኤል፡- ይኸውልህ አንድ ምሳሌ ልንገርህ፡፡ ‹‹ለካ ለካ

ያንተ ዓለም፣ ወዲህ ወዲያ ፔንዱለም›› የምትለዋ የዘፈኑ ግጥም ኤዲት ሲደረግ ነበርኩኝ፡፡ እና ያኔ ‹‹በናታችሁ ልብስ ስለካ እዚህች ቦታ አስገቡኝ›› አልኩ፡፡ ፊልሙ ላይ የምሰራው ልብስ ሰፊ ሆኜ ነው፡፡ እና ለካ፣ ለካ ማለት ልብሱን ለካ እንደማለት ነው፡፡ በፊልሙ ላይ ግን ዝም ብለህ ፊልሙን ባታየውም ደግሞ ‹‹ለካ ከእኔ ጋር አልነበርክም›› የሚል ትርጉም ይሰጥሃል፡፡ የውጪዎቹን ስራዎች እያደነቅንና የእነሱን ተሞክሮ እየቀሰምን መሄድ ያለብን ይመስለኛል፡፡ ታይታኒክ ፊልም ለእኔ ምርጥ ፊልም ነው፡፡ የፊልሙን ማጀቢያ ሙዚቃ የሰራችው ሴሊንዲዮን ናት፡፡ ይህ ማጀቢያ ሲሰራ ስሎው ነው፡፡ ከፊልሙ ጋር ልክክ ብሎ ገብቶ እንዳትወጣ አድርጎ ዘፈኑን በሰማህ ቁጥር ብዙ የፍቅር ትውስታ እንዲኖርህ ያስችላል፡፡ ይሄ ዘፈን ቴክኖና ሐውስ ሆኖ ወጥቷል፡፡ ወደ ጭፈራ ዘይቤ ሆኖ ቀርቧል፡፡ እኔ የሄለን በርሔንም ሙዚቃ እኔ አንዳንዴ ሲጨፍሩበት አያለሁ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ ከፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው መነሳሳትን የሚፈጥር ይመስለኛል፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- ከሰሞኑ ‹‹ዜማ አማን›› በሚል ርዕስ አዲስ አልበም በፕሮዲውሰርነት አቅርበሃል፡፡ በዚህ አልበምህ ካመጣኸው ድምፃዊያን ኃይለየሱስ አንዱ ነው፡፡ ኃይለየሱስ ከሙዚቃው አካባቢ ጠፍቶ ነበርና የት አገኘኸው?

አማኑኤል፡- የኃይለየሱስ ነገር እንደማንኛውም አድማጭ እኔንም ይቆጨኝ ነበር፡፡ ተማሪ ሆኜ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት እያለሁ እሱን ለማየት ለመስማት ስል ኤግዚቢሽን ማዕከል ድረስ እሄድ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ያንን የመሰለ ድምፅ ይዞ ጠፋ፡፡

‹‹ይለፍ ዕድሜ፣ አንችን ስል ቆሜ›› የሚለው ወረድ ብሎ ጀምሮ በኋላ ላይ በጣም ከፍ የሚል ነው፡፡ ሀይለየሱስን ውስጤ ሁሌም ስለሚያስበው በቀጥታ እሱ ነው ይህን የሚዘፍነው ብዬ ወስኜ ደወልኩለት፡፡ እሱም ለረጅም ጊዜ ይፈልገኝ ነበርና ተነጋገርን፡፡ ዘፈኑን ሰጠሁት፡፡ በአጭር ጊዜ ይዞት ሰራው፡፡ አድማጭም በጣም የእሱን ዘፈን ወዶታል፡፡ ኃይለየሱስ የሚገርም ድምፃዊ ሲሆን፣ አብሬው በመስራቴ ደስተኛ ነኝ፡፡

ዘ-ሃበሻ፡- በአልበምህ የተካተቱት ድምፃዊያን በአሜሪካና በኢትዮጵያ የሚኖሩ ናቸውና እነሱን ማሰባሰቡና መጠበቁ አላስቸገረህም?

አማኑኤል፡- በጣም ተስፋ የሚያስቆርጥ ደረጃ ያደርሳል፡፡ አንዳንዴ ምን ውስጥ ነው የገባሁት? እስከማለት ደርሼ ነበር፡፡ ሙዚቃ ግን ከገባህበት አይለቅህም፡፡ አንዳንዴ ፈተና ቢበዛብ ህም በእልህ ተስፋን ሰንቄ ለአድማጭ ላበቃው ችያለሁ፡፡ ወደ አምስት ዓመት ያህል የፈጀብኝም ለዚህ ነበር፡፡

ሂጓይን ... ከገጽ 21 የዞረ

ቢበዛ ያስወጣሉ፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች ጎል አግቢዎች ብቻ አይደሉም፡፡ ወደ ኋላ እየተመለሱ ኳስን ከመሀል ይዞ መውጣት እና እንደ ፕሌይ ሜከር ሌሎቹን የቡድን ተጨዋቾችን መርዳት እንዲሁም ከማጥቃት በተጨማሪ የመከላከል አጨዋወቱን ማገዝ ያውቁበታል፡፡

ቬንገር ብዙ ጊዜ የወደፊቱ ጊዜ በመመለከት ችሎታቸው ቢታወቁም ለሂጓይን ዝውውር ሊከፍሉ ያሰቡት ዋጋ የወቅቱን የአውሮፓ እግርኳስ ዝንባሌ ችላ ያሉ አስመስሏቸዋል፡፡ ከርናቢዩው ልጅ ይልቅ በአነስተኛ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ለገበያ የቀረበውን ካርሎስ ቴቬዝ ዝም ብለው ከማሳለፋቸውም ሌላ ለዝውውሩ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ይበቃዋል እየተባለ ያለውን ሮቤርት ሌቫንዶቭስኪ ለመግዛትም ገፍተው አልሄዱም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሂጓይን ዝውውር በተለያየ ምክንያት ቢደናቀፍ በሚል በዋጋ ረከስ የሚሉትን ዴቪድ ቪያ ወይም ሚቹን ለማስፈረም ሙከራ አላደረጉም፡፡

እነዚህ ሁሉ ተጨዋቾች ዘመናዊው እግርኳስ የሚፈልጋቸው አይነት አጥቂዎች ናቸው፡፡ ጎሎች ያገባሉ፣ የጎል እድሎች ይፈጥራሉ እና ቀዳዳዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ቬንገር ሂጓይንን አስፈርመው የፊት መስመሩ ዋነኛ መሪ ካደረጉት ቡድኑ ትንንሽ ቡድኖችን ሲያገኝ በርከት ያሉ ጎሎች ሊያስቆጥር ይችላል፡፡ ሆኖም ከትልልቆቹ ጋር ሲፋጠጥ በአማራጭ ማጣት ይቸገራል ሲሉ ስጋታቸውን የሚያብራሩ ጥቂት አይደሉም፡፡ ቡድኑ ጎሎች እንዳያገባ ሲከለክል ተስፋ መቁረጥ እና መርበድበድ ይጀምራል፡፡ ይህ በራሱ የአርሰናል ትልቅ ችግር ጎል ያለማስቆጠር ሳይሆን የመከላከል ድክመት እና የአዕምሮ የበላይነት ማነስ መሆኑን ያሳያል፡፡ ባለፉት በርካታ ዓመታት የመድፈኞቹን ክፍተት በሚገባ ላስተዋለ ቬንገር ሁለት ምርጥ አጥቂዎች በ60 ሚሊዮን ፓውንድ ገዝተው ችግሮችን ሁሉ እንደማይፈቱ ግልፅ ነው፡፡ ስለሂጓይን ዝውውር zehabesha,com ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያነቡ ጋብዘናል።

ለአንድ ቀን ድግስ ብለው እቃ አይግዙ፤ እኛ የድግስ እቃዎችን

እናከራይዎታለን

በመጨረሻ…፣ በመጨረሻ አርሰናል ከፍተኛ ገንዘብ ሊያወጣ ነው? በመጨረሻም ትልቅ ተጨዋች ሊገዛ ነው? ይህ ያለፉት ሳምንታት ወሬ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት አብዝቶ ፋይናንሳዊ የጥንቃቄ ጉዞ እያደረገ የዋንጫ መደርደሪያውን ባዶ ላስቀረው የክለብ ደጋፊዎች ይህ ትልቅ ዜና ነው፡፡ አርሰን ቬንገር በስልጣናቸው እያሉ ትልልቅ ተጨዋቾች ሲገዙ መመልከት ለክለቡ አፍቃሪዎች ያጓጓል፡፡ የከዋክብት መምጣት በስኬት ማጣት ፊታቸው የጠቆረባቸውን የኢምሬትስ ታዳሚዎች በደስታ ይሞላል፡፡ ሆኖም የትኞቹ ትልልቅ ተጨዋቾች? የሚለው ጥየቄ ብዙ ያነጋግራል፡፡

