23
ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ ‹‹ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ተሸማቅቀው፣ ክብርና ነፃነት አጥተው እየኖሩ ነው›› አቶ ገብሩ አስራት (የወቅቱ የመድረክሊቀ-መንበር) የወር ወጪው 100 ብር የማይሞላው አሜሪካዊ - በኢትዮጵያ የአንድነት ፓርቲ ሊቀ-መንበር የሆኑት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በፖለቲካው ዓለም ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በተመለከተ አቋሟቸውን በትናትናው ዕለት አመሻሽ በይፋ አሳወቁ፡፡ ወ/ት ብርቱካን በፓርቲያቸው ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ የገለፁት በአንድነት ፓርቲ መካከል በተከሰተው ውዝግብ የተነሳ ከፓርቲው የተሰናበቱና መርህ ይከበር በሚል የተከፋፈሉትን ወገኖች በማደራደር ላይ ለሚገኙ ሽማግሌዎች በፃፉት ደብዳቤ ነው፡፡ በትላንትናው ዕለት በግዮን ሆቴል የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ባሉበት፣ ‹‹ከወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተሰጠ አጭር መግለጫ›› በሚል ርዕስ በአሁን ወቅት ያላቸውን አቋም ገልፀዋል፡፡ እንደ ወ/ት ብርትኳን መግለጫ ከሆነ፣ ‹‹የፖለቲካ ትግል ተሳትፎዬ በዘመን ሲለካ አጭር መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ወደ ትግሉ እንድገባ የገፋፋኝ በኢትዮጵያ የተሟላ የዜጎች ነፃነትና ማሕበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን የነበረኝ የወጣጥነት ፍላጎቴ ነው›› ብለዋል፡፡ የዚህ ፍላጐት ዋስትና መኖር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተመስርቶ ወይም ይሄ ፍላጐታቸው ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ እና ነገም የሚኖር መሆኑን ጠቅሰው፣ ከጀመሩት ነገር የማፈግፈግ ነገር እንደሌለባቸውና ወደፊትም እንደማይኖር ገልፀዋል፡፡ ብዙ ወገኖች በትግሉ ከሳቸው ይጠብቁ የነበረ ቢሆንም ‹‹የሚጠብቁትን ‹‹ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ትግል ብርቱካን ታፈገፍጋለች ብሎ መጠበቅ አይታሰብም›› ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በአገራችን የሚሰራጩ በርካታ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጋዜጦችን በማተም የሚታወቀው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በጋዜጦች የማተሚያ ዋጋ ላይ እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አሳወቀ፡፡ ከ2000 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እስካሁን ስድስት ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ያደረገው ማተሚያ ቤቱ የአሁኑ ጭማሪ ግን እስካሁን ከተደረገው ፍጹም የተለየና እስከ 47 በመቶ እንደሚደርስ ማተሚያ ቤቱ ለተለያዩ ጋዜጦች የላከው ደብዳቤ ያትታል፡፡ የጋዜጣ አሳታሚዎች ‹መንግስት ነጻውን ፕሬስ ወደ መቃብር ለመክተት ቆርጦ መነሳቱን ያሳያል› በማለት ሆን ተብሎ ፕሬሱን በኢኮኖሚ ለማዳከም ከመንግስት የወረደ አቅጣጫ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡ በጋዜጦች ላይ አስደንጋጭ የህትመት ዋጋ ጭማሪ ተደረገ ‹‹መንግስት ነጻውን ፕሬስ ወደ መቃብር ለመክተት ቆርጦ ተነስቷል›› አሳታሚዎች ወደ ገፅ 19 ዞሯል ወደ ገፅ 19 ዞሯል በሰሜን አፍሪካና በአንዳንድ የአረብ አገራት የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ አድማሱን በማስፋት ወደ ኢትዮጵያም ሊዛመት ይችላል የሚል ግምት የሚሰጡ ወገኖች አሉ፡፡ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ግን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ‹የተዛባ አመለካከት› ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ ዳዊት ከበደ በውጭ የሚገኙ ዕውቅ ኢትዮጵያውያንን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና የፖለቲካ ተንታኞችን አስተያየት በማካተት ቀጣዩን ጽሑፍ ይዞ ቀርቧል፡፡ የሰሜን አፍሪካው አመጽና የአቶ መለስ ምላሽ በተንታኞች እይታ የመለስ ዜናዊ እና የኦሕዴድ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ 3 10 ተ ጠ የ ቅ የሕፃናት ጉዳይ ባለቤትነቱ የማን ይሆን? 1 አፍታ በየመን ስጋት አርግዘን ስጋት ለብሰናል ትጥቃችንን ማን አስፈታን ? ባሏን ጎዳው ብላ መንታ ወለደች

Awramba Times Issue #159

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 ‹‹ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ተሸማቅቀው፣ ክብርና ነፃነት አጥተው እየኖሩ ነው››

አቶ ገብሩ አስራት(የወቅቱ የ’መድረክ’ ሊቀ-መንበር)

የወር ወጪው 100 ብር

የማይሞላው አሜሪካዊ - በኢትዮጵያ

የአንድነት ፓርቲ ሊቀ-መንበር የሆኑት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በፖለቲካው ዓለም ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በተመለከተ አቋሟቸውን በትናትናው ዕለት አመሻሽ በይፋ አሳወቁ፡፡

ወ/ት ብርቱካን በፓርቲያቸው ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ የገለፁት በአንድነት ፓርቲ መካከል በተከሰተው ውዝግብ የተነሳ ከፓርቲው የተሰናበቱና መርህ ይከበር በሚል የተከፋፈሉትን ወገኖች በማደራደር ላይ ለሚገኙ ሽማግሌዎች በፃፉት ደብዳቤ ነው፡፡ በትላንትናው ዕለት በግዮን ሆቴል የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ባሉበት፣ ‹‹ከወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተሰጠ አጭር መግለጫ›› በሚል ርዕስ በአሁን ወቅት ያላቸውን አቋም ገልፀዋል፡፡

እንደ ወ/ት ብርትኳን መግለጫ ከሆነ፣ ‹‹የፖለቲካ ትግል ተሳትፎዬ በዘመን ሲለካ አጭር መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ወደ ትግሉ እንድገባ የገፋፋኝ በኢትዮጵያ የተሟላ የዜጎች ነፃነትና ማሕበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን የነበረኝ የወጣጥነት ፍላጎቴ ነው›› ብለዋል፡፡

የዚህ ፍላጐት ዋስትና መኖር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተመስርቶ ወይም ይሄ ፍላጐታቸው ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ እና ነገም የሚኖር መሆኑን ጠቅሰው፣ ከጀመሩት ነገር የማፈግፈግ ነገር እንደሌለባቸውና ወደፊትም እንደማይኖር ገልፀዋል፡፡ ብዙ ወገኖች በትግሉ ከሳቸው ይጠብቁ የነበረ ቢሆንም ‹‹የሚጠብቁትን

‹‹ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ትግል ብርቱካን ታፈገፍጋለች ብሎ መጠበቅ አይታሰብም››

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳበአገራችን የሚሰራጩ በርካታ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጋዜጦችን በማተም የሚታወቀው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በጋዜጦች የማተሚያ ዋጋ ላይ እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አሳወቀ፡፡ ከ2000 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እስካሁን ስድስት ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ያደረገው ማተሚያ ቤቱ የአሁኑ ጭማሪ ግን እስካሁን ከተደረገው ፍጹም የተለየና እስከ 47 በመቶ እንደሚደርስ ማተሚያ ቤቱ ለተለያዩ ጋዜጦች የላከው ደብዳቤ ያትታል፡፡ የጋዜጣ አሳታሚዎች ‹መንግስት ነጻውን ፕሬስ ወደ መቃብር ለመክተት ቆርጦ መነሳቱን ያሳያል› በማለት ሆን ተብሎ ፕሬሱን በኢኮኖሚ ለማዳከም ከመንግስት የወረደ አቅጣጫ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡

በጋዜጦች ላይ አስደንጋጭ የህትመት ዋጋ ጭማሪ ተደረገ

‹‹መንግስት ነጻውን ፕሬስ ወደ መቃብር

ለመክተት ቆርጦ ተነስቷል››

አሳታሚዎች

ወደ ገፅ 19 ዞሯልወደ ገፅ 19 ዞሯል

በሰሜን አፍሪካና በአንዳንድ የአረብ አገራት የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ አድማሱን በማስፋት

ወደ ኢትዮጵያም ሊዛመት ይችላል የሚል ግምት የሚሰጡ ወገኖች አሉ፡፡ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ

ግን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ‹የተዛባ አመለካከት› ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ ዳዊት ከበደ

በውጭ የሚገኙ ዕውቅ ኢትዮጵያውያንን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና የፖለቲካ ተንታኞችን

አስተያየት በማካተት ቀጣዩን ጽሑፍ ይዞ ቀርቧል፡፡

የሰሜን አፍሪካው አመጽና የአቶ መለስ ምላሽ በተንታኞች እይታ

የመለስ ዜናዊ እና የኦሕዴድ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ

ጃዋር ሲራጅ መሀመድ

3 10

ተ ጠ የ ቅ

የሕፃናት ጉዳይ ባለቤትነቱ የማን ይሆን?

1 አ ፍታ

በየመን ስጋት አርግዘን ስጋት ለብሰናል

ትጥቃችንን ማን አስፈታን?ባሏን ጎዳው ብላ መንታ ወለደች

Page 2: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾” ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

›²ÒϨc”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”

Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\c<^õ›?M Ó`T

¯UÅ™‹ ›uu „L

cKV” VÑeƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ}hK ¨ÇÏ

¢Uú¨<}` îG<õ SpÅe õeN

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 ®911 62 92 82 0911 15 62 48

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

¾›d�T>¨< ›É^h›^Ç ¡/Ÿ}T kuK? 09

¾u?ƒ lØ` 191Ÿ›^ƒ Ÿ=KA ¨Å úÁd uT>¨eŨ< S”ÑÉ’ Ÿ^e S¢”” ÉMÉà ›Kõ wKA ¨Å GÑ` õp` +Áƒ` SÑ”ÖÁ ›eóMƒ Là uT>Ñ–¨< vI[ ’Òi Q”í Óu= ¨<eØ

ማን ምን አ ለ

2

አንዲት ሀገር የሕዝቧ አዕምሮ ድምር ውጤት ናት ይባላል፡፡ እውነት ነው፡፡ ሀገር ያሏት ሳይንቲስቶች፣ ኢኮኖሚስቶች፣ ወታደራዊ ጠበብቶች፣ ትጉህ አርሶ አደሮች፣ የጥበብ ባለሙያዎች፣ ወዘተ ድምር ውጤት ናት፡፡ ስለዚህም፣ የምትገኝበት ማንኛውም ተጨባጭ ሁኔታ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው ማለት ነው፡፡ ይሁንና ግን፣ መታለፍ የሌለባቸው ተጨማሪ ሁለት መሰረታዊ ነጥቦችም አሉ፡- እነዚህም፣ የመሪዎቹ አዕምሮ ድምር ውጤትስ ምን ይመስላል? መሪዎቹን የከበቧቸው አማካሪዎቻቸው ድምር አዕምሯዊ ውጤትስ? የሚሉት ናቸው፡፡ ይህን ጉዳይ መጠየቅ ይኖርብናልን? ደግሞስ የምንጠይቀው ለምንድን ነው? በእርግጥም ይህን ጥያቄ አበክረን መጠየቅ አለብን፡፡ እንጠይቃን፤ ተገቢውን ምላሽ እስክናገኝ ደጋግመን እንጠይቃለን፡፡ ምክንያቱም የቱንም ያህል በሁለንተናዊ ዘርፍ በቂ መጠንና ብቃት ያላቸው ዜጎች የአዕምሮ ድምር ውጤት የላቀ ሊሆን ቢችልም፣ የመሪዎቹ አእምሮ ድምር ውጤት የሚጠበቀውን ያህል ካልሆነና እንዲሁም አማካሪዎቹ ራሳቸው መካሪ የሚያሻቸው ሆነው ከተገኙ ጉዳዩ ‹‹ማኛ ጤፍ ዘርቶ ጓያ ማጨድ›› እንደሚሉት መሆኑ አይቀርም፡፡ የተወሰኑ ተግባራዊ ማሳያዎችን እዚህ ላይ ማንሳቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሰሞኑን ለአንድ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ ሬዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ላይ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ስላላቸው መልካም ግንኙነቶች ቀጥሎ ባለው መልኩ የመሰከሩት የራሱን ጥያቄ አጭሯል፤ ‹ሕዝቡ ከመሪዎቹ የበለጠ ልባም ነው፤ ... ›› ሲሉ የተናገሩት አቶ መለስ፣ የችግሩን ምንጭ፣ ‹‹ … ጠቡ በፖለቲካ መሪዎችና ኃላፊዎች እንጂ ሕዝቦች ላይ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ … ሌሊት ሲጋቡ [የኤርትራና የኢትዮጵያ ተወላጆች] አይተን እንዳላየን ዝም እንላለን፡፡ ለበዓል ፍየል ወይም ዶሮ ይዘው ድንበር ሲሻገሩም እንደዛው፡፡ … ››፡፡ ይህ አባባል የገለጠው ወይም ያጋለጠው አንድ ትልቅ እውነታ አለ፡- የሁለቱም ሀገራት ሕዝቦች አዕምሮ ድምር

ውጤት ሀገራቱን ታላቅና ዜጎቻቸውንም በዓለም ፊት አንገታቸውን እንዲደፉ ካደረጋቸው ተመጽዋችነት የተላቀቁ ኩሩ ማድረግ በተቻለው ነበር፡፡ ይሁንና ግን የፖለቲካ መሪዎቹ አዕምሮ ድምር ውጤት ከዚያ የተለየ ነው፡፡ ይህንንም፣ ታሪክም መሪዎቹ ራሳቸውም እንዳየነው እየመሰከሩ ነው፡፡ መሪዎቹ የሕዝቡን ያህል ልባም ባለመሆናቸው ዜጎቻቸው ብዙ - እጅግ ብዙ - ነገሮችን አጥተዋል፡፡ አንዱን ሰበዝ ብቻ እንምዘዝ ቢባል እንኳ በጋራ ተጠቅመው በጋራ መክበር የሚያስችላቸው የባሕር በራቸው ‹‹የግመል ውኃ ማጠጫ›› መሆኑን ለመመልከት ተፈርዶባቸዋል፡፡ በእርግጥ የመዘዝነው ሰበዝ በኤርትራና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለው ዋንኛው ዕሴት ነው ለማለት አይደለም፡፡ ታሪክ በማይፋቅ ሁኔታ የመዘገባቸው አንድ ሺህ አንድ ትላልቅ መንፈሳዊ ትስስሮች አሉ፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ድምር ውጤት ግን ሊሆን ከሚገባው የሚፈለግ ነገር ይልቅ በተቃራኒው ሲሸሹት በኖሩት አዘቅት ውስጥ እንዲገኙ አስገድዷቸዋል፡፡ የሚያልፉ የመንግስት ባለሥልጣናት በማያልፍ ሕዝብ ላይ ያሳረፉት ጠባሳ ነው፡፡ በእርግጥ ጠባሳው መሻሩ አይቀርም፡፡ ጊዜ፣ ጉልበት እና አንጡራ ኃብት ማሟጠጡ ግን አይቀርም፡፡ ለዚህም ነው በወሳኝ ነጥቦች ላይ መነጋገር አለብን የምንለው፡፡ እስኪ ሌላ ተጨማሪና ተጨባጭ ማሳያም እንፈትሽ፡፡ ባለፈው ወር አጋማሽ፣ አንድ ሳምንት ‹‹የፈጀ›› እና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሰብሳቢነት ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፡፡ በስብሰባውም በከፍተኛ ኃላፊት ላይ የነበሩ ተገምግመው ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡ አስተዳደራዊው እርምጃም የሚደነቅ ነው፡፡ በአስተውሎት ሊቃኝ የሚገባው ቁም ነገር ግን መገምገማቸውና መሰናበታቸው ሳይሆን መቼ፣ እንዴት እና ከዚያስ የሚሉትና ተያያዥ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይህም የአንድ ክልል ባለሥልጣናት ጉዳይ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ ሹማምንት ላይም ሁሉ ሊተገበር እንደሚገ በአጽንኦት እንገልፃለን፡፡ ግምገማውን ተከትሎ የተደረሰበት ውሳኔ ገመናውን በመግለጥ የአንድ ሀገር መሪዎች አዕምሮ ድምር

ውጤት በሀገሪቱ ላይ የሚያስከትለውን ምስቅልቅል ጠቋሚ ነው፡፡ በየትኛውም ዕይታ ቢሆን በሀገሪቱ ውስጥ ሰፊ ድርሻ ያለው የአንድ ክልል የገንዘብና ኢካኖሚ ልማት፣ የገቢዎች፣ የመንገድና ትራንስፖርት፣ የባሕልና ቱሪዝም፣ የውሃ፣ . . . ቢሮ ኃላፊዎች በነበራቸው የሥራ ተነሳሽነት ችግር፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ዓመል፣ ወዘተ ከኋላፊነታቸው ተነሱ ሲባል በኃቀኝነት ግብር ከፍሎ ሀገሩን እንደሀገር የበለጸገች ለማድረግ በሚታትረው ሕዝብ ላይ ግፍ መፈጸም ይሆናል፡፡ በየትኛውም ዘርፍ ያለ የአንድ ተቋም ኃላፊ የሥራ ተነሳሽነት ችግር ካለበት ምን ዓይነት ተምሳሌት ሊሆን ይችላል? የኃላፊነቱ ሸክም ዜጎችን ማገልገል ሳይሆን ግለኝነት (ኪራይ ሰብሳቢነት የሚባለው) በሆነበት ሁኔታ እየተጓዝን ያለነው ወዴት ነው ተብሎ ሊጠየቅ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ድምር ውጤቱ የሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ነውና፡፡ በነገራችን ላይ፣ ‹‹የሥራ ተነሳሽነት ችግር›› ማለት ማከናወን የሚጠበቅበትን ባለማከናወን ሊደረስበት የሚገባውን ግብ ማጓተት ወይም ማጨናገፍ የሚል ትርጉም አለው፡፡ የሥራ ተነሳሽነት ችግር በአንድ ዝቅተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ በሚገኝ ግለሰብ ሲፈጸም እንኳ ተቋሙን ብሎም ሀገሪቱን መጉዳቱ አይቀርም፡፡ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት›› የሚለውም ተመሳሳይ አንድምታ አለው፡፡ ተግባራቱ ተጠቃለው ሲታዩ ሀገር መጉዳት ማለት ነው፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ ሁሉ ተገቢውና ወቅታዊው አስተዳደራዊ እርምጃ ሳይዘገይ ሊወሰድ ግድ ይላል፡፡ አበክረን መጠየቅ አለብን ያልነው ሌላው ወሳኝ ነጥብ፣ በመሪዎቹ ዙርያ ያሉት አማካሪዎች ጉዳይ ነው፡፡ የመሪዎቹ አማካሪዎች እነማናቸው? እንዴት ይመረጣሉ? እስካሁን በነበረው ጉዞ ሀገሪቱን የት አደረሷት? የሚሉት መጤን ይኖርባቸዋል፡፡ የመሪ አማካሪዎቹ አዕምሮ ድምር ውጤትም የአንዲትን ሀገር አቅጣጫ ከሚወስኑት መሰረታዊ

ግብአቶት አንዱ ነው፡፡ ‹‹መካሪ የሌለው ንጉሥ ያለዓመት አይነግስ›› የሚለው የሀገራችን ቆየት ያለ ብሂል የገንቢ አማካሪ አስፈላጊነትን አመላካች ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ጥሩ አማካሪ የሌለው መሪ ምንም መካሪ ከሌለው የባሰ ጉዳት የሚያስከትል እንደሆነ የሀገራችን ታሪክ ምስክር ነው፡፡ አማካሪዎቹ እነማን ናቸው? የሚመረጡበት መስፈርትስ? ወዘተ እያልን የእያንዳንዳቸውን ግለ-ታሪክ መበርበር አንፈልግም፡፡ ዓላማችንም አይደለም፡፡ በእርግጥ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አሁን ድረስ በለስ የቀናውን የሚያማክሩ እንዳሉ እንመለከታለን፡፡ ሰሚ አጥተው ይሆን? ምክራቸው ሁሉ ተመካሪዎቹ መስማት የሚፈልጉትን መናገር ሆኖ ይሆን? ወይስ ምን? ኃላፊነት እንዳለበት ዜጋ በግለሰብ ደረጃ ልንጠይቀው የሚገባን መሆን አለበት፡፡ ከዚያ ይልቅ ግን የአበክሮአዊ ጥያቄያችንና መልዕክታችን ነጥብ፣ በመልካም አማካሪዎች የተከበበ ሞራላዊ ብቃት ያለው መሪ ለአንድ ሀገር ታላቅነት ወሳኝ የሆነውን የሕዝቦች አእምሮ ድምር ውጤት ቁልፍ በእጁ የያዘ መሆኑን መጠቆም ነው፡፡ መልካም ራዕይ ያለው መሪ፣ መልካም ራዕይ ያላቸው አማካሪዎች የበለፀገች ሀገርን ይፈጥራሉ፡፡ ከዚያ ውጪ የቱንም ያህል የካበተ የሕዝብ እሴት ቢኖር መሪና አማካሪ አያያዙን ካላወቁበት ‹‹በእጅ ያለ ወርቅ እንደመዳብ ይቆጠራል›› እንደሚሉት ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ሁላችንንም ይጎዳል፣ ሲጎዳን ኖሯል፡፡ በተረፈ ብልሹ አስተዳደር በታየባቸው ኃላፊዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች የዘገዩ ከሆኑ እንዳልተወሰዱ ይቆጠራሉ - ጥፋቱን አያካክሱትምና፡፡ ከተቻለ፣ ደግሞም ከመዘዙ አንጻር በተቻለ መጠን በየዕለቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ ... መሪዎች አመራራቸው፣ አማካሪዎች የሚያቀርቡት ኃሳብ፣ በተለያየ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች ደግሞ በሚጠበቅባቸው ተግባር ምን እያደረጉ ነው ተብሎ ይፈተሸ፡፡ የአስተዳደራዊ እርምጃ ስኬታማነት መለኪያው የቃጠሎውን አመድ በማፈስ ሳይሆን ሳይቃጠል በቅጠል መከላከል ሲቻል ብቻ ነው..

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

የአስተዳደራዊ እርምጃ ስኬታማነት መለኪያው፡-የቃጠሎውን አመድ በማፈስ ሳይሆን፣

ቃጠሎውን በቅጠል መከላከል ሲቻል ብቻ ነው

‹‹ይህ አይነቱ አፈሳ ተራ በተራ ለሁሉም የሚደርስ ይመስለኛል፡፡››

አቶ በቀለ ነጋየኦፌዴን ዋና ፀሐፊ

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በኦሮሚያ ውስጥ ስለታሰሩት አባሎቻቸው ጉዳይ ለፍትሕ ጋዜጣ ከሰጡት

አስተያየት የተወሰደ፡፡

‹‹አሁን ግን ቤተመንግስት ከገባሁ በኋላ ከጓዳም መውጣት እያቃተኝ ነው እንጂ አራዳ ብገባ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ መዝናናት

ለሰው ልጅ አስፈላጊ ነው፡፡››

ፕ/ር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ “በወጣትነትዎ በምን ነበር

የሚዝናኑት?” በሚል ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት

ምላሽ፡፡

‹‹አብዛኛው ሰው በመኪና የሚጓዘውን ያህል በእግሩም ይጓዛል፡፡››

ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ‹የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው በትራንስፖርት ተገልጋዮች ላይ

ጫና አያሳድርም› ለማለት ያቀረቡት መከራከሪያ

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

የአሳታሚው አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

Page 3: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

የመለስ ዜናዊ እና የኦሕዴድ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ

ኮሜንተሪፕሬዝዳንቶች አስተናግዳለች፡፡

በየወቅቱ መሰል እርምጃዎችን የመወሰዱ ዓላማ በክልላዊ መንግስታት ደረጃ የሥልጣን መጠናከርን (መከማቸትን) መከላከልን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ከዚህም በላይ፣ ከሚመለከታቸው የየፓርቲዎቹ አለቆች ይልቅ፣ ሕወሓት በክልልና በዞን ደረጃዎች ላሉ ቁልፍ ኃላፊነቶች የሚደረገውን ሹመት በተዘዋዋሪ ይቆጣጠራል፤ በመሆኑም፣ ተሿሚዎቹ ለቅርብ የበላዮቻቸው ሳይሆን ለዋናው ‹‹ፓትሮን›› ታማኝ እንዲሆኑ ይደረጋሉ፡፡ ይህም የክልላዊ መሪዎች የራሳቸውን ‹‹ደንበኞች›› ለማቋቋም የሚያስችላቸውን የኪራይ ሀብት ያሳጣቸዋል፡፡

የ2005ቱ ምርጫ ይህን ታክቲክ ለጊዜውም ቢሆን አጨናግፎት ነበር፡፡ ላለፉት 15 ዓመታት፣ የኦሮሞ ኤሊቶችን ማቃቃርና ማግለል ኦሕዴድን ለማዳከም እና የበታች እንደሆነ ለማቆየት እንደቁልፍ ስትራቴጂ የታየ ነበር፡፡ ያም ሆኖ፣ ድንገተኛውን የአማራ ስጋት ማንሰራራት ለመቋቋም፣ አቶ መለስ ከኦሮሞ መራጮች ጋር ሰላም ለመፍጠር ሙከራ ከማድረግ በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበራቸውምና ያን ጊዜ አባዱላ ገመዳ ከተረጋገጠ ታማኝነታቸው ጋር ብቅ አሉ፤ በተለይ ያ የእርሳቸው ታማኝነት በ2001 ውስጥ በተከሰተው የሕወሓት የውስጥ ቀውስ ወቅት የተረጋገጠ ጉዳይ ነበር፡፡

የኦነግ የምንጊዜም ጠላት የሆኑት አባዱላ ገመዳ፣ ከተሿሚዎች መካከል በማፈንገጥ ወይም በማሴር እምብዛም የሚጠረጠሩ አልነበሩም፡፡ በመሆኑም፣ ምንም እንኳን ለአጨር ጊዜ ቢሆንም፣ ኦሕዴድን ለ‹‹ማሻሻል››፣ የተማሩ ኦሮሞዎችን ለማባበልና እንዲቀላቀሏቸው ለማድረግ ያስቻላቸውንና አስቀድሞ ተደርጎ የማይታወቅ ዓይነት ሥልጣን ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ እጅግም ነበር የተሳካላቸው፡፡ የጀመሩትም በተሳታፊዎች የተሰነዘሩ ሁሉንም ወቀሳዎችና ትችቶች ድርጅቱ አምኖ የተቀበለባቸውን ትላልቅ ኮንፍረንሶችን በማዘጋጀት ነበር፡፡ ለድክመቶቹ የተማረው ኃይል መገለል እንደምክያት ቀርቦ ነበር፡፡ እናም፣ በአንድ ወቅት የተማሩትን ጠባብ ብሔርተኞች እና የዴሞክራሲ ጠላቶች ብሎ በአደባባይ ላወጀ ድርጅት የወሰደው እርምጃው የብዙዎችን አፍ በአግራሞት ያስከፈተ ነበር፡፡

በመቀጠልም አባዱላ ተማሪዎች፣

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

3

የማባበል ስትራቴጂ ያልታሰቡ ውጤቶችና ማምከኛ እርምጃዎችሁሉም ያልተገደበ ሥልጣን

እንዳላቸው ገዥዎች፣ ጥቅም አስጠባቂ (‹‹ፓትሮን››) በሆኑበት በጥቅም የተሳሰረ ሥርዓት ላይ የሚመረኮዙ ናቸው፡፡ በመሰል ሥርዓቶች፣ ‹‹ደንበኞች›› ለሚያሳዩት ታማኝነትና ለሚሰጡት ድጋፍ በተለዋጭ ዋነኛው “ፓትሮን” የሥልጣንና የቁሳዊ ጥቅም ክፍፍልን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡ ከሁሉም በላይ፣ ጥቅሞቹ በ”ፓትሮኑ” የበታች እና ተገዥ በመሆን ላይ እጅግ የሚወሰኑ ናቸው፤ በተጨማሪም፣ ለእርሱ ፍላጎቶቹና ጥቅሞች ካለአንዳች ማወላወል ተገዥ መሆን የሚጠበቅባቸው መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ አምባገነኖች ቀጥተኛ የሥልጣን ተዋረድን ለማስጠበቅ (ከገንዘብ ጋር የተያያዘ) የሕዝብ ሀብት ምዝበራን ይፈልጉታል፡፡ ሆኖም ግን አንዳንዴ አግድሞሻዊ ቡድኖች ብቅ ማለታቸው አይቀርም፤ በዚህም ንዑስ-ፓትሮኖች የራሳቸውን መረብ ይዘረጋሉ፡፡ መሰል ጉዳዮች ሲያጋጥሙ፣ እነዚያ ቡድኖች የዋናውን “ፓትሮን” ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል አቅም ሊያጎለብቱ ይችላሉ፡፡

መቼም መቋጫ የሌለው ብወዛ፣ ከኃላፊነት ማፈናቀል እና መሾምና መሻር በአቶ መለስ የደንበኝነት ፓርቲዎች የተለመዱ ሲሆኑ ግባቸውም መሰል ችግሮችን ማስቀረት ነው፡፡

ከአንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አምባገነን አንስቶ እስከ ዋነኛው ክልላዊ ኃላፊ ድረስ፣ አንድ ሰው በአንድ ኃላፊነት ላይ ለማገልገል የሚፈቀድለት አማካይ ጊዜ 2.5 ዓመታት ብቻ ነው፡፡ ለአቶ መለስ ሥልጣን ዋነኛ ስጋት ተደርገው በሚታዩት በሁለቱ ክልሎች ብወዛው ከዚህም የባሰ ነው፡፡ በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ሱማሌ (ኦጋዴን) አስራ ሁለት ፕሬዝዳንቶችን ያፈራረቀች ሲሆን በተመሳሳይ ወቅት ኦሮሚያ አምስት

የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - ኦሕዴድ - በቅርቡ ከፍተኛ የማፅዳት ዘመቻ አከናውኗል፡፡ ለአቶ መለስ ታማኞች አይደሉም ተብለው የታዩትን ማስወገድ ለድርጅቱ የተለመደ ተግባር ቢሆንም፣ 120 ከፍተኛና መካከለኛ ደረጃ አባላትን የጠራረገው የቅርቡ ትርዒት ግን እሰከዛሬ ከታዩት መካከል የሚስተካከለው የለም፡፡ ‹‹የኢፌዴሪ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ›› የሆኑትን አባዱላ ገመዳን ጨምሮ፣ የተቀረውን የድርጅቱን አመራር ዕጣው እንደሚጠብቃቸው ነው የሚነገረው፡፡

ስጋቶችን አስቀድሞ የመመከት ማመካኛዎችየተወገዙት ግለሰቦች የሙስና

እና የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተባለውን ተግባራዊ ለማድረግ ብቃት የላቸውም የሚል ውንጀላ ቀርቦባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን፣ የማፅዳት እርምጃው፣ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ትግበራ ለማመቻቸት በሚል ነው የተወሰደው የሚለውን ምክንያት መቀበል አስቸጋሪ ነው፡፡ በመጀመርያ ደረጃ፣ በቅርቡ ከአንድ ዓመት በፊት፣ እነዚሁ ሰዎች ራሳቸው በአስተዳደራዊ ውጤታማነት ረገድ ኦሮሚያን ለተቀሩት ክልሎች ሞዴል እንድትሆን በማድረግ ሙገሳ የተቸራቸው ናቸው፡፡ ሁለተኛ፣ እቅዱ ከ2010-2015 ድረስ የሚዘልቅ የአምስት ዓመት እቅድ ተብሎ ነው የሚገመተው፡፡ መሰል ‹‹አዲስ›› እና ከፍተኛ ግቦችን በማቀፉ ውጤታማ ለመሆን እጅግ አስቸጋሪ የሆነን ፖሊሲ ስኬታማ እንዲሆን ለማድረግ የሚደረግ ዝግጅት መካሄድ የነበረበት በእቅድ ደረጃ ሳለ እንጂ በትግበራው እርከን ግማሽ ርቀት ከተጓዘ በኋላ አይደለም፡፡ እናም፣ ይህ የተወሰደው የማፅዳት ዘመቻው ከእቅዱ ጋር አንዳች ግንኙነት የሌለው ስለመሆኑ ሌላ አመላካች ማስረጃ ነው፡፡

አንዳንዶቹ ባለሥልጣናት የሙስና ተግባር መፈፀማቸው የማይካድ እውነታ ነው፤ ምክንያቱም በአቶ መለስ ኢትዮጵያ ሙስና ለፖለቲካ ሥልጣን አንዱ

ቅድመ-ሁኔታ ነውና፡፡ እንደሚባለው ከሆነ፣ የተወገዱት ግለሰቦች በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተማዎች ውስጥ በሕገ-ወጥ የመሬት ሽያጭ ተሳትፎ ነበራቸው፡፡ ሆኖም ግን፣ ለምን የጠፋው ከጠፋ በኋላ አሁን እርምጃ ተወሰደ?

የሕዝቡን ጉስቁልና ባለሥልጣናቱ ቸል ባይሉት ኖሮ፣ ተፈፀሙ የተባሉትን ወንጀሎች መከላከል፣ አልያም ቢያንስ ከሶስት ወይም አራት ዓመታት በፊት እንዲቋረጡ ማድረግ በተቻለ ነበር፡፡ ለምሳሌ፣ በ2008 ውስጥ፣ በገላን ከተማ ውስጥ ለ47 መኖሪያዎች መገንቢያነት ሊውል የሚችል መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ ከመሸጥ ጋር በተያያዘ አንድ የሙስና ጉዳይ ተከስቶ ነበር፤ እናም፣ ይህ ጉዳይ ይመለከተናል ያሉ ዜጎችን ያካተተ አንድ የፍቃደኞች ቡድን ስድስት ወራት የፈጀ ጥልቅ ምርመራ ያካሂዳል፤ ቡድኑ በምርመራውም ሀሰተኛ ዶክመንቶችን፣ ደረሰኞችን፣ የባንክ መዝገቦችን፣ ምስሎችንና በግለሰብ ደረጃ የተደረጉ የድምፅ ልውውጦችን ያካተተ ጠንካራ፣ ሊካድ የማይችል ማስረጃ ያሰባስብና የምርመራውን ውጤት የጠቅላይ

ሚኒስትሩን ቢሮ ጨምሮ ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ያቀርባል፡፡ ሆኖም ግን፣ በወንጀል ፈፃሚዎቹ ላይ እርምጃ ሊወሰድ ሲገባ፣ እና ለጠቋሚዎች ጥበቃ ይደረጋል ተብሎ ቃል እንደተገባው ቃሉ ሳይጠበቅ ቀርቶ፣ ማስረጃውን አሳልፎ ለመስጠት ራሱን ያጋለጠው ግለሰብ ወዲያው ነበር የወከባ ሰለባ የሆነው፡፡ በመጨረሻም ሀገሪቱን ለቅቆ ለመሸሽ ተገደደ፡፡ የተቀረውም ቡድን የገንዘቡን ዱካ በመከተል፣ የገንዘቡ የመጨረሻ መዳረሻ በአንድ ባለሥልጣንና የፌዴራል ሚኒስትር ስም የተመዘገበ የባንክ መዝገብ መሆኑን ያስረገጠ ተጨማሪ ማስረጃም ለማግኘት ችሎ ነበር፡፡ ይህም በተለይ በምርመራው የታወቀው ዋነኛው ሰው ስለምን በቅርቡ በተካሄደው የማፅዳት ዘመቻ ሳይነካ ቀረ ለሚለው በማብራሪያነት ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡

በአጠቃላይ፣ የመሬት ሽያጭን የተመለከተው መጠነ-ሰፊው የሙስና ቅሌት ድብቅ የሆነ ተግባር አይደለም፡፡ ስለዚህም፣ በቅርቡ የተወሰደው እርምጃ ከመሬት ሽያጭ ጋር የተያያዘ ነው የሚለው ማመካኛ፣ እንደው ሌላው ቢቀር ቅንነት የጎደለው ነው፡

ጃዋር ሲራጅ መሀመድ፣ የፖሊቲካል ሳይንስ

ተመራማሪና ተንታኝ ናቸው

ወደ ገፅ 9 ዞሯል

ጃዋር ሲራጅ መሀመድ

Page 4: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

የሰሜን አፍሪካው አመጽና የአቶ መለስ ምላሽ በተንታኞች እይታ

ፊ ቸ ር4

በአሜሪካ - ኦሐዮ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ዴይተን ዩኒቨርሲቲ ፍልስፍና የሚያስተምሩት ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ፤ ኢትዮጵያን ባሰቡ ቁጥር ሁሌም አንድ ጉዳይ በቁጭት ያንገበግባቸዋል፡፡ “እኔ ተምሬ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ ሙሉ ወጪዬን የሸፈነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆኖ ሳለ፤ ያስተማረኝን ድሀ ወገኔን እንደመካስ አሜሪካውያንን ለማስተማር መገደዴ ሁሌም እረፍት ይነሳኛል” ይላሉ በትካዜ፡፡ ፕሮፌሰር መሳይ የኢህአዴግ መንግስት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ከአንድ ዓመት በኋላ ‹በፖለቲካ ልዩነት› ምክንያት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲባረሩ ከተወሰነባቸው 42 ምሁራን አንዱ ናቸው፡፡ በመሳይ ዕምነት ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የተመሰቃቀለ ፖለቲካ ዋናው መንስኤ ኢህአዴግ የሚከተለው በብሔር ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል በሚጽፏቸው መጽሐፎች፣ በድረ-ገጾች አማካኝነት ለንባብ በሚያበቋቸው የተለያዩ መጣጥፎቻቸውና ቃለ-ምልልሶቻቸው የብሄረተኝነትን አደጋ ሳያነሱ የማያልፉት፡፡ በእነዚህ ጽሁፎቻቸው የኢህአዴግን መንግስት ከረር ባለ ሁኔታ ይተቻሉ፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ የመንግስት ለውጥ ሳይደረግ ያስተማራቸውን ሕዝብ ገብተው ለማገልገል እንደሚቸገሩ ያላቸውን ስጋት ከጽሁፎቻቸውና መግለጫዎቻቸው በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ፕሮፌሰር መሳይ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካና በአንዳንድ የመካከለኛ ምስራቅ አገሮች የተከሰተውን የሕዝብ አመፅ ከአገራቸው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማነጻጸር በቅርብ መከታተላቸውን መነሻ በማድረግ “Are Ethiopians angry enough to revolt?” በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቁት መጣጥፍ የኢህአዴግን መንግስት በምርጫ ሳጥን ለማሸነፍ መሞከር ስላቅ ስለመሆኑ ከምርጫ 2002 ውጤቶች መገንዘብ እንደሚቻል በማውሳት ተቃዋሚዎች የተለየ ስትራቴጂ መከተል እንዳለባቸውና ለዚህ ደግሞ የሰሜን አፍሪካን ልምድ ከመቅሰም ውጪ ምንም ምርጫ እንደሌላቸው ካሉበት ሆነው ምክራቸውን ይለግሳሉ፡፡ ከሁለት ወር ተኩል በፊት አንድ ወጣት ቱኒዚያዊ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቆ የስራ ዕድል ለማግኘት ባለመቻሉ፣ እንዲሁም በፖሊሶች የደረሰበት መንገላታት አበሳጭቶት ራሱን አቃጥሎ ለሞት በመዳረጉ ምክንያት የተቀጣጠለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ፣ ቱኒዝያዊውን ቤን ዓሊ ከመንበረ ስልጣናቸው በማሰናበት ወደ ግብጽ ተዛምቶ፣ ፕሬዚዳንት ሙባርክን ከስልጣናቸው እንዲባርሩ በማድረግ አካባቢውን አናግቶ የዓለም ሚዲያዎች ግንባር ቀደም ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል። ሕዝባዊው እንቅስቃሴው በሁለቱ አገሮች ብቻ ሳይወሰን፣ ከሰላሳ ዓመት በላይ የመንን ይገዙ የነበሩትን ፕሬዝዳንት አብደላ ሳላህን፣ ቀጥሎም በሱኒት እስላም ሞናርኪ ወደምትዳደረው ባህሬይንና ወደ አልጄሪያ እንዲሁም ወደ ሊቢያና ሌሎችም የአረብ አገሮች በመዛመት አካባቢውን እያመሰው ይገኛል።

አወዛጋቢው ጥያቄ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ይቻላል ወይስ አይቻልም?

በሰሜን አፍሪካ የታየው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች፣ የሲቪክ ማሕበረሰብ ተወካዮች እና የኢትዮጵያን መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዙ አብዝተው የሚነቅፉት ወገኖች ‹በቃ› በሚል አንድ የጋራ መሪ ቃል የሰሜን አፍሪካው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊደገም ይገባል የሚል እምነት አንግበው በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ግን ኢህአዴግ የአባላቱን ቁጥር ከአምስት ሚሊዮን በላይ አድርጎ ሕዝቡ ውስጥ በተለያዩ ወጣትና ሴቶች ማህበራት አማካኝነት የቁጥጥር መረቡን በዘረጋበት ሁኔታ፤ ሲቪክ ማሕበራት በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ እንዳይሆኑ በአዲሱ አዋጅ ተገድበው፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በእርስ በርስ ሽኩቻ ተሰነጣጥቀው በሕዝቡ ዘንድ እምነት ባጡበት፤ እንዲሁም ዜጎች ለመብታቸው መከበር የሚያደርጉትን ትግል እርግፍ አድርገው በመተው የዕለት ኑሮአቸውን ብቻ ለማሸነፍ በተጠመዱበት በአሁኑ ወቅት፤ የሰሜን አፍሪካውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር ‹የማይታሰብ› ሲሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት በአሁኑ ወቅት ደግሞ የአንድነት/ መድረክ አመራር አባል የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ግን የፖለቲካ ድርጅቶቹ መዳከም እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር እንቅፋት እንደማይሆን ይከራከራሉ ‹አንድ የፖለቲካ ድርጅት በራሱም ችግር ወይም ገዢ መደቦች በሚፈጥሩት ተጽእኖ ምክንያት ሊዳከም ይችላል፡፡ ሁልጊዜም የድርጅት ሥኬት እና ክሥረት አለ፡፡ የማህበረሰቡ ችግር እስካልተፈታ ድረስ ድርጅቶች ቢዳከሙ እንኳ ሕዝቡ ራሱን በማደራጀት ያንቀሳቅሰዋል እንጂ ትግል አይቆምም› ይላሉ፤ በነጋሶ እምነት ጭቆናና ብዝበዛ በአንድ አገር መኖሩ መተማመን ላይ እስከተደረሰ ድረስ ሁሌም ሕዝብ ይሄንን ለመለወጥ መንቀሳቀሱ አይቀርም፡፡ ድርጅቶች ከሕብረተሰቡ ውስጥ ይወጡና የሕዝብን ችግር አንጥረው አውጥተው ለሕዝብ ካቀረቡ በኋላ በዚያ ላይ የተመሠረተ ፕሮግራም በማውጣትና በማስተባበር ታግለው ህብረተሰቡን ያታግላሉ ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡ጠ/ሚ/ር መለስ ግን ይህንን መላምት ‹የተዛባ አመለካከት› ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ ‹ኅብረተሰቡ ከዚያ በፊት የነበረውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ዐይቶ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሐሳቡን ገልጧል። በተነጻጻሪ ከእናንተ በተሻለ የልማት ሥራ የሚሠራልን የለም ብሎ የአምስት ዓመት ኮንትራት ለኢሕአዴግ ሰጥቷል። …ኢሕአዴግ ይኼን ካልፈጸመ ሕዝቡ በሚቀጥለው ምርጫ ሊዘርረው እና ሊያባርረው እንደሚችል ኢሕአዴግም ሕዝቡም ያውቃል።…ለዚህ ነው በሰሜን አፍሪካ እንዳለው ዓይነት ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም የምንለው። በአሁኑ ሰዓት ኢሕአዴግ ኮንትራቱን ለመፈጸም ነው ሌት ተቀን የሚሠራው። ሕዝቡም የአፈጻጸም ችግር አለ ብሎ ካመነ መንግሥትን ለመገምገም የሚያስችል በቂ መድረክ አለው።› ይላሉ፡፡የዲቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ ተመራማሪና ተንታኝ የሆኑት የጀርመኑ ዶ/ር ፍቃዱ በቀለ ግን ‹በአቶ መለስ ምላሽ አልስማማም› ባይ ናቸው፡፡ ‹አቶ መለስ ሕዝቡ መንግስታቸውን እንዲገመግም በቂ መድረክ አለው የሚሉን ከአምስት ዓመት በኋላ ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። ይሁንና ግን እንዲነሳባቸውም የማይፈልጉት አንድ ወሳኝ ጥያቄ ላቅርብላቸውና አስራ ዘጠኝ ዓመት ያህል በስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመን ምን እንደሰሩ እስኪ ይንገሩን ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መናርና መጥፋት፣ መጠነ ሰፊ ስራ አጥነት፣ የመኖሪያ ቤት እጥረት፣ የትራንስፖርት ችግር፣ ረሀብ በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቶ ህዝቡ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ እያለ በአንጻሩ ደግሞ ለገዢው መደብ ቅርበት ያላቸው ሹማምንት እጅግ በተንደላቀቀ ሁኔታ ሲኖሩ ጠ/ሚ/ሩ የሕገ መንግስትን አንቀጽ እየጠቀሱ ዋ! ትንፍሽ ትሉና ብሎ ማስፈራራት በየትኛውም የሞራል መመዘኛ ተገቢ አይደለም› ይላሉ - ዶ/ር ፍቃዱ፡፡

የነፍጥ አልባ ትግል(nonviolent struggle)

ወይስ የጎዳና ላይ ነውጥ ( riots) ?

