27
ቴቴቴቴቴቴ ቴቴ ቴቴቴ ቴቴቴቴቴ ቴቴቴ (ቴቴቴ ቴቴቴቴ)

100% Technology Copy Manual

Embed Size (px)

DESCRIPTION

This document ( amharic version) gives technology workers a clue as to how to identify and copy technolgy.

Citation preview

Page 1: 100% Technology Copy Manual

ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስልት

( ረቂቅ ማኑዋል)

ፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/አጄንሲ

ሰኔ 2005 ዓ. ም

አዲስ አበባ

Page 2: 100% Technology Copy Manual

ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስልት

ይዘት ገጽ

መነሻ ኃሳብ/ አስፈላጊነት -----------------------------------------

ዓላማዎች ------------------------------------------------------------

ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስራ-----------------------

- ምንድነው፣

- ከዬት ይገኛል፣

- ዬትና በማን ይተገበራል፣

- መቼና ለምን ይተገበራል

- እንዴት ይተገባራል?

ድጋፍና ክትትል እና ግምገማ -------------------------------------

Page 3: 100% Technology Copy Manual

ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስልት

1. መነሻ ሀሳብ/አስፈላጊነት

የቴ/ሙ/ት/ስ/ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራን መተግበር ከጀመርን ዓመታት ያለፉ ቢሆንም በአፈጻጸሙ ዙሪያ

ከስትራቴጂያችን አንጻር የተለያዩ ተግዳሮቶች ሲያጋጥሙ ይስተዋላል፡፡ ለአብነትም የእሴት ሰንሰለቶችን

በመከተል የልማት ፕሮግራሞቻችንን ፍላጎት ነቅሶ በማውጣት የሚፈለገውን ቴክኖሎጂ መቶ በመቶ ቀድቶ

ለሚፈለገው ዘርፍ አለማቅረብና ተወዳዳሪነትን በጉልህ ማረጋገጥ አለመቻል እንደ ዋና ዋና ችግሮች ሊታዩ

ይችላሉ፡፡

የእነዚህ ችግሮች መገለጫዎችም በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቻችን አሁንም

ቢሆን በምርጥ ቴክኖሎጂ እጦት ምክንያት የምርትና የአገልግሎታቸው ጥራት ዝቅተኛ ስለሆነ በአገር ውስጥ

በቀላሉ ተሰርተው ገቢ ምርቶችን መቀነስ በሚችሉባቸው እንደ ከእንጨትና ከብረታብረት የተሰሩ የቤትና ቢሮ

እቃዎች ላይና በዝቅተኛ ቴክኖሎጂ በሚሰሩ የእጅ መሳሪዎች እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታቸውን

ማረጋገጥ አለመቻላቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአብዛኛዎቹ ኮሌጆቻችን ውስጥ እስካሁን የተመረቱ

ቴክኖሎጂዎች ይህንን ችግር መፍታት ስላልቻሉ በብዛት ሳይሸጋገሩ በየቦታው ተከምረው መታየታቸውና

ጥራታቸውም ከደረጃ በታች መሆናቸው ነው፡፡

የቴክኖሎጂ ስራዎቻችን ከኢኮኖሚና ፋይናንስ አዋጭነት አንጻር ባለመታየታቸውና በኢንተርፕሬነርሺፕ ክህሎት

ባለመታገዛቸው የማምረቻ ዋጋዎቻቸው ትክክለኛ ያልሆኑና ተአማኒነት የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ

ከተወዳዳሪነት አንጻር ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቻችንና ልማት ፕሮግራሞቻችን እምብዛም እሴት

የማይጨምሩ ከእንጨት ሪፍሪጄሬተሮችን ከላሜራ የልብስ መተኮሻ ካውያዎችን የመሳሰሉ ስታንዳርዳይዝድ

ምርቶችን ለማምረት እየሞከርን ያለንበት ቦታዎችም ይስተዋላሉ፡፡

በተጨማሪም በአንዳንድ ኮሌጆችና ክልሎች ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ በመቅዳት ስልታችንን በሚገባ

ካለመገንዘብ የተነሳ አዲስ የፈጠራ ስራዎችን በመስራትና ነባር ቴክኖሎጂዎችን በመለወጥ

(modification) ምክንያት በአላስፈላጊ የዲዛይንና ሳይንሳዊ ትንተና ስራዎች ላይ ጊዜያቸውን እያጠፉ

ይገኛሉ፡፡

ስለዚህ በተደጋጋሚ በፈረንጆቹ "there is no need to invent a wheel again" እንደሚሉት

ቀደምት አምራቾች በአሁን ዘመን በስራ ላይ የዋሉ ማናቸውንም ቴክኖሎጂዎች ከማምረታቸው በፊት በቂ

የዲዛይንና ሳይንሳዊ ትንተናዎች ያደረጉ በመሆናቸው እኛ በዚህ ስራ ላይ አብዛኛውን ጊዜያችንን ማባከን

አይኖርብንም፡፡ ይልቁንም ማተኮር ያለብን ለልማት ፕሮግራሞቻችን በተለዩት የትኩረት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ

Page 4: 100% Technology Copy Manual

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቻችንን ተወዳዳሪነት ያሳድጋሉ የምንላቸውን ቴክኖሎጂዎች በፍጥነት ፈልገን

በትክክል ቀድተን፣ አምርተንና ፈትሸን በማሸጋገሩ ስራ ላይ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ነው ቴክኖሎጂን መቶ

በመቶ መቅዳት የሚለውን ስልት መከተል አለብን የምንለው፡፡

እስካሁን በስራ ላይ የዋለው የቴክኖሎጂ ሽግግር ማኑዋል የቴክኖሎጂ ሽግግር አተገባበርን ታሪካዊና

ጽንሰሃሳባዊ መሰረት በግልጽ ያስቀመጠና በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታም የአተገባበር ቅደም ተከተሎችን

ያስቀመጠ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ወደ መሬት ወርደን የቴክኖሎጂ ሽግግር አተገባበራችንን ስናይ ከላይ የተጠቀሱት

ችግሮች እያጋጠሙን ያሉት ማኑዋሉን በትክክል ተገንዝበን ባለመከታለችን መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

በመሆኑም ለወደፊቱ ያሉብንን ተግዳሮቶች አስወግደን የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎቻችንን በተገቢው ሁኔታ

ከልማት ፕሮግራሞቻችን ተወዳዳሪነት አንጻር በመቃኘት መተግበር ያስችለን ዘንድ ይህን ቴክኖሎጂን መቶ

በመቶ የመቅዳት ስልት አተገባበር ቼክሊስት በተጨማሪነት ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል፡፡

2. የቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ዓላማዎች

ለኢንደስትራላይዜሽን መሰረት ለሆኑት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚሰጡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሰልጣኞችና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ቴክኖሎጂን

መቶ በመቶ የመቅዳት አቅም ለመገንባት፣

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቻችንን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሊያደርጉ የሚችሉ ምርጥ ቴክኖሎጂዎችን በማቀብና በማከማቸት የተሻለ ገበያና የስራ ዕድል መፍጠር እንዲችሉ

ለማገዝ፣

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቻችንን ምርትና አገልግሎት ጥራት ለማሳደግ፣

በቀጣይነት ቴክኖሎጂን ለማሻሻል፣ለማላመድና ለፈጠራ ስራ መሰረት ይጥላል፣

Page 5: 100% Technology Copy Manual

3. ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስራ ምንድነው? በማን፣ ዬት፣ መቼ፣ ለምንና እንዴትስ

ይተገባራል?

3.1. ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ መቅዳት ምንድነው?

ስለ ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ መቅዳት ከማንሳታችን በፊት መጀመሪያ የቴክኖሎጂን ምንነት መረዳት ይፈልጋል፡፡

የተለያዩ መዝገበ ቃላት ቴክኖሎጂን በተለያዩ አስተሳሰቦች የተረጎሙት ቢሆንም በምንከተለው የቴክኖሎጂ

አቅጣጫና በዚህ ማኑዋል መሰረት ቴክኖሎጂ ማለት አንድ አዲስ እሴት በመፍጠሩ ወይም በመጨመሩ

ምክንያት ተጠቃሚዎች ወይም ደንበኞች ከሌሎች አብልጠው በፍላጎት ሊገዙት የሚችሉት ቁስ፣ ማምረቻ

መሳሪያ፣ አሰራር ወይም አገልግሎት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡

ቴክኖሎጂን በሁለት አይነት ማለትም በምርት/ አገልግሎት እና በማምረቻ ቴክኖሎጂዎች ከፍለን ማየት

እንችላለን፡፡ የምርት ቴክኖሎጂ የምንለው ሰዎች በነፍስ ወከፍ የሚጠቀሙበት (consume የሚያደርጉት)

እንደ ምግብና ሸቀጣ ሸቀጦች ሲሆኑ የማምረቻ ቴክኖሎጂ ደግሞ እነዚህን የምርት ቴክኖሎጂዎች

የምናመርትበት መሳሪያዎች ወይም ማሽኖች ናቸው፡፡

ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ መቅዳት ማለት በቀላሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነት ያላቸውን እነዚህን እቃዎች፣

መሳሪያዎች ወይም አገልግሎቶች አፈላልገን አግኝተን አንድ በአንድ አካሎቻቸውን ፈታተንና ውስጣቸውን

ፈትሸን በመቅዳት ለአገር ውስጥ ገበያ ማቅረብና ማስቀረት ነው ብለን መውሰድ እንችላለን፡፡

3.2. የሚቀዳውን ቴክኖሎጂ ከዬት እናገኛለን?