በእርግጥ ይህ ክረምት በኢምሬትስ ትልቅ ተጨዋች እንዲያመጣ ይጠበቃል፡፡ ይህ ጥያቄ ባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅቶች ሲነሳ ቢቆይም አሁን ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሷል፡፡ የውድድር ዘመኑ ከተጠናቀቀ ወዲህ አርሰናል የዝውውር ገበያው ዜናዎች ማጣፈጫ ሆኗል፡፡ እስካሁን ጠብ ያለ ነገር ባይኖርም የክለቡ ስም ከዌይን ሩኒ፣ ስቴፋን ዩቬቲች፣ ጎንዛሎ ሂጓይን እና ባለፉት ቀናት ደግሞ ከሉዊስ ሱአሬዝ ጋር ተነስቷል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ተጨዋቾች ዝውውሩ እውን ሊሆን የተቃረበ የሚመስለው የሂጓይን ነው፡፡ ክለቡ አርጀንቲናዊውን አጥቂ በማስፈረም የደጋፊዎችን እምነት መልሶ ለማግኘት የቆረጠ ይመስላል፡፡

የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ትልቅ ግዢ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ለዚህ ልጅ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ማውጣት ይገባል? የሚለው ጥያቄ ከብዙዎች አዎንታዊ መልስ ቢያገኝም ጥቂቶች ደግሞ ተጨዋቹ ቡድኑን ከሚጠቅመው ይልቅ ክለቡ የደጋፊዎችን ልብ ለመደለል ሊጠቀምበት ሊሆን ይችላል ሲሉ ይጠራጠራሉ፡፡

ሂጓይን ጎል ጨራሽ ነው፡፡ በየውድድሩ ዘመኑ ከ20 በላይ ጎሎች ለማስቆጠርም አይቸገርም፡፡ ሆኖም ይህ ለአርሰናል ዋንጫ ያመጣል? ይህንን የሚጠራጠሩ ብዙ ናቸው፡፡ ምክንያቱም አርሰናል ሻምፒዮን ለመሆን ከጎል አግቢም በላይ ያስፈልገዋል፡፡

የሂጓይን መምጣት በኦሊቪዬ ዢሩ ቀጣይ ሚና ላይ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ፈረንሳዊው ጎል ከማስቆጠር መሰረታዊ ችግሩ በስተቀር የተሟላ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ሂጓይን ሊፈፅማቸው የማይችሉ እና የእንግሊዝ እግርኳስ አጥብቆ የሚጠይቃቸውን ብቃቶችን ይዟል፡፡ ቬንገር ሁለቱን አጥቂዎች በአንድነት ለመጠቀም ፍላጎቱም ሆነ ዕድሉ የሚኖራቸው አይመስልም፡፡ ስሊዘህ ዢሩ ወደ ተጠባባቂ ወንበር ወርዶ ሂጓይን በቋሚነት የፊት መስመሩን ይመራል ማለት ነው፡፡ ይህ ግን ብዙ ጥያቄዎች ያስከትላል፡፡ ዘመናዊው እግርኳስ በተለይም በፕሪሚየር ሊጉ የሚተገበረው አጨዋወት ቴክኒካዊ እና ጎል ጨራሽ ተጨዋቾችን ብቻ የፊት አጥቂነት መጠቀም አያስመርጥም፡፡ በዚህ ረገድ ሲታይ ለአርሰናል ከሂጓይን ይልቅ ሌሎቹ ስማቸው ከክለቡ ጋር የተያያዙ አጥቂዎች ይሻሉታል፡፡

ለሂጓይን ይከፈላል ተብሎ የሚጠበቀው የዝውውር ሂሳብ 25 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ነው፡፡ ሆኖም ከአርጀንቲናዊው በተለይ በፕሪሚየር ሊጉ ምርጥነታቸውን ያስመሰከሩት ሩኒ ወይም ሱአሬዝ ከ30-35 ሚሊዮን ፓውንድ (ሂጓይን .. ወደ ገጽ 20 የዞረ)

ሮማን አብራሞቪች ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ከመጡ 10 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ራሺያዊው ቢሊየነር ቼልሲን በእጃቸው ካስገቡ ወዲህ ወደ ታላቅነት አሸጋግረውታል፡፡ ሰውዬው የእንግሊዝን እግርኳስም መቀየር ችለዋል፡፡ አብራሞቪች በቼልሲ ባለቤትነት ቆይታቸው የፈፀሟቸውን አብይ ኩነቶች እንመልከት፡፡

በእግርኳስ ፍቅር መውደቅ በ2003 ነበር፡፡ በቻምፒየንስ ሊጉ ሪያል

ማድሪድ በአስደናቂ መልኩ ማንቸስተር ዩናይትድን 4-3 ማሸነፍ ቻለ፡፡ በኦልድትራፎርድ ጨዋታውን ለመመልከት ከታደሙት መካከል ብዙም የማይታወቁ ራሺያዊ ቢሊየነር አንዱ ነበሩ፡፡ በምሽቱ ግጥሚያ በመመሰጣቸው ቀጣይ ጉዟቸው የእግርኳስ ክለብ መግዛት እንደሆነ ወሰኑ፡፡ ከበርቴው ጊዜያቸውን ሳያጠፉ ቼልሲን የግላቸው አደረጉ፡፡

ቼልሲ በለንደን የሚገኝ መሆኑና የአክሲዮን መዋቅሩ ክለቡን በቀላሉ እንዲያገኙት አድርጓቸዋል፡፡ ክለቡን ለመግዛት በአብራሞቪችና በወቅቱ የቼልሲ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ትሬቨር ቢርች መካከል ውይይት ተደረገ፡፡ ‹‹አብራሞቪች ክለቡ ሊገዛ መፈለጉን ሙሉ ለሙሉ ለማመን ተቸግሬ ነበር›› ይላል ቢርች፡፡ አብራሞቪች ክለቡን ለመጠቅለል የተጠየቁትን ገንዘብ ለመክፈል ተስማሙ፡፡ ከቢርች ጋር ያደረጉት

ድርድርም 20 ደቂቃ ብቻ የፈጀ ነበር፡፡ ቢርች በወቅቱ የቼልሲ ባለቤት የነበሩት ኬን ቤትስን ካነጋገሩ በኋላ በቀጣዩ ቀን በዶርቼስተር ሆቴል ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ፡፡ አብራሞቪች ቼልሲን ለመግዛት 140 ሚሊዮን ለመክፈልና እዳውን ለመሸፈን በመስማማት ድርድሩ ተቋጨ፡፡ ከዚያም ሮማን በሁለት ወራት ውስጥ ለተጨዋቾች ግዢ

ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ አውጥተዋል፡፡ በሁለት ዓመታት ጊዜ ደግሞ ጆን ቴሪ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ማንሳት ችሏል፡፡ የእንግሊዝ እግርኳስም በለውጥ ጎዳና መጓዙን ጀመረ፡፡

የአሽሊ ኮል ውዝግብ አቭራሞቪች ያለገደብ ገንዘባቸውን

እንደሚያፈሱ ግልፅ የሆነው ወዲያው ነበር፡፡ በገንዘብ ጡንቻቸው የሚፈልጉትን መግዛት እንደሚችሉ አሳዩ፡፡ የወቅቱ የማንቸስተር ዩናይትድ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ፒተር ኬንየንን ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ በማምጣት ሽግግሩን በፍጥነት መከወን ጀምረዋል፡፡ አብራሞቪች ካግሊያሪን ለመግዛት ሙከራ አድርገው እንደነበርም ተዘግቧል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው የሰማያዊዎቹ ኮከብ የነበረው ጂያን ፍራኮ ዞላ የጣልያንን ክለብ ለመቀላቀል በመፈለጉ ተጨዋቹን በስታምፎርድ ብሪጅ ለማቆየት ሲሉ