የግብጽን አብዮት የተመለከቱ ብዙ ሰዎች ሕዝቡ ሙባረክን በሶስት ሳምንታት

ትግል ብቻ ማውረድ የቻለ ይመስላቸዋል የሚለው የፖሊቲካ ተንታኙ ጃዋር መሐመድ የአብዮቱ ጥንሥስ የተጀመረው ከስምንት ዓመት በፊት (እ.ኤ.አ 2003) እንደሆነና ለረጅም ጊዜ ተከፈፍለው ሲናቆሩ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ከኮሚኒስቶች እስከ ኢስላሚስቶቹ) እና ማህበራዊ ድርጅቶች (ለወጣቶች፣ ሴቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ሰራተኞች መብት ውዘተ የሚሟገቱ) በመሰባሰብ ተባብረው ለውጥ ለማምጣት ኪፋያ (በቃ!) የሚባል ጥምረት አቋቋሙ። የስብስቡ ዓላማ የሆስኒ ሙባረክ አምባገነናዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፣ የእሱ ልጅ፣ ጋማል ሙባረክ ስልጣን እንዳይወርስ መታገል ነበር። ሰላማዊ ትግልን እንደ ብቸኛ ስልት በመቀበል፣ አደራጆቻቸውን ( activists and organizers) የዚህን የትግል ዘዴ በስፋት እንዲማሩ ማመቻቸታቸውን ጃዋር ይተነትናል። ፕሮፌሰር መሳይ በበኩላቸው ‹በግብፅም ሆነ በቱኒዚያ በማሕበረሰብ መሪዎች አስተባባሪነት ሕዝቡ ተግባራዊ ያደረገው፤ ነፍጥ አልባ ትግል (non-violent struggle) በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥም የመንግስት ለውጥ እንዲኖር ዓላማ ያላቸው ሰዎች ማድረግ የሚጠበቅባቸው ለእንደዚህ አይነቱ ትግል ሕዝቡን ማስተባበር ብቻ ነው› ሲሉ የግል ምልከታቸውን ያቀርባሉ፡፡ በርካታ የዓለማችን የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች በግብአትነት የሚጠቀሙበት ‹from Dictatorship to Democracy› በሚል ርዕስ ታዋቂው ጄን ሻርፕ በአልበርት አንስታይን ኢንስቲትዩት ያሳተመው የነፍጥ አልባ ትግል ስትራቴጂን የሚተነትነው መፅሐፍ ነው፡፡ (በ University of Massachusetts Dartmouth የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰርና የኖቬል ዕጩ የነበረው ጄን ሻርፕ የጻፋቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የነፍጥ አልባ ትግል ስትራተጂ ቀመሮች እንዳሉ ይታወቃል) ፕ/ር መሳይም የጄን ሻርፕ ስትራቴጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ የማይሆንበት ምክንያት እንደሌለ ይከራከራሉ፡፡ ጃዋር ግን ህዝባዊ አመጽ ብቻውን ለውጥ ለማምጣት በቂ እንዳልሆነ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፤ ይለናል፡፡ በሰላማዊ ትግል (nonviolent struggle) አምባገነናዊ ስርዓትን ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማሸጋገር ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት ይጠይቃል በማለት፡፡ አያይዞም ‹ከመነሻው የዚህ አይነት የትግል ስልት ጽንሰ ሀሳብ ጠንቅቆ መረዳት፣ ይህን እውቀት በስፋት ለህዝቡ ማድረስ፣ ብዙሃኑን ህዝብ ሊያስማማ የሚችል ዓላማ ማፍለቅ፣ በጥናት ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂ ማውጣት ወሳኝ ነው። ሰላማዊ (ነፍጥ አልባ) ትግል ስንል አንድነት፤ ቅድመ ዝግጅት እና ሰላማዊ ዲሲፕሊን ያለው ንቅናቄ (movement) ማለታችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከተራ የጎዳና ላይ ነውጥ (riots) ጋር ነጥሎ መመልከት ግድ ይላል› ሲል ያብራራል፡፡

አስር ጊዜ እያሰሩ በይቅርታ መፍታት ሰልችቶናል

የ1997ቱ የምርጫ ውጤት ይፋ መደረግ ተከትሎ ተቃዋሚዎች ፓርላማ እንደማይገቡ በይፋ ባሳወቁ በሳምንታት ውስጥ የቅንጅት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ “የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂ” በሚል ርዕስ አንድ ሰነድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህ ሰነድ በአብዘኛው የሚያትተው

ከጄን ሻርፕ አመፅ አልባ ስትራቴጂ የተወሰዱ ነጥቦችን መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ሰነዱ ግን “የቅንጅት አመራሮች ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ ሙከራ አድርገዋል ለሚለው ክስ በዋነኛ አስረጅነት እንደቀረበና በአመራሮቹ ላይም የዕድሜ ልክ ፍርድ እንዲወሰን ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም፡፡

አንቀጽ - 9!የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ለአመፅ አልባ ትግልም ሆነ ለየት ባለ ስትራቴጂ ለሚደረግ የፓለቲካ ትግል አንድ ወሳኝ ሕገ መንግስታዊ አንቀጽ ይጠቅሳሉ፡፡ የሕገ መንግስት የበላይነትን በሚያትተው የሕገመንግስቱ ክፍል (አንቀጽ 9) ሕገ መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ እንደሆነ፤ ማንኛውም ዜጋ ሕገ መንግስቱን የማስከበርና ለሕገ መንግስቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት እንዳለበት ከዘረዘረ በኋላ በአንቀጹ ንዑስ ቁጥር 3 ላይ እንዲህ ይላል “በዚህ ሕገ-መንግስት ከተደነገገው ውጪ በማናቸውም አኳኋን የመንግስት ስልጣን መያዝ የተከለከለ ነው”፡፡ ይህ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ ኢህአዴግ ከምርጫ ውጪ ያሰጉኛል ለሚላቸው የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ወሳኝ የማጥቂያ መንገድ፣ ለምዕራባዊያን የዕርዳታ ለጋሾቹ ደግሞ አይነተኛ የማሳመኛ ድንጋጌ አድርጎ እንደሚጠቀምበት ይገለጻል፡፡

በርካታ ተንታኞች እንደሚሉት በሐምሌ ወር 1999 ዓ.ም የቅንጅት አመራሮች ከእስር ሲፈቱ፤ አመራሮቹ እንዲፈርሙት የቀረበላቸው ሰነድ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ ዘጠኝ ላይ የሰፈረውን የሚመለከት ነው፡፡ (የተፈረመው ሰነድ ‹ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ህገ መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ ለማፍረስ ተንቀሳቅሰናል፤ በዚህም መንግስትንና የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን…ለወደፊቱም ህገ መንግስቱንና በህገ መንግስቱ መሰረት የተቋቋሙ ተቋማትን ለማክበርና ለማስከበር እንንቀሳቀሳለን› ይላል) ይህንን መነሻ በማድረግ አስተያየት እንዲሰጡ የዚህ ፊቸር ጸሐፊ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ የሕግ ባለሙያ፤ አቶ መለስ በንግግራቸው መሐል ‹መታሰር፤ ይቅርታ ጠይቆ መፈታት፤ ተመልሶ መታሰር መንግሥትን እንደሰለቸው ሁሉ እነርሱንም ይሰለቻቸዋል ብለን እናስባለን› የሚል አገላለጽ የተጠቀሙት ይህንን በውስጠ ወይራ ለማስታወስ ነው ብለዋል፡፡

ትግል ከውጭ ወይስ ከውስጥ?በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመጪው ግንቦት ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል የሚል ዓላማ አንግበው የተለያዩ ኮሚቴዎችን አዋቅረው በማስተባበር ላይ መሆናቸውን በተለያዩ ሚዲያዎች ይገልጻሉ፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ አንዱ አካል እንደሆነ የሚታመነው ‹የድል ቀን› የተሰኘ ቡድንም ‹ፌስ ቡክ› በተሰኘው ማሕበራዊ መረብ ወደ 10ሺህ የሚጠጉ አባላትን አቅፎ መረጃዎችን እየተለዋወጠ እንደሆነ በማህበራዊ መረጃ መረብ (ፌስ ቡክ) ላይ ያለው የቡድኑ መረጃ ይጠቁማል፡፡የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ባለፈው ማክሰኞ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እየተካሄደ ስላለው ቅስቀሳ ለቀረበላቸው ጥያቄ በዝምታ ከማለፍ ውጪ ምንም ምላሽ መስጠት አልፈለጉም፡፡ አደገኛ አቅጣጫ ሊይዝ ይችላል በሚባል ሁነት ላይ ሚኒስትር ዴኤታው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የተጠቀሙበት ስልት በመግለጫው ላይ የታደሙትን ጋዜጠኞች ማስደመሙ አልቀረም፡፡ አንድ ጋዜጠኛ እንዳውም መንግስታቸው ለሁኔታው የሰጠውን ግምት አሳባቂ ነው ብሎታል፡፡ ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጃዋር መሀመድ ግን ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ ገና በእንጭጭነት ደረጃ ላይ እንዳለ ነው የሚገልጸው። ‹አንዳንዱ ውጪ አገር ቁጭ ብለን የትግል ጥሪ ስላስተላለፍን ብቻ ሁሉም አልጋ በአልጋ ሆኖ የሚሳካ ይመስለዋል› የሚለው ጃዋር ‹ሀገር ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች ደግሞ እኛ ተቃዋሚዎች ጠንካራ ባንሆንም ህዝቡ በሰሜን አፍሪካ ያሉ ወንድሞቹ በሚያደርጉት እንቅስቃሴና ድል ልቡ ተነሳስቶ ዘራፍ ብሎ ብቻውን እንዲነሳ

በዳዊት ከበደ

Page 5: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

የሰሜን አፍሪካው አመጽና የአቶ መለስ ምላሽ በተንታኞች እይታ

ፊ ቸ ር 5

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የሚጠብቁት ይመስላል ሲል በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች በሚሰጡት መግለጫ ግራ እንደተጋባ ይገልጻል፡፡ በእርግጥ እሮሮ የበዛበት ህዝብ እምቢ በቃን ብሎ ሊነሳ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ይኖሩ ይሆናል። ሆኖም ግን እንደዚያ አይነት ሁኔታ ወዴት እንደሚያመራ አይታወቅም በማለት በሊቢያ ያለውን ሁኔታ በምሳሌነት ይጠቅሳል ‹ሊቢያዎች ያለበቂ ቅድመ ዝግጅት ተነስተው ጋዳፊን አናወጡት። ዝግጅት እንደሌላቸው የምናውቀው የጦር መሳሪያ በእጃቸው ስለወደቀ ብቻ በትግል መሃከል የስትራቴጂ ለውጥ አደረጉና በነፍጥ መፋለም ጀመሩ። ይህ እነሱን ያዳከመና ጋዳፊን ደግሞ እጅግ የጠቀመ ስትራቴጂ ነው› ሲል ሁኔታውን ያነጻጽራል። እናም ይላል ጃዋር ኢትዮጵያ ውስጥ ገንቢ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ በቂ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ነው በማለት የመጀመሪያው እርምጃ ትግሉ ልቡም፣ እግሩም፣ ጭንቅላቱም ሀገር ውስጥ መሆን እንዳለበት ያሰምርበታል። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከአንድ ወር በፊት ከአዲስ ነገር ድረ-ገጽ ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ‹የ1997 ሕዝባዊ መነቃቃት ባለመሳካቱ እና የ2002 ምርጫን የተመለከቱ ሰዎች ኢህአዴግ የማይነካና ከመንበረ ስልጣኑ ንቅንቅ እንደማይል አድርገው ለመደምደም የተገደዱበት ሁኔታ አለ፡፡› ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡ ኢህአዴግ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስና ሲስተሙን ለመዘርጋት ከፍተኛ ጉልበቱን እንዳፈሰሰ የሚገልጹት ነጋሶ ‹አሁን ግፍና ጭቆናው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍታት አልቻለም፡፡ … የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ አፍኗል፡፡ የሰብዓዊ መብቶችን እየጣሰና የመውደቂያ እርምጃዎቹም እየታዩ በመሆናቸው ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም›› ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ለድረገጹ ገልጸዋል፡፡

ቆይታ በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ቀደም ባሉ ጊዜያት በየሁለት ወሩ መግለጫ ይሰጡ የነበሩት አቶ መለስ ባለፈው ቅዳሜ ግን ባልተለመደ ሁኔታ እጅግ ዘግይተው (ከሰባት ወራት በኋላ) ነበር ከጋዜጠኞቹ ጋር የተገናኙት፡፡ በዚሁ መግለጫቸው በርካታ ዕድል

የሰጡት ለመንግስት ጋዜጠኞች እንዲሁም ከመንግስት ጋር ቅርበት አላቸው ተብለው ለሚገመቱ የ‹ግል› ፕሬስ አባላት ሲሆን ሰፋ አድርገው ምላሽ የሰጡትም ከእነዚሁ ወገኖች ለተሰነዘሩ ‹ልማታዊ› የሚሰኙ ዓይነት ጥያቄዎች ነው፡፡ (አውራምባ ታይምስ በመግለጫው ላይ እንዲገኝ እንጂ ጥያቄ እንዲሰነዝር ዕድል እንዳልተሰጠው ልብ ይሏል)፡፡ ከግሉ ፕሬስ አባላት መካከል የቁም ነገር መፅሄት ዋና አዘጋጅ ታምራት ኃይሉና የአዲስ አድማሷ ጋዜጠኛ ኤልሳቤጥ ዕቁባይ ዕድሉን ሲያገኙ በአገር ውስጥና በውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አነጋጋሪ የሆነ ምላሽ ያስገኙ ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል፡፡ ጋዜጠኛ ታምራት የጠ/ሚ/ሩ ደመወዝና ማህበራዊ ተሳትፎ የሚመለከት ጥያቄ የሰነዘረ ሲሆን ጋዜጠኛ ኤልሳቤጥ ደግሞ “በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያም ሊከሰት ይችላል ወይ?” የሚል ጥያቄ አቅርባለች፡፡ ጠ/ሚ/ሩ ለሁለተኛው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ የዚህ ፊቸር ዋነኛ ማጠንጠኛ ሆኗል፡፡ አቶ መለስ ለጥቂት ሴኮንዶች አሰብ አደረጉና እንዲህ አሉ “የእኛ ሕገ መንግስት ትግሎች በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ሰፊ ጎዳና የከፈተ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሚደረግ የስልጣን ለውጥ ሕገ ወጥ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ ሕገ-መንግስቱን ማክበርና ማስከበር እንዳለበትም አስቀምጧል” ያሉት አቶ መለስ አያይዘውም “ከ10 ወር በፊት ምርጫ ተካሂዶ ሕዝቡ የነበረው መንግስት እንዲቀጥል በካርዱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ይህ በሆነ በአስር ወር ውስጥ መንግስትን በነውጥ የሚያስወግድበት ምንም አይነት ሎጂክ (ስነ አመክንዮ) የለም” ሲሉ ሲሉ ምላሽ ሰጡ፡፡

ኮንትራቱ የተገኘው በውዴታ ወይስ በግዴታ?

የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር መሐመድ እንደ ዶ/ር ፍቃዱ ሁሉ በአቶ መለስ መከራከሪያ ነጥቦች አይስማማም፡፡ ኢትዮጵያ በየአምስት ዓመቱ ምርጫ ስለምታካሂድ የሰሜን አፍሪካና መካከለኛ ምስራቅ አይነት ወላፈን አይነካትም ማለት የዋህነት ነው በማለት “ከሊቢያ በስተቀር የሕዝባዊ አመፅ ወላፈን የገረፋቸው አገሮች እኮ ልክ እንደ ኢትዮጵያ በየአምስት ዓመቱ

(እንዲሁም አንዳንዶቹ በየአራት ዓመቱ) ምርጫ ሲያካሂዱ የቆዩ ናቸው?” ሲል ይጠይቃል፡፡ “እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ አንዳንዶቹ በፓርላማቸው ውስጥ ተቃዋሚዎች በርካታ ወንበሮች አሏቸው፤ የግሉ ፕሬስም በብዛትና በነፃነት ከኢትዮጵያ እጅግ በተሻለ ሁኔታ ይንቀሳቀስባቸዋል፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ነፃነትን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከእነዚህ አገሮች እጅግ የባሰች እንጂ የተሻለች አይደለችም” በማለት የፖለቲካ ነፃነት እንደ አንድ መከራከሪያ ሆኖ መቅረቡ ከአቶ መለስ ደጋፊዎች በስተቀር ማንንም እንደማያሳምን ይከራከራል፡፡ “ምርጫ ሲባል የዜጎች አፍ ሳይሸበብ፣ ተመጣጣኝና የመወዳደር አቅም ያላቸው የተቃዋሚ ቡድኖች ከአፈናና መድሎ ነፃ በሆነ ሜዳ ገለልተኛ የአጫዋችነት ሚና ባለው ዳኛ የሚመራ መሆን አለበት” የሚለው ጃዋር አቶ መለስ “ኮንትራት” የሚሉን በዚህ መንገድ የተገኘ ኮንትራን እስከሆነ ድረስ “ሕገ መንግስቱ ትግሎች በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄዱ ሰፊ ጎዳና የከፈተ ነው” የሚለው አገላለፅ “በተጨባጭ የማይታይ መከራከሪያ” ሲል ውድቅ ያደርገዋል፡፡ አቶ መለስ ግን የሰሜን አፍሪካ አይነት ህዝባዊ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲደገም የሚፈልገው ሻዕቢያ ብቻ እንደሆነ በማብራራት በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ግን የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚ ከመሆን የዘለለ ሚና እንደሌላቸው በመግለጽ ‹ሻዕቢያ አዲስ አበባን ባግዳድ አደርጋታለሁ ብሎ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን ሁሉ ሰብስቦ መሣርያ እና ፈንጅ በማስታጠቀ እየላከ ነው› በማለት ተችተዋል፡፡ ይህን ትችት ጃዋር በዚህ ጉዳይ ላይ የሻዕቢያን ስም ማንሳት አቶ መለስ ተቃዋሚዎቻቸውን

ለመደፍጠጥ የሚጠቀሙበት ስትራተጂ ይለዋል፡፡ ‹አቶ ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲሰፍን ይደግፋሉ ማለት ዘበት ነው። የአቶ መለስ ፍላጎትም እንደዛው ነው በማለት ሁለቱም መሪዎች በሁለቱም አገሮች ያለው ሁኔታ ባለበት እንዲቀጥል ነው ፍላጎታቸው፤ የአንዱ መኖር ለሌላው መኖር ዋስትና ነው፡፡› በማለት ሁለቱም አገሮች የፖለቲካ ተቀናቃኛቸውን ለማጥቃት ይህ አይነቱን ስትራቴጂ እንደሚጠቀሙ አስተያየቱን ይሰጣል፡፡

የአፍሪካ አምባገነኖች፤ የግሎባል ኢኮኖሚና የፖለቲካ አወቃቀር

በርካታ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኞች ህዝባዊ አመጽ በተነሳባቸው በእነዚህ አገሮች ላይ የነበረው የአገዛዝና የኢኮኖሚ አወቃቀር ከዓለም አቀፋዊ የግሎባል ኢኮኖሚና የፖለቲካ አወቃቅር ጋር በጥብቅ በመተሳሰሩ የተፈጠረ የተዛባ ሁኔታ ምክንያት ነው ሲሉ ያስረዳሉ። ዶ/ር ፈቃዱ በቀለም ከእነዚህ ተንታኞች ጋር ይስማማሉ፡፡ ከአለፉት ስላሳ ዓመታት ጀምሮ በዓለም አቀፍ በከፍተኛ ደረጃ የሚካሄደው የግሎባል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በተለይም በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ውስጥ ኢኮኖሚያዊ መዛባትን፣ የህብረተሰብና የባሕል ውድቀትን፣ በዚያውም መጠን የመንግስት አውታሮች መጠናከርና አገዛዞቹ የሕዝብ አለኝታ ከመሆን ይልቅ ለራሳቸው ብቻና በራሳቸው ዓለም ውስጥ ወደ መኖር እንዲገደዱ አድርጓቸዋል የሚሉት ዶ/ር ፍቃዱ አሁን ሕዝባዊ እንቅስቃሴና አመጽ የተከሰተባቸው አብዛኞቹ አገሮች፣ በአሜሪካና በተቀረው የምዕራቡ ዓለም

ካፒታሊስት የፀረ-ሽብር አጋሮችና የገበያ ኢኮኖሚ አራማጆች ተብለው ሲወደሱ፣ በዚያው መጠንም ዕርዳታ በገፍ ይፈስላቸው እንደነበር በግልጽ ይታወቃል ይላሉ፡፡ጃዋርም የዶ/ር ፍቃዱን ሀሳብ ይጋራል፡፡ ነጻ የፖለቲካ ፉክክር በሌበት ሀገር ከዜጎች መብት ረገጣ በተጨማሪ ሙስና፣ ድህነት እና የብሄራዊ ጥቅም (national interest) መሸርሸር አለ። በእነዚያ ሀገራት አምባገነኖች የህዝብን ሀብት በመቦጥቦጥ እራሳቸውን እና ዘመዶቻቸውን ሲያካብቱ ነው የሚኖሩት። ይህ ደግሞ አብዛኛው ዜጋ በድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲርመጥመጥ ያስገድደዋል። በተጭማሪም እነዚህ አምባገነኖች ህዝባቸውን መጨቆኛና ስልጣናቸውን ማራዘሚያ የውጭ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህን እርዳታ ለማግኘት የህዝባቸውን አንድነት እና የአገራቸው ጥቅም ለውጭ ኃይሎች ይቸረችራሉ። ይህ በዜጎች ውስጥ ቁጭት እና ንዴት ይፈጥራል። በሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የተነሳውን ወላፈን ካቀጣጥሉት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ይህ ነው ይላል። እነዚህ አምባገነኖች የመጨቆኛ መሳሪያዎቻቸው የሆኑትን የስለላ ተቋማትና ወታደሮቻቸው ከአሜሪካ በሚመጣ ዕርዳታና ሎጂስቲክ ይታገዝ እንደነበር ራሳቸው እርዳታውን የሚለግሱት የምዕራብ መንግስታት በግልጽ ይናገራሉ የሚሉት ዶ/ር ፍቃዱ አንድ ምሳሌ በመጥቀስ ስለሁኔታው አሳሳቢነት ሲገልጹ ‹ከሶስት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካው አምባሳደር (ዶናልድ ቡዝ) በቱኒዚያና ግብጽ እየተፈጠረ ያለው ሁኔታ እንዳሰጋቸው በመግለጽ እንደ ግብጽና ቱኒዚያ አይነት ህዝባዊ አመጽ እንዳይመጣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችን በአንድ ሆቴል ውስጥ ሰብሰበው አነጋግረዋቸዋል› ይላሉ። በዶ/ር ፍቃዱ ግምት ይህ ማለት አሜሪካንም ሆነ የተቀረው የምዕራቡ ዓለም ለአካባቢው መረጋጋት አይነተኛ ሚና ትጫወታለች የሚላትን ኢትዮጵያ ከእንደዚህ አይነቱ አደጋ ለመጠበቅና ለአቶ መለስ መንግስት አስፈላጊውን ዕርዳታ በማመቻቸት የውስጥ ለውስጥ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ …

‹አቶ ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲሰፍን ይደግፋሉ ማለት

ዘበት ነው። የአቶ መለስ ፍላጎትም እንደዛው ነው በማለት ሁለቱም መሪዎች በሁለቱም አገሮች ያለው ሁኔታ ባለበት እንዲቀጥል ነው ፍላጎታቸው፤ የአንዱ

መኖር ለሌላው መኖር ዋስትና ነው፡፡›

Page 6: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 20036

በ1806 በለንደን የተወለደው ጆን ስትዋርት ሚል የዩቲሊታሪያን ማህበራዊ ፅንሰ-ሀሳብ አፍላቂውና የኢኮኖሚስቱ ጀምስ ሚል የበኩር ልጅ ነው፡፡ አስደናቂው የልጅነት ዘመን ታሪኩ በህወይቱ መጨረሻ ገደማ፣ የጤንነቱ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በተረዳ ጊዜ በ1870 በፃፈው ግለ-ታሪክ የተገለፀ ነው፡፡ የጀርሚ ቤንትሃም እና የፍራንሲስ ፕሌስ እገዛ ታክሎበት በቤት ውስጥ በአባቱ አማካኝነት ትምህርቱን የተከታተለው ጆን ስትዋርት ሚል የግሪክ ቋንቋ በሶስት ዓመቱ፣ ላቲንኛ በስምንት ዓመቱ መናገር የጀመረ ሲሆን፣ በ12 ዓመቱ የሎጂክ ፍልስፍና፣ እንዲሁም በ13 ዓመቱ ፖለቲካል ኢኮኖሚ መማር ጀምሯል፡፡ በ1813 ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሆኖ የፕሌቶን የመጀመሪያ ስድስት ምልልሶች ከዩቲፍሮ እስከ ዜቲተስ ድረስ መጀመሪያ በተፃፈበት ግሪክኛ አጥንቶ ጨርሷል፡፡ ሚል 14 ዓመት እስኪሞላው ድረስ እኩያውን አይቶ አያውቅም፡፡ ግለ-ታሪኩ ሱታተም ባልተካተተ የእጅ ፅህፈት ውስጥ የልጅነት እድሜው እጅግ ምቹ እንዳልነበር ይናገራል፤ ‹‹የእኔ የልጅነት ጊዜ ፍቅርን ሳይሆን ፍርሃትን የሚያስተምር ነበር፡፡››

በ1821 እና በ1822 ዓመታት ከሕግ ፈላስፋው ጆን ኦስቲን ጋር የሮማን ሕግ ያጠና ሲሆን ዱሞንት ወደፈረንሳይኛ የተረጎማቸውን የቤንትሃም ሥራዎች ማንበብ ጀምሯል፡፡ በ1823 ለሠራተኛው መደብ የለንደን ነዋሪዎች የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን የሚመለከት ሥነ-ፅሁፍ በማሰራጨቱ ለአንድ ሌሊት ለእስር ተዳርጎ ነበር፡፡ ሚል በ19 ዓመቱ በኢስት ኢንዲያ ካምፓኒ ውስጥ መዝገብ ያዥ ሆኖ እየሰራና በተመሳሳይ ሰዓትም የቤንትሃም ፀሐፊ (ረዳት) በነበረበት ጊዜ ‹‹Rationale of Judical Evidence›› ለተሰኘው ባለአምስት ጥራዝ የቤንትሃም ሥራ አርታዒ ነበር፡፡ እናም እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንድነት ተደምረው ለአዕምሮ መታወክ ቢያበቁት የሚገርም አይደለም፡፡ በ1826 እና በ1827 ዓመታት ውስጥ ሚል እጅግ ስልቹ፣ ድብርት የወረረውና ትኩረት ማድረግ የተሳነው ሆኖ እራሱን አገኘው፡፡ እራሱ እንደተናገረው ከሆነ፣ ወደቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ አስተዋፅኦ ከነበራቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ የዎርድስዎርዝ ግጥሞችን ማንበቡ ነበር፡፡

በ1830 ከሀሬት ቴይለር ጋር ተዋወቀ፤ የነፍሱ አቻ ስለመሆኗ በአንድ ጊዜ ነበር የተረዳው፡፡ ሁለቱ ሰዎች እስከ 1851 - የቴይለር ባለቤት እስኪሞት ድረስ - ሳት ሳይላቸው ጓደኝነትን ሲያጣጥሙ ከቆዩ በኋላ ጋብቻቸውን ፈፀሙ፡፡ ሀሬት ቴይለር በ1858 ትሞታች፡፡

ጆን ስትዋርት ሚል ከ1865-1868 ድረስ በዌስትሚኒስትር የፓርላማ አባል ሆኖ ቆይቷል፡፡ በጋዜጦች ላይ የሚያቀርባቸውና ለመተረክ እጅግ ውስብስብ የሆኑት ሌሎች ሥነ-ፅሁፋዊ ሥራዎቹ ሎጂክ፣ ኤቲክስ፣ አናሊቲክ ሳይኮሎጂ፣ ኢኮኖሚክስ እና ፖለቲካን ያቀፉ ነበሩ፡፡ ትኩረታችንን የሳቡትና የምናተኩርባቸው ሥራዎቹ “On Liberty (1859)”፣ “Utilitarianism (1861)”፣ እንዲሁም “Considerations on Representative Government (1861)” የተሰኙት ይሆናሉ፡፡ የህትመት ጊዜያቸውን ቅደም ተከተል ከግምት አለማስገባቱ ምቹ

ሆኖ ተገኝቷል፡፡[ U t i l i t a r i a n i s m

(ዩቲሊታሪያኒዝም) በማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት ‹‹ጠቃሚያዊነት›› የሚል አቻ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን ብዙዎችን የሚጠቅም ወይም ለብዙዎች ደስታን የሚፈጥር ድርጊት ትክክለኛ ድርጊት ነው የሚል አስተምህሮት ነው፡፡] እናም የጆን ስትዋርት ሚል “Utilitarianism” ሥራ መጀመሪያ ‹‹ፍሬዘርስ›› መፅሔት ላይ ነበር የታተመው (በመፅሐፍ መልክ የወጣው በ1862 ነበር)፡፡ ሚል ይህንን መፅሐፍ የፃፈበት ዓላማ የቤንትሃምን እና የአባቱን የጀምስ ሚልን የጠቃሚያዊነት

እሳቤ ካርላይል እና ሌሎች ፈላስፎች በመጠን ወይም በቁጥር በሚለካ ደስታ ላይ የሚያተኩር ፍልስፍና ለአሳማ ብቻ የሚመጥን አስተምህሮት እንደሆነ ከሚሰነዝሩበት ትችት ይታደገው ዘንድ ነው፡፡ በዚህ ሥራው ጥቂት የመግቢያ ነጥቦችን ከጠቃቀሰ በኋላ የሚከተለውን የጠቃሚያዊነት ትንታኔ ያቀርባል፡-

የሞራል መሠረቶችን፣ ጠቃሚነትን (utility)፣ ወይም የከፍተኛ ደስታ መርሆን የተቀበለ ሥርዓት ወይም ምልከታ ድርጊቶች ደስተኝነትን በሚፈጥሩበት መጠን ልክ ትክክል እንደሆኑ፣ እንዲሁም የደስተኝነትን ተቃራኒ ለማመንጨት በሚያዘምሙበት መጠል ልክ ስህተት እንደሆኑ ያምናል፡፡ ደስተኝነት ሲባል የታለመውን እርካታ (pleasure)፣ እና የስቃይን ወይም የህመምን አለመኖር ማለት ነው፤ ደስተኝነት የለሽ (unhappiness) ሲባል የታሰበው ህመም (pain)፣ እና የእርካታ እጥረት ነው፡፡ - (Utilitarianism Ch.2)

እርካታ ከራሱ በቀር የማንኛውም የመጨረሻ ግብ ምክንያት ወይም መምጪያ ያልሆነ ላዕላይ ወይም ጠቅላይ ጥሩ ነገር ነው፡፡ እርካታ ሁሉም ሰው በውስጡ እና ለራሱ የሚሽተው (የሚፈልገው) ነው፡፡ ሚል ሁሉም ሰው በትክክል ከሚሽተው

ጋር የተያያዘ ካልሆነ በቀር ‹‹ተፈላጊ›› (desirable) የሚለውን ቃል መጠቀም ትርጉም አይሰጥም ብሎ ያስባልና፣ እርካታ ስለዚህም ላዕላይ የሆነ አስፈላጊ የመጨረሻ ግብ (end) ነው፡፡ ይህ የመጨረሻው ነጥብ በቶማስ ሆብስ እና በቤንትሃም ውስጥ እንደምናገኘው ዓይነት - ‹‹ጥሩ››፣ ስለዚህም ‹‹ተፈላጊ›› የምናላቸው ሀሴትን ወይም ደስታን ለምናገኝባቸው ነገሮች የምንሰጣቸው ስሞች ናቸው - ተመሳሳይ ስማዊነት (nominalism) ይታይበታል፡፡ ነገር ግን ሚል ነጥቡን ያቀረበበት መንገድ በአሉታዊ መልኩ የሚታወቅና ድፍንፍን

ያለ ሲሆን በዚህም በኤፍ.ኤች ብራድሊይ “Ethical Studies(1874)” እና በጂ.ኢ. ሙር “Principia Ethica(1903)” አሳመኝ በሆነ መልኩ ተተችቶበታል፡፡ ለቤንትሃም እንደሆነው ሁሉ፣ ለሚልም ሥነ-ልቦናዊ ሄዶኒዝም ግለሰባዊንም ሆነ ማህበራዊ ምግባሮችን ይጠቁማል፡፡ (ሄዶኒዝም ከፍተኛው ጥሩ ነገር እና የሰው ልጅ ህይወት ትክክለኛው ግብ እርካታ ነው የሚል የሞራ ፅንሰ-ሀሳብ ነው፡፡) የአንድ ሰው ታላቅ የሆነ ደስታን የመሻት ሁኔታ የግለሰቡ ብቸኛ ውስጣዊ ግፊት ወይም ተነሳሽነት ነው፤ የሁሉም ሰው ከፍተኛ ደስተኝነት የማህበራዊ ጥሩነት መስፈርትና የሞራላዊ ድርጊት ዓላማ ነው፡፡ ነገር ግን ሚል ሁሉም እርካታዎች እኩል አይደሉም ሲል ይከራከራል፡፡ እርካታ ከሞራላዊ ጥራት (ብቃት) አንፃር ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ የሚል ደረጃ ሊወጣለት ይችላል፤ የህሊና እርካታዎች ከአካላዊ እርካታዎች የላቁ ሲሆኑ በዚህም ይበልጥ ተፈላጊ (desirable) ናቸው፡፡ ሚል እንደሚለው፣ ‹‹አሳማ ሆኖ እርካታን ከማግኘት የሰው ልጅ ሆኖ አለመርካት የተሻለ ነው፤ አንድ ቂል ሰው ሆኖ እርካታን ከማግኘት ይልቅ ሶቅራተስን ሆኖ አለመርካት ይሻላል::›› - (Utilitarianism Ch.2) ማንኛውም ብቁ ፈራጅ - ሁለቱንም የእርካታ ዓይነቶች ያየ ማንኛውም ሰው - ከላይ የተጠቀሰውን ተመሳሳዩን ያስባል፤ ሆኖም ተመሳሳዩን የማያስብ ማንኛውም ሰው ብቁ ፈራጅ

አይደለም፡፡ እዚህ ላይ ሚል የእርሱን የሞራል ፍልስፍና ከቲ.ኤች. ግሪን ‹‹ግለ-ምሉዕነት›› (self-realisation) ጋር ጎን ለጎን በማዳበር፣ ምንም ሳይታወቀው የቤንትሃምን የጠቃሚያዊነት (Benthamite Utilitarianism) የጠራ ውሃ አጨቀየው፡፡ የሰው ልጆች ዝም ብለው እርካታን በመፈልግ ወይም በመከተል ጥሩውን ነገር አያገኙም፤ ይልቁንም ‹‹ከፍተኛውን የአዕምሮ ችሎታቸውን ጥቅም ላይ የሚያውል የአኗኗር ምግባር›› ለራሳቸው በማግኘት እንጂ፡፡ ተቃርኖ ያጠላበት የሚል

የቤንትሃምን ጠቃሚያዊነት መልሶ የመገንባት ሙከራ ባልተጠበቀ መልኩ ብቁ አይደለም፡፡ መከራከሪያው አንዳንድ እርካታዎች ወይም አንዳንድ ዓይነት እርካታ ከሌሎች የበለጡ እንደሆኑ ከሚገልፅ እራሱን የማይከላከል ምልከታ የሚዘል አይደለም፡፡ እርካታ እራሱ ከፍተኛው ጥሩ ነገር ነው የሚለውንና ነገር ግን እርካታዎች በብዛት ብቻ ሳይሆን በጥራትም ይለያያሉ የሚለውን ሀሳብ በተመሳሳይ ሰዓት መጠቆም የሚኖረውን ችግር የተረዳ አይመስልም፡፡ የሚል መከራከሪያ ከዚህ ችግር የማይላቀቅ ወይም ነፍስ የማይዘራ አልነበረም (አንድ ሰው ከቤንትሃም የጠቃሚያዊነት ዋነኛ መመዘኛ አንፃር የህሊና እርካታዎች ከአካላዊ እርካታዎች ይልቅ የበለጠ የዳበሩ፣ ረጅም ጊዜ ቆይታ ያላቸው፣ ይበልጥ ንፁህ እና የመሳሰሉት እንደሆኑ መከራከሪያውን ሊያቀርብ ይችላል)፤ ነገር ግን እራሱ ሚል ሊታደገው ሙከራ አላደረገም፡፡

[ጆን ስትዋርት ሚል ትክክለኛው ነፃነት የሌሎችን ጥረቶች ሳናደናቅፍ የራሳችንን መልካም ነገር በራሳችን መንገድ የመፈልግ ወይም የመከተል ነፃነት እንደሆነ ይገልፃል፡፡ እንዲሁም ከሁሉም የመንግስት ሥርዓት ዓይነቶች የውክልና መንግስት የተሻለ መሆኑን ያናገራል፡፡ በሁለቱ ነጥቦች ዙሪያ ሳምንት በስፋት እንመለሳለን፡፡]

የጠቃሚያዊነት አስትህሮት እና ግለሰባዊ ደስታ

ጆን ስትዋርት ሚል /1806-73/

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የጫጩት ማስፈልፈያ ማሽኖችን

ኢንኩቤተሮችን

የአንድ ሰው ታላቅ

የሆነ ደስታን የመሻት

ሁኔታ የግለሰቡ ብቸኛ

ውስጣዊ ግፊት ወይም

ተነሳሽነት ነው፤ የሁሉም

ሰው ከፍተኛ ደስተኝነት

የማህበራዊ ጥሩነት

መስፈርትና የሞራላዊ

ድርጊት ዓላማ ነው፡፡

የ ፖ ለቲካ ፈ ላ ስፎች

መጠናቸው ከትንሽ እስከ ትላልቅ •ማለትም ባለ 50፣100፣200፣300፣400፣500... •ወዘተ እንቁላል በመያዝ ጫጩቶችን ማስፈልፈል የሚችሉ የክልል ደንበኞች ሙሉ ክፍያ •በአድራሻችን ከላኩ ወይም በአካል ከከፈሉ በሚኖሩበት ከተማ ሆነው ማሽኑን የሚረከቡበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡ በብዛት ለሚያዙ የዋጋ ቅናሽ አለን•

ሻያ ኤሌክትሮ መካኒካል ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

በተመጣጣኝ ዋጋ በነጠላና በብዛት እናቀርባለን ይጠይቁን መጠናቸው ከትንሽ እስከ ትላልቅ ማለትም

ስልክ 0911 69 31 02/0913 54 87 21/

Page 7: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

ባሏን ጎዳው ብላ መንታ ወለደች

7

ዛሬ በሀገራችን ብዙ ዜጎችን የፖለቲካው ሁኔታ በጥልቅ ያሳስባቸዋል፡፡ ሌሎችን የሚያስጨንቀው ደግሞ የኢኮኖሚው ጉዳይ ነው፡፡ የቀሩት ዜጎችም ኢኮኖሚውም ይሁን ፖለቲካው ሊጠገን ይችላል፣ የሚያሳስበው የሀገሪቱ የባህል ድልድይ መሰበር ነው ይላሉ፡፡

አሁን አሁን በከተማውም ሆነ በገጠሩ የያገባኛል ባይነት ወይም የኃላፊነት ስሜት አየጠፋ ነው፡፡ ለታሪክ፣ ለባህልና ለማንነት ግድ የለሽ ሆነናል፡፡ ፍርሀትና ተስፋ ቢስነት ተንሰራፍቷል፡፡የአልኮልና የጫት ሱሰኝነት ትልቁን ትንሹን፣ ወንዱን ሴቱን፣ ተማሪና ሰራተኛውን ሁሉ በአንድ መርከብ ላይ አሳፍሯል፡፡ የእርስ በእርስ መተሳሰብ፣ መግባባትና ስምምነት ጎድሏል፡፡ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ ደግነት፣ በራስ መተማመንና የአትንኩኝ ባይነት ስሜት ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ ሄዷል፡፡ የሚታመን፣ በቃሉ የሚገኝ፣ ከራሱ አልፎ ለሌሎችም የሚያስብና የሚቆረቆር ዜጋ ማየት ብርቅ እየሆነብን ነው፡፡ ስስት፣ ግለኝነት፣ ስንፍናና ጥገኝነት ነግሷል፡፡ ከሚሰሩት የሚያሴሩት እየበዙ ነው፡፡ ከእጅ ይልቅ ምላስ ተወዷል፡፡

በየእለቱ እንደምንታዘበው ‹‹ነውር›› የምንለው ነገር ጠፍቷል፡፡ አይናችንም፣ በጆሯችንም ክፉ ክፉው ይገባል፡፡ በአደባባይ ላይ ሰዎች ተናንቀው ሲናረቱ ትርዒቱን በነፃ የሚከታተል እንጂ ጠጋ ብሎ የሚገላግል ሞኝ ወይም እብድ ሆኖ ይታሰባል፡፡ ወደምግብ ቤት ብትዘልቁ እጅን ታጥቦ ቧንቧውን ከፍቶ የሚሄደውን ሰው ብዛት ሥራ አስኪያጆቹ ይቁጠሩት፡፡ በየመፀዳጃ ቤቱ ግድግዳ ላይ የሚፃፈውን እዚህ ለመጥቀስ ይከብዳል፡፡ በሕዝብ አደባባይና በየአውራ ጎዳናው ላይ ምራቁን ጢቅ እያለ፤ ሶፍቱን፣ የሙዝ ልጣጩን የትም እየወረወረ የሚጓዘው አያሌ ነው፡፡ ማጭበርበር፣ ውሸትና ማታለል የኑሮ

ዘይቤ ሆኗል፡፡ የተበደረውን ገንዘብ ወይም የተዋሰውን ዕቃ በአግባቡ የሚመልስ አንሷል፡፡ መተማመን ጎድሏል፡፡ የተማረ፣ ያልተማረ፣ ድሃ ወይም ኃብታም ሳይል የመልካም ሥነ-ምግባር ችገሮች በሁሉም ዘንድ ይታያል፡፡ የሀገር ፍቅርና ሰብዓዊ ስሜት ቀዝቅዟል፡፡ የውጭ ባህል አድናቂነትና ምርኮኝነት እየጨመረ ነው፡፡ የውጭውን የምንከታተለው ጠቃሚና በጎውን ቢሆን እንዴት መልካም በሆነ ነበር፤ እንክርዳድና ገለባውን ብቻ ሆነ እንጂ፡፡

ለመሆኑ የከበረ ባህላችን እንዲዋረድ፣ እሴታችን እንዲራቆት፣ እምነታችን እንዲላላ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? ትጥቃችንን ማን አስፈታን? የምለውም ይህንኑ የባህል መሸርሸርና የስብዕና መራቆት ነው፡፡ እንዲህ የምብሰለሰልበትን ጥያቄ ለአንድ ወዳጄ አነሳሁለት፡፡ ወዳጄም ሲመልስ፣ ‹‹ግሎባላይዜሽን እየበዛ ሲመጣ፣ የኑሮ ውድነትና ድህነት እየተስፋፋ ሲሄድ፣ ብዙ ሰው ውጥረት ውስጥ ሲገባ፣ የአኗኗር ዘይቤውም እየተቀየረ ይሄዳል›› አለኝ፡፡ ድህነት ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ግኝት አይደለም፤ በድህነትና በጨዋነት፣ በክብርና በኩራት አልኖርንምን? ቁሳዊ ብልፅግና ሥነ-ምግባርን ያላብሳል ወይ ብዬ ተሟገትኩ፡፡ ወዳጄ በሰጠኝ ምላሽ፣ ‹‹አሁን’ኮ ፀዐዳ የለበሰውም ነው እየተቸገረ ያለው፡፡ ዱሮ በልብሱም፣ በፊቱም ስታው ይሄ ችግረኛ ነው ትላለህ፡፡ አሁን ግን የቱ እንዳለው፣ የቱ እንደቸገረው አታውቅም፡፡ ብዙ ሰው የሚራብ፣ ብዙ ሰው የሚቸገር ከሆነ የሚታሰበው ስለሥነ-ምግባር ሳይሆን ስለሆድ ይሆኗል፡፡ ‹‹እንዴት ሆዴን ሞልቼ አድራለሁ እንጂ፣ እንዴት ስሜንና ክብሬን ጠብቄ፣ እንዴት ቃሌን አክብሬ እኖራለሁ?›› የምትልበት ምክንያት የለም››፡፡ እንደእርሱ አባባል ከሆነ፣ የኑሮ

ውድነትና ውጥረቱ አኗኗርን፣ አስተሳሰብን ያበላሻል፡፡ በዚህ ሳቢያ ግለኝነትና ራስን ብቸኛ ማዕከል አድርጎ መንቀሳቀስ እየበረከተ ሄዷል፡፡

የሥነ-ምግባር፣ የባህልና የእምነት ትጥቃችንን ማን አስፈታን የሚል ጥያቆዬን ይዤ ወደ ጂንየስ የኢንተርፕርነርሺፕ የሥልጠናና የምክር አገልግሎት ማዕከለ ጎራ አልኩኝ፡፡ ‹‹ዓለማችን ባለራዕይ ዜጎችን መፍጠር ነው›› የሚለው የዚሁ ማዕከል ባለቤትና አሰልጣኝ ዶ/ር ወሮታው በዛብህ ይባላሉ፡፡ ዶክተሩ፣ ‹‹ራዕይ የሌላቸው ሰዎች በሚበዙበት ሀገር ግዴለሾች ይበዛሉ፡፡ የይቻላል ባዮች ማነስ፣ ከእጅ ወደአፍ የሆነ ኑሮ የሚገፉ፣ ተሸናፊዎች የበዙበት፣ ባለራዕዮች ያነሱበት ሀገር እጣ ፈንታው ድህነትና ውድቀት ነው›› ይላሉ፡፡

ዶ/ር ወሮታው በዛብህ በሀገራችን ለሚታየው የባህል ድቀት መንስዔ በዋናነት ሶስት ነጥቦችን ያስቀምጣሉ፡፡ የመጀመሪያው ቤተሰብ ሲሆን፣ ሁለተኛው ት/ቤቶች፣ ሶስተኛው ሥርዓቱ ነው፡፡ ይህንኑ ሲያብራሩም፣ ‹‹በአሁኑ ወቅት ከእኔ ጀምሮ ወላጆች ልጆችን ለማሳደግ የዕለት ከዕለት ኑሮው አላደርስ ብሎን ለልጆች የሚሆን ግዜ እየጠፋ፣ ለልጆች ማስተማርና መንገር የሚገባቸው አይነገርም፡፡ ለምሳሌ እኔን አባቴ እጄን ይዘው ቤተ-ክርሰቲያን ሄጄ፣ አደን አብሬ ወጥቼ፣ እርሻ አብሬ ሄጄ፣ አረም አርሜ፣ ጠብ-መንጃ ተሸክሜ፣ ከበቅሎ ፊት እየሮጥኩ በቅሎዋ ከቀደመች የእርሷን አለንጋ እኔ እየቀመስኩ ነው ያደግኩት፡፡ ‹‹ውሃ ጠማኝ›› ብዬ ከመንገድ መቅረት አልችለም፡፡ ሳይጠማህ፣ ሳይርብህ፣ ሳትፈተን ነው እንዴ የምታድገው? ነገ ሀገርህ ላይ አንድ ችግር ቢከሰት እኔም ልጅ ወልጃለሁ የምለው፤ ተርበህ ድንበርህን ስታስከብር፣

ተጠምተህ ጥቃትን ስትከላከል፣ ጥረህ ግረህ ቤተሰብህን ስታስተዳድር መሆኑ ይነገርሀል፡፡ ትንሽ ሥራ ስንይዝ የ100 እና የ150 ብር ደመወዝ ተቀጣሪ ሆነን እንኳ ‹‹ቤት ሥሩ፣ እንዴት በኪራይ ቤት ትኖራላችሁ? ቆጥቡ፣ ሰው እንዴት ያገኘውን ሁሉ ይበላል? አስቡ፣ ልብ ግዙ›› እያሉ ይነግሩን ነበር፡፡ በወላጆቻችን ዘንድ እንቅልፍና ስንፍና አይወደድም፡፡ አንቅልፍና ስንፍና ድህነትን ይወልዳል ይሉናል፡፡ ይሄን አይነት ኩትኮታ እኔ ዛሬ ልጆቼ ላይ አላደርገውም፡፡ ትላንት አባቴ በእኔ ላይ የነበራቸው ትኩረትና እኔ ዛሬ ልጆቼ ላይ ያለኝ ትኩረት በጣም የተራራቀ ነው፡፡ የባለቤቴ እናት በልጆቻቸው ላይ የነበራቸው ተኩረተና ዛሬ ባለቤቴ በልጆቿ ላይ ያላት ትኩረት በጣም ይለያያል፡፡ ይሄ የላላ መስመር በስፋት ያለ ይመስለኛል፡፡››

ዶ/ር ወሮታው ሌላው የሚያነሱት የሥነ-ምግባር ትምህርትን ነው፡፡ ይህንኑም ከራሳቸው የአስተዳደግ ዘመን ጋር በማስተያየት፣ ‹‹ከቄስ ት/ቤት ጀምሮ ስለሥነ-ምግባር እንማራለን፡፡ የግብረ-ገብ መምህራችን ከቤተ-ክርስቲያን መጥተው የት/ቤት ፕሮግራም ተይዞላቸው ያስተምሩን ነበር፡፡ ከወላጆቻችን ጋር ቤተ-ክርስቲያን እየሄድን፣ በት/ቤትም ፈሪሀ እግዚአብሔርን እየተማርን፣ ስለሥራ፣ እንቅልፍና ስንፍናን በሚያወግዝ ሁኔታ እራስን ስለመቻል አዘውትሮ ሲነገር፣ የሥነ-ምግባር መተላለፍ ሲያስቀጣን፣ በታሪካችንና በባህላችን እንድንኮራ ሲነገረን አድገናል፡፡ ዛሬ እንደማየው ግን ት/ቤቶች በዚህ አኳያ የሚገባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ አልቻሉም፡፡ እኔም የህፃናት ት/ቤት አለኝ፡፡ በቅርቡ ሰልፋቸው ላይ ተገኘሁና

ታዋቂው የፊልም አክተር ጃኪ ቻን አንድ ተልዕኮ ለመፈፀም ከባልደረቦቹ ጋር በሄሊኮፕተር ይጓዛል፡፡ ወታደሩ፣ ጃኪ ቻንና ባልደረቦቹ የተሳፈሩበት ሄሊኮፕተር ይመታና አየር ላይ በመጋየቱ ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ ለመውደቅ ይገደዳል፡፡ የሞቱት ይሞቱና ከተረፉት መሀል አንዱ ጃኪ ቻን ሆነና ከአየር ላይ እየተምዘገዘገ መጥቶ ጫካ ውስጥ ይገባል፡፡

ከጫካው በቅርብ ርቀት የሚገኙት ጎሳዎች ለአደን ወደ ጫካው ሲመጡ ጃኪ ቻን ራሱን ስቶ ጫካው ውስጥ ያገኙትና ተሸክመው ቤታቸው ወሰዱት፡፡ ጃኪ ቻን ከሦስት ቀን በኋላ ከገባበት ሰመመን ሲወጣ አይኑ እንግዳ ነገር አየ፡፡ ዙሪያውን የከበቡት ሰዎች አዲስ ሆኑበት፡፡ ከጎሳዎቹ መሀል እሱ ብቻ ነው ለየት የሚለው፡፡ ብቸኝነት ተሰማው፤ እንባ አቀረረ፤ መጨረሻ ላይ የሚያደርገው ሲጠፋው፣ “...እኔ ማነኝ?” እያለ በተደጋጋሚ ጮኸ፡፡ በጣም ጮኸ፡፡ (ከላይ የሰፈረው ትረካ፣ ‘Who Am I?’ ከሚለው የጃኪ ቻን ፊልም ውስጥ ተቀንጭቦ የተወሰደ ጽሑፋዊ መግለጫ ነው፡፡)

በእርግጥም ማንነትን አለማወቅ ያስጮሃል፤ ሰው በገዛ ሀገሩ፣ መንደሩ፣ ያውም ሁለት ዓይነት ፀጉር ባበቀለበት እርስቱ ላይ ብቸኝነት ሲሰማው ያስጮሃል፡፡ ሰው እንዴት በሰው ተከቦ ብቸኝነት ይሰማዋል? የሶስት በጎችን ቆዳ የፈጀ ልብስ ለብሶ እንዴት ይበርደዋል? ... ብለው አንዳንዶች የዋህ ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡

ነገር ግን አስከፊ ጊዜ ከመጣ 80 ሚሊየን ማገዶ እየነደደ አንድ ሰው ላይወብቀው ይችላል፡፡ መልካም ዘመን ላይ ከደረስን ደግሞ በሚጠባ ህፃን ትንፋሽ 80 ሚሊየን ህዝብ ተሟሙቆ ሊኖር ይችላል፡፡

የኢትዮጵይ ሰዎች ‹እኔ ማነኝ?› ብለው የሚጠይቁበት ጊዜ አሁን ይመስላል፡፡ አንድ ዓይነት ደምና ባንዲራ ያላቸው ሰዎች ‹እኔ ማነኝ?› ብለው መጠየቅ ባይኖርባቸውም ማህበር፣ ድግስ እና ጉባኤ በተስፋፋ ቁጥር ጥያቄው መነሳት ይጀምራል፡፡

ሲጀመር ህብረትና አንድነት የሌላቸው ሰዎች የማህበር ፈቃድ ሊሰጣቸው አይገባም ነበር፡፡ ግን ጊዜው የማን አለብኝነትና የምን ታመጣለህ ስለሆነ ከጉልበተኞች ጋር ቡጢ እየተለዋወጡ መዝለቅ ከባድ ነው፡፡ አንድ የሕግ ተቆርቋሪ ከስንት ማህበር ጋር ተፋልሞ ይችለዋል? የድግሱን ወጥ የሚያማስሉትም ቢሆኑ ወጣቸውን እንደሚቀቅሉበት እሳታቸው እየተፋጁ ተቆርቋሪዎችን ሁሉ አመድ አፋሽ አድርገዋቸው የለ እንዴ?