በዓለማችን ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የተሰማሩበትን ዘርፍ ትርፋማ እንዲሆንና በገበያም ውስጥ ተወዳዳሪ

ሆኖ እንዲቆይ የማያቋርጥ ምርምር በማድረግ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረውም ሆነ ለዋውጠው ለገበያ

በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ ምርቶች ወይም ቴክኖሎጂዎች የዓለም አንዷ ገበያ ወደ ሆነችው አገራችንም

በገቢ ምርትነት ይገባሉ፡፡ አንዱ የምርጥ ቴክኖሎጂ ምንጫችን እነዚህ ገቢ ምርቶች ናቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ

በ direct foreign investment ወደ አገራችን ገብተው በሚገኙ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ

የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በአገራችን ውስጥ እየተመረቱ የሚገኙ የኤክስፖርት ምርቶችም እንደ ቴክኖሎጂ

ምንጭነት ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ በምስልና በቪዲዮ ተለቀው

የሚገኙ ነጻ መረጃዎች የሚገኙ ቴክኖሎጂዎች ናቸው፡፡

3.3. ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ መቅዳት ዬትና በማን ይተገበራል?

በተለያዩ የልማት ፕሮግራሞቻችን ተሰማርተው የሚገኙ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቻችን እንደ ምንም

አንዴ ያገኙትን ቴክኖሎጂ በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆነው ለመሸጥ የሚያስችላቸውን የዕለት ተዕለት ስራዎች

Page 6: 100% Technology Copy Manual

በመስራት ላይ ስለሚያተኩሩ አዳዲሶቹን አፈላልጎ ለመቅዳት ጊዜ፣ አቅምና ፍላጎቱ አይኖራቸውም፡፡

በማምረቻዎቻቸው አካባቢም ለዚህ አገልግሎት የሚሆን ትርፍ ቦታ ይኖራቸዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡

ስለዚህ ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስራዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋሞች ወይም

መሰረተ ልማቶች ውስጥ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተቋሞቻችን የቴክኖሎጂ መፍለቂያ ማዕከላት

ይሆናሉ የምንለውም ለዚህ ነው፡፡ በተቋሞቹ ስር የሚተዳደሩት የምርት ማዕከላትም (Production Units)

ከአሁን በፊት እንደሚሰሩት አንዴ ገበያ ላይ የዋለን ቴክኖሎጂ በብዛት በማምረት ለገበያ በማቅረብ

በቴክኖሎጂው ገበያ የውድድር ምህዳር ላይ አላስፈላጊ ተጽዕኖ መፍጠር የለባቸውም፡፡ ይልቁንም የስራ

ድርሻቸው መሆን ያለበት ምርጥ ቴክኖሎጂዎችን መቶ በመቶ መቅዳትና መፈተሸ መሆን ይኖርበታል፡፡ እንደዚህ

በምንልበት ጊዜ ግን ኢንተርፕራይዞቹ በሂደቱ ውስጥ ድርሻ የላቸውም ማለት አይደለም፡፡

ለተወዳዳሪነት የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ ፍላጎትን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመለየት ስራዎችን ( መቶ በመቶ

የተቀዳውን ቴክኖሎጂ በመፈተሽ፣ በማብዛትና በማሸጋገር ዙሪያ ያሉትን ተግባራት) ከማከናወን አንጻር ከፍተኛ

የስራ ድርሻ እንደሚጠበቅባቸው መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት

ስራዎች በዋናነት በማን መተግበር እንዳለበት ግንዛቤ መውሰድ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሰው ሀብታቸውን ቴክኖሎጂን መቶ

በመቶ በመቅዳት ስራዎች ላይ ለማዋል ፍላጎቱም ሆነ አቅሙ የላቸውም፡፡ ስለዚህ ይህ ስራ መሰራት ያለበት

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምህራን/ አሰልጣኞች እንደሆነ ይጠበቃል፡፡

በፕሮጄክት ላይ የተመሰረተ የአሰለጣጠን ዘዴ ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ ከመቅዳት አሰራር ጋር በቀጥታ

ግንኙነት ያለው ስለሆነ ከሁሉም በፊት ፕሮጄክትን መሰረት ባደረገ ስልጠና ዘዴን በመጠቀም

የአሰልጣኞቻችንን ክህሎት ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ በመቅዳት ስራ ላይ መገንባት አማራጭ የሌለው ስራ

ነው፡፡ አሰልጣኞች የተለያዩ አዋጭ ፕሮጄክቶችን ራሳቸውን ችለው መስራታቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡

በየኮሌጆቹ የሚሰሩ ፕሮጄክቶችም ከመሰራታቸውና ወደ ኤግዝቢሽን ከመውጣታቸው በፊት በቴክኒካል፣

ኢኮኖሚካልና ፋይናንሻል አዋጭነታቸው ላይ በዘርፉ ባሉ ባለሙያዎችና ደንበኞች አስተያየት ሊሰጥበት

ይገባል፡፡ ያላለቁ ቴክኖሎጂዎችንም ወደ ኤግዚቢሽኖች ማቅረቡ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለው ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ፕሮጄክትን መሰረት ባደረገ የስልጠና ሂደት ውስጥ በሚገባ ያለፉ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች ብቻ ቴክኖሎጂን

መቶ በመቶ የመቅዳት ስራን በብቃት ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡

3.4. ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ መቅዳት መቼ ይተገበራል?