ነበር፡፡ የቼልሲው ባለቤት በወቅቱ በግዢ ሪከርድነት

ሊያዝ የሚችል 50 ሚሊዮን ፓውንድ ለአርሰናል በማቅረብ ቲዮሪ ሆንሪን ለማስፈረም ሞክረው ነበር፡፡ ሮማን ዕድሜው ለገፋው አንድሬ ሼቭቼንኮ ግዢ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ማውጣታቸው ስህተት ከፈፀሙባቸው ዝውውሮች አንዱ ሆኗል፡፡

የሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች ለማምጣት አብራሞቪች እጃቸውን ወደ ኪሳቸው ከማስገባት ወደኋላ አይሉም፡፡ ቼልሲ የትኛውንም ተጨዋች ለማስፈረም ከአቅሙ በላይ እንደማይሆን ማመን ጀመረ፡፡ ለተጫዋች ዝውውር ከፍተኛ ሂሳብ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆኑ በበርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ ሆነ፡፡ የአሽሊ ኮል ዝውውር ውዝግብ በጥሩ ምሳሌነት ይጠቀሳል፡፡ ጆዜ ሞውሪንሆ ከአርሰናሉ የግራ መስመር ተጨዋች ጋር በለንደን አንድ ሬስቶራንት በመገናኘት በመወያየታቸው ቼልሲ ያለ አርሰናል ፍቃድ ኮልን በማነጋገሩ ጥፋተኛ ተብሎ ነበር፡፡ አርሰን ቬንገርም በወቅቱ የቼልሲን አቀራረብ ህገወጥ የፋይናንስ ስራ ብለውት ነበር፡፡ በመጨረሻ አብራሞቪች የሚፈልጉትን ተጨዋች አግኝተዋል፡፡ ኮል ወደ ቼልሲ ከመጣ ወዲህ ክለቡ ስምንት ታላላቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል፡፡

አዲስ የልምምድ ማዕከል የአብራሞቪች ረብጣ በተጨዋቾች ዝውውር ላይ ብቻ አልፈሰሰም፡፡ በቼልሲ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ መሰረተ ልማት በማካሄድ ላይም ውሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቼልሲ በፋይናንስ አቅሙ በዓለም ላይ ከሚገኙ ታላላቅ ክለቦች ጎራ የሚቀላቀልበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡ ዴሎይቴ ባወጣው መረጃ ቼልሲ አርሰናል፣ ኤሲሚላን፣ ሊቨርፑልና ጁቬንቱስን

በመብለጥ ከዓለም ታላላቅ ክለቦች ዝርዝር ላይ በአምስተኛነት ተቀምጧል፡፡ በአብራሞቪች ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ክለቡ ትርፍ አስመዝግቧል፡፡ ከ700 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ የሆነው ብድር ወደ ወለድ የማይከፈልበት ብድር ተሸጋግሯል፡፡ ክለቡ አሁን ከእዳ ነፃ ነኝ ሊል ይችላል፡፡

ሮማን ቼልሲን በሁሉም ዘርፍ በፍጥነት እንዲያድግ ያደረጉት ጥረት በግልፅ ይንፀባረቃል፡፡ ከሀርሊንግተን የልምምድ ማዕከል በ2007 ወደ ተከፈተው ኮብሃም መዛወር ችለዋል፡፡ አብራሞቪች በወጣት አካዳሚው ላይ ያፈሰሱት ገንዘብ አሰልጣኞች ለወጣቶች እድል ለመስጠት በቂ ጊዜ ስለማያገኙ ስኬታማ ለመሆን አልቻለም፡፡ ቼልሲ ወጣቶችን እንዲያፈራ ያላቸው ፅኑ ፍላጎት ግን አነስተኛ ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡

(ስለአብራሞቪች በzehabesha.com የስፖርት አምድ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይኖራል።)

ከባድ ሸክም ከአርሰን ቬንገር ትከሻ ተነሳ፡፡ በጣም ከባድ፤ ለዚያውም የ10 ሚሊዮን ፓውንድ ሸክም፡፡ ሴባስቲያን ስኩዊላቺ፣ ዴኒልሰን እና አንድሬ አርሻቪን ያለምንም ጥቅም ክለቡን በደመወዝ መልክ በዓመቱ በድምሩ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ሲያስወጡ ኖረዋል፡፡ አሁን የአርሰናል ንብረት አይደሉም፡፡ ይህም ለደጋፊዎች መልካም ዜና ነው፡፡ ሆኖም ወሬው በእርግጥም መልካም እንዲሆን አሰልጣኙ 10 ሚሊዮን ፓውንድን መልሰው ለቡድኑ ማጠናከሪያ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ፈረንሳዊው ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት የተሸረፈ እና የተቆጠበውን ገንዘብ ለማይወደደው የክለቡ ቦርድ አሳልፈው ከሰጡ የተጨዋቾቹ ሽያጭ የፈጠረው ደስታ ከደጋፊዎቹ ጋር አይቆይም፡፡

ይሁን እንጂ አርሰናል ለዓመታት ያለአግባብ ታቅፎ የያዛቸውን እና ላልተገባ የደመወዝ ወጪ የዳረጉትን ተጨዋቾች መሸኘት መጀመሩ እንደበጎ ጅምር ተወስዶለታል፡፡ በተለይ አሰልጣኙ እነዚህን ሂያጆች በአዳዲስ እና በተሻሉ ተጨዋቾች ካልተተኩ እርምጃቸው ሙሉ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ቬንገር ተጫዋቾችን ለመሸጥ ወይም በነፃ ለመልቀቅ አዲስ አይደሉም፡፡ ሆኖም ሰውዬው ምርጥ ተጫዋቾቻቸውን ከሸኙ በኋላ ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ያሉ ከዋክብትን ለመተካት ሲቸገሩ ኖረዋል፡፡ ለዓመታትም በተመሳሳይ መልኩ ተጉዘዋል፡፡

ቬንገር ዴኒልሰን ትቶት የሄደውን 50 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ እንዲሁም የስኩዊላቺን 60 ሺ ፓውንድ እና የአርሻቪንን 85 ሺ ፓውንድ ተቀብለው አርሰናልን መጥቀም የሚችሉ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ማምጣት ይችላሉ፡፡ የዝውውር ሂሳቡን ትተን ስለደመወዝ ብቻ ካወራ አሰልጣኙ የሶስቱን ተሰናባቾች ገንዘብ ተጠቅመው ሁለት ትልልቅ ስም ያላቸው ተጨዋቾችን በ90 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ

ሊያስፈርሙ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ትልቅ ተጨዋች እና ሁለት ሌሎች የቡድኑን ጥልቀት እና ጥራት ከፍ የሚያደርጉ ከዋክብትን ደመወዝ ቀጥ አድርጎ ይይዝላቸዋል፡፡

አርሰን የማይጠቀሙባቸውን ተጨዋቾች መሸኘታቸው እና በሌሎች መተካታቸውን በጀታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲጠቀሙ ከማድረጉም ሌላ የቡድናቸውን ጥራት በትልቁ ያሳድግላቸዋል፡፡ ቬንገር በግብ ጠባቂ ቦታ ወጣቶችን ቢይዙም አንዳቸውም በደጋፊዎች እምነት የሚጣልባቸው አልሆኑም፡፡ በኢምሬትስ ከቮይቾች ቼዝኒ እና ሉካስ ፋቢያንስኪ በመቀጠል የቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ የነበረው ቪቶ ማኖኔ ወደ ሰንደርላንድ ሲያመራ የተሸጠበት ዋጋ ይፋ ባይሆንም አርሰናል 2 ሚሊዮን ፓውንድ ሳያገኝበት እንዳልቀረ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መድፈኞቹ በንፅፅር ወጣት የሚባልን የ25 ዓመት በረኛ ቢያጡም የጣልያናዊው ክለቡን መልቀቅ ለሌላ ልምድ ያለው ግብ ጠባቂ በር መክፈቱ እርግጥ ይመስላል፡፡ በተለይ ከአርሰናል ጋር ድርድር ላይ መሆኑ የሚነገርለት ዡሊዮ ሲዛር ክለቡን

ከተቀላቀለ ለሌሎቹ ሁለት ወጣት ፖላንዳዊያን ጥሩ ልምድ ሊያካፋል እና ቡድኑንም ወደ ውጤት ሊያመራ ይችላል፡፡

ሌላኛው የክለቡ ተሰናባች በኤምሬትስ ረጅም ጊዜ የቆየው ዮሀን ዡሩ ነው፡፡ ስዊዘርላንዳዊው ተከላካይ በተለይ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከሁለት የካፒታል ዋን ግጥሚያዎች ውጪ በቋሚነት የጀመረው ግጥሚያ የለም፡፡