ይገርማል! ገና ለሚቀጥሉት አምስት ሺህ ዓመታት ሲገርመኝ ይኖራል፡፡ (የተሰጡትን ወራቶች በሚገባ የኖረ ሰው ብዙ ሺህ ዓመታታ የኖረ ያህል ደስ ይለዋልና ነው፡፡) የእስራኤል መሪ የነበረው ሙሴ ማርያም የምትባል እህት ነበረችው፡፡ ይህቺ እህት ተብዬ በዘመናችን እንደተነሱት የቡድን አባቶች ዓይነት ሴት ነች፡፡ ዘርና ሃይማኖት የማይለየው ፍቅር ሙሴን ከኢትዮጵያ ሴት ጋር ያፋቅረዋል፡፡ ትዕዛዙ የፍቅር ነውና ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን (ሀበሻዋን) ሴት ለማግባት ሲዘጋጅ፣ የሙሴ እህት “እንዴት?” አለች፡፡

እንዴት ያለ ዘርህ፣ ያለ ነገድህ፣ ያለ ዜግነትህ፣ ያለ ብሔርህ፣ ያለደምህ ... ትጋባለህ? በሚል ስሜት ተነሳስታ ኢትዮጵያዊቷን ማግባት እንደሌለበት ስትነግረው ሙሴ ሳይሆን አምላኳ ተቆጣት፡፡ ዘረኝነትን ታስፋፋ ነበር፤ ሙሴ በእስራኤል “ማህበር” ብቻ እንዲታቀፉ ለማድረግ ያደረገችው ጥረት በረሃ ላይ ቀረ፡፡

ከበሮ አንስታ ያመሰገነችው አምላኳ ሕገ-ወጥ ማህበር ለመመስረት ያደረገችውን ጥረት ከግምት በማስገባት ክስ መሰረተባት፤ ተጠርጣሪዋ የክስ መዝገቧ ሲመረመር ወንጀሉ ከባድ ሆኖ ተገኘ፡፡ ወንድሟን በማህበር አስታቅፋ ኢትዮጵያዊቷን ለመፈንገል ያደረገችው ጥረት በሞት እንድትቀጣ ዋጋ አስከፈላት፡፡ አፈንጋጯ እህት በሞት ተቀጥታ ጭው ባለ በረሃ ተቀበረች፡፡

የሚገርም ታሪክ ነው፤ ከታሪኩ በላይ የሚገርመው ነገር ደግሞ ቅጣቱና የቅጣቱ ተፈፃሚነት ነው፡፡ ለካ አለአግባብ

መቧደንና ቀለም እየለዩ ማንጓጠጥ “በሞት” ያስቀጣል፡፡ ይህ ታሪክ የአንድ ሀገር ሰዎች ቀርቶ የማይተዋወቁ፣ በካርታ ላይ አቀማመጥ አራምባና ቆቦ የሆኑ ሀገራት እንኳን መለያየት እንደሌለባቸው ያስገነዝባል፡፡ ይሄኔ የሙሴ እህት ቅጣቷን ባትቀበልና ወንጀሏ ተድበስብሶ ቢቀር ኖሮ አንድ ጥያቄ ይፈጠር ነበር፡፡ ለሚስትነት የታጨችው ኢትዮጵያዊት ሴት “እኔ ማነኝ?” እያለች ጭንቅላቷን በጥያቄ ታፈነዳው ነበር፡፡ ሰው መሆኗን ታውቃለች፤ ግን የሙሴ እህት ያነሳችው የመቧደን ጥያቄ ሰው መሆኗን እንድትጠራጠር ያደርጋት ነበር፡፡

ዛሬ ግን መከፋፈል እንደ ጌጥ ነው የሚታየው፤ ያውም በስንት መከራ ከመሬት ውስጥ ተፈልጎ እንደሚገኝ ጌጥ፡፡ እገሌ የማን ነው? ሲባል የኢትዮጵያ ማለት የቀረ ይመስላል፡፡ “ኧረ እሱ እኮ የእነ እንኮይት ማህበር አባል ነው” ይባላል፡፡

ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ ሙሴ እህት የዘረኝነት ማህበር ሲያቋቁሙ ይታያሉ፡፡ ጥረታቸው ሲከሽፍና እነሱ በሞት ቀርቶ በአርጩሜ ሲቀጡ እንኳን አይታዩም፡፡ አንዱ ወጠጤ ተነስቶ የራሱን ማህበር ሰርቶ ማህተም መምታት ይጀምራል፡፡ የድጋፍ ማህተም የሚመታላቸው ደግሞ ከማህበሩ ስራ አስኪያጅ ጋር የብሔር ወይም የንግድ ግንኙነት ካላቸው ነው፡፡

ዛሬ የመንደር እድር ለመግባት የዘር ሀገር ይቆጠራል፤ ሽበት ካበቀሉ አባቶቼ እግር ሥር ቁጭ ብዬ ከሰማኋቸው ታሪካዊ ወሬዎች አንዱ ዕድር ነው፡፡ “ድሮ እድር ለመግባት የቀበሌ መታወቂያ ብቻ በቂ ነበር፤” ይላሉ - የሀገር ዋልታ ሽማግሌዎች፡፡ ዛሬ በመታወቂያው ፈንታ “ቋንቋ” ሆኗል የእድሩ መስፈርት፡፡

ምንኛ ይናገራል? ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ነው? ጥያቄዎቹ ቢቀረፉም እስካሁን አልተወገዱም፡፡ ዘፈኗን በሰማሁ ቁጥር እንደተወርዋሪ “ኮከብ” አንዳች ኃይል ፈጥራ የምታስደምመኝ አርቲስት ከ‹‹ጨጨሆ›› በፊት ያወጣችው አልበሟ ውስጥ ‹አንድ አድርገን› የሚል ዘፈን በተራ ቁጥር ሁለት ላይ ይገኛል፤

‹ ‹ ድ ሮ መች ነበር ዘር መርጦ ጎረቤት፣

‹‹በጧቱ በጥንቱ በእናት በአብዬ ቤት?”የሚል መጠይቃዊ ስንኝ በመቋጠር የዘረኝነት ትብታብ እንዲፈታ በሙያዋ ተማፅናለች፡፡ በእርግጥም ሁሉንም ሰው ሊያሳስበው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው አስፈላጊውን ማህበራዊም ሆነ ፖለቲካዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት ‹‹ሰው›› ብቻ መሆን በቂው ነበር፡፡ ግን በአፈንጋጭ ማህበራት ምክንያት ሰው ከመሆን ባሻገር ያሉ የአጥንት ቆጠራዎች ከፍተኛ ስጋት እየፈጠሩ ነው፡፡ ውሻ ይመስል አጥንት እየተከተሉ ብይን መስጠት ሊያስቀጣ ይገባል፡፡ መድፍ የታጠቀው ፋሽስት ያልለያያት ሀገር ዛሬ ‹‹ማህተም›› የታጠቁ ‹‹ማህበራት›› እጅግ እጅግ ያሰጓታል፡፡

ብሔር ማለት እኮ በቀላል ትርጉም አንደኛው የፍጡራን ስብስብ ጋር የሌለው መስዕብ ሌላኛው ስብስብ ጋር ሲገኝ ብሔር ይባላል፡፡ ብሔርን ጌጥ የሚያሰኘውም ይኸው ልዩነት ነው፡፡ ግን ደግሞ ብሔር የፈለገውን ያህል ውበትና ጌጥ ነው ቢባልም ሰው ከመሆን አይቀድምም፤ አይበልጥምም፡፡ አሁን ግን የአቀማመጥ መዛባት ተፈጥሯል፡፡ ሰው ከላይ ብሔር ከታች መሆን አለበት እንጂ፣ የኩንግፉን ካራቴ ይመስል ተከረባብቶ ብሔርተኝነት የሰው ልጅን ሊመራው አይገባም፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ከሚመስሉት ሰዎች ጋር እየኖረ ‹‹እኔ ማነኝ?›› የሚል ጥያቄ ካነሳ አደጋ ላይ ስለመሆኑ ከሦስት ምስክሮች የበለጠ ማመሳከሪያ ነው፡፡

አንድ ሰው ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ጅቦች መሐል ቢያገኘው ‹‹እኔ ማነኝ?›› ሊል ይችላል፡፡ ጥያቄውም ተገቢና ወቅታዊ በመሆኑ ከጅቦቹ መሐል ወጥቶ ማንነቱን ፍለጋ መዞር አለበት፡፡ ግራ የሚያጋባው ነገር ግን እንዲህ ነው፡፡ በማን አለብኝነት የሚተዳዳረውን ከፊሉን የኢትዮጵያ ህዝብ ለማብራሪያነት ልጠቀምበት እስኪ!

አንድነት ስትሰብክ ከከረመችው

በሰሎሞን ሞገስ

[email protected]

በታዲዎስ ጌታሁን

ትጥቃችንን ማን አስፈታን?

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ኮሜንተሪ

Page 8: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003የ አቤቶ ወግ8

አንድ ወዳጄ በ1811 ዓ.ም የተወለዱት ሼህ ሁሴን ጅብሪል በቃል ሲናገሩት የነበረውን እና ቦጋለ ተፈሪ በዙ የተባሉ ፀሐፊ በመፀሀፍ ያሳተሙትን ‹‹ትንቢተ ሼህ ሁሴን ጅብሪል›› የተሰኘ መፀሀፍ በቅርቡ አውሶኝ ነበር፡፡ ሼሁ አስገራሚ ሼህ ናቸው፡፡ ያልገጠሙት አይነት ግጥም ያልተነበዩት አይነት ትንቢት የለም፡፡ ደግሞ ግጥማቸው ቲጣፍጥ!! ለዛሬ መግቢያ ታኽል… ይቺን ልወርውርና በቀጣይ ለሚኖሩን ወጎቻችንም እንቃመሳቸዋለን፡፡ ‹‹ተቴድሮስ አንስቶ ተፈሪ ድረስዘመኑ ይበቃል የዘውድ ንጉስንጉስ አለ ብለህ አትወሳወስ በምርጫ ታልሆነ የለም የሚነግስ›› ይላል፡፡ ልብ አድርጉ ሼሁ ይህንን ሲሉ 1850 ዓ.ም አካባቢ ቢሆን ነው፡፡ ይኽው የሼህ ሱልጣን ትንቢት ደረሶ ከሀገር አቀፍ ምርጫ እስከ ሟሟያ ምርጫ እየተደረገ መሪያችንን መምረጥ ከጀመርን ቆየን (በቅንፍ ሼሁ በትንቢታቸው ምርጫው አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለበትና እንደሌለበት አልጠቀሱም!) ባለፈው ሳምንት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ‹‹ገና ከተመረጥን አስር ወር እንኳ ሳይሞላን… ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን ሌት ተቀን ደፋ ቀና እያልን... ምን አደረግን ምን በደልን እና ነው ህዝባዊ ተቃውሞ የሚነሳብን…›› ሲሉ አንዲት ደፋር ጋዜጠኛ ለጠየቀችው ጥያቄ መልስ ሰጥተው ነበር፡፡ ደፋሪቱ እንዲህ ብላ ነበር የጠየቀቻቸው፡፡ ‹‹ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በሰሜን አፍሪካ እና በሌሎች የአረብ አገራት እየተነሳ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ በኢትዮጵያ ውስጥም ለማንሳት የሚያስችል የህዝብ ብሶት አለ ይባላል እርስዎ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አልዎት…›› ነበር ያለቻቸው፡፡ በነገራችን ላይ ይቺ ጋዜጠኛ እዚሁ ሀገር እዚችው አዲስ አበባ በሚታተም አንድ ጋዜጣ ላይ የምትሰራ ስትሆን አለቆቿ ‹‹በአሁኑ ጊዜ ለህዝብ እና ለሀገር መሞት ኋላቀርነት ነው›› በሚለው ሰሞነኛ ንግግራቸው ታላቅ አድናቆትን የተጎናፀፉ ናቸው፡፡ አድናቆት የሚለውን በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ አድርጋችሁ ከትምህርተ ጥቅሱ ውስጥ ደግሞ ትምህርተ ስላቅም ጨምሩልኝ፡፡ የሆነ ሆኖ ልጂቱ ለጠየቀችው ጥያቄ ሌላው ቅጣት ቢቀር በግምገማ ቁም ስቅሏን ሳታይ እንደማትቀር ይጠረጠራል፡፡ አንድ ወዳጄ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ‹‹ገና አስር ወር እንኳ ሳይሞላን…›› ያሉትን ደግሞ እያለልን ‹‹እንዴት ነው ነገሩ እኛ ሃያ አመት ሞላቸው ብለን ግንቦት ላይ በታላቅ ድምቀት ልደታቸውን ልናከብር ደፋ ቀና እያልን እነርሱ ገና አስር ወር እንኳ አልሞላንም ይላሉ እንዴ…? ወይስ እኒህኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ሌላ ናቸው?›› ሲል ጠይቆን ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው እኛ አብዝተን ስንጨነቅ የነበረው

የጠቅላይ ሚኒስትራችን ደሞዝ እንደ አርቲስቶቻችን ሁሉ ‹‹የሕዝብ ፍቅር›› ብቻ ነው ማለት ነው?

የጠቅላይ ሚኒስትራችን ደሞዝ ስለማነሱ እንጂ እድሜያችን ስለማነሱ አልነበረምና ምላሽ ሳንሰጥ ዝም አልነው፡፡የምር ግን የጠቅላይ ሚኒስትራችን ደሞዝ ማነስ አላሳሰባችሁም? በአዲስ አበባ ኑሮ ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር ምኗን ከምን ያደርጓታል? በእውነቱ ከሆነ ያስጨንቃል፡፡ በዚህ ኑሮ ይቺ ደሞዝ… እንኳንስ ከወር ወር ይቅርና ከሳምንት ሳምንትስ ታደርሳቸዋለች

እንዴ…? እዚችጋ አፈር ስሆን የማትታለፍ ሆናብኝ ነው ከዚህ በፊት የሰሟትን አንድ ቀልድ ልድገምልዎ… ልጁ በትምህርት ቤታቸው የአስማት ትርኢት የሚያሳይ ሰው ስለመጣ ለመግቢያ የሚሆን ገንዘብ ከአባቱ ይጠይቃል፡፡ አባትየው ይህንን ሲሰሙ በየሰባበ ሰበቡ ገንዘብ አምጡ የሚባለው ነገር በንዴት ብግን አድርጓቸው ‹‹የለኝም›› አሉት፡፡ ልጁ ቢነጫነጭባቸው ጊዜ ‹‹እኔ አባትህ በዝች የወር ደሞዝ ይሄን ሁሉ ቤተሰብ አስተዳድራለሁ፡፡ ለመሆኑ ይሄ የምትለው አስማተኛ ከዚህ የበለጠ አስማት ይችላል?›› ብለው ጠየቁት፡፡ ድፍረት አይሁንብኝና ጠቅላይ ሚኒስትራችን ይህ አይነቱ የአስማት ችሎታ ከሌላቸው በስተቀር በዚች ደሞዝ ልጆቻቸውን አስተምረው አብልተው እና አልብሰው እንዴት ይሆንላቸዋል? ለዛውም ደግሞ የርሳቸው ልጆች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ዋጋ… ተመንም ስላልወጣበት የትየለሌ ነው!ብቻ በእውኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን በዚች ደሞዝ እሺ ብለው በመስራታቸው ትህትናቸውን እያደነቅን ደሞዝ መዳቢውን ባለስልጣን ስንወቅስ ሰነበትን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከዚህ ከደሞዝ ጋር በተያያዘ የሰጡትን ምላሽ ልብ ያለ አንድ ወዳጃችን ምን አለን መሰልዎ… ‹‹አይይይይይ… ሲል እጅግ አድርጎ ካዘነ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንደ አርቲስቶቻችን ደሞዜ የህዝብ ፍቅር ነው፡፡ ቢሉን ይሻላል እንጂ ይሄ ደሞዝ የሀገራችንን መልካም ገፅታ የሚያጎድፍ ይመስለኛል›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቶናል፡፡ እውነትም ግን በርሳቸው ደረጃ ይቺን ብር ደሞዝ ብሎ ከመናገር ‹‹ደሞዜ የህዝብ ፍቅር ነው!›› ማለት በስንት ጣዕሙ፡፡ ልክ ይሄንን ፅሁፍ እየፃፍኩ ሳለ አርቲስት አሸናፊ ከበደ በመታተመሙ የተነሳ ለገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን ኮንሰርት ጓደኞቹ ሊያዘጋጁለት መሆኑን የሚገልፅ ፖስተር አየሁ፡፡ ተመልከቱ አርቲስቶቻችንስ ወዳጆቻቸው ይዘፍኑላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን አይበልባቸውና አንድ ነገር ቢሆኑ ምን ሊባል ነው የሚመለከተው ክፍል ድጋሚ ቢመለከተው ደስታዬ ወደር የለውም፡፡ ወዳጄ ሰላምም አላልኮት እኮ… እንዴት ሰነበቱልኝ ሁዳዴ ፆሙ እንዴት ይዝዎታል…? እስቲ እግረ መንገድዎን ፀሎት ቢጤ ያድርጉልኝ፡፡ ሰሞኑን አንድ ወዳጄ በአንድ ግብዣ ፕሮግራም ላይ ለመገኘት እድሉን አግኝቶ ነበር፡፡ ያው ዘንድሮ የመግዛት አቅማችን ኮሳሳ በመሆኑ የግብዣ ዕድል የሚገጥማቸው የተባረኩ ናቸው፡፡ እናም ይህ የተባረከ ወዳጄ በግብዣው ላይ የፆም የፍስግ ተብሎ ከተለየው

ቦታ የፍስክ የሚለውን መርጦ ለማንሳት ሄደልዎ፡፡ ታድያ ይሄ ወዳጃችን ምንም እንኳ የተባረከ ቢሆንም አቋሙን ሲመለከቱት ግን ክስት ብሎ የወላድን አንጀት የሚያንሰፈስፍ ምስኪን ነበር፡፡ ታድያ ተቺ አይጠፋምና አንዱ ምን ብሎ ተቸው መሰልዎ አቋምህ የፆም የምትበላው የፍስክ… እንዴት ነው ነገሩ?›› አለው፡፡ ለነገሩ ዘንድሮ ቢበሉ ቢጠጡም ስጋቱ ራሱ ከሰውነት ጎዳና ያወጣል፡፡ የነዳጅ ዋጋ

ክለሳው እንኳ ራሱ በየወሩ ምን ያህል ኪሎ እንደሚያስቀንስ የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ነዳጅ ካልኩኝ አይቀር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከተጠየቁት ጥያቄ ውስጥ አንዱ ስለ ነዳጅ የተጠየቁት ይገኝበታል፡፡ እርሳቸውም ‹‹የነዳጅ ዋጋ ድጎማ አይደረግም፡፡ ነዳጅ ላይ ድጎማ ማድረግ ሀብታሞችን መደጎም ማለት ነው፡፡›› ሲሉ መልሰዋል፡፡ ሲያብራሩም ደሀው በእግሩ ስለሚሄድ የትራንስፖርት እና የነዳጅ ዋጋ አያሳስበውም እኛ ደግሞ የሚያሳስበን የደሀው ችግር እንጂ የሀብታሞች ችግር አይደለም፡፡ አይነት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይህንን የሰማ አንድ ከትራንስፖርት ዋጋው ጭማሪ በኋላ በእግሩ ጉዞ የሚያደርግ ወዳጃችን ‹‹እኒህ ሰውዬ ደሀው በእግሩ ጉዞ የሚያደርገው ተፈጥሮው መሰላቸው እንዴ…? የአቅም ችግር እኮ ነው የሚያስኳትነን!!›› ሲል አምርሮ ምላሻቸውን ተቃወመው፡፡ እኛ ግን እሳቸው ያሉትን እየደገምን እውነታቸውን ነው የሚያሳስበን የምግብ ዋጋ ነው እንጂ ነዳጅ የሀብታም ነው፡፡ አልን እርሱም ‹‹የዚህ የዚህማ ከነጭርሹ ምን አሳሰባችሁ ደሀው ፆም ውሎ ስለሚያድር ሀብታም ለሚበላው ምግብስ ለምን ትጨነቃላችሁ…?›› ሲል ቅጥ አልባ በሆነ መልኩ አማረረ፡፡ እኛ ወዳጆቻቸው ግን ይህንን ምላሻቸውን ቀድተን ለስልካችን ጥሪ ‹‹ringing ton›› አድርገነዋል፡፡ በመጨረሻም

ቮሊቦል ግብፅ እና ኢትዮጵያእዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ‹‹የዞን አምስት ሀገራት ቮሊቦል ሻምፒዮና›› በሚል የሴቶች ቮሊቦል ጨዋታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ታድያልዎ ባለፈው የግብፅ ብሄራዊ ቡድን በኬኒያ ክፉኛ ተሸንፎ ነበር፡፡ ታድያ የግብፅ ቡድን ለሽንፈቱ አሳማኝ የሚባል ምክንያት አቅርቧል፡፡ ‹‹በግብፅ ተቀስቅሶ የነበረው ህዝባዊ ጥያቄ ስፖርቱ ላይም ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡›› ብለው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከዛ ቀጥሎ ከኢትዮጵያ ጋር ተጫውተው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቡድን በአደገኛ ሁኔታ አሸነፉ፡፡ ማ… ግብፆች! ከዚህ ጋር ተያይዞ ግብፅ ባለፈው የተሸነፈችው በሀገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ ቁጣ ባሳደረው ተፅዕኖ ነበር መባለሁን ያስታወሰ አንድ ወዳጄ የግብጽን ተጫዋቾች ኢትዮጵያስ አሁን ለምን የተሸነፈች ይመስላችኋል? ሲል ጠይቋቸው ነበር፡፡ ለካስ ግብፆችን በሽሙጥ የሚደርስባቸው የለምና! ምን ብለው እንደመለሱለት ያውቃሉ? ‹‹በልባቹ ያለውን ሀሳብ መርምሩ!›› አላሉት መሰልዎ፡፡ ወዳጄ ለዛሬ በዚሁ ይበቃናል፡፡ እንሰነባበት፡፡ አማን ያሰንብተን!

‹‹እኒህ ሰውዬ ደሀው በእግሩ ጉዞ የሚያደርገው ተፈጥሮው መሰላቸው

እንዴ…? የአቅም ችግር እኮ ነው የሚያስኳትነን!!›› ሲል አምርሮ

ምላሻቸውን ተቃወመው፡፡ እኛ ግን እሳቸው ያሉትን እየደገምን እውነታቸውን

ነው የሚያሳስበን የምግብ ዋጋ ነው እንጂ ነዳጅ የሀብታም ነው፡፡ አልን

Page 9: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 9

በየመን ያለ ሀበሻ ቁጥሩ ሲጠራ የሚያምን የለም:: ትክክል የማይመስል ነገር ነው:: በሕጋዊና ሕጋዊ ባልሆነ ሁኔታ የመን ውስጥ ያለ ኢትዮጵያዊ ከ80,000 በላይ ነው:: 5,000 የምንጠጋው በUNHCR ስር ያለን ስንሆን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለማቋረጥ እና የመን ለመኖር ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ ተነስተው በባህር በየእለቱ የሚገቡትን መገመት ይከብዳል:: ከ4,000,000 በላይ ትውልደ ሀበሻ አለ:: ከአረብኛው ቀጥሎ ሕዝቡ በሰፊው የሚናገረው አማርኛ ቋንቋ ነው ማለት ይቻላል:: ይህ የሚያሳየው የመናዊያን እና ኢትዮጵያዊያን አብረው የኖሩ ሕዝቦች መሆናቸውን ነው:: ነገር ተገልብጦ ሆኗል:: ትላንት ችግራቸውን ለመቅረፍ ወደ ሀገራችን እንዳልተሰደዱ ለሀበሻ ያላቸው ጥላቻ ኢትዮጵያን እጀ ሰባራ ያሰኛታል:: ለነገሩ እንኳን የተጠለለባት ከአብራኳ የወጣውስ ነካሽ እንጂ አይዞሽ ባይ መች ሆናት?... ቢሆን ኖሮ ከነቀዞች ማላቀቂያው ሰዓት አሁን ነበር::

የመን ስላለ ሀበሻ ይህን ያህል ካልኩ ወደ ተነሳሁበት የስጋት መስመር ላቆልቁል:: በአረቡ ዓለም እየተቀጣጠለ ያለው የለውጥ ማዕበል ማነው ባለተራ እያለ የሚያዳርስ ይመስላል:: ወጉ አይቅርብኝ ብለው ነካ ነካ የሚያደርጉ ሀገራትም አልጠፉም:: እኛ በስደት ከእጅ አይሻል ዶማ ኑሮ የምንኖርባት የመን አንዷ የእንቅስቃሴው ማዕበል የሚያናውጣት ነች:: የመፋጠጡን ነገር ተዉኝ:: ተፋጠዋል... እኛም ሊመጣ የሚችለውን ችግር አስበን ስጋት አርግዘን... አጋት ለብሰን...በስጋት አንሾካሹከን ነው ያለነው:: ለ32 ዓመታት ሀገሪቷን ሲመሩ የነበሩት አሊ አብደላ ሳላህን ከሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ወገኖች ብቅ ካሱ ሳምንታትን እያስቆጠሩ ነው:: በዛው መጠን ደጋፊዎቻቸውም “ማፊሽ አህሰን አሊ አብደላ ሳላህ!!” የሚል የዘውትር መፈክራቸውን እያሰሙ ፎቶ ይዘው አደባባይ ይውላሉ::” ‹‹እንደ አሊ አብደላ ሳላህ ጥሩ የለም›› ማለት ነው:: ይህ በሰነዓ ነው:: በትእዝና በአደን ደግሞ ከዚህ የተለየ አመጹ የከፋና ሰልፍ የሚወጡትም ቁጥር የበዛ ነው:: በተለያየ ቦታ ውጥረት ውስጥ ያለችው የመን የእርስ በእርስ ጦርነቱ ረገብ በማለቱ ሕዝቡ ተደስቶ ነበር:: አሁን ከቱኒዝ የተነሳው የአመጽ ማዕበል ግብጽን፣ የመንን፣ ጆርዳንን፣ ሊቢያን፣ ባህሬንን፣ ሳዑዲ፣ ኦማንን

መነካካቱ የሚታወቅ ነው:: የመን በዩንቨርስቲ ተማሪዎች

የተጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ በቶሎ እንዲበርድ ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳላህ አስበው በዩንቨርስቲ ውስጥ የሚከፈለውን ክፍያ ከመቀነስ ጀምሮ በነጻ እስከማድረግ ያለ እርምጃ ወስደዋል:: የሀገሪቷ ፕሬዝዳንት የሥልጣን ዘመን ማብቂያ 2013 ነው:: ፕሬዝዳንት አሊ አብደላህ ሳላህ ከ30 ዓመት በላይ አስተዳድረዋል:: ሀገሪቷን አሳድገዋታል የሚሉ ሞልተዋል:: ምን ያሳድጋታል ኑሮው ከፋ የሚሉት ሕዝቡ ሁኔታው እና ያለው ችግር ፈንቅሎት ነው ተቃውሞ የወጣው የሚሉ ናቸው:: መንግስት ሰሞኑን በተቃዋሚዎቸ የተደረገውን የሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ በማየት 10% የደሞዝ ጭማሪ ለወታደሩ ክፍል፣ 4% ደግሞ ለመንግስት ሠራተኞች ጭማሪ ቢያደርግም ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር ተነጻጻሪ አይደለም የሚሉ ወገኖች አሉ:: ሁኔታው ለፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳላህ አሳሳቢ ስለሆነ እንደሆነ የደሞዝ ማሻሻያ ያደረጉት ተቃዋሚዎችም ሆን የመገናኛ ብዙሃን ይጠቅሳሉ::

ፕሬዝዳንቱን ለ2011 ማብቂያ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ የጠየቁት ተቃዋሚዎች ሰነዓ ውስጥ ዳይሪ የሚባል ዩንቨርስቲው ያለበት አካባቢ ድንኳን ጥለው ሲቀመጡ የፕሬዝዳንቱ ደጋፊዎችም ያንኑ አድርገው ፊት ለፊት ተፋጠዋል:: አሁን አሁን የድንኳኑም መጠን እየጨመረ ነው:: ታህሪር የሚባለው ቦታም እንዲሁ የፕሬዝዳንቱ ደጋፊዎች ድንኳን ጥለው ተቀምጠዋል:: ባለፈው ሳምንት ውስጥ ማታ ላይ ስለሁኔታው ለማወቅ ሄጄ ሳለ ድንኳን የጣሉበት ቦታ መጠን ጨምሮ አካባቢው በሰው ተጨናንቆ መንገድ ተዘግቶ አየሁ:: የሚገርመው ደግሞ ዝግጅታቸው ተጠናክሮ ድንኳኖቹ ውስጥ ለምሽግ ይሁን ብርድ ለመከላከል ባላወኩት ሁኔታ በብሎኬት ግንብ ይገነባል:: ያለው የጥበቃ ሁኔታም እየተጠናከረ ፍተሻው እየከበደ ነው:: ያሳስባል፤ አስጊ ነገር አርግዧል:: ደጋፊዎቹ ምግብም ሆነ የቀን ወጭ ተችለው እንደሆነ የተቀመጡት ተቃዋሚዎች ይናገራሉ:: ይህ ሕዝቡ ሁሉ የሚያውቀው ነገር ነው::

በየመን ካለው የውጭ ዜጋ ከብዛት አንጻር ተጎጂ የሚሆነው ሀበሻ እንደሆነ ይታወቃል:: ኤምባሲውም ባለፈው አርብ ሕዝቡን ሰብስቦ “በጊዜ ወደቤት ግቡ”ብሏል::

“ሰውየው ንግግር አደርጉ” ያሉት ትናንሽ ጥቅማ ጥቅም ናፋቂዎች ወደ ኤምባሲ እየቃረሙ የሚወስዱትን ወሬ ጥለው የኤምባሲውን ለእኛ ሲያቀብሉ “በጊዜ ወደቤት ግቡ፣ ሞባይላችሁን ካርድ ሞልታችሁ አስቀምጡ፣ አደጋ ወይም ችግር ሲገጥማችሁ ወዲያው ደውሉ፣ ኮሚኒቲ ተመዝገቡ፣ ችግር ቢነሳ እንኳን ኢትዮጵያዊነታችሁን ታውቆ ወደ ሀገር እንድትገቡ” አሉ አዲሱ ቆንጽላ ሲሉ አበሰሩን:: ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ ይላሉ አባቶች:: በሞባይል ተጠርተው ሊደርሱ አይደለም ግፍ የሚፈጸምባቸው ዜጎቸ ኤምባሲ ሄደው አቤት!!!..ሲሉ እኛ ለገረድ አልመጣንም ማለታቸው ያቆሰለው ሁሉ ኧረ!!...ዛሬ ምን ታያቸው? ገንዘብ ፈልገው? ሲል ተደምጧል:: ኮሚኒቲ ለመመዝገብ ፓስፖርት ወይም መታወቂያ የሚያስፈልግ ሲሆን ያ ካለ ኮሚኒቲ መመዝገቡ ለምን አስፈለገ? ኢትዮጵያዊነትን አይገልጽም?

አንደኛ፣ አልቀርብ ያለውን ሕዝብ ወደ ኤምባሲውና ኮሚኒቲው ማቅርቢያ መንገድ ነው ፍላጎታቸው:: ምንም እንደማይጠቅማቸው ያወቁትን ኤምባሲ ቅንጣት እምነት አይጥሉበትም:: የተበደሉ ወገኖች እንኳን ሲገጥሙ ‹ኩሩቤል ጋር ሄዱ› ነው የሚባሉት:: ማንም ኤምባሲ ሂድ አይልም:: ኩሩቤል ማነው? ትሉ ይሆናል ዛሬ ርዕሴ ስላልሆነ በቀጣይ ከUNHCR ጋር በተያያዘ እመለስበታለሁ::

ሁለተኛ፣ 3000 ሺህ የነበረውን ቀንሰን በ2000 የየመን ሪያል እያሉ እያስከፈሉ ስለሆነ የሚመዘግቡት ለጥቅም ሲሉ ነው እያለ ስደተኛው ሲያማርር ተሰምቷል:: መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል ነው:: እዚህ ያሉ እህቶች ያሳዝኑኛል:: በጉለበታቸው ፋገው ያመጡትን ዝቅተኛ ክፍያ ሊበላቸው ያሰፈሰፈው ብዛቱ... ደላላው፣ መኖሪያ ፍቃድ አሰሪው፣ የትዳር ጭንብል ያጠለቅው ወንድ፣ ኤምባሲው... ብቻ ሁሉ የያዙትን ሊያራግፋቸው ነው የሚጥረው:: በእርግጥም አራግፈው መታከሚያ፣ ሀገር መግቢያ የሚያጡ ሞልተዋል::

ማንም በኤምባሲው እምነት አላሳደረም:: ምክንያቱም ከዚህ በፊት ኤምባሲው ለዜጋው ምንም ሲያደርግ አይታወቅም:: ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች ያሉት ኤምባሲ የቀብር ቦታ ጠይቆ ያላዘጋጀ፣ ዜጋው ሲሞት ለመቅበር ቦታ ጠፍቶ

በየፍሪጅ ውስጥ ሬሳ ሲበሰብስ ዝም የሚል ኤምባሲ፤ ተበደልን ሲባል የራሳችሁ ጉዳይ የሚል ኤምባሲ፤ ዜጎቹ የመኖሪያ ፍቃድ ማሰሪያ ቦታ አጥተው ጀበሀ የሚባል የኤርትራ ተቃዋሚ ቡደን የየመንን መንግስት አስፈቅዶ ማሰራት ሲጀምር፣ ብሎም ከ5000 በላይ ኢትዮጵያዊያን ከ100-300 ዶላር ተበልተው ሲቀሩ ምን አገባን ያለ ኤምባሲ ሞባይላችሁን ካርድ ሙሉ የሚለው ቢጠራ ሊመጣ ነው? ሁሉን ያነጋገረ ጉዳይ ነበር:: የቀብር ቦታ እንኳን ከቻይኖች ጋር ጥገኛ ሆነን ነበር:: እነሱም ከልክለው የተቀበረውንም የሀበሻ ሬሳ አውጥተው ሲጥሉ ዝም ያለ ኤምባሲ ቢደወልለት ይደርሳል? እዚህ ያለ ሀበሻ በሙሉ የሚያውቀው ነገር አለ ሲሞት የሙስሊም ስም እየተቀየረለት ነው የሚቀበረው:: ይህን ኤምባሲውም ያውቃል::

ውጥረቱ ያየለበት ምስኪን ስደተኛ ወደ UNHCR ቢሮ ብቅ ቢልም ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ አግኝቶ ተስፋው ጨልሞበት ስጋት ብቻ ሳይሆን ፍርሀቱም አይሎበት እንዳለ አለ:: ‹‹ምንም ልናረግላችሁ አንችልም:: ባለው ሁኔታ ሁለት ቦታ ቢሯችንን ዘግተናል:: የከፋ ነገር ቢመጣ እዚህ ያለውን ቢሮም ዘግተን እንሄዳለን:: ባጀት ስለሌለን ዘግተን ከመሄድ ውጭ ምንም ልናረግላችሁ አንችልም::›› ለሚመለከተው ሁሉ አቤት ቢባል ምላሽ የለም::

እዚህ ያለ ሀበሻ የየመን ፖለቲካ አይደለም ችግሩ:: ሀገርስ ቢገባ የሚጠብቀው ምንድን ነው? ብዙውም አሁን ያሉት ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳላህ እንዲቀጥሉ ነው ፈጣሪውን የሚለምነው:: ምክንያቱም ሕዝቡ ለሀበሻ ያለው አመለካከት ጥሩ ስላልሆነ ችግር ቢነሳ ይጨርሱናል የሚል ፍርሀት አለው:: በእርግጥም ሀቅ ነው:: ሼህ የሚባሉ የጎሳ መሪዎች አሉ እያንዳንዳቸው የታጠቀ ሠራዊት አላቸው:: ለሀበሻ ፍርሀቱ ብዙ ነው:: የምናሳዝን ፍጥረት... ኤምባሲው በስሩ ላሉ አልሆነላቸው፤ UNHCRም ቢሆን የፈለጋችሁትን ሁኑ ነው ያለው፡፡ መጨረሻችን ምን ይሆን?

ሀገር አንገባ እኛስ ጫንቃችን ላይ የተጎበረ ነቀርሳ አለ አይደል? እስከመቼ በመንከራተት እና በስደት እንኑር? እስኪ ሰላም ያሰንብተንና እንገናኝ፡፡

ቸር ሰንብቱ

በግሩም ተ/ሃይማኖት (ከየመን)

በየመን ስጋት አርግዘን ስጋት ለብሰናልኮሜንተሪ

መምህራን እና ቴክኖክራቶች ከእርሳቸው ጋር አብረው እንዲሰሩና የሚፈልጓቸውን ለውጦች ለማምጣት እንዲቀላቀሏቸው ጥያቄያቸውን አቀረቡላቸው፡፡ ጥያቄያቸውንም የበለጠ ጋባዥ ወይም አጓጊ ለማድረግ፣ ለአስተዳደራዊ ኃላፊነቶች ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪን ማዕከል ባደረገ መልኩ የገንዘብ ማበረታቻዎች በተጨማሪ ቀረቡ፡፡ በምርጫው ወቅት የኦሮሞ ድምጽ ተደፍቆ የነበረ የመሆኑ እውነታ ሲታይና ኦነግ ወደሀገር ቤት የመምጣቱ ተስፋ መሟሸሹ፣ የአባዱላን አዋጭ ጥያቄ ላለመቀበል የሚቀርብ ያን ያህል ጠንካራ ምክንያት አልነበረም፡፡ በሺህዎች የተቆጠሩ የቅርብ ጊዜ ምሩቃን፣ መምህራንና ቴክኖክራቶች ቢሮክሲውን ተቀላቀሉ፡፡ በድህረ-ምርጫ ቀውስ ወቅት አቶ መለስ ተወጥረው የነበረ በመሆኑ፣ አባዱላ ወደተለያዩ ክልላዊ ቢሮዎች እነዚህን ምልምሎች በኃላፊነት ለመመደብ አንፃራዊ ሥልጣን አግኝተው ነበር፡፡

ድንገተኛውና ኃይለኛው እርምጃ በርካታ ለውጦችን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያመጣ ነበር፡፡ የተሻለ የተማሩ እና የሰለጠኑ ቴክኖክራቶች የአስተዳደራዊ ጉዳዮችን በበላይነት መምራት በመጀመራቸው፣ የአገልግሎት አቅርቦቶት በከፍተኛ ደረጃ ተሻሻለ፡፡ አዲስ መጤዎች በፊት ለበለጠ ነፃነት የሚሟገቱ ነበሩና በገበሬው ላይ የሚሰነዘረው ቀጥተኛ አፈና እንዲሁ እንዲላላ ሆነ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ አዲሱ ፕሬዝዳንት ከመራጮች ጋር በመቀላቀል፣ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ክብረ-በዓላት ላይ በመሳተፍ፣ ቅሬታዎቻቸውን በማዳመጥ እና አንዳንዴም ለጥያቄዎቻቸው ፈጣን ምላሽ በመስጠት የነቃ ተሳትፎን ያማከለ አስተዳደራዊ አካሄድን ነበር ተግባራዊ ያደረጉት፡፡ ለውስጣዊ የፓርቲ ውጥረች በአባታዊ አቀራረብ በአንጃዎች መካከል የአስታራቂነት ሚናን በመጫወትና ለየትኛውም ወገን ሳያዳሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመቅረፍ ተሳክቶላቸውም ነበር፡፡ ይህም፣ ክልላዊ ችግሮችን ለበላይ አለቆቻቸው ከማስተላለፍ ይልቅ እዛው በክልል ቢሮዎች መፍትሔ ተሰጥቷቸው እንዲወስኑ ለማድረግ ያስቻላቸው ነበር፡፡ እናም፣ በሆነ ወቅት እጅግ ይጠሉ የነበሩት ሰው ያሳኳቸውን ለውጦች ሕዝቡ በመመልከት ዳግም ቀና ብሎ ይመለከታቸው ጀመር፡፡

የአምስት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸውን ግማሽ ያህሉን ከተጓዙ በኋላም የአባዱላ ታዋቂነት እጅግ ናኘ፤ ይህንንም እንደ አዲስ ስጋት ከተመለከቱት አቶ መለስ ጋር እንዲላተሙ አደረጋቸው፡፡ መጀመሪያውኑ የኦሕዴድ በራስ መተማመንና ጥንካሬ እየጎላ ነበርና የአባዱላ ተፅዕኖና ሥልጣን ይሸበብ ዘንድ ግድ ሆነ፡፡ ገፅታቸውንም ለማጠልሸት በርካታ ታክቲኮች ተግባራዊ ተደረጉ፡፡ አባዱላ ከገነቡት ቤት ጋር የተያያዘ አንድ ‹‹የተረሳ›› የሙስና ውንጀላ ለሁለተኛ ጊዜ ነፍስ ዘራ (ጉዳዩ በመጀመርያ የታወቀውና በአባዱላ ላይ የተሰነዘረው በ2004 ውስጥ ነበር)፡፡

የአቶ መለሰ ምልምሎች ፣ የስም ማጥፋት

ዘመቻውን በፊት አውራሪነት በመሩ አንዳንድ ‹‹ገለልተኛ›› ጋዜጦች በመታጀብ፣ አባዱላን በፓርቲው ኮንፍረንስ ላይ እንዲያንጓጥጧቸው ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡

የኦሕዴድ ተራ አባላት አባዱላን ለመከላከል ሲንቀሳቀሱና በእርሳቸው ላይ የተነሱባቸን ባገለሏቸው ወቅት፣ የአቶ መለስ ስትራቴጂ እሳት ነበልባል መልሶ ራሳቸውን መፋጀት ጀመረ፡፡ ይህም አባዱላን ከፓርቲ ሊቀመንበርነት እና ከክልላዊ ፕሬዝዳንትነታቸው ለማስወገድ የተላለፈውን የአቶ መለስን ትዕዛዝ የኦሕዴድ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በግልፅ በተቃወመበት ወቅት የታየ ነበር፡፡

በተዘዋዋሪ መንገድ ውስጣዊ መፈንቅለ-ሥልጣን ለማካሄድ ተቀነባብሮ የተካሄደው ሙከራ ሲከሽፍ (ታክቲኩ በክልሉ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ላይ ውጤታማ በሆነ መልኩ የተተገበረ ነበር)፣ አባዱላ ከዋናዎቹ አዛዣች ቀጥተኛ ግፊት ተደረገባቸው፤ እናም ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዱ፡፡ የአባዱላን መነሳት ተከትሎ እና የእነዚያን ስህተቶች ዳግም መከሰት ለማስቀረት፣ ክልላዊው መንግስት ከእንደገና እንዲዋቀር ተደረገ፡፡ በክልላዊ መንግስት የሥልጣን ጨዋታ ይህን ያህል ግንኙነት የሌላቸው መጤ አዲሱ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡ ፉክክርን ለመፍጠርና በፕሬዝዳንቱ እጅ የሥልጣን መከማቸትን ለመከላከል አራት አዳዲስ የምክትል ፕሬዝዳንትነት ወንበሮች ተፈጠሩ፡፡

ያም ሆኖ ግን የአባዱላን ምዕራፍ ለመዝጋት ሙሉ በሙሉ በጣም ቀላል አልነረም፡፡ ማሻሻያዎችን ለማደናቀፍ ሙከራ በማድረግ አቶ መለስን በመውቀስ፣ ሕዝቡ በአባዱላ መወገድ ላይ የተሰማውን ቅዋሜና ቁጣ መግለፁን ገፋበት፡፡ በርካታ የዳግም ማጥመቅ ሴሚናሮች ቢካሄዱም፣ ቢሮክራሲው ከአዲሶቹ ተሿሚዎችና አንዳንዴም ከአንዳንድ የፌዴራል ባለሥልጣናት የሚተላለፉለትን ትዕዛዞች ቸል በማለት ወይም ከቁብ ባለመቁጠር ቁጣውን መግለፁን ቀጠለበት፡፡ አዲሱ ፕሬዝዳንት ራሳቸው በሁኔታው ተስማምተው ነበር ነው የሚባለው፡፡ ኦሕዴድ ዳር ተመልካች የተደረገበት የፌዴራል ካቢኔ ብወዛ ሌላው ተጨማሪ ቅሬታ ጫሪ ጉዳይ ነበር፡፡

በአቶ መለስ የማባበል ስትራቴጂ ያልታሰቡ ውጤቶች ምክንያት የሕወሓት እና የኦሕዴድ ‹‹የደንበኝነት›› ግንኙነት ሻክሯል፡፡ አባዱላ ቀጥተኛውን የታማኝነት ፍሰት በማስተጓጎል የራሳቸውን አግድሞሻዊ ቡድን ገንብተው ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ በሩን ለተማረው ሕብረተሰብ በመክፈት ኦሕዴድ አስቀድሞ ከታለመለት - ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን አቋርጠው የወጡ ሰዎች ስብስብ ማድረግ - በላይ በተፃራሪው ኦሕዴድን የቴክኖክራቶች ስብስብና ብቃት ያለው የኃይል መቀመጫ አድርገው ለመለወጥ ተሳክቶላቸው ነበር፡፡ ለዚህ ዋነኛው አስረጂ የኦህዴድ አዲስ የፓርላማ አባላት የትምህርት ደረጃ

እጅግ የተሻለ መሆኑ ነው፡፡ በግርድፉ ከአስሩ ውስጥ ስምንቱ የመጀመርያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ አላቸው፡፡ በዚህ ላይ ዲግሪ ያላቸው የምርቋን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እድገት አሳይቷል፡፡

ይህ ሁኔታ በራሱ አስቀድሞም ለአቶ መለስ ጠንካራ ስጋት መጋረጡ እንዳለ ቢሆንም፣ በቅርቡ ሰሜን አፍሪካን ያጥለቀለቁ አብዮቶች ማዕበል ስጋቱን ይበልጥ ያባባሰው ነው፡፡ ስለዚህም፣ ‹‹ፓትሮኑ›› ጥቃት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፤ እናም የወቅቱ የማፅዳት እርምጃ አግድሞሻዊውን ቡድን ለመበታተን የተደረገ እርምጃ ነው፡፡ የወቅቱ እርምጃ፣ እንደው አለው ቢባል እንኳ፣ እጅግ ኢምንት ግንኙነት ነው ከሙስና እና ከብቃት ግንባታ ጋር የሚያያዘው፡፡ በመልዕክተኞች አማካኝነት የተደረጉት ትዕዛዞች ውድቅ ከተደረጉ በኋላ አቶ መለስ ራሳቸው የኦሕዴድን ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ በመሰብሰብ ችግር ፈጣሪዎችን ካላስወገዱ በስተቀር አስከፊ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ነበር የዛቱባቸው፡፡ እናም፣ የስም ዝርዝር ተፅፎ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡

በተከተዩም የሳምንት መጨረሻ፣ ከ120 የሚበልጡ አባላት ግምገማ በተባለው መንገድ ተነቅሰው ወጥተዋል፡፡ የአባዱላ መገኘት አመራሩን ያዋህደዋል በሚል ስጋት ሆን ተብሎ ወደውጭ ሀገር ተልከው ስብሰባው እንዲያመልጣቸው ነበር የተደረገው፡፡ በስብሰባውም አለመገኘታቸው እንዲሁ የአጋጣሚ ጉዳይ ተብሎ ታልፏል፡፡ ሂደቱንም የአንጃዊ ፍልሚያ ገፅታ ለመስጠት የሕወሓት ‹‹ታዛቢዎች›› እንደኩማ ደመቅሳና አለማየሁ ኦቶምሳ ያሉትን በማሞገስ አባዱላንና ‹‹የእርሳቸውን የቅርብ ወዳጆች›› አበክረው ተችተዋቸው ነበር፡፡ ይህም ታክቲክ ሊሠራ አልቻለም፤ ከዚያ ይልቅ በሌሎች አባላት፣ ለሙሉ ድምፅ ትንሽ የቀረው፣ ተቃውሞ ተሰነዘረበት፡፡ በስብሰባው ላይ ከተስተጋባው ሞቅ ያለ የቃላት ልውውጥ ጋር ተደማምሮ፣ ዒላማ የተደረጉት ግለሰቦች ወደመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ ከተፈቀደ አመፅ ሊያነሳሱ ይችላሉም የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር፡፡ እናም፣ ጨለማ ነው በሚል ሰበብ፣ ከመሰብሰቢያ አዳራሽ በ‹‹ልዩ ኃይሎች› በፍጥነት ከመሰብሰቢያው አዳራሽ እንዲወጡ ተደርገው፣ ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኝ ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግለትና በተገለለ እስር ቤት ውስጥ ተይዘው እንዲቆዩ ሆኗል፡፡ ያም ሆኖ ግን፣ የአባዱላ መረብ ሙሉ በሙሉ እንዲበታተን ቢደረግ እንኳን (ያ ደግሞ አጠራጣሪ ነው) ከኦሕዴድ ዳግም የማያወላዳ ታዛዥነትንና ታማኝነትን መልሶ ለማግኘት እጅግ አስቸጋሪ የሚሆን ጉዳይ ነው፡፡

የአቶ መለስ ተከታዩ የስትራቴጂ አጣብቂኝከላይ እንደተገለፀው፣ ከአምስት ዓመታት

አስቀድሞ፣ አቶ መለስ የኦሮሞ ተማሪዎችን ድጋፍ ለማግኘት የማባበል ስትራቴጂ ተግባራዊ አድርገው ነበር፡፡ ወደ መጀመርያ አካባቢ ለአዳዲሶቹ የኮሌጅ ምሩቃን ቦታ ለማበጀት ሲባል ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ የነበራቸው ቢሮክራቶች ዳር ተመልካች እንዲሆኑ ተደርገው ነበር፡፡ የኮሌጅ ምሩቃን ቁጥር እጅግ ሲጨምር፣ አዲሶቹን ለማቀፍ ሲል ሥርዓቱ አስተዳደራዊ ቢሮክራሲውን

ለማስፋፋት ተገደደ፡፡ በ2010 ምርጫ ላይ ባቀረቡት የጥናት ወረቀታቸው ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንደጠቀሱት፣ ከ2005 እስከ 2010 ‹‹የአካባቢያዊ አስተዳደር ምክር ቤት 600 ሺህ የሚጠጉ አባላት ቁጥር ወደ 3.5 ሚሊዮን እድገት ያሳየ ሲሆን፣ ‹‹የኢሕአዴግ ፓርቲ አባላት ቁጥር ከ760 ሺህ ... ከ5 ሚሊዮን በላይ አድጓል››፡፡ አብዛኛው መስፋፋት የተካሄደው በኦሮሚያ ውስጥ ሲሆን፣ ሁሉም የሚከፈላቸው በመንግስት ነው - ልክ እንደ ደሞዝተኛ ተቀጣሪዎች ወይም በቋሚነት ከግብር ነፃ ክፍያ የሚቀበሉ ናቸው፡፡

በኦሕዴድ ውስጥ ያለው ለውጥ ቀስቃሽ ኃይል ለአቶ መለስ ጠንካራ አጣብቂኝ የሚጋርጥባቸው ነው፡፡

- በማባበል ስትራቴጂ መቀጠል አይቻላቸውም፤ ምክንያቱም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ምልምሎችን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም አይኖራቸውም፡፡ የዛሬ አምስት ዓመት እንደተደረገው አሁን ያሉትን ተቀጣሪዎች በሌሎች መተካት አደጋ አለው፤ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ያሉት ተቀጣሪዎች እንደማናቸውም አዲስ ተቀጣሪዎች የተማሩ ናቸው፡፡ በሥርዓቱ የሚገለሉ ከሆነ ደግሞ ባላቸው የውስጥ ፓርቲ እውቀት ምክንያት አደገኛ ጠላት ሆነው ሊወጡ ይችላሉ፡፡

- ሥርዓቱ የሚፈልገውን አቅም (ገንዘብ) ቢያገኝ እንኳን (ለምሳሌ ለውጪ ዜጎች የሚያደርገውን የመሬት ሽያጭ የበለጠ በማጠናከር)፣ ያ የማባበል ስትራቴጂን ቀጣይ ሊያደርግ የሚችል ይሆናል፤ እና ዘግይቶም ቢሆን ኦሕዴድ በተማሩ ብሔርተኞች መሞላቱና በበላይነት መመራቱ የማይቀር ነው፡፡ ይህ በአንፃሩ ወጣትና የተማረ የህብረተሰቡ ክፍል፣ ከሀገሪቱ ሕዝብ ትልቁ እና እጅግ ሀብታሙ ክፍል እየተጨቆነ ሳለ እንደበታች የመቀጠሉ ነገር አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡

- እንዲሁም ስትራቴጂውን መለወጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣት የኮሌጅ ምሩቃን ወደፓርቲው እንዲገቡ የሚስባቸው ብቸኛው ማበረታቻ ቅጥር በመሆኑ፣ የመሰል ማበረታቻ አለመኖር ምልመላን ብቻ ሳይሆን አስቸጋሪ የሚያደርገው በኦሮሞ ወጣቶች እና በሥርዓቱ መካከል እንደ አዲስ የገነፈል ግጭት እዲከሰት የሚያደርግም ጭምር ነው፡፡ ሥራ አጥ የሆኑትን የኮሌጅ ምሩቃንን በመመልከት የኮሌጅና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ወደፊት ሥራ እናገኛለን በሚል የተስፋ ቃል ተታልለው የፓርቲው አባል ማድረግ የሚቻል አይሆንም፡፡

ያም ሆኖ ግን፣ የደህንነት ተቋማትን ሕወሓት በብቸኝነት መቆጣጠሩን እስከቀጠለ ድረስ፣ ኦሕዴድ በቂ ብርታት እና ድርጅታዊ ጥንካሬ አግኝቶ ራሱን ችሎ የመንግስት ሥልጣን የመያዙ እድል የመነመነ ነው፤ ቢሆንም ግን ያ እውን ሊሆን የማይችል ነው ማለት አይደለም፡፡ጃዋር ሲራጅ መሀመድ፣ የፖሊቲካል ሳይንስ ተመራማሪና ተንታኝ ናቸው

የመለስ ዜናዊ እና የኦሕዴድ...