Page 7: 100% Technology Copy Manual

እስካሁን ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባሮቻችንን ሙሉ በሙሉ መቶ በመቶ በመቅዳት ያላተኮረና የልማት

ፕሮግራሞቻችንን ተወዳዳሪነት ከማድረግ አንጻር ይህ ነው የሚባል ግብአት ካለማምጣቱም በላይ የተሰሩ

ቴክኖጂዎችም በተወሰኑ ጊዜዎች ብቅ እያሉ የሚጠፉና የሚረሱ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ዓለማችን ዳይናሚክ በሆነ ውድድር ውስጥ ያለችበት ወቅት በመሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እየተለዋወጡ

ያሉት በሚያስገርም ፍጥነት ነው፡፡ የሙያ ደረጃ ምደባችንም ይህንኑን ሂደት የሚከተል መሆኑ ይታወቃል፡ በሌላ

በኩልም የምንከተለው የምርት ጥራትና ምርታማነት ማስጠበቂያ የካይዘን ስርአታችንም የማያቋርጥና ተከታታይ

የሆነ የማሻሻያ ስራዎችን ካልሰራንና በአንድ ወቅት ስኬት ላይ ብቻ ተንጠልጠለን ቁጭ ካልን ገበያ ውስጥ

ተወዳዳሪ መሆን እንደማንችል ያረጋግጥልናል፡፡ ከዚህ በመነሳት ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት

ተግባራችንም የአንድ ወቅት ተግባር ሳይሆን በተለያዩ የልማት ፕሮግራሞቻችን ላይ ተሰማርተው ያሉ ጥቃቅንና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቻችን ምርቶችና አገልግሎቶች ጥራትና ምርታማነት ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ

የቴክኖሎጂ ተግዳሮቶችን በተከታታይነት ነቅሶ በማውጣትና መፍትሄ በማስቀመጥ በአለም አቀፍ ደረጃ

ምንጊዜም ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ መሆን እንዳለበት መገንዘብ

ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስራችን እንደ አንድ መደበኛ ስራ የማያቋርጥ ነው

ማለት ነው፡፡

3.5. ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ መቅዳት ለምን?

አሁን ያለንበት ዘመን አለማቀፍ የኢኮኖሚ ትስስር የሰፈነበት ሲሆን ኢትዮጵያም የዚሁ ትስስር አካል ናት፡፡ ከዚህ

ጋር ተያይዞ የሚከሰተው አለምአቀፍ የገበያ ውድድር ደግሞ ድንበር ዘለል ከመሆኑ የተነሳ በመጪው ጊዜ

የገበያው ባለቤት የሚሆኑት በሂደቱ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ኢንተርፕራይዞች

ብቻ ናቸው፡፡ አንድ ኢንተርፕራይዝ ደግሞ ከተወዳዳሪዎቹ ልቆ እንዲገኝ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ለገበያው

የሚያቀርበው የቴክኖሎጂ ወይም የምርት ጥራትና የዋጋ ተወዳዳሪነት ነው፡፡ አንድ ኢንተርፕራይዝ ለገበያ

የሚያቀርበው ብቻ ሳይሆን በየጊዜው እየተሻሻለ የሚመጣና የደንበኛውን ቀልብ ስቦ በቀላሉ መሸጥ የሚችለው

ቴክኖሎጂ ከሌለው በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ መቀጠል አይችልም፡፡

ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው ደግሞ በቀደምት አምራቾች የተሰሩ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ያሉ

አዋጭ ቴክኖሎጂዎች በገቢ ምርትነት ወደ አገራችን እየገቡ ነው፡፡ ስለዚህ በአገራችን ውስጥ ገበያ ለመፍጠር

ጊዜ ፈጅ በሆኑ የምርምር ስራዎች ላይ ከመኳተን እነዚህን ተክኖሎጂዎች ምንም ሳናስቀር መቶ በመቶ

በመቅዳት ወይም በመኮረጅ ገበያውን መፍጠርና ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችል ቀላልና አቋራጭ መንገድ

ስለሆነ ነው፡፡

Page 8: 100% Technology Copy Manual

3.6. ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ መቅዳት እንዴት ይተገበራል?

ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ ለምዳት ከመነሳታችን በፊት መሰራት ያለበት ስራ የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን የመለየት

ስራ ነው፡፡ የተክኖሎጂ ክፍተቶች የመለየት ስራ የሚተገበረው የእሴት ሰንሰለት ትንተናን በመጠቀም ነው፡፡

የእሴት ሰንሰለት ማለት አንድ ምርት ወይም አገልግሎት ሲመረት ጥሬ እቃን ከማዘጋጀት ጀምሮ ምርቱ ተመርቶ

አልቆ የሚፈለገውን አሴት ሰጥቶ ደንበኛው እጅ እስኪገባ ድረስ ያለውን ከጫፍ አስከ ጫፍ ሂደት የሚያሳይ

ትንተና ነው፡፡ በዚህ ትንተና አማካይነት በያንዳንዱ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችና ችግሮቹን ለመፍታት

የሚያሰፈልጉ ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ በመለየት መወሰን እንችላለን፡፡በእሴት ሰንሰለት ትንተና የቴክኖሎጂን

ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የክህሎትና ሌሎችንም የመፍትሄ እርምጃ የሚፈልጉ የግብአት ችግሮችንም ልናይበትና

ልንለይበት እንችላለን፡፡

ለምሰሌ ያክል በአገራችን ብዛት ያላቸው ጥቃቀንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከእንጨትና ከብረት የተለያዩና

ብዛት ያላቸው የእንጨት የቤትና ቢሮ እቃዎች እያመረቱ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ

መሆን ባለመቻላቸው የተለያዩ የእንጨት የቤትና ቢሮ እቃዎች ከማሌ¡ ያና ከቻይና ከመሳሰሉት አገራት በብዛት

አየገቡ እየተሸጡ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ የኢንተርፕራይዞቹን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ክፉኛ በመጉዳት ላይ ከመገኘቱም

በላይ ኢንተርፕራይዞቹ በዝቅተኛ የጥራት ደረጃ ገበያ ውስጥ ከመኖር በበለጠ ገቢ ምርት በማስቀረትና ብሎም በአለም

አቀፍ ገበያ ለመወዳዳር የሚያስችላቸው ቁመና ላይ አይደሉም፡፡

እንግዲህ አንድ ተክኖሎጂን መቶ በመቶ በመቅዳት ስራ የሚሰራ ሰው የዚህን ችግር መነሻ ለማግኘትና ለችግሩም

መፍትሄ ለማፈላለግ በመጀመሪያ የምርቱን/ ንኡስ ዘርፉን/ ዘርፉን የእሴት ሰንሰለት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

ለአብነት በኢንዱስትሪ ዘርፍ በማኑፋክቸሪንክ ንኡስ ዘርፎች አንዱ የሆነውን ከእንጨት የቤትና ቢሮ እቃዎች

ምርት የእሴት ሰንሰለት ለማየት አንሞክር፡፡

Page 9: 100% Technology Copy Manual

ከእንጨት የቤትና ቢሮ እቃዎች ማምረት የእሴት ሰንሰለት

ከላይ ከእሴት ሰንሰለቱ ለማየት እንደሚቻለው ከእንጨት የቤትና ቢሮ አምራች የሆኑ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገቢ ምርቶችን በመተካት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ

ከሚያደር ¹ ቸው ጉዳዮች አንዱ በእንጨት መሰንጠቂያዎች በደንብ ደርቀው የወጣላት ጣውላ ስለማያገኙና ባልደረቀ ጣውላ የሚሰራ እቃ ደግሞ ጥራቱ ዝቅተኛ ይሆንና ተወዳዳሪ አያደርግም ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ በመቅዳት ስራ ላይ የተሰማራ ባለሙያ በመጀመሪያ የተሰማራበት ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዳይሆን የሚያደርጉ የቴክኖሎጂም ሆነ የሌሎች ችግሮችን የአሴት ሰንሰለቱን ተከትሎ ነቅሶ ማውጣት ይጠበቅበታል፡፡

ለምሳሌ ከላይ በሚታየው የእንጨት ፈርኒቸር የእሴት ሰንሰለት መሰረት የሴክተሩ መሰረታዊ ችግር በእንጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካዎች ውስጥም ሆነ በፈርኒቸር አምራቾች የማድረቂያ ቴክኖሎጂ ችግር መኖሩ ነው፡፡

ስለዚህ የቴክኖሎጂ ባለሙያው በቀጥታ የእንጨት ማድረቂያ ቴክኖሎጂን ወይም ማሽን በዘርፉ አሉ ከሚባሉ ድርጅቶች ወይም ፋብሪካዎች ማፈላለግ ነው፡፡