በጃንዋሪ ወደ ጀርመኑ ሆኖቨር በውሰት አቅንቶ 16 ጨዋታዎች ካደረገ በኋላ ክለቡ ዝውውሩን ቋሚ ለማድረግ ፍላጎት አሳይቷል፡፡ ሆኖም የ26 ዓመቱ ዡሩ ከሀኖቨር ይልቅ የክለቡን ተፎካካሪ ሀምቡርግን መቀላቀል የመረጠ ሲሆን አዲሱ ክለቡም አሁን ዝውውሩ በውሰት ውል ተይዞ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ በቋሚነት ሊገዛው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡ ይህም በመሀል ተከላካይ ቦታ የስዋንሲውን አሽሊ ዊልያምስ ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት ያጠናከርለታል፡፡ የ2012/13 የውድድር ዘመንን በውሰት ውል በጁቬንቱስ ያሳለፈው ኒክላስ ቤንድትነርም በኤምሬትስ እህል ውሃው አልቋል፡፡ በገዛ ፈቃዱ ወደ አርሰናል እንደማይመለስ በትዕቢት ሲናገር የቆየውን ዴንማርካዊ ደጋፊዎቹ ማየት አይሹም፡፡ ባለፉት ቀናት በወጡ መረጃዎች መሰረት የጀርመኑ ኢንትራክት ፍራንክፈርት

በግዙፉ አጥቂ ላይ ያለውን ፍላጎት አጠናክሯል፡፡ የተጫዋቹ ወኪል ቶም ብሩክስም ‹‹አሁን ብዙ ባልናገር እመርጣለሁ፡፡ ሆኖም ዝውውሩ በቀናት ውስጥ እውን እንደሚሆን ተስፋ አለኝ›› ሲል ጉዳዩ እያለቀ መሆኑን አብራርቷል፡፡ በአርሰን ዌንገር ዙሪያ ተጨማሪ ማንበብ ከፈለጉ zehabesha.com ላይ ይግቡ።

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page

የፎቶ ግራፍ ምንጭ hamrofootball

የፎቶ ግራፍ ምንጭ ዘጋርዲያን

የፎቶ ግራፍ ምንጭ ሬውተርስ

Augsburg College፡ 2211 Riverside Avenue South, Minneapolis, MN 55454

ለበለጠ መረጃ 612-986-0557 ይደውሉ

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ከደበበ ወልደገብርኤል ክፍል 3ና የመጨረሻው መርማሪዎቹ ተጠርጣሪውን ወደ ጎባ ከተማ ፖሊስ

ወስደው ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያደርጉ ባለፈው ዕትማችን የቆምንበት ነበር፡፡ ቀጥሎ ያለውን ልናስነብባችሁ ሰንቀን ቀርበናል፡፡ ጥያቄ ሲቀርብለት አጥጋቢ መልስ ባለመስጠቱና ጉዳዩም መርማሪዎች ላይ ጥርጣሬ ስለፈጠረ

የዛቻ ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተነገረው ሰው ማንነትና ሥራ-ለመለየት ተጨማሪ ምርመራ ከተደረገ በኋላ ቡድኑ ወደ ሮቤ ከተማ በመሄድ ከፍተኛ ክትትልና የመረጃ ማሰባሰብ ሥራ ሲያደርግ ቦጋለ የተባለ መፅሐፍ ቤት ወይም ዳቦ ቤት ይሰራል የተባለው ሰው ውሸት እንደሆነና የተባለውን ሥራ የሚሰራ ሰው የሌለ መሆኑን አረጋገጠ፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ዲንሾ ከተማ የተጓዘው የምርመራ ቡድን ባደረገው ጥረት የሟችን ቤተሰብ አፈላልጎ በማግኘት አስፈላጊውን መረጃ ካጠናከሩ በኋላ ቀጣዩ ሥራ ወላጅ ቤተሰቦችን ወደ ጎባ እንዲመጡ በማድረግ ለወንጀሉ አፈፃፀም ሊረዳ የሚችል ፍንጭ የሚገኝ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ የማጠናከር ስራ ማከናወን ሆኗል፡፡

በዚህም መሰረት አባት ቄስ ንጉሴ ገ/ስላሴ፣ እህት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ንጉሴ እና ወ/ሮ ዘውዴ ንጉሴ የተባሉት ዲንሾ ከተማ ተገኙ፡፡ ሌላኛዋ እህት ወ/ሮ ወለላ ንጉሴ ደግሞ ሮቤ እንደምትኖር ያውቁ ነበርና ፈልገው አገኟት፡ ፡ ከሟች ጋርም ሮቤ ከተማ ውስጥ በቅርበት እየተገናኙ አልፎ አልፎ ይጠያየቁ እንደነበር አመልካች ፍንጭ ተገኘ፡፡ የሟች ቤተሰቦች ፖሊስ ጣቢያ ሲደርሱ ለቅሷቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው የመርዶ ቀዬ አስመሰሉት፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብም ቀስ በቀስ የለቅሶውን ድምፅ እየሰሙ የሀዘኑ ተካፋይ ሆኑ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀምና በሟች ቤተሰቦች ሌላ ችግር እንዳይፈጠር ፖሊስ የወንጀል መከላከል ስራውን አልዘነጋም፡፡

ሁኔታውንም አረጋግቶ የመጡበትን እዲያስረዱ ለማድረግ አግባባቸው፡፡ ከፖሊስ፣ከአስተዳደር ከቀበሌ የመዋቅር አካላትና የሀገር ሽማግሌ እንዲሁም ከተውጣጡ የሕብረተሰቡ ክፍሎች

ጋር ሆነው የሟችን ወላጅ ቤተሰቦች እያፅናኑም መረጃም በሚስጥር እየተለዋወጡ ከፖሊስ ጣቢያው ወጡ፡፡

ከግቢው 15ዐ ሜትር ርቀት ከተጓዙ በኋላ ወደ ቢንጃ የገጠር ቀበሌ ገ/ማህበር በሚወስደው መንገድ ታጠፉ፡፡ በቦታው ደረሱ እና ከግቢው ውስጥ ገቡ፡፡ ከግቢው ውስጥ በክርስትና እምነት ተከታዮች አለምን ሲሰናበቱ የቀብር ስነስርዓት የሚፈፀምበት ክልል መሆኑን እንዳዩ በእጅጉ እያለቀሱና እየጮኹ ለቅሶና ዋይታውን አቀለጡት፡፡ የአልማዝ አስከሬን በክብር ያረፈበትን ቦታም አሳዩዋቸው፡፡ በእለቱ የነበረው ለቅሶና ከባድ የሀዘን ትእይንት ተረጋግቶ እንዳበቃ እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡ የሃይማኖት አባቶችም ማፅናናት ካደረ ጉላቸው በኋላ የቤተክርስቲያኑን ቅጥር ግቢ ለቀው ወጡ፡፡

የምርመራ ቡድኑ እና የሟች ቤተሰቦች 6 ኪሎ ሜትር ወደ ምዕራብ ጎባ ተጉዘው ደረሱ፡፡ ከተባለው ቦታም ሲደርሱ በርካታ አባቶች፣ ምዕመናን እና የምዕራብ ጎባ ቀበሌ የየቀጠናውና የጎጥ ተጠሪዎች ተሰባስበው ጠበቋቸው፡፡ ሰፊ ውይይትም አደረጉ፡፡ መርማሪዎችም አጋጣሚውን ተጠቅመው የተለያዩ መረጃዎችን ሰበሰቡ፡፡

በዚህ ስፍራ የገዳሙ አካባቢ ነዋሪዎች እና ምዕመናን ሲያነጋግራቸው የነበረው ነገር “እንዴት በዚህ ቅዱስ ስፍራ እህታችን ተገድላ ተጣለች” የሚል ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የምርመራ ቡድኑ ከወረዳው አቃቢ ህግና ከፖሊስ የወንጀል

መከላከል አባላት ጋር ስራቸውን ተከፋፍለው ለ17 ቀን ያህል በየአቅጣጫው ተሰማርተው አንዱ ቡድን በገዳሙ

አካባቢ፣ ሌላው በሮቤ ከተማ፣እንዲሁም ሌሎች አጋሮች የተገኘውን መረጃና ፍንጭ እየጨመቁና እየተነተኑ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አለው ባሏቸው ነገሮች ዙሪያ ውጤት ለማምጣት መሮጣቸውን ቀጥለዋል፡፡ ሟች በሮቤ ከተማ ውስጥ ቤት ተከራይታ