Page 10: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003እ ን ግ ዳ10

‹‹ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ተሸማቅቀው፣ ክብርና ነፃነት አጥተው እየኖሩ ነው››

አቶ ገብሩ አስራት(የወቅቱ የ’መድረክ’ ሊቀ-መንበር)

በኤርትራ መንግሥት ላይ እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎች ዓላማ ምንድነው ?ጠ/ሚ/ር መለስ ለ‹አሰና› ራዲዮ የሰጡት ቃለ-ምልልስ ምን መዘዝ አለው ?የሰሜን አፍሪካ ሕዝባዊ አብዮቶች ኢትዮጵያን የሚነካት እንዴት ነው ?በእነዚህና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ ባልደረባችን ውብሸት ታዬ የወቅቱ የ’መድረኩ’ ሊቀ-መንበር ከሆኑት አቶ ገብሩ አስራት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ከወራት በፊት በ‹አረና ትግራይ› ፓርቲ ስም አጠቃላይ ጉባዔ መጠራቱን ተከትሎ ያለመግባባት ተከስቶ ነበር፡፡ አሁን ሁኔታው በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?እንግዲህ ባለፈው ግዜ አረና ውስጥ አንድ ቡድን ተነስቶ፣ ‹‹ሕጋዊው አረና እኔ ነኝ፤ ጉባዔም ጠርቼ አከናውኛለሁ›› የሚል መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡ በእርግጥ በወቅቱ እኛም ሁኔታውን ተቃውመን መግለጫ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ተግባር የሰከነ፣ የተወሳሰቡ ነገሮችን የመፍታት ብቃት ያለው መንግስት የሚያደርገው ሳይሆን፣ አሳፋሪና ደካማ አካሄድ ነው፡፡ ለነገሩ ተደረገ በተባለው ሕገ-ወጥ ጉባዔ ላይ ከአንዱ በስተቀር አብዛኞቹ የድርጅቱ አባላት አይደሉም፡፡

በወቅቱ ለምርጫ ቦርድ አላመለከታችሁም? ፖሊስና ሌሎች አካላትስ በእንቅስቃሴው ላይ የነበራቸው ሚና ምን ነበር?አመልክተናል፡፡ የጉባዔ አጠራሩ የድርጅቱን አራት አምስት የመተዳደሪያ ደንቦች የጣሰ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገሪቱን ሕግም ያልተከተለ ነው፡፡ እኛ በአጭሩ ‹‹ውንብድና›› እንደነበረ ገልፀናል፡፡ ለሕግ አካላት ... (በምፀት ሳቅ ካሉ በኋላ) ለሁሉም የአስተዳዳር አካላት፣ ለፖሊስ፣ ለፀጥታ ክፍል አሳውቀናል፡፡ የሆነው ግን እንዲያውም ለሕገ-ወጦቹ የሕግ ከለላ መስጠት ነበር፡፡ ጥበቃ አድርገውላቸዋል፡፡ በጠራራ ፀሐይ የተደረገ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የውንብድና ተግባር ነው፡፡

በምርጫ ቦርድ በኩል ለጉባዔው እውቀና ተሰጥቷል? በሕጉ መሰረት እንደሚደረገው ሁሉ የቦርዱ ተወካይ በጉባዔው ላይ ተገኝተዋል?ቦርዱ ዕውቅና አልሰጣቸውም፡፡ የሚሰጥበት አግባብም፣ መሰረትም የለውም፡፡

አሁን የድርጅቱ ጽ/ቤትና ንብረት በማን ስር ነው? በእኛ ስር ነው፡፡ በእርግጥ ጥቃቱ ወደዚያም ሊቀጥል ይችላል፡፡ አይደረግም የምንልበት ነባራዊ ሁኔታ አይደለም ያለው፡፡

በትግራይ ውስጥ እያካሄዳችሁት ያለው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? በተለይ ከምርጫው በኋላ? እኛ እያካሄድን ያለነው ፖለቲካ የጦርነት ያህል ከሚደርስብን ጫናና እንግልት ጋር በመታገል የሚሰራ ነው፡፡ ጦርነት ነው፡፡ እስካሁን በጽናት ስለተቋቋምነው ነው እንጂ በቀላሉ የሚደናገጥ ፓርቲ ቢሆን ኖሮ ትግራይ ላይ መንቀሳቀስ የሚቻልበት ሁኔታ የለም፡፡ በአባሎቻችን ላይ በርካታ እንግልቶች እየተፈፀሙ ነው፡፡ ለምሳሌ በምርጫው ዋዜማ ቦንብ ተወርውሮበት የነበረ አባላችን (አቶ አያሌው በየነ) በቅርቡ ፊታቸውን በጭምብል በሸፈኑ ሰዎች በኮብራ ታፍኖ ተወስዶ ሌሊቱን ሲደበድቡት ካደሩ በኋላ፣ ጠዋት አምጥተው ጥለውታል፡፡ ሽሬ እንደስላሴ ከተማ ላይ ነው፡፡ ሌሎች የታሰሩ አሉ፡፡ ተክላይ አርዓያ የተባለው አባላችን የቀድሞውን የትግራይ አፈ-ጉባኤ በተንቀሳቃሽ ስልክ የአጭር መልዕክት ሰድበሃል ተብሎ እስካሁን በእስር ላይ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ነገሮች

ሞልተዋል፡፡ አንዳንዶቹ በመንግስት ደረጃ ይፈፅማሉ ተብለው እንኳን አይታሰቡም፡፡ ትዳር እስከማፋታት ሁሉ ተደርሷል፡፡ ‹‹ፀረ ሕዝብ ነው፤ ከእርሱ ጋር ከሆንሽ ... ›› በሚል፡፡

እርስዎ በሊቀ-መንበርነት እየመሩት ወዳለው ‹መድረክ› ስንመለስ፤ ብዙዎች ድርጅቱ በተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳለ ይሰማቸዋል፡፡ አልፎ አልፎ በሚደረጉ ውይይቶች ብቻ ተወስኗል የሚል አስተያየት ይደመጣል፡፡ ምላሽዎ ምንድነው?መድረክ ከምርጫው ማግስት ጀምሮ ዝም ብሎ ቁጭ አላለም፡፡ የተለያዩ መግለጫዎችን ሰጥቷል፡፡ በተጓዳኝ የሕዝብ ሥራዎች ... ብዙም ባይሆን በሁለት ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባና በሐዋሳ አድርጓል፡፡ በዋነኛነት እየሰራ ያለው ግን ድርጅቱን ወደ ግንባር በማሳደግ ዙሪያ ነው፡፡ ይህ መታወቅ አለበት፡፡ በእርግጥ ሕዝባዊ ስብሰባ፣ የሚሰራጩ ፅሁፎች በስፋት ደግሞ መግለጫዎች ባለመሰጠታቸው ድርጅቱ ፀጥ ያለ ሊመስል ይችላል፡፡ የራሱን ሥራ ግን እየሰራ ነው፡፡ በጠንካራ መሰረት ላይ ለመቆም ገንቢ ውይይቶች መደረግ ስላለባቸው ነው ጊዜ ወስደን እየተወያየንባቸው ያለነው፡፡

በቅርቡ በአንዳንድ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት እና በሌሎቹ ስፍራዎች ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በአምባገነን መሪዎች ላይ ተካሂደዋል፡፡ የሚፈለገውን ያሳኩ፣ እስካሁን በትግል ላይ ያሉም አሉ፡፡ የአፍሪካውያን ጉዳይ በተዘዋዋሪም ቢሆን ስለሚነካን በዚህ ጉዳይ ላይ እንደ ድርጅት የተወያያችሁበት አጋጣሚ ነበር?ጉዳዩ መነሳቱ አይቀርም፡፡ እንዳልከው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሀገራችንን ይነካል፡፡ ግን ደግሞ ጥልቀት ባለው መንገድ ውይይት የተደገበት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በሀገራችን ያለው ሁኔታ የበለጠ አሳሳቢ ነው፡፡ የሀገራችን ሁኔታ በእነዚህ ሀገራት ከሚታየው ሁለንተናዊ ችግር የሰፋ ነው እንጂ ያነሰ ወይም የተሻለ እንዳልሆነ እኛ ኢትዮጵያውያን እናውቀዋለን፡፡ ይህንኑ በማሰብም አስቀድመን ለመንግስት ባለአምስት ነጥብ የድርድር ኃሳቦች አቅርበን ነበር፡፡ አንዱ የሕግ የበላይነት ይረጋገጥ የሚል ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ በርካታ ነጥቦችን አንስተናል፡፡ ሌላው የመንግስት ሜዲያዎች ፍትሐዊ አጠቃቀም ይስፈን የሚል ነው፡፡ የውጭ እርዳታና በሁሉም የፋይናንስ አጠቃቀም ላይ የተዛባው አሰራር እንዲቀር የሚልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

መሰረታዊ ፍጆታ በሚባሉ ሸቀጦች ላይ የቁርጥ ዋጋ ተመን መመሪያ ከወጣ በኋላ አብዛኞቹ ሸቀጦች ከገበያ እየጠፉ ነው፡፡ ለውጭ ንግድ በዝቅተኛ ዋጋ እየቀረበ እንዳለ የሚነገረው ስኳር እንኳ ሙሉ ለሙሉ ከገበያ ከመጥፋት አልፎ አንዳንዶች እንደሚሉት ‹‹የኮንትሮባንድ ዕቃ›› እየሆነ ነው፡፡ የቀውሱ መሰረታዊ ችግርና መፍትሄው ምንድነው ይላሉ?አሁን እየሆኑ ያሉትን ነገሮች አስቀድመን ገልፀን ነበር፡፡ መንግስት መዳሰስ የነበረበትን መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር መፈተሽ አለበት እንጂ በቁጥጥር ፖሊሲ ኢኮኖሚን

ወደ ገፅ 15 ዞሯል

Page 11: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 11

የጽሁፌ መነሻ ቅዳሜ የካቲት 12 ቀን 2003 ዓ.ም በወጣው አውራምባ ጋዜጣ ኮሜንታሪ ዓምድ “የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን ፋይዳቢስነት” በሚል ርዕስ፣ በዶ/ር ፈቃዱ

በቀለ የቀረበው ነው፡፡ በጠቀስኩት ጽሁፍ ውስጥ አንባቢን ውዥንብር ውስጥ የሚከቱና እውነት ላይ ያልተመረኮዙ የተምታቱ አስተሳሰቦች በመስፈራቸው ሚዛናዊ የሆነ ግንዛቤን ለመፍጠር ነው ጥቂት ነገር ለማለት ብዕሬን ያነሳሁት፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅትን ምንነት? ኢትዮጵያ እየሔደችበት ስላለው አቅጣጫና ሌሎች ጉዳዮችን ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እንቅስቃሴ የጀመረችው ድርጅቱ ከተቋቋመ ሁለት ዓመታት በኋላ እኤአ በ1997 ዓ.ም የታዛቢነት ቦታ እንዲሰጣት በማመልከት ነው፡፡ በድርጅቱ ሕግ መሠረት ማመልከቻ ያቀረበ ሀገር በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አባል ለመሆን ድርድር መጀመር ይኖርበታል፡፡ ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ በኩል 10 የሚደርሱ የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው የድርጅቱ አባል መሆን የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ሲገመግሙ ቆይተዋል፡፡ ሥራው ሰፊና ውስብስብ እንደመሆኑ መጠን የውስጥ ሥራዎችን ማጠናቀቅ ባለመቻሉ፣ ኢትዮጵያ የታዛቢነት ጊዜዋ እንዲራዘም እ.አ.አ በ2002 ዓ.ም ጥያቄ ቀርቦ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ የታዛቢነት ጊዜው በተራዘመ በዓመቱ ድርድሩን የመጀመርም ጥያቄ ቀርቧል፡፡ ዶ/ር ፈቃዱ እንዳሉት እአአ በ2003 ለአባልነት ማመልከቷ ትክክል ቢሆንም፣ ሂደቱን ካለመገንዘብ የተነሳ “ውይይቱ” (ድርድር እንጂ ውይይት የሚባል ነገር የለም) ከሁለት ዓመታት በፊት እንደተጀመረ ያወሳሉ፡፡ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት እንዳለባቸውና የሚካሄደውም ድርድር ከድርጅቱ ጋር ሳይሆን እሱ “መርጦ” ካስቀመጣቸው ጋር መሆኑንም ይነግሩናል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል ሀገራት አራት ደረጃዎችን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ደረጃ ለዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ጥያቄ ማመልከቻ የማቅረብና የአባልነት ሂደቱን የሚከታተል የስራ ቡድን /working party/ ማቋቋም ነው፡፡ በዚህ ደረጃ የድርጅቱ አባል ለመሆን የፈለገ ሀገር ፍላጎቱን በፅሁፍ ለድርጅቱ ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡ ጥያቄው በአባል ሀገራት በሙሉ ተቀባይነት ሲያገኝ የአባልነት ሂደቱን በቅርበት የሚከታተል የሥራ ቡድን በአጠቃላይ ምክር ቤቱ አማካኝነት ይቋቋማል፡፡ ማንኛውም አባል ሀገር በሥራ ቡድኑ ውስጥ መሳተፍ ይችላል፡፡ ልብ በሉ፤ ድርድሩ የሚካሄደው ድርጅቱ “መርጦ” ባስቀመጣቸው ሳይሆን፣ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ሀገር በሚሳተፍበት ሂደት ነው፡፡ ሁለተኛው፤ መረጃ የማሰባሰብ ደረጃ ሲሆን፣ አመልካች ሀገር የውጭ ንግድ ስርዓትን የሚያሳይ መግለጫ /memorandum of Foreign Trade Regime/ አዘጋጅቶ መላክ ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሥራ ላይ ስላሉ የጉምሩክ ቀረጦች፣ ለግብርና ስለሚሰጡ የሀገር ውስጥ ድጋፎችና የወጪ ንግድ ድጎማዎች፣ እንዲሁም የአገልግሎት ንግድ ዘርፍንና የአዕምሮ ንብረትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎችና የተለያዩ መረጃዎች ለጽ/ቤቱ ይላካሉ፡፡ አባል ሀገራት ከቀረቡት መረጃዎች ተነስተው ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አመልካች ሀገር ምላሽ ይሰጣል፡፡ ኢትዮጵያ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው ደረጃ ላይ ነው የምትገኘው፡፡ የውጭ ንግድ ስርዓት መግለጫዋን እአአ በ2006 ዓ.ም በማቅረቧ ከተለያዩ ሀገራት ለቀረቡት 423 ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥታለች፡፡ፀሐፊው ከ2003 ዓ.ም በኋላ ሁሉ ነገር ተቋርጦ በ2008 ዓ.ም ድርድሩ እንደተጀመረና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምንም ሥራ እንዳልተከናወነ የገለጹት፣ አሳሳችና እውነታውን ለመረዳት ካለመሻት ወይም በጥልቀት ጉዳዩን ሳይመረምሩ ብዕርና ወረቀትን ከማገናኘት የመነጨ ይመስለኛል፡፡

እ.አ.አ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ የውጭ ንግድ ስርዓት መግለጫውን ከማዘጋጀት በፊት በግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ በቢዝነስ፣ በኮንስትራክሽን፣ በማከፋፈል ሥራ፣ በቱሪዝም፣ በኃይል አቅርቦት፣ በፋይናንስ፣ በቴኮሙኒኬሸን፣ በትራንሰፖርትና በመሳሰሉት ዘርፎች ከሀያ በላይ የአንደምታ ጥናቶች ተከናውነዋል፡፡ በበርካታ ዘርፎችም ጥናቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ድርድሩን በሥርዓት ለመምራትና ሀገራዊ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ ለማጠናቀቅ የስቲሪንግና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡ ዋናውን የድርድር ሃሳብ በማቅረብና ሃሳቦችን ለማፍለቅ እንዲረዳ የተዋቀረው የቴክኒክ ኮሚቴ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያካተተ፣ በግለሰብ ደረጃ በዓለም ንግድ ድርጅት የካበተ ልምድ ያላቸውና መፅሐፍ ያዘጋጁ፣ በውጭ ዓለምም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን ያሳተፈ ነው፡፡ ሚስተር ማይክ ሙር ያብራሩት በሙሉ በኢትዮጵያ እየተሰራበት ያለውን ሂደት የሚያሳይና የማይቃረን ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ማይክ ሙር የድርጅቱ ዳይሬክተር ጀኔራል እንጂ ዋና ፀሐፊ አለመሆናቸውን መግለፅ እወዳለሁ፡፡ በድርጅቱ ዋና ፀሐፊ የሚባል መዋቅርም እንደሌለ ፀሐፊው ቢገነዘቡት መልካም ይሆናል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት ምንነትና ለኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ ምን እንደሆነ ማሳወቅና ማስረፅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በፀሐፊው እንደተገለፀው ሳይሆን፣ የሚያስገኛቸው ዕድሎችና ፈታኝ ሁኔታዎች ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ አውደጥናት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ተካሂዷል፡፡ ወደፊትም አቅም በፈቀደ መጠን የሚቀጥል ይሆናል፡፡ እነዚህ የማሳወቂያ ፕሮግራሞች በመንግስት ብቻ ሳይሆን፣ በልማት ንግድ ዙሪያ የሚሳተፉ እንደ OXFAM-GB እና ACCORD ባሉ ግብረሠናይ ተቋማትና የንግድ ምክር ቤቶች ጭምር ይከናወናሉ፡፡በስማ በለው የተፃፈውና ባለሙያዎች ማብራሪያ ያልሰጡበትን ክስተት የዘገበው የፀሐፊው ብዕር ሰሞኑን ከሰሜን አሜሪካ ልዑካን እንደመጡና በአቶ ወንደሰንና በአቶ አበበ አማካይነት ገለጻ እንደተደረገ ይገልፃል፡፡ ይህ ቅጥፈት ነው፤ እንደእውነቱ ከሆነ የዓለም ንግድ ድርጅትን በሚመለከት ከሰሜን አሜሪካ የመጣ ልዑክ አልነበረም፡፡ ይህን አስመልክቶም በባለሙያዎች የተሰጠ ገለፃም አልነበረም፡፡ ምናልባት ከዓለም ንግድ ድርጅት ጋር ተያይዞ የሌሎችን ሀገራት ልምድ ለመቅሰም በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ የተካሄደውን አውደ ጥናት ማንሳታቸው ከሆነ፣ ድርድሩን ወደእኛ ፍላጎትና የልማት አቅጣጫ እንዲያዘነብል ለማድረግ ካምቦዲያና የመንን በመምረጥ ከእነሱ ጠቃሚውን ተሞክሮ በመውሰድ ላይ ያጠነጠነ ሲሆን፣ ሀገሮቹን በዋና ተደራዳሪነት ከመሩ ባለሙያዎችም ልምድ መቅሰም ተችሏል፡፡በወቅቱ የኢትዮጵያ የሥራ ቡድን ሰብሳቢና የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ዳይሬክተር ጉዳይ አዲስ አበባ ለሥራ ጉዳይ ተገኝተው ስለነበር አጋጣሚውን በመጠቀም ጠቅለል ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ ጄኔቫ፣ ካምቦዲያና የመን በየትኛው በጂኦግራፊ ትምህርት ሰሜን አሜሪካ ውስጥ እንደሚገኙ ፀሐፊው ቢያብራሩት ይሻል ነበር፡፡ ከተሳታፊነት ውጭ በምንም መልኩ ዐውደ ጥናቱ ላይ ማብራሪያ ያልሰጡ ሰዎችን ያለአግባብ ስም ማንሳት ተገቢ አይመስለኝም፡፡

ዶ/ር ፈቃዱ በጽሁፋቸው ምን ለማለት እንደፈለጉና ሃሳባቸውን በግልፅ ለማስቀመጥ ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡ ባለሙያዎቹ፣ ድርጅቱ በተለይም ያልበለፀጉ አገራት ጠበቃ በመሆን በአባል ሀገራት መካከል ምርቶቻቸውን “እንዲያራግፉ” ያመቻቻል ብለዋል፤ ይሉናል፡፡ በዓለም ንግድ ድርጅት ዙሪያ እውቀት ያላቸው የተጠቀሱት ባለሙያዎች ይቅርና በግሉ ዘርፍ የተሰማራው ማንኛውም የንግዱ ህብረተሰብና የሁለት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ የወሰደ አርሶ አደር “ምርትን ማራገፍ” (dumping) በዓለም ንግድ ድርጅት ህግ የሚያስጠይቅ፣ ይህንን በሚያደርጉ ሀገራት ላይም አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ማለት የተፈለገው ስለ ገበያ ዕድል (Market Access) ከሆነ እንደ ኢትዮጵያ ያለ በልማት ወደኋላ ለቀረ ሀገር በተለያየ ሁኔታ በተሰጡ ዕድሎች፣ ለምሳሌ በአሜሪካ የተሰጠ የአፍሪካ እድገትና ዕድል ድንጋጌ፣ ከመሳሪያዎች በስተቀር ሁሉንም ምርቶች (Everything But Arms) ወደ አውሮፓ ህብረት ከቀረጥና ኮታ በነፃ እንዲያስገቡ፤ እንዲሁም ወደ ጃፓን፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ካናዳ ወዘተ የተሻለ የገበያ ዕድል የተሰጠበት የአንድ ወገን ችሮታ አለ፡፡ እነዚህ የአንድ ወገን ችሮታዎች በድርድር ያልተገኙና አንድ ሀገር አባል ስለሆነ ወይም ስላልሆነ የሚያገኛቸው ሳይሆን በተፈለገ ጊዜ ሊነሳ የሚችል ነው፡፡ ከድርጅቱም ጋር ከዶሀ የልማት አጀንዳ ጋር ተያይዞ ካልሆነ በስተቀር እምብዛም የሚገናኝ አይደለም፡፡ ሦስተኛው የድርድር ደረጃ፤ አመልካች ሀገር ከዋና ዋና የንግድ ሸሪኮች ወይም ለአንድ ሀገር ገበያ ፍላጎት ካላቸው ጋር ታሪፍን መወሰንና የአገልግሎት ገበያን ለውድድር ክፍት በማድረግ የሁለትዮሽ፣ እንዲሁም ህጎቹን በተመለከተ እንዳለ የመቀበል (Single under taking) የመልቲላተራል ድርድር ማካሄድ ነው፡፡ ህጎቹን አባል እንደሆኑ ተግባራዊ ማድረግ የሚቸገሩ አገሮች የጊዜ ገደብና አስፈላጊ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላለ በልማት ወደኋላ ለቀረ ሀገር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ አዳዲስ ተቋሞችን ለማቋቋምና ህጎችን ለማሻሻል የመሸጋገሪያ ጊዜ ይሰጣል፡፡ እንደመታደል ሆኖ የእኛ ህጎች በአብዛኛው ከድርጅቱ ጋር የሚስማሙ መሆናቸውን የተካሄዱት ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ እዚህ ላይ፣ ድርጅቱን ለመቀላቀል ለምን ረዥም ጊዜ ይፈጃል? ከቻይና በላይ የፈጀባቸውና አሁንም ያልተቀላቀሉ ሀገሮችስ የሉም ወይ? (ሩሲያና አልጀሪያን ያጤኗል)፡፡ የኢትዮጵያስ ሁኔታ እንዴት ይታያል? የሚለውን ግልፅ ማድረግ ይገባል፡፡ ሀገራት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በሚያደርጉት የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር፣ ገበያቸውን “ልቅ” ማድረግ የሚባል ነገር የሌለ ሲሆን፣ የሚጠበቅባቸው የታሪፍ መጠናቸውን ጣሪያ ማበጀት ነው፡፡ በዚህ ረገድ አመልካች ሀገራት ሦስት ስትራቴጂዎችን ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ አንድ፣ ምርት በመውሰድ፡፡ በምሳሌ ላስረዳ፤ ልብሶችን በተመለከተ በኢትዮጵያ በአብዛኛው አሁን የሚሰራበት ታሪፍ (Applied Tariff) 35% ነው፡፡ በድርድሩ ወቅት ኢትዮጵያ ከልማቷ አኳያ በመመልከት ጣሪያውን ከሚሰራበት እኩል፣ ከሚሰራበት በላይ እና ከሚሰራበት በታች አድርጋ ልታስቀምጥና ልትደራደር ትችላለች፡፡ የምርቱን በብዛት መግባት የምትፈልግ ከሆነ ከ35% በታች

ታደርገዋለች፤ ከለላ የሚያስፈልግ መሆኑን ካመነች ከ35% በላይ የከላላ መጠን ላይ ታስቀምጠዋለች፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከ100% በላይ ማድረግ ተችላለች፡፡ በእኛ የእድገት ደረጃ ላይ የሚገኙና ቀደም ሲል አባል የሆኑ ሀገራት በታሪፍ የገቡትን ግዴታ ስንመለከትም ተመሳሳይ ሁኔታ እናስተውላለን፡፡ እአአ በ2004 ድርጅቱን የተቀላቀሉት ኔፓልና ካምቦዲያ በድርድሩ ወቅት የነበራቸውና የሚሰራበት አማካይ የታሪፍ መጠን እንደቅደም ተከተላቸው 12.7% እና 14.2% የነበረ ሲሆን፣ ተደራድረው ያገኙት አማካይ የታሪፍ ጣሪያ 26% እና 19% ነበር፡፡ ይህም ወደፊት ከሚሰሩበት በላይ ታሪፍ መጨመር እንኳን ቢያስፈልጋቸወ የፖሊሲ የመጫወቻ ቦታ መተዋቸውን ያመለክታል፡፡ ስለዚህ “ልቅ” የሚለው አመለካከት፣ አመልካቹ ሀገር እስካልፈለገው ድረስ የሚፈጠር አይደለም፡፡ በአገልግሎት ዘርፍም እንዲሁ ሌሎች ሀገራት ቴሌን፣ ፋይናንስን ጠየቁ ማለት ለውጭ ባለሀብቶች እንደከፈት ስምምነት ተደረሰ ማለት አይደለም፡፡ አባል ሀገራት ከአመልካች ሀገሮች እንዲከፈትላቸው የፈለጉትን ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ (ድርድር መሆኑ እንዳይረሳ)፡፡ አመልካች ሀገራት ደግሞ በልማት መጠናቸው ሊሰጡት የሚፈለጉት ወይም ግዴታ የሚገቡበትን ልክ አውጥተው አውርደው ጥናት አድርገው ይወስናሉ፡፡ ይህ በድርድር የሚወሰን ሆኖ አባል ሀገራቱና አመልካች የሚስማሙበት ደረጃ ላይ ያደርሳቸዋል፡፡ በእስካሁኑ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ልምድ በአገልግሎት ዘርፍ አመልካች ሀገራት በርካታ ውስንነቶችን በማስቀመጥ የገቡበት ሁኔታ አለ፡፡ ያም ሆነ ይህ ምን ይከፈታል? ምን አይከፈትም? የሚለው የሚወሰነው ዘርፉ የሀገራችን ፖሊሲዎችና ስትራቴጄዎችን ከማሳካት አኳያ ያለው ፋይዳ፣ ካለን የድርድር አቋም፣ ይህንንም ለማስጠበቅ ያለን ዝግጁነትና የተደራዳሪ ሀገሮች አቋም ጭምር ተዳምሮ ስለሚሆን ከወዲሁ ለመተንበይ ያስቸግራል፡፡ ያም ሆኖ እንደ ኢትዮጰያ ያሉ ሀገራትን አባልነት ለማፋጠን በልማት ወደኋላ ከቀሩ አባል ሀገራት በተውጣጣ ኮሚቴ መመሪያ እንዲዘጋጅ ተደርጎ በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ እአአ በዲሴምበር 2002 ፀድቋል፡፡ ይህ መመሪያ ሂደቱ ቀለል ባለና በተስተካከለ መንገድ መካሄድ እንዳለበት አስቀምጧል፡፡ በዚህም መሠረት ጠቅላላ ጉባኤው ካስተላለፋቸው ውሳኔዎች መካከል፡-

የገበያ ዕድልን - በተመለከተ በዕቃዎች በአገልግሎት ንግድ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገታቸውን ያላገናዘበ ግዴታ እንዲገቡ አባል ሀገራት ጫና እንዳያደርጉና አባል ሀገራት የዕድገት ደረጃቸውን፣ የፋይናንስና የንግድ ፍላጎታቸውን ግምት ውስጥ ያስገባ ግዴታ ብቻ እንዲገቡ፣

የዓለም ንግድ - ድርጅት ህጎችን በተመለከተ በስምምነቶቹ ውስጥ የሚገኙት ለታዳጊ ሀገራት በልዩ ሁኔታ እንዲታዩ የሚደረጉ (“Special & Differential Treatment Provisions”) በሁሉም በሂደቱ ውስጥ ባሉ በልማት ወደኋላ የቀሩ አገሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የእነዚህ ሀገሮች ፍላጎት ካልሆነ በስተቀር የፕሉሪላተራል ስምምነቶች አባል ለመሆን እንደቅድመ ግዴታ እንደማይቀመጡ ወይም ግዴታ እንደሌለባቸው የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ፀሐፊው የኢኮኖሚክስ ባለሙያና በዓለም

ንግድ ድርጅት ዙሪያ ለመጻፍ የሞከሩ እንደመሆናቸው መጠን፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች አወቃቀር ምን እንደሚመስል ይጠፋቸዋል ብዬ ባልገምትም፣ ስለ ዓለም ንግድ ድርጅት ያስቀመጡት እጅግ የተዛባና ሚዛናዊ ያልሆነ ትነታኔ በእውን አደረጃጀቱንና አሰራሩን አውቀው ወይስ ከተራ አሉባልታ በመነሳት የሚል ጥያቄን ጭሮብኛል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት በመሠረቱ የሚወስነውም፣ እንዲህ አድርጉ የሚለውም ነገር የለም፡፡ የድርጅቱ ተግባራት በዋናነት የዓለም አቀፍና የብዙሃን የንግድ ስምነነቶች እንዲተገበሩ ማድረግና ማስተዳዳር፣ የንግድ ድርድሮች መድረክ ሆኖ ማገልገል፣ በአባላት መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች እንዲፈቱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ የአባል ሀገራትን የንግድ ፖሊሲዎች መገምገምና ለታዳጊ ሀገሮች በንግድ ፖሊሲ ጉዳዮች የቴክኒክ ዕገዛና ስልጠናዎችን መስጠት ነው፡፡ ድርጅቱ ሀገራት ማድረግ የሚገባቸው ላይ ውሳኔ አያሳልፍም፡፡ ውሳኔዎች የሚተላለፉት የሁሉም አባል ሀገራት ተወካዮች በሚገኙበት በሚኒስትሮች ጉባኤ ወይም በጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ በእነዚህ አካላት የሚተላለፍ ውሳኔ በሁሉም መግባባት በሚለው መርህ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሁሉም አገር እኩል አንድ ድምፅ ይኖረዋል፡፡ ማንኛውም ሀገር ሊተገብር የማይፈልውን ሕግ ሥራ ላይ እንዳይውል ማድረግ ይችላል፡፡የዓለም ንግድ ድርጅትን መቀላቀል ከሚያስገኛቸው ዕድሎች ውስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ምርቶችን ወደ - አባል አገራት ለመላክ የተረጋገጠ የገበያ ዕድል፣

በ ድ ር ጅ ቱ - መሠረታዊ መርሆዎች መሠረት በየጊዜው የሚወጡ ፖሊሲዎችና ህጎችን ሀገራት በግልፅ የማሳወቅ ግዴታ ስለሚኖርባቸው በሀገራቱ ላይ ድንገተኛ አድሎአዊ የንግድ ዕቀባ ሊደረግ አለመቻሉ፣

የ ድ ር ጅ ቱ - ስምምነቶችን መቀበል ለውጭ ባለሀብቶች ጠንካራ መተማመኛ በመሆኑ ለውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት መርዳቱ፣

የሀገራቱ የውጭ - ምርቶች ከድርጅቱ ስምምነት ውጭ በማናቸውም ባል ሀገር እንዳይገቡ ቢደረግ የድርጅቱን የንግድ ግንኙነቶች መድረክ በመጠቀም መፍትሄ ማግኘት መቻሉ፣

በንግድ ሥርዓቱ - የሚፈጠረው ውድድር የተሳለጠ የንግድ ግንኙነት እንዲኖር ስለሚያስችል ሸማቹ ሕብረተሰብ በተሻለ ዋጋና ጥራት አማራጭ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለማግኘት ዕድል እንዲያገኝ ማድረጉ፣

ንግድ ነክ የሀገር - ውስጥ ፖሊሲዎችና አዋጆች ከድርጅቱ ስምምነቶችና መሠረታዊ መርሆዎች ጋር እንዲጣጣሙ ስለሚደረግ በተወሰኑ ዘርፎች ለሚገኙ የተወሰኑ ቡድኖች (interest lobbying group) ፍላጎት ማሟያ እንዳይውሉ ማድረጉ፣

ግልፅነት እየሰፈነ - እንዲሄድ የሚያመቻች በመሆኑ ሙስናና ጥገኝነትን መቀነስ ማስቻሉ እና

በንግድ ስርዓቱ - የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ማበረታታቱ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በሮቢንስን ክሩሶን የኢኮኖሚ መርህ ማጠንጠን የሚቻልበት ዘመን አልፏል፡፡ በግሎባላይዜሽን ዘመን ወደ ኋላ ላለመገፋት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ኢትዮጵያን የመሰለች አገር አባል እንዳትሆን መፈለግ፣ ዘላለም የዓለም ንግድ ድርጅት በሁለት አህጉር ወይም በሁለት ሀገር ነው የሚመራው በማለት ያልተገባ ምክንያት ከማቅረብ፣ ስርአቱ ውስጥ በመግባት ፈተኝ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ ከመሰል ሀገሮች ጋር አብሮ መታገል ሁላችንም የሚጠበቅብን የቤት ሥራ ነው፡፡ የዓለም ንግድ 97% የሚካሄደው በአባል ሀገሮች መካከል መሆኑ ግልፅ ሊሆንልን ይገባል፡፡ ድርድሯን እያጠናቀቀች ያለችው ሩሲያ በቅርቡ ስትቀላቀል ወደ 99.3% ገደማ ይደርሳል፡፡ ኢትዮጵያ አባል ባትሆንም ተወደደም ተጠላም የምትገበያያቸው ሀገሮች በሙሉ አባላት በመሆናቸው ህጎቹ ተፈፃሚ ናቸው፡፡ ስለዚህ አባል መሆን ይጠቅማል፡፡ አይጠቅምም የሚለው የተዘጋ አጀንዳ ላይ ከመነታረክ ይልቅ ያለንን ሀይል በሙሉ በመጠቀም የምንገባበት የድርድር ሂደትና አቋም የሀገራችንን ጥቅሞች ባስጠበቀ መልኩ እንዲሆን በየተሰማራንበት መስክ የበኩላችን አስተዋጽኦ ማድረግ የዜግነት ግዴታ መሆኑን እያስገነዘብኩ የዛሬውን ፅሁፌን በዚሁ ላብቃ፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ፅንፈኛ የተዛቡ አመለካከቶች

በልሳነወርቅ ጎርፉ

/አቶ ልሳነወርቅ ጎርፉ በንግድ ሚኒስቴር የመልቲ-ላተራል ንግድ ግንኙነት ድርድር ቡድን መሪ ናቸው፡፡/

Page 12: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

p Ç T@ S ´ “ —ዳ ሰ ሳ

12

በንፍታሌም

“...ከአራት ወራት በኋላ ሰማንያ አንደኛ አመቴን እጀምራለሁ፡፡ ከአለፈው ምዕተ ዓመት ከተረፉት ጥቂት ኢትዮጵያውያኖች መካከል ነኝ ማለት ነው፡፡ በዚህ ባለንበት ዘመንም የደርግና የወያኔ ትውልዶች አርባ ዓመት ሊሞላቸው ነው፡፡ ከአለፈው ትውልድ ጀምሮ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ወደ አምስት ትውልዶች ይሆናሉ፡፡ ከእነዚህ አምስቱ ትውልዶች ውስጥ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ የደርግና የወያኔ ትውልዶች ናቸው፡፡ ያነሰችና የተዋረደች ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ናቸው፡፡...” ይህ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም “ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፣ ፖለቲካና ምርጫ” በሚል ርዕስ ከፃፉትና በቅርቡ ለህትመት ካበቁት መቅድም ውስጥ ቃል በቃል የተወሰደ ነው፡፡ ፕሮፌሰሩ አሁን ለአንባቢያን ካቀረቡት መፅሐፍ በተጨማሪ፣ በ1996ዓ.ም “የክህደት ቁልቁለት” በሚል ርዕሥ አሳተመውት የነበረውን መፅሐፍ በ”ደባልነት” አስጠርዘው አበርክተዋል፡፡ በአጭሩ ሁለት መፅሐፎችን በአንድነት ነው ለአንባቢያን ያበረከቱት ማለት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ የዛሬ የመፅሐፍት ዳሰሳችን ዋንኛ ትኩረት የሚሆነው “ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፣ ፖለቲካና ምርጫ” በሚል ርዕሥ የፃፉት ነው፡፡ ይህ መፅሐፋቸው በአንድ ጥራዝ ተሸክፎ ወደ አንባቢያን ዘንድ ሲደርስ “የመጀመሪያው” ነውና፡፡ ደራሲው ፕ/ር መስፍን “አዲስ” መፅሐፋቸው ባህል፣ ባህላዊ ድርጅቶች በኢትዮጵያ፣ ባህልና ፖለቲካ፣ ባህላዊው የስልጣን ምንጭ፣ ዴሞክራሲ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ተሪካዊ ችግሮች፣ ኢትዮጵያዊነትና አገር ተረካቢው ትውልድ፣ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን፣ ተባብረን ኢትዮጵያን እናድን... ወዘተ በሚሉ 15 ምዕራፎች ከፋፍለውታል፡፡ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ሥር ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵዊነት ሁለንተናዊ ዕድገት ዕንቅፋት ናቸው ያሏቸውን ጉዳዮች ያወሳሉ፡፡ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ማነስና መዋረድ ዕንቅፋት ናቸው ያሏቸው ወገኖች ሰይፍ ጨብጠው ጊዜያዊ የሥልጣን መንበር ላይ የተፈናጠጡ መሪዎችና ለሆዳቸው የገበሩ ፀሐፊዎች እንደሆኑም በአጽንኦት ይዘክራሉ፡፡ ለዚህም አባባላቸው አብነት ይሆናቸው ዘንድ በዋናኝነት የአፄ ቴዎድሮስን ታሪክ በመቅድማቸው ውስጥ በሚከተለው መልክ ያጣቅሳሉ፡፡“... በአፄውም፣ በደርግም፣ በወያኔም ዘመን አፄ ቴዎድሮስ ትልቅ ሥም የተሰጣቸው ነበሩ፡፡ ቴዎድሮስ የስልጣን ዘመናቸውን የጀመሩት በሎሌነት ነው፡፡ ከሎሌነት ወደ ሽፍትነት፣ ከሽፍትነት ወደ ንጉሥነት ተረማመዱ፡፡ ስለቴዎድሮስ ያልፃፈ እኔ ነኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ደራሲ የለም፡፡ (በአንፃሩ ሥለ ሚኒሊክ የሞከሩ ጥቂቶች ናቸው፡፡) ቴዎድሮስ ምን ሰሩ? አንደኛ፣ በዘመነ መሳፍንት የኢትዮጵያን የመከፋፈል አደጋ አገዱ፡፡ ሁለተኛ፣ ባይሳካም በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሥራ እንዲጀመር ሞከሩ፡፡ አንድ ጊዜ ተተኩሶ የበቃው መድፍ አስሰሩ፡፡ ያንን መድፍ መቅደላ ላይ አወጡት፡፡ ይህ ቀላል እንዳይመስላችሁ፡፡ ዛሬ ያንን መድፍ ከመቅደላ ማውረድ አይቻልም፡፡ ሦስተኛ፣ ራሳቸውን ገደሉ፡፡ ከዚህ ሌላ ስለቴዎድሮስ

የሚነገር የለም፡፡...”ፕሮፌሰሩ ይቀጥላሉ፡-“ባህል ሆኖ የተላለፈልን ለህዝቡ ስቃይና መከራ መፍትሄ የሚሆነውን ወይም የሚፈለግበትን መንገድ ሳይሆን፣ ያው ጭካኔና የጭቆና ሥርዓት እየተወደሰ የሚተላለፍበትን ነው፡፡ ለዚህ ነው ባህላችን ገዳይን የሚያወድስና የሚያከብር የሚሆነው፡፡ ገዳይን እያወደሱ ሰላምና መረጋጋትን፣ ዕድገትንና ብልፅግናን መመኘት አይጣጣሙም፡፡... ለዚህ ነው ሻዕቢያና ወያኔ ከሽፍትነት ወደ ሥልጣን የተሸጋገሩት፡፡ ዛሬው ብዙ ‘’ጀግኖች’’ ያንኑ ፈለግ ተከትለው ሥልጣንን በዱላና በሰይፍ ለማግኘት ለራሳቸው መደበቂያ ዋሻ፣ ለየዋሆች ጎረምሶች ከሞቱ በኋላ የሚሰጧቸውን የጀግንነትና የመስዋዕትነት ሊሻን እያዘጋጁ ከሩቅ የሚያቀራሩት፡፡....” (ሠረዝ የኔ) (ከገፅ 1-3)

ሥልጣን በመሣሪያ የመቆጣጠር ባህል የሀገሪቷን ዕድገት አንቆ የያዘ ዓይነተኛ ችግር መሆኑን በ”አዲሱ” መፅሐፋቸው በአፅንኦት የገለፁት ፕ/ር መስፍን፣ በደርግ የተካሄደው የመንግሥት ሥርአት ለውጥ የሥልጣን ጥማት በተጠናወታቸውና ከመጋረጃ በስተጀርባ ባሉ ኃይሎች አቅጣጫውን እንደሣተ ይተነትናሉ፡፡

“... እነሱ የለመዱት ከበስተጀርባ ሆነው ተማሪዎችን መንዳት እንጂ ፊት ለፊት ቀድመው በመምራት አልነበረም፡፡ ደርግ ከመጋረጃቸው ሲያስወጣቸው ተደናበሩ፤ በዚህ ጊዜ ወደ ውጭ አገር ወይም ወደ ጫካ ሽሽት ተጀመረ፡፡ ጥቂቶቹ ሞቱ፤ ጥቂቶቹ ተመልሰው ድምፃቸወን አጥፍተው ይኖራሉ፡፡ የሸሹትም እንዲሁ ፖለቲካን በሩቁ ብለው ኑሮአቸውን ይኖራሉ፡፡ አሁንም በስደት ያሉት ከሩቅ ይንፈራፈራሉ፡፡ አንዳንዶቹም በአምስት መቶ ካሬ መሬትና በሹመት እየገበሩ ይገኛሉ፡፡” (ገፅ 38-39)

ትውልድ ካለፈው ሳይማር ያንኑ ስህተት እየደገመ መሄዱ አሳዛኝ መሆኑን፣ ከጥሬ የሥልጣን ጥም ጋር በተያያዘ ስህተት ቢያንስ ሦስት ትውልዶችን መጥበሱንም ያስረዳሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ (በኢህአደግ ዘመን) ደግሞ አዲስ የስልጣን ጥምን የሚያጋግል የሩቅ መድረክ መከፈቱንም ያወሳሉ፡፡

“ብዙ በአሜሪካና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአገኙት አዲስ የሥልጣን ጥምን የሚያጋግል የሩቅ መድረኮች ከፍተው በቀረርቶ በሽለላ የስልጣን ጥምን ይቀሰቅሣሉ፡፡’’ (ገፅ 11)

ፕሮፌሰር መስፍን በጣም የተማሩ የሚባሉትም፣ በፈረንጅ አገረ ሃያና ሰላሣ ዓመታት የኖሩትም፣ ቢያንስ በተግባር ደረጃ ፖለቲካ ምን እንደሆነ ያውቃሉ ማለት አያስደፍርም ባይ ናቸው፡፡

‘’... አስራ አምስት ሺህ ኪሎ ሜትር ከኢትዮጵያ ርቆ የሚኖረው፣ አለ እኔ ለኢትዮጵያ የሚያስብ የለም የሚለውም፣ እትብቱ የተቀበረበትን ክዶ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም የሚለውም አይለይም፡፡ የሁለቱም አዕምሮ በርቀት ዝጓል፡፡ በስድነት ባልጓል፡፡’’ (ገፅ 12)

እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አባባል የሰከነ የፖለቲካ ትግል የታየው በ1997 ዓ.ም ነው፡፡ ይህ የሰከነ ሠላማዊ

የፖለቲካ ትግል መስዋትነት ቢያስከፍልም አሁንም አልቆመም፡፡

‘’ ...አሁንም በአስራ አምስት ሺህ ኪሎ ሜትር የማይበገር ምሽግ ውስጥ በምቾት ተቀምጠው ሰላማዊና ህጋዊ የፖለቲካ ትግል መስማት የማይፈልጉ መሣሪያ ሳያነሱ፣ ዒላማቸው ላይ ማነጣጠር ሳይችሉ፣ በራዲዮና በስልክ ቀረርቶ የሥልጣን ጥማቸውን የሚወጡ እየመሠላቸው አለ እኛ ማንም አይናገር የሚሉ አዲስ አገዛዝ ሊመሰርቱልን የሚዘጋጁ አሉ፡፡’’ (ገፅ 53) ይላሉ፡፡

እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አባባል በኢትዮጵያ ሥር የሰደደው ሥልጣንን በኃይል የመቆናጠጥ ባህል በርካ ችግር የፈጠረ ነው፡፡ መሪዎች ህዝቡን ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዙ የሚያደርጋቸው ባህል ነው፡፡ መሪው በጭቆና መግዛት የሚወደውን ያህል ህዝቡ በጭቆና ስር

መገዛትን ይለምዳል፡፡ በአገዛዝ ስርዓት ውስጥ ገዢና ተገዢ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ

አብረው ይኖራሉ፡፡ (ገፅ 45)በዚሁ ገፅ ህዳግ ‘’በቅርቡ

የዱሮው ሽፍታ ያሬድ ጥበቡ በጣም ተናዶ የኢትዮጵያ ህዝብ በጭቆና ስር ለመኖር ተገዷል ብሎ በአንድ ጋዜጣ ፅፎ ነበር፡፡ ሁነቱን ቢይዘውም አስተሳሰቡን ስቶታል፡፡ ንዴት አስተሳሰብን ያዳልጣል...’’ ሲሉ ትችትም ሰንዝረዋል፡፡

ፕ ሮ ፌ ሰ ሩ በ’’አዲሱ’’ (አዲስ የሚለውን ቃል በትምህርተ ጥቅስ መቀመጡን ልብ ይበሉ) መፅሐፋቸው በሰላማዊ የትግል ስልት የሥርአት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ደጋግመው በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡

‘’በመጀመሪያ በግዴታ ከታሪካችን የወረስነውን

የጦረኝነት ባህርይ ከውስጣችን ነቅለን ማውጣት እንዳለብን የሚያጠራጥር አይደለም፤ ... በስልጣን ላይ ያሉት በኃይልና በጠመንጃ መመካታቸውን ትተው ነገን እያሰቡ አመራራቸውን በህግና በሥነ-ስርዓት ላይ ቢያደርጉ ተቃዋሚዎቻቸውን ወደ ጦርነት አይጋብዙም፡፡... ያለ ጠመንጃ ወደ ሥልጣን ኮርቻ ላይ መውጣትና መውረድ የሚቻል መሆኑን ሊያስተምሩን ይገባል፡፡... የሥልጣን ጥም አለባቸው ከሚባሉ ሰዎች እንዲህ አይነቱ ቅን መንፈስ መጠበቅ የዋህነት ነው የሚሉ ወገኖች መኖራቸውን አውቃለሁ፡፡ ግን እስቲ ቅን መንፈስን እንሞክረው..’’ (ገፅ 64) ሲሉ ገዢዎችንና ተቃዋሚዎችን ይመክራሉ፡፡

ይህንንም ዕውነታ ለማሣካት ውይይትና ክርክር አስፈላጊ እንደሆነ፣ ነገር ግን ውይይቱም ሆነ ክርክሩ በቅንነት መንፈስ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት (ገፅ 53) ያሰምሩበታል፡፡

ጠቅለል ባለ መልኩ ፕሮፌሰር መስፍን ‘’ሥልጣን ባህልና አገዛዝ፣ ፖለቲካና ምርጫ’’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ለአንባቢያን ያበረከቱት መፅሐፍ ሠላማዊ በሆነ መልኩ የመንግስት ሥርአትን ለመተካት፣ ለዘመናት ተጣብቶን የኖረውን አስቸጋሪና ፈርጀ ብዙ ባህል፣ በአዲስ ባህል መቀየር ብሎም ወደስኬት ማምራት ይቻላል የሚል ቱባ መልዕክት የያዘ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የፕሮፌሰር መስፍን መፅሐፍ “ፍፁምና የተዋጣለት ነው” የሚባል አይነት ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ምክንያቱም በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍለው የቀረቡት ጥቂት ክፍሎች፣ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መድረኮች ወይመ ህትመቶች የተነገሩ ወይም ለአንባቢያን የቀረቡ ናቸው፡፡

ለምሳሌ ያህል በምዕራፍ 4 “ባህልና ባህላዊ ድርጅቶች” በሚል ርዕሥ (ከገፅ 18-27) የቀረበው ፅሁፍ ፕሮፌሰሩ ከ40 ዓመት በፊት በዕድሮች ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ነው፡፡ በምዕራፍ 8 “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ችግሮች” በሚለው ርዕሥ ሥር (ከገፅ 56-62) በጀርመን አገር የኢትዮጰያውያን ስብሰባ ላይ የተደረገ ንግግር ነው፡፡ ምዕሪፍ

9 “ጭቆና ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ” (66-81) በሚል ርዕስ ስር የቀረበው ፅሁፍ በሰኔ ወር 1989 ዓ.ም በጦቢያ መፅሔት ታትሞ ለንባብ የቀረበ ነው፡፡ በምዕራፍ 11 “እኛና ይህቺ መሬት፣ ህይወትና ሞት” በሚል ርዕሥ (ከገፅ 82-93) ሥር የቀረበውም ፅሁፍ እንዲሁ፡፡ በምዕራፍ 14 “የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን” (ከገፅ 37-145)፣ እንዲሁም በምዕራፍ 15 “ተባብረን ኢትዮጵያን እናድን” በሚል ርዕሥ ሥር (146-160) በዋሽንግተን ዲሲ በ1996 የቀረበ ንግግር ነው፡፡

ከዚህ አንፃር የፕሮፌሰሩን መፅሐፍ የተዋጣለትና የታሰበበት ነው ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ከላይ ለአብነት የጠቀስናቸው ምዕራፎች በንግግር በቀረቡት ወቅት ወይ ለህትመት በበቁበት ዘመን የተባ ቁርኝትና ጠንካራ መልዕክት ቢኖራቸውም፣ (ያላቸው መሆኑ ባይካድም) አሁን በመፅሀፍ መልክ በአንድነት ለአንባቢያን ሲቀርቡ ዘመን ተሻጋሪ ቁም ነገር የማስተላለፍ ብቃት አላቸው ማለት አይቻልም፡፡ በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ በሀገሪቷ የተከሰተውን ችግር ለማሳየት ፅሐፊው ለአብነት የጠቀሷቸው ጉዳዮች፣ አንድን ወቅት ወይም ጊዜ ከማሳየት ባለፈ፤ የዳበረና የጠነከረ መሠረት ላይ የቆሙ አይደሉም፡፡ ምናልባት ለአብነት የጠቀሷቸውን ክስተቶች እንደገና ቢያዩአቸው ኖሮ የበለጠ ሊያዳብሯቸው የሚያስችላቸውን ሌሎች ሁነቶችን በማከል የተሻለ ዕይታ እንዲኖረን ማድረግ ይችሉ ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡

ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን በመፅሐፋቸው ውስጥ አንድን ጉዳይ ለመተንተን እንደምሳሌ የሚያነሷቸው አንዳንድ ጉዳዮች በጥያቄ ምልክት ውሰጥ የሚወድቁ አይነት ናቸው፡፡ ለዚህ አባባላችን አስረጅ ይሆነን ዘንድ በምዕራፍ 13 “ምርጫ 2002” በሚል ርዕስ ስር፣ በምርጫው ሂደት ዋና ዋና ተዋናዮች ናቸው ሲሉ ያሰፈሩትን ክፍል መጥቀስ ይበቃል፡፡

ፕ/ር መስፍን በምርጫ 2002 ተዋናይ ከነበሩት መሀል አንዱ ኢህአዴግ መሆኑን ያወሳሉ፡፡ “ሁለተኛው ተዋናይ ያልነው ቡድን በተቀናቃኝነት የተሰለፈው ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የተከፋፈለ ቢሆንም ዋናዎች የሚባሉት መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ መድረክና ሌሎች ትንንሽ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ በተቀናቃኝ ቡድኖች መሀል ያለው ልዩነት ምንድነው? ዶ/ር ነጋሦና አቶ ስዬ ወደአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከገቡ በኋላ አንድነትን ወደ ኢህአዴግ የሚያሰጠጋ የፕሮግራም ለውጥ ከማድረጉ በቀር ከባድ ልዩነት ያላቸው አይመስለኝም...” (ገፅ 113) ይላሉ፡፡ (ሠረዝ የኔ)

ፕሮፌሰሩ ምርጫውን በተመለከተ ይህንን የ”አይመስለኝም” ሀሳብ ያነሱት ጠንካራና አሳማኝ በሆነ መሠረት ላይ ቆመው መሆኑ ያጠራጥራል፡፡ የሰዎችን ስም ለማንሳት ካልሆነ በቀር፣ የምሳሌው ፋይዳ በመፅሀፋቸው ይዘው ከተነሱት አብይ ጭብጥ አንፃር እዚህ ግባ የሚባል ፋይዳ ያለው አይመስልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እሳቸው የተሳካ ለውጥ ለማምጣት ‘’በቅን መንፈስ መወያየት ያስፈልጋል’’ ሲሉ ያሳፈሩትን ሃሳብ የሚጣረስ ዓይነት ነው፡፡

ሌላም! ሌላም! ሌላም! የሆነ ሆኖ ፕሮፌሰር መስፍን

አጠቃላይ የሆነ ሀገራዊና ሰላማዊ ለውጥ ለማምጣት ይቻል ዘንድ መቀረፍ ያለባቸው አስተሳሰቦች እንዳሉ በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡ እኔም በከፊል በሀሳባቸው እስማማለሁ፡፡ የማልስማማባቸው ነገሮች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ፣ ቀሪውን ለአንባቢያን መተው ነው የሚሻለው፡፡

አበቃሁ!