1. የደን ልማት 2. ለጣውላ የሚሆኑ

ዛፎች ቆርጦ ማዘጋጀት

3. የጣውላ ምርት 4. የቤትና ቢሮ እቃዎች

ምርት.5. ለገበያ ማቅረብ.5. ለገበያ ማቅረብ3. የጣውላ ምርት3. የጣውላ ምርት 4. የቤትና ቢሮ እቃዎች

ምርት

4. የቤትና ቢሮ እቃዎች

ምርት1. የደን ልማት1. የደን ልማት 2. ለጣውላ የሚሆኑ

ዛፎች ቆርጦ ማዘጋጀት

2. ለጣውላ የሚሆኑ

ዛፎች ቆርጦ ማዘጋጀት

3.1 በትክክል የደረቀና

ያልጎበጠ ጣውላ ማምረት

3.1 በትክክል የደረቀና

ያልጎበጠ ጣውላ ማምረት4.1 ገቢ ምርቶችን

የሚተኩ ምርቶችን

በማምረት ተወዳዳሪ

መሆን

4.1 ገቢ ምርቶችን

የሚተኩ ምርቶችን

በማምረት ተወዳዳሪ

መሆን

5.1 ጥራቱን የጠበቀ

ምርት በተፈለገ ጊዜና ቦታ

ለደንበኛ ማቅረብ

5.1 ጥራቱን የጠበቀ

ምርት በተፈለገ ጊዜና ቦታ

ለደንበኛ ማቅረብ

3.2. ከ ችግሮች አንዱ

ለገበያ የሚቀርበው ጣዉላ

ደርቆ ያልወጣለትና የጎበጠ ነው

ነው ( የማድረቂያ ቴክኖሎጂ

የለም)

4.2. ከችግሮች አንዱ

በደንብ ባልደረቁ ጣዉላዎች

የሚሰሩ እቃዎች ጥራት ዝቅኛ

ስለሆነ ተወዳዳሪ አያደርጉም

ችግሮች

1.

2.

Page 10: 100% Technology Copy Manual

ስእል 1. የተለያዩ መጠን ያላቸው የጣውላ ማድረቂያ ቴክኖሎጂዎች(technoware)

በመጀመሪያ ደረጃ ቴክኖሎጂው/ ማሽኑ በአገር ውስጥ ከተገኘ የሚከተሉትን ስራዎች መስራት ያስፈልጋል፡፡

1. ማሽኑን ካለበት ቦታ ወደ ራስ ወርክሾፕ ማምጣት ወይም ባለበት ቦታ መስራት እንዲቻል ማመቻቸት፤

2. የማሽኑን አሰራር በጥልቅ ማጥናትና መረዳት

3. ማሽኑን አካለት አንድ ባንድ መፈታታትና መስሪያ ንድፍ መስራት

4. ማሽኑን በነበረበት ሁኔታ መልሶ መገጣጠም

5. በንድፉ መሰረት እያንዳንዱን አካል መፈብረክ

6. የተፈበረኩት አካላት በንድፉ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ

7. የተፈበረኩትን አካላት በንድፉ መሰረት ልክ እንደ ዋናው መገጣጠም ( በዚህ ደረጃ ፕሮቶታይፕ ሰራን ማለት ነው፡፡)

8. የተገጣጠመውን ማሽን መስራት አለመስራቱን ለሰአታት አንደ ስራው ሁኔታ test run በማድረግ ማረጋገጥ

9. በ test run የታዩትን ግድፈቶችም ሆነ ማስተካከያዎች ማድረግና ማረም

10. ማሽኑን ወደሚፈለገው ስራ ቦታ ወስዶ በምርት ላይ መሞከርና የሚያጋጥሙ ቴክኒካል ችግሮችን ሪኮርድ ማድረግ

11. ያጋጠሙ ችግሮችን እንደገና ማረምና ለአብዠዎች ማስተላለፍ

ከላይ የተዘረዘሩት ስራዎች በእሴት ሰንሰለቱ መሰረት እንደ ችግር የወጣው ቁሳዊው ቴክኖሎጂ ወይም tec ሀ noware እንነደሆነ በመውሰድ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ እንጨትን ማድረቂያ ሌሎች

ለምሳሌ የእንጨት አደራደርንና ሳይበላሽ የማቆያ ዘዴዎችንም አንደ አሰራር ቴክኖሎጂ ወይም infoware በመውሰድ ልንቀዳ እንችላለን ማለት ነው፡፡

ስእል.2 የእንጨት አደራደር ቴክኖሎጂ (infoware)

Page 11: 100% Technology Copy Manual

በሁለተኛ ደረጃ ቴክኖሎጂው አገር ውስጥ የማይገኝ ከሆነም የተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ ያሉትን መረጃዎች በመፈላለግ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን መግኘት ይቻላል፡፡ ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ለአብነት

በአካባቢ ያሉ ጥሬ ግብአቶችን በመጠቀም የእንጨት ማድረቂያ ማሽን መስራት አንደሚቻል ከ dnr.wi.gov/files/pdf/pub/fr/FR0396.pdf "buildind your own lumber dry lumber dry klin with local buliding materials" የሚል መመሪያ ማግኘት ተችሏል፡፡

በዚህ አይነት ሌሎችንም ቴክኖሎጂዎች አፈላልጎ በማግኘት መቅዳት ይቻላል ማለት ነው፡፡ ከተለያ ምንጮች የምናገኛቸውን ንድፎች ካለን ተጨባጭ ሁኔታና የግብአቶች ሁኔታ ጋር በማጣጣም ከላይ

በተጠቀሱት ቅደም ተከተሎች መሰረት ቴክኖሎጂን መቅዳት እንችላለን፡፡

ይህ ሰነድ ለመነሻነት ያክል በአንድ ንኡስ ዘርፍ ላይ በመመስረት መቶ በመቶ ሊቀዱ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በምሳሌነት አቀረበ እንጂ ዝርዘር ንድፎችን የማቅረብ አላማ እንደሌለው ሊታወቅ