እንደምትኖርና ቀን ቀን ቅመማ ቅመም ንግድ ገበያ እየሰራች ማታ ማታ ትምሀርት እንደምትከታተልና

እራሷን ለመለወጥና በወጣትነት ጊዜዋ የአቅሟን ሁሉ በማድረግ ኑሮዋን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት ታደርግ እንደነበር የተጨበጠ መረጃ አለ፡፡

የመጀመሪያው ጥርጣሬ በህይወት ዘመኗ ዲንሾ ከተማ ውስጥ የትዳር ጥያቄ ቀርቦላት እርሷና ቤተሰቦቿም እምቢ በማለታቸው ሳቢያ ለጋብቻ ጠይቀው በነበሩ ቤተሰቦችና በሟች ቤተሰቦች መካከል የቆየ ቅሬታ እንደነበርና በተለይ የሟች የቅርብ ዘመድ በሆኑት ቄስ ንጉሴ ላይ ተሰንዝሮ

በነበረው ዛቻ እና ማስፈራራት የሟች አባት ዲንሾ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሄደው አቤቱታቸውን አቅርበው ነበር፡፡ የምርመራ ቡድኑ ከዚህ ጥርጣሬ ተነስቶ ሶስት ተጠርጣሪዎችን አስሮ ሲያጣራ ቢሰነብትም ይህንን ጉዳይ የሚያጠናክር መረጃ ባለመኖሩ እስረኞች ተፈትተው ወደ ሌላ የጥርጣሬ አቅጣጫ ለማዘንበል ተገዷል፡፡

በሦስተኛ የምርመራ ቡድኑ የጥርጣሬ አቅጣጫ ደግሞ ከሟች ጋር አብሯት የሚኖር የፍቅር ጓደኛ እንዳለና ይህ ሰው ለጋብቻ ሲጠይቃት በትዳር አብራ ለመኖር ፍቃደኛ ባለመሆኗ የግለሰቡን የትዳር ጥያቄ ወደ ጎን በማለቷ “ለምን ናቀችኝ” የሚል እሳቤ በውስጡ አድሮበት ስውር የግድያ ወንጀል ፈፅሞባት ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አጭሮባቸዋል፡፡ በአራተኛው የምርመራ ቡድን ለውይይት የቀረበው ደግሞ ሟች በህይወት እያለች ሮቤ ከተማ በነበረችበት አጋጣሚ ማንነቱን በውል የማታውቀው ግለሰብ አባትሽ መምሬ ንጉሴ በጠና ታመዋል ነገ ዛሬ ሳትይ ተዘጋጂና አብረን ሄደን እንጠይቃቸው እያለ ሲያጨናንቃት እንደሰነበተና ጉዳዩ ግራ ሲያጋባት ስልክ ደውላ የአባቷን ሁኔታ ባረጋገጠችበት ወቅት የተባለችው ነገር የተሳሳተ እንደሆነና አባቷም ጭራሽ እንዳልታመሙ አረጋግጣለች፡፡ ያልታመሙና በሠላም ዲንሾ ከተማ ባለው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ያሉ መሆኑን በተረዳች ጊዜ ዝም ብላ በጉዳዩ ስትገረም ከቆየች በኋላ ውላ አድራ ለወላጆችዋ እና ለእህቶችዋ ነግራ እንደነበርም በምርመራ እንደተደረሰበት ምን አልባት ይህ ነገር የመርማሪ ዎቹን ጥርጣሬ በይበልጥ ሊያጎላ የሚችል መረጃ ቢሆንም ሟች የሰውዬውን ማንነት ባለመግለጿ ምርመራውን አስቸጋሪ ቢያደርግባቸውም መረጃው ግን አግኝተዋል፡፡ የአምስተኛው ምርመራ ቡድን የጥርጣሬ አቅጣጫ ደግሞ ሟች በህይወት ዘመኗ የራሷን ገመናና የግሏን ሚስጥር ለማንም ሰው የማትገልፅና የማታካፍል ሴት መሆኗን በቅርብ የሚያውቋት ሰዎች፣ወላጅ ቤተሰቦቿና፣እህቶቿም ጭምር መረጃ በመስጠታቸው ያልተደ ረሰበት ለግድያ የሚያበቃ ጉዳይ ይኖር ይሆን ብለው ለመንቀሳቀስ መርማሪዎቹ ሞክረው ሁኔታው ዝግ ቢሆንም በትዕግስት በጉዳዩ ዙሪያ የምርመራ ስራቸውን በስፋትና በጥልቀት አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

በዚህ የምርመራ ሂደትም በወንጀሉ የሚጠረጠሩ ሰዎችን ለማግኘት በርካታ ፖሊሳዊ ትንታኔዎች ተደርገዋል፡፡ የእስካሁኑ የምርመራ ግኝት የተጠርጣሪ ግለሰቦችን ስም ተለይቶ ባለመቀመጡ መርማሪዎቹ ገና ብዙ ሥራ ከፊታቸው እንደሚጠብቃቸው በማመን አማራ ጮችን ማፈላለግና

መጠቀም ግድ ይላልና ሀሳቦችን ማመንጨት ጀመሩ፡፡ በሮቤ ከተማ ውስጥ በአደገኛ ወንጀለኛነት የሚጠረጠሩ

ወጣቶችን መረጃ ማሰባሰብ አንዱ ምዕራፍ ነበር፡፡ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ ወጣቶችንም መዳሰስ እንዳለበት በምርመራ ቡድኑ የሚታመን ጉዳይ ነበር፡፡የምርመራ ቡድኑ በትንተና እና በቅድመ መረጃ ማሰባሰብ ወቅት የተገኙትን መረጃዎች ገምግሞ ከፍተኛ ጥንቀቄ በማድረግ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተማምነዋል፡፡

የምርመራ ቡድኑ ካካበተው የመረጃ ስብስብ በመነሳት የወንጀሉ አፈፃፀም ውስብስብና በተቀናጀ መንገድ እንደሚሆን አስቀድሞ በመተንበይ ወንጀለኛው ላይ ለመድረስ ብዙ መላ ምቶችን እየተነተነ በየአቅጣጫው መጓዙን እንደቀጠለ ነው፡፡

ከዚህም በመነሳት ይበልጥ ትኩረቱን ወደ ሳበው አንድ ግለሰብ አነጣጥሯል፡፡ ይህ ሰው ሟች አልማዝን በአልጋ አንጣፊነት ቀጥሯት የነበረ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት፤እርሷም የፍቅር ጥያቄውን ባትቀበለውም ለጊዜው አማራጭ በማጣቷ በሰላም ለመኖር ስትል ጥያቄውን ለማስተናገድ ተገዳ እንደነበር ጉዳዩን የሚያውቁ ተናግረዋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ በማርገዟም ለአስረገዛት ሰው ከብዙ ጭንቀት በኋላ ማርገዟን ነገረችው፡፡ እርሱም በማርገዟ ተቀይሞ “የራስሽ ጉዳይ” ቢላትም አልማዝ ግን ሌላ አማራጭ የሌላት በመሆኑ ለችግሯ መፍትሔ ለማግኘት ስትል ሰውዬውን ተለማምጣ ለፅንሱ ማቋረጫ ሦስት መቶ ብር በብድር መልክ ስለሰጣት ፅንሱን ማስወረድ ቻለች፡፡

ይህ ከሆነ በኋላ ሀብትና ጉልበቱን ተማምኖ የሴትነት ክብሯን የተፈታተናትን ሰው ለመራቅ ወሰነች፡፡ ያሰበችው ይሳካ ዘንድም ትንሽ ቤት ተከራይታ በአነስተኛ ገንዘብ የቅመማ ቅመም ንግድ ጀመረች፡፡ እራሷን ለመቻል በጥረቷ ጥላው የወጣችው ሰው እንደገና አፈላልጎ አድራሻዋን አገኘ የፍቅር ግንኙነቱንም በኃይል ተጠቅሞ ድጋሚ ለማስቀጠል በማሰቡ ነጋ ጠባ ቤቷ ድረስ እየመጣ ማስቸገሩን ቀጠለ፡፡ የትም ብትሄድ ከወንዶች የትንኮሳ ጥያቄ ማምለጥ የማትችለው አልማዝ ለዚህ ያበቃትን ቁመናና የሴትነት ው በቷን እያማረረች የተሻለ አማራጭ እስክታገኝ ድረስ ተሸንፋ መኖርን እንደ አማራጭ መውሰዷን አብረዋት ይኖሩ የነበሩ ጎረቤቶቿ ያዩትና ይሰሙት የነበረውን ለምርመራ ቡድኑ አስረድተዋል፡፡ የምርመራ ቡድኑም ይህንን ፍንጭ ተከታትሎ ባደረገው እልህ አስጨራሽ ምርመራ አንድ ቀን ከሠርግ ውላ ስተመለስ አቁሞ እንደዛተባትና ፅንሱን ለማስወረድ የሰጣትን ሦስት መቶ ብር እንድትመልስለት መጠየቁን የምርመራ ቡድኑ ደርሶበታል፡፡