የፕሮፌሰር መስፍን መፅሐፍ ሲቃኝ

‘’ ...አሁንም በአስራ

አምስት ሺህ ኪሎ ሜትር

የማይበገር ምሽግ ውስጥ

በምቾት ተቀምጠው ሰላማዊና

ህጋዊ የፖለቲካ ትግል መስማት

የማይፈልጉ መሣሪያ ሳያነሱ፣

ዒላማቸው ላይ ማነጣጠር

ሳይችሉ፣ በራዲዮና በስልክ ቀረርቶ

የሥልጣን ጥማቸውን የሚወጡ

እየመሠላቸው አለ እኛ ማንም

አይናገር የሚሉ አዲስ አገዛዝ

ሊመሰርቱልን የሚዘጋጁ አሉ፡፡

- የመፅሐፉ ርዕሥ:- ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ :- የክህደት ቁልቁለት - የመፅሐፉ ደራሲ:- ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም- የመፅሐፉ ገጽ ብዛት:- 164+184 = 348- መፅሐፉ የታተመበት:- 2003 ዓ.ም - የመፅሐፉ ዋጋ ፡- 60 ብር

Page 13: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

p Ç T@ S ´ “ —ኪን ዜናዎች አፍታ1

13

ሙያ ስለሆነ ከህብረተሰብ በላይ መኖር አለብህ፡፡ ካልተማረ ህብረተሰብ ጋር መቅረብ የለብህም›› አሉኝ፡፡ ‹‹ባለቤቴ ሦስተኛ ክፍል ያልጨረሰች በመሆኗ ያልተማሩ ሰዎች መራቅ ይከብደኛል›› አልኳቸው፡፡

አራት ልጆች የወለደችልህ ጃማይካዊቷ ባለቤትህ [አሁን ተፋተዋል] ያልተማረችው ለምንድን ነው?በችግር ምክንያት፤ ደሀ ነበረች፡፡ ያደገችው በአያቷ እጅ ነበር፡፡ ከዚያም በቤት ሠራተኝነት ሰርታለች፡፡

ስትታይ ወጣት ትመስላለህ እንጂ ዕድሜህ... [ሳቅ]51 ዓመቴ ነው፡፡ ሰዎች ስነግራቸው አያምኑኝም፡፡ ከ35 ዓመት ያለፍኩ አይመስላቸውም፡፡

ብዙዎች ይጠራጠሩሀል፤ ‹‹ሰላይ ነው!›› እንደሚሉህ ታውቃለህ? ብዙ ሰው እንደዚያ ይጠረጥረኛል፡፡ አሁን ያለሁት አዋሽ መልካሳ ነው፡፡ እዚያ ምን ምስጢር አለና ነው የምሰልለው? ‹‹ሰላይ ነህ!›› የሚሉኝ ምን እንደምሰልል ነግረውኝ አያውቁም፡፡ ቢጠራጠሩኝም ምንም ችግር የለብኝም፤ ምን አገባኝ?

እሺ!... ለምን በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለህ? አሁን የመጣሁት በዋናነት የህክምና መፅሐፎችን ለማንበብ ብቻ ነው፡፡

መጽሐፍ ለማንበብ ኢትዮጵያ ድረስ ምን አመጣህ?የማዋለድ ቀዶ ጥገና ልምድ ስለሌለኝ እውቀቴን ለመከለስ በዚያው ወደ ሶማሌ ላንድ ስለምሄድ ነው፡፡

ከቦታስ አዋሽ መልካሳን የመረጥከው ለምንድን ነው? እዚያ ብዙ ሰው ስለማውቅና ጓደኞች ስላሉኝ ነው፡፡ በብዛትም ምግብ

በኢትዮጵያ ፍቅር ብስክስክ ያልክ ይመስለኛል፡፡ በተደጋጋሚ የምትመጣውም ለዚህ ይሆን?ለመጀመሪያ ጊዜ በ1977 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ወቅቱ በአገሪቷ ከፍተኛ ድርቅ የነበረበት ቢሆንም አብሬያት ከመጣኋት የሴት ጓደኛዬ ጋር በተወሰነ መልኩ ጉብኝት አድርጌ ተመልሻለሁ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የመጣሁት የህብረተሰብ ጤና ትምህርት በጥቁር አንበሳ ለመከታተል ሲሆን ኢህአዴግ መቀሌ ላይ በደረሰበት በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ እንደ አሁኑ አመጣጤ ሁሉ የህክምና እውቀቴን ለማዳበርና ለመከለስ እመጣለሁ፡፡ ሌላ ጉዳይ የለኝም፡፡

ኢትዮጵያ ተመችታሀለች?አዎ! ጥሩ ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንድ ባለጌዎችም አሉ፡፡ ብዙ ጓደኞች አሉኝ፡፡

የጥሩ ሰው መመዘኛህ ምንድን ነው?ጥሩ ሰው የሚታወቀው በረዥም ጊዜ ነው፡፡ በአጭር ጊዜ የሰውን ማንነት ማወቅ አይቻልም፡፡ ለረዥም ጊዜ ወዳጅ መሆን የሚችሉት ጥሩ እንደሆኑ እረዳለሁ፡፡

ባለጌዎች የምትላቸውስ...?በአሁኑ ጉዞዬ በአዋሽ መልካሳ ብዙ ባለጌ ወጣቶች አግኝቻለሁ፡፡ በመጀመሪያ ወር ከተጠጉኝ በኋላ የጥቅም ተስፋዬ ሲቋረጥ [ወይ አማርኛን ማቀላጠፍ አትሉም?] ሁሉም ሸሹኝ፡፡ ስለዚህም አሁን በዚያ ያሉ ጓደኞቼ ትልቅ ናቸው፤ ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ፡፡ ጥቁር አንበሳ ውስጥ የህክምና ትምህርት ስማርም ባለጌዎች ነበሩ፡፡ አይወዱኝም፣ ይሰድቡኛል፣ ሊጣሉኝ ይሞክሩም ነበር፡፡ ብዙዎቹ ኩራተኞች ናቸው፡፡ ደሀ ሰው ይንቃሉ፡፡ የእኔ ጓደኞች ያልተማሩና በትንንሽ የሥራ መደቦች ላይ የሚገኙ ስለነበሩ እነሱን ቅር ያሰኛቸው ነበር፡፡ አስተማሪዬ የነበሩት አንድ ዶክተር ሁልጊዜ እኔን ማባረር ይፈልጉ ነበር፡፡ ልታረቃቸው ፈልጌ ስጠይቃቸው ‹‹የህብረተሰብ ጤና (Community Health) በጣም ትልቅ

ይጋብዙኛል፡፡ አዲስ አበባ በማታ ያለው ቅዝቃዜ ይከብደኛል፡፡

በአዲስ አበባ ስትዘዋወር የምትጠቀመው የመጓጓዣ አማራጭ? ከድሮው አንፃር የአንበሳ አውቶብስ ዋጋ አራት እጥፍ ሆኗል፣ ታክሲ ደግሞ ሁለት እጥፍ፡፡ በብዛት ታክሲ ራቅ ወዳለ ቦታ ስለማይሄድ አንበሳ አውቶብስ እጠቀማለሁ፡፡ እንደ ሁኔታው የሁለቱም ተጠቃሚ ነኝ፡፡

ለምሳሌ 31 ቁጥር አውቶብስ ወዴት እንደምትሄድ ታውቃለህ? ከለገሀር ተነስታ ሽሮሜዳ፡፡ ከትላንት ወዲያ ሄጄባት ነበር፡፡ [ያነጋገርኩት ከ20 ቀን በፊት ነው] 1 ብር ከ35 ሳንቲም የከፈልኩ መሰለኝ፡፡ ጥበብ ገዝቼ መጥቻለሁ፡፡ [60 ቁጥር ወዴት እንደምትሄድም በጥርጣሬ ውስጥ ሆኖ በትክክል መልሷል፡፡ ‹‹...ረዥም የምትሄድ መሰለኝ- ደብረዘይት›› በማለት፡፡] አሜሪካ መኪና የሌለው ሰው የሚጠቀመው አውቶብስ ነው፤ በሚኒ ባስ አንሄድም፡፡ እዚያ የራሳችንን ዕቃ እንሸከማለን፡፡ እዚህ አገር ጤነኛ ሰው ለትንሽ ልጅ ገንዘብ ሰጥቶ ያሸክማል፡፡ እዚህ መሸከም ክብረ-ነክ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ በእኛ አገር ግን ተቃራኒ ነው፤ ክብር የሚነካው ጤነኛ ሰው ዕቃ ቢያሸክም ነው፡፡ [ምላሽ የሰጠው በመብሰክሰክ ስሜት ውስጥ ነው፡፡ እኔ አማርኛን ሲቀነጥስ በመገረም እስቃለሁ፡፡ በዚህ መሀከል ኮቱን ገልጦ ወደ ቀኝ ጎኑ እጁን በመስደድ አከከ፡፡ ቀጣዩ ጥያቄዬም ተወለደ፡፡]

የሚያሳክክህ ምነው... አልታጠብክ ይሆን? ዛሬ ጠዋት አልታጠብኩም፡፡ ትላንት ግን ታጥቤያለሁ፡፡ ለምን እንደሚያሳክከኝ እኔንጃ፡፡ እዚህ አገር ማከክ ነውር ነው

አራት ልጆችና ዘጠኝ የልጅ ልጆች ያሉት ይህ አሜሪካዊ፣ ኢትዮጵያን ደጋግሞ ጎብኝቷል፡፡ አማርኛ ‹‹አቀላጥፎ››

ይናገራል፤ እየተኮለታተፈም ለማንበብ ይሞክራል፡፡ በፈረንጅ አፍ የሚጠቀመው መግለፅ ሲከብደው ብቻ ነው፡፡

‹‹ግብዣ በጣም እወዳለሁ›› ከሚለው አዳም ሴልስ (ዶ/ር) ጋር አንድ አፍታ ቆይታ ያደረገው አቤል ዓለማየሁ በዚህ

ቃለ-ምልልስ ከመዝናናትዎም በላይ ‹‹ወቸ ጉድ!›› እያሉ ከራስዎ ጋር የሚያነፃፅሩት ነገር መኖሩን ያምናል

የወር ወጪው ብር የማይሞላው አሜሪካዊ - በኢትዮጵያ

100

ወደ ገፅ 16 ዞሯል

አሸናፊ ከበደን ለመታደግ የሙዚቃ ኮንሰርት ይካሄዳል

ለድምፃዊ አሸናፊ ከበደ የገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን ‹‹የዓመቱ ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት›› የተሰኘ ዝግጅት ነገ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ ምሽት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሸን ማዕከል ይቀርባል፡፡ በዝግጅቱም ላይ ድምፃዊያን አለማየሁ እሸቴ፣ ተሾመ ወልዴ፣ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ፍቅር አዲስ ነቃ-ጥበብ፣ ዳዊት መለሰ፣ ዳዊት ፅጌ እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ ድምፃዊያን ከዳዊት ባንድ ጋር ያቀነቅናሉ፡፡ ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ እና ክበበው ገዳም ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የዝግጅቱ አስተባባሪ ዳዊት ፅጌ ጉዳዩን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ የአዳራሽ ኪራዩን የሚሸፍኑት አቶ አብይ ወርቁ የተባሉ ድምፃዊውን ይረዱት የነበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡

ድምፃዊ አሸናፊ ከበደ ለሦስት አመት ከስድስት ወር ያህል በህመም ላይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አገግሞ ዳዊት ባንድ በነፃ ያሳተመለትን አዲስ አልበም አውጥቷል፡፡ በዝግጅቱ ላይም አዳዲስ ስራዎቹን ይዞ እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡ የመግቢያ ዋጋው 25 ብር ነው፡፡

‹‹ያ ልጅ›› ፊልም ይመረቃልሳንቶስ ፊልም ፕሮዳክሽን ያቀረበው እና ሀኒባል አበራ ፕሮዲውስ

ያደረገው፣ በበሀይሉ ዋሴ ተደርሶ እና ተዘጋጅቶ የቀረበው ‹‹ያ ልጅ›› ፊልም ከነገ በስቲያ- መጋቢት 12 ቀን ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት በአዲስ አበባ ብሔራዊ ቴአትር፣ በናዝሬት ሞርሞር ሲኒማ፣ በባህር ዳር ሴባስቶፖል ሲኒማ፣ በዱባይ ሸራተን ሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተመሣሣይ ሰዓት እንደሚመረቅ ሳንቶስ ፊልም ፕሮዳክሽን አስታወቀ፡፡

‹‹ያ ልጅ›› አዝናኝ የፍቅር ፊልም 1፡41 ርዝመት ያለው ሲሆን 315 ሺህ ብር እንደወጣበትና ማክዳ አፈወርቅ፣ አኒባል አበራ፣ ፍቅርተ ዳሳለኝ፣ ሚካኤል ታምሬ፣ ሄኖክ በሪሁን እና ሌሎችም ተዋንያን እንደተሳተፉበት ፕሮዳክሽኑ ገልጿል፡፡

‹‹ድንግል ነሽ ይላሉ›› መድብል ይመረቃል

የአርቲስት መርዓዊ ስጦት ልጅ የሆነችው አቢ መርዓዊ የፃፈችው ‹‹ድንግል ነሽ ይላሉ›› የግጥም መድብል ዛሬ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በኢትዮጰያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡

ምራኤል ተማሪዎቹን ያስመርቃልምራኤል ኢንተርናሽናል የአስተሳሰብ ለውጥ እና የስኬት ትምህርት

ቤት ያሰለጠናቸውን ከ40 በላይ ‹‹አሸናፊ ተማሪዎች›› ዛሬ ከቀኑ 8፡00 በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ያስመርቃል፡፡

እድሜያቸው ከ14-67 ዓመት የሚደርሱ ሰልጣኞች ህይወታቸውን እንዴት እንደሚመሩ እና በአገራችን እንዴት ለውጥ እንደሚያመጡ ከፍተኛ ስልጠና እንደተሰጣቸው ምራኤል አሳውቋል፡፡

Page 14: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 200314

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በሊሙ ኮሳ ወረዳ ከሳምንት በፊት በአክራሪ ሙስሊሞች ቅዱስ ቁርአን ተቀደደ በሚል በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት መድረሱን እና በጥቃቱም የወረዳ አስተዳደር አካላት መሳተፋቸውን ረቡዕ የወጣው ሳምንታዊው ሰንደቅ ጋዜጣ አስነብቦናል፡፡ ይኸው ድርጊት ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት በዚሁ በጅማ ዞን በበሻሻ አካባቢ በሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ተፈጽሟል፡፡ ነገ ደግሞ ተረኛው ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋራ በማኅበራዊ ኑሮ በመተባበርና በመከባበር በሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ላይ ላለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ይህ ደግሞ ወቅት እየጠበቀ የሚከሰትና ቀጣይነት የሚኖረው ከሆነ አገሪቱን እንደ አገር፤ ሕዝቧን እንደ ሕዝብ የሚፈታተን ተቀጣጣይ አደጋ ይሆናል፡፡ የሃይማኖት እኩልነት እና ነፃነት ፅንሰ-ሀሳብ ምንነት ከዓለም አቀፍ ሕግጋትና ከሀገራችን ሕጎች አንፃር መረዳት ለችግሩ መፈታት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ይኖረው ከሆነ ይኸው፡፡ሃይማኖት ብዙ ይዘትና ትርጉም ቢኖረውም ዋናውና መሠረቱ እግዚአብሔርን በእውነት አለ ብሎ ተጨባጭ ወይም ቁሳዊ ማረጋገጫ ሳይኖር ክስተቱን በልብ መቀበል ነው፡፡ ይህንም በቃል መመስከር፣ በግብር መግለጽም ነው፡፡ የትኛውም ሰው በሚኖርበት ማኅበረሰብ ሃይማኖቱን ሊፈጽም የሚችለው በነፃ ኅሊና አውጥቶና አውርዶ አስቦ አእምሮው የፈቀደለትን ያህል ሲረዳ ነው፡፡ ሃይማኖት እንደየ ግለሰቡ እና የማኅበረሰቡ የአስተሳሰብ ሁኔታ በትምህርት፣ በፍላጎትና በነፃ ኅሊና በሚኖረው ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ እንጂ መንግሥት ወይም ግለሰብ በሚያወጣው ሕግና በኃይል በማስገደድ አንድን ሃይማኖት ማጥፋትና ሌላውን ማስፋፋት አይቻልም፡፡ ሁሉም ሃይማኖት በየራሱ የገነባው መንፈሳዊ እሴት ቢኖረውም አንዱ ከሌላው ጋር የሚኖረውን ማኅበራዊ ምሉዕነት (integrity) አይቃረን ይሆናል፡፡ በተለይ በብዝኃ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ውስጥ ሊኖረው የሚገባው ማኅበራዊ ምሉዕነት በግዳጅ ‹‹የእኔን ብቻ›› ተቀበል የሚባል ከሆነ ታላቅ አደጋ ነው፡፡ ማኅበራዊ መስተጋብሩን ከመጉዳቱም በላይ አገራዊ ችግር ወደመሆን ሊሸጋገር ይችላል፡፡ ስለሆነም ማንም የራሱን ሃይማኖት እና ሃይማኖታዊ ዕሴቶች ትክክል ነው ብሎ ለሌላውም መግለጽ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሁሉም ሃይማኖቶች ትክክል አይደሉም በሚል የሌላውን ሃይማኖት ለመጫን መነሳት ተገቢ አይደለም፡፡ አንዱ ባለው መረዳትና ዕውቀት የእርሱን ሃይማኖት ብቸኛው የእውነት መንገድ አድርጎ መውሰድ መብቱ ነው፡፡ ነገር ግን ይኽን አስተሳሰቡን በአጋጣሚ ባገኘው ኀይል በመመካት የሌላውን በማንቋሸሽ ለጊዜው ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ መብትና አግባብ ግን ሊሆን አይችልም፡፡ ፈጣሪ ለሰው ልጅ ሁሉ የሰጠውን ውዴታና የአእምሮ ነፃነትን የሚገፋ ኢ-ሕጋዊ ግብር ነው፡፡ሃይማኖት በብዝኃ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ውስጥ በራሱ የግጭት መንሥኤ አይሆንም፡፡ ነገር ግን የግጭት ሰለባ የሚሆንባቸው ዕድሎች ሰፊ ናቸው፡፡ ብዙን ጊዜ ሃይማኖትን ለግጭት ሰለባ የሚያደርጉ ኹነቶች በሙሉ ከሃይማኖታዊ አስተምህሮ ውጪ የሆኑ ናቸው፡፡ ሁሉም ሃይማኖት ከሚመራበት አስተምህሮ ከመሠረታዊው የሃይማኖት እሴት እንዲሁም ከሃይማኖት እኩልነት መርሆች አንፃር ራሱን መመልከቱ ለብዝኃ ሃይማኖት ተከባብሮ መኖር ማለፊያ ነው፡፡ይኽም ጽሐፍ ከዚህ አኳያ ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ይሞክራል፡፡ የመጀመሪያው ሁሉም ሕግ አውጪ፣ አስፈፃሚና ተርጓሚ ኃላፊነታቸውን በምን አግባብ መወጣት አለባቸው? የሚለውን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በብዝኃ ሃይማኖት ውስጥ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አንፃር የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት ከሕግ አንፃር በምን አግባብ መፈታት አለበት የሚለው ነው፡፡

1. የሃይማኖት እኩልነትየእኩልነት ፅንሰ-ሀሳብ የመንግሥተ ሕዝብ /democracy/ ፅንሰ-ሀሳብ መሠረት ነው፡፡ የእዚህ ፅንሰ-ሀሳብ መሠረት የሃይማኖት ፅንሰ-ሀሳቦች ከሚመሠረቱባቸው ‹‹የሰው ዘር በተፈጥሮው እኩል ነው›› ከሚለው ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ሰው ከሥነ-ሕይወት ቅርጽ አንፃር ሲታይ /ሁሉም ሰው/ እኩል ቅርጽ ይዞ አይታይም፡፡ አንዱ አጭር፤ ሌላው ረዥም፤ አንዱ ጥቁር ሌላው ነጭ፤ ወዘተ የመሆን ጠባይንና ሌሎች ተመሳሳይ ልዩነቶች ይዞ እንደሚወለድና ሆኖም እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ እንዲሁም ሰዎች በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ዘንድም የምጣኔ ሀብት፣ የማኅበራዊ ኑሮ እኩልነት፣ የሥነ-ልቡናና የሥነ ምግባር ልዩነት በግልጽና በተጨባጭ ሁኔታ ይታያል፡፡ስለዚህ የሰዎች በሥነ-ሕይወት እና በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ባላቸው ደረጃ እኩል ያለመሆን በተፈጥሮአቸው እኩል መሆናቸውን አያሳጣም፡፡ ‹‹በሕግ ፊት እኩል መሆናቸው መረጋገጥ አለበት›› ከሚለው ንድፈ-ሀሳብም ጋር ተቃርኖ /ተቃራኒ ነገር/ የለበትም፡፡ በአጠቃላይ በሥነ-ሕይወት ቅርጽ እኩልነት የለም ማለት በሰዎች መካከል በሕግ ፊት እና በዜግነት እኩል አለመሆንን አያስከትልም፡፡ የሰው ልጅ ከዚህ ተፈጥሮአዊ እኩልነት የተነሣ በሕግ ፊትና በሕግ እኩል መሆኑን በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሥነ-መንግሥት ፈላስፋ የሆነው ሩሶ /Rouseau/ እኩልነት ከሰዎች የተፈጥሮ መብቶች አንዱ መሆኑን አመልክቷል፡፡ የዚህ ሰው ንድፈ-ሀሳባዊ ትንታኔም ለአሜሪካ የነፃነቶች መግለጫዎች እና ለፈረንሳይ የሰውና የዜጋ መብቶች መግለጫ መሠረታዊ ምንጭ ሆኖ አገልግሏል፡፡ እነዚህ መግለጫዎች በሙሉ ሰዎች ሁሉ እኩል ፍጥረቶች መሆናቸውን፤ ከፈጣሪያቸውም ዘንድ የማይወገዱ መብቶችን መጎናጸፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ /Declaration of independence - (መቅድም)/ መግለጫዎቹም ለሌሎች ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌዎች መታወጅ በኋላም በተከታታይ የተደነገጉ የዓለም አቀፍ ሕግጋት እና ሕግጋተ መንግሥት ‹‹በሕግ ፊት እና በሕግ እኩልነትን›› አካትተው እንዲይዙ አድርገዋል፡፡ ይኽ ዓይነቱን የሕግ አስተሳሰብ የሕግ ማዕቀፍ አካል ካደረጉ ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ሀገራችን ናት፡፡ ይኽንንም ከሕገ መንግሥቶቻችን፣ ከወንጀል ሕግና ከፍትሐ ብሔር ሕጎቻችን ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ እኩልነትን አስመልክቶ በኢትዮጵያ በ1948፣ 1980 እና 1987 ዓ.ም ሕገ መንግሥት ማንም ሰው በሕግ ፊት እኩል መሆኑ ተደንግጓል፡፡ /የኢትዮጵያ 1948 ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37፣ 38፣ - የ1980 ሕገ መንግሥት አንቀጽ 36 (1)፣ (2) - የ1987 ሕገ መንግሥት አንቀጽ 25/ ይኽም እኩልነት በዘር፣ በብሔር፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሀብትና በትውልድ ብቻ ሳይሆን በሃይማኖትም ጭምር መሆኑን ሕግጋቱ አካተው ይዘዋል፡፡ የ1997 ዓ.ም የወንጀል ሕግም የሰውን የማኅበራዊ ኑሮ ደረጃ፣ ዘርን ወይም የሃይማኖትን ልዩነት ሳያደርግ በሁሉም ሰው ላይ በትክክል እንደሚፈጸም ሲደነገግ፣ የ1952 ዓ.ም ፍትሐ ብሔር ሕግ ደግሞ ማንኛውም ሰው በሰብዓዊ መብት የመጠቀም መብትና በኢትዮጵያ

ሕገ መንግሥት የተመለከተው የሰው ልጅ ነፃነት የተረጋገጠ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ይኽም መብት የሃይማኖት ልዩነት እንደማያደርግ ይገልጻል፡፡ /የወንጀል ሕግ ቁጥር 4፣ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 8/ ስለዚህ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ ምንም ዓይነት የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግበት ከሌሎች ጋር በሕግ ፊት እኩል መሆኑ ወይም የሕግ ጥበቃ መብት ያለው መሆኑ ስለመረጋገጡ እነዚህ ሕግጋት ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡ በየሕገ መንግሥቱ ተቀርጾ የሚገኘው የሃይማኖት እኩልነት፣ የምጣኔ ሀብትና የማኅበራዊ አመጣጥ ደረጃን እኩልነት የሚመለከት ሳይሆን በሕግ ፊት እኩልነትን የሚመለከት ነው፡፡ ይኽ ዓይነቱን ሕገ መንግሥታዊ እኩልነት በሁለት መልኩ መመልከት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው በሕግ ፊት እኩልነት ሲሆን ሁለተኛው የሕግ እኩልነት /የመብት እኩልነት/ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ሕገ መንግሥታዊ የሃይማኖት እኩልነት አተረጓጐማቸውና አፈጻጸማቸው በብዝኃ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ውስጥ ጥንቃቄ የሚያሻቸው በመሆናቸው አተረጓጐማቸውንና አፈፃጸማቸውን ከእኩልነት መሠረታዊ ዐውድ አኳያ መመልከቱ እጅግ ጠቃሚ ስለሚሆን በአጭሩ እነሆ፡፡

1.1 በሕግ ፊት የሃይማኖት እኩልነት /Equality before the Law/በሕግ ፊት የሃይማኖት እኩልነትን ማረጋገጥ በቀጥታ የሚመለከተው ሕግ አውጪውን አካል ሳይሆን ሕግ ተርጓሚውንና አስፈጻሚውን አካል ነው፡፡ ምክንያቱም የሃይማኖት እኩልነት የመረጋገጡ እውነት የሚታየው ሕግ አውጪው ሕግ ሲያወጣ ሳይሆን በሕግ አተረጓጎምና አፈጻጸም ብቻ ስለሚሆን ነው፡፡ የሃይማኖት እኩልነት መርሕ ሊጠበቅና ሊከበር የሚችለው በእነዚህ አካላት አማካኝነት ነው፡፡ ይኽ ማለት ግን በሕግ አተረጓጎምና አፈጻጸም ዙሪያ ሕግ አውጪውን በቀጥታ አይመለከተውም ለማለት እንጂ ጭራሹኑ አያገባውም ማለት አይደለም፡፡በሀገራችንም ሆነ በሌሎች ዓለማት ሕግጋተ መንግሥት ላይ የሚገኙት የሃይማኖት እኩልነት መርሆዎች የሕግን ማስፈጸም ተግባርና ግዴታ የሚመለከት ነው፡፡ የአስተዳደርና የዳኝነት አካላት ምንም ዓይነት ልዩነት ሳያደርጉ ለሁሉም ሃይማኖት እና ተከታዮች ሕግን በእኩልነት የማስፈጸም፣ የመተርጎም ተግባርና ግዴታ ነው፡፡ በሕግ ፊት የሃይማኖት እኩልነት በሚቀመጥበት ቅርጹ አዘውትሮ የሚተረጎመው በፍርድ ቤት በሚደረግ የፍርድ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ነው፡፡ ይኽም በእኩል የሚጠበቀውን የሥነ-ሥርዓት እኩልነት /procedural equality/ አስመልክቶ ነው፡፡ ከዚህ አልፎ ግን የየትኛውንም ሃይማኖት አስተምህሮ እና ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ ግንኙነት እኩልነትን አያረጋግጥም፡፡ ስለዚህ ሃይማኖቶች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ናቸው ሲባል ከዚህ አንጻር መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በብዝኃ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ውስጥ ሁሉም ሃይማኖቶች በሕግ ፊት እኩል ናቸው ሲባል በሃይማኖታዊ ቦታዎች ሥርጭት እኩል መሆን አለባቸው የሚል አይደለም፡፡ ለምሳሌ በሐረር ጀጎል ግንብ ውስጥ ሦስት መቶ መስጊዶች ሲኖሩ አንድ ቤተክርስቲያን አለ ይባላል፡፡ ይኽ ማለት ግን ባለ አንዱ ቤተክርስቲያንን ከባለ ሦስት መቶ መስጊድ በሕግ ፊት

እኩል አይደለም ማለት አይደለም፡፡ በሌላ አገላለጽ የባለ አንድ ቤተክርስቲያን መብት በሕግ ፊት ለማረጋገጥ የባለ ሦስት መቶ መስጊድ ባለቤትን እድገትም መግታት ሳይሆን ሕጉ የሚፈቅደውን ዕድል በሕግ አተረጓጎም አለማፈን ነው፡፡ከዚሁ ጋር በተያየዘ አንድ ምሳሌ መጨመር ይቻላል፡፡ ይኽውም የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች ወንጀል ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡ በሕጉም መሠረት ሕግ አስፈጻሚውና ተርጓሚው ሕጉን ማስፈጸምና መተርጎም ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነዚህ አካላት ለማመጣጠን ወይም የሌላኛው ቤተ እምነት ቅር ሊሰኝ ይችላል በሚል ብቻ የሌላውን እምነት ተከታይ ወንጀለኛ አድርገው ቢያቀርቡ በሕግ ፊት የሃይማኖት እኩልነት አረጋገጡ ሳይሆን ሕግ ጣሱ ነው የሚባለው፡፡ ማመጣጠን ማለት በሕግ ፊት እኩል መሆን አይደለምና፡፡

1.2 የሕግ እኩልነት /Equality of Law/ይኽ የእኩልነት መርሕ የሚመለከተውና የሚሠራው አስቀድመን እንደተመለከትነው ሕግን የማስፈጸምና የመተርጎም ሥልጣን የተሰጣቸውን የመንግሥት አካላት ብቻ ሳይሆን ሕግ አውጪውን አካል ጭምር ነው፡፡ ሕግ አውጪው በብዝኃ ሃይማኖት ውስጥ ሕግ በሚያወጣበት ወቅት ሁሉንም ቤተ እምነታት ተጠቃሚ የሚያደርግ ሕግ እንዲያወጣ የሚያስገድድ መርሕ ነው፡፡ ይኽ የሕግ እኩልነት መርሕ በሃይማኖቶች መካከል እኩል አለመሆንን ለመፍጠር ወይም ለአንድ ሃይማኖት የተለየ የተጠቃሚነት ዕድልን ለመስጠት የሚያስችል ሕግን ለመደንገግ ሕግ አውጪው ሥልጣን እንደማይኖረው የሚያሳይ መርሕ ነው፡፡ሕግ አውጪው የመንግሥት አካል አንዱን ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት ወይም እርሱ ተከታይ የሆነበትን ሃይማኖት ለመጥቀም የሚያስችል የሕግ ድንጋጌ እንዲኖር ማድረግ እንደማይችል የሕግ እኩልነት መርሕ ዕግድ ይጥላል፡፡ በዚህ መርሕ መሠረት የሁሉንም ሃይማኖቶች እኩል ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ እንጂ አንዱን ብቻ ለመጥቀም ሲባል የሚወጣ ሕግ አይኖርም፡፡በመሆኑም የየትኛውም ሃይማኖት ተከታዮች የሕግ እኩልነት /Substantive equality/ መርሕ ተጠቃሚዎች ለመሆን በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ ያላቸው ቁጥር መብዛትና ማነስ እንቅፋት ሊሆን አይችልም፡፡ ሕግ አውጪውም አካል ሕጉን በሚያወጣበት ወቅት በብዙኃኑ ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የሃይማኖት ተከታዮችን ተጠቃሚነትም በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን እንዳለበት መርሁ ያስገድዳል፡፡ በሕግ እኩልነት መርሕ መሠረት በማኅበረሰቡ ውስጥ አብላጫ የምዕመን ቁጥር ያለው ቤተ እምነት ብቻ አምልኮውን የሚፈጽምበት ቦታ እንዲያገኝ፣ ወይም በማኅበረሰቡ ውስጥ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ቤተ እምነታት /Minority Religions/ በሃይማኖታቸው እንዳያምኑ ወይም አምልኮአቸውን እንዳይፈጽሙ ማድረግ ተቀባይነት የለውም፡፡ /የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀጽ 27/ ለምሳሌ ከአፋር ሕዝብ ውስጥ 95.3% ሙስሊም ነው፡፡ ቀሪው 3.9% ደግሞ ክርስቲያን ነው፡፡ ከቁጥር ስብጥሩ አንፃር አብዛኛው ሕግ አውጪ፣ አስፈጻሚና ተርጓሚ ሙስሊም መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ እንዲሁም ደግሞ ከትግራይ ማኅበረሰብ ውስጥ 95.6% ኦርቶዶክስ ሲሆን ቀሪው 4% ደግሞ ሙስሊም ነው፡፡ /Summary and statistical Report of the 2007 population and housing census Results. Pp.105-111/ አሁንም ከዚህ የፐርሰንት ስብጥር አንጻር አብዛኛው ሕግ አውጪ፣ አስፈጻሚ እና ተርጓሚ ኦርቶዶክስ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር አይኖረውም፡፡ ይኽ ዓይነቱን የፐርሰንት ስብጥር በሕግ እኩልነት መርሕ መሠረት ስንመለከት የአፋሩ 95.3% ሙስሊም ከ 3.9% ክርስቲያን እንዲሁም የትግራዩ 95.6% ኦርቶዶክስ ከአራት በመቶ ሙስሊም በሕግ ፊትና የሕግ ጥበቃ በማግኘት ረገድ እኩል ናቸው፡፡ ሕግ አውጪም ሆነ ሕግ አስፈጻሚውና ተርጓሚው ተግባሮቻቸውን እንዲያከናውኑ የሚጠበቀው በዚህ መርሕ ነው፡፡ በዚህ መርሕ መሠረት የቁጥር

መብለጥና ማነስ ለብዝኃ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ችግር አይሆንም፡፡ ችግር የሚሆነው ይኽን መርሕ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሕግ የአንድን ሃይማኖት ብቻ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሞከረ ዕለት እና አስፈጻሚውና ተርጓሚውም ለአድሎአዊ አሠራር ሰለባ ከሆኑ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም በብዝኃ ሃይማኖት ማኅበረሰብ የሃይማኖትን እና የሃይማኖት ተከታይን ቁጥር መብዛትና ማነስ ልዩነት ሳያደርግ የሕግ እኩልነትንና ተጨባጭ የሕግ ጥበቃን ማረጋግጥ ከተቻለ ለማኅበረሰቡ ሁለንተናዊ አኗኗር ማለፊያ ነው፡፡ /የሰብአዊ መብቶች ሁሉ አቀፍ መግለጫ አንቀጽ 7 እና የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀጽ 26/

2. የሃይማኖት ነፃነትነፃነት አንድ ሰው የሌሎችን ነፃነትና መብት እስካልነካና እስካልደፈረ ድረስ የሚፈልገውን ማድረግ መቻሉ ነው፡፡ አንድ ሰው የሚፈልገውን ማድረጉ ነፃነቱ ሲሆን የሌሎችን ነፃነት ማክበሩ ደግሞ ግዴታው ነው፡፡ የአንዱ ሰው ነፃነት የሌላው ሰው ነፃነት ከሚጀምርበት ያቆማል፡፡ይኽ መሆኑ ደግሞ ነፃነትን ስድና ገደብ የለሽ ሳይሆን የፈለጉትንና የተመኙትን ለማድረግ ያለመቻል ፅንሰ-ሀሳብ ያለበት መሆኑን አመላካች ነው፡፡ ምክንያቱም የአንድ ሰው ነፃነት የሌላው ሰው ግዴታ፤ የሌላው ሰው ግዴታ የአንድ ሰው ነፃነት ነው፡፡ ስለዚህ ነፃነት ከግዴታ ተለይቶ ሊኖር አይችልም፡፡ የአንዱ መብት የሌላውን መብት ይገድባል፡፡ የአንድ ግለሰብ ነፃነት ዳር ድንበሩን ሊያልፍና የሌላውን ነፃነት ሊነካ ስለሚችል ዳር ድንበሩ በሕግ ይወሰናል፡፡ ነፃነቱም በዚያ የሕግ ማዕቀፍ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በየትኛውም ቦታ የመዟዟር መብቱ ሰብዓዊና ሕጋዊ መብቱ ነው፡፡ ይኽ ሰው ግን የመዟዟር መብቱን ተጠቅሞ ሌላ ሰው ግቢ ገብቶ ቢዘዋወር ወንጀለኛ ነው፡፡ እርሱ የግለሰቡን የመኖሪያ ቤት አለመደፈር መብት ሊደፍር ችሏልና፡፡ ነፃነት ገደብ አለው ሲባል አንዱ ከዚህ አንፃር ነው፡፡ የሃይማኖት ነፃነትም ከዚሁ የነፃነት ዓይነት የሚደመር ነው፡፡ የሃይማኖት ነፃነት ሲባል ማንኛውም ሰው በአንድ ሃይማኖት ለማመንና ይኽንኑ ሃይማኖት ለማስፋፋት፣ ሥርዓተ አምልኮትን በግልጽ ለመፈጸም እንዲሁም ደግሞ በምንም ዓይነት ሃይማኖት ላለማመንና ምንም ዓይነት ሥርዓተ አምልኮ ላለመፈጸም ያለው ነፃነት ነው፡፡የሃይማኖት ነፃነትና አጠቃቀም መብት በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን በሚመለከቱ ሰነዶችና በኢትዮጵያ በአለፉት ሕግጋተ መንግሥትና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥትም ተረጋግጧል፡፡ይኽውም የ1948 ዓ.ም ሕገ መንግሥት ይኽን ነፃነት ሲገልጽ ‹‹የሕዝብን መልካም ጠባይ ወይም ጸጥታን ወይም በፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት የሚኖሩ ሰዎች የሃይማኖታቸውን ሥርዓት አክብረው በነፃ ከመፈጸም አይከለከሉም›› /አንቀጽ 40/ በማለት ሲሆን የ1980 ዓ.ም ሕገ መንግሥት ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያውያን የኅሊናና የሃይማኖት ነፃነት የተረጋገጠ ነው፡፡ የሃይማኖት ነፃነት አጠቃቀም የሀገርንና የአብዮትን ደኅንነት እንዲሁም የሕዝብን መልካም ሥነ-ምግባርና የሌላውን ዜጋ ነፃነት የሚነካ መሆን የለበትም›› /አንቀጽ 47 (1)/ በማለት ነው፡፡ እንዲሁም 1987 ዓ.ም ሕገ መንግሥትም ይኽን መብት ያረጋገጠው ‹‹ማንኛውም ሰው የማሰብ የኅሊና እና የሃይማኖት ነፃነት አለው፡፡ ይኽ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ የመከተል የመተግበር የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል›› /አንቀጽ 27 (11)/ በማለት ነው፡፡ ይኽ ሕገ መንግሥት ከላይ ከጠቀስናቸው ሁለት ሕግጋተ መንግሥታት እጅግ ይለያል፡፡ ይኸውም የሕገ መንግሥቱ አብዛኛው ክፍል የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን አሟልቶ ከመያዙም ባሻገር የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ ሙሉ በሙሉ የሰብዓዊ መብቶች የዓለም አቀፍ መግለጫ /አንቀጽ 54/፣ የሲቪልና የፖለቲካ መብት ዓለም አቀፍ መግለጫና /አንቀጽ 19/፣ የአፍሪካ

የሃይማኖት እኩልነት እና ነጻነት በብዝኃ ሃይማኖት

በታደሰ ወርቁ

የ ህግ የ በ ላይ ነት

ነጻነት አንድ ሰው የሌሎችን ነጻነትና መብት

እስካልነካና እስካልደፈረ ድረስ የሚፈልገውን

ማድረግ መቻሉ ነው፡፡ አንድ ሰው የሚፈልገውን

ማድረጉ ነጻነቱ ሲሆን፣ የሌሎችን ነጻነት ማክበሩ

ደግሞ ግዴታው ነው፡፡ የአንዱ ሰው ነጻነት፣

የሌላው ሰው ነጻነት ከሚጀምርበት ያቆማል፡፡

Page 15: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 15

የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተርን መሠረት ያደረገ መሆኑም ጭምር ነው፡፡ ይኸው ሕገ መንግሥት እና እነዚሁ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱት ሰነዶች የሃይማኖት ነፃነት ሊገደብ የሚችልበትንም የሕግ አግባብ ይገልጻሉ፡፡ በእነዚህ ድንጋጌዎች ሁሉ የተጠቀሱት የሃይማኖት ነፃነት ተግባራዊነታቸውም በፍትሐ ብሔር ሕግም የተጠበቀ ነው፡፡ /የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 14/

3. የሃይማኖት ነፃነት የሚገደብበት የሕግ አግባብ

አስቀድመን እንደተመለከትነው መብቶች በባህርያቸው እርስ በእርሳቸው ይገዳደባሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በተለይ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ የእምነት ነፃነት ከመሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች አንዱ ቢሆንም የሚገደብበት ሁኔታ አለ፡፡ ይኽም የሕዝብ ደኅንነትን፣ ሰላምን፣ ጤናን፣ ትምህርትን፣ የሞራል ሁኔታንና የሌሎችን ዜጎች መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች ለመጠበቅ መንግሥት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ነው፡፡ /አንቀጽ 27 እና 28/ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 90 ንኡስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንም ሰው እምነቱን በግልም ሆነ ከሌሎች ጋር ለማስተማር እና ለመግለጽም እንዲሁም

የአንድ እምነት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን በነፃነት ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸውን የሃይማኖት ትምህርትና አስተዳደር ተቋማትን የማቋቋም መብት እንዳላቸው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 27 (2) ላይ ተደንግጓል፡፡የየትኛውም እምነት ተከታይ ከላይ የተገለጸውን መብት በመጠቀም የሚያደርገው የትኛውም እንቅስቃሴ የሕዝብን ጤና፣ ትምህርት፣ ደኅንነትና፣ ሰላም የማያናጋ እንዲሁም ምንም ጉዳት የማያደርስ ወይም የሌሎችን ዜጎች የእምነት ነፃነት መብት የሚጋፋ መሆን የለበትም፡፡ አንድ ሰውም ሆነ የእምነት ተቋም የራሱን እምነት ለማስፋፋት በሚያስተምርበት ወቅት ትምህርቱ የሌሎችን እምነት ተከታዮች ክብርና ሞራል የሚነካ ከሆነ የሌሎቹን የእምነት ነፃነት መብት ተዳፍሯል፡፡ ይኽ መሆኑ ደግሞ በሕዝብ መካከል ግጭት በማነሣሣት የሕዝብን ደኅንነትና ሰላም አስቀድመን እንደገለጽነው አደጋ ላይ ስለሚጥል በወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ የደፋሪውን የእምነት ነፃነትም የሚገድብበት የሕግ አግባብ አለ፡፡ይኽ የእምነት ነፃነት የሚገደብበት እና በወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትልበት የሕግ አግባብ በወንጀል ሕግም ተደንግጓል፡፡ ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን

ለማስፋፋት የሚዘጋጁ ጉባኤዎችን በቃል በማስፈራራት፤ በኃይልም ወይም በጉልበት ወይም በማንኛውም ዘዴ በማይገባ ሁኔታ መበጥበጥ ወይም ማወክ ቅጣትን ያስከትላል፡፡ /የወንጀል ሕግ አንቀጽ 490(1)/ከሕግ ውጭ በሆነ ሁኔታ የሕዝብን መሰብሰቢያ አደባባይ ወይም ለሕዝብ ክፍት በሆነ ስፍራ ወይም ሕዝብ ሊመለከትና ሊሰማ በሚችልበት ቦታ ላይ በንግግር ወይም በምልክት ሃይማኖትን ማስነወር ወይም የሚያስቅ የሚያስነውር ሁኔታን ማሳየት መሳደብ ወይም ክብርን በሚነካ ሁኔታ መናገር ወይም በማምለኪያ ምልክቶች፣ በሃይማኖት ሥርዓታት በሃይማኖት አገልጋዮች ላይ መናገር በምልክትም ሆነ በቃል ይህን የመሰለ የመናቅ የማዋረድ ተግባርን መፈጸም በሕግ እንደሚያስቀጣ ተደንግጓል፡፡ /የወንጀል ሕግ ተራ ቁጥር 816/ ሌላው የሃይማኖት ነፃነትን በመጠቀም የተፈቀደ የሃይማኖት በዓል ወይም የሃይማኖት ተግባር እንዳይፈጸም መከልከል፣ ለአንድ አምልኮ ወይም ለአንድ በዓል የተመረጠን የአንድ ሃይማኖት የግል ቦታ ወይም ሥዕል ወይም አንድ ሌላ ንዋየ ቅድሳትን በግልጥ ማርከስ፣ የሃይማኖት ስሜትን መንካትም እንዲሁ ያስቀጣል፡፡ /የወንጀል ሕግ ቁጥር 492 ሀ ና ለ/

ከዚሁ ከሃይማኖት ነፃነት ጋር በተያያዘ አንድ ሰው ወይም ተቋም የራሱን እምነት ለማስፋፋት በፕሬስ ውጤቶች ሊጠቀም ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በዚህ የፕሬስ ውጤት የሌሎችን እምነት ማንቋሸሽ አማኞቹንና የእምነቱን አስተማሪዎች ክብር መንካት በመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነት በአዋጅ ቁጥር 590/2001 ዓ.ም/ 85 አንቀጽ 39፣ 41 እና 45 ሥር በተደነገገው መሠረት ያስቀጣል፡፡እንግዲህ ማንም ሰው የመረጠውን እምነት በነፃነት የመከተልና የማስፋፋት ነፃነት ከዓለም አቀፍ እስከ ብሔራዊ ሕግጋት ገደብ የለሸ ወይም ፍጹማዊ ነፃነት አለመሆኑን ወይም በሕግ አግባብ የሚገደብበትን ሁኔታም ተመልክተናል፡፡የእምነት ነፃነት በሕገ መንግሥቱ ልዩ ቦታ ከተሰጣቸው መሠረታዊ የሰው ልጆች መብቶችና ነፃነቶች አንዱ እንደመሆኑ መጠን፤ መሠረታዊ መብቶችንና ነፃነቶችን በማመላከት የተደነገጉት የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ሀገሪቱ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕጎች፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችና የዓለም አቀፍ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም እንዳለበት የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 13 (2) ያስገድዳል፡፡ በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌደራል

መንግሥትና የክልል መንግሥት ሕግ አውጭ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ አካላት እነዚህን ሰብዓዊ መብቶች የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ ስለሆነም ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ቤተ እምነት ተከታዮች የሚኖሩባት ሀገር በመሆኗ የዚህ ሕግ አተረጓጎምና አፈጻጸም ጥንቃቄ ያሻዋል፡፡ ይኽ መኾኑ ደግሞ መሠረታዊ ጥቅሞች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ሕጉ ለሁሉም ዜጎች ዋስትና መሆኑን በየትኛውም ቤተ እምነት ተከታይ ዘንድ ማረጋገጥ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሁሉም ቤተ እምነቶች ተከባብረውና ተስማምተው እንዲኖሩ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው፡፡ የዚህ አዎንታዊ ውጤት በሀገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ የራሱ የሆነ በጎ አንደምታ ስለሚኖረው በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ራሳቸውን ከላይ ከጠቀስኳቸው የሕግ አግባብ አንጻር ማየት፣ መፈተሽና መገምገም ይኖርባቸዋል፡፡ የጅማውም ጥቃት በዚሁ መነጽር ሊታይ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ችግሩ Grigory Pomerants የተባለው ሩሲያዊው ፈላስፋ ‹‹The devil begins with Froth on the lips of an angel entering into battle for a holy and just cause›› ብሎ እንደገለጸው ነውና፡፡

ማስተዳዳር አይቻልም፡፡ በእርግጥ ተገቢ የሆኑ ቁጥጥሮች አይደረጉ አንልም፡፡ ነገር ግን የገንዘብ ፖሊሲው ካልተስተካከለ፣ የበጀት ፖሊሲው ካልተሻሻለ፣ የውጭ ምንዛሪ አካሄዱ በደንብ ካልታየና በዚህ ዙሪያ ጥብቅ ፖሊሲ ካልተወሰደ ችግሩ ይቀጥላል፡፡ በሌላ በኩል የምርት አቅርቦት ችግር መፈታት አለበት፡፡

የዋጋ ግሽበትና የኑሮ መወደድ ጉዳይ ለሰሜን አፍሪካው ቀውስ ሰበብ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በእኛ ሀገር ካለው ስር የሰደደ ድህነትና የኑሮ ውድነት ጋር የሚያመሳስለው ምንድነው?በጣም ብዙ ነገሮች ያመሳስሉታል፡፡ ለነገሩ የሚብሰው የእኛ ነው፡፡ ከዚያ በተጨማሪ ወደሥራ አጥነት ስንመጣ ሁኔታው አሳዛኝ ነው፡፡ ዛሬ እኮ አንድ ዜጋ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ጨርሶ ኮብል ስቶን ሥራ ሲሰራ እያየን ነው፡፡ ... ይኼ ደረጃውን የሚመጥን ሆኖ አይታየኝም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ሥራ አጥ ሆነዋል፡፡ እና መንግስት መፍትሄ ማምጣት አለበት፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ ነገሮች እየባሱ መሄዳቸው ያሳስበናል፡፡

ሰሞኑን ለየት ባለ ሁኔታ በኢሕአዴግ መንግስት በኩል እየተገለፁ ካሉት ነገሮች አንዱ የኤርትራ መንግስት ይወገድ የሚለው አቋም ነው፡፡ የኤርትራ መንግስት በወረራው ወቅት በትምህርት ገበታ ላይ የነበሩ ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በጨፈጨፈበትና በጦርነቱ በተሸነፈበት ወቅት እንኳ ሰፊ የማስወገድ ዕድል እያለ ያልተደረገውን ዛሬ ለምን አዲስ አጀንዳ ሆኖ መጣ? ገዢው ፓርቲ የቀድሞ ድርጅትዎ ከመሆኑም አኳያ ከሚያውቁት ባህርይው በመነሳት ቢመልሱልኝ? ... (እየሳቁ)፡፡ ጥሩ፡፡ ኢሕአዴግን በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ የሚከተላቸውን ስልቶችም አውቃለሁ፡፡ የስልቶቹ ዋንኛ ማጠንጠኛዎች ምንድናቸው ስንል ዋናውን አጀንዳ ሸሽቶ በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ሕዝብ እንዲያተኩር ነው የሚያደርገው፡፡ በሀገራችን ያሉ ዋና ጉዳዮችስ ምንድናቸው? አንዱ ስር የሰደደ የመንግስት ባለሥልጣናት ሙስና ነው፡፡ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ ሥራ አጥነት ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ የኑሮ ውድነት በሀገራችን ከፍተኛ ቦታ ይዟል፡፡ የሕግ የበላይነት ችግር ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ተሸማቀው ክብርና ነፃነት አጥተው እየኖሩ ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ ይህ ሆኖ እያለ ራሱ የሚፈጥረውን ችግር ለመሸፈን ሁልጊዜ አንድ አጀንዳ ቀርጾ የሕዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ያዞራል፡፡