ይገባል፡፡ ስለዚህ የተለያዩ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎቻችን በዚህ ምሳሌ መሰረት በተሰማሩበት ዘርፍ ቴክኖሎጂዎችን መቶ በመቶ በመቅዳት ተወዳዳሪነት ከማጎልበትና ይህንን ሰነድም ከማሻሻል አንጻር

የበኩላቸውን አስተዋጽዎ ሊጫወቱ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስራ ክትትልና ድጋፍ ስራ የዋናው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ክትትልና ድጋፍ መመሪያና ቼክሊስት አተገባበር አካል ነው፡፡በዚህም መሰረት በአሰልጣኞች

ልማት ግቦች ተግባር አንዱ የሆነው ፕሮጀክትን መሰረት ባደረገ ስልጠና የአሰልጣኞችን ቴክኖሎጂን 100% የመቅዳት አቅም የመገንባትና ፤ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሌላኛው ተግባር የሆነው የቴክኖጂ ድጋፍ

የመስጠት የአፈጻጸም ደረጃዎች ተገምግመውና ደረጃ ወጥቶላቸው አስፈላጊው የክትትል፣ የድጋፍና የእርምት ስራዎችን ማከናወን ይችላል፡፡ቴክኖሎጂን መቶ በመቶ የመቅዳት ስራ የክትትልና ድጋፍ ቼክሊስት ከዘህ በታች በተቀመጡት ሰሌዳዎች ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡

ሴለዳ 1. የአሰልጣኝ ልማት

የአፈጻጸም ደረጃ ተግባር ( የአሠልጣኝ ልማት)1. በትኩረት ዘርፎች ብቃት

ያላቸው የሲና የቢ ደረጃ የኢንዱስትሪና ተቋም አሰልጣኞችን ማፍራትና

ማሟላት

2. ፕሮጀክትን መሰረት ባደረገ ስልጠና

የአሰልጣኞችን ቴክኖሎጂን 100%

የመቅዳት አቅምመገንባት

3. የግል ተቋማት አሰልጣኞችን

የቴ/ሙ/ት/ ስ አሰልጣኞ የብቃት

ማዕቀፍ አካልማድረግ

4. የውጭ ባለሙያዎችን አቅም አሟጦ

መጠቀም

ከበቂ በታች ከትኩረት ዘርፎች አንፃር የተቋማትና የኢንዱስትሪ

አሰልጣኝ ያልመደበና የቀጣይ ፍላጎት እቅድ የሌለው

የአሰልጣኞችን የክህሎት ክፍተት ያልለየ

በተቋሙ መመዘን ያለባቸውን አሰልጣኞች

ለይቶ ለማስመዘን ምንም ዝግጅት ያላደረገ

የትኩረት ዘርፎችን መሰረት ያደረገ እቅድ

ያላዘጋጀ

አጥጋቢ በተቋም ደረጃ ከትኩረት ዘርፎች አንፃር አሰልጣኝ ያሟላና የቀጣይ ፍላጎት እቅድ

ያለው

ክፍተትን ለይቶ ከእሴት ሰንሰለት ትንተና በመነሳት የአሰልጣኙን

ቴክኖሎጂን ከ 60-79% የመቅዳት አቅም

መገንባት የቻለ

የተመዛኞችን መረጃ በማደራጀት ለምዘና

ማዕከል ያቀረበ

የትኩረት ዘርፎችን መሰረት ያደረገ እቅድ

በማዘጋጀት የተቋምና ኢንዱስትሪ መሪ አሰልጣኝና መሪ መዛኝ

ማፍራት የጀመረ

ጥሩ ከትኩረት ዘርፎች አንፃር የኢንዱስትሪ ውስጥ

አሰልጣኝ የማፍራት እቅድያለው

ክፍተትን ለይቶ ከእሴት ሰንሰለት ትንተና በመነሳት የአሰልጣኙን

ቴክኖሎጂን ከ 80-94% የመቅዳት አቅም

መገንባት የቻለ

የተቋሙን አሰልጣኞች ሙሉ በሙሉ ያስመዘነ

የፈሩ መሪ አሰልጣኞችና መዛኞች የውጭ

ባለሙያዎችን ተክተው መስራት መጀመራቸው

Page 12: 100% Technology Copy Manual

በጣም ጥሩ በትኩረት ዘርፎች የኢንደስትሪ ውስጥ አሰልጣኝ ያፈራ

ክፍተትን ለይቶ ከእሴት ሰንሰለት ትንተና በመነሳት የአሰልጣኙን

ቴክኖሎጂን ከ 95% በላይ የመቅዳት አቅም

መገንባት የቻለ

የተቋሙን አሰልጣኞች ሙሉ በሙሉ

ለአሰልጣኝነት ያበቃ

የፈሩ መሪ አሰልጣኞችና መዛኞች ቀሪ የተቋምና

የኢንዱስትሪ አሰልጣኞችንና

መዛኞችን ማብቃትመጀመራቸው

ምርጥ ተሞክሮ

ሴሌዳ 2. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አግልግሎት

የአፈጻጸም ደረጃ

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ግቦች1. የጥራትና ምርታማነት

ማሻሻያ ድጋፍ መስጠት2. የቴክኒክ ክህሎት ድጋፍ

መስጠት3. የስራ ፈጣሪነት ድጋፍ

መስጠት4. የቴክኖሎጂ

ድጋፍ*መስጠት5. በተሰጠ የተሟላ ድጋፍ

በጥ/አ/ተቋማት ሃብት እንዲፈራ ማድረግ

ከበቂ በታች

የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ስርአት የሚተገበርባቸውን

ጥ/አ/ተ/ ከአካባቢው የልማት ፕሮግራሞች በመነሳት ያልለየና ያላቀደ

ከሙያ ደረጃ በመነሳት የአንቀሳቃሾችን

የክህሎት ክፍተት ያልለየ

ከሙያ ደረጃ በመነሳት የአንቀሳቃሾችን የስራ

ፈጣሪነት የክህሎት ክፍተትያልለየ

የአካባቢውን የእድገት ቀጠና ተከትሎ የዘርፉን እሴት ሰንሰለት ትንተና፣ ማፒንግ እና ዕቅድ ያላዘጋጀ፣

የተሟላ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በመስጠት

በጥ/ አተቋማት ሀብት እንዲፈራ ለማድረግ ዕቅድ ያላዘጋጀ

አጥጋቢ

የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ

ስርአት (ካይዘን) ላይ ፈጻሚዎችን አብቅቶ የመጀመሪያ

ምዕራፍ የሆነውን የ 5 ኤስ

ትግበራ ከእቅዱ 60-79% ያከናወነ

ከተለዩት ክፍተቶች በመነሳት አንቀሳቃሾችን በደረጃ አንድ

ላይ ከእቅዱ 60-79% ማብቃት የቻለ

ከተለዩት ክፍተቶች በመነሳት አንቀሳቃሾችን

በስራ ፈጣሪነት በደረጃ

አንድ ላይ ከእቅዱ 60-79% ማብቃት የቻለ

ከእሴት ሰንሰለት ትንተና በመነሳት ችግሮችን ለይቶ በየትኩረት ዘርፎቹ

ከእቅዱ 60-79% ተፈላጊ ቴክኖሎጂ መረጣ ያከናወነ

በተሟላ ድጋፍ በጥ/አ/ ተቋማት

ከእቅዱ 60-79% ሀብት እንዲፈራ ማድረግ የቻለ

ጥሩ

የ 5 ኤስ ትግበራን በሁሉም

የስራ ቦታዎች ተግብሮና 7 ቱን የብክነት አይነቶች በመለየት

ከእቅዱ 80-94% ማስወገድ የጀመረ

ከተለዩት ክፍተቶች በመነሳት አንቀሳቃሾችን በደረጃ ሁለት

ላይ ከእቅዱ 80-94% ማብቃት የቻለ

ከተለዩት ክፍተቶች በመነሳት አንቀሳቃሾችን

በስራ ፈጣሪነት በደረጃ

ሁለት ላይ ከእቅዱ 80-94% ማብቃት የቻለ

ተፈላጊውን ቴክኖሎጂ መርጦ፣ ለተመረጠው ቴክኖሎጂ ትንተና ሙሉ ሰነድ ከእቅዱ 80-94% ያዘጋጀ፣

በተሰጠ የተሟላ ድጋፍ

በጥ/አ/ ተቋማት ከእቅዱ 80-94% ሀብት እንዲያፈራ

ማድረግ የቻለ

በጣም ጥሩ

የለውጥ ሃሳቦችን በማፍለቅ፣

7 ቱን የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ መሳሪያዎችን

በመጠቀምና አሰራሮችን ስታንዳርዳይዝ በማድረግ

ቀጣይነት ያለው መሻሻሎችን

ከእቅዱ ከ 95% በላይ ማስመዝገብ የጀመረ

ከተለዩት ክፍተቶች በመነሳት አንቀሳቃሾችን በደረጃ ሦስት

ላይ ከእቅዱ ከ 95% በላይ ማብቃት የቻለ

ከተለዩት ክፍተቶች በመነሳት አንቀሳቃሾችን

በስራ ፈጣሪነት በደረጃ ሶስት ላይ ከእቅዱ

ከ 95% በላይ ማብቃትየቻለ

በተዘጋጀው ትንተና መሰረት ምርጡን ቴክኖሎጂ 100% በመቅዳት የ/ጥ/አ/ ኢንተርፕራይዞችን የመጠቀም አቅም በመገንባት ከዕቅዱ ከ 95% በላይ ያከናወነ፣

ከእቅዱ ከ 95% በላይ ሀብት እንዲፈራ ማድረግ የቻለ

ምርጥ ተሞክሮ

Page 13: 100% Technology Copy Manual