‘ፍቅር እና ወንጀል” በሚለው አምዳችን በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ እዚህ አሜሪካ ውስጥ የሚፈጸሙ እውነተኛ የፍቅርና የወንጀል ታሪኮችን እንዲሁም ሌሎችን ዘገባዎችን እናቀርብበታለን።

የጤፍ እንጀራችን ለምን ተወዳጅ

እንደሆነ ለማረጋገጥ ዛሬውኑ

ይቅመሱት

እውነተኛ የፖሊስ ምርጥ

ምርመራ

651-214-2584 ወይም 651-489-9220 ደውሉ

ተመስገን... ከገጽ 7 የዞረ

ይሄ የአንድ ጋዜጠኛ ተግባር ሊሆን ይገባዋል? ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆነ አገር የሌለው ብቻ ነው። አገር

የሌለው ደግሞ ማን አለ? ማንም የለም። ጋዜጠኛ ብሆንም የራሴ የሆነ የፖለቲካ አቋም አለኝ። ጽሑፎቼ ላይ አቋሞቼ ሊንፀባረቁ ይችላሉ። ሥርዓቱ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመተቸት ያልከውን ጽሑፍ ጽፌዋለሁ። አምስት ዓመት ያህል የጻፍኩት ግን ‹‹የፈራ ይመለስ›› ብቻ ብዬ አይደለም።

የአንድነት ፓርቲ ልሳን ከነበረችው እና ስትንፋስዋ ከተገታው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ፣ የፖለቲካ አቀንቃኝ (Political Activist) ስለ መሆንህ ጥያቄ ቀርቦልህ ‹‹አዝማሚያው ሊኖር ይችላል›› ብለህ ነበር። ታዲያ ይህ ከጋዜጠኝነት መርሕ ጋር በእጅጉ አይጋጭም?

‹‹የፖለቲካ አቀንቃኝ ነህ?›› ያለው ጠያቂው እንጂ እኔ አይደለሁም።

አንተም ግን ‹‹አክቲቪስት ነኝ ባልልም እስከ ዛሬ ፍትሕ ታደርግ የነበረው ከዚህ የዘለለ አይደለም›› ስትል ምላሽ ሰጥተሀል። ‹‹ጽሑፎቼ ያንን ስያሜ ለማሰጠት አጋድለው ሊሆን ይችላል›› ነው ያልኩት። አንባቢ ከጽሑፍህ ተነሥቶ አርበኛ ሊልህ፣ ፅንፈኛ ሊልህ፣ የተቃውሞ ፖለቲካ አቀንቃኝና ሌላም ሊልህ ይችላል። እነዚህ ሁሉ ምድቦች ግን እኔ ውስጥ የሉም። ራሴን የምቆጥረው በአገሩ ላይ የተሻለ ነገር እንዲፈጠር የሚጥር አንድ ጋዜጠኛ አድርጌ ነው።

ስለ ስደተኛ ጋዜጠኞች ያለህ አቋም ምንድን ነው? ኧኧኧ… [ሳቅ… የቁጥብነት ስሜት እየታየበት] ማንም ሰው

‹‹ለምን የእኔን ፅዋ አልጠጣም?›› ብለህ ልትወቅሰው አይገባም።

የራሱ መከራ የመቀበል አቅም የት ድረስ እንደሆነ ያውቀዋል። እዚያ ደረጃ ሲደርስ ማንም ሰው ይሰደዳል። ለእኔ ግን መሰደድ የሚወገዝ ተግባር ነው።

ጋዜጠኛ መፍራት/መሸሽ የለበትም እያልክ ነው? የመፍራት ጉዳይ ብቻ ሆኖ ሳይሆን ችግሩ እኮ ያለ ነገር

ነው። እናንተ ጋዜጣ ለመጀመር ፈቃድ ጠይቃችሁ የነበረው የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ‹‹ልከሰስ ነው›› ብሎ በሸሸበት፣ አዲስ ነገሮች የተሰደዱበት ሁኔታን እያወቃችሁ ነው። እና ታዲያ ‹‹ይህ ጸበል ለእኛ አይደርሰንም›› ብላችሁ ታስ ባላችሁ? ታዲያ ልከሰስ ነው፣ ልታሰር ነውን ምን አመጣው?

ስለዚህ ለተሰደዱ ጋዜጦች ምንም ክሬዲት አትሰጥም ማለት ነው?

[እየሳቀ] ያው ገልጬዋለሁ ‹‹የተሰደዱ ጋዜጠኞች ለፍተዋል፣ ሠርተዋል›› ብዬ ላስተካክለው? [ሳቅ] የእውነት ሠርተዋል፤ ለፍተዋል። ሲሰደዱ መከራን የመቀበል አቅማችን እዚህ ድረስ ነው ብለው ነው። ባይሰደዱም ያሉት ነገር (እስር) ሊተገበርባቸው ይችል ነበር። የእኔ ቅሬታ ኢሕአዴግ የለየለት አፋኝ በመሆኑ የጋዜጣ ፈቃድ ሲወስዱ ይህ እንደሚሆን ስለሚያውቁት ከመሰደድ ይልቅ ፊት ለፊት መጋፈጡ የተሻለ ነው የሚል ነው። የምንፈልገውን ውጤት የምናመጣው መስዋዕትነት በመክፈል ነው። ጋዜጠኛ የሐሳብ ተዋጊ ነው፤ ምሽጉ ደግሞ ሚዲያው ነው። ስለዚህ መስዋዕትነቱን እየከፈለ ምሽጉን መልቀቅ አይገባውም። ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ግን በምንም መልኩ ጥፋተኛ ልናደርጋቸው አይገባም። የሸሹ ሰዎች ጥፋተኛ ናቸው አለማለቴ እንዲታወቅልኝ ግን እፈልጋለሁ።

አገር ውስጥ ሆነው የሰላ ትችት ለሚሰነዝሩት ክብር ሰጥቶ በተቃራኒው የተሰደዱትን ክሬዲት ማሳነስ ልክ ይሆናል? አገር

ውስጥ ካሉት ከተሻለ በውጪ ወጥተውም አበርክቷቸው ያልተቋረጠ (እየሠሩ ያሉ ጋዜጠኞች) አሉ ብዬ ስለማስብ ነው። እንዳሉት የሚታሰሩ ከሆነስ ወጥተው የሚችሉትን ማበርከታቸው ተገቢ አይሆንም?

ግልፅ እንዲሆን የምሻው ስደተኛ ጋዜጠኞች ፈሪዎች፣ የማይሸሹ ጋዜጠኞች ደግሞ ደፋሮች ናቸው አላልኩም። ድፍረት እና ፍርሃትን ከዚህ ውስጥ እናውጣው! ነገር ግን የቁርጠኝነት ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። መከራ የመቀበል ደረጃ ልዩነት እና የስልት ጉዳይም ነው። እኛ (ፍትሖች) ‹‹እዚሁ ቆስለን፣ እዚሁ ደምተን እንሠራለን›› ስንል፣ ሌሎች ጋዜጠኞች ደግሞ ‹‹ከመታሰር ከአገር ውጪ ሆኖ አስተዋፅኦ ማድረግ የተሻለ ነው›› ይላሉ። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ነው። በእኔ እምነት ግን ከአገር ውጪ ሆኖ መሥራት የተሻለ አይደለም፤ እዚህ ሆኖ የመጣውን በጸጋ መቀበሉ የለውጡን ቀን ያቀርበዋል። በተረፈ ትክክሉ ለየራሳችን የሚተው ነው።

የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን አስመልክቶ ‹‹ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ ነገር ይኖራል ጠብቁ›› ብለህ ፌስቡክ ላይ ገልጸህ ነበር። በሁለተኛው ቀን ማረፋቸው ተነገረ። የኢሕአዴግ የውስጥ ምንጮች አሉህ?