አንድ ምሳሌ አያይዘው ቢጠቅሱልኝ?በምርጫው ወቅት የሆነውን ማየት እንችላን፡፡ መድረክን ‹‹ፀረ-ሕዝብ ነው፣ የጥፋት ኃይል ነው፡፡ የደርግ ኢሰፓ ስብስብ ነው›› የሚል የሌለና አቅጣጫ የሚያስት ፕሮፓጋንዳ ሲጠቀም ነበር፡፡ ሕዝቡን በማስደንገጥ መድረክ ቢመረጥ ሀገሪቱ እንደምትበጠበጥ ማስፈራራት ነበር፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው ረጋ ብሎ የፖሊሲና የመሰረታዊ ጥያቄዎችን አጀንዳ አያነሳም፡፡ የኢሕአዴግ ሥልት ሁል ግዜ ይኸው ነው፡፡ አንዳንዴ እኮ በአንዳንድ አካባቢዎች የሌለውን ጠላት ሳይቀር ‹‹ደርግ መጣላችሁ›› ይላል፡፡

ስለዚህ በኤርትራ ላይ እየተሰጡ ያሉት መግለጫዎች የዚሁ ድራማ አካል ናቸው ብለው ያምናሉ? ፍርሃት ለመፍጠር ነው፡፡ ‹‹ሻዕቢያ አዲስ አበባን ባግዳድ ሊያደርጋት ነው›› የሚል ሥልት ቀይሷል፡፡ ዓላማው ሕዝቡ ‹‹ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን›› እንደሚባለው ‹‹የባሰ አታምጣ›› ብሎ እንዲያስብ ነው እንጂ ሻዕቢያ ሀገራችንን ምንም ሊያደርጋት አይችልም፡፡ በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ወቅት ሆኑ እንደተባሉት ዓይነቶቹም ቢሆኑ በፀጥታ ክፍሉ ደረጃ ሊፈቱ የሚችሉ እንጂ ከፍተኛ የፖለቲካ ጉዳዮች አይደሉም፡፡ ሀገር ሊያናጉ አይችሉም፡፡

ለአንባቢዎቻችን የበለጠ ግልፅ እንዲሆኑ፣ በአመክንዮ አስደግፈው ቢያቀርቡልኝ?ዌል ... ሻዕቢያ እኮ አሁን በራሱ ችግር ውስጥ እየዳከረ ነው፡፡ መንግስት ራሱ ኤርትራ ውስጥ ባለው ችግር የኤርትራ ወጣቶች ሀገር ጥለው እየተሰደዱ ነው እያለ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሻዕቢያ የራሱን ችግር ሳይወጣ አዲስ አበባን ባግዳድ ያደርጋል ማለት የማይመስልና እርስ በርሱ የሚጣረስ ነው፡፡ በእርግጥ ሻዕቢያ የጸጥታ ችግሮችን ይፈጥራል፡፡ መፍጠሩንም ቀጥሏል፡፡ የሌሎች መሳርያ በመሆን የኢትዮጵያን መረጋጋት ከማይፈልጉ ኃይሎች ጋር ይሰራል፡፡ በሚባለው ደረጃ ሊሆን አይችልም እንጂ፡፡

በነገራችን ላይ፣ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ‹አሰና› ለተባለ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የሬዲዮ ጣቢያ በትግርኛ ሰፊ ቃለ-ምልልስ መስጠታቸው በተለያዩ ሜዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ተከታትለውት ከሆነ በተለይ ትኩረትዎን የሳቡት ነጥቦች የትኞቹ ናቸው?እንግዲህ በዚህ ቃለ ምልልሳቸው ‹‹አስመራ ቤተ-መንግስት ላይ ዝንጀሮ ቢኖርም፣ ከእሱም ጋር የሰላም ስምምነት እንፈራረማለን›› ብለዋል፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው የምፈልገው ‹‹የድንበር ኮሚሽኑ የኤርትራ የሆነ መሬት

ለኢትዮጵያ ሰጥቷል›› ብለው ከአንድ መሪ የማይጠበቅ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ዳኞቹ የእናንተ ነው ብለው የሰጡንን መሬት እሳቸው ግን ‹‹እኔ የኤርትራ መሆኑን የማውቀው መሬት ለእኛ ተሰጥቷል፡፡ እነ ጾረና ... ›› ብለው በኢትዮጵያ ላይ ምስክር ሆነው ቆመዋል፡፡

ሌላስ፣ ያስተዋሉት ነገር ይኖር

ይሆን?ተማፅኗቸውን ነው! እኔ የኤርትራ ወዳጅ ነኝ ከማለት አልፈው ከመጀመርያ ጀምሮ የዚያ አካባቢ ወዳጅ መሆናቸውን ደጋግመው ገልፀዋል፡፡ ‹‹አብረን እንስራ፣ እንጠቃቀም›› በሚለው ላይ አጠንጥነዋል፡፡

ይህ የጠ/ሚ/ሩ ‹‹የኤርትራ መሬት ለእኛ ተሰጥቷል ምስክርነት›› ወደፊት

በሀገራችን ላይ ችግር አይፈጥርም? ኤርትራውያኑ በመሪ ደረጃ የተሰጠውን ቃል ማስረጃ አድርገው ወደ ሕግ ሊሄዱ አይችሉም?በትክክል እንጂ፡፡ የኤርትራን መሬት እንመልስና ባድመን ስጡን የሚል መደራደሪያ ሁሉ አቅርበዋል፡፡ የዚህ ዓይነት ድርድር የለም፡፡ በመሰረቱ እኮ የአልጀርሱ ስምምነት በሻዕቢያ ተጥሷል፡፡ የ25 ኪሎ ሜትር የፀጥታ ቀጣናውን ሲጥስ ስምምነቱ ፈርሷል፡፡ ስለዚህ የትኛውም ፍርድ ቤት ኢ-ፍትሐዊ ውሳኔ ቢወስን አጋጣሚውን ተጠቅመን እኛም አንገዛበትም፤ መሬታችን ይመለስ ማለት እንችላለን፡፡ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ በኖርማላይዜሽን ስለመሬት ልውውጥ የድርድር ሃሳብ እያቀረቡ በሌላ በኩል ሻዕቢያ አዲስ አበባን ባግዳድ ሊያደርጋት ነው ማለት እርስ በርሱ የሚጣረስ ነው፡፡ የሰውን ቀልብ፣ የሰውን ኃሳብ የማስቀየር እርምጃ ነው፡፡

የመጨረሻ ጥያቄዬ፣ በውጭ ሀገር በሚገኙና ከሰላማዊ ትግል ውጭ ያሉ አማራጮችን የተሻሉ ናቸው ብለው በሚያራምዱ ወገኖች ላይ ይሆናል፡፡ ስኬታማ የሚሆኑባቸው መንገዶች ይኖራሉ ብለው ያምናሉ?እንግዲህ እኔ ከማምንበት የትግል ስልት ብነሳ ይሻላል፡፡ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በመሰረቱ ሀገር በቀል መሆን አለበት፡፡ ይህ ማለት ሕዝቡ በአማራጭነት ቀርቦለት በቀጥታ መሳተፍ አለበት፡፡ በእርግጥ በውጭ የሚገኙት በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በመሰላቸው መንገድ አይሳተፉ ወይም አያገባቸውም ማለት አይደለም፡፡ ዋንኛው እንቅስቃሴ መሆን ያለበት እዚሁ ነው፡፡ እውነት ነው፣ እዚህ ባለነው የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በርካታ እንግልቶች ይደርሳሉ፡፡ እንዲህም ሆኖ የትግሉ ማዕከል እዚህ ሆኖ የውጭው ደጋፊ እንቅስቃሴ ቢሆን የተሻለ ይሆናል፡፡

በትጥቅ ትግል አማራጭ ላይ አስተያየትዎ ምንድነው?እ ... (በሃዘኔታ ጥቂት ቆየት ብለው) ... እዚህም ላይ የተለወጠ ነገር ነው ያለኝ፡፡ በትጥቅ ትግል ሄዶ ዴሞክራሲን ማስፈን ይቻላል ወይስ አንድን በብረት የሚገዛ አምባገነን መንግስት አንስቶ በሌላ አምባገነን መተካት የሚለውን ትልቅ ጥያቄ ውስጥ አስገባዋለሁ፡፡ ከዚያ በላይ ግን ጤናማ የማይሆነው ከሻዕቢያ ጋር ተባብሮ ይህችን ሀገር አቃናሁ የሚለው ትንሽ ችግር ያለበት ይመስለኛል፡፡ ሰዎች የየራሳቸው ምርጫ አላቸው፤ ይህን አከብራሁ፡፡ የእኔ ብቻ ነው ትክክል ብዬ አላስብም፡፡ የሌሎችን ኃሳብና ዕምነት መናቅ ይሆናልና፡፡ የተሻለው መንገድ ግፉም፣ እንግልቱም፣ መከራውም፣ እስሩም ቢኖሩም በሕዝባችን መካከል መታገል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

‹‹ዜጎች በገዛ ሀገራቸው...

አንዱ ስር የሰደደ የመንግስት ባለሥልጣናት ሙስና ነው፡፡ ትልቅ ጉዳይ

ነው፡፡ ሥራ አጥነት ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ የኑሮ ውድነት በሀገራችን ከፍተኛ

ቦታ ይዟል፡፡ የሕግ የበላይነት ችግር ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ ዜጎች በገዛ

ሀገራቸው ተሸማቀው ክብርና ነፃነት አጥተው እየኖሩ ነው፡፡

Page 16: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

ሴት

16

እንዴ?[ቶሎ መመለስ ለካ ከባድ ነው?... ‹‹ነውር›› አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለሆነም እንደየሰዉ ይለያያል፡፡ እንደ ነውር የሚቆጥሩት አሉ...] ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ ትወዳለህ አሉ፡፡ ሰው ከጋበዘኝ ግብዣውን እቀበላለሁ፡፡ ነገር ግን በራሴ ገንዘብ አልጠጣም፡፡

አንተስ ሰዎችን ትጋብዛለህ?እምምምም... አንዳንድ ጊዜ ከአገሬ ስመጣ ጋብዛለሁ፡፡ አቅም ብዙ የለኝም፡፡

አሜሪካ የምትሰራው የት እና ምንድን ነው? ወህኒ ቤት ውስጥ የህክምና አገልግሎት እሰጥ ነበር፡፡ [ያወራነው ኢትዮጵያ ሆቴል ነው፡፡ እጄን ወደ ጎን እየቀሰርኩ...] ይህ መ/ቤት ምን እንደሚባል ታውቃለህ?መከላከያ ሚኒስቴር፡፡

የሚኒስትሩ ስም ማን እንደሚባልስ ታውቃለህ?ሰምቼ ነበር፡፡ ስልጤ ነው፡፡ ድሮ የአገር ውስጥ (የፌዴራል ጉዳይ) ሚኒስትር ነበር፡፡ ስሙ ተረሳኝ [አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ይባላሉ፡፡]...ስልጤ ነው አይደል?

ትክክል ነህ፡፡ [በጣም ሳቅኩኝ][ፈገግ እያለ] ለምንድን ነው የምትስቀው?

ብዙ ነገሮችን [የተፃፉም ሆነ ያልተፃፉ] ከኢትዮጵያዊያን በላይ ታውቃለህ፡፡ የምስቀውም ገርሞኝ ነው፡፡ እሺ! ያኔ የብጥብጡ ጊዜ (በምርጫ 97) እዚህ ነበርኩ፡፡ የበፊቱ ወርዶ እሱ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሆነ፡፡ አሜሪካ እያለሁ ነው የመከላከያ ሚኒስትር የሆነው፡፡

በፈረንጅ አፍ ‹‹አንቱ›› የሚል ቃል የለም፡፡ በአገራችን ግን ትልቅ ሰው ‹‹አንቱ›› ብለን እንጠራለን፤ የአክብሮትም ነው፡፡ አንተ ደግሞ አማርኛ ትችላለህና ይህን ተለማምደሀል?ባህሉን በደንብ ባላውቀውም ላለመሳሳት እሞክራለሁ፡፡ እዚህ አገር ሰውየው ዶክተር ከሆነ ከሥራ ውጪ ‹‹ዶክተር›› እየተባለ ይጠራል፡፡ አሜሪካ ግን ከሥራ ውጪ ማንም ሰው በሙያ ስሙ አይጠራም፡፡ አዋሽ መልካሳ እኔን የሚጠሩኝ በስሜ ስለሆነ ዶክተር አልመስላቸውም፡፡ ትልቅ ሰዎች ግን ‹‹ዶክተር አደም›› ይሉኛል፡፡

እዚህ (ኢትዮጵያ) በእድሜ ከእኔ በታች ያለ ሰው መልኩ ታላቄ ለሚመስል ‹‹እርስዎ›› እላለሁ፡፡ በኋላ ሳውቅ ግን አርማለሁ፡፡

በህይወትህ ደስተኛ ነህ?አዎ! በጣም፡፡ በተለይ እዚህ ስኖር በትንሽ ገንዘብ መንቀሳቀስ ስለምችል፤ ሳልሰራ መኖር ስለምችል ደስ ይለኛል፡፡ በወር ከአንድ መቶ ብር በላይ አልፈጅም፡፡ አዋሽ መልካሳ ስኖር በወር ከ6 ዶላር በላይ አላወጣም፡፡ ስድስት ዶላር ብቻ? [ከእሱ ጋር ባወራን ወቅት ስድስት ዶላር የነበረው ምንዛሪ 100 ብር አይሞላም ነበር፡፡ አሁን 100.8 አካባቢ ሆኗል] አዎ! ለቤት ኪራይ 80 ብር እከፍላለሁ፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ ይጋብዘኛል፡፡ አቅም ስለሌለኝ ብዙ ወጪ አላወጣም፡፡ የምዝናናው ከሰዎች ጋር በማውራት ነው፡፡ ሌላ ፈረንጅ ከስድስት ዶላር በላይ እንደሚያወጣ አውቃለሁ፡፡ በቀን ስንቴ ትመገባለህ?ሲጋብዙኝ እበላለሁ፡፡ አዲስ አበባ የማርፍበት ዶ/ር ነጋሽ ረዘነ ጋር በቀን ሦስቴ እበላለሁ፡፡ አዋሽ መልካሳ... በጣም አላጠናሁትም ግን በቀን አንደ ጊዜ ብቻ መብላት እችላለሁ፡፡ ከክፍሌ ስለማልወጣ እና ብዙ ስለማልንሸራሸር አይርበኝም፡፡ ከአምስት ወር በፊት ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ 94 ኪሎ ግራም ነበርኩ፡፡ አሁን 25 ኪሎ ቀንሻለሁ፡፡ ሰሞኑን ግን ዶ/ር ነጋሽ ጋር ስላለሁ ትንሽ ጨምሬያለሁ፡፡ ሰው ቤት ወይም ምግብ ቤት ካልተጋበዝኩ ‹‹ፊኖ›› (የስንዴ ገለባ) እበላለሁ፡፡ አሜሪካ ብዙ ሰው ፊኖ ይወዳል ግን ዋጋው ውድ ነው፡፡ እዚህ ርካሽ ስለሆነ በአጓት አድርጌ [አጓት ለምኜ] እበላለሁ፡፡ በጣም ጣፋጭ ነው፡፡ እዚህ አገር የተለያዩ ቅር ያሰኙህ ነገሮች እንዳሉ ነግረኸኝ ነበር ምንድን ናቸው?ለሙያዬ አይመቸኝም፣ ብዙ ቢሮክራሲ አለ፡፡ ለምሳሌ ሶማሌ ላንድ እሰራለሁ፡፡ የህክምና እና የሥራ ፈቃድ ለማግኘት ከአንድ ቀን በላይ አይፈጅም፡፡ እዚህ ግን በጣም ረዥም ጊዜ ይፈጃል፡፡ አሁን አልፈለኩም፣ ነገር ግን ባለፈው ጊዜ ስመጣ ፈቃድ በአንድ ዓመት መጨረስ አልቻልኩም ነበር፡፡ ለመኖር እና ለመጫወት ግን ይመቸኛል፡፡ ለመኖር በጣም ርካሽ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብዙ የተማሩ ወጣቶች ሰው እንደሚንቁ ታዝቤያለሁ፤ አስገርሞኛልም፡፡ የሁለት

ዓመት የቱሪስት ፈቃድ አለኝ መሄድ፣ መመለስ እችላለሁ፡፡

መንገድ ላይ በተለይ ነጮች ስትንቀሳቀሱ ገንዘብ እንድትሰጧቸው ብዙ ነዳያን እየተከተሉ ይጠይቋችኋል፡፡ [ወፍራም ገንዘብ አላችሁ ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡]በተለይ አዋሽ መልካሳ ስለሚያውቁኝ ብዙ አያስቸግሩኝም፡፡ አዲስ አበባ ያላወቁኝ አንዳንዴ ይጠይቁኛል፡፡ ግን ስለሌለኝ አልሰጣቸውም፡፡ በተለይ ወደ ገጠር፤ አማራ አካባቢ ስሄድ መለመን ነውር በመሆኑ አይጠይቁኝም፡፡ ፈረንጅ ሁሉ ያለው የሚመስላቸው አሉ፡፡ እኔን ግን በቴሌቪዥን አይተውኝ ስለሚያውቁ ገንዘብ ባይጠይቁኝም እንዳዋራቸው በመጠየቅ ጊዜዬን ይገሉብኛል፡፡

አምላክ አንተን ነጭ እኔን ጥቁር አድርጎ የፈጠረበት የተለየ ምክንያት ያለው ይመስልሀል?አይመስለኝም፡፡ ቀለማችን ለምን እንደተቀያየረም አይገባኝም፡፡ ምናልባት በፀሐይ ብርሃን ምክንያት ይሆናል፡፡ [ሳቅ] በአሁን ሰዓት በዓለም ላይ የሃይማኖት ዘመን አብቅቶ ሳይንስ እየተካው ነው ይባላል፡፡ ትስማማለህ?አይሁድ ነኝ ግን በሳይንስ አምናለሁ፡፡

የአይሁድ ሃይማኖትና ሳይንስ ብዙ አይጋጩም ይባላል... አዎ ብዙ አይጋጩም፡፡ ሃይማኖት ሁሌም ከሳይንስ ጋር ይጋጫል ማለት አይደለም፡፡ አንስታይን አይሁድ ነበር፡፡ [በነገራችን ላይ አንስታይን በህይወት ቢኖር ኖሮ ባለፈው ሰኞ 135 ዓመት ይሞላው ነበር] ነገር ግን ሁሉንም ማስኬድ ችሏል፡፡ እኔም የማምነው ሁለቱንም በማስኬድ ነው፡፡

በጣም የምትወደው ነገር?ግብዣ፡፡

የቅፅል ስም ሀብታም ነህ አሉ...ሌባው፣ ሰላይ፣ ቆቄ ይሉኛል፡፡ [ከእኔ ጋር ወሬውን እንደጨረሰ ጥቁር አንበሳ አካባቢ የሕዝብ ስልክ ለመደወል የሚያስችለው ካርድ በኪሱ መኖሩን አረጋግጦ ተጓዘ፡፡ ከዚያ ወደ ኦሎምፒያ ያመራል - በእግሩ፡፡ አሁን የሚገኘው አዋሽ መልካሳ ነው፡፡]

የወር ወጪው 100 . . .

የአድራሻ ለውጥ ማስታወቂያ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ የአድራሻ ለውጥ አድርጓል፡፡ በመሆኑም አዲሱ ቢሮ ከአራት ኪሎ ወደፒያሳ በሚወስደው መንገድ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ መሆኑን ለውድ

አንባቢዎቻችንና የማስታወቂያ ደንበኞቻችን እናሳውቃለን፡፡

አሳታሚው

የማይገመተው ዓይነት ድፍረት - በመረጃው መስኮት

መቼም ዘመኑ የመረጃ ነው፡፡ ብዙ ዓይነት መረጃዎች በተለያዩ መንገዶች/Channels/ ለተገልጋዩ ይደርሳሉ፡፡ መረጃዎች ሁሉ ግን እንደወረዱ አገልግሎት ላይ መዋል የለባቸውም፡፡ መፈተሽ አለባቸው፡፡ መመረጥ መመርመር አለባቸው፡፡ ለዛሬ አንዱን እንይ፡፡

በፈጣን የመረጃ መለዋወጫነቱ፣ በአዝናኝነቱ እና ተገልጋዮቹን በቀላሉ በማገናኘቱ ይታወቃል፡፡ ለአንዳንዶቻችን ‹ለብዙዎቻችን› ቢባል ይቀላል እንደ ሱስም እየሆነ መጥቷል፡፡ በዚህ እንደኢትዮጵያዊነታችን የመረጃ ቴክኖሎጂን እንደውሃ በተጠማንበት ዘመን መረጃን በፍጥነት በመቀባበል መልኩ ‹ይበል› የሚያሰኝ ነገር ነው - ፌስ ቡክ፡፡

አንዳንዶች ደግሞ ከዚህ አሳንሰው ይመለከቱታል፡፡ መረጃን በፍጥነት ከመለዋወጥ አንፃር ጠቃሚ ነው ባይ ናቸው፡፡ ከፊሎቹ ደግሞ የመቀጣጠሪያ ገጽ ነው ይሉታል፡፡ ሌሎች ደግሞ የግል ምስጢሮች በአደገኛ ሁኔታ የሚባክኑበት የመረጃ መስኮት ነው ሲሉ አምርረው ይተቹታል፡፡ ለዚህም ነው መረጃዎች ሁሉ ግን እንደወረዱ አገልግሎት ላይ መዋል የለባቸውም፡፡ መፈተሽ አለባቸው፡፡ መመረጥ መመርመር አለባቸው የምንለው፡፡

አንድ የፌስ ቡክ ነገር የማይጥመው ወዳጄን በገጹ ፈልጌው ማጣቴን ብነግረው ‹ህይወት የሚሆነኝ ፌክ ቡክ ሳይሆን ባንክ ቡክ ነው› ብሎም እንደቀለደብኝ አስታውሳለሁ፡፡ በዚህ ዙሪያ ብዙ በመባሉ ለጊዜው ተወት እናድርገው እና ወደሌላ ነጥብ እንለፍ፡፡

የትምህርት ደረጃ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ...)፣ እድሜ 26፣ ያላገባ.... እና ወዘተ ስለእሱ የተተነተኑ ማንነቱን እንድናውቅ የሚያደርጉን ነገሮች ናቸው፡፡ የእሷም እንደዛው፡፡ ነገር ግን ስንቶቹ እውነት ስንቶቹ ውሸት እንደሆኑ ለማወቅ የሚያዳግትበት ሁኔታም አለ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ያወራኋቸው መሰሎቼ ፌስ ቡክን በሙሉ ልብ ‹ጥሩ ነው› ለማለት የከበዳቸው ይመስላል፡፡ ለዚህም ነው ‹አንዳንዴ ኑሮው ከሃገር ውጭ የሆነ ሰው ወደሃገሩ ሊመለስ የወራት ጊዜ ሲቀረው የሚጠቀመው ድረ-ገጽ ነው› ያሉኝ፡፡ እንደነዚህ ወገኖች አስተያየት ይህ ደርሶ ተመላሹ ሰው በሚቆይበት የእረፍት ጊዜ ‹ልታዝናናው› እና ተገቢ ባልሆነ አገላለጽ ‹እንዳይደብረው› የምታደርገውን ሴት ሊፈልግ ይችላል፡፡

ወደውጪ ከተመለሰ በኋላስ? በጉዳዩ ላይ ዳሰሳ ያደረጉና ባለተሞክሮዎች እንደሚሉት እሱን የማግኘቷ ነገር ብዙም አይደለም፡፡ እሷ እንዳታገኘው ለማድረግ መድከም አይጠበቅበትም ‹block› የምትለዋን ቁልፍ መጫን ብቻ ነው ባይ ናቸው፡፡ ያ ብቻም አይደለም፣ ተጠራጣሪ ጓደኛ ላላቸው ሴቶች ፌስ ቡክ የዕለት ተዕለት ግጭት መፍጠሪያም ነው፡፡ በእሷ ምስል ላይ የተሰጠው አስተያየት (comment) ፍቅረኛዋን ላያስደስተውና ‹ይህ አስተያየት ሰጪ ሰው ማነው?› የሚል ጥያቄም ውስጡ እንዲያጭር ሊያደርገውም ይችላል፡፡

በእርግጥ ተገቢ መረጃዎችን ከመለዋወጥ አንጻር ፌስ ቡክ ጥሩ ጎን አለው፡፡ አሁን ላለንበት ማህበረሰብ የማያስፈልጉ የሚባሉ ለዕይታ ጥሩ ያልሆኑ ምስሎችን በፌስ ቡክ መለጠፍ (post ማድረግ) አይችሉም፡፡ እንዲያ ከሆነ በ24 ሰዓት ውስጥ ያን ምስል ከገጽዎ ላይ እንዲያወጡ ያስጠነቅቃል፡፡ ያ ካልሆነ ከ24 ሰዓት በኋላ የፌስ ቡክ ደንበኝነትዎ ተሰርዞ ይደርሱበታል፡፡

ሴቶችን በፌስ ቡክ ውስጥ ስንመለከትስ ምን እናይ ይሆን? የማንገምተው ዓይነት ድፍረት፡፡ እኔ በግሌ ያንን ታዝቤያለሁ፡፡ ሴቶች ከማህበረሰቡ ጋር በአካል ከሚጋፈጡት ይልቅ በፌስ ቡክ በተለየ እና አሳማኝ በሆነ መንገድ ይጋፈጡታል ብለን እንድናስብ ያደርገናል፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ በፌስ ቡክ (በተለይ በሴቶች) ያላቸውን ድጋፍ አላስተዋልን ይሆን? አንዳንዴ ይሄ ድብቅ አብዮት ምን ይሆን? እንድንል የሚያደርግ ነው፡፡ ያ ለምን ይሆናል? እንድንልም ያደረገ ነው፡፡ ምን አልባትም እነዚህ ሴቶች ‹አደባባይ ወጥተሽ ይሄን ተናገሪ› ብንላቸው አያደርጉትም ይሆናል፣ ምን አልባትም እነዚህ ሴቶች በፌስ ቡክ ያነሱት ሃሳብ ሃገርን የሚቀይር ይሆናል፣ ምናልባት...፡፡ እዚያ ላይ የሚገርም እና የሚያስደንቅ እንዲሁም ያላሰብነው ነገር ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በሴቶች አንደበት ተቀምሮ ተጽፎም እናገኛለን፡፡

እንዲሁም ‹ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ እንዲህ ብትሆን› ብለው በአስተያየት መስጫ (comment box) እንደቀልድ ጣል የሚያደርጓት አስተያየት ‹ምነው አገር በሴት ብትመራ?› የሚያስብል ድባብን /ቁጭትን/ ይፈጥራል፡፡ ለነገሩ ሴቶች አደባባይ ወጥተው አይናገሩም እንዴ? ድፍረት የላቸውም እንዴ? ወይስ ምንድነው? ካልን፤ ይናገራሉ፣ ተናግረዋልም፡፡ ታሪክ ደግሞ በአስገራሚ ድባቡ ይህን እውነት ይገልጠዋል የሚል ምላሽ እናገኛለን፡፡ ለመናገር ግን ባዶ የፖለቲካ ድብብቆሽ ሳይሆን እውነተኛ የትግል መስመርና ለነጻነት የቆረቡ አጋሮችን ይፈልጋሉ፡፡

እንዲያ ስል በእርግጥ ወንዶች በፌስ ቡክ ሃሰባቸውን ለመግለጥ አይደፍሩም ማለቴ እንዳልሆነ አንባቢዎቼ ሊገነዘቡልኝ ይገባል፡፡ ነገር ግን ሃሳብን ያለፍርሃት በመግለፅ በኩል ሴቶች እንዳልታደልን አድርገን እንቆጥርና ሃሳባችንን እናምቀዋለንና ነው፡፡

አሁን ያለንበትን ሁኔታ ለማደስ ኢንተርኔት ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ በኢንተርኔት በምንፈጥረው ነገር ሴቶች በተለይም ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱት የመጀመሪያ ተጠቂዎች ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ ነውና ጥንቃቄ ይሻል፡፡ የማሕበረሰብ መረጃ መረቡ ለጥቃት ሊውል ይችላልና፡፡ ደግሞ ለዚህም ነው አንዳንድ የኢንተርኔት ፖስታዎች የተገልጋዮቹን ኪራይ በምንጠይቅበት ወቅት የእድሜ ሁኔታን አረጋግጠው እንድንጠቀም ፍቃድ የሚሰጡን፡፡ የሳምንት ሰው ይበለን!

ለነገሩ ሴቶች አደባባይ ወጥተው አይናገሩም እንዴ? ድፍረት የላቸውም እንዴ? ወይስ ምንድነው? ካልን፤

ይናገራሉ፣ ተናግረዋልም፡፡ ታሪክ ደግሞ በአስገራሚ ድባቡ ይህን እውነት ይገልጠዋል የሚል ምላሽ እናገኛለን፡፡ ለመናገር ግን ባዶ የፖለቲካ ድብብቆሽ ሳይሆን እውነተኛ የትግል መስመርና ለነጻነት የቆረቡ አጋሮችን ይፈልጋሉ፡፡

Page 17: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 ል ዩ ቅ ኝ ት 17

በውብሸት ታዬ

ስፍራው የመብራት ኃይል መ/ቤት ፊት ለፊት ነው፡፡ በዚህ ስፍራ የጄ/ል ደጎል አደባባይ የሚገኝ ሲሆን አደባባዩን ዞረው ወደጊዮርጊስ ከማቅናትዎ በፊት አያሌው መስፍን መዚቃ ቤትም ሳይደርሱ አንድ ትኩረትዎን የሚስብ የቴክኖሎጂ ትሩፋት ይመለከታሉ፡፡ ይኸውም በቅርብ ጊዜ የተተከለ፣ በአንድ ጊዜ አራት ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችልና ውበት ያለው የሕዝብ ስልክ አምድ ነው፡፡ አንዳንድ ነገሮችን በርቀት በመመልከት እርግጠኛ የሆነ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም፡፡ ስለዚህ ቀረብ ብለው መመርመር ይኖርብዎታል፡፡ በዚህ ማሕል ፒያሳ ላይ በሚገኝ የስልክ አምድ ላይ አራት ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎችን ይመለከታሉ፡፡ የስልኮቹን እጀታዎች ማንሳት ሲጀምሩ ‹Insert card or coin› የሚል መመሪያ በምስለ መስኮቱ ላይ ያነባሉ፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት ካርድ ወይም ሳንቲም ይጨምሩ መሆኑ ነው፡፡ ብዙ ተገልጋይ ካርድ እንደማይጠቀም ይገመታል፡፡ ስለዚህ ከኪስዎ ውስጥ ሳንቲሞች ያወጡና በቀፎዎቹ ጉሮሮዎች ውስጥ ቁልቁል መላክ ይጀምራሉ፡፡ እስኪ ወደ አራቱም ቀፎዎች ሳንቲሞች በመጨመር የሚሆነውን እንይ፡፡ የመጀመርያው፤- የከተቱበትን ሳንቲም ውጦ ጭጭ ብሏል፡፡ ለማንኛውም በሚል ሌላ ሳንቲም ጨመሩበት፡፡ የተለየ ነገር የለም፡፡ በመጠኑ ቅር እያለዎትና እየተገረሙ ወደሚቀጥለው የስልክ ቀፎ ይዞራሉ፡፡ ሳንቲም መቀበል ብቻ! አራቱም አይሰሩም፡፡ ሁለት መረታዊ ጥያቄዎች ቢነሱ ተገቢ ይሆናል፡፡የመጀመርያው ዜጎች/ተገልጋዮች/ ለሚከፍሉት ክፍያ ተገቢውን አገልግሎት እንደማያገኙ እየታወቀ ቢያንስ [ሥራ ሳይጀምሩ ሥራ ባቆሙት] ስልኮች ላይ ‹አይሰራም!› የሚል ለምን አይለጠፍ?ሁለተኛው፤- እጅግ አስከፊ በሆነ ድህነት ላይ ከምትኖረው አገራችን የተሰበሰበና በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገዛ መሳርያ እንዲህ መናኛ መሆኑ ሲታወቅ ጉዳዩን በባለቤትነት የሚከታተል ወገን የለም? የሚያሰኝና ሌላም፡፡ በመርሕ ደረጃ ማንኛውም ተገልጋይ ወደሚፈልገው ሥፍራ የስልኮቹን ቁጥሮች ከመምታቱ በፊት አገልግሎቱን በሚሰጠው ተቋም ላይ ትምክህቱን ማሳረፍ መቻል አለበት፡፡ ውጤቱ ግን በተቃራኒው ብለውት፣ ብለውት ኪስዎን አራቁቶ ጉዳይዎንም ሳይሞሉ መባከን ብቻ ከሆነ ማበሳጨቱ አይቀርም፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን በየቦታው የተተከሉትን የሕዝብ ስልኮች የተጠቀሙበት ተሞክሮ ሊኖር ይችላል፡፡ ያደረግናቸው የዳሰሳ ጥናቶች ወይም ‹ልዩ ቅኝታችን› በአብዛኛው ላይ የተከሰተውን ዓይነት ስሜት የሚፈጥር በመሆኑ በዘልማዳዊ አባባል ‹ምን ሰይጣን ነው?› የሚል ተስፋ መቁረጥን ያሰፍናል፡፡ ለዛሬ በተወሰኑ የከተማችን የሕዝብ ስልክ መገኛዎች እየተዘዋወርን ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ እንቃኛለን፡፡ ከዚያ በፊት ግን አንዴ ‹ምን ሰይጣን ነው?› የሚለውን መጠይቅ አንስተናልና ይህ የመገናኛ ቴክኖሎጂ የአገራችንን አፈር ከረገጠ ጀምሮ ከዚህ አባባል ጋር የተቆራኘበትን፣ በዚህም በዕሳት እንዲቃጠል ውሳኔ ሳይቀር የተላለፈበትን የዘመን ዳራ እንመልከት፡፡ 121 ዓመታት ወደኋላ መመለሳችን ነው፡፡

ንጉሱ ማተባቸውን ሊበጥሱ?ጊዜው ኢትዮጵያና ኢጣሊያ በአፍላ ፍቅር ላይ የነበሩበት፣ እኔ እብስ አንቺ የሚባባሉበት እንደበር የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ፡፡ “እጅግ ፍቅር እጅግ ጠብን የፈጠረበትን” የአድዋ ቁርቁስ ለጊዜው ስንተወው በ1882 ዓ.ም ራስ መኮንን ኢጣሊያን ጎብኝተው ሲመለሱ ይዘውት የመጡትን የስልክ መነጋገሪያ መሳሪያ ታሪክ እናገኛለን፡፡ ራስ መኮንን የስልኩን ቀፎ የሰጡት ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ አክብሮት ለነበራው አጤ ምኒልክ ነበር፡፡ አጤ ምኒልክም ወዲያውኑ የቴክኒክ ባለሙያቸው ለነበረው እስቴቬኒን ለተባለ ፈረንሳዊ ቤተ መንግስታቸው ውስጥ መስመሩን እንዲዘረጋ አዘዙት፡፡ ከምኒልክ አራሽ እስከ ግምጃ ቤታቸው ተዘረጋ፡፡ /መረጃዎቹን በሙሉ ያገኘናቸው በ1984 ዓ.ም ከታተመው የጳውሎስ ኞኞ ‹አጤ ምኒልክ› ታሪካዊ መድብል ነው/ የዝርጋታ ሥራው በዚህ መንገድ ከተጠናቀቀ በኋላ የተከሰቱት ጉዳዮች ድራማዊ ተውኔት የተሞላባቸው ይመስላሉ፡፡ ምክንያቱም በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በአገራችን የስልክ ንግግር ሊደረግ ነውና፡፡ ንጉሱ በተነገራቸው መሰረት የስልኩን እጀታ አንስተው ወደ

ግምጃ ቤት ሹማቸው ደወሉ፡፡ ቦታው በጣም ይራራቃል፡፡ ድምፁ ግን ጥርት ያለና በአጠገባቸው እንዳለ ሰው አይነት ነው፡፡ ዛሬ ላይ ተሁኖ ሲታሰብ ምንም ላይደንቅ ይችላል፡፡ ጉዳዩ ንጉሱን በእጅጉ መሰጣቸው፡፡ እንዲያውም ተጠራጠሩ፡፡ ስለዚህ መነጋገሪያውን አስቀምጠው የግምጃ ቤት ሹሙ በቅርባቸው ይገኝ እንደሆነ ለማጣራት በመስኮት አጮልቀው ለመመልከት በቁ፡፡ ነገሩ ግን በዚያው አላበቃም፡፡ ነገር ይዞባቸው መጣ፡፡ ቀሳውስቱ “አጤ ምኒልክ ጋኔን እያነጋገሩ ነው” በሚል ተራማጅ አስተሳሰብ በነበራቸው መሪ ላይ ተነሱባቸው፡፡ ከዚህም አልፈው ስምንት ልዑካንን የያዘ ቡድን ወደቤተ መንግስት በመላክ ‹ከቤተ መንግስትዎ ይውጣ ከአገሪቱም ጭራሽ ይጥፋ› የሚል ማሳሰቢያቸውን ገለፁላቸው፡፡ ንጉሱ በእጅጉ ተቆጡ፡፡ እንዲያውም “ለእናንተስ ያ ቴዎድሮስ ነበር መድሃኒታችሁ” ሳይሉ አልቀሩም እየተባለ ይቀለዳል፡፡ ሆኖም ንዴታቸውን በመዋጥ መልዕክተኞቹን ለቀጣዩ ቀን ከቀጠሯቸው በኋላ ጳጳሱን ጨምሮ በርካታ መኳንንት በነበሩበት ቀጥሎ ያለውን ጥበባዊ ተውነት ‹ተወኑ›፡፡ “እኒህ ቀሳውስት ስለመሳርያው ምንነት ብነግራቸውም በቁማቸው ይቃዣሉ፡

፡ ሥራዬንም እያደናቀፉኝ ነው፡፡ ስለዙህ ...” ካሉ በኋላ እጃቸውን አንገታቸው ላይ ባደረጓት ማተባቸው ላይ በማሳረፍ /ለመበጠስ በቋፍ ላይ እንዳለ ሰው በማስፈራራት/ “...ከእንግዲህ ወዲያ የኦርቴዶክስ ኃይማኖቴን ትቼ ከነሱ ለመለየት ስል ኃይማኖቴን መለወጤ ነው!” አሉ፡፡ ሁኔታው በጉባኤው ለተገኙት አስደንጋጭ ስለሆነባቸው “እባክዎ ኃይማኖትዎን አይለውጡብን ‹ያም ነገር› እዚያው ይቀመጥ” አሏቸው፡፡ የሚገርመው ቀሳውስቱ የስልክ መስመሩን የዘረጋውን እስቴቬኒን በኃይማኖት ጉዳይ መግባቱን እንዲያም እንደመከሩት መግለፁ ነው፡፡ አንድ እንመርቅላችሁ፡፡ ስልክ አጤ ምኒልክ ቤተ መንግስት ከገባ ከሁለት ዓመት በኋላ የፍርድ ሚኒስትር ለነበሩት አፈ ንጉስ ነሲቡም ተዘረጋላቸው፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን እየተነጋገሩበት ባሉበት ሰዓት የተላጠውን ሽቦ ነኩትና ነዘራቸው፡፡ የአፈ ንጉሱ የንስሃ አባትም ስልኩን ውጪ በማውጣት በእሳት አቀጠሉት፡፡ ይህን ከ100 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ ሲያነቡ የዛሬዎቹ የመንገድ ላይ ስልኮችም እኮ ተግባራቸው በእጅጉ የሚነዝር ነውና ተሰብስበው ሊቃጠሉ ይገባል ሊያሰኝዎ ይችላል፡፡ እስኪ ቅኝታችንን ቀደም ሲል ካቆምንበት

እንቀጥል፡፡ ብዙ ሳንርቅ ማዘጋጃ ቤት ጀርባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ፊት ለፊት በርካታ የሕዝብ ስልክ አምዶች ቆመው እናገኛለን፡፡ ለነገሩ የቴሌ ጽ/ቤትም እዚያው በአቅራቢያው አለ፡፡ እዚህ ተተክለው ከነበሩት ሰባት ያህሉ የተነቀሉ፣ አራቱ እጀታ የሌላቸው ሌሎቹ የማይሰሩ ሲሆኑ አገልግሎት የሚሰጡት ሁለቱ ብቻ ሆነው አግኝተናቸዋል፡፡ ወደ አራዳ የገበያ ማዕከል ፊታችንን በማዞር በየግድግዳው ላይ የተሰየሙትን የስልክ ቀፎዎች ስንቃኝ፡- ከቴሌ አጥር ጋር ተያይዞ ባለው የመጀመርያ በር ውጭ ላይ ሁለት በሳንቲም የሚደወልባቸው ሆኖም የማይሰሩና በውስጣቸው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ወይም ድርጅት ንብረቶች ስርዓት ባጣ ሁኔታ ታጭቀው ይመለከታሉ፡፡ በሩን አለፍ ሲሉ በግድግዳው ላይ ሁለት በካርድ የሚደወልባቸው ሆኖም አንዱ እጀታ የሌለው ሁለተኛው የማይሰራ፣ ፎቶ ሲሃም አጠገብ አራት ስልኮች፤- ሁለቱ እጀታ የሌላቸው፣ አንድ የካርድና አንድ የሳንቲም መደወያ፤- ሆኖም ሁለቱም የማይሰሩ...ወዲህ ተሸግረው፡- ሲኒማ ኢትዮጵያ ፊት ለፊት ከጄ/ል ደጎል አደባባይ ፊት ለፊት እንዳየነው ሁሉ አራት ቀፎዎችን የያዘ

ዘመናዊ የስልክ አምድ እናገኛለን፡፡ ከአራቱ ሁለቱ በካርድ የሚሰሩ ቢሆንም በሳንቲም በኩል ግን አራቱም ውጠው “አላየንም” የሚሉ ሆነው ያገኟቸዋል፡፡ እንዲህ እያልን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያሉትን የስልክ ቀፎዎች አንድ በአንድ መፈተሻችንን ስንቀጥል እጀታቸው የተቆረጠ፣ ሳንቲም ውጠው የሚያስቀሩ፣ ፈፅሞ የማይሰሩ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለመፀዳጃ አገልግሎትነት እየዋሉ ሊገለገልባቸው በራቸውን በሚከፍት ወገን ላይ የጤና ቀውስ የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ቦሌ መድኃኒዓለም ት/ቤት አጠገብ፣ ቦሌ ቴሌ በር ላይ፣ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል አጠገብ፣ 22 ማዞሪያ፣ ትራፊክ ጽ/ቤት በር ላይ፣ ለም ሆቴል፣ መርካቶ፣ የከተማ አውቶቡስ ተራ፣ ለገሃር ቴሌ ፊት ለፊት፣ ወዘተ፣ ወዘተርፈ ችግሩ ጎልቶ ከሚታይባቸው ቦታዎች በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

“ኢትዮጵያን ከቀጣዩ ዘመን ጋር ማገናኘት”

- ራስ ሳይጠና ጉተና ስናልፍ ስናገድም፣ ስንወጣ ስንወርድ የምንመለከታቸው የአገር ኃብት ፈስሶባቸው የወጡ፣ አሁንም ገቢው ለማን እንደሆነ ባይታወቅም የተገልጋዩን ገንዘብ ውጠው የሚያስቀሩ ስልኮች ነገር አነሳን እንጂ ተገልጋዮች በተቋሙ ላይ የሚያነሷቸው ችግሮች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ ምንም ወይም ጥቂት ደውለው ከፍተኛ መጠን ያለው የዋጋ መጠየቂያ መጣብን የሚሉ የቤት ስልክ ተጠቃሚዎች፣ በተቆራረጡ እና በታፈኑ የሞባልይ ንግግሮች “ሰዎቹ ጠለፉት እንዴ?” በሚል የግል ነፃነታቸውን የሚያጡ ተገልጋዮች፣ … የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት የሞሉት ‹CDMA› በውስጡ ያለው ገንዘብ ግማሹ እንኳን ሳይነካ ተጨማሪ ካልሞሉ መገልገል አይችሉም የሚባሉ /ይህን ልዩ ቅኝት አስመልክቶ ስንወያይ በነበረበት ሰዓት እንኳ በዝግጅት ክፍላችን ውስጥ ኢንተርኔት በምንገለገልበት ወቅት የ17 ብር ዋጋ ያለው የ‹CDMA› ካርድ በውስጡ እያለ በተመሳሳይ ችግር ተጨማሪ እንድንሞላ ተጠይቀናል፡፡ እነዚህና የመሳሰሉት ሕፀጾች በቅርቡ ስያሜውን የቀየረው ተቋም መሪ ቃሉን ‹ዓላማችን ኢትዮጵያን ከቀጣዩ ዘመን ጋር ማገናኘት ነው› የሚል ማድረጉ በምን መልኩ? የሚል ጥያቄ ያስነሳበታል፡፡ በምን መልኩ ነው አገራችን ከቀጣዩ ዘመን ጋር የሚያገናኛት? … ይህን የምንለው ተቋሙ በቅርቡ ባደረገው የሰራተኛ አመዳደብ ላይ በህይወት የሌሉ ወገኖችን ሳይቀር በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ መድቦ እንደነበር፣ ወደአስር ሺህ የሚቆጠሩት ሰራተኞቹ በአየር ላይ ተንሳፈው እንዳሉና ሌሎቹንም ሳንጠቃቅስ ነው፡፡ ልዩ ቅኝታችንን ከመጨረሳችን በፊት ግን፤- ዛሬ በዓለማችን ላይ የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ እየተገነባ ይገኛል፡፡ “ዘመኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘመን ነው” የሚለው አባባል የሚያንፀባርቀውም ይህንኑ ነው፡፡ ወደአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ ግን ገዝተን ያስገባናቸውን የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በአግባቡ ባለመያዝ፣ ሲበላሹ ባለመጠገን ከዚያ አልፎ ብዙዎች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት የዜጎችን የማይገሰሱ የግል ነጻነቶች ለመድፈር እየተጠቀምንባቸው እንደምንገኝ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ወገኖች በተደጋጋሚ የገለፁት ነው፡፡ “International Telecommunication Union” በየዓመቱ በሚያወጣው መረጃ አገሪቱ በዘርፉ በዝቅተኛ ደረጃ ካሉ የመጨረሻ 10 አገራት አንዷ ከመሆን ተላቃ አታውቅም፡፡ ዘርፉን አንድ ብለው ከጀመሩ የአፍሪካ አገራት ግን አንዷ ነበረች፡፡ በኢንተርኔት ኢንፎርሜሽን ከአፍሪካ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለችው አሁንም አገራችን ኢትዮጵያ ናት፡፡ በቴሌፎን ዕድገት፣ በሞባይል ቁጥር ዕድገት፣ ወዘተ ዝቅተኛ ከመሆኑም በተጨማሪ አገሪቱ በዘርፉ ኢኮኖሚዋን በመደጎም በኩል ያላት የዓመታዊ ገቢ አሃዝ ከሁለት በመቶ በታች ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች በጥሞና ካልተመረመሩ እንደ ዘርፉ ባለሙያዎች ማስጠንቀቂያ ኢትዮጵያን ከመጪው ጊዜ ጋር ማገናኘት ይቅርና በአደገኛ ሁኔታ ከሌላው ዓለም ጋር እንድትቆራረጥ ያደርጋታል!

የሕዝብ ስልኮች ማገናኘት ወይስ ማቆራረጥ?

Page 18: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003ፓ ር ላ ማ18

በሱራፍኤል ግርማ

ለአንድ ወር ዕረፍት ላይ የከረመው የኢፌዴሪ 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መጋቢት 6 ቀን 2003 ዓ.ም 15ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማከናወን ወደ መደበኛ ስራው ተመልሷል፡፡

የግብርና ሚኒስቴርን የ2003 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማዳመጥ አጀንዳው በነበረው የማክሰኞው ጉባኤ የተመዘገበው የቀሪዎች ቁጥር 172 ሲሆን፣ ስብሰባውም የተመራው በምክትል አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ነበር፡፡

የሚኒስቴር መ/ቤታቸውን ሪፖርት ለማቅረብ በም/ቤቱ የተገኙት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው ሪፖርቱን ማሰማት የጀመሩት ስለ መ/ቤታቸው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም አፈፃፀም በመግለፅ ነበር፡፡

በ2002/2003 የምርት ዘመን የለማውን ሰብል ከተባይና ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ጉዳት በመከላከል በወቅቱ እንዲሰበሰብ ለማድረግ አርሶ አደሩንና አጋር አካላቱን በማንቀሳቀስ በተደረገ ርብርብ ሰብሉን በወቅቱ ለመሰብሰብ መቻሉን፣ በቅድመ ምርት ትንበያ መረጃ መሰረት በብርዕ፣ በአገዳ፣ በቅባትና ጥራጥሬ ሰብሎች ረገድ 196.6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ሚ/ሩ ገልፀዋል፡፡ እንደ ሚ/ሩ አባባል ከሆነ የተጠቀሰው የምርት መጠን ካለፈው የምርት ዘመን የ8.78% ጭማሪ ያሳየ በመሆኑ የግብርናው ዘርፍ አሁንም “ፈጣንና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ዕድገት” ማስመዝገቡን ቀጥሏል፡፡

ምንም እንኳን የሚኒስትሩ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት” አባባል ሁለ ነገሯን በግብርና ላይ መሠረት ላደረገችው ኢትዮጵያ አማላይና አስደሳች ዜና ቢሆንም፣ “ታዲያ በየዓመቱ አንዲህ ዓይነት ዕድገት ካለ ማሊዮኖች ለምን ለረሐብ ይዳረጋሉ?” የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ባዘጋጀው የሪፖርት ሰነድ ላይ ከሰፈሩት የዕቅድ አፈፃፀሞች መካከል “ዘላቂ የተፈጥሮ ኃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀምን”

በተመለከተ የተጠቀሰው አንዱ ነው፡፡ የደን ሽፋንን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት የሚያጋጥመውን የዛፍ ዘር አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችል የዛፍ ዘር ማበጠሪያና ማከማቻ ማዕከል በደቡብ ክልል እየተገነባ እንደሆነ የሚያስረዳውን ሰነድ ለም/ቤቱ ያነበቡት አቶ ተፈራ ደርበው “በቀጣይም በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች የሁለት ማዕከላት ግንባታ ለማስጀመር የዲዛይን ሥራ እየተከናወነ ይገኛል” ሲሉ የ”አረንጓዴውን ዘመቻ” ሂደት አብራርተዋል፡፡

የግብርና ሚ/ሩ ካቀረቡት ሪፖርት ውስጥ በይበልጥ ትኩረት የሳበው በግብርና ዘርፍ ስለተከናወነው ‹‹ኢንቨስትመንት›› የሚገልጸው ክፍል ነው፡፡

“በግሉ ዘርፍ በግብርና ልማት የሚካሄደው ኢንቨስትመንት ሰፋፊ መሬትና ውሱን ጉልበት ባላቸው አካባቢዎችና ለከተሞች ቅርብ በሆኑ በውሱን መሬትና ሰፊ ጉልበት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የግብርና መሬቶች ማምረት የሚቻልባቸው አካባቢዎች እንደየባህሪያቸው የሚካሄዱ እንዲሆኑም በዕቅድ ተቀምጧል” ያሉት አቶ ተፈራ በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ ሰጥተው ነበር፡፡

ሊለሙ የሚችሉ ሰፋፊ መሬቶች ባሉባቸው የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች ለእርሻ ተስማሚ የሆኑ ቦታዎችንና መሬቶችን በመለየት፣ መሬቱ ለየትኛው የግብርና ምርት ተስማሚ እንደሆነ በማጥናትና በመለየት፣ መሬቱን በመሬት ባንክ ተደራጅቶ እንዲያዝ በማድረግና በማስተዋወቅ “ቀልጣፋና ልማታዊ”

በሆነ መንገድ በሊዝ ለባለሐብቶች እየተሰጠ እንደሚገኝ፣

በዚህም መሰረት በግማሽ ዓመት አንድ ሚሊዮን 896 ሺህ 228 ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ መግባቱ በአጠቃላይ ወደባንኩ የገባውን የመሬት መጠን 3.6 ሚሊዮን ሄክታር እንዳደረሰው፣

ከዚህ መሬት ውስጥም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች 342 ሺህ 99 ሄክታር መሬት በሊዝ መተላለፉ እና የሚካሄደው የሰፋፊ መሬቶች ኢንቨስትመንት ስራ የአካባቢ እና የህብረተሰብ ደህንነት ጥበቃን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ሚ/ሩ ለም/ቤቱ አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን “የሐገሪቷን የምግብ ዋስትና ሊያረጋግጥ አልቻለም” ከሚለው የተለመደ ትችት ባሻገር ግብርና ሚኒስቴር ሰፋፊ ለም መሬቶችን ለውጭ ባለሐብቶች እያከራየ መገኘቱ ለተጨማሪ ትችትና ማሳሰቢያ እየዳረገው ይገኛል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተጋበት በሚገኘው ለውጭ ባለሐብቶች ለም መሬት የማከራየት ተግባር የተነሳ በርካታ ወገኖች “ይህ የመሬት ቅርምት ነው፡፡ ኢንቨስተሮቹ ያመረቱትን ምርት ቀጥታ ወደ ውጭ ስለሚልኩ ለኢትዮጵያዊያን የሚተርፋቸው ከይዞታቸው መፈናቀል፣ ባስ ሲልም ዘመናዊ ባርነት ነው” የሚል ነቀፌታ ሲያቀርቡ ቢቆዩም መንግስት ዝምታን መርጦ ቆይቶ ነበር፡፡

ከአንድ ወር በፊት ግን ግብርና ሚኒስቴር በጋምቤላ ክልል የሚገኝ በጥብቅ ደን የተሸፈነ ቦታን ለሕንድ ኩባንያ በሊዝ መስጠቱን

ተከትሎ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ “ኧረ ባካችሁ የሚሰጥና የማይሰጥ ቦታ ለዩ” የሚል ይዘት ያለው ማሳሰቢያ እንዲፅፉ መገደዳቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

ከፕሬዝዳንቱ ማሳሰቢያ በተጨማሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንም ጉዳዩን አስመልክቶ ከስድስት ወራት በፊት ለግብርና ሚ/ር ደብዳቤ ቢፅፍም ምላሽ አለማግኘቱን የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ይፋ አውለውት ነበር፤ ምንም እንኳን ከአንድ ሰሞን መነጋገሪያነት ባያልፍም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኢኮኖሚክስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር በፍቃዱ በቀለ፣ ግብርና ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ የሚገኘውን ለውጭ ባለሀብቶች መሬት የማከራየት ተግባር የካቲት 5 ቀን 2003 ዓ.ም አውራምባ ታይምስ ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ “ቅኝ ግዛትን በግብዣ!” ሲሉ መኮነናቸው ይታወሳል፡፡

ዶ/ሩ፣ የግብርና ሚኒስቴር ተቀዳሚ ተግባር መሬት ማከራየት ሳይሆን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባው ባስገነዘቡበት ጽሁፍ “የኢህአዴግ መንግስት ይህንን እርምጃ ሲወስድ ውስጥ ለውስጥ በራሱ ተነሳሽነት የሚፈፅመው ድርጊት እንጂ ሕገ-መንግስቱ ስለሚፈቅድ ወይም ፓርላማ ውስጥ ውይይት ተደርጎበትና ተመክሮበት እንዲሁም በደንብ ተጠንቶ እንዳልሆነ ገልፅ ነው፡፡ ይህ በኢህአዴግ አገዛዝና ለጊዜውም ቢሆን አልፎልናል ብለው በሚንደላቀቁ ጊዜ አመጣሽ ግለሰቦችና ቡድኖች የሚካሄደው አሳዛኝ ድርጊት በቀላሉ ሊወገድ የማይችል የፖለቲካ፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የአካባቢ ቀውስ ጥሎ እንደሚያልፍ መታወቅ አለበት” ብለው ነበር፡፡

የግብርና ሚኒስቴርን የስድስት ወር ሪፖርት ያዳመጠው የም/ቤቱ 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የተጠናቀቀው፣ በም/ቤቱ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ላቀረባቸው ጥያቄዎች አቶ ተፈራ ደርበው ምላሽ ከሰጡ እና ም/ቤቱም ሚኒስቴር መ/ቤቱ የታዩበትን ጉደለቶች እንዲያሻሽል “ካሳሰበ” በኋላ ነበር፡፡

ፓርላማው ከዕረፍት መልስከዚህ መሬት ውስጥም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ

ባለሀብቶች 342 ሺህ 99 ሄክታር መሬት በሊዝ መተላለፉ እና የሚካሄደው የሰፋፊ መሬቶች ኢንቨስትመንት ስራ

የአካባቢ እና የህብረተሰብ ደህንነት ጥበቃን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ሚ/ሩ ለም/ቤቱ አስረድተዋል፡፡

ለአውራምባ ታይምስ አንባቢያንበጋዜጣ የህትመት ዋጋ ላይ ማተሚያ ቤት ባደረገው አስደንጋጭ የዋጋ ጭማሪ ምክንያት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በጋዜጣችን መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ የዋጋ ማስተካከያ

ለማድረግ እንደምንገደድ እንገልጻለን አሳታሚው

Page 19: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 ዜ ና ዎ ች 19

አምባሳደር ሙሴ ኃይሉ የሲልቨር ስታር

አዋርድ ተሸላሚ ሆኑበኤልያስ ገብሩ ዓለም አቀፍ የስትራቴጂክ ጥናት አሶሴሽን (ISSA) ኢትዮጵያዊውን ሙሴ ኃይል (አምባሳደር) ባላቸው ዓለም አቀፋዊ ግንኙነትና ላደረጉት የሰላም ጥረት የሲልቨር ስታር አዋርድ ተሸላሚ አድርጎ መረጣቸው፡፡ተቋሙ ሽልማቱን ለአምባሳደሩ ሰሞኑን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተከናወነ ስነ-ስርዓት ያበረከተው ሰላምን ለማምጣት፣ በተለያዩ ሐይማኖቶች እና ማሕበረሰቦች መካከል መግባባት፣ መተማመን እንዲኖር የጋራ እሴቶቻቸው እንዲዳብር በመላው አፍሪካ ከሚገኙ መንግስታትና የተለያዩ አካላት ጋር ለመስራት ለዓመታት ላደረጉት ጥረትና ላስገኙት ውጤት ዕውቅና ለመስጠት መሆኑን የጠቀሰው ተቋሙ “ሌሎች ሊያደርጉልህ የምትፈልገውን ሁሉ አንተም ለሌሎች አድርግ” የሚለውን የወርቃማውን ሕግ የበለጠ በመላው ዓለም ለማስፋፋት ጠንክረው በመስራት በአርአያነት የሚጠቀስ ተግባር በማከናወናቸው ጭምር መሆኑን ጠቅሷል፡፡ “ሜዳሊያው ለሰው ልጅ ሲሉ ሁልጊዜም የሚታወስ ስራን ለሰሩ ሰዎች በተቋሙ በኩል የሚበረከት ከፍተኛ ሽልማት ነው፡፡” ሲሉ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ሚስተር ግሪጎሪ ኩፕሌይ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም አምባሳደር ሙሴ በአፍሪካ ከፍተኛ እውቅና ከማግኘታቸው በተጨማሪ ለሰው ልጅ ባደረጉት የተለየ አስተዋጽኦ እ.ኤ.አ በ2010 መጨረሻ ላይ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ከተሰጣቸው 73 ሰዎች መካከል አንዱ እንደነበሩ ገልፀዋል፡፡ ተቋሙ “ጎልድ ስታር አዋርድ” ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን ይህም ለመንግስታትና ለሀገር መሪዎች ወይም እጅግ በተለየ ሁኔታ አዘጋጅ ኮሚቴ በሚያደርገው ምርጫ ሲሆን የሲልቨር ስታር ሽልማቱ ደግሞ በካቢኔ ደረጃ ላሉ ሰዎች እና በሌላ የመንግስት አካላት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎችና የግል አገልግሎት ለሚሰጡ አካላት የሚበረከት ነው፡፡ ተሸላሚዎቹ ከሚበረከትላቸው ሜዳሊያ በተጨማሪ በከፍተኛ የተመራማሪነት መብት ደረጃ በማንኛውም ጊዜ ተቋሙን እንዲቀላቀሉ የሕይወት ዘመን አባልነት ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ተቋሙ የኪር ጊዝ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስካር አካየቭ፣ ለቀድሞው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ካስፓር ዌይንበርገር፣ የግብፅ መከላከያ ሚኒስትር ፊልድ ማርሻል መሀመድ አብደል ሃሊም አቡ ጋዛላ፣ ለቀድሞ የአሜሪካ የውጨ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ሄይግ፣ ለቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት አብራሃም ባባንጊዳና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ተሸላሚው አምባሳደር ሙሴ በሃይማኖት በሚፈጠሩ አለመግባባቶች የመፍትሔ ሃሳብ በማፈላለግ የመቻቻልና የመከባበሩን ባህል ለማዳበር፣ ሰላምን ለማጎልበትና ለማስፈን፣ እንዲሁም የተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል ጥሩ የመቀራረብ መንፈስ ለመፍጠር ዓላማው አድርጎ የሚሰራው የኢንተርፌይዝ ፒስ ቢዩልዲንግ ኢንሽዬቲቭ (አይ.ፒ.አይ) የቦርድ ሰብሳቢና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የዩናይትድ ሪሊጂንስ ኢንሽየቲቭ (ዩ.አር.አይ) ልዩ ተጠሪ ሲሆኑ፣ ሸላሚው እ.ኤ.አ በ1982 የተመሰረተና መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገ፣ በብሔራዊ አስተዳደር በተለይም በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ጥበቃ እንዲሁም በስትራቴጂ ፖሊሲ ዙሪያ የሚሰራ ማህበር ነው፡፡

92 ሺህ 490 ቶን ቡና ወደ ውጭ መላኩ ተገለፀ

በሱራፍኤል ግርማ በ2003 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ 92 ሺህ 490 ቶን ቡና ወደ ውጪ መላኩን የግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው ገለፁ፡፡ መጋቢት ስድስት ቀን 2003 ዓ.ም ለፓርላማ የመ/ቤታቸውን ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ተፈራ እንዳሉት በመንፈቅ ዓመት ውስጥ 135 ሺህ ቶን ቡና ለመላክ ታቅዶ ነበር፡፡ይሁንና ጥራቱ ተረጋግጦ ወደ ወደብ ለመሸኘት ከታቀደው መጠን ውስጥ ወካይ ናሙና ከተወሰደ በኋላ በተከናወነው የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሊያገኝ የቻለው 92 ሺህ 490 ቶን ያህሉ ነው፡፡ “ክንውኑ ከዕቅዱ ጋር ሲነፃፀር 69 በመቶ ነው” ያሉት አቶ ተፈራ፣ ከተላከው ቡና ውስጥ 32 ሺህ 310 ቶን የታጠበ መሆኑንና ቀሪው 51 ሺህ 770 ቶን ያልታጠበ መሆኑን በመናገር ለምርመራ ከቀረበው ውስጥ ደግሞ 626 ቶን የታጠበ፣ እንዲሁም 2 ሺህ 41 ቶን ያልታጠበ በድምሩ 3 ሺህ 67 ቶን ቡና የጥራት መስፈርቱን ባለማሟላቱ እንዲስተካከል ከተደረገ በኋላ ወደ ወደብ መላኩን አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 158 አዲስ እና ነባር የቡና ላኪ ድርጅቶችን ለመገምገም ታቅዶ 148 አዲስ እና ነባር ላኪ ድርጅቶች መገምገማቸው ተገልጿል፡፡ የግብርና ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው ከጠቀሷቸው ነጥቦች ውስጥ የአበባ ምርትን የሚመለከት የሚገኝ ሲሆን፣ በዘርፉ ለታየው ክፍተት፤ ድርጅቶች በአመራረት ቴክኖሎጂና የማኔጅመንት ብቃት አለመጠናከራቸው፣ የጥራት ጉድለትና የማምረቻ ወጪ መናር በዋና ምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡ በሪፖርት ሰነዱ ላይ በሰፈረው መሠረትም፣ በስድስት ወራት ውስጥ 1058.5 ዘንግና 26.7 ሺህ ቶን አትክልትና ፍራፍሬ ወደ ውጭ አገር በመላክ 156.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 800.1 ሚሊዮን የአበባ ዘንግ (75.6%) እና 43.7 ሺህ ቶን አትክልትና ፍራፍሬ (163.7%) ወደውጭ በመላክ 91.35 ሚሊዮን ዶላር (58.5%) ለማግኘት ተችሏል፡፡ አደጋ መከላከልንም አስመልክቶ አቶ ተፈራ ለም/ቤቱ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር፡፡ የምግብ ዕርዳታ የሚሹ አካባቢዎችንና የህዝቡን ቁጥር በመለየት በአራት ዙር በአማካይ በየዙሩ ለ2.3 ሚሊዮን ህዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ አቅርቦት ድጋፍ መሰጠቱን ያስታወቁት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ‹‹የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት መጠንን አሁን ካለበት 4ዐ5 ሺህ ሜትሪክ ቶን በ2003 በጀት ዓመት 155 ሺህ ሜትሪክ ቶን በመግዛት 560 ሺህ 700 ሜትሪክ ቶን ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል›› ብለዋል፡፡

‹‹ሰፋፊ ለም መሬቶች ለውጭ ባለኃብቶች ሲሰጥ ጥንቃቄ ያስፈልጋል››

- ፍራንክሊን ሲ. ሙርበሱራፍኤል ግርማ መቀመጫቸውን ሮም ባደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ውስጥ ከፍተኛ የልማት አማካሪ የሆኑት ፍሪክሊን ሲ. ሙር፣ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣው መሬትን ለውጭ ባለሀብቶች የማከራየት ሂደት ጥንቃቄ እንደሚያሻው ገለፁ፡፡ የልማት ባለሙያው ይህን ያሉት ትናንት አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከተውጣጡ ጋዜጠኞች ጋር በምግብ ዋጋ መናር ዙሪያ የስልክ ኰንፍረንስ ባደረጉ ጊዜ ነው፡፡ ‹‹በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣው የመሬት መቀራመት በሦስተኛው ዓለም የሚገኙ ገበሬዎችን ከማፈናቀሉና የምግብ ዋጋን ከማናሩ አኳያ ምልከታዎ ምን ይመስላል?›› የሚል ጥያቄ ከአውራምባ ታይምስ የቀረበላቸው ፍራንክሊን ሲ.ሙር የተመጠነ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሂደቱን የመሬት መቀራመት ለማለት የሚቻለው በሊዝ ስምምነቶች የተነሣ የአንድ ወገን ብቻ ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ መሆኑንና በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በደንብ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ያስገነዘቡት ባለሙያው ‹‹ቢሆንም ግን ስምምነቶች ሲከናወኑ ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡ ከግብርና ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ መሰረት በስድስት ወራት ውስጥ 1ሚሊዮን 896 ሺህ 228 ሄክታር መሬት ወደ ባንኩ ገብቷል፡፡ ከተጠቀሰው አጠቃላይ መጠን ውስጥ ደግሞ ለውጪና ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች 342 ሺህ 99 ሄክታር መሬት ተሰጥቷል፡፡ በአሜሪካ ኤምባሲ በተካሄደው የስልክ ኰንፍረንስ ላይ እንደተገለፀው የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር ያላደጉ አገራት የምግብ ዕጥረትን እንዲያስወግዱ 3.5 ቢሊዮን ዶላር መድቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተፈጠረው የምግብ ዋጋ መናር አገራት የሚከተሏቸው የኤክስፖርት ዕቀባ ፖሊሲ፣ ተገቢ ባልሆነ ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለው የምርት ማከማቸት እንዲሁም ግልፅነት የጐደለው ዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ዋና ምክንያቶች መሆናቸው በኰንፍረንሱ ላይ ተገልጿል፡፡

በኤልያስ ገብሩ

ንግድ ሚኒስቴር ከትናንት በስቲያ በሚሊኒየም አዳራሽ ‹‹የንግድ አሰራራችን ለውድድር የተመቸ በማድረግ የንግዱን ሕብረተሰብ የልማት አቅም ለማጎልበት እንሥራ›› በሚል መርህ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ እና የንግድ አሰራር የሸማቾች ጥበቃ አዋጆችን በተመለከተ ለንግዱ ማሕበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ለመስጠት የጠራው ስብሰባ ያለበቂ መግባባት ተጠናቀቀ፡፡ ከተስብሳቢዎች መሃከል ከፊሎቹ ውይይቱን ረግጠው ወጡ፡፡ በፕሮግራሙ መሠረት ውይይቱ ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይደረጋል ተብሎ ቢታሰብም ዘግይቶ ከረፋዱ አራት ሰዓት በኋላ ተጀምሯል፡፡ በወቅቱም የንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አብዲራህመን ሼክ መሐመድ፣ ሚኒስትር ድኤታው አቶ አሕመድ ቱሳ፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ፕሬዝዳንት አቶ እየሱስ ወርቅ ዛፉ፣ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኑረዲን መሐመድና የንግድ አሰራርና ሸማቾች ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወጋየሁ ገ/ሃና በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡ የንግድ ሚንስትሩ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ‹‹በቅርቡ በወጡት የንግድ ሕጎች ላይ ለመወያየትና ግንዛቤ ለመያዝ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት በንግድ ሪፎረም ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት አጠናቅቆ በትግበራ ላይ ይገኛል›› ካሉ በኋላ፣ በጥናቱ ወቅት ጎልተው ከወጡ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ውስጥ ጥቂቶቹን ገልፀው ነበር፡፡ ሕገወጥ የንግድ ተግባራት መበራከትና በዘርፉ ነፃና ፍትሐዊ የገበያ ውድድር አለመዳበር፣ የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችና ሸቀጦች በገበያ ላይ በስፋት መገኘት፣ በገበያ መዋቅር ውስጥ የተሟላና የተጠናቀረ ለውሳኔ የሚረዳ ወቅታዊ መረጃ አለመኖር፣ በግብይት ሥርዓት ተዋንያን ላይ በቂ መረጃ አለመገኘትና የምርቶችና አገልግሎቶች ፍሰት በግልፅ የታወቀ አለመሆኑ እንደችግር ተጠቅሰዋል፡፡ እንዲሁም ሕብረተሰቡ ለሚከፍለው ገንዘብ ተመጣጣኝ ምርት (አገልግሎት) ገበያ ውስጥ ማግኘት ላለመቻሉ ምክንያቱ በገበያ የሚታይ የሥነ ምግባር ጉድለት በመኖሩ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡ ሸቀጦችን ከባዕድ ነገሮች ጋር በመደባለቅ ለተጠቃሚ ማቅረብ፣ ሰው ሰራሽ እጥረትን በመፍጠር የሸቀጦችን ዋጋ እንዲንር ማድረግ፣ ባልተረጋገጡ ሚዛንና መስፈሪያዎች ግብይት ማከናወንም የችግሩ አካሎች ሆነው ተገልፀዋል፡፡ አቶ አብዲራህማን በመግለጫቸው የምርቶችን ፍሰት ከመነሻ እስከ መድረሻ ተከታትሎ ማግኘት አለመቻል፣ የሚሰጠው የምዝገባ ቁጥር ልዩ መለያ ያለው ባለመሆኑ ተደጋጋሚ ምዝገባዎች መከናወናቸው፣ ምዝገባ ያከናወኑ አካላት በቅንጅት በማዕከል የማይሰሩና መረጃ የማይለዋወጡ መሆናቸውን ጨምረው የገለፁበት ሁኔታ ነበር፡፡ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታትና የአገሪቷን የንግድ አሰራር ዘላቂነት ባለው መንገድ ሥርዓት ለማስያዝና የንግዱን ዘርፍ የሚመለከት በመንግስት የተቀረፁ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ወደ መሬት አውርዶ በመተግበር ዘመናዊ የሆነ የንግድ አሰራር ሥርዓት ለመዘርጋትና የዘርፉን መሠረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችሉና አስፈላጊ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎች እና ተዛማጅ ጉዳዮች የተዘጋጁት ሁለቱ አዋጆች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቀው ሥራ ላይ እንዲውሉ መደረጋቸውንም አስታውሰዋል፡፡ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅን በተመለከተ

ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ኑረዲን በበኩላቸው በፀደቀው አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሠረት የንግድ ምዝገባ አገልግሎት የሚጠይቁ ነጋዴዎች ሰባት መስፈርቶችን ማሟላት የግድ እንደሚገባቸው አፅንኦት በመስጠት ገልፀዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የንግድ ፍቃድን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርን፣ የተረጋገጠ የንግድ ሥራ አድራሻን፣ የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅን፣ የተረጋገጠ ካፒታል እና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችን የንግዱ ማሕበረሰብ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በአዲሱ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ መሠረት ሥራ ላይ ያሉ ነጋዴዎችን በአዲስ መልክ የመመዝገቡ ሥራ ከሰኔ 30/2003 በፊት ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ አቶ ኑረዲን ጠቅሰው፣ የንግድ ፈቃድ ለማግኘትም ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የግድ መሆኑን አስምረውበታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም ባለፉት ዓመታት የነፃ ገበያ ውድድር እንዲሰፍንና ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ተግባራትን ለመከላከል የንግድ አሰራር አዋጅ ወጥቶ በሥራ ላይ ውሎ እንደነበር፣ የሸማቾችን ጥበቃ በተመለከተ ሕጉ የተሟላ ድንጋጌዎችን ያላስቀመጠና በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው የሸማቾችኝ ቅሬታ በዳኝነት ለመፍታት የሚያስችል አለመሆኑ በዕለቱ ከመድረኩ የተነሳ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያም በተጠቀሱትና በሌሎች በሕጉ በታዩት ክፍተቶች ምክንያት የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ እንዲፀድቅ መደረጉንና አዋጁን አስመልክቶ አቶ ወጋየሁ አጠር ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

ከ100ሺሕ ብር እስከ 20 ዓመት ቅጣት

በአዲሱ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አዋጅ ቁጥር ስምንት ላይ ‹የበላይነትን አለአግባብ የመጠቀም ድርጊቶች› በሚል ርዕስ ንዑስ አንቀፆች ውስጥ ምርትን መገደብ፣ የንግድ ዕቃዎችን ማከማቸት ወይም መደበቅ ወይም በመደበኛው የንግድ መሥመር እንዳይሸጡ ማድረግ ወይም መያዝን...ወዘተ የተላለፈ ማንኛውም ነጋዴ የዓመታዊ ገቢውን 15 በመቶ ወይም የአመታዊ ገቢውን መጠን መወሰን ባልተቻለ ጊዜ ከብር 500 ሺሕና እስከ አንድ ሚሊዮን ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እና ከአምስት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ እንዲሁም የዚህን አዋጅ አንቀጽ 35 በመተላለፍ የንግድ ዕቃዎችን አከማችቶ ወይም ደብቆ የተገኘ ማንኛውም ነጋዴ ከብር 2000 ሺህ እስከ 4000 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 30 ንዑስ ቁጥር ስድስት ላይ ደግሞ አንድ ሸማች አንድን የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛቱ ወይም የገንዘብ መዋጮ በማድረጉ ተጨማሪ የገንዘብ ወይም አይነት ጥቅም እንደሚያገኝ በመግለፅ በሸማቾቹ አሻሻጭነት ከእሱ ቀጥሎ ሌሎች ሸማቾች የንግድ ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን የሚገዙ ወይም የገንዘብ መዋጮ የሚያደርጉ ከሆነ፣ ወይም በሽያጭ ስልቱ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ፣ የፒራሚድ የሽያጭ ስልት ተግባራዊ ማድረግ ወይም ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር ቅጣቱ ከባድ ነው፡፡ እንዲሁም በዚህ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር 10 ላይ ለሰው ጤና ደህንነት አደገኛ የሆኑ፣ ወይም ምንጫቸው ያልታወቀ፣ ወይም የጥራት ደረጃቸው ከተቀመጠላቸው ደረጃዎች የወረዱ፣ ወይም የተመረዙ፣ ወይም የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ፣ ወይም ከባዕድ ነገሮች ጋር የተደባለቁ የንግድ ዕቃዎችን ወይም

አገልግሎቶችን ማዘጋጀት፣ ወይም ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ ያስቀጣል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ንዑስ አንቀጾች የተላለፈ ማንኛውም ነጋዴ ከብር 100ሺህ - 200 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እና ከ10-20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ አቶ ኑረዲን ህጉን አጣቅሰው ጠንከር አድርገው ተናግረዋል፡፡ ሌሎች መሰል ቅጣቶችም በአዋጁ ላይ ተዘርዝረዋል፡፡

‹‹ውይይቱ ይኼ አልመሰለንም››

ከሚኒስትሩ ንግግርና ከባለሙያዎቹ ማብራሪያ በኋላ መድረኩ ለንግዱ ማሕበረሰብ ክፍት ሆኖ ነበር፡፡ ‹መንግስት በወሰደው የዋጋ ማረጋጋት እርምጃዎችና በአሁን ወቅት በንግዱ ዘርፍ ስላሉት ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያያተን ለችግራችን መፍትሄ የምናገኝ መስሎን እንጂ ውይይቱ ይኼ አልመሰለንም› የሚለው የአንድ አስመጪ የመጀመሪያ አስተያየት ነበር፡፡ መንግስት በግብር ከፋይ መለያ (Tin number) ዙሪያ ያሉበትን የቤት ስራዎች ሰርቶ ሳያጠናቅቅና ሚኒስቴር መ/ቤቱ በቂ የአሰራር ዘዴዎችን ባልዘረጋበት ሁኔታ ልዩ መለያ ያለው የምዝገባ ቁጥር ማዘጋጀትና አዋጅን ወደማስፈፀም ለምን ገባ? በግብር ከፋይ መለያ ችግር የተነሳ ብዙ አስመጪዎች ዕቃዎቻችን በመጋዘን ውስጥ ስለሚገኙ፣ ‹ዕቃ በመጋዘን አከማችታችኋል› ተብለን ልንቀጣ ነው ወይ? በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መ/ቤት በኩል ያሉብን ችግሮች ለምን አይፈቱልንም?...የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ አቶ አሕመድ ቱሳም የዕለቱ ውይይት በቀረቡት አዋጆች ዙሪያ በመሆኑ የሚነሱ ጥያቄዎች በነዚህ ዙሪያ ብቻ መሆን እንዳለባቸው እያለሳለሱ ቢያሳስቡም፣ በተከታታይ ለጥያቄ ዕድል የተሰጣቸው ነጋዴዎች በመንግስት በኩል ብዙ ችግሮች እንዳሉ፣ ውይይቱ መንግስት የቤት ስራውን ከጨረሰ በኋላ ቢሆን የተሻለ እንደሚሆን፣ የንግድ ም/ቤት ለችግራቸው ምንም የፈየደላቸው ነገር እንደሌለ፣ ተቋሙና እነርሱ እንደማይተዋወቁና የአዋጆቹ አፈፃፀም ሂደት እንዳስፈራቸው የሚገልፁ ስጋት አዘል ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ አቅርበዋል፡፡ በዕለቱ ውይይት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አሰራር ብዙሃን ነጋዴዎችን ያስደሰተ አልነበረም፡፡ ከነጋዴዎች ለሚነሱት እያንዳንዱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ሞቅ ያለው ጭብጨባ የተቸረው ሲሆን፣ ተሰብሳቢዎቹ ቀስ በቀስ በመሰላቸት ስሜት ነጋዴዎቹ ከአዳራሹ ሲወጡ ታይተዋል፡፡ ይህንንም በመመልከት ሚኒስትሩና ሚኒስቴር ድኤታው ተሰብሳቢዎች ውይይቱን በትዕግስት ጠብቀው እንዲጨርሱ በተደጋጋሚ ቢገልፁም፣ በጣም በርካታ ነጋዴዎች አቶ አሕመድ ቱሳ ማብራሪያ እየሠጡ ባሉበት ወቅት ውይይቱን በአንዴ ረግጠው ወጥተዋል፡፡ ይኼም የሚኒስትር ድኤታው ንግግር በግድ ቋጭቶታል፡፡ በመጨረሻም የንግድ ሚኒስትሩ ለተቀሩት ነጋዴዎች ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር በተፈጠረው ክስተት ቅር እንደተሰኙ ጠቁመው፣ በአዋጆች ዙሪያ በቀጣይም ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች እንደሚዘጋጁ ገልፀዋል፡፡ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉም ነጋዴዎች ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሳያዳምጡ ውይይቱን ረግጦ መውጣት ተገቢ አለመሆኑን ተናግረው ‹በወጡት የንግዱ ማሕበረሰብ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ› ካሉ በኋላ ጥቂት ንግግር በማድረግ ውይይቱ 7፡30 ተጠናቋል፡፡

ሆኜ ባለመገኘቴ ያሳዝናል፡፡ ቢሆንም፣ ያለ በቂ ምክንያት ያደረኩት አለመሆኑን እንዲረዱልኝ እጠይቃለሁ›› ብለዋል፡፡

በእስር ቤት የነበረው ቆይታቸውን ሲገልፁ፣ ‹‹አጭሩ የፖለቲካ ህይወቴ በርካታ ነገሮችን አስተምሮኛል፡፡ በኢትዮጵያ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትግል በርካታ ውስብስብ ሂደት ስላሉበት፣ የጐለበተ እውቀት እንደሚያስፈልግ ተረድቻለሁ፡፡ ስለዚህ ለተወሰነ ጊዜ ከፓርቲ አመራርነት ራሴን ገታ በማድረግ ለመማር ወስኛለሁ›› ብለዋል፡፡

በእስር ቤት የነበረው ቆይታቸው የትግል ህይወታቸውን ለመመርመር እድል

ንግድ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ውይይት ነጋዴዎች ረግጠው ወጡ

(ሪፖርታዥ)

፡ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አሳታሚ በበኩላቸው ጋዜጦች የህትመት ማቆም አድማ ማድረግ እንዳለባቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነው፣ አድማስ አድቨርታይዚንግ ኃ/የተ/የግል/ማ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ገነት ጎሳዬ ድርጅታቸው በአሁኑ ሰዓት 70 ሺህ ብር ገደማ ለማተሚያ ቤት እየከፈለ መሆኑን አስታውሰው፡፡ በአዲሱ ጭማሪ መሰረት ግን በየወሩ የ120 ሺህ ብር ጭማሪ እንደሚያስከፍላቸው በቅሬታ ይገልጻሉ፡፡ መፍትሄው ምንድነው? ስንልጥያቄ ያቀረብንላቸው ወ/ሮ ገነት ‹አሳታሚዎች

ተሰባስበው አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው፡፡› የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው ጉዳዩ የፕሬስ ነፃነት ፈተና ነው ይላሉ፡፡ ‹ችግሩ የአሳታሚ ድርጅቶች ጉዳይ ተደርጎ መወሰድ የለበትም› የሚሉት አቶ አማረ መንግስት ከእያንዳንዱ ጋዜጣ በስተጀርባ ያሉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ መረጃ ፈላጊ ዜጎችን መመልከት ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ አቶ አማረ የሚዲያ ተቋም እንደ አንድ መደበኛ የቢዝነስ ተቋም ብቻ ሳይሆን ከአገሪቱ መሰረታዊ የዴሞክራታይዜሽን

እንደሰጣቸውም ጨምረው አብራርተዋል፡፡ በእስር ቤት የነበረው የመንፈስ ስብራት እንዳለ ሆኖ፣ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ትግል ብርቱካን ታፈገፍጋለች ብሎ መጠበቅ እንደማይቻልና እንደማይታሰብ ዕውነትና እምነታቸው እንደሆነ አስምረውበታል፡፡

በመጨረሻም፣ ‹‹ሀገሬንና ሕዝቦቼን ከትናንትና በበለጠ አከብራቸዋለሁ፤ ይህም አስከ አጥንቴ ድረስ ይሰማኛል፤ የማይነጥፍ አክብሮትም እንደነበረኝ በታላቅ አክብሮት እገልፃለሁ፡፡ ቃሌ አይለወጥም፡፡ አለኝ፤ ቃሌ አይለወጥም›› ሲሉ መግለጫቸውን በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡

እሴት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ በመሆኑ መንግስት በዝምታ ማለፍ የለበትም ካሉ በኋላ በላቲን አሜሪካ ያሉ አገሮች ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ታክስ በመቀነስና የሕትመት ዋጋን በመደጎም የፕሬስ ነጻነትን እንደሚያበረታቱ አስታውሰዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መስሪያ ቤታቸው ስለ ጉዳዩ በቂ መረጃ እንደሌለው ገልጸው ‹‹ዝርዝር መረጃ ሲኖረን አስተያት እንሰጣለን›› ብለዋል፡፡ ዘግይቶ በደረሰን ዜና የጋዜጣ አሳታሚዎች የፊታችን ሰኞ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ዙርያ ለመነጋገር ፕሮግራም መያዛቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

‹‹ከኢትዮጵያ ፖለቲካ...

በጋዜጦች ላይ..

Page 20: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003ጤ ና20

‹አንድን ግለሰብ በተደጋጋሚ ሊገጥሙት ከሚችሉ የጤና ችግሮች መካከል በእንግሊዘኛው አጠራር ኢፒስታክሲስ ተብሎ የሚጠራው በአፍንጫ የደም መፍሰስ የሚያስከትለው ነስር ነው፡፡› ሲሉ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ይኼ ችግር በሕፃናት ላይ የሚከሰትበት የተለመደ ምክንያት የአፍንጫ መድረቅ ሲሆን ነስር ለአዋቂ ሰዎች ከፍተኛ የደም ግፊት ችግር ሊኖርባቸው እንደሚችል የማስጠንቀቂያ ምልክት መሆኑም ይገለፃል፡፡በጣም አልፎ አልፎ፣ ነስር የደም መፍሰስ ችግር መኖሩን፣ የአፍንጫ እድገት፣ ካንሰር ወይም የሉኬሚያ (በጣም ብዙ የነጭ ደም ሕዋሶች በመመረታቸው ምክንያት የሚከሰት ስር የሰደደ በሽታ ሲሆን ታማሚውን አቅም ሊያሳጣውና አንዳንዴም ሊገድል የሚችል ነው) ችግር መኖሩን ተቋሚ ነው፡፡ በመሆኑም፣ ማንኛውም የአፍንጫ ነስር ተደጋግሞ በመጠንከር የሚከሰት ከሆነ የሕክምና ዶክተሮች ጋር በመሄድ ምርመራ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ከአፍንጫ ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ቁስለቶችና መሰል ችግሮች በአፍንጫ ቀዳዳዎች ውስጥ ደም እንዲፈስ ምክንያቶች ናቸው፡፡

አይነቶቹሁለት ዓይነት የነስር ዓይነቶች አሉ፡፡ በጣም የተለመደው አንቲሪየር የተባለው (ፊት ለፊት ወይም ለፊት የቀረበ) ሲሆን ፓስቲሪየር ደግሞ ከአፍንጫ ከጀርባ በኩል የሚከሰት በመሆኑ ይበልጥ የሕክምና ክትትል ይፈልጋል፡፡ አንዳንዴም በጣም ከባድ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የሚፈስሰው ደም ከአፍንጫ ፈሳሽ ቋት እና ከአይን ሊመጣ ይችላል፡፡ ትኩስ ወይም የረጋ ደም ወደ ሆድ በሚፈስበት ጊዜ ማቅለሽለሽ፣ ነስርና ማስመለስ ሊከተሉ እንደሚችሉ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ሆኖም፣ ችግሩ አንዳንዴ በጣም ከባድ ሲሆን በጣም አነስተኛ ሞትን 㜎ይስከትላል፡፡ እ.ኤ.አ በ1999 በአሜሪካን አገር ከ2.4 ሚሊዮን ሞት መካከል በነስር አራት ሰዎች ብቻ መሞታቸው ተዘግቧል፡፡

መነሻውነስር በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ነገር ግን፣ ለችግሩ የሚያጋልጡ ምክንያቶች በአጠቃላይ በሁለት ተከፍለዋል፡፡ እነዚህም ሎካልና ሲስተሚክ ተብለው ይገለፃሉ፡፡ ቁጥራቸው በዛ ያሉ የነስር ችግሮች ‹ይኼ ነው› ተብሎ የሚታወቅ ምክንያት እንደሌላቸውም የዊኪፒዲያ ድረ ገፅ መረጃ ያስረዳል፡፡

የሎካል ምክንያት የሚባሉት ብለንት ትራውማ (ፍጥነት በታከለበት ሁኔታ የፊት ገፅ በቦክስ ሲመታና አንዳንዴም የአፍንጫ መሰበር ሲከሰት፣ ባዕድ ነገሮች ለምሳሌ ጣቶች አፍንጫን በሚነኩበት ጊዜ፣ ኢንፍላማቶሪ ሪአክሽን (ለምሳሌ የአፍንጫ መቅላት፣ በኢንፌክሽን መቁሰል ወይም ማበጥ)፣ የመተንፈሻ መስመሮች በኢንፌክሽን መመረዝ፣ ስር የሰደደ የሳይነስ ችግር፣ አለርጂ ወይም የአከባቢ አየር ፀባይ የማይለመድ ሲሆን ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ምክንያቶችም አሉ፡፡ አካላዊ መዛባት፣ በዘር የሚተላለፍ ቁስለት፣ አደገኛ አደንዛዥ ዕፆች (ኮኬይን)መጠቀም፣ ውስጣዊ የአፍንጫ ክፍል ዕጢ፣ በተለይ በቀዝቃዛ ክረምት ጊዜ አነስተኛ ዕርጥበት አዘል አየርን ወደ ውስጥ መሳብ፣ የአፍንጫን ፈሳሽ ለማድረቅ የሚረዳ መድኃኒት ‹ናሳል ካኑላ 02›፣ በአፍንጫ የሚሸተቱ የተለያዩ ሽቶዎች ለረዥም ጊዜ ከተወሰዱ እና የአፍንጫ መድኃኒቶችን ያለአግባቡ መጠቀም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በተጨማሪም፣ አውሮፕላን ለማረፍ ዝቅ ሲል ወይም ሰዎች ለዋና ከከፍታ ቦታ ቁልቁል ተወርውረው ውሃ ውስጥ ሲገቡ (ኦቲክ ባሮትራሙማ)፣ ቀዶ ጥገና (ሴፕቶፕላስቲ እና ፈንክሽናል ኢንዶስኮፒክ ሳይነስ ሰርጀሪ)ና የአልቅት መራባት በምክንያትነት ይገለፃሉ፡፡ ሁለተኛውና ሲስተማቲክ ተብለው በምክንያትነት ለነስር ችግር የሚቀርቡት ደግሞ አለርጂዎች፣ የኢንፌክሽን በሽታዎች (ለምሳሌ ጉንፋን)ና፣ ለአስፕሪን መድኃኒት አለርጂ የሆነው ደም ግፊት በዚህ ውስጥ ተመድበዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ምክንያቶችም አስፕሪን፣ ፌሶፌናዳይን፣ ዋርፋሪን፣ ኢዩፕሮፌን፣ አይሶትሪቲኖይን፣ ዴስሞፕሪሲን፣ ጂንሴንግ እና ሌሎች የመድኃኒት አይነቶች ናቸው፡፡ የአልኮል መጠጥ በቫሶዳይሌሽን ጊዜ (የደም ማስተላለፊያ መስመሮች ይሰፉና የደም ግፊት መጠን እንዲያንስ ያደርጋል)፣ የደም ማነስ፣ የሕብረሕዋስ አገናኝ በሽታ፣ የደም መልስ ጫና ጨምሮ ልብ ተገቢውን ሥራ መሥራት አለመቻል፣ እርግዝና (አልፎ አልፎ)፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ፈሳሾች የሚተላለፉበት መስመር መዛባትና የቫይታሚን ‹ሲ› እና ‹ኬ› እጥረት ምክንያት መሆናቸው ተገል±ል፡፡

...በቂ ጊዜ መስጠትነስር በሚያጋጥምበት ጊዜ ቁጭ ብሎ በቀስታ ስስ የሆነውን የአፍንጫ ክፍል በጣቶች ይዞ በመጭመቅ የአፍንጫ ቀዳዳዎችን ለ10 ደቂቃ ያህል መዝጋት ይመከራል፡፡ እንዲሁም ወደፊት ዘንበል ማለት

ደምን ላለመዋጥና በአፍ ለመተንፈስ ይረዳል፡፡ ደም መፍስስ መቆም አለመቆሙን ለማወቅ ቢያንስ 10 ደቂቃ ያህል መጠበቅ አስፈላጊ ሲሆን ብዙ በአፍንጫ የሚከሰቱ የደም መፍሰስ ችግሮችን በቂ ጊዜ በመስጠት በዚህ መንገድ መቆጣጠር ይቻላል፡፡ በተጨማሪም፣ በአፍንጫ መሸጋገሪያ ቦታ ላይ ቀዝቃዛ ነገር ወይንም በረዶ ማድረግ ነስርን ለመከላከል የራሱ ጥቅም ያለው ቢሆንም የውስጠኛውን የአፍንጫ ክፍል በፋሻ መጠቅጠቅ አይመከርም፡፡ እንዲሁም ሰዎች በሚነስራቸው ጊዜ መተኛት እንደማይኖርባቸው የሕክምና ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ ከነስር በኋላ ለረዥም ሰዓታት በአፍንጫ አየር መሳብም ሆነ ማስወጣት የማይመከር ሲሆን ችግሩ የማያቋርጥ ከሆነና ከጠነከረ ናሳል ስፕሬይ ዲኮን ጀስታንት የሚባሉትን አፍሪንና ኒዮሲኒፍራይን የአፍንጫ መርጫዎችን አንዳንዴ መጠቀም ይቻላል፡፡ እነዚህም አነስተኛ የደም መተላለፊያ መስመሮች እንዲዘጉና ነስሩን ለመቆጣጠር ያግዛሉ፡፡

ባለሙያዎችን ማግኘት መቼ?

ነስሩ ከ20 ደቂቃ በላይ ያልቆመ ከሆነ፣ በጭንቅላት ጉዳት የተነሳ አፍንጫ መድማት ከጀመረ (ድንገት የራስ ቅል ተሰንጥቆ ሊሆን ስለሚችል ኤክስሬይ ምርመራ መደረግ ተገቢ ነው)ና ድንገት አፍንጫ ተሰብሮ ከሆነ ለድንገተኛ የሕክምና አገልግሎት ወደሚመለከተው የሕክምና መስጫ ተቋም ማምራት ያስፈልጋል፡፡ በሕፃናት ላይ የተከሰተው የአፍንጫ ደም መፍሰስ በጣም ከተደጋገመ እና ነስሩ ከቅዝቃዜ ወይም ከሌላ አነስተኛ ከሆኑና ለአፍንጫ ከማይመቹ ችግሮች ጋር ካልተያያዘ የሕክምና ባለሙያዎችን ማማከር ግድ ነው፡፡

ለማቆምናከቆመ በኋላቅዝቃዛ ቤትና ትነት ያዘለ አየር ተደጋጋሚ የነስር ችግር ላለባቸው ሰዎች ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ እንዲሁም በክረምት ወራት ለዚህ ችግር የሚያገለግሉ እንደ ናሳል ሳላይን ስፕሬይ እና በውሃ የሚሟሙ ጄሊዎች (ለምሳሌ አይር ጄል) ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ ለሰዎች ደም በአፍንጫ በኩል መጥቶ ሲፈስ መመልከት አስፈሪ ነገር ሊሆን ቢችልም በዚህ ወቅት መረጋጋት አስፈላጊያቸው ነው፡፡ ከዚህ በታች

የተጠቀሱትን መፍትሄዎች በአግባቡ ከተጠቀሙ ውጤታማ በሆነ መልኩ የነስር ችግርን ማስወገድ እንደሚቻል መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

ቁጭ ብሎ 1. በተወሰነ ደረጃ ወደፊት ዘንበል ማለት የመጣው ደም እንዲወጣ እንጂ ወደ ጉሮሮ እንዲመለስ አለማድረግ፡፡ አለበለዚያ ደም ወደ ውስጥ ከተመለሰ የማቅለሽለሽ፣ የማስመለስና የተቅማጥ ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ በጀርባ ሙሉ በሙሉ ተንጋልሎ መተኛት ወይም ወደፊት ይበልጥ ማዘንበል ጥሩ ባለመሆኑ ጭንቅላትን ከልብ በላይ ቀና አድርጎ መጠበቅ ነስርን ይቀንሳል፡፡ 2. የአፍንጫን ስስ ክፍል (አጥንት ካለበት ዝቅ ብሎ የሚገኘው)ን በመቆንጠጥና ለአምስት ደቂቃ ያህል ጨምቆ መያዝ፣ አሁንም ነስሩ የማይቆም ከሆነ ደግሞ በድጋሚ ለ10 ደቂቃ ያህል የተባለውን የአፍንጫ ክፍል ጨመቆ መያዝ ይመከራል፡፡ ይኼ በሚሆንበት ጊዜ መተንፈስ በአፍ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ነስሩ በድጋሚ የማይቆም ከሆነ ከላይ እንደተገለፀው ድንገተኛ የሆነ የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት መንቀሳቀስ የግድ ይላል፡፡ ቀዝቃዛ በረዶን በአንገት ጀርባ ወይም በግንባር በኩል ማድረግ በመፍትሔነት ቢጠቀስም ቀዝቃዛውን በረዶ አፍንጫ ላይ ማድረግ ግን አያስፈልግም፡፡ ...የሚነስረው ደም እንደቆመ ወዲያውኑ የውስጠኛውን የአፍንጫ ክፍል ማፅዳት ጥሩ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የቆመውን ደም በድጋሚ በመቀስቀስ ነስሩ እንዲከሰት ስለሚያደርገው ነው፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን፣ ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም በአተነፋፈስ ላይ ጥንቃቄ በማድረግ አፍንጫን ሊያደሙ የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች ከማድረግ መቆጠብ ብልህነት ነው፡፡

ቅዝቃዛ ቤትና ትነት ያዘለ አየር ተደጋጋሚ የነስር ችግር

ላለባቸው ሰዎች ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ እንዲሁም በክረምት

ወራት ለዚህ ችግር የሚያገለግሉ እንደ ናሳል ሳላይን

ስፕሬይ እና በውሃ የሚሟሙ ጄሊዎች (ለምሳሌ አይር

ጄል) ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

በኤልያስ ገብሩ

ነስርነስር

Page 21: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 ተ ጠ የ ቅ 21

በሱራፍኤል ግርማ

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ከሆኑ ችግሮች ውስጥ አንዱ ወላጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት በማጣታቸው የተነሳ ተንከባካቢ ያጡ ሕፃናት ቁጥር መበራከት ነው፡፡ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት ከመበራከታቸው ጋር በተያያዘ ደግሞ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማትም ቁጥር አብሮ እየተበራከተ ይገኛል፡፡

ተቋማቱ መበራከታቸው ባልከፋ ነበር፡፡ ችግሩ ግን በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ የሕፃናት ማሳደጊያዎች ውስጥ ከበጣም ጥቂቶቹ በስተቀር አብዛኞቹ በውስጣቸው ላሉት ሕፃናት ምቹ አለመሆናቸው ነው፡፡

በዚህ ዙሪያ ከተለያዩ ወገኖች የሚደመጡ ቅሬታዎችን ይዘን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ጥያቄዎችን አቅርበን ነበር፡፡

ከኤጀንሲው ባገኘነው መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መቶ የሚሆኑ የሕፃናት ማሳደጊያዎች የሚገኙ ሲሆን፤ በደቡብ፣ በአማራ፣ በሐረሪ እና በድሬዳዋ የተመዘገቡት 108 ናቸው፡፡ ከአጠቃላዮቹ ውስጥ አብዛኞቹ ችግር ያለባቸው ቢሆንም፣ 38ቱ ደግሞ ለሕፃናቱ የጤና ሁኔታ እጅግ አስጊ ናቸው፡፡

38ቱ ተቋማት አንድ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋም ሊያሟላ የሚገባቸውን የመመገቢያ፣ የመጫወቻ፣ የማደሪያ እና የመማሪያ አገልግሎቶች ካለማሟላታቸው በተጨማሪ ለሕፃናቱ ደህንነት አስጊ ቢሆኑም፣ እስከዛሬ ድረስ እርምጃ አልተወሰደባቸውም፡፡

አውራምባ ታይምስም ‹‹ምን እስኪሆን ነው የሚጠበቀው?፤ ለምን አይዘጉም?›› በሚል ላነሳችው ጥያቄ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓሊ ሲራጅ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹በቀጣይነት እነዚህ ተቋማት የሕፃናት ማሳደጊያ ሆነው ሊቀጥሉ አይችሉም›› እንደሚሉት አቶ ዓሊ ከሆነ፣ ተቋማቱ ያልተዘጉበት ምክንያት ሕፃናቱ የሚዛወሩበት ሁኔታ እስኪመቻች የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ ነው፡፡

ኤጀንሲው የሚቆጣጠራቸው ተቋማት ላይ ብዙ ጊዜ ድንገተኛ ፍተሻ አለመደረጉ እና ፍተሻ የሚከናወነውም በዓመት አንዴ ብቻ መሆኑ ጉድለት ላለባቸው ተቋማት ችግራቸውን ለመሸፋፈን በቂ ዕድል ስለሚሰጥ የክትትልና የቁጥጥር ሥራው ላይ ቀላል የማይባል ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ግን በዚህ አይስማሙም፡፡ ኤጀንሲው ለክትትል ከመሄዱ በፊት ከተለያዩ አካላት ስለተቋሞቹ በቂ መረጃ አሰባስቦ እንደሚሄድ የሚገልጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ለሚያሳድጋቸው

ሕፃናት በቂ ያልሆነ እንክብካቤ ሲያደርግ የነበረ ተቋም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያላሟላቸውን ሊያስተካክል ስለማይችል ከነጉድለቱ እንደሚገኝና ለመሸወድ እንደማይመች በማስረዳት ይሞግታሉ፡፡

በዓመት አንዴ ብቻ ፍተሻ መደረጉ በቂ ስለመሆኑ ጥያቄ ባቀረብንላቸው ጊዜም የሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ኤጀንሲው የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማትን ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉንም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ነው የሚከታተለው፡፡ ስለዚህ የሕፃናት ጉዳይ የእኛ ሥራ ብቻ አይደለም፡፡ የብዙ ባለድርሻ አካላትም ሥራ ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር እና ሌሎችም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱም ተመሳሳይ ሥራ ስለሚያከናውኑ የእኛ በዓመት አንዴ መፈተሽ በቂ ነው›› የሚል ነበር፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ተቋቁሞ ሥራውን ከጀመረበት ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ እንዲዘጉ የተደረጉ ማሳደጊያዎች ዘጠኝ መሆናቸውን፣ ኤጀንሲው በአዋጅ ቁጥር 621/2001 ከተቋቋመ ወዲህ በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግበው የነበሩ ተቋማት ዳግም እንዲመዘገቡ መደረጉንና ችግር ያለባቸው ታግደው ሌሎቹ እንዲቀጥሉ መደረጋቸውን ለሚገልፁት አቶ ዓሊ ሲራጅ፣ ‹‹የተዘጉት ተቋማት ሕፃናት ከመረከባቸው በፊት ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች እንዳሟሉ ሳታረጋግጡ ነው ፈቃድ የሰጣችሁት?›› በማለት ጠይቀናቸው፣ ‹‹በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ማሟላታቸው መረጋገጥ አለበት፤ በዚህ ላይ ተጠናክረን መስራት አለብን ብዬ አስባለሁ›› ሲሉ መልሰዋል፡፡

ተመልካች ያጡ ሕፃናት?ኤጀንሲው በቅርቡ የ2003

ዓ.ም የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከተነሱ ነጥቦች መካከል በሕገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ተቋማት መዘጋታቸውን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ አንዱ ነው፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደሰፈረው፣ ‹‹ቤተር ፊውቸር›› የተባለ የአዶብሽን (ጉዲፈቻ አፈላላጊ) ኤጀንሲ ‹‹በሕገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውር ውስጥ ሲሳተፍ ቆይቷል››፡፡ ድርጅቱ ከተለያዩ አካባቢዎች ያመጣቸውን ሕፃናት በአዲስ አበባ አስተዳደር በተለያዩ ክ/ከተሞች ‹‹ተጥለው›› የተገኙ በማስመሰል፣ በሀሰተኛ መረጃ ሕፃናቱ ወደውጭ ሀገራት እንዲላኩ ‹‹ሲሰራ መገኘቱን›› መግለጫው ያስረዳል፡፡ ‹‹ቤተሰብ ያላቸውን ሕፃናት፣ በሀሰተኛ መረጃ ቤተሰብ የሌላቸው በማስመሰልና ቤተሰቦችን በገንዘብ በመደለል ሕግን በመተላለፍ

የሚሰራ መሆኑ በመረጋገጡ፣ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አጣርቶ ፍቃዱ እንዲሰረዝ ለኤጀንሲው ባሳወቀው መሰረት ድርጅቱ እንዲዘጋ ውሳኔ ተላልፎበታል›› ይላል መግለጫው፡፡

ነገር ግን የተጠቀሰው ድርጅትም ሆነ ሌሎች በማሳደጊያ ስም ተቋቁመው በጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች በኩል ሕፃናትን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደባዕድ ሀገር ሲያዘዋውሩ የተገኙና እንዲዘጉ የተወሰነባቸውን ተቋማት ኤጀንሲው አለመክሰሱ ጥያቄ ያጭራል፡፡

በሕገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ድርጅቶችን ፈቃድ ከመሠረዝ ባለፈ ለምን ክስ እንዳልተመሰረተባቸውና በየዓመቱ በኤጀንሲዎች በኩል ስንት ሕፃናት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደውጭ ሀገራት እንደሚላኩ የጠየቅናቸው አቶ ዓሊ፣ ‹‹እርግጥ ነው እስካሁን የከሰስናቸው የሉም፡፡ ግን መከሰስ የለባቸውም የሚል አቋም ኖሮን አይደለም፡፡ ምናልባትም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የከሰሷቸው ይኖራሉ፤ ቁጥሩም ለእኛ ሳይሆን ለሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚ/ር ነው ሪፖርት የሚደረገው፤››

የሕፃናት ጉዳይ ባለቤትነቱ የማን ይሆን?የሕፃናት ጉዳይ ባለቤትነቱ የማን ይሆን?

ሲሉ ነበር ምላሽ የሰጡን፡፡ እኛም ጥያቄዎቻችንን

ይዘን ‹‹ይመለከታቸዋል›› ከተባሉት ተቋማት አንዱ ወደሆነው የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አመራን፡፡

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብይ ኤፍሬም፣ ሕፃናትን በተመለከተ የመሥሪያ ቤታቸው ኃላፊነት የሕፃናት መብቶችና ጥቅሞች እንዲከበሩ የሚመለከታቸው አካላትን ማስተባበር መሆኑን አፅንዖት በመስጠት ነበር ለጥያቄዎቻችን መልስ መስጠት የጀመሩት፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ የከሰሳቸው ተቋማት ስለመኖሩ የጠየቅናቸው አቶ አብይ፣ ‹‹እኛ የምንሰራው የሕፃናቱን መብቶችና ጥቅሞች በማስከበር ዙሪያ ንቅናቄ መፍጠር፣ የሚመለከታቸውን አካላት ማስተባበር እንጂ የመክሰስ ሥራ አንሰራም፡፡ እሱን የሚመለከተው ፍትህ ሚኒስቴር ነው›› ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚ/ር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ አብይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ምን ያክል ሕፃናት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደውጭ እንደሚላኩ መረጃ እንዳለው በጠየቅናቸው ጊዜ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን መሆኑን ነበር የነገሩን፡፡

ምንም እንኳን የሴቶች፣ የሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ‹‹ሕገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውር

የሚመለከተው ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው›› ቢለንም፣ ወደተጠቀሰው ሚኒስቴር መ/ቤት ባመራን ወቅት ያገኘነው ምላሽ ግን ግራ አጋቢ ነው፡፡

በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ሸለመ፣ ‹‹በሕገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውር ላይ አንሰራም፡፡ ይኼ ጉዳይ ወደ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ተላልፏል›› ማለታቸው ግራ ከማጋባቱ በላይ፣ ‹‹ታዲያ የሕፃናትን ጉዳይ ማነው በኃላፊነት እየሰራ ያለው?›› የሚል ጥያቄ እንዲነሳ ያስገድዳል፡፡

በሕገ-ወጥ መንገድ ሕፃናትን ወደ ውጭ ሀገራት መላካቸው ተረጋግጦ እንዲዘጉ የተወሰነባቸው ድርጀቶች ለሕገ-ወጥ ድርጊታቸው ለምን እንዳልተከሰሱ ላነሳነው ጥያቄም መልስ ለማግኘት የሶስት አስፈፃሚ አካላትን ደጅ ለመርገጥ ተገደናል፡፡ መጀመሪያ ጥያቄውን ያቀረብንለት የበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ ጉዳዩን ወደ ‹‹ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት›› መራ፤ ከዛም የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚ/ር የመክሰስ ኃላፊነቱን ወደ ፍትሕ ሚ/ር አስተላለፈ፡፡ ፍትህ ሚኒስቴር ያገኘናቸው የሥራ ኃላፊዎች ደግሞ በበኩላቸው መረጃውን ማግኘት የሚቻለው ከዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት መሆኑን ቢገልፁልንም በጽ/ቤቱ ‹‹ጉዳዩን ይበልጥ ያውቁታል›› የተባሉት ባለሙያ ‹‹ሥልጠና ላይ ናቸው›› በመባሉ ለጥያቄያችን መልስ ሳናገኝ ቀርተናል፡፡

Page 22: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003

አጥቂው- መከላከያ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አሸናፊ ቡድን ለመውለድ ግማሽ መንገድ ተጉዟል፡፡ የመጀመሪያውን

ዙር በመሪነት “አጠናቋል” ብሎ መናገር ስህተተኛ የሚያስብልበት ዕድል ጠባብ ስለሆነው የመከላከያ እግር ኳስ ቡድን አቤል ዓለማየሁ ታሪክን በማጣቀስ ሰፊ ሀተታዊ ፅሁፍ አዘጋጅቷል፡፡

ስ ፖ ር ት22

ባለሙያው ሹል ጥርስ ያለውን የኮንስትራክሽን መኪና መሪ ከወዲህ ወዲያ ይጠቀልላል፡፡ ሰርስሮም አለታማውን ድንጋይ ብዙ ትንንሽ ያደርገዋል፡፡ ሰሞነኛው ዝናብ ከመንገድ ግንባታ ስራው ጋር ተደማምሮ ስፍራው ጨቅይቷል፡፡ ሰራተኞችና መኪኖች ውር ውር ይላሉ፡፡ በአካባቢው የሚገኘው የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ የልምምድ ሜዳ፣ ሆስቴል እና የአሰልጣኞች ቢሮ አካቶ የያዘው ጊቢ የመንገድ ቁፋሮው ወደ ታች መዝለቅ አርቀው የሰቀሉት አስመስሎታልና ተራምዶ መግባትን ለጊዜውም ቢሆን ታሪክ አድርጎታል፡፡

ቀኑ ረቡዕ አራት ሰዓት ላይ፣ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አናት ላይ የተቀመጠው መከላከያ የዕለቱን ልምምድ የሚጀመርበት ጊዜ ቢሆንም ውቡ የተንጣለለ የልምምድ ሜዳ ያለወትሮው ራቁቱን ሆኖ ይታያል፡፡ አንዳንድ ተጨዋቾች መደበኛ ልብሳቸውን፣ ሌሎች የክለቡን ቱታ ለብሰው ወደ ክለቡ መዝናኛ አዳራሽ በመግባት ላይ መሆናቸው ያየ የዕለቱ ልምምድ መሰረዙን ይጠረጥራል፡፡ በእለቱ አጠቃላይ ስብሰባ በመኖሩ ሳቢያ ለተጨዋቾች እረፍት በመሰጠቱ ነው አዲሱ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ቡድን ለመሆን የሚንደረደረውን የመከላከያ ቡድን አባላት የሚያበቃው ሜዳ ጾሙን መዋሉ፡፡

ከሁለት ቀሪ ጨዋታዎች (አዳማ ከነማ ከሀዋሳ ከነማና ከመከላከያ ጋር ከሚያደርገው) በስተቀር አንደኛውን ዙር ያሟሸው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በመሪነት የተቀመጡትን ቡድኖች ትኩረት ሰጥቶ የተመለከተ የፕሪምየር ሊጉን የሚያነሳ አራተኛ ቡድን ሊወለድ ስለመቻሉ ሰፊ ግምት ያሳድራል፡፡

በፕሪምየር ሊጉ የ14 ዓመት ጉዞ “አሳዛኝ” የተባለውን አደጋ ከአዲግራት ወደ መቀሌ ሲያመራ በመኪና መገልበጥ ሳቢያ ካስተናገደው አዳማ ከነማ ጋር አንድ ቀሪ ጨዋታ የሚቀረው መከላከያ በሰባት ጎል ልዩነት ካልተሸነፈ በስተቀር ሊጉን በመሪነት ማጠናቀቁን አረጋግጧል፡፡

አወዛጋቢ የዳኝነት ውሳኔ በታየበት ጨዋታ ከደደቢት ጋር የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያደረገው ኢትዮጵያ ቡና 2-1 አሸንፎ ያገኘው ጣፋጭ ሦስት ነጥብ ከሊጉ መሪ መከላከያ ጋር በእኩል ነጥብ እንዲቀመጥ ቢያደርገውም በስድስት ጎል አንሶ ሁለተኝነትን አስከብሯል፡፡ የአምናው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ‹‹ክስተት›› ደደቢት ከአዳማ ከነማ እና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረጋቸው ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች ሽንፈትን መጎንጨቱ መሪዎቹን አንጋጦ ለመመልከት ተገዷል፡፡ በ24 ነጥብ እና በስምንት ጎል ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ አንደኛውን ዙር ስለማጠናቀቁ ማረጋገጫ በእጁ የለም፡፡ ከደደቢት ጋር እኩል ነጥብ ሰብስቦ በአንድ ጎል የተበለጠው የሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሀዋሳ ከነማ አዳማ ከነማን ካሸነፈ አሊያም ነጥብ ከተጋራ ደደቢትን ቦታ ይቀይረዋል፡፡ ከትላንት በስቲያ መብራት ኃይልን 2-0 ያሸነፈው አዳማ ከነማ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎቹን ካሸነፈ ሦስተኛ ሆኖ የማጠናቀቅ እድል አለው፡፡

በታንዛኒያ በተካሄደው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሻምፒዮና ላይ ወሳኝ ሦስት ተጨዋቾችን ያሰመረጠው መከላከያ (ዑመድ ኡኩሪ፣ ሳሙዔል ውሐበ እና በዳሶ ሆራ) አራትና ከዚያ በላይ ያስመረጡ ክለቦች ከጨዋታ እንዲታቀቡ የሚያዘው የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳዳሪያ ደንብ ስላልፈቀደላቸው ሦስት የሊጉን ጨዋታ ከሦስት ቋሚ ተሰላፊዎቻቸው ውጪ ማድረግ ግድ ብሏቸው ስለነበር ነጥቦች ለመጣል ተገደዋል፡፡ ሁለት አቻና ብቸኛውን ሽንፈት በኢትዮጵያ ቡና የቀመሱት በዚሁ ወቅት ነው፡፡

የከፍታው ምስጢር?የመሿለኪያው መንገድ ግንባታ

እግር ኳስ ክለቡን ጊቢ ከፍ እንዳደረገው ሁሉ መከላከያ ቤት በሁሉ ረገድ ከፍታ እየታየ ነው፡፡ የክለቡ በጀት እድገት አሳይቷል፤ ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ በመሆን፡፡ ከዚህ ውስጥ አንድ ሚሊዮን የሚሆነው ዘንድሮ የተቋቋመውን ወጣት ቡድን ጨምሮ ለደሞዝ ይውላል፡፡ በጀት ካነሰ የስፖርት ክለቡ ቦርድ ክፍተቱን

የሊጉ መሪ የመከላከያ እግር ኳስ ቡድን •

መከላከያን በቁጥር31- በሊጉ የሰበሰበው ነጥብ

14- በሊጉ ያደረገው የጨዋታ ብዛት ቁጥር

9- በሊጉ ያሸነፈው የጨዋታ ቁጥር

4- በሊጉ ነጥብ የተጋራበት የጨዋታ ቁጥር

1- በሊጉ የተሸነፈበት የጨዋታ ቁጥር

35- በሊጉ ያገባው የጎል ቁጥር

17- በሊጉ የተቆጠረበት የጎል ቁጥር

ለመሙላት ይንቀሳቀሳል፡፡ ክለቡ በተጨዋቾች ደሞዝ

ክፍያ በአገሪቱ ቀዳሚ መሆኑን በዚህ ዓመት አሳይቷል፡፡ የክለቡ አንደኛ ደረጃ ደሞዝ ሦስት ሺህ አንድ መቶ (3100) ብር ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጡት 2900 ብር ወር ላይ ኪሳቸው ይከታሉ፡፡ 2700 ብር ዝቅተኛ የክለቡ የዋና ቡድን ተጨዋቾች ደሞዝ ነው፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ የአሰልጣኞች ሪከርድ በሆነ ሂሳብ 100 ሺህ ብር የዝውውር ከፍለው አሸናፊ በቀለን የቡድኑ አሰልጣኝ አድርገዋል፡፡ የሚከፈለው ወርሃዊ ደሞዙ (12 ሺህ ብር) ገ/መድህን ኃይሌ ከወራት በፊት ደደቢትን ለማሰልጠን የተስማማበት 20 ሺህ ብር ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቦ ነበር፡፡ አሰልጣኝ አሸናፊ ተጨዋቾች ለዝውውር የሚከፈለው የዝውውር ሂሳብ 250 ሺህ ብር መድረሱን ግንዛቤ ውስጥ በመክተት ለዝውውር ከተሰጠው ገንዘብ እና ወርሀዊ በላይ ጠይቆ እንደነበረ የሚናገሩ አሉ፡፡ ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ በመመደብም ተጨዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች ሰብስበዋል፡፡ የራሳቸው የልምምድ ሜዳ ካላቸው ጥቂት ክለቦች አንዱ ነው፡፡ የሜዳው ውበት ጥሩ እንክብካቤ እንዳለው ያሳብቃል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ገለፃ የክለቡ የጀርባ አጥንት ሠራዊቱ ነው፡፡ ከመደበኛ ተራ ወታደር እስከ ጀነራል ማዕረግ ላይ ያሉ ወርሃዊ መዋጮ ያደርጋሉ፡፡

አስተያየት ሰጪዎች ይህ በመከላከያ እግር ኳስ ቡድን ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ የታየ ከፍተኛ መነቃቃት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

አዲሱ አሸናፊ በ1984 ዓ.ም. ወደ ስልጠና

ዓለም የገባው የቀድሞው የኢትዮጵያ ባንኮች አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ መጠኑ ቢለያይም በቅድመ ውድድር ዘመንም ሆነ በውድድር መሀከል የሚሰጠው ልምምድ “ጠንካራ” ነው፡፡ “ልምምዱ ከተጨዋች አቅም ጋር ያልተመጣጠነ ነው (ከባድ ነው)” እያሉ የሚተቹት ተጨዋቾች ቢኖሩም በሊግ ውድድሮች ላይ እንደ ማራቶን እስከ ክር መበጠሻው ድረስ ለመዝለቅ ልምምዱ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው የሚመሰክሩም አሉ፡፡

ከንግድ ስራ ኮሌጅ ‹‹በባንኪንግ እና ፋይናንስ›› የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው አሸናፊ ራሱን ለማዳበር ከስልጠና ረጂ መሳሪያዎች ጋር ጓደኝነቱ መልካም ነው፡፡ በተጨዋቾች ፎቶ ባሸበረቀው ቢሮው በደረስኩም ጊዜ ትኩረቱን በእግር ኳስ ማዳበሪያ ገላጭ ጥራዝ ላይ አድርጎ ነበር፡፡

የአሸናፊ ቡድን በአካል ብቃት ላይ አተኩሮ ኳስን ወደፊት ለመጫወት ይሞክራል፡፡ በተለይ ዘንድሮ በመከላከያ የሰራው ቡድን በስልጠና ህይወቱ ኳስን ወደ ፊት የሚጫወት (በማጥቃት ላይ የተመረኮዘ ጨዋታን የመረጠ) ነው፤ አጥቂ ቡድን ለመገንባቱ የቡድኑ ስብስብ እንደረዳው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ያምናል፡፡ በህፃንነት እድሜው ከ1977 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያን እግር ኳስ በጥልቀት መከታተል የጀመረው ጋዜጠኛው “መከላከያ በየቦታው የማጥቃት ባህሪ ያላቸው ተጨዋቾች ይዟል ይህም የቡድኑ ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ እንዲኖረው አድርጓል” ባይ ነው፡፡

ዑመድ ኡኩሪ፣ በዳራ ሆራና ጫላ ድሪባ ለአጥቂው መከላከያ ፈጣን የጎል አነፍናፊዎች ናቸው፡፡ አሰልጣኝ አሸናፊ ሦስቱንም በአንድ ላይ ደጋግሞ አጫውቷቸዋል፡፡ በሁለት እና በአንድ አጥቂም የሚጠቀምበት ጊዜ አለ፡፡ ሁሉም ጎል አስቆጣሪ ናቸው፡፡ በተለይ ሰባት ጎል ያስቆጠረው ጫላ ድሪባ የሊጉ ክስተት ነው፡፡ 14ኛውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዙር በአንክሮ የተከታተለው አስር አለቃ ጫላ ድሪባ ‹‹የብሔራዊ ቡድን ጥያቄ እንዴት ቀረበለት?›› ብሎ አይጠይቅም፡፡ ረዥሙ አጥቂ አይን ውስጥ የከተተው እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ በራስ መተማመኑ የአንጋፋ ተጨዋች ያህል ነው፡፡ ከሙገር የመጣው በዳሶ ሆራም የመከላከያ የአጥቂ መስመር “አስፈሪ” የሚል ሐረግ እንዲለጠፍለት ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡ ይህም ከፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ የተቀመጠው ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ለሚያደርገው ጥረት በጎል ማምረቱ በኩል ስጋት ውስጥ እንዳይገባ አድርጎታል፡፡

አማካዮቹ ፋሲካ አስፋው እና ሳሙኤል አለባቸው የክለቡ የመሀል ምሶሶዎች ናቸው፡፡ የማጥቃት እንቅስቃሴው እንዲፋጠን ኳስ ወደ ፊት በማንሸራሸሩ በኩል የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ቁርጠኛው አምበሉ አይናለም ኃይሉ የብረት ማገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝም ትኩረት በመስረቁ የዋሊያዎቹን ተከላካይ ለማጠናከር አማራጭ ሆኗል፡፡ ቁጥሮች ግን መከላከያ በንፅፅር ሲታይ ጥሩ ተከላካይ መስመር እንደሌለው ያሳያሉ፡፡ 17 ጎል ከተቆጠረበት መከላከያ በተሻለ ሲዳማ ቡና፣ ሀዋሳ ከነማ፣ ሀረር ቢራ፣ ቅ/ጊዮርጊስ በራቸውን አስከብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብ/ቡድንን በር የመጠበቅ ሰፊ ዕድል ያለው ይድነቃቸው ኪዳኔ የመከላከያ በር ከ17 በላይ ግብ እንዳይቆጠርበት ኳስ በማምከኑ በኩል የተሳካ የውድድር ዓመት እያሳለፈ ነው፡፡ ቡድኑን ከኋላ በመምራት በኩልም አስተዋፅኦው የሚናቅ አይደለም፡፡ ‹‹ጎሎች ያስተናግድ የነበረው የመከላከያ መረብ በሌሎች ዓመታት አንፃር ዘንድሮ ለውጥ አሳይቷል፡፡ ለዚህም ይድነቃቸው ትልቅ ስራ እየሰራ ነው›› ሲል መሸሻ ወልዴ አጭሩን ግብ ጠባቂ ያወድሳል፡፡

ነፃነት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ

ተጨዋቾች ጋር የመሸሻ ወልዴን ያህል ቅርበት ያለው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ አማካሪያቸው፣ ስህተታቸውን ጠቋሚያቸውና መልካም ጎናቸውን ማሳያ

መኩሪያ (የክቡር ዘበኛ ቡድን) እንዲሁም የጦር ሰራዊት ቡድን የነበረው መቻል የንጉሳዊ አስተዳዳር ውሳኔ ሰለባ ሆነው ነበር፡፡ በዚህም ሳቢያ ወታደር ሆነው በሲቪልነት ቅ/ጊዮርጊስን ጨምሮ በሌሎች ክለቦች ውስጥ ገብተው ለመጫወት ተገደው ነበር፡፡

በ1967 ዓ.ም. የወታደራዊ ስርዓት በስልጣን ማማው ላይ “ጉብ” ሲል የወታደራዊ ቡድኖችም ተስፋ ለመለመ፡፡ አላግባብ እንደወጡ አስታውቀውም ወደ ውድድር ሜዳ ከሲቪል ቡድኖች ጋር ተቀላቅለው እንዲጫወቱ ተፈቀደላቸው፡፡ ቡድኑም ‹‹መቻል›› ተባለ፡፡ ይህ ቡድን ምድር ጦር የሚል ስም ወጥቶለት የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስልጣን ላይ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ጠንካራ ተፎካካሪ ቡድን ሆኖ አሳልፏል፡፡ ‹‹በ1983 ዓ.ም. ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን ሲያልፍ ቡድኑ ፈረሰ፡፡ እስኪደራጁ ድረስም ስም እየተሰጣቸው ያወታዎችን ያደርጉ ነበር፡፡ ››

ሙሉዓለም እጅጉ፣ ደረጃ በላይ፣ ቡታ አስመሮም፣ ካንጋሮ (በረኛ) ያካተተው ምድር ጦር የበርካታ ደጋፊ ባለቤት ነበር፡፡ በተለምዶ ሚስማር ተራ የሚባለው ቦታ [በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችና የመብራት ኃይል ደጋፊዎች የሚቀመጡበት] በ”ጦሩ” ደጋፊዎች የተያዘ ነበር፡፡ በካታንጋም ይታደማሉ፡፡ የቡና ደጋፊዎች በተቆጣጠሩት ቀኝ ጥላ ፎቅም ‹‹ይነግሱ›› ነበር፡፡

በምድር ጦር ዘመን የነበረው የእግር ኳስ ፉክክር ይፋፋም ነበር፡፡ ጎልማሳ እና አንጋፋ የስፖርት ቤተሰቦች ስለዚህ ጊዜ ዞር ብለው ሲያወጉ ፊታቸው ይፈካል፡፡ የምድር ጦር ደጋፊዎች በአዎንታዊም ሆነ አሉታዊ መልኩ የሚያነሷቸው ቢኖርም የእግር ኳስ ሜዳው ድምቀት እና ግለት መሠረት እንደነበሩ ግን ማንም ይስማማል፡፡

‹‹ምድር ጦር ጨዋታ ሲኖረው ስታዲየሙ ይሞላል፡፡ የመግቢያ ገንዘብ ስለሌለን ተጨዋቾች በሚያሟሙቁበት በኩል (በከማን አንሼ) ተንጠልጥለን እንገባለን፡፡ ያን ካልቻልን ዛፍ ላይ ወጥተን ለማየት እንሞክራለን፡፡ “ጋሼ አስገቡን” እያልን ከሚገባ ሰው ጋር ተቀላቅለን ለመግባት ጥረት እናደርጋለን፡፡ ይህ ሁሉ ካልተሳካ ጨዋታ ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃ ሲቀር በሮች እስኪከፈቱ እንጠብቅ ነበር›› በማለት ምን ያህል ለጨዋታው ጉጉ እንደነበሩ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ይናገራል፡፡ 90 ደቂቃ ላለመሸነፍ ጠንካራ ፉክክር የሚያደርገው “ጦሩ” የዳኛው ፊሽካ እስከሚነፋ ድረስ መጫወት የሚያስችል ትንፋሽ ያላቸው ተጨዋቾች የተሰባሰቡበት እንደነበር ይነገራል፡፡ ‹‹ትልቁ የቡድኑ ብቃት ወኔና ያልበገር ባይነት ስሜታቸው ነው፡፡ እየተመሩ እንኳን አንድ ነገር ሊፈጥሩ የሚችሉ ስለሆኑ አታምናቸውም፡፡ ተጨዋቾች ያላቸው ትንፋሽ አስገራሚ ነበር›› የሚለው መሸሻ በወቅቱ የሁሉም ቡድኖች የተፎካካሪነት ደረጃ ጣሪያ የነካበት ስለነበር ከባዱ ከስታዲየም መቅረት እንጂ መምጣት አልነበረም፡፡

‹‹ሀማሬሳሆ... ጦሩ ነመኛታ... ጦሩ ነመኛታ...›› በሚል ዜማ ስታዲየሙን የሚያርዱ ደጋፊዎች ምድር ጦር ካለው ቤታቸው አይቀሩም፡፡ መሸነፍን ካለመውደድ የተነሳ ወቀሳን ያስከተሉባቸው ግጭቶች ውስጥ ይገቡም ነበር፡፡ በክራንች ‹‹ኩርኩም›› የሚያቀምሱም ነበሩ፡፡

ከአሁኑ ቡድን ውስጥ እንደቀድሞው የሰራዊቱ አባላት የሆኑ ተጨዋቾች አሉ፡፡ አይናለም ኃይሉ፣ ጫላ ድሪባና ገመቹ በቀለ ‹‹ሚሊተሪ›› ናቸው፤ ሲጠሯቸው አስር አለቃ ማለትዎን እንዳይረሱ፡፡ በጨዋታ ዘመኑ ፀሐይ ግባት እና መከላከያን በአምበልነት ያገለገለው የክለቡ ምክትል አሰልጣኝ በለጠ ገ/ኪዳንም መቶ አለቃ ከስሙ ፊት የሚቀድም ማዕረግ ነው፡፡

ዑመድ ለምን ጎላ?ጋምቤላ በተለምዶ ‹‹ባሮ

ማዶ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተወልዶ እንዳደገው ዑመድ ኡኩሪ በዘንድሮ ዓመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ተደጋግሞ የተነሳ ስም ማግኘት ይከብዳል፡፡

አጥቂው በየሰፈሩ ስሙ እንዲናኝ ጎልቶ የወጣበት በታንዛኒያ የተካሄደው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሻምፒዮና በዲ ኤስ ቲቪ መተላለፉ ጠቅሞታል፡፡ ካምቦሎጆ ብቅ የማይሉ እንኳን ስለ ዑመድ ማውራት ጀምረዋል፡፡ በብሔራዊ ቡድንና በመከላከያ 11 ቁጥር ለብሶ ሜዳ የሚገባው ዑመድ በሊጉ አስር ጎል አስቆጥሯል፡፡ ጠንካራ ሹት ይመታል፡፡ ፍጥነቱ ሰውነት ያርዳል፡፡ የሊጉ አስፈሪና አስጨናቂ አጥቂነትን ካባ ደርቧል፡፡

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

መስታወታቸው ነው፡፡ ‹‹መሼ›› በመከላከያ ዘንድሮ ካያቸው ጥሩ ነገሮች አንዱ ነፃነት ነው፡፡ ‹‹በፊት መከላከያ ውስጥ ያለው የተጨዋቾች ቁጥጥር በቀድሞ ጊዜ እንደነበረው በጣም የጠነከረ አይደለም፡፡ ከአሰልጣኛቸው እና ከአመራሮች ጋር የመነጋገር ባህል አዳብረዋል፡፡ ይህ ደግሞ እግር ኳስ የሚፈልገው ቁልፍ ነገር ነው›› በማለት ጥሩውን ጎን ያሳያል፡፡

ሰባት የመከላከያ ተጨዋቾች ከክለቡ ፈቃድ አግኝተው ከክለቡ ሆስቴል ውጪ (በቤታቸው) ይኖራሉ፡፡ የአቋም መዋዠቅ ካሳዩ ግን ወደ ሆስቴል እንዲመለሱ ይደረጋል፡፡

“ጦሩ ነመኛታ...”ሰራዊቱን የሚወክል የእግር

ኳስ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው በ1937 ዓ.ም. ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በ1936 ጠቅል ብለው ውድድር ለማድረግ ሲሰናዱ የወታደር ቡድን ማሳተፍ ስላልተፈቀደ ተጨዋቾቹ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ገቡ፡፡ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ‹‹ንጉሱ ጋር ሄደው ጠይቀው ተፈቀደላቸው፡፡ ከዚያም ስማቸውን ጦር ሰራዊት ብለው መወዳደር ጀመሩ›› ይላል፡፡

ጦር ሰራዊት- መቻል፣ ምድር ጦር የሚሉ ስሞችን ቀያይሯል፡፡ 20ኛው ሜካናይዝድ ከዚያም በ1990 ዓ.ም. በተጀመረው የኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ባድመን ለማስለቀቅ በተካሄደው ዘመቻ ስም ፀሐይ ግባት ይባል የነበረው ቡድን በኋላ ላይ መከላከያ ጠቅሎታል፡፡

መቻል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ አይረሴ ታሪክ ያኖረ ቡድን ነው፡፡ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ የሻምፒዮና ዋንጫን ከፍ ማድረግም ችሏል፡፡

በ1957 ወታደራዊ ቡድኖች ከሲቪል ቡድኖች ጋር አብረው መጫወት የለባቸውም በሚል ፈረሱ፡፡ ስለሆነም ኦሜድላ፣ ንብ (የአየር ኃይል ቡድን)፣

አስጨናቂው አጥቂ •ዑመድ ኡኩሪ

Page 23: Awramba Times Issue #159

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 159 ቅዳሜ መጋቢት 10 2003 23

ተማሪዎቹ መምህሯን ተከትለው፣ ‹‹I am genius;›› ይላሉ፡፡ ልጆቹንም፣ ‹ትርጉሙ ምንድነው?› አልኳቸው፡፡ አንድም የመለሰልኝ ልጅ አልነበረም፡፡ በተግባር የማይገለጥ፣ ከዓመት ዓመት ቃሉን እየደገምን የምንሸጋገር ከሆነ፣ ስንት ሺህ ዜጋ ያለሥራ ቤት እንደተቀመጠ እንዲህ ያሉ ተጨማሪ ዜጎችን ማፍራት ይሆናል፡፡ ‹አንድ ሰው ማስትሬት፣ ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ ይዞ ከራሱ አልፎ ሌላውን መርዳት ሲገባው እቤቱ ቁጭ ካለ፣ ትምህርቱ ያልፈታው አንድ ችግር አለ ማለት ነው› ብለዋል፡፡

የሥልጠና ማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ሌላው ያነሱት ነጥብ የሥርዓትን ጉዳይ ነው፡፡ የሥርዓት መለዋወጥ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ያልሰሩ ሰዎች የሚደርሱበት የማይገባ ቦታ፣ ጥረቱ ያልታየ፣ የወጣ የወረደበት የማይታወቅ ሰው ፎቅ ሰርቶ፣ ብዙ ንብረት አካብቶ ሲታይ አቋራጭ መንገዶች እንዳሉ ታች ያለው ሕብረተሰብ ይገነዘባል፡፡ ዶ/ር ወሮታው ይህንኑ ሀሳባቸውን ሲያጠናክሩ፣ ‹‹የእነበቀለ ሞላ፣ የእነተካ ኢገኖ፣ የእነጌታቸው ቢራቱ፣ የእነ ሰዒድ መሀመድ ብርሀነ፣ የእነሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ እድገትና ሩጫ በግልፅ ይታያል፡፡ መውደቅ መነሳታቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ያልደከሙ ሰዎች እድገትና ብልፅግና ከታየ፣ ድንገተኛ እድገት የሚስተዋል ከሆነ፣ ሌላ አቋራጭ መንገድ መኖሩ ይታሰባል፡፡ ለምሳሌ፣ በደርግ ግዜ ያ ሁሉ የደከመ ሰው ንብረት መወረሱና ያልደከሙ ሰዎች በዚያ ቤት ውስጥ ገብተው በነፃ መኖራቸው፣ የሰሩት ቤታቸውን ሲያጡ፣ ያልሰሩት አከራይተው በነፃ መኖራቸው ተገቢነት አልነበረውም፡፡ ይሄ የተዛባ የሥርዓት ለውጥ በሕብረተሰቡ አመለካከት ላይ የፈጠረው ትልቅ ተፅዕኖ አለ፡፡ ስለሆነም ሥርዓቱ ያልሰራውን የሚሸልም፣ ያለደከመውን የሚያበረታታ መሆን የለበትም፡፡

ዶ/ር ወሮታው

የመገናኛ ብዙሃኑን ሚናም ሳያነሱ አላለፉም፡፡ ‹‹ሚዲያው አብዛኛውን ግዜ የሚያወራው ቼልሲና ሊቨርፑል [የእንግሊዝ የእግር ኳስ ክለቦች] እያለ ነው (የመንግስት ሚዲያ ሳይቀር)፡፡ ዛሬ የእግር ኳስ ጨዋታን የሚያሳዩ ድንኳኖች መብዛታቸውን እያየን ነው፡፡ የእኛን ችግር ደብቀው ሌላ የሚደነቅ፣ የእኛን ኑሮ የሚሸፍን ነገር በስፋት ያቀርባሉ፡፡ የእኛን ጉዳይ መፈትፈትና ማቡካት ሲገባን በየእለቱ የሚያቀርቡልን የማንቼና የቼልሲን ጨዋታ ነው፡፡ አያውሩ አይደለም፡፡ ግን እንዴት ይሄንን ያህል ግዜውን ይይዙብናል? ይሄ እኮ ‹የራሷ ሲያርባት የሰውን ታማስላለች› እንደተባለው ነው፡፡›› ሲሉ ኢንተርፕርነሩ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡

በቅርቡ እጄ ላይ የገባች ‹‹ወደቅኝ ግዛት የሚወስደው ባቡር›› የምትል አነስተኛ መጽሐፍ አንብቤ ነበር፡፡ የመጽሐፏ ደራሲ አቶ ቴዎድሮስ ተስፋዬ ናቸው፡፡ ሀገርን፣ ባህልና ታሪክን መሠረት በማድረግ የተፃፈችው ይህችው መዳፍ የምታክል መጽሐፍ፣ በአሁኑ ወቅት ስለሚታየው አሳሳቢ ሁኔታ የሚከተለውን ሀሳብ አስፍራለች፤ ‹‹የሀገር ባህል አልተከበረም፣ ተዋርዷል፡፡ የሕዝብ ማንነት፣ ባህልና እምነት ሁሉ አልተከበረም፣ ተዋርዷል፡፡ ሕዝብ ሰለሀገሩ ጥሩ አመለካከት እንዳይኖረው ተመርዟል፤ ዳር ድንበር አልተጠበቀም፤ የሕዝብ ጤና አልተጠበቀም፤ ጥራት ያለው፣ ማንነትን ያገናዘበ ትምህርት የለም፡፡ ሕዝቡ ከመንፈሳዊውም ሆነ ከገሀዳዊ ጠላቶቹ አልተጠበቀም፤ ያለጥበቃና ያለተከላካይ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ሕዝብ አንድነቱና ሰንደቅ ዓላማው ሁሉ አልተጠበቀም፣ አልተከበረም... ›› (ገፅ 20-21)፡፡

መጽሐፏ ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል የተዳረግንበት መንስዔ የሀገሪቱ መንግስት፣ የውጭ ኃይሎች (ምዕራባውያን) ተፅዕኖ እንዲሁም በተቃዋሚዎች ዙሪያ

እንዲሰባሰቡ የተደረጉ ኃይሎችና ቅጥረኞች ጭምር መሆናቸውን በአፅንኦት ትገልፃለች፡፡ የሀገሪቱ መንግስት የሕዝቡን አመለካከት፣ ባህል፣ ታሪክና ማንነት ፈፅሞ ማክበርና ማስከበር ያልቻለበትንም ምክንያት በዚህችው መጽሐፍ ላይ እንደሚከተለው ተጠቅሷል፡-

1ኛ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት አመጣጡ በኃይል መሆኑ፣

2ኛ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት ይረዳ የነበረው በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠ ላ ቶ ች መሆኑ፣

3ኛ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት የኮሚኒስት ስሪት ያለው መሆኑና ስለማንነት፣ ባህልና ሃይማኖት ደንታ ቢስ መሆኑ፣

4ኛ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት የአመራር አካላት ረጅሙን እድሜያቸውን ያሳለፉት በጫካ መሆኑ ህዝቡ ላዳበረው ባህል፣ አመለካከት፣ ታሪክ ሁሉ ደንታ ቢ ስ መሆናቸው (ከገፅ 21-22)፡፡

የአመራሩና የሥርዓት ጉዳይ ከተነሳ ስንሻው ተገኝ የተባሉ ጸሐፊ ከዓመታት በፊት ‹‹የመሪዎቻችን ቋንቋና ‹ውበቱ››› በሚል ርዕስ በጦቢያ መጽሔት ባቀረቡት መጣጥፋቸው ላይ ሲገልፁ፣ ‹‹ስለቀድሞ ነገስታት የወጣትነት ዘመን ስናነብ በመኳንንት ወግ ቤተ-መንግስት ውስጥ ምርጥ መምህራን ተመድበውላቸው የሀገራቸውን ታሪክና ባህል ጠንቅቀው፣ ለመሪነት የሚያበቃቸውን ትምህርት ተከታተሉ የሚለውን ነጥብ አስታውሳለሁ፡፡ የአመራር ትምህርት ይሰጥ የነበረው እንዴት ነበር? ለምሳሌ ንጉሱን በተመለከተ በወጣትነት ዘመናቸው የፊደል ብቻ ሳይሆን የመሪነት ትምህርት ግንዛቤ እንዲያስጨብጡላቸው ተመድበውላቸው የነበሩትን አንዳንድ የካቶሊክ ቀሳውስት (አባ ሳሙኤልና አባ የሮም ወዘተ እናስታውሳለን) ብለዋል፡፡

ትጥቃችንን ማን አስፈታን? ለሚለው ጥያቄ ከላይ እንደጠቀስኩት እነዚህን የመሳሰሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦች ይነሳሉ፡፡ ለችግሩ መፍትሄም ዶ/ር ወሮታው ያቀረቡት ሃሳብ እዚያው ችግሩ ያለበትን ቦታ በማከም ላይ ነው፡፡ የልጆች አስተዳደግና የትምህርት አቀራረቡን በማረም፣ የሥርዓቱን ባህሪ በማጥራት የተስተካከለ ማሕበረሰብና ጤናማ ዜጋ ማፍራት የሚቻል እንደሆነ አበክረው ገልፀዋል፡፡

ከላይ ያነሳሁላችሁ ወዳጄ በበኩሉ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችን ማብዛት አለብን ይላል፡፡ እርሱ እንደሚለው፣ ‹‹በጀግንነት የተዋደቁ፣ ለእውነትና ለቃላቸው የታመኑ፣ በፍቅር ወይም በሌላው ማህበራዊ ሕይወት ምሳሌ የሆኑ ሰዎች ታሪካቸው መወራት፣ ሙያቸው በስፋት መተረክና መነገር መቻል አለበት፡፡ እነዚህን ጀግኖች ለአዲሱ ትውልድ ማስተዋወቅ መቻል አለብን፡፡ እኛ ግን የሰውን ድክመትና ክፋት እንጂ በጎ ነገሩን ማውራት አንወድም፡፡ የሰውን ትልቅነት የማውራት ችግር አለብን፡፡ ‹እከሌ 24 ሰዓት ነው የሚሰራው፡፡ በዚህም ምክንያት አድጓል፣ ተለውጧል› የሚል ምሳሌ ማምጣት አለብን፡፡ ስለኳስም፣ ስለጥበብም ስታወራ ድሮ እነወጋየሁ ንጋቱ ትኩረታቸው ክፍያ ላይ አልነበረም፡፡ በእርግጥ አሁን ኑሮ ተወዷል፡፡ ግን የቤተሰባቸው አባል ሞቶ በእለቱ ሕዝብ አክብረው መድረክ ላይ ይገኙ ነበር እያልክ በምታወራው ሁሉ መልካም ነገሮችን መግለፃ፣ አርዓያ መፍጠር መቻል አለብህ›› ብሏል፡፡

ውድ አንባብያንስ፣ ምን ቢሆን ይበጃል ትላላችሁ? የቀረችንን ትጥቅ እንዳንፈታ የእያንዳንዳችን ድርሻና ኃላፊነት ምን ይሁን?

ትጥቃችንን ማን...

ሀገር አብራክ ተገኝተው፣ ድግስ እየደገሱ ከፊሉን ስለሚያበሉት ከፊሉ ላይ ደግሞ ትሪ ስለሚሰቅሉበት ወገኖች ማውራት ተገቢ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሰው መሆናቸውን እስከትናንት ማታ ድረስ አምነን ነበር፡፡ የምሽቱ ጨለማ ሲገፈፍ ግን አውሬነታቸው አብሮ ተገለጠ፡፡ ለካ ሰው ናቸው ብለን በቸርነት ውሃ ቀድተን ያጠጣናቸው ወገኖች ከጀርባቸው የሚነድ ትልቅ የእሳት ባህር አለ፡፡ ያንን እነሱ ለሁለት ነገሮች ይገለገሉበታል፤ አንደኛውን የድግሳቸውን ወጥ ሲያበስሉበት ሌላውን ደግሞ ከእነርሱ ጋር በተንኮል፣ ሰነድ በማቃጠል እና መረጃ በማጥፋት የማይተባበራቸውን ሰው ሁሉ ይፈጁበታል፡፡

ድግስ መደገስ ጥሩ ነው፤ ድግስን የመሰለ ነገር የለም እኮ፡፡ ምክንያቱም ድግስ ማለት መብላት መጠጣት ማለት ነው፡፡ ይህ ፅሁፍ የተፃፈበት ዓለማ የጋዜጣው ዓምድ ባዶ እንዲሆን ስለተፈለገ አይደለም፡፡ ወይም ደግሞ ሌላ አስቂኝ ፅሁፎችን እያተሙ አንገብጋቢ ጉዳዮችን ችላ ማለት ይቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሚገስፅ ጠፍቶ ሀገር የተመሰቃቀለች ዕለት ምን ሊውጠን ነው? የየትኛዋን ጋለሞታ ጎፎሬ ስታበጥሩ ነው ሀገሪቱ አይሆኑ የሆነችው? ከሚል ጥያቄ ለመዳን ሁሉም ኃላፊነቱን ይወጣ፡፡

አንዳንድ አፈንጋጭ ድግሳዊያን በሚደግሱት ድግስ ምክንያት ዜጋው የባይተዋርነት ስሜት ሊሰማው አይገባም፡፡ ድግሳችሁን እንድጠላ የሚያደርገኝ ነገር የጥሪ ካርዳችሁ የሚታደለው ሃይማኖት፣ ዘር፣ ደሀ፣ ደደብ

... እየለየ በመሆኑ ነው፡፡ በጥሪ ካርደችሁ አማካይነት ብዙዎች በራቸውን ዘግተው አለቀሱ፡፡ ለድብድብ ጊዜ ሰይፍ የሚያቀብል ሰው በሞላበት ሀገር የተገፉ ሰዎችን ለማባበል ግን ጎዳናው ሁሉ ጭር ይላል፡፡

ይሔ የመቧደን ጣጣ የሃይማኖት ሰዎችን ጭምር እያመሳቸው ነው፡፡ መዘምራኑም ሆነ ሰባኪያኑ ፎቶቿቸውን

የመጽሔት ሽፋን ላይ እያስወጡ መሰዳደብ፣ ‹‹ሰማዕትነት›› የቡድን ጉባኤ በማሰናዳት የሚገኝ ይመስል ጥድፊያው ሁሉ ጉባዔ አዘጋጅቶ ሌሎችን መሳደብ ነው፡፡ ለምሳሌ አንደኛውን ገባዔ ጥሎ ወደ ሌላኛው ጉባዔ የተሸጋገረ ሰው ስብከታዊ በሆነ አሽሙር ይሰደባል፡፡ ‹‹ይሁዳ፣ አርዮስ፣ ንስጥሮስ፣...›› ወዘተ ተብሎ በከሃዲነት ይፈረጃል፡፡ ጉባዔያቸውን የተቀላቀለውን

ግለሰብ ደግሞ ‹‹ጴጥሮስ፣ ማትዮስ፣ ያዕቆብ ...›› እየተባለ ይሽሞነሞናል (ይሔ የሚሆነው አንድ ሃይማኖት በሚከተሉ ሰዎች መካከል መሆኑ አይረሳ)፡፡ የእምነቱ ተከታዮችም እዚህም እዚያም በሚመሰርቱት የመከፋፈል ጉባዔዎች ምክንያት ተከፋፍለው ይቀራሉ፡፡ በደህናው ጊዜ መከፋፈልና ማካፈል የሒሳብ መጽሐፍ ላይ ለሰፈሩ ቁጥሮች ነው እንጂ ... ፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚያናድደው የነገሮች መበላሸት ሳይሆን ነገሮችን የሚያበላሹ

ሰዎችን መቅጣት አለመቻል ነው፡፡ ይሔ ማህበር ያኛውን ማህበር የጎዳ መስሎት መለያየትን በሰፊው ሊያውጅ ይችላል፡፡ ያኛው ጉባኤም እንደዛው፡፡ ግን አይደለም፡፡ በማህበር ምክንያት የምትጎዳው ሀገር ነች፡፡ ብዙ የማህበርና የጉባዔ አራማጆች ከተቃራኒያቸው በልጦ ለመገኘት በሚያደርጉት ሩጫ ውስጥ የምትረጋገጠው ሀገር መሆኗን ሁሉም ሊያውቀው ይገባል፡፡ ቡድን ቡድን ከልጆች ጨዋታ አልፎ ሀገር መናድ የለበትም፡፡

ባሏን ጎዳው ብላ...

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ n ‹ SgÝ“ ”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–< M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

መከላከያ ከደደቢትና እና ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ባደረጋቸው ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች ላይ የጎን ጉዳት ላይ ሆኖ በመሰለፉ ዑመድ ብቃቱ ደብዝዞ ነበር፡፡ አሁን በብሔራዊ ቡድን ልምምድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከጉዳቱ እያገገመ ነው፡፡ ይህም አሰልጣኝ ኢፌም ኦኑራን አስደስቷል፡፡ በቀጣዩ ሳምንት በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ናይጄሪያን በሌጎስ ለሚገጥመው ቡድን አደራውን ለመውጣት ጤንነቱ ይበልጥ እንደሚሻሻል ተገምቷል፡፡

በአስር ጎል በሁለተኛ የከፍተኛ ጎል አግቢነት ደረጃ ላይ የተቀመጠው አይን አፋሩ አጥቂ ከመከላከያ ጋር ዋንጫ ለመሳም፣ በግሉም የከፍተኛ ጎል አግቢነቱን ፉክክር በበላይነት ለማጠናቀቀ እንደሚጥር ይገልጻል፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካዊው ጆሞ ኮስሞስ ቡድን ሊያደርገው የነበረው

ዝውውር ‹‹በቪዛ ማጣት ችግር›› እንዳልተሳካ ቢገልፅም በዝውውሩ ዙሪያ ጥርጣሬ ያደረባቸው ሰዎች የጉዞው ወሬ ተበጀተ እንጂ የደቡብ አፍሪካው ክለብ ለመከላከያ ያቀረበው ጥያቄ እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡ የአር ኤንድ ቢ እና የራፕ ሙዚቃ አድናቂ የሆነው ዑመድም ይህንን አልካደም፡፡ ግንኙነት ያደርግ የነበረው በሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ከሚጫወተው ፍቅሩ ተፈራ ጋር ነበር፡፡ ለደ/አፍሪካ ኤምባሲ 8 ሺህ ብር አስይዞ ቢጠባበቅም ጥያቄው ምላሽ ማግኘት ስላልቻለ ‹‹ሁሉን ነገር ጨርሳችሁ ንገሩኝ ከእንግዲህ እኔ የማደርገው ጥረት የለም›› ሲል ምላሽ እንደሰጠው ይገልፃል፡፡ ‹‹በቀጣይ ወደ ግማሽ ሚሊዮን ብር ተከፍሎት ወደ ቅ/

ጊዮርጊስ ሊያመራ ነው!›› ተብሎ የሚወራውን ወሬ ፈገግ እያለ እንደማያውቀው ይናገራል፡፡ ከመከላከያ ጋር እስከ 2004 ዓ.ም. መጨረሻ የሚያቆየው ውል አለው፡፡

አራተኛ ቡድንና ሰባተኛ ሰው የመሆን ጉዞ

አስራት ኃይሌ፣ ስዩም ከበደ፣ ሰርቪያዊው ሰርዲዮቪች ሚሊቱን “ሚቾ” ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ጨብጠው መሳም ችለዋል፡፡ ሐጎስ ደስታ [ነፍስ ይማር] እና ጉልላት ፍርዴ መብራት ኃይልን እየመሩ የሊጉ ሻምፒዮን ሆነዋል፡፡ “ጋሽ ከማል” ከአዋሳ ከነማ ጋር ሁለት ጊዜ ዋንጫ ስመዋል፡፡

ዘንድሮ ሊጉ አዲስ አሸናፊ ቡድን ካገኘ አራተኛ ዋንጫ የሳመ ክለብ ይሆናል፡፡ አሸናፊው አሰልጣኝም ሰባተኛው የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ የሳመ ሰው ይሆናል፡፡ ሚቾ አምስት፣ አስራት፣ ስዩም

ከበደ እና ከማል ሁለት ጊዜ ዋንጫ በማንሳት ይመራሉ፡፡

መከላከያ እና ትውልዱ ከሰዴን ሶዶ (ምዕራብ ሸዋ) የሆነው አሸናፊ በቀለም አራተኛ ክለብ እና ሰባተኛ ሰው ለመሆን ማራቶኑን በመሪነት አጋምሰዋል፡፡ ይህ ብቻ በሊጉ ለሁለቱም አዲስ ሪከርድ ነው፡፡

የሴቶች ብ/ቡድን እና ባንኮችን (በአሁን አጠራሩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) አሰልጥኖ የሚያውቀው አሸናፊ ምህንድስናው ተሳክቶ የአሸናፊነቱን መንገድ ከቀየሰ በአትሌቲክስ ስፖርት ዝና ያለው መከላከያም የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ይስማል፡፡ ሊጉም ‹‹አዲስ አሸናፊ አሰልጣኝ ወለድኩ›› ብሎ ስለሚያውጅ፤ አሸናፊ- አሸናፊ በመሆኑ “ስምን መልዐክ ያወጣዋል” የሚለው አባባል በእሱ ላይ መስራቱ ይረጋገጣል፡፡

ለዚህ ፅሁፍ ማዳበሪያነት የመከላከያ እግር ኳስ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ እና ከፍተኛ የበላይ •አመራሮችን አስተያየት ለማካተት በአካል ተገኝቼ ተደጋጋሚ ሙከራ ባደርግም ‹‹ለመናገር የክለቡ ፈቃድ ያስፈልጋል›› ለሚለው መተዳደሪያ ደንብ ፈቃድ ሰጪ አካል ባለማግኘቴ

አልተሳካም፡፡ ስለ እግር ኳስ ለማውራት ፈቃደኝነት አለመኖር ምን ይሉታል?

አጥቂው. . .