ምንም የማያከራክረው ፍትሕ በአገሪቷ ትልቅ ጋዜጣ ነበረች፤ ዋና መስፈርቱ የኅትመት ቁጥር በመሆኑ። የብዙ ሰዎችን ትኩረት ስለሚስብ መረጃዎች ወደ እኛ ይመጣሉ። ሥርዓቱ አገርን እየጎዳ እንደሆነ የሚገነዘቡ የሥርዓቱ ወሳኝ የሆኑም/ያልሆኑም ሰዎች አገርን ከማዳን አኳያ፣ እኛን በማመን አንዳንድ መረጃዎችን ያቀብሉናል። ጽሑፎችህ ጥልቀት እንደሌላቸው እና ሰዉ ‹‹የእኔ›› ብሎ እንዲያነብ ሰሞነኛ ብሶታዊ ስሜትን ማንፀባረቅ ላይ እንደምታተኩር የሚተቹህ አሉ።

ሁሉም ጽሑፎቼ ላይ ባይሆንም ይሄ ዓይነት ነገር አለ ብዬ አስባለሁ። ፍርሃትን በመግፈፍ ሕዝብን ወደ አደባባይ መሰብሰብን ስለማልም፤ [አደባባይ ስል አብዮት አደባባይ አይደለም] ሕገ- ወጥነትን እምቢ እንዲል የማንቃት ባሕሪ ዋና ዓላማዬ ስለሆነ ሕዝባዊ እና ስሜታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩራለሁ። በአገራችን ላይ የጠፋው ነገር የርዕዮተ ዓለም ዳሰሳ እና ትንተናዎች ሳይሆን [ይሄን በቂ ምሁራን ብለውታል] ፍርሃትን ማሸነፍ ነው። ለዚህ ደግሞ መፍትሄው አብዮታዊ ዲሞክራሲን ከሊበራል ዴሞክራሲ ጋር እያነፃፀርክ መተንተን አይደለም። የጠቀስካቸውን ጉዳዮች መዳሰስ ነው። ከዚህ አኳያ እንዳልከው ጥልቅ ትንታኔ ላይኖረኝ ይችላል። ‹‹የፈራ ይመለስ›› ለማለት ጥልቅ ትንታኔ አያስፈልግህም። አምስት ዓመት የተጻፉት ጽሑፎች ሁሉ ጥልቀት የሌላቸው ናቸው ብዬ ግን አላስብም።

ከሐሳብ ሙግት ይልቅ ግለሰቦችን ‹‹መጭረፍ›› ላይ ታተኩራለህ። መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ፕ/ር አንድሪያስ እሸቴ፣ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ፋሲል ናሆምና ሌሎችም ላይ ግላዊ መሠረት ያለው ትችት አቅርበሀል። ችግሮች ያሉት ግለሰቦቹ ጋ ነው ወይስ ተቋማዊ አሠራሩጋ?

ገበያ ላይ ከዋሉ 197 የፍትሕ ኅትመቶች ውስጥ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጽሑፍ ላይ እኔ አለሁ። [በነገራችን ላይ የፍትሕ የመጀመሪያዎቹ ሕትመቶች ላይ ተመስገን በስሙም ሆነ በብዕር ስም የጋዜጣዋን ከግማሽ በላይ ገጾች ይሸፍን ነበር።] ከዚያ ውስጥ ግለሰብ ላይ ያተኮርኩት በጣም ጥቂት ጽሑፎች ላይ ነው። ግለሰቦች ላይ የጻፍኩት እኮ አምስት ጊዜ ብቻ ነው።

(በመጽሐፉ ላይ የተካተተው የተመስገን ቃለ ምልልስ ይህ ብቻ አይደለም። ተጨማሪ ቃለ ምልልሱ በzehabesha.com ላይ ይገኛል።)

መዝ. ዳዊት 68:31

ዘወትር አርብ ከምሽቱ 6-8 ሰዓት የምናደርገው ፕሮግራም የተጠበቀ ነው

1901 Portland Ave. South Minneapolis, MN 55404

በእግዚአብሔር እጅግ የተወደዳችሁ ወገኖቼ! ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ እግዚአብሔር በየግላችን፣ በየቤተሰባችን፣ በየነገዳችን፣

አልፎም እንደ አንድ ሃገርና ሕዝብ ሊጎበኘን እንደተነሳ እርግጠኛ ነኝ። በአውሮፓውያን ዘመን

አቆጣጠር ከኦገስት 1 ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ

ከጠዋቱ 10 እስከ ረፋዱ 12 ሰዓት ለህፃናት፣ ለልጆች፣ ለወጣቶች፣ ለአባቶችና እናቶች በአጠቃላይ

ሕዝባችንን ወክለን ጸሎት እናደርጋለን።

በጸሎትና ሕዝባችንን በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ለመድረስ የምትፈልጉ

ለፓስተር ደስታዬ በ612-225-8269 ይደውሉ።

በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ሆናችሁ ፀሎት ለምትፈልጉ ለፓስተር ደስታዬ በስልክ ቁጥር 612-225-8269

በተጨማሪም ለልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ለጸሎትና በአሁኑ ወቅት ከትምህርት ቤት በእረፍት ላይ ላሉ ህጻናትና ወጣቶች ያላቸውን የ እረፍት ጊዜ ከኛ ጋር እንዲያሳልፉ

እግዚአብሔርን የማመስገኛ ጊዜ አመቻችተናል። በመሆኑም ልጆቻችሁ ከኛ ጋር ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ለምትሹ ወላጆች ደውላችሁ ማስመዝገብ

የምትችሉ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እገልጻለሁ።

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

ከ8 ወደ 10 እንጀራ አደገ

በወንድማችን ምስጋናው የተከፈተው አዲሱ አልፋ ጋራዥ መኪናዎ በማንኛውም ሰዓት ብትጋጭ ወይም ቀለም ሲፈልጉ ቀጠሮ አክብሮ በፍጥነት ያድሳል፤ ለማንኛውም ጥገናም ወደ ጋራዣችን ይምጡ፤ በቂ የሰው ኃይል አለን!

Alpha Auto SalesAlpha Auto Sales Lowest Price Guaranteed!

213 West 29th Street, Minneapolis, MN 55408 651-239-6540

የኛ ትርፍ የደንበኞቻችን ደስታ ነው

We Guarantee Customer SatisfactionWe Guarantee Customer Satisfaction

Interest Interest Free Free

FinancingFinancing

አሜሪካንን... ከገጽ 18 የዞረ

ገባኝ ምን ማለት እንደፈለገ በ እርግጥ ጠርጥሬያለሁ… “ጀለሴ በቃ ዝምብለሽ ነው ምንም አታርፊም ማይሌጅዋ

ማለቴ እድሜዋ ሄዶዋል አርጣለች መውለድ አትችልም የፈረንጅ አሮጊት ናት ልልህ ፈልጌ ነው…”

ማሙዴ ሌላ ሲጋራ አቀጣጠለ አስተናጋጅዋ መጥታ ታዘዘችን እኔ የምርጫዬን አዘዝኩ…ማሙዴም ምርጫውን አዘዘ ግን ምን አይነት መጠጥ እንዳዘዘ ስሙ አሁን ትዝ አይለኝም አብሮኝ ያለው ጉዋደኛዬም የሚፈልገውን አዘዘ…በኔ ምርጫ ግን ማሙዴ ተገረመ እና…

“ፍሬንዴ ታውቂበታለሽ አንቺኛዋ የገባሽ ነሽ አንቺ ግን በቃ ደንበኛ ሸዋ ነሽ…”

አለኝ እና ሳቁን ለቀቀው… ምክንያቱን ታውቅ የለ እንዴ?… አንድ ሁለት ማለት

አላቃተኝም። እያየሃቸው አይደለ እንዴ ፖሊሶቹን ስራ በዝቶባቸው…

አልኩት… “ውይ ውይ ይቅርታ ለነገሩ ዲ ዩ አይ …” ጠጥቶ በመንዳት ስላለ ወንጀል ማለቱ ነው… “የሚበረታው እኮ አትላንታ ነው አንቺ ከመጣሽበት

ከተማ ዲሲ ብዙ አያካብዱም ደስ የሚልሽ በየመጠጥ ቤቱ እና መዝናኛው ደጃፍ ተኮልኩለው የምታያቸው ፖሊሶች መጀመሪያውኑ ሰክረህ ወይንም ሞቅ ብሎህ ገድገድ ብለህ ሲያዩህ ሰር ጠጥተህ መንዳት አትችልም እንዳትነዳ ብለው

ይገላግሉሃል…” በአካባቢው የማያባራ ግርግር እና ሁካታ በሰዎች ሁኔታ

እየደጋገምኩ ስገረም… ማሙዴ በስጨት ብሎ… “ጀለሴ አይግረምሽ ላፍ እዚህ ዛሬ ነች በቃ ነገ ብሎ ንገር

የልም እዚሁ ይበላል ይጠጣል ሲነጋ ትንሽ ለሽ ተብሎ ወደ ስራ ታቀጥኚዋለሽ የሰራሽውን እዚሁ ነው የምታወድሚው በቃ ዲሲን ቶሎ ለቀህ ሙቭ ካላደረግሽ መቃብርሽም እዚሁ ነው…”

ይሄን እያወራን እየተጨዋወትን ሳለ ጉዋደኛዬን ዞር ብዬ ስመለከተው በስልኩ ከፌስ ቡክ ጋር ቢዚ ሆኖዋል ልረብሸው አልፈለግኩም። በዚሁ ቅስበት ሁለት ወጣት ሴቶች ማሙዴን እየጮሁ እየጠሩት በየተራ ተጠመጠሙበት ለእኔ እና ለጉዋደኛዬ ሰላምታ አቅርበውልን ሲያበቁ…

አንደኛዋ… “ማሙዴ ጋብዘን ወይ እንጋብዝህ…” አለችው… “እኔም ተጋባዥ ድምጻዊ ነኝ ዛሬ…” ሲላት… “ታዲያ መርከቡ ቦታ ካለው እኛንም አሳፍረና ምን

አለበት…” አለችችው… ሌላዋ ቤቱ ውስጥ ከተለቀቀው የ እንግሊዘኛ ሙዚቃ

በላይ ከስፒከሮቹ የሚወጣውን ድምጽ ድምጽዋ በልጦ እንዲሰማ እየጣረች…

ጉዋደኛዬ አነጋገርዋ ገርሞት ነው መሰል እሱም ድምጹ እንዲሰማ ጮክ እያለ መለሰላት…

“ለጊዜው መርከብ አይደለም እያሽከረከርን ያለነው…” ቢላት… ማሙዴ ፈጠን ብሎ… “ጢሎ ገባሽ ልጆቹ ጀልባ ነው የያዙት ጀልባ ደግሞ

ታውቂያለሽ ብዙ ሰው አታሳፍርም ትቂት ሰው ነው የምትይዘው…አንዳቸው ካፒቴን አንዳቸው ረዳት እኔ ደግሞ አሳ አጥማጅ ሆነን ነው የዲሲውን ባህር በ አነስተኛ ጀልባ እያቁዋረትን ያለነው…”

ብሎ ሁለታችንንም አሳቀን። ግን ግብዣ ነው የጠየቁት ለሃገራችን ልጆች ያን ያህል ንፉግ መሆን እንደሌለብን እናስባለን እና እኔም ጉዋደኛዬም ያሻቸውን እንዲያዙ ፈቀድንላቸው። ከተንጠለጠልንበት የባለጌ ወንበር ባለግማሽ ማ ዕዘን ጠረጴዛ እንዲጋሩን አመላከትኩዋቸው። አዘው መጨዋወት ጀመርን። አለባበሳቸው የ እርቃን ያህል ነው።

ሆኖም ጥቂት እንደቆየን አንደኛዋ ፈጠን ፈጠን የምትለው…

ካላስቸገርናችሁ እራት አልበላንም… አለች… ታዲያ ምን ችግር አለው እዘዙዋ አብረን እንበላለን አለ…

ጉዋደኛዬ… “እንደዛ ከሆነ ሃበሻ እንሂድ እዛ ነው ጥሩ ምግብ ያለው… አለች ፈጣንዋ… በአንድ ሃሳብ ተስማማን እና ሂሳባችንን ዘግተን ከማራኪ

ልንወጣ ስንጣደፍ ያስተናገደችን አስተናጋጅ… “ይሄን ያህል ሂሳብ ከፍላችሁ አስር ብር ቲፕ ትንሽ

አይከብድም…”

እያለች ገላመጠችን… “የተውንላትን ያህል ጨምረንላት አመስግነን ወደ ሃበሻ

ተጉዋዝን እዚያው ፊትለፊት። ሃበሻ ምግብ የሚሸጥበት ቤት ነው። ምግብ ለማግኘት

ታዲያ ባልኮኒው ፊትለፊት መሰለፍ እና ቀይ መብራት ያለው ቦኖ መቀበል ያስፈልጋል። ተራችንን ጠብቀን ምግባችንን አስቀርበን እየተመገብን ሳለን የት እንደሚኖሩ ጠየቅኩዋቸው።

ሁለቱም ቨርጂኒያ እንደሚኖሩ ነገሩኝ። የዚህን ጊዜ ማሙዴ እጁን አስጠግቶ ቆንጠጥ አደረገኝ…

ምንድነው በሚል መንፈስ አየት ሳደርገው… ወደጆሮዬ ጠጋ ብሎ… “እዚሁ ዲሲ ዩ ስትሬትን ያቃጠሉ ከሁለት በላይ ቦይ

ፍሬንዶች ያሉዋቸው አምታቾች ናቸው” ሲለኝ በውስጤ ፈገግ አልኩኝ… ማሙዴ ጣጣ የለውም መናገር ጀመረ… “ጀለሴ እዚህ እኮ ልክ ሃገር ቤት የጨርቆስ ልጆች

ሰፈራቸውን ሰትጠይቂያቸው ቦሌ…እንደሚሉት ነው ገባሽ አይደለ …”

ብሎ ሲስቅ… አንገቴን እየነቀነቅኩ በምልክት እንደገባኝ አሳየሁት… ፈጣንዋ እና ቀለብላባዋ ፈጠን ፈጠን እያለች… “ምን ለማለት ፈልገህ ነው ?… ብላ ማሙዴን ገላመጠቸው። ቀጠልኩኝ… የት ነው የምትሰሩት ? አልኩዋቸው ሁለቱንም (አሜሪካንን... ወደ ገጽ 17 የዞረ)

ሳፋሪ ፋሽን የሙስሊም ሃይማኖታዊ አልባሳትን ለወንዶችም ሆኑ ለሴቶች በብዛትና በጥራት ይዞ ቀረበ።

በተጨማሪም ሽቶዎች፣ የፀሐይ

መነጽሮች፣ የጸጉር ውበት መጠበቂያዎች፣ የቆዳ ማስዋቢያዎች፣ ቀበቶዎችንና ጫማዎችን ይዞ ቀረበ።

ከዱባይ የመጡ ብርድ ልብሶችን እና ትራሶችን

በተመጣጣኝ ዋጋ

በተጨማሪም በተወከል ኤክስፕረስ ገንዘብ ወደፈለጉበት

ሃገር በፍጥነት እናደርሳለን።

የቴሌፎን ቢሎችን እኛ ጋር መክፈል ይችላሉ።

የማዕድ ቤት እቃዎችም አሉን።

607 Cedar Ave Minneapolis, MN 55454

July 2013 ᴥ volume IV ᴥ No. 53 ሐምሌ 2005 ᴥ ቅጽ IV ᴥ ቁጥር. 53

ገጽ page ለበለጠ መረጃ www.zehabesha.com

At Furniture CFW we understand your goal of having a warm and inviting home – not just a house. We offer the highest quality furniture, a vast array of styles, and excellent value so that your goal can easily become a reality.

2941 Chicago Ave Minneapolis, MN 55407 612-998-5300

We offer Fairytale We offer Fairytale

Wedding Settings and Wedding Settings and

fantasy event fantasy event

decor by a Professional decor by a Professional

Florist. Elegant back-Florist. Elegant back-

drops and fabulous drops and fabulous

floral arrangements. floral arrangements.

We are conveniently located at 2508 Riverside Ave.,

in Minneapolis. Call us at (612) 338- 2275 or

(763) 498-2554 or visit us at www.riversidekellofloral.net

SERVICES: Church decorations Reception hall decorations, including

aisle treatment Bouquet, boutonnières & corsage- silk or Natural

Chair covers table close Cake table décor

We can create a custom wedding floral arrangement, floral centerpiece, flower girl

basket, or any floral design for that special occasion. We listen to your ideas and

use our artistic abilities to create floral works of art for your wedding.

ALL MANNER OF HIGH END DECORATIONSALL MANNER OF HIGH END DECORATIONS tailored to suit your dream and funds! We are available for all of your

wedding decoration needs

የአድራሻ ለውጥ

አድርገናል

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት

ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ

ